ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

前往频道在 Telegram

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ! . ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤ ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

显示更多
7 486
订阅者
-524 小时
-97 天
-3330 天
帖子存档
ጠጠር! . (#ፈይሠል_አሚን) . ከአቅም ሁሉ መሐል. . . እያንጠፋጠፈ፣ካለኝ ከነበረኝ፣ “መጋፈጥ” ብቻ ቀረኝ! እነሆም…. ጎልያዶች ፊት ቆምኩኝ፣አንተን ተማምኜ፤ ታጥቄያለሁ ጠጠር፣ እኔም ዳዊት ኾኜ! . @huluezih @huluezih

አያነቡንም፣ርእስ ይሠጡናል! . (#ፈይሠል_አሚን) መርምረው አልለዩን፣ ዘልቀውም አላዩን፤ ተቀምጠን በገሃድ፣በጭፍን ያልፉናል፤ አያነቡንም! ርእስ ይሠጡናል! እኔ. . . ለነፍስ የምገለጥ፣ብርሃን የከበበኝ፣ “ሽፋን-አልባ መጽሐፍ ነኝ. . . ልብ ያለው ያንብበኝ! . @huluezih @huluezih

አያልፍልኝም! . (#ፈይሠል_አሚን) . ብጥር አልተሳካም፣ ታግዬ አልቻልኩም፣ በሰው መንገድ ብሔድ፣የእውነት ብብሰለሰል፤ ለእኔ አልተሠጠም፣ ይኼን ጊዜ መምሰል! አይሳካም ለእኔ፣ ከቶ አያልፍልኝም፣ መቼም ከፍ አልልም፣አሁን ካለሁበት፤ መምሰል፣ጭራ መቁላት. . . ስለማልችልበት! . @huluezih @huluezih

. . .of the day!😎
. . .of the day!😎

ዐውቀዋለሁ ልቤን… “ቀረሁበት እንጂ፣የቀረብኝ የለም”፣ ብዬ ሳልታበይ… ለጊዜ ሠጠሁት፣ ፍርዱን አክለፍልፎ፣ቀኑን በቀን ያምጣ፤ እናያለን ያኔ. . . ማን ማንን እንዳጣ! . (#ፈይሠል_አሚን) . @huluezih @huluezih

