ch
Feedback
Construction Proxy

Construction Proxy

前往频道在 Telegram

#1 construction portal to get: ✅ construction news ✅ construction market ✅construction materials price ✅engineering estimates ✅ Sub contract https://constructionproxy.com Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot

显示更多

📈 Telegram 频道 Construction Proxy 的分析概览

频道 Construction Proxy (@constructionproxy) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 518 名订阅者,在 商业 类别中位列第 3 478,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 726

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 518 名订阅者。

根据 20 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 7,过去 24 小时变化为 -1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 31.55%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 6 157 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 30

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
#1 construction portal to get: ✅ construction news ✅ construction market ✅construction materials price ✅engineering estimates ✅ Sub contract https://constructionproxy.com Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot

凭借高频更新(最新数据采集于 21 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 商业 类别中的关键影响点。

19 518
订阅者
-124 小时
-27
+730
帖子存档
photo content

#Chinese_again ቢሮው ከቻይናው የኮሚዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ(CCCC) ጋር የግንባታ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ከቻይናው የኮሚዩኒኬሽን ኮ
#Chinese_again ቢሮው ከቻይናው የኮሚዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ(CCCC) ጋር የግንባታ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ከቻይናው የኮሚዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ(CCCC) ጋር የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሰረተልማቶች የተሟሉለት የትራፊክ ማኔጅመንት ማዕከል የሚያገለግል ዘመናዊ ህንፃ ለመስራት የግንባታ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ፕሮጀክቱም 831,843,924.43 እንደተመደበለትና በ18 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ በፊርማ ስነ-ስርዐቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም ይህ ግንባታ ሙሉለሙሉ የሚከናወነው ከምድር በታች ሲሆን ወደታችም 4 ወለሎች ይኖሩታል፡፡ የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ ሐሙስ ታህሳስ 23/2012 ዓ/ም

photo content

Caption this, happy Monday
Caption this, happy Monday

Chinese ..... again .... ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረዋ - ሶሞዶ - ሰቃ - ሲሞዶ - ሊሙ መንገድ ግንባታን ለማስጀመር ነው ወደ ስፍራው ያቀኑት። የማና፣ ሊሙ ኮሳ እና ሊሙ ሰቃ ወረዳዎችን የሚያቋርጠው መንገድ፥ 94 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው ግንባታው በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል። ለመንገድ ፕሮጀክቱ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ የቁጥጥር ስራውን ጨምሮ ሙሉ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል። ግንባታውን የቻይናው ቱ ሲ ጁ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሲያከናውነው ኋይት ናይት ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ደግሞ የቁጥጥር ስራውን የሚሰራ ይሆናል። የመንገድ ፕሮጀክቱ በወረዳ 21 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በገጠር ከ8 እስከ 10 ሜትር ስፋት ይኖረዋል።

More than 30 Chinese Contractors working on road projects with value of more than 60billon birr, only 2 Chinese companies have “pass” performance, all others failed.

ብቃታቸው ተረጋግጦ በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ማሽነሪዎች ውስን መሆናቸው ተመለከተ **************** የኮስተባ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ታህሳስ 16 ቀን 2012 ዓ.ም **************** በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ማሽነሪዎች በአገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ለማድረግ እንዲቻል የወቅቱን የኮንስትራክሽን ስራዎች ዘመኑ የሚጠይቀውን ግብዓቶች በመጠቀም የሚሰሩ ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁና በተቀመጠላቸው ጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁ የማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታመናል፡፡ ይህንን እውን ለማድረግም የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ምዝገባ ዳይሬክቶሬት በ2012 ኣ.ም እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ምዝገባ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በዚሁ መሰረት 571 ለሚሆኑ ባለ ጎማ እና ባለሰንሰለት ተንቀሳቃሽ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አዲስ ምዝገባ በማካሄድ ብቃት ማረጋገጫ ተስጥቷል፡፡ እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ያልሆኑ (አስፓልት ባቺንግ ፕላንት፣ ኮንክሪት ባቺንግ ፕላንት፣ ክሬሸር፣ ታወር -ክሬን እና የመሳሰሉ ማሽነሪዎች ) 64 አዲስ ምዝገባ በማካሄድ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ለ824 ተንቀሳቃሽ፣ እንዲሁም ለ 94 ተንቀሳቃሽ ላልሆኑ ማሽነሪዎች የዕድሳት / የቦሎ/ አገልግሎት በመስጠት የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ በሌላም በኩል ለ1211 ማሽነሪዎች ለዋስትና መያዣነት፣ የዕግድ ጥበቃ፣ የስም ዝውውር እና ዕገድ ላይ አገልግሎት መሰጠቱን ከተቋሙ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ምዝገባ ዳይሬክተሬት ተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ እንዲያም ሆኖ በርካታ ማሽነሪዎች ሳይመዘገቡ እና ብቃታቸው ሳይረጋገጥ በግንባታ ስራ ላይ እንደተሰማሩ የሚገመት ሲሆን፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍም የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ባለንብረቶች እንዲያስመዘግቡና በህጋዊነት እንዲሰማሩ ማስታወቁ ተመልክቷል፡፡ ብቃታቸው ያልተረጋገጠ ማሽነሪዎችን በግንባታ ስራ ላይ ማሰማራት ለግንባታ መጓተት፣ ለጥራት ጉድለት፣ ለዋጋ መናር እና ለአካባቢ ደህንነት ስጋት ምክንያት እንደሚሆን ከዳይሬክቶሬቱ የተገኘው መረጃ አስታውቋል፡፡ ብቃታቸው ያልተረጋገጠላቸውና ያልተመዘገቡ ማሽነሪዎችን በስራ ላይ አውሎ መገኘት በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል በመገንዘብ ምዝገባ ያላካሄዱ አካላት የሕጋዊነት መስመርን መከተል እንደሚገባቸው ተሰምሮበታል፡፡

