የጥበብ እመቤት 📜
前往频道在 Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
显示更多未指定国家未指定类别
270
订阅者
+224 小时
+107 天
+15330 天
帖子存档
270
የብቸኝነት ጥላ
ሰፊው ዓለም ጠቦኝ ሰው በሞላበት
ብርሀኑ ጠፍቶብኝ በጨላማ እውነት
የብቸኝነት ጥላ በላዬ ላይ አጥልቶ
የሳቅኩበት ዘመን እንደጉም በኖ
ከሰው ማሀል ሁኜ ሰው ናፈቀው ልቤ
ትዝታህ ብቻ ነው ሚዞረው ከብቦኝ
ብቻዬ ስኳትን በሰው መሀል ቁሜ
ባዶነት ገደለኝ ደማብኝ አካሌ
ድምፅህ ለመስማት ጆሮዬ ቢጓጓም
ያለፈው ትዝታ ዛሬ አይመልስልኚም
ብቸኝነት ጥላ ተከብቤ ዛሬ
በናፍቆት ተቀጣሁ ጠፍቶብኝ መኖሬ።
270
If you are depressed
You art living in the past.
If you are anxious.you are
Living in the future .
You are living in the present.
✍️ Lao.Tzu270
አስመሳይ ....
ሁሌ ልወደድ ባይ ለሰው ጥሩ መሳይ
ንግግሩ ካፉ ፍቅሩ ካንገት በላይ
የቆመ ከሰው ጋር ሰው መስሎ የሚታይ።
ስቆ ሚያታልል
ልሙት ብሎ እሚምል
ወዳጅ መሰሎ ቀርቦ
የሚወጋ ከቦ
ከዛ ሰው ተጠንቀቁ
ስለሳቀ አትሳቁ
ከላይ ወዳጅ መስሎ የእውነት አፍቃሪ
አስመሳይ ክፉ ነወ ሳይሞቱ ቀባሪ
270
ስለ ህይወት....
ወጣ ውረድ የህይወት መንገድ ነው
ነገር ግን ማቆያ ቦታ አይደለም
በትዕግስት መፅናት ማለት ወደ ስኬት
መድረሻ ምዕራፍ መግባት ማለት ነው።
ሀዘን በደስታ መከራ በስኬት የሚተካው የፅናት
ዋጋ ሲከፈል ነው።የትዕግስት ፍሬዋ ሲቀመስ
ሁሉም መራራ ነገር ይረሳል።
270
M✍️ለአዕምሮ ሠላም የሚሰጡ የጥበብ መንገዶች
✍️1.ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር።
✍️2.ከሚረብሹህ ሰዎች ራስህን አርቅ፡
✍️3.ሁልጊዜ ለፈጣሪህ ምስጋና አቅርብ።
✍️4. የሁሉንም ሰው ደስታን መጠበቅ አቁም::
✍️5. ቂም መያዝ የራስን ቤት እንደ ማቃጠል ነው።
✍️6. በዛሬው በረከትህ ላይ ትኩረት አድርግ።
✍️7.ስለማትቀይረው ነገር መጨነቅን ተው።
✍️8.ደስታህን በሰዎች እጅ ላይ አታድርግ።
✍️9.ትናንት ላለፈው ስህተት ራስህን አትቅጣ።
270
*_<<ተወዳጆች>>_*
*(ስለ ልብ መታወክና ስለ እምነት)*
*"ልጄ ሆይ፣* በውስጥህ የጭንቀትና የፍርሃት ማዕበል ሲነሳብህ አትደንግጥ።
የነፍስ ጠላት ሰይጣን አንተን ተስፋ ለማስቆረጥና ካለህበት መስመር ለማውጣት በትዝታዎች፣ በጥርጣሬዎችና በትልልቅ የጭንቀት ሐሳቦች ልብህን ይወጋዋል።
በእነዚህ ሐሳቦች ላይ አትደገፍ፣ አትከራከራቸውም።
ልብህ ግራ ሲጋባ ‘ *ጌታ ሆይ* ፣ እኔ ደካማ ነኝና አንተ እርዳኝ፣ አንተ ጠብቀኝ’ በማለት ራስህን ዝቅ አድርግ። ሰይጣን አንተን ሊያጠፋህ ሲመጣ፣ አንተ ወደ እግዚአብሔር ስትሸሽ ያኔ ኃይሉ ይደክማል።
ጭንቀትህ የቱንም ያህል ታላቅ ቢሆን፣ የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ከዚያ በላይ ሰፊ ነው።
ዛሬ የምታየው ጨለማ ነገ ብርሃን ሆኖ ያልፋል። ጽኑ ሁን፣ በትዕግሥትም ጠብቀው።"
270
የሚያጽናናሽ ሁሉ ራሱ ቁስል የሌለበት አይደለም"
የሚሰጥሽም ሁሉ ከአንቺ የበለጠ ያለው ሰው አይደለም
መስጠት ገንዘብ ወይም ንብረት ብቻ መካፈል አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች የቀራቸውን ትዕግስት ያካፍሉሻል በልባቸው የቀረውን ተስፋ ይሰጡሻል
ከራሳቸው ረጅም ሀዘን በፊት የመጨረሻዋን ፈገግታ እንኳ ከአንቺ ጋር ይካፈላሉ "
ስለዚህ ለሚያሳዩሽ ፍቅርና ደግነት አክብሮት ስጪ'
#ያ በእውነት ውድ ነውና»
270
Repost from Never Give up!!!
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
ሕይወት ብርሃንና ጥላ ድብልቅልቅ ያለባት መድረክ ናት። አስደሳች ጊዜያት እንደ ብርሃን ሆነው ሲታዩን፣ ፈተናዎች ደግሞ የጥላውን ክፍል ይወክላሉ። ብዙውን ጊዜ ብርሃኑን ብቻ እንፈልጋለን፣ ጥላውን እንሸሸዋለን። ነገር ግን፣ ብርሃን ያለ ጥላ ትርጉም አይኖረውም፤ ጥላም ያለ ብርሃን ሊኖር አይችልም። ጨለማ የብርሃንን ዋጋ ያስታውሰናል፣ ፈተናዎች ደግሞ ውስጣዊ ጥንካሬያችንን ያጎለብቱታል። እያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፍ፣ መልካምም ይሁን አስቸጋሪ፣ የራሱ የሆነ ትምህርት ይዞ ይመጣል። እነዚህን ሁለቱን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ስንቀበል፣ ሕይወትን በሙሉ ምሉዕነቷ የመኖር ጥበብ ይገለጥልናል።
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
270
ትርጉም የለሽ ግቦች ካላቸው መሀከል አትሁን👌
አንድ ገበሬ ሁልጊዜ በመንገድ ዳር እየተቀመጠ መኪና እስኪያልፍ የሚጠብቅ ውሻ ነበረው። አንድ መኪና ብቅ ሲል ብቻ ውሻው እየጮኸና ለመቅደም እየሞከረ በመንገዱ ