الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
前往频道在 Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
显示更多未指定国家未指定类别
2 158
订阅者
无数据24 小时
+1817 天
+41530 天
帖子存档
Repost from Abu Sehl Al-Selefiy
የመንግስት ካሜሪዎችን በመፍራት ክልክላዎቹን ከመዳፈር እንታቀባለን ...
ግን .... አምላካችን አሏህ እያየን ፣ መላኢኮች እየፃፋብን ሐራም ነገሮችን እናተራምሳለን ... ወደሐራም እንመለከታለን ... ሙራቀባችን ደክሟልና !
ኧረ አሏህን እንፍራ !
ከደርስ የተቆረጠ መልእክት
https://t.me/MerkezulimamiAhmed
لا تستلم لظروف الحياة مهما كانت مُعقدة ، حتى لو شعرت أن اليوم سيء والغد أسوأ ، فمع مرور الأيام سترى فرج الله واقعاً بين يديك
"የሕይወት ሁኔታዎች ምንም ያህል የተወሳሰቡ ቢሆኑ ተስፋ አትቁረጥ /አትሸነፍ፤፣ ዛሬ መጥፎ እንደሆነና ነገም ከዚህ የባሰ እንደሚሆን ቢሰማህም እንኳ ፣ቀናት ሲያልፉ የአላህ እፎይታና መፍትሔ በእጆችህ መካከል እውን ሆኖ ታየዋለህ ፣
ኢንሻአሏህ ያረብ አግዘኝ ኢላሂ ........!
✍ ስደት እንደት ነዉ ???
ስንት መከረና ችግር ያሳለፈች
ትችትና ስድብ ዘለፋን. ያየች
በስደት ሀገርላይ የተንከራተተች
ያረበ ሀገር እህት እጅግ ጠንካራነች ።
ደልቷት ያልኖረች ሁሌ ያለቀሰች
እባዋን ለብቻ ደምም ያፈሰሰች
በአይኖቿ ሙሉ እባን ያዘለች
ከላይ ስትታይ እጅግ የተዋበች
ዉስጣግን በሀዘን እጂግ የተጎዳች
የስደቷ ጀግና ለስንቱ የቆመች
ለራሷ ተርባ ለሌሎች. ያበላች
እሷ ሳትለብስ ሌሎች. ያለበሰች
ከችግር አሮቋ ስንቶችን ያወጣች
ያረብ ሀገር እህት በጣም ትለያለች
✍ ምንም ያላየች
ዘርቀለም ሳትለይ ጎሳ ያልጠየቀች ሰዉን በሰዉነት እጂግ ያከበረች የታመመ አሳክማ ለተራበ ያበላች የናትነት አንጀት በዉስጧ. ያዘለች ወንድሜነዉ ብላ ለስንቱ የቆመች ሀገርና ሰፈራ አድራሻ ያለየች ሁሉን በኩልነት አይታ እያዘነች ስንት በሽተኛን ሰበብሁና. አዳነች ??✍ ግን መልሳቸዉ ምንሆነ ?? እሷ ስትወድቅ መነሳት ሲያቅታት እጂግ ተጎድታ መነሳት. ሲሳናት ያ እህቴ እያለ እጅግ የበላት የራስሽ ጉዳይ ብሎ ገፈተራት ። ብርሽን በያዝሽ ማን በትኒዉ አለሽ ? እኔ አንሽኝ ብየ መቸ. ጠይእኩሽ የራስሽ ጉዳ እህት ጅቡ ይብላሽ አሁንስ እኔ ተነስቻለሁኝ አታስፈልጊኝም ያረብ ሀገር ስት ምንም አታምሩኝም በማለት በጅምላ ጀመረ. ሊገርፋት በተሳለ ሰይፉ ተነሳ ሊቆርጣት ያንሁሉ ዉለታ ባንደዜ. እረስቶት የነበረበትን ችግር ወደሀላ ትቶት ተነሳ ጀግናየቱን እህቱን. ሊገላት ። ይህነዉ ያፈራችዉ ከዛ. ከደግነት አምላሹ ሆነ እሷን. በመዉጋት ። ✍ ሁሉም ገፈተራት 9/10 አመታት ሁኖሻል ታዳ ድህነት እንደት ይነካሻል ?? ተኝተሽ እየዋልሽ ይላታል ባልገሻል ከሰላሳዉ ጋራ መላላስ ይዘሻል በቁስላይ ቁስል. እየጨመሩላት ለማይድን በሺታ አጋልጠዉ ሰጡዋት ስንት መከራና ሀዘን ያሳለፈች አባቷን እናቷ በስደት ያጣች እሚያፀናናት እንኳን ካጠገቡዋያጣች ይሄ ዉለታ እረሽ በዚህ መልኩ ወጋት ለማይድን በሽታ እህቴ. ጣላት ✍ በቃ አትንኩን ። የራሳችሁ ችግር ሲወገድላችሁ አብሽሩ እያልን እንዳ አልቀሰንላችሁ ምናለ መልካም ባታደርጉ ቢያርፍ ምላሳችሁ ?? እንደእባብ መርዝ በከለን ቃላችሁ ። አላህ ያዘነለት ትንሺች. ሲቀሩ ሌሎቹ ወደኛ ቀረቡ ለቀብሩ እኛን አፍር ደፍነዉ ንብረት ሊበሉ አረ ታዉ ወገን ትንሽ. አስተዉሉ ። ያረብ ሀገርን ሴት ዉለታ አትብሉ ። ታሳዝናላችሁ ። ኡሙ አብዲል ወሓብ ከበሀር ማዶ https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
بِيَدِكَ الْخَيْرُ إِنَّكَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ فلا نصر إلَّا به، ولا استئناس إلَّا معه، ولا نجاح إلَّا بتوفيقه. الأمر كله بيد الله؟ العطاء والمنع، والخير كله أصله وزمامه بيد الله وحده سبحانه وتعالى. الاعتماد المطلق ؟ لا تظن أن نصراً ينزل من غيره، ولا أن طمأنينة وسكينة تحل في القلب إلا بقربه والأنس به. التوفيق أساس النجاح مهما أخذ الإنسان بالأسباب، يظل التوفيق الحقيقي مرهوناً بمشيئة الله ومدده.
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
🚨አዲስ ቻሌንጅ ለቻነል ባለቤቶች በሙሉ 🚨
🛜 ቻናላቺሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ ማሳደግ የምትፈልጉ ብቻ አናግሩኝ 🔽
👉 1k+ subscribers 🟢
👉 2k+ subscribers 🟢
👉 4k+ subscribers 🟢
👉 6k+ subscribers 🟢
👉 10k+ subscribers 🟢
⚠️ ከ1000 ጀምሮ እንቀበላለን ℹ️
💎ቻናል በነፃ ለመሳደግ ያናግሩን ፍጠኑ🔽
Repost from 💌
🌿 የቀኑ መልዕክት
የልብ ሰላም በገንዘብ ሳይሆን፣ በአላህ ቅርበት ነው የሚገኘው።
ዛሬ ጥቂት ዚክር፣ ጥቂት ኢስቲግፋር፣ ጥቂት ቁርአን...
ልብህ የሚፈልገውን እረፍት ታገኛለህ።
🤲 አላህ ሆይ! ልባችንን በዚክርህ አረጋጋ፣ በታዛዥነትህም ላይ አጽናን። አሚን።
.
