1 177
订阅者
+224 小时
+477 天
+10530 天
帖子存档
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
▶️ ከሙብተዲዕ ማስጠንቀቅ ሌሊት ተነስቶ ከመስገድ ፣ ኢእቲካፍ ከማድረግ ይበልጣል
ኢብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :-
ለኢማም አህመድ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ተባሉ :-
"ሰውየው ይጾማል ፣ ይሰግዳል ፣ መስጊድ ውስጥ ኢእቲካፍ ያደርጋል ካንተ ዘንድ ተወዳጁ እንዲህ አይነቱ ሰው ነው ወይስ ስለሙብተዲዖች የሚናገረው?"
ኢማም አህመድ እንዲህ አሉ ፡ -
“ቢቆም ቢሰግድ ፣ ኢእቲካፍ ቢያደርግ ጥቅሙ ለራሱ ነው ፤ በቢድዓ ሰዎች ዙሪያ ቢናገር ግን ጥቅሙ ለሙስሊሞች ነው ፣ ስለዚህ እርሱ በላጭ ነው፡፡”
ይህ ለሙስሊሞች ሐይማኖት የሚሰጠው ጥቅም አጠቃላይ እንደሆነና በአላህ መንገድ የመታገል አይነት እንደሆነም አብራራ፡፡ የአላህን መንገድ ፣ ዲኑን ፣ ጎዳናውን ፣ ሸሪኣውን ከቢድዓና ከሙብተዲዖች ማጽዳት ፤ በዲኑ ላይ የሚያደርሱትን ድንበር ማለፍ መከላከል "ዋጅቡል ኪፋያ" መሆኑ የሙስሊሞች ስምምነት ነው፡፡ የእነዚህን ሰዎች ጉዳት የሚከላከሉ አካላትን አላህ ባያቆም ኖሮ ዲኑ በተበላሸ ነበር፡፡ ብልሽቱ ጦረኛ የሆኑ ከሐዲያን በሙስሊሞች ላይ የበላይ በሆኑ ጊዜ ከሚያበላሹት የከፋ ይሆን ነበር፡፡ ጦረኛ የሆኑ ከሐዲዎች ልቦችን እና በውስጥ ያለውን ዲን ቀድመው አያበላሹም - በተከታይነት እንጅ፡፡ (ሙብተዲዖች) ግን ቀድመው ልቦችን ያበላሻሉ፡፡”
فتاوى ابن تيمية (28\231-232)
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
ታላቁ ታቢዒይ ኢማም አል-ሐሰን አል-በስሪ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ «ስለ ልግስና (ቸርነት) በጥልቀት ተመለከትኩኝ፤ ለእርሱም በአላህ ላይ መልካም ከመጠራጠር (ሑስኑ-ዘን) ውጪ ሌላ ስርም ሆነ ቅርንጫፍ (መሰረት) አላገኘሁለትም። የስስት (የንፍገት) ስርና ቅርንጫፍም በአላህ ላይ መጥፎ ከመጠራጠር (ሱኡል-ዘን) የመነጨ ነው። 📚 [ሹዐቡል-ኢማን፡ 13/320]📌 ዋናው መልዕክት በአጭሩ የልግስና ምስጢር፦ አንድ ሰው ለአላህ ብሎ ሲሰጥ አላህ ይተካኛል፣ ባዶዬን አይተወኝም፣ በሰጠሁትም ላይ ምንዳ ይከፍለኛል ብሎ በአላህ ላይ መልካም ስለሚጠረጥር ነው። የስስት ምስጢር፦ በአንጻሩ አንድ ሰው እጁን ሲይዝ (ሲሰስት) ከሰጠሁኝ እደኸያለሁ፣ ሀብቴ ያልቃል በሚል ሰይጣናዊ ፍርሃት በአላህ ላይ መጥፎ ስለሚጠረጥር ነው። ዋና መልዕክቱ፦ ልግስናም ሆነ ንፍገት ከልብ እምነት (የአላህን ቃልኪዳን ከማመንና ከመጠራጠር) ጋር በቀጥታ የተያያዙ መሆናቸውን ነው። https://t.me/HussinAssilty
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
قال الامام التابعي الحسن البصري -رحمه الله-:
" نظرتُ في السخاء فما وجدتُ له أصلاً ولا فرعًا إلا حسنُ الظن بالله عز وجل، وأصلُ البخلِ وفرعُهُ سوء الظن بالله عز وجل ".