photo content

መንግሥት የሲሚንቶ ዋጋን ለማረጋጋት ከ100 ብር በላይ በመቀነስ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ በሩት ሙሴ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች የሲሚንቶ ዋጋ ለማረጋጋት ከአንድ መቶ ብር በላይ ቅናሽ በማድረግ ለሸማቾች ማቅረብ ጀመሩ። በጥቅምት 7/2012 በንግድ ሚኒስቴር በተወሰነው መሰረት ግንባታ ለሚያከናውኑ እና ማስረጃ መቅረብ ለሚችሉ ነዋሪዎች የሚቀርብ ሲሆን፣ ለመንግሥት እንዲሁም ለሃይማኖት ተቋማት የተሰጠ ኮታ መኖሩም ታውቋል። በገበያ ላይ 330 ብር የሚሸጠው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት፣ በኢንዱስትሪ ግብአቶች አቅራቢ በኩንታል በ255 ብር እንደሚቀርብ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እመቤት ሙሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በገበያ ላይ 350 ብር የሚሸጠው ደርባ ሲሚንቶ፣ በማከፋፈያዎቹ ግን በ234 ብር ከ59 ሳንቲም ቀርቧል። ፋብሪካዎቹ ለገበያ ከሚያቀርቡበት ዋጋ ቅናሽ በማድረግ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት በአዲስ አበባ ለአብነት ኮልፌ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ማቅረብ መጀመሩንም እመቤት ጨምረው ገልፀዋል። ለግለሰብ ተጠቃሚ ደንበኞች በአንድ ጊዜ 100 ኩንታል ሲሚንቶ መግዛት የሚቻል ሲሆን፣ ይህንንም ለማግኘት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የፀደቀ የቤት ፕላን፣ ስድስት ወር ወይም የጊዜ ገደብ ያላለፈበት የግንባታ ፈቃድ፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና ከወረዳው ጽሕፈት ቤት የሚጻፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማሟላት እንደሚያስፈልግ መመሪያው ይደነግጋል። ለአጥርና ለጥገና ሥራዎች በአንድ ጊዜ እስከ 50 ኩንታል መግዛት እንደሚቻልም ተገልጿል። ምርቱን ማግኘት ለሚፈልጉ አምራች ድርጅቶችም ከፍተኛው ማግኘት የሚችሉት የሲሚንቶ መጠን ከአራት መቶ ኩንታል የማይበልጥ ሲሆን፣ ይህም በየወሩ የሚሰጥ ነው። ድርጅቶቹ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ በተጨማሪ ፈቃዱን ከሰጠው አካል የማምረት አቅማቸውን እና ወርሃዊ የሲሚንቶ ፍጆታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ለመንግሥት እና ለሃይማኖት ተቋማት እስከ መቶ ኩንታል የሚሰጥ ሲሆን፣ ለግለሰብ ከተቀመጡት መስፈርቶች በተጨማሪ የተቋማቱ ኀላፊዎች የፈረሙበት የግዢ ጥያቄ ደብዳቤ መቅረብ እንዳለበት ተደንግጓል። በአገሪቱ ዉስጥ በሚታየዉ የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ምክንያት ከሥራ የተስተጓጎለ የመንግሥትም ሆነ የግለሰብ ግንባታ ወደ ሥራ እንዲመለስ በማሰብ እና የገበያ ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የኢንዱስትሪ ግብአት ልማት እና የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የበኩላቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል። የሲሚንቶው ቅናሽ እስከመቼ እንደሆነ የጊዜ ገደብ አልተወሰነም። ነገር ግን የገበያውን ዋጋ ለማረጋጋት አዲስ አበባ ከሚገኙ የሽያጭ ማእከላት ባሻገር በአማራ፤ በኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ ክልል ለማስፋፋት እንደታሰበ እመቤት ተናግረዋል። addismaleda.net - አዲስ ማለዳ

Anyone new about this?
Anyone new about this?

📌 A team from the Ministry of Construction and the Office of the Auditor General traveled throughout the country to audit cobblestone projects that were started in 2005. The World Bank supported the project financing close to 8 million USD for the construction audit. The Cobblestone Project started in 2005 in a bid to create job opportunities for youth, and to provide attractive and long-lasting road and pavement in Ethiopian cities. According to data from the Ministry of Construction and Urban Development, the cobble stone project has created close to half a billion jobs and more than 2,220 km of roads in over 140 cities between 2005 and 2014.

photo content

እኔ የምለው የመንግስት ባለስልጣናት ለምንድነው የኤክካቫቴር ኦፕሬተር ነን አሉ? PS dear government officials your people are not as idiots as you think th
+3
እኔ የምለው የመንግስት ባለስልጣናት ለምንድነው የኤክካቫቴር ኦፕሬተር ነን አሉ? PS dear government officials your people are not as idiots as you think they are, stop excessive show off in construction site.

Excise Tax Rate Table 1 Amharic.docx1.22 KB

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ የአማርኛ.docx0.89 KB

It’s not just you Ethiopian Roads Authority website is down.
It’s not just you Ethiopian Roads Authority website is down.

Construction Proxy - Telegram 频道 @constructionproxy 的统计与分析