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_ዘጠኝ(⓳)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #ተስኒም ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
▫▫▫▫▫▫#ምዕራ_ሶስት▫▫▫▫▫▫
"እንደ አበባ አብባ - ሽታዋ ቢጣፍጥም፣
እሾህ ሆና ወጋችኝ - መድኃኒት የለውም።
በአቂዳ ስም መጥታ - ልቤን የሰረቀች፣
የስደቱን ድካም - ሁሉንም ረሳች።
አይከል የጥልቁ መርዝ - አይከል የማር መጋረጃ፣
ዛሬ ሆንሽብኝ - የነፍሴ ማረጃ።"
ከአይከል በኋላ... ዱባይ ለእኔ ባዶ ሆነች። ብርሃኑ ጨለመ፣ ሥራው ታከተኝ። "ለዚህች ሴት ነበር ወይ?" የሚለው ጥያቄ የሕሊናዬ ጅራፍ ሆነ። የአባቷ ሞት ሳይሆን የእሷ ክህደት ነው የሞት ሞት የሆነብኝ።
የንቃተ ሕሊና ንጋትና የመዝጊያ ቃል።
በዚያ የሐዘንና የሥቃይ ማዕበል ውስጥ ሆኜ፣ የሱና ወንድሞቼ የለገሱኝ ምክር እንደ ነፍስ መድኃኒት ሆኖ ከውድቀቴ አነሳኝ። ከቀናት በኋላ ግን... ያቺ የክህደት አዝመራዋን የሰበሰበችው አይከል፣ ወደ ሳዑዲ ተመልሳ በድፍረት ደወለችልኝ። በሰላም ምድር ላይ ሆኜ በሞትና በሕይወት መሃል መኖሬን እንኳ ሳታውቅ፣ ስለ ራሷ ሕይወትና ስለ አገር ቤት ሁኔታ ልታወራኝ ሞከረች።
ታገሥኳት። ነገር ግን ዝምታዬን እንደ ሞኝነት ስትቆጥረው፣ ያወኩትን እውነት በአንደበቴ ስተፋው ደነገጠች። ስልኩን ዘግታ በስቅስቅ ለቅሶ የታጀበ "ሪከርድ" ላከችልኝ። "ቤተሰብ አስገድዶኝ ነው ያገባሁት" የሚለው ሰበቧ፣ ለኔ ግን በደረቀ ቁስል ላይ ጨው የመነስነስ ያህል ነበር። አስገድደውሽ እንኳ ቢሆን፣ ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም? ለምንስ ተስፋዬን በእንባ አራጨሽው? የሚለው ጥያቄዬ በልቤ ቢታመምም፣ እኔ ግን እንዲህ አልኳት፦ "በይ... የባልሽን ሀቅ ጠብቂ!"
የአይከል ታሪክ በእኔ ሕይወት ላይ እዚህ ጋር አበቃ። ነገር ግን የጣለችብኝ ጠባሳ" ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ መማሪያ ከሆነ። ብዬ በዚህ መልኩ አዘጋጄሁት
"ያለ ኢስቲኻራ - በስሜት መነዳት፣
መጨረሻው ፀጸት - የመንፈስ ስብራት፤
አዋቂ ነኝ ስል - በጅልነት ወድቄ፣
ዛሬ ግን ነቃሁኝ - በዕውቀት ተመርቄ።"
ውድ ወጣቶች (ሸባቦች) ሆይ! ይህንን ታሪክ ያወራሁላችሁ ለሐዘን ወይም ለልብ ወለድ ለቧልታ ለመታወቅ አይደለም።
"ሁሉን አውቃለሁ" ባይነትና ያለ ኢስቲኻራ (ጌታህን ሳጠይቅ) መጓዝ እንደ እኔ ለከፋ ውድቀት ይዳርጋል። አላማችሁ እንደ እኔ የተጃጃለ እንዳይሆን፣ እያንዳንዱን እርምጃችሁን በተቅዋ (አላህን በመፍራት) እና በዕውቀት ላይ መሥርቱት።
አደራ ይላቹኋል ...
የወሎው ለጋ ወጣት፣ የበረሃው ስደተኛ፣ የባሕሩ ተሳፋሪና የሳዑዲው እስረኛ... ዛሬ ዱባይ ላይ ሆኖ ታሪኩን በድል ቋጨ። አልላቹሁም ይቀጥላል ትልቁ ታሪክ ከዚህ ቡኋላ ነው
ተከተሉኝ.......