መስከረምን እወዳታለሁ! (8) #ፈይሠል_አሚን (በዓመት አንድ ቀን ብቻ የሚነበበው ተከታታይ ታሪክ እነሆ ስምንተኛ ዓመቱ wow!😮) . ይህን ስናገር ዛሬ ሰዎች እንደሚገምቱት ልቤ አይደነግጥም። እንደቀድሞም አይሰበርም። አሁን ልቤ ብዙ ነገር አይገርመውም። መስከረምን ያክል እኩል እሣት፣እኩል በረዶ የገጠመው በምን ይገረማል? የሰው ልጅ በየዓመቱ አዲስ ዓመት ሲመጣ አዲስ ሕይወት እጀምራለሁ ይላል። እኔ ግን የጀመርኩት ሕይወት አዲስ አልሆነም። እኔ በአንድ ጉዳይ ስባክን መስከረም ደረሰ።ዓመት ተቀየረ።የጠፉት ወፎች ተመለሱ፣ የከሰሙ ግንዶች እንቡጥ ፀነሱ። አልተቀየርኩም።መስከረም ግን ተቀየረች። “ምን ያህል ነው የምትጠብቀው?” ይሉኛል. . . እኔ ዝም ስል ልቤ ይመልሳል:- “እስከ መቼ እንደሚጠብቅ አላውቅም፤ ግን የሚጠብቀው ሰው እስከሌለ ድረስ ይመስለኛል” ይላል። ዝም እላለሁ።ልቤ አንዳንዴ ከአፌ ይልቅ እውነት እንደሚናገር ስለማውቅ። ⸻ አምና መስከረም ጠብቶ በአስራ ሁለተኛው ቀን የውዷ መስከረም ሠርግ ተደገሰ። መስከረም 12 ድረስ የነበሩትን ቀናት ተከፋፍሎ እንደተቀመጡ የዶሮ ብልት ቆጠርኳቸው። አንድ። ሁለት። ሦስት። አስራ አንድ። አስራ ሁለት። እሷ ልትዳር ነው።እኔም ልቤን ልቀብር ነው።ሠርግ እና ቀብር አንድ ቀን ላይ መዋል እንደሚችሉና አንዱ ከቁብም እንደማይቆጠር ተረዳሁ። ልዩነቱ በአንዱ ላይ ሰዎች ነጭ ጋቢ ለከጥሎሽ ጋር ይሠጣሉ፣ በሌላው ላይ ጋቢ ለብሰው ያዝናሉ። ወደ ሠርጉ ስሄድ አንድ ሰው “ለሙሽራዋ ምን ይዘህ መጣህ?” አለኝ።(ይኼ ሰላይ!) “ምንም።” “እንዴ? በባዶ እጅ?” “በባዶ እጅ አይደለም። የአሥራ ሁለት ዓመት ፍቅር ይዣለሁ።” * መስከረም ወደ አዳራሹ ገባች።የሠርግ ልብስ ለብሳ።ፊቷ ላይ ደስታ ነበር።እኔ ግን ፊቷን እያየሁ በውስጤ አንዲት ልጅ ታየችኝ። የልጅነቴ መስከረም።በጎዳና ላይ ከእኔ ጋር የምትሮጠው።የእኔን እንጀራ ከእኔ ጋር የምትካፈለው።እኔ ስወድቅ የምትስቅብኝ። እሷ ስትወድቅ ግን የማለቅስላት። ያች መስከረም ከዚህች መስከረም ጋር ተመሳሳይ ፊት ነበራት።ግን ተመሳሳይ ልብ አልነበራትም። ምናልባት ሰው እያደገ ሲሄድ ፊቱ በመስታወት ይታያል፤ ልቡ ግን…..ይጠፋል? እኔንጃ! ⸻ ሙሽራው መጣ።አምሮበታል።ጥሩ ልብስ ነበረው። ጥሩ መኪና እንዳለው በሰፈሩ ተወርቷል።ጎበዝ ነጋዴ ነውም ተብሏል።ሰዎች ሁሉ “እድለኛ ልጅ ነው” አሉ። እኔ ግን አንድ ነገር አሰብኩ።እድለኛ ማለት ሁሉን ያገኘ ሰው ነው? ወይስ ያገኘውን ማጣት የማይፈራ ሰው? መልሱን አላገኘሁም። ከመፈላሰፍ በፊት ሆድ መሙላግ ይቀድማል ብዬ ሔጄ ቡፌ አነሣሁ። ⸻ ሠርጉ እየተጠናቀቀ ነበር። መስከረም ከሙሽራው ጎን ቆማ ፎቶ ትነሳ ነበር። እኔ ግን በርቀት ቆሜ ዐየኋት። እና በዚያኅ ቅጽበት ብዙ ነገሮች በሕሊናዬ እየተጨረፉ ማለፍ ጀመሩ። አባቷን፣የበዓል በጎች፣ ያ ሐሰተኛው ፓይለት፣ሕመሟ፣ አልጋዋ፣ ኬኩ. . .ያም የአምስት ብር ሥዕል ይዞ የመጣውን ልጅ ሳይቀር አሰብኩ። ድንገት እንባዬ ከዓይኔ አምልጦ ወደ ጉንጬ ፈሰሰ። ማንም ሳያየኝ በፍጥነት እንባዬን ጠርጌ ወደ ሙሽሮቹ እያየሂ ፈገግ አልኩ። “ምንድነው ያስለቀሰህ?” የሚል የሴት ድምጽ ሰማሁ። ዞር ብዬ ሳያት ልቤ ደነገጠ። ጠይም ቆንጆ ሴት ወይን ይዛ ቆማለች። ውበቷን ከማድነቅ ይልቅ ማልቀሴን መካድ መረጥኩ። እሷ ግን ክህደቴ አልገረማትም። “አንተ ስላላየኸኝ እንጂ ሳለቅስ ብታየኝ እክድ ነበር” ብላ ሳግ ተናነቃት። “ይኼ ከሃዲ!” አለች ሙሽራዋን እያየች። የኔን ህመም የተሸከመ ሰው ያገኘሁ መሰለኝ። ሁለት ከሃዲዎች ሲጋቡ እንባ እያፈሰሱ የቀሩ ሁለት ነፍሶች ተገናኙ። እኔ እና ጠይሟ ቆንጆ። ምንም ዐይነት የታሪክ ማብራሪያ ሳልጠይቅ እጄ ዘርግቼ “ፋሲካ እባላለሁ!” እጄን ሠድጄ: መልሳ እጇን ዘርግታ “መስከረም እባላለሁ” አለች በፈገግታ። ድንግጥ አልኩ። ደግሞ ሌላ መስከረም? ድንጋጤዬ ግራ አጋብቷት “ምነው?” አለች። የሙሽሪቷን ስም አልሰማችም መሰለኝ። የዓመት ሰው ይበለን! ለክፍል 9 ያድርሰን! . @huluezih @huluezih

