(የወጣቶች አለም)🌏 عَالَمُ الشَّبَاب
前往频道在 Telegram
🌟 እንኳን ወደ "የወጣቶች አለም" በሰላም መጣችሁ! 🌟 በኢስላማዊ እሴቶች፣ በአኽላቅ፣ በቁርኣን እና በሐዲሥ ብርሃን የወጣቶችን የዱንያ እና የአኺራ ስኬት ለማጎልበት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ። 💡 ኢስላማዊ እውቀት | 🚀 አነቃቂ ምክሮች | 📚 የመልካም ስነ-ምግባር መመሪያዎች💥1ታሪክ 💥2የትዳር ተሞክሮዎች 💥3ኢስላማዊ የእውቀት ፈተና ተቀላቀሉን፤ በእስልምና ብርሃን አብረን እንደግ! 🌙✨
显示更多未指定国家未指定类别
319
订阅者
无数据24 小时
+207 天
+4630 天
帖子存档
Repost from N/a
ጥያቄ 🤔❓
#ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው
ምርጥ እና ጠቃሚ ቻናልያገኛል ።
1] አያተል ኩርሲይ የሚገኘው በየትኛው
ሱራ ውስጥ ነው?
💥የጧት ዚክር እንዳንረሳ!
اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.
አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል በአንተ ለምሽት እንበቃለን በአንተ ህያው እንሆነናን በአንተም እንሞታለን መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
🌟اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلً
መልካም ውሎ☕️🍫☕️🍫
•━════✿🍃🌺🍃✿════━•
💥💥💥💥💥 የሳምንቱ የትዳር ወግ — 5⃣ ⚜️✍️ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ 💫 እንዴት ናችሁ ያ አህባብ? ባለፈው ክፍላችን «የኢስቲኻራህና የሱና መንገድ» በሚለው ርዕስ ላይ ተወያይተን በኮመንት አስተማሪ ሐሳቦችን አጋርታችሁኛል — ጀዛኩሙላሁ ኸይረን! 🤲✨ ዛሬ ደግሞ ነገሮችን ቀለል አድርገን ወደ ሌላኛው ወሳኝ ቅድመ-ትዳር ርዕስ እንሸጋገራለን፦ የዛሬው ርዕስ፦ በትዳር ውይይት ወቅት ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ አራት ነጥቦች! 💬🌸 ብዙ ጊዜ ለትዳር ስንነጋገር ተገቢውን ወሰን ጠብቀን በግልጽ መነጋገር ይከብደናል። ወይ እጅግ አፍረን ዋና ዋና ነገሮችን ሳንጠይቅ እንቀርባለን ወይም ደግሞ ወደ አላስፈላጊ ወሬ እንገባለን። ነገር ግን ቀለል ባለ መንገድ እነዚህን 4 ነገሮች ማወቅ ቀጣዩን መንገድ ግልጽ ያደርገዋል፦ መወያየት ያለብን 4 ነገሮች፦ 📖 1. የዲንና የአስተሳሰብ አቋም፦ የእለት ተእለት የዲን ልምዱ (ሶላት፣ ቁርኣን) እንዴት ነው? ለዲን ያለው ቦታና ወደፊት በጋራ ለመበራታት ያለው ፍላጎት ምን ይመስላል? 🌱 2. የህይወት ግቦችና እቅዶች፦ ስራ፣ ትምህርት፣ ወይም የወደፊት የመኖሪያ ቦታ ላይ ያሉት እቅዶች ምንድን ናቸው? ሁለታችሁም ወደ አንድ አቅጣጫ ነው የምትጓዙት ወይስ አስተሳሰባችሁ ይራራቃል? 🤝 3. የቤተሰብና የማህበራዊ ህይወት እይታ፦ ከቤተሰብ ጋር ያለው ቁርኝትና ክብር ምን ይመስላል? የትዳር አጋር ለቤተሰብ የሚሰጠው/ የምትሰጠው ቦታ ለነገው ቤት ሰላም ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። 💡 4. የባህሪና የቁጣ አያያዝ፦ ሰው ሲቆጣ ወይም ነገሮች እንደፈለገው ሳይሆኑ ሲቀሩ እንዴት ያስተናግዳቸዋል? ትዕግስትና ምክንያታዊነት በትዳር ውስጥ በጣም አስፈላጊ ባህሪያት ናቸው። ትዳር የሁለት ሰዎች የህይወት ጉዞ በመሆኑ፣ ገና ከመጀመሪያው በሐቅና በግልጽነት ላይ የተመሰረተ ውይይት ማድረግ ከብዙ ውዥንብር ያድናል! 🕊️✨ 🤔 ጥያቄ ለእናንተ፦ ከትዳር በፊት በሚደረግ ውይይት ወቅት ለአንተ/ልአንቺ ጭራሽ ስምምነት ላይ ልትደርሱበት የማትችሉት (Deal breaker) የሆነ ነገር ምንድነው? ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇 👉 ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! እስቲ እንወያይበት! ✨ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✍️ 𝒁....