📚شعب الإيمان (٣٢٠/١٣)
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
✍🏻 *لمن يخذل صاحب السنة فيقول له :( اشتغل بعيوبك عن عيوب الناس ) عندما يرد على الجماعات الضالة ودعاتها*
🔸 قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله:
*( الردّ على الباطل - سواء بدعة قولية أو عقدية أو فعلية -: هو الحق ، وتركه هو العيب ، وإذا قيل لمن يردّ ذلك: اشتغل بعيبك عن عيوب غيرك ، قلنا لهم: وهذا من عيبي إن لم أردّ على الباطل ؛ لأن الرد على الباطل واجب ).*
📚 فتح ذي الجلال والإكرام ٣٣٢/١٥
لا تتعصب لأحد فلا يجوز التعصب للعلماء!
*❐ قال الشيخ عبد العزيز بن باز رحمه الله
▪️لا يجوز أبداً التعصب لزيد أو عمرو ، ولا لرأي فلان أو علان ، ولا لحزب فلان أو الطريقة الفلانية ، أو الجماعة الفلانية ، كل هذا من الأخطاء الجديدة ، التي وقع فيها كثير من الناس .
▪️فيجب أن يكون المسلمون هدفهم واحد ، وهو اتباع كتاب الله وسنة رسوله - عليه الصلاة والسلام - في جميع الأحوال ، في الشدة والرخاء ، في العسر واليسر ، في السفر والإقامة ، وفي جميع الأحوال .
وعند اختلاف أهل العلم ينطر في أقوالهم ، ويؤيد منها ما وافق الدليل من دون تعصب لأحد من الناس .
مجموع فتاوىومقالات (٣٠٩/٢٣) 】..
▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎
*❐ قال ابن عثيمين رحمه الله ⬇️*
▪️نجد بعض طلاب العلم يكون عند شيخ من المشايخ، ينتصر لهذا الشيخ بالحق والباطل ويعادي من سواه، ويضلله ويبدعه، ويرى أن شيخه هو العالم المصلح، ومن سواه إما جاهل أو مفسد، وهذا غلط كبير، بل يجب أخذ قول من وافق قوله الكتاب والسنة وقول أصحاب رسول الله صلى الله عليه وسلم اهـ.
*("كتاب العلم"/للعثيمين/ص 89-91)*
http://t.me/shekabunuhaahmed
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
▶️ ሁለቱ የሰው ልጅ ፍላጎቶች
የአላህ መልእክተኛ - አለይሂሶላቱ ወሰላም - እንዲህ አሉ :-
"የአደም ልጅ እያደገ ሲሄድ ሁለት ነገሮች አብረውት ያድጋሉ። የገንዘብ ፍቅርና ረጅም እድሜ የመኖር ፍላጎት።"
ሐዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
በአቡ ኢልሀም ሙሀመድ ኑር ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ የኪታብ ትምህርቶች ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል
ቻናሉን ሼር ሼር ያድርጉ ይቀላቀሉ።
https://t.me/sunah6769
በአቡ ኢልሀም ሙሀመድ ኑር ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ የኪታብ ትምህርቶች ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል
ቻናሉን ሼር ሼር ያድርጉ ይቀላቀሉ።
https://t.me/sunah6769
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
በ 22/09/2018 ቅዳሜ ምሽት በአባይ ማዶ የመስጊድ ግዥ የገንዘብ ማሰባሰቢያ የቴሌግራም ቻናል የኦን ላይን ስርጭት በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ የተሰጠ ፈትዋ
Repost from የሰለፎች መንሀጅ (አቡ አመተሏህ ሙሀመድ ኡመር አደራውይ)
ዱንያ ላይ የሆነን ነገር ትፈልጋለህ ?