▫▫▫▫▫▫#ምእራፍ_ሶስት▫▫▫▫▫
-------
፦ የንጋት ኮከብና የሐላሏ መንገድ
የአይከል ክህደት ያስከተለብኝ ቁስል ገና ሳይሽር፣ ነፍሴ ግን በባዶነት ውስጥ መዳከር ሰልችቷት አዲስ ተስፋ መፈለግ ጀመረች። እናቴ የምትናፍቀው ያ የልጅነት ወግ፣ እኔም የምመኘው ያ የትዳር ረፍት እውን ይሆን ዘንድ "አልረፍ ያለችው ነፍሴ" ዳግም ዓይኗን ገለጠች። ምንም እንኳ ልቤ በተደጋጋሚ በክህደት ጩቤ ቢደማም፣ አሁንም ግን ለኔ በተጻፈችው "የግራ ጎኔ" ላይ ተስፋ አልቆረጥኩኝም ነበር።
ያኔ.....ነው እንግዲህ... በድንገት አንዲት የሱና እንቁ፣ አንዲት የሰለፍያ ኮከብ በሕይወቴ ማኅደር ላይ ብልልልልልልልልልልጭጭጭ አለች። ስሟ ለጊዜው በምስጢር ይቆይና፣ እሷን ባየሁ ጊዜ ውስጤ ሌላ ድንጋጤ ተሰማው። ነገር ግን እንደ ቀድሞው በስሜት አውሎ ንፋስ መነዳት ሰልችቶኛል፤ በሐራም ፍቅር አጥር ውስጥ መታጠር ደክሞኛል። "የሰለቸኝ የሐራም ፍቅር ነው" አልኩ ለራሴ።
መቼም የኔ ነገር
በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ" ነውና
ስለዚህ ይህችን የተከበረችና በዕውቀቷ የምትታወቅ የሱና እንስት ለማግኘት፣ መንገዴን በሸሪዓዊ አጥር ለማጠር ወሰንኩ። ራሴ ቀርቤ ከማናግራት ይልቅ፣ አንዲት የቅርብ እህቴን መካከለኛ አድርጌ የልቤን ፍላጎት ገለጥኩላት።
እንዲህ አልኩ፦
"በሐራም ጎዳና - ስንት ዘመን ባከንኩ፣
በክህደት ጩቤ - ስንት ጊዜ ታመምኩ፤
ዛሬ ግን ፈለግኩኝ - የሐላሏን መንገድ፣
በሸሪዓ አጥር - በክብር ልራመድ።"
እህቴ ልጅቷን ለማናገር ተነሳች። ነገሩ ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። ያቺ የሱና እንስት "የሚዲያ ትዳር አልፈልግም" በማለት ብርቱ ፈተና ደቀነችብን። ክብሯንና ዲኗን የምትጠብቅ ጠንካራ ሴት ነበረችና በቀላሉ እጅ አልሰጠችም።
ነገር ግን እህቴ ተስፋ ሳትቆርጥ፣ ስለ እኔ ማንነትና ስለ እውነተኛ ፍላጎቴ ደጋግማ በማስረዳት በመጨረሻ የማግባቢያውን ቁልፍ አገኘችው።
እህቴ መጥታ "አማናዬን ተወጥቻለሁ፣ መንገዱን አመቻችቻለሁ" ስትለኝ፣ ደስታዬ ወሰን አጣ። አሁን እኔና ያቺ የተከበረች እንስት በቀጥታ ልንገናኝ ነው።
ፈርቻለሁ! አዎን፣ ያንን ሁሉ የበረሃና የባሕር መከራ ያለፍኩት እኔ፣ ዛሬ በሐላሏ መንገድ ፊት ስቆም ተንቀጠቀጥኩ። እንደ አይከል ልቤን የሰረቀችው በውበት ብቻ ሳይሆን፣ በዕውቀቷ፣ በሥርዓቷና በሂጃቧ ነበር። "አላሁ አክበር!" አልኩኝ፤ የጌታዬን እዝነት እያደነቅኩ።
"አይከልን የውበት - ማር መስላ መጣች፣
ይህች ግን በዕውቀቷ - ነፍሴን አከመች፤
ስርዓቷ ግርማ - ሂጃቧ ውበቷ፣
ሆነችኝ የቤቴ - የንጋት ብርሃኗ።"
መቼም የኔ ጉድ አያልቅም እያልን አልቦ ዘመድ ለነዳይ" ነውና ተረቱ
ክፍል⓴ እንቀጥል
የጨረቃዋ ብርሃንና የጥርጣሬው ድቅድቅ ጨለማ በሚል ይቀጥላል
ያ አሏህ...