Repost from N/a
ጥያቄ 🤔❓
#ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው
ምርጥ እና ጠቃሚ ቻናልያገኛል ።
1] አያተል ኩርሲይ የሚገኘው በየትኛው
ሱራ ውስጥ ነው?
ሰው ሲያያቹ ምትፈሩ ሰዎች....
🍂ስንትሺህ አይን ያለው እንጀራ ሳታቅማሙ ሳትፈሩ እየበላቹ ሁለት አይን ያለውን ሰው እንዴት ትፈራላች 🤭
እኔ አደለሁም ያልኩት
ላጤያን አብሽሩልኝ 😉
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
🌱@Binaulzat
➡️ ላሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላይ
"لا حول ولا قوة إلا بالله"
(ብልሀትም ሆነ ሀይል የለም
በአላህ ቢሆን እንጂ)
ምላሳችን አንዳንዴም
ኸይር ነገር ታውራ እንጂ
ደጋግማቹ ዘክሩበት
ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡ አንደበት እንጂ መልክ
አይናገርም፡፡ መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡ ስነ
ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡ እምነትና ፍቅር እንጂ
መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡ መልክ የላይ ማንነትን እንጂ
የውስጥ ሰብእናን አይገልፅም፡፡ ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር፣
ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡
እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው።
ሰናይ ለይል 😉
💥💥 እይታ 😳 5⃣ 🤓
ከዓላማ አልፎ ወደ ተውፊቅ፦ 📖✨
በክፍል 4 ስለ ማንነትና ስለ ሲስተም ለውጥ (Identity & Systems) ተነጋግረናል! ዛሬ ደግሞ በሰጠችሁኝ አስተያየት መሠረት፦ የገነባነውን አዲስ ማንነትና የየቀኑን ሲስተም በቁርኣንና በሐዲስ እንዴት እንደምናስደግፈውና ዘላቂ እንደምናደርገው እናያለን! 🧠🌱
አንድ አማኝ «እኔ ሶላቴን ጠባቂ ነኝ» ወይም «እኔ ቁርኣንን አፍቃሪ ነኝ» ብሎ ማንነቱን ሲቀርፅ ያ ማንነት በባዶ ተስፋ ሳይሆን በአላህ እገዛና በጽናት የሚገነባ ነው! ⚙️✨
📖 1. ትንንሽ ግን ዘላቂ ሥራዎች (የነቢዩ ﷺ መንገድ)፦
ሲስተም ማለት የየቀኑ ትንንሽ ልምዶቻችን ናቸው ብለናል። ነቢዩ ﷺ ይህንን ታላቅ እውነት ሲያስተምሩን፦
«ከሥራዎች ሁሉ ወደ አላህ ይበልጥ ተወዳጁ — ትንሽም ብትሆን ዘላቂ የሆነችዋ ናት!» (ቡኻሪና ሙስሊም)
በየቀኑ 2 ገፅ ቁርኣን ማንበብ በወር አንድ ጊዜ 30 ገፅ ከመግፋት ይበልጥ አላህ ዘንድ ተወዳጅና ማንነትን የሚቀይር ነው!
❤️ 2. የውስጥ ለውጥ የውጭን ውጤት ይወስናል፦
ማንነታችንና አስተሳሰባችን ሳይቀየር የውጭ ህይወታችን አይቀየርም አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ እንዲህ ይለናል፦
«አላህ በህዝቦች ዘንድ ያለውን (መልካም ነገር) አይለውጥም እነሱ በነፍሶቻቸው (በውስጣቸው) ያለውን እስከማይለውጡ ድረስ!» (ሱረቱ ራዕድ፡ 11)
ልባችንንና አስተሳሰባችንን ስንቀይር አላህ ሁኔታችንንና ተግባራችንን ያገራልናል።
🤲 3. ተውፊቅና ኢስቲዓና (በአላህ መታመን)፦
ምንም ያህል አሪፍ ሲስተም ብንቀርፅና ማንነታችንን ብንቀይር ያለ አላህ እገዛና ተውፊቅ ምንም ማድረግ አንችልም። ለዚህ ነው በየሶላታችን «አንተን ብቻ እንገዛለን፤ ባንተም ብቻ እንታገዛለን» (ሱረቱል ፋቲሓ) እያልን የምንደግመው። ጥረታችንን ከዱዓ ጋር ማያያዝ የመጨረሻው የስኬት ሚስጥር ነው!