እንግዳውስ 👉ሶስት ነገሮችን በመፈፀም
(በመተግበር ) ላይ አደራህን
ሸይኽ ሱለይማን አር- ሩሀይሊ (ሀፊዞሁሏህ )
https://t.me/sunah123
https://t.me/yeselfochmenhaj
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷ለሳውዲ መሪዎች ታላቅ ምስጋናና ዱዓ ይገባቸዋል
ከሁሉ በላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል ፡ -
وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا ۗ
“ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይሆናል”
(አል-ኢምራን ፡ 97)
ሶስተኛው የሳውዲ መንግስት - በአሏህ ችሮታና ፈቃድ - አንድ ምዕተ አመትና ከዚያ በላይ - (1343- 1447) - አጠናቀቀ፡፡ እናም መንግስቱ ሐጅን በመቆጣጠር ፣ ምእመናን በመንከባከብ ታላቅና ተወዳዳሪ የሌለው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የሰው ፣ የቁሳቁስና ከፍተኛ የቴክኖሎጅ አቅሞቹን ሁሉ ለእነርሱ ተጠቅሟል፡፡ ለሁለቱ ቅዱሳን መስጊዶች እና ለጎብኝዎቻቸው ከፍተኛ እንክብካቤ አድርጓል፡፡ ስለሐጅ እና ኡምራ ስርአቶች መሪ ዳዒያን እና መጽሐፍትን ያገኛሉ፡፡ ሁሉም ተውሒድን እና ሱናን መከተልን ያውጃሉ፡፡
ስለዚህ ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ ለሳውዲ መሪዎች ቅን የሆነውን ጎዳናና ስኬትን እንዲሰጣቸው ፣ በተቀደሰው የአላህ ቤት የሐጅን ስርዓት በመቆጣጠር እና የተከበሩ የአላህ እንግዶችን በማገልገል እንዲረዳቸው ዱዓ አድርጉ፡፡
በተውሂድና በሱና ባንዲራዎች ተከበው ሙስሊሞችም በደህንነትና በመረጋጋት የሐጅ ስርዓታቸውን ያከናውናሉ፡፡ (ለበይክ አሏሁምመ ለበይክ ለበይክ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ) የሚልን የተውሂድ ቃል እንጅ ሌላን አትሰሙም፡፡
ለመቃብር ፣ ለመቅደሶች ፣ ለዶሪሆች ፣ (ለአምልኮ) ዚያራዎች ፣ ከሙታኖች ፍላጎቶቻቸውን እና እፎይታዎችን የሚሹበት የጭንቅ ጊዜ የሚማጸኑባቸው ቦታዎች ሳውዲ ውስጥ የሉም፡፡ ለዚህች የተባረከች አገር ክብር ይህ ብቻ በቂ አይሆንምን?! የተውሒድን አንገብጋቢነት አምልኮት ፍጹም ለአላህ የሚገባ መሆኑን ለሚገነዘብና ታሪክን መላልሶ ለዳሰሰ ለዚህች አገር መሪዎች በተውሂድ እና በሱና ላይ ጸንተው እንዲኖሩ ፣ ከሴረኞችና ከክፉዎቹ ተንኮል እንዲጠብቃቸው ሁሉን ቻይ ወደሆነው አምላክ ዱዓ ማድረግ አይገባምን?
የሳውዲን መንግስት የሚጠሉ አንዳንድ ሒዝብያዎች ይህንን ታላቅ አገልግሎት ሲመለከቱ በጣም ተደንቀዋል፡፡ ምክንያቱም ከአብዮትና ከማነሳሳት ደጋፊዎች በሰሙት ተቃራኒ ስለነበር፡፡
ሁሉን ቻይ የሆነው አሏህ እንዲህ ብሏል ፡
وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِي الْأَرْضِ كَمَا اسْتَخْلَفَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ الَّذِي ارْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّن بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا ۚ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ
“አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ፣ ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው ፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል - በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው ከተገዙኝ፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡”
(ሱረቱ ኑር ፡ 55)
ዶክተር ሸይኽ ሁሴን አስስልጢ
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
قال الله تعالى (ومن دخله كان آمنا )
أتمَّت الدَّولة السُّعوديَّة الثَّالثة قرنًا وزيادةً (١٣٤٣-١٤٤٧) بفضل الله تعالى وتوفيقه وهي تتولى إمارة الحجِّ وترعى الحجَّاج، وتقدم لهم خدمة جليلة لا نظير لها وسخرت لهم جميع إمكاناتها البشرية والمادية والتقنية العالية وعناية فائقة بالحرمين وقاصديهما وتجد المرشدين والدعاة والكتب التعريفية بمناسك الحج والعمرة كلها تصرخ بالتوحيد والمتابعة فادعوا الله تعالى أن يرزق ولاتها الهدى والسَّداد وأن يعينهم على الإشراف على حجٍّ بيت الله الحرام وخدمة ضيوف الرحمن تحوطه أعلام التَّوحيد والسُّنَّة، ويُؤدِّيه المسلمون في أمنٍ وطمأنينةٍ ولا تسمع إلا كلمة التوحيد (لبيك اللهم لبيك لبيك لا شريك لك لبيك) ولا مكان للقبور والأضرحة والمزارات والمشاهد وطلب الحوائج وإغاثة اللهفات من الأموات ألا يكفي هذا فخرا لهذه الدولة المباركة ؟ لمن يدرك أهمية التوحيد وإخلاص العبادة للباري وراجع التاريخ ألا تستحق منا أن ندعو الله تعالى للولاة بالثبات على التوحيد والسنة وأن يُسلِّمهم من شرور الكائدين ومكر الحاقدين.
وقد انبهر بعض الحزبيين المبغضيين للدولة السعودية لما رأى هذه الخدمة العظيمة لأنه خلاف ما سمعه من دعاة الثورة والتهييج.
قال الله تعالى :( وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِي الْأَرْضِ كَمَا اسْتَخْلَفَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ الَّذِي ارْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّن بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا ۚ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ ٥٥ النور.
ተኩረት ስጥ አንተ ያአላህ ባሪያ፦
العيد سيعود.. ومواسم الخير ستعود.. لكن نحن هل نعود أم أن هذا آخر العهد؟العيد سيعود... لكن هل سنكون من أهل العيد القادم؟
✅ مواسم الخير ستعود... لكن هل ستُكتب أسماؤنا في سجل الأحياء أم الأموات؟
✅ فاغتنم يومك، وأكثر من التوبة والاستغفار والعمل الصالح، فما مضى من العمر لن يعود، وما بقي منه لا يُعلم متى ينتهي﴿وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ﴾ [الحجر: 99]
🌿 ትርጉም
ዒድ እንደገና ይመጣል... የበጎ ሥራ ወቅቶችም ይመለሳሉ... ግን እኛ እንመለስ ይሆን? ወይስ ይህ የመጨረሻ ጊዜያችን ይሆን?
✅ ዒድ ይመጣል... ግን ቀጣዩን ዒድ ከሚያገኙት ሰዎች መካከል እንሆን ይሆን?
✅ የበጎ ሥራ ወቅቶች ይመለሳሉ... ግን ስማችን ህያው በሆኑ ሰዎች መዝገብ ውስጥ ይጻፋል ወይስ በሟቾች?
✅ ስለዚህ ዛሬን ተጠቀምበት፤ ተውባን፣ ኢስቲግፋርን (ምሕረት መጠየቅን) እና መልካም ሥራዎችን አብዛ።
ምክንያቱም ካለፈው ዕድሜህ የሄደው ፈጽሞ አይመለስም፤ የቀረውም መቼ እንደሚያበቃ ማንም አያውቅም።
አላህ ነብዩን እንድህ ይላቸዋል
📖 ﴿የቂን (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛው።﴾ [አል-ሒጅር፡ 99]
✔️ አላህ እኔንና እናንተን የቀጣዩን ዒድ በኢማንና በጤና ከሚያገኙት ሰዎች ያድርገን፤ መጨረሻችንንም መልካም ያድርግልን።
የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) አል- ወሎዊይ ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል።
👇👇👇👇👇
https://t.me/sunah123
Repost from ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
እውነተኛ ሱኒይ የሆነ ሰው የቢድዐ ሰው ሲነካ አይቆጣም!!