ብዙ ነው ያየሁት! . (#ፈይሠል_አሚን) . ከጊዜ ቀድሜ… በዚህች አጭር ዕድሜ. . . ብዙ ዐየሁ የማይታይ! ብዙ አጣሁ የሚታይ አፍርሶ እየሠራኝ፣ነቅሎ እየገጠመኝ፣ ምድር ከዘራችው፣የለም ያልገጠመኝ! ብዙ ነው ያየሁት. . . ሩቅ ነው የመጣሁት. . . ብቻ በመንገዴ “ደንታ” ነው ያጣሁት! . @huluezih @huluezih

የት ነው? . (#ፈይሠል_አሚን) . አምላክ የት ነው ያለው? ምድር ላይ ወይስ በሰማይ ቤት? ብለው ሲጠይቁኝ.... መልስ አለ እኔ ዘንድ በፅኑ የማምነው ጊዜና ሥፍራ ድቅድቅና ብራ ምንም ሳይቀይረው ምንም ሳይወስነው "አምላክ ከኔ ጋር ነው!" . @huluezih @huluezih

የመሐል ሰው . (#ፈይሠል_አሚን) . መንገድ ነን ለአንዳንዱ. . . ወደ አሻው እስኪደርስ፣የሚጠለልበት፤ ከህመሙ እስኪሽር የሚጋደምበት፤ ነደን 'ምናበስለው. . . ከስመን 'ምናበቅለው. . . እኛ ያልጀመርነው፣ እኛ 'ማንጨርሰው፤ መሐሉ ነን ለአንዳንዱ ሰው! ክንፍ እስኪያቆጠቁጥ ከርሞ መዘጋጃ. . . እስኪያሳክከው፣ጥፍሩን መሞረጃ ትያትር ነን ለአንዳንዶች. . . ሕይወትን መልመጃ! . @huluezih @huluezih

እንዲህ ባለ መልኩ ቲክቶክ ላይ ግጥሞቼንና ጽሑፎቼን እየለቀቅኩ ነው:: የሚመቻችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ...ሊንኩ እነሆ! https://www.tiktok.com/@huluezih?_r=1&_t=ZS-95G4kqdAgHk