አንዳንዴ ቃላቶችን ማውጣት እየተሳነን
ያረብ....ብለን ዝም እንላለን
አንተ ከቃላቶች በላይ የውስጥን
#ሰሚነህ። #ያረብ...🤲
فذكر فان الذكرى تنفع المؤمنون
አስታውስ ማስታወስ ለሙዕ ሚኖች ትጠቅማለች
📢📢⬆️⬆️ ንቁ ጀዋላቹሁን ለ20 ደቂቃ ጣል አርጉና ወጀላቺን በዝቷል እዝነትን እንጠይቅ💦💦💔
አላህ ሱብሐነ ወተዓላ በሌሊት የመጨረሻ ሶስተኛ ክፍል ወደ ቅርብ ሰማይ ወርዶ ↪️"ለማኝ የሚለምነኝ የለምን? እሰጠዋለሁ፤ ይቅርታ የሚጠይቀኝ የለምን? እምረዋለሁ" ↩️በማለት ይጠራል። በዚህ ሰዓት ቆሞ የሚሰግድ አካል የዚህን ታላቅ እዝነትና ምንዳ ተቋዳሽ ይሆናል።⤵️⤵️
↪️ኢጃዛቤት ያሉትን ቀስቅሷቸው ↩️
በሌሊት ተነስተው ለሶላት የቆሙ እና ቤተሰቦቻቸውን ወይም ጓደኞቻቸውን ወደ አላህ ዚክርና ሶላት የቀሰቀሱ ሰዎች የራሳቸውን የሌሊት ሶላት አጂር ከማግኘታቸውም በላይ፣ ያነሷቸውን ሰዎች የሰላት ምንዳ ተካፋይ ይሆናሉ።↩️
በዱአቹህ አስታውሱኝ ባረከሏሁ ፊኩም💦
ወድሜ ?! ነብዩሏህ ዩሱፍን አስታውስ ?! ለዝሙት ራሳቸውን አዘጋጁላቸው ): የሳቸው ወደአሏህ ያደረጉት ልመና ያሱበሀን አሏህ⤵️
قَالَ رَبِّ ٱلسِّجۡنُ أَحَبُّ إِلَيَّ مِمَّا يَدۡعُونَنِيٓ إِلَيۡهِۖ وَإِلَّا تَصۡرِفۡ عَنِّي كَيۡدَهُنَّ أَصۡبُ إِلَيۡهِنَّ وَأَكُن مِّنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ
ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው፡፡ ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ? አለ፡፡↩️
የመጀመሪያው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
ኡስታዝ አህመድ አማን
https://t.me/Mf11q?livestream=e146c6f1f438b9c6f5
https://t.me/Mf11q?livestream=e146c6f1f438b9c6f5
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
.📣🎤 🚨አስደሳች ዜና 🚨
💘 የእስላማዊ ትላልቅየቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 3 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉 5k Subscribers
👉 8k subscribers
👉12k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
Repost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
ቀጥታ ስርጪት ተጀምሯል
ሱረቱ ዩኑስ ከቁጥር ( "15" )
የገባችዉ አተዉጡ ተከታተሉ ትጠቀማላቹህ ታተርፋላቹህ ?!✅
ተ
ጀ
ም
ሯል
☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️☕️🍫🍫🍫
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
.📣🎤 🚨አስደሳች ዜና 🚨
💘 የእስላማዊ ትላልቅየቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 3 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉 5k Subscribers
👉 8k subscribers
👉12k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
በጊዜ መጨዋት እና ወደኋላ መንጓደድ ወንጀል ነው
አላህ ጊዜ ሰቶት ያልተጠቀመበት ሰው ወንጀለኛ ነው ውጀል የግድ ሰውን መስደብ ገንዘብ መቀማት ዝሙት መስራት ብቻ አደለም
ጊዜን በዋዛ ፈዛዛ ማሳለፍ ማባከን እራሱ ወንጀል ነው
ፀፀቱ ደሞ በሁለቱም አገር ነው
የመጀመሪያው ፀፀት ዱኒያ ላይ ነው እድሜ ከሄደ እና እርጂና ላይ ባለን ሰአት ወይይይ ምናለ በወጣትነቴ ተምሬ በሆነ በማለት መፀፀት ግን ዋጋ የለውም እንዳውም ዋጋ እድንከፍል ያደርገናል እንጂ✅
ትልቁ ፀፀት ደግሞ አኼራ ላይ ነው ዋ ጥፋቴ ወደ ዱኒያ በተመለስኩኝ ብሎ መከጀል💧💦አላህ ይጠብቀን
ዛሬን ተጠቀሙበት ተማሩ መልካምን ስሩ
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
! ፈጥኖ የመለስ Add የሚለውን በመንካት ምርጥ ቻናል ይሸለም
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
ጥያቄ
በቀን ዉስጥ ስንት ዋጅብ ሶላት አለ ❓
ሁሉም ሰው ባቀመሰው ልክ ይቀምሳታል ለበቀል እራስህን አታዘጋጅ ጊዜ በራሱ ይበቀልልሃልእያንዳንዱ ሰው በሰዎች ላይ ላደረገው በጎም ሆነ መጥፎ ነገር ተገቢውን ምላሽ በጊዜ ሂደት ማግኘቱ አይቀሬ ነው። ለበቀል ብሎ ራስን ማዘጋጀት እና ጉልበትን ማባከን የራስን ሰላም መረበሽ ነውና ጊዜን ለፍርድ መተው ሁልጊዜም ጥበብ ነው። ።ጊዜ ሀሰተኛውን ይለያል እያንዳንዱንም ሥራ በሰፈረበት ይለካል።
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
💘 የእስላማዊ ትላልቅ የቴሌግራም ቻናል መግዛት የምትፈልጉ አሁኑኑ አናግሩን 💵
እጃችን ላይ 1 ቻናል አለ ፍጠኑ
👉12k subscribers
🎯በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ🔽
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_ስምንት (⓲)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #አይከል ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
የራጎው መርዝና የቃሉ መፍረስ
የሙሐመድ ልጅ አገር ገብታ የአባቷን ሕይወት አኼራ መሸኘት ዜና እንኳን ሳይነግረኝ፣ በሰው በኩል ሰማሁት። "በሐዘን ተሰብራ ይሆናል" ብዬ በቅንነት ቴክስት እያደረግኩ ዐሥራ አምስት ቀናት አለፉ። ያኔ ግን... ያ በሳዑዲ በረሃ ድራማ ስትሰራብኝ የነበረው መርዝ፣ ዛሬ በገዛ አገሯ ላይ ሊረጭብኝ ሰዓቱ ደርሶ ነበር። እናቴ "ልጄ አግባ" እያለች ስትማጸነኝ፣ እምቢኝ ብዬ ተስፋ ያደረግኳት ያቺ "የሙሐመድ ልጅ" ዛሬ ሌላ ገጽታዋን አሳየችኝ።
እኔ በሰላም አገር ይችልጅ "ሀዘኑ በርትቶባት ነው በብዙ አመት ተለይታው የነበረው አባታ ሳትጠግበው ወደ አኼራ ሄደባት ብዬ ስለሷ በእርምጃዬ ልክ አስባለሁ።!!
ያኔ .... ነበር አንግዲህ አንድ ቀን ደወልኩኝ ልጠይቃት
በጉጉትና በሥጋት ደወልኩ። ስልኩ ተነሳ፤ ነገር ግን ድምጯ አልነበረም። አንድ ባዕድ ወንድ ስልኩን ነጥቆ "ምን ፈልገህ ነው?" ብሎ በቁጣ ዘጋብኝ። "ወንድሟ ይሆን? ወይስ ዘመዷ?" ብዬ በሞኝነት ራሴን እያታለልኩ ደግሜ ደወልኩ። ያ ሰው ግን ዳግም አንስቶ "ደህና ነች፣ አትረብሽ!" ብሎ ሲዘጋብኝ፣ የልቤ ትርታ መፋጠን ጀመረ።
ማመን አቃተኝ
"አንደበቷ ማር ነው - ልቧ ግን መርዝ ሰንቋል፣
ተስፋዬን ሰብራ - ዛሬ ተለውጣለች፤
በስልክ ሽቦ ላይ - የሌላ ወንድ ድምፅ፣
ልቤን አደማው - እንደ ሾርጣ ጅራፍ።"--------------------
ያ ሌሊት ለኔ እንደ ሺህ ዘመን ረዘመብኝ። ዱባይ ሆኜ በሐሳብ ማዕበል ስዋኝ፣ እንቅልፍ ከዓይኔ ርቆ አደረ። ጠዋት ወደ ሥራ ስገባ ፊቴ አብጦ፣ ዓይኖቼ በእንባ ተሞልተው፣ ነፍሴ በጭንቀት ታውካ ነበር። ቀኑ አልፎ መሸ። ያንን አስፈሪ ምስጢር የአባታን ሞት የነገረኝን ዘመዷን ደወልኩለት።
ያኔ ነው እንግዲህ... ሰማይ ወደታች መጥታ" የረገጠችኝ፣ ምድርም ተከፍታ የዋጠችኝ የመሰለኝ! ጆሮዬ የሰማው ቃል የሞት ያህል ከበደኝ።
አንባቢያን ሆይ! ተመልከቱ። እኔ በየመን በረሃ፣ በጅቡቲ ባሕር፣ በሳዑዲ እስር ቤት ያለፍኩት፣ ዛሬ ላይ እንዲህ ልሰበር ነበር? "አላህ ሆይ! በማልችለው አትፈትነኝ" ብዬ ጮኽኩ። ያ የሙሐመድ ልጅ የደበቀችው ምስጢር፣ ያ ከሳዑዲ ጀምሮ ሲከረፋኝ የነበረው ሽታ... ዛሬ እውነቱ ሲገለጥ፣ ነፍሴ በቁሟ ተቀበረች።
"ጆሮዬ የሰማው - መርዶ ሆኖ መጣ፣
ተስፋዬ ነጎደ - እንደ ደመና ሽታ፤
የሙሐመድ ልጅ ሆይ - መርዝሽን ረጨሽው፣
ያለፍኩትን መከራ - ሁሉንም ረሳሽው።"
ስሟን ላስተዋውቃችሁ፤ እስካሁን የተደበቀው ስሟን ለማወቅ ጓጉታችኋል አይደል?