—————
እውነተኛና በአላህ ዲን ላይ ፅናት ያለው ሱኒይ (ሰለፊይ) የሆነ ሰው ለየትኛውም ስሜታዊ (ቢድዐና ሙብተዲዕ) ለሆነ አካል መነካት አይቆጣም!!።
ሁመይድ ኢብኑ ሙንሂብ (ረሂመሁላህ) አንድ ሰው አባበክር ኢብን ዐያሽን እንዲህ ብሎ ሲጠይቀው ሰምቻለሁ አለ:- “አባበክር ሆይ! ሱኒይ ማለት ማን ነው? አባበክርም እንደሚከተለው መለሱ:- ስለ ስሜት (የስሜት ባለ ቤት በክፉ) ሲጠቀስ አንዳችም የማይወግን የሆነ አካል ነው። አሉ” [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱና አላለካኢይ 1/82]
በአሽ-ሸሪዐህ ዘገባ አቡበክር ኢብኑ ዐያሽ እንዲህ ብለዋል:- “ሱኒይ ማለት እርሱ ፊት ስለ ቢድዐ ሲወሳ የማይቆጣ ነው።” [አሽ-ሸሪዐህ ሊል ኣጁሪ 5/550]
ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ አካል ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ አላህ እርም ያደረጋቸው ነገሮች ሲደፈሩ ይቆጣል!!። ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ ሰው ስለ ሺርክና ቢድዐ ባለየ ቤቶች ከመናገር ተቆጥበናል አይልም!!።
ኢብኑ ዐሳኪር - ረሂመሁላህ - ታሪኹ ዲመሽቅ በተሰኘው ኪታባቸው ከዑቅባ ኢብኑ ዐልቀመህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ የሚል ዘግቧል:- “አርጣአ ኢብኑል ሙንዚር ዘንድ ነበርኩና ከተቀማመጡ ሰዎች ከፊላቸው እንዲህ አለ:- ከሱና ሰዎች ጋር የሚቀማመጥና የሚቀላቀል ሆኖ ሳለ፣ ስለ ቢድዐ ሰዎች ሲወሳ ደግሞ ተውን! ስለነሱ እዚህ አታውሩ። የሚል ስለሆነ ሰው ምንትላላችሁ? አለ፣ አርጠአ ኢንዲህ በማለት መለሰ:- እሱ ከነርሱ ጋር ነው (ከቢድዐ ሰዎች ነው) የእርሱን ነገር አያምታታባችሁ፣ አለ። አልቀማ - ረሂመሁላህ- የአርጠአን ንግግር በወቅቱ አልተቀበልኩትምና ወደ ታላቁ ሰለፍ ኢማሙል አውዛዒይ - ረሂመሁላህ- ዘንድ ሄድኩኝ አሉ። አውዛዒይ ደግሞ እንዲህ ያለ ነገር ከደረሰው ግልፅልፅ የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ የነበረው ገላጭ ሰው ነበር። (ጉዳዩን ሳወሳለትም) አውዛዒይ:- አርጠአ እውነት አለ፣ (የተናገረው እውነት ነው)፣ ይህ ስለነሱ ከመናገር ይከለክላልን?፣ ታዲያ እነሱን በመጥቀስ ጠንከር ካልተባለ መች ነው ከነሱ ማስጠንቀቅ የሚቻለው?!።” [ታሪኹ ዲመሽቅ 8/15]
ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “አንድ ሰው ከቢድዐ ባለቤት ጋር ሲጓዝ አይተሀው፣ (የዚያን የቢድዐ ሰው) አስተሳሰብ እንደማይቀበለው በመሃላ አስረግጦ ቢነግርህ እንኳ እውነት ብለህ አትቀበለው!።”