. . .of the day!😎
. . .of the day!😎

ቀጣይ ዓመት ራሴ ላነበው ለራሴ የጻፍኩት (ማንም እንዳያነበው!) . ዕጣ-ፈንታ ዕድሜ ሠጥቶህ ይኽን እንድታነብ ከፈቀደልህ፣ እንደ ለኸድ የጨለመውንና የጠበበውን መንገድ ማለፍህን እንደማትረሳ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ተስፋ መቁረጥ ጥርሱን አግጥጦ የገፋህን ቅጽበት፣ ቀናት ሁሉ በማይገለጥ ሰንኮፍ ተጋርደው አልነጋ ሲሉ፤በአኬልዳማ ተደልድለው መራመጃ የነፈጉህ መንገዶች፤ አቅም ባጣም በሹክሹክታ ‹‹ያልፋሉ!›› ስልህ ከመጣህበት በላይ የምትደርስበትን ጸዳል ጉብታ በከሲታ ተስፋ ውስጥ. . .ተስፋ አድርጌ ነው፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት ደክሞህ ነበር፡፡ ዕጣ-ፋንታ ጨክኖብህ በሕይወትህ ረግጠህ የማታውቃቸው አዚማም ሥፍራዎች ላይ ቆመሃል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ፣ ፍርድ ቤት፣ ወጌሻ ቤት፣ ሐኪም ቤት…ሰው ፊት ሌሎችም፡፡አፈር ልሰህ ወደ ሕልምህ እንዲያቀናህ ያበቀልከውን ፍሬ ሌባ ያለ ኀፍረት ወስዶብሃል፡፡ ድፍረትና ጭስን ተመስለህ በመርፌ ቀዳዳ እንደምትወጣ ፍርሃት በዋጠው ለሆሳስ ነግሬህ ነበር፣ አላሳፈርከኝም…ዛሬ እዚህ ደርሰሃል፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት ዓለም ተገልብጦብህ ነበር፡፡በደም፣ በሥጋ በመንፈስ የተዛመዱህ ጀርባቸውን እንጂ ፊት አልሠጡህም፡፡የኋላ ታሪክህንና የሚደርስልህ ነገህን ረስተው በቆምክበት ሥፍራ መዝነው አቅልለውሃል፡፡ ይጎትቱኛል ያልካቸው መዳፎች ገፍተው ወደ መቀመቅ እንድትወርድ በይነውብሃል፡፡ ፍርሃት ባደበዘዘው ለሆሳስ ነግሬህ ነበር…..‹‹ያልፋል!›› ብዬ፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት…..ደርሶብህ የማያውቀው የመተት ፍላጻ ተወርውሮ ቤትህ ገብቶ ገርበብ ያለ በርህን ዘግቶ፣ ክፍት መስኮትህን ደፍኖ ከሁሉ አራርቆህ፣ የጨበጥከውን ነጥቆ፣ የጎረስከውን አስተፍቶህ ብዙ ቀናትና ወራት ሳይነጉልህ…በድቅድቅ ውስጥ ማንም ሳያይህ ከራስህ ጋር ስትታገል፣ ባልተዘጋጀ ትከሻ ላይ ሲህር ሌላ ሸክም ኾኖ ሲያጎብጥህ፤ ከገጠመህ ይልቅ የሚመጣውን ተዓምር አስቤ ፍርሃት ባደበዘዘው ለሆሳስ ‹‹አይዞህ! ይኽም ያልፋል!›› ብዬህ ነበር፡፡(ይኸው! አለፍከው አይደል?) ‹‹ንገረኝ!›› ሲሉህ እንዴት እንደምትገልፀው ተቸግረህ፣ የምትወደውን ብዕር ጨለማ ውስጥ ጥለህ መናገር ከብዶህ….በዝምታ ከዝምታ ጋር ታግለሃል፡፡ የምትተነፍስበትን ብዕር እንጂ ፈገግታህን እና ጨዋታህን አልጣልክም፡፡ያንኳኳሃቸው በሮች ወቅታቸው ስላልደረሰ እንጂ መከፈታቸው እንደ ቂያማ የማይቀር ቀጠሮ መኾኑን ከሕመሞችህ ልቀው ባይሰ´ሙህም ነግሬህ ነበር፣አላመንከኝም ነበር፡፡ ዛሬ እዚህ ስለደረስክ እኮራብሃለሁ፡፡ ሦስት ነገር አትርሳ….ትንሽ ሻማ ይዘው ጨለማህ ድረስ መጥተው ብርሃናቸውን ያካፈሉህን፣ የተፈጠረው ሳይገባህ፣ የተናገርከው ሳይገባቸው ጆሮ የሠጡህን! ደግሞም ችለው ያልቻሉትን፣ መንገድ መጠቆም ሲችሉ መንገድህን የዘጉትን፣ ጥሩ ቃል እንኳ እንደ መስቀል ወፍ የራቃቸውን፡፡ ሦስተኛ. . .ማን እንደኾንክ አትርሳ፡፡ አሁን ያለህበት ብሩህ ቀን ሲያዘናጋህ ይኽን ጽሑፍ አንብብ፡፡ያለ መሣሪያ ጦርነት ውስጥ ገብተህ የወጣህ፣ ያለ ምሽግ ከፈንጂ ጋር የተጋፈጥክ፣ ራስህን አጥተህ ራስህን ያገኘህ ልበ-ብረት ነህ፡፡ እኮራብሃለሁ! . @huluezih

. . .of the day!😎
. . .of the day!😎

. . .of the day!😎
. . .of the day!😎

. . .of the day!😎
. . .of the day!😎

የእሳት ጠባሳ! . (#ፈይሠል_አሚን) . እሳት ኾንኩ መሰል. . . እንዳልነድ፣እንዳልጠፋ፣ማግዶ እያቆየኝ፤ ከሩቅ የጠራሁት፣በሩቅ ነው የሚያየኝ! . እሳት ኾንኩ መሰል. . . ዝናቡ አባራ፣ ክረምቱም አለፈ፤ ካበሰልኩት ይልቅ. . . ያከሰልኩት ብቻ. . . ለወሬ ተረፈ! . እሳት ኾንኩ መሰል. . . የነደድኩለት ሸሸኝ፣መንገዱን ቀጠለ፣ የነካሁት፤የነካኝ. . .እየተቃጠለ! ሬሳ ትንፋሽ የለው፣አይሞትም አበሳ፤ በገሃድ አያዩትም፣የእሳትን ጠባሳ! . @huluezih @huluezih

. . .of the day!😎 @huluezih
. . .of the day!😎 @huluezih

. . .of the day!😎 . @huluezih
. . .of the day!😎 . @huluezih