አይከል ትባላለች። ቆንጅዬ ስም ያላት፣ እንደ ሚዳቋ ቀልጣፋ፣ እንደ ጸደይ ዝናብ ትሁት የሆነች ልጅ ነች። ያኔ... ነበር እንግዲህ የወደድኳት፤ 'አይን ካልመረጠ ልብ አይፈርድም' እንዲሉ፣ እውነቱን ለመናገር የመረጥኳት ያኔ ነበር።
በእኔ ልብ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ክብር ያላትና የነገሰች ሴት ነበረች። ለመንገስ ዘውድ፣ ለመከበር ግርማ ሳይኖራት በልቤ ዙፋን ላይ ተቀመጠች። ማፍቀር የሚለው ቃል ለራሱ እስከማይገልፀው ድረስ አፈቅራታለሁ።
ይህ ግን ማፍቀር ብቻ አይደለም፤ ለእኔ ከመውደድ በላይ መውደድ፣ ዓለም የሆነ ፍቅር ነው። አንዳንዴ ወደ ሰማይ ቀጥ ብዬ፣ ጨረቃን የአይከል ጥላ እያልኩ፣ ከጨረቃ ጋር የማወራበትና በብቸኝነት የምተክዝበት ሌሊት ሁሉ ያልፍ ነበር።
'ጨረቃ ምስክሬ፣ ሌሊቱ አዝመራዬ' ሆኖ ስለ እሷ ውበት ስቀኝ ነጋሪ ሳይኖረኝ ይነጋል።በጣም አምናት ነበርና... እሷ ለኔ ዓለሜ ነበረች፤ 'ጨረቃን ከሰማይ፣ እሷን ከመሬት' አወዳድሬ እኩል የማያቸው ስጦታዬ ነበረች።
አይከል
ስሟ አይከል... የነፍስ ስንቅ፣
ትህትናዋ... የልብ ምርቅ።
ቀልጣፋ ናት... እንደ ሚዳቋ፣
ለእኔ ግን ነች... የዓለም ጓቋ።
ያኔ መርጬ... በልብ አነገስኳት፣
ከመውደድ በላይ... በነፍሴ ቀደስኳት።
"አፈቅርሻለሁ" ... ቃሉ ምን ሊረባ?