አቡ ሷሊህ አል-ፈራእ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:- ለዩሱፍ ኢብኑ አስባጥ ስለ ወኪዕ አንስቼ የተወሰነች ስለተከሰተች ፊትና አወራሁት፣ ይህን ጊዜ ዩሱፍ እሱ ራሱ እንደ ኡስታዙ ነው አለኝ፣ (ኡስታዙ ሀሰን ኢብኑ ሀይን) ማለቱ ነው። ለዩሱፍም መልሼ ይህ ሀሜት እንዳይሆን አትፈራም? አልኩት፣ አንተ ሞኝ እንዴት ሀሜት ይሆናል?፣ እኔ እኮ ለእነዚህ ከወላጆቻቸው የበለጠ መልካም ነኝ!፣ እኔ እነሱ በፈጠሩት አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሰዎች ተከትለዋቸው እንዳይሰሩበትና በወንጀሉም ተጠያቂ እንዳይሆኑ ነው የምከላከለው፣ እነሱን ከፍ ከፍ እያደረገ የሚያወድሳቸው ሰው በነሱ ላይ እጅግ በጣም አደገኛ ነው!፣ አለ።” [አስ-ሰይር 7/364]
ትክክለኛ ሱኒይ ሰለፊይ የሆነ ሰው ስለ አህሉል ቢድዐህ እና ከቢድዐህ ሰዎች መደረግ ስላለበት ተመዩዝ ሲነገር አይጨንቀውም!! ልቡ አይጠብም!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን 👇👇 #join ያድርጉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
✅ አድስ የተጀመረ የሙስጦለሀ ኪታብ
📚 متن البيقونية
የኪታቡን PDF ለማግኘት 👇👇👇
https://t.me/sunah6769/1788
https://t.me/sunah6769/1788
🎤أبو إلهام محمد نور ( وفقه الله )
⏹ክፍል 5
https://t.me/sunah6769
https://t.me/sunah6769
https://t.me/sunah6769
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
🌟 ልዩ የፈትዋ ፕሮግራም ጥሪ 🌟
📛 በተለያዩ ዲናዊ ጉዳዮች ላይ
የቀረቡ ጥያቄዎች መልስ
የሚያገኙበት ልዩ የፈትዋ
ፕሮግራም‼️
✳️ ቀን - ግንቦት 22 (ቅዳሜ)
✳️ ሰአት - ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ
🔺️ መልስ - በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ
(ከባህር ዳር)
🔴 ቦታ፦ በአባይ ማዶ ቢላል
መስጅድ የቴሌግራም ግሩፕ
🔗 የግሩፕ ሊንክ፦ https://t.me/bilalmesji 👈
❓ ጥያቄ አለዎት?
በተለያዩ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ጥያቄ በቦታችን ሊንክ @Fetawa_bot በኩል በማንኛውም ሰዓት አስቀድማችሁ መላክ ትችላላችሁ!
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
Repost from ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel
💥#የጁሙዓ_ኹጥባ💥
√√√√√√√√√√
📄ርዕስ:
"መሀይምነት ትልቅ አደጋ እንደሆነ "
الجهل خطرعظيم
አንኳር ነጥቦች
👉ኢልም መማር እንዳለብን
ሌሎችም..