የባህሪና የህይወት ለውጥ የሚጀምረው ከውስጥ ልብህ/ሽ ነው! የየቀኑን ትንንሽ መልካም ልምዶች በአላህ እገዛ አጽንተን ስንይዝ ማንነታችን ፍጹም ይቀየራል! 🏃♂️💨
💥 ይህንን ክፍል ያዘጋጀሁላችሁ ባለፈው በኮመንት በሰጣችሁኝ አስተያየት መሠረት ሀሳቦችን ከቁርኣንና ከሐዲስ ማስረጃዎች ጋር አዋህጄ ነው ለሁላችንም አላህ ጠቃሚ ያድርግልን! 📚💚
💭 እስኪ ጥያቄ ለእናንተ፦ በየቀኑ ሳታቋርጡ (በትንሹም ቢሆን) በዘላቂነት ለመስራት የወሰናችሁት አንድ የዲን ወይም የዱንያ በጎ ልምድ ምንድነው ? ነይቱ ካልነየታቹም (ለምሳሌ፦ የጧት አዝካር፣ 2 ገፅ ቁርኣን፣ 5 ገፅ መጽሐፍ...) ኮሜንት ላይ አጋሩን! 👇
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✍️ 𝒁 ........🙃 🌸
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የናንተስ ከፋ ማሻአላሕ የለ ኢንሻአላሕ የለ 🤧🤧 ምንድነውውውውውውውውውውውው ችግራቹ🥵
ደሞ ግሩፑላይያላቹ ሰዎች እንዳትታፈሱ ኑ ወደ ቻናሉ ተናግሪያለው እኔ
ወጣትነት... ማንም የማይረዳው ሕመም 💔🔥ቤተሰብ አንተን እየጠበቀ ነው... እውነት አይደለም? ራሰህን አበርትተህ በትልቅ ሞራልና ተስፋ ልትሰራ ስትወጣ ደግሞ፦ 📍 መንገዱ ጥምዝምዝ ይሆንብሃል 📍 ስራው ከጠበቅከው ውጭ ዝንፍ ይላል 📍 የቅርብ ጓደኞችህ ሳይቀር ልውጥውጥ ይሉብሃል... ሁሉ ነገር ግራ አጋብቶህ ምንድነው ነገሩ? እያልክ ነው አይደል? ይህ ወጣትነት ይባላል! 🧠⚡ ትከሻህ በደንብ ሳይጠነክር፦ • ቤተሰብ፣ ስራን፣ ፍቅርን ሁሉንም በአንድ ላይ መሸከም አእምሮህ በብዙ ነገር ሲወጠርና ትዕግስትህ በሚፈታተኑ ነገሮች ሲከበብ... ይሄ ሁሉ በወጣትነት መከፈል ያለበት ዋጋ ነው። ግን እናልፈዋለን! ✊✨ ምክንያቱም ከሁሉ በላይ የሆነው አላህ (ሱ.ወ) አለልን! ምክንያቱም ወድቆ መቅረት የሰነፎች መንገድ ነው! ዝም ብለህ አሻግረህ አስበው፦ ይህንን ፈታኝ ጊዜ አልፈኸው ስትስቅበት ቤተሰብህ ባንተ ሲኮራ የደከምክበትን ውጤት ስታገኝ... ሁሉም ነገር በጊዜው ያምራል ኢንሻ አላህ! ትንሽ ሰብር ብቻ! ☘ ወጣትነት (በተለይ ወንድነት💪) ማንም የማይረዳው የውስጥ ሕመም አለው... ግን ጥርሳችንን ነክሰን እናልፈዋለን ከዛም በትልቅ ፈገግታ እንስቃለን! ያ አኺ... አብሽሩ! ያልፋል! 💪💚 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 👉 እስኪ ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉት ዛሬ በርታ የምንለው ወንድም ያስፈልገናል አብሽሩ በሎቸው ! ⬇️
.
እረ we should be proud of
ourselves wellahi 👏👏
ዋጥ አድርገን ያለፍነውን ፡
እኛ እና አሏህ ነን የምናውቀው❤️🩹
በርቺ ጀግኒት ነፍሴ
ሰሉ አለነቢ እህባብ
በኔ ላይ አንድ ሰለዎት ያወረደ አሏህ በሱላይ 10 ያወርድበታል ብለዎል ነብያችን ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
ኮመንቱን በሰለዎት😊
🥀ከሰዎቹ ሁሉ ቆንጆዎቹ ትላልቅ ህፃናት ናቸው ....🫶🏼
〰ትላልቅ ህፃናት በእድሜ ትልቅ ናቸው።አርጅተዋል ፣ ሸብተዋል ።ግና ቀልባቸው እንደ አምስት አመት ህፃን ነው ..ለሰው ያዝናሉ ፣ስለ ሰው ይጨነቃሉ 🥹
እዝነት በመጥፋቱ በአለም ላይ "ሞት ..ችግር...ርሃብ...#ስደት
..ጦርነት በዛ "ተሳሳትኩ?
🤲🏻አላህ ሆይ ለባሮችህ አዛኝ የሆነችን ቀልብ ስጠን ፤ከጨካኞችም አታድርገን
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
🌱@Binaulzat
ኢማናችንን ቻርግ ምናረገው በሰሏት ፣ቁርዕን በመቅራት ፣አዝካሮችን በማብዛት ፣እውቀትን በመማር አሏህን በማወቅ ወዘተ እና ቻርግ ማለቁን አይተን ቻርጅ እንደምናረገው ኢማናችንንም መድከሙን አይተን ቻርጅ ልናረገው ይገባል አሏህ ያግዘን
https://vt.tiktok.com/ZSqwgDcS4/