ውቅያኖስ ታክሎ... በቁንጥጫ እምባ።
ሌሊቱን ለጨረቃ... ምስጢሬን አውጋለሁ፣
በእሷ ትዝታ... ብቸኝነቴን እረሳለሁ።
መውደድማ ቀለለ... ስሙም ረከሰብኝ፣
አይከል ማለትማ... "ሕይወት" ሆነብኝ።
የአይከል ክህደትና የሕሊና ስብርባሪ
በስልክ ሽቦ ላይ የሚንቀጠቀጠው የዘመዷ ድምፅ፣ ልክ እንደ መርዛም ጦር የልቤን ግድግዳ ሰነጠቀው። ጆሮዬ ለማመን የከበደውን፣ ሕሊናዬ ሊሸከመው የማይችለውን ያንን መራራ መርዶ እንዲህ ሲል ተፋው፦ "አይከል... አይከል እኮ አገባች!"አለኝ
ያኔ... ሰማዩ በላዬ ላይ የተደፋ፣ ምድሪቱም እግሬ ስር የራደች መሰለኝ። አባት ገና ተቀብሮ፣ ዐፈሩ ሳይደርቅ፣ ሐዘኗን በሐዘን ልጋራ በተቆራረጠ ቴክስት ስማጸናት፤ እሷ ግን በበረሃው ዓለም "እንዳትጎዳኝ አደራ" እያለች በአላህ ስም የለመነችኝን ያንን ቅዱስ ቃል በጭቃ ላይ ረገጠችው። ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ የሁለት ዓመት ቃል ኪዳናችንን እንደ ቆሻሻ ጨርቅ ወርውራ፣ የሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ገብታ የደስታዋን ድግስ ትቆርጣለች።
ስልኬን አውርጄ ወረወርኩት።
ተሸነፍኩ! በእራጎ ሰቆቃ ያልተንበረከከው፣ በየመን በረሃ ጥም ያልታከተው፣ በሳዑዲ ድንበር የጥይት እሩምታ ያልፈራው ነፍሴ፤ ዛሬ በአይከል የክህደት ጩቤ በቁሜ ተቀበረ። ባዶ እግሬን ተራራ ስወጣ፣ በባሕር ማዕበል ስናወጥ፣ በሳቢያ ዱላ ስገረፍ... "ያልፋል" እያልኩ ራሴን ያጽናናሁት ለእሷ ብዬ ነበር። እንዲህ አልኩ፦
"በረሃው አላሸነፈኝ - ጥይቱ አልገደለኝ፣
የአይከል ክህደት ግን - በቁሜ ቀበረኝ።
ባሕሩን ተሻግሬ - ድንበሩን አልፌ፣
ዛሬ እቤትሽ ደረስኩ - በሐዘን ተመትቼ።
አቤት ውርደት! "እንዳትጎዳኝ" የሚለው ቃሏ በልቤ ላይ እንደ ማኅተም ታትሞ፣ ከአገር ከአገር እየቀየርኩ ለታማኝነት ስገላዘዝ እሷ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሊቶች ያወራናቸውን ምስጢሮች በአንዲት ጀምበር ክዳ ሌላ ጎጆ ቀለሰች። ከሥራ ራቅኩ፣ ከቂርዓቴ ተለየሁ። ዓለም በዓይኔ ላይ ጠበበች። ያቺ የነገርኳት እራቢያ በጆሮዬ ያንሾካሸከችው "የወንድ በቀል" ዜማ ትዝ አለኝ። ሴት ልጅን፣ በተለይም "የሰለፍያ እንስት" የምትለውን ማንነቷን ጠላሁት።
ምሬቱ አንጀቴን በላው። "አልፈልግህም፣ ሌላ አግብቻለሁ" ብላ በግልጽ ብትነግረኝ ኖሮ እንዲህ አልሰበርም ነበር።እኮ አልኩኝ" ግን ምስጢሯን አጭቃ፣ ስልኳን በባላ አስነስታ፣ የሁለት ዓመት የሕይወት ጉዞአችንን በመከራ ጽዋ ስትደፋው... ልቤ ተቦጫጨቀ።ደም አለቀስኩ ሀቂቃ
አይከል ሆይ
"አንተ የኔ ነህ" ያልሽው፣ ያ ያንደበቴ ማር፣
ዛሬ መርዝ ሆኖብኝ፣ ልቤን ሲሰባብር።
በሰው አገር ምድር፣ ብቸኝነት ሲወጥረኝ፣
"እንዳትጎዳኝ አደራ" ብለሽ፣ በቃልሽ ስታስረኝ፤
እኔ ተይዤ ስገባ፣ ስጋትሽ የነበረው፣
ዛሬ ሌላ ወንድ አቅፈሽ፣ በሰከንድ ረሳሽው?
አባትሽ ገና ሞቶ፣ ዐፈሩ ሳይመለስ፣
እንባሽ ሳይታበስ፣ ሐዘንሽ ሳይለሰልስ፤
እንዴት ወር ባልሞላ፣ የደስታ ድግስ ደገስሽ?
ያለፍንበትን ቃል፣ በእሳት አቃጠልሽው።
እኔ የሙሐመድ ልጅ፣ በክህደትሽ አልጠፋሁም፣
በቆሰለ ልቤም ቢሆን፣ ተስፋን አልቆረጥኩም፤
አንቺ ግን...
የባልሽን ሐቅ ጠብቂ፣ በበቀል የታወርሽ፣
የእኔን የነፍስ ቁስል፣ በሠርግሽ ድግስ ቀየርሽ።
ክፍል⓳ ይቀጥላል