መደመጥ ያለበት ምክር አዳምጡና ተጠቀሙበት
🎙በሸይኽ ሙሀመድኑር አቡ ኢልሀም አል ወለዊይ (ሐፊዘሁላህ)
🕌 በዳረ ሱና መስጂድ
አዲስ አበባ - አለም ባንክ
t.me/DarASSunnah1444
t.me/DarASSunnah1444
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷ኢኽዋኖች - እንኳን ደስ አላችሁ‼️⁉️
የአቂዳ -የሱናችሁ መሪ - የሐሰነል በና አገር
የፊርአውን መዲና - የግብጿ ቆሻሻ ምድር
ፈጠረችላችሁ - አዲስ የቢድአ መንገድ
ሴትና ወንዱን ቀላቅሎ - በአንድ ሶፍ መስገድ፡፡
የእኛዎቹ ኢኽዋኖች
የሐሰነል በና ፈረሶች
የቢድአ አጋሰሶች፤
ይህን ለማየት ስላበቃችሁ
እንኳንም ደስ አላችሁ‼️
በየአዳራሹ - በየዳእዋው
በየሰርጉ - በየለቅሶው
የኖራችሁበትን መደበላለቅ - ሳይለዩ ወንድን ከሴት
ግብፆች አሳደጉላችሁ - ወደ መስጊድ፣ ወደ ሶላት፤
ባልረባ ኢኽዋናዊ - የሴት አለባበስ
በየአደባባዩ - በየጎዳናው
በየመንገዱ - በየገበያው
የተልከሰከሰው ውበት - እንደ መኸሩ ገለባ
ከወንዶች የኢድ ሶላት - ከሶፋቸው መሀል ገባ፤
እንግዲህ፡-
ውበትን ሙባሸራ እያየህ - ወንድምዬ
ያለከልካይ መኮምኮም ነው - ኢኽዋንዬ!
ከሶላትህ በፊት፡-
ከኋላህ ያለችውን - መልክና ውበቷን
ከጎንህ ያለችነውን - ሽንጥና ፊቷን
ከፊትህ የቆመችውን - ዳሌና ተረከዟን
ሱጁድ ላይ ያለችውን - ጀርባ፣ መቀመጫዋን
ትኩር -ልብ ብለህ እያየህ - ወንድምዬ
ሳትሳቀቅ መኮምኮም ነው - ኢኽዋንዬ!
በሶላትህ መሀል፡-
ውበትና መልኳን
ሽንጥና ዳሌዋን
ተረከዝ - መቀመጫዋን
በአይነ ህሊናህ እየቃኘህ - ወንድምዬ
እንግዲህ መኮምኮም ነው - ኢኽዋንዬ፡፡
ሶላትህን ስታሰላምት፡-
ፊቷን - ደም ግባቷን
አፍንጫ - ከንፈሯን
ቅድብና አይኖቿን
አበጥረህ እያየህ - ወንድምዬ
አንግዲህ መኮምኮም ነው - ኢኽዋንዬ፡፡
ካሰላመትህ በኋላ፡-
ስላየኸው የሴት ልጅ ውበት
ስለሰፈረባት የቁንጅና መአት
ተፈኩር እያደረክ በተደማሚነት
ተስቢህ፣ ተህሚድ… ልትል ነው - ወንድምዬ
እንዲህ እያረጉ መኮምኮም ነው - ኢኽዋንዬ፡፡
ከመስጊድ ለመውጣት፡-
አብረሀት እያልክ - ረመድ፣ ረመድ
በመስጊዱ መሀል - ጎርደድ፣ ጎርደድ
ጫማህን እያነሳህ አብረሀት
“ሶላት” እንዴት ነበር እያልካት
ውብ ድምጿን እየሰማህላት - ወንድምዬ
እንግዲህ መኮምኮም ነው - ኢኽዋንዬ፡፡
የአቂዳ -የሱናችሁ መሪ - የሐሰነል በና አገር
የፊርአውን መዲና - የግብጿ ቆሸሻ ምድር
ፈጠረችላችሁ - አዲስ የቢድአ መንገድ
ሴትና ወንዱን - ቀላቅሎ ባንድ መስገድ፤
የእኛዎቹ ኢኽዋኖች
የሐሰነል በና ፈረሶች
የቢድአ አጋሰሶች፡፡
ይህን ለማየት ስላበቃችሁ
እንኳንም ደስ አላችሁ‼️
በዶክተር ጀማል ሙሐመድ - ሐፊዞሁሏህ -
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
ወደ ክፍለ ሀገር የሄዳችሁ ወንድም እና እህቶች፦
✍ ወደ ክፍለ ሀገር (ገጠርም ሆነ ከተሞች) ለዘያራ የተጎዛችሁ ሰዎች፣ እዚያ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ተውሂድን (አላህን በብቸኝነት ማምለክን) ማስተማር እና ሽርክን (በአላህ ላይ ማጋራትን) መከልከል ትልቅና የመጀመሪያው ተግባራቸው ሊሆን ይገባል።
ይህ ለምን አስፈለገ? እንዴትስ መሆን አለበት? የሚሉትን ነጥቦች በሚከተለው መልኩ በአጭሩ እንያቸው፡-
1. የተውሂድ እና ሽርክን የመከልከል አስፈላጊነት
✅ የነቢያት ሁሉ ጥሪ በመሆኑ፡ አላህ ወደ ሁሉም ህዝቦች የላካቸው ነቢያት በሙሉ የመጀመሪያ ጥሪያቸው «አላህን ብቻ ተገዙ፤ ከእርሱ ውጭ ሌላ አምላክ የላችሁም» የሚል ነበር። ወደ ክፍለ ሀገር የሄዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች ይህንን የነቢያት ፈለግ መከተል አለባችሁ።
✅ በክፍለ ሀገር ያሉ ክፍተቶች፡ በብዙ የሀገራችን ክፍለ ሀገራት የዲን እውቀት ማነስ፣ ባህልና ዲን መደበላለቅ ይታያል። በዚህም ምክንያት ሰዎች ሳያውቁት ወደ ተለያዩ የሽርክ ተግባራት (ለምሳሌ፡ ጠንቋይ ቤት መሄድ፣ ከፈጣሪ ውጭ ያሉ አካላትን መለመን፣ መሻይኾችንና ወልዮችን፣ በዛፍና በወንዝ መማል፣ ወዘተ) ሊገቡ ይችላሉ። ስለዚህ እውነታውን የሚያስታውሳቸው ይሻሉ።
✅ የስራዎች ሁሉ መግቢያ በመሆኑ፡ አንድ ሰው ተውሂዱ ካልተስተካከለ የሚሰራው ሰላት፣ ፆምና ሌላውም መልካም ስራ አምላክ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም። ስለዚህ ከምንም ነገር በፊት ተውሂድ ይቀደማል።
2. ወደ ክፍለ ሀገር የሚሄዱ ሰዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ ስልቶች (አደቦች)
ዳዕዋ (ጥሪ) ሲደረግ ሰዎቹ እንዲቀበሉንና ልባቸው እንዳይሸሽ ጥበብ የተሞላበት መንገድ መከተል ያስፈልጋል።
✅ በእውቀት መናገር፡ ስለ ተውሂድም ሆነ ስለ ሽርክ አስከፊነት ከመናገራችን በፊት ጉዳዩን በቁርአንና በሀዲስ ማስረጃ ጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል።
✅ በገርነትና በጥበብ መቅረብ፡ አላህ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርኦን ሲልካቸው እንኳን «ለስላሳን ቃል ተናገሩት» ነው ያላቸው። ክፍለ ሀገር ያሉ ወገኖቻችን ደግሞ አላህንና መልእክተኛውን የሚወዱ፣ ነገር ግን እውቀት ያጡ ሊሆኑ ስለሚችሉ በጥሩ ስነ-ምግባርና በርህራሄ ሊያዙ ይገባል።
✅ ከተግባራዊ ስራ ጋር ማሳየት፡ በክፍለ ሀገር ማህበረሰብ ዘንድ ንግግር ብቻ ሳይሆን የተናጋሪው ስነ-ምግባር፣ ታማኝነትና ሰዎችን መርዳት ትልቅ ቦታ አለው። በተግባራችን ስንማርካቸው ንግግራችንን ለመስማት ዝግጁ ይሆናሉ።
ማጠቃለያ ወደ ክፍለ ሀገር የሄዳችሁ ወንድም እና እህቶች ሙስሊም ሁሉ የነብዩን (ﷺ) አደራ ተሸካሚ መሆኑን ማወቅ አለበት። በሄደበት ቦታ ሁሉ አላህን በብቸኝነት የማምለክን ብርሃን በመንዛትና ሰዎችን ከሽርክ ጨለማ በመታደግ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ማበርከት ይኖርባችኋል። ይህ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።https://t.me/sunah123 https://t.me/sunah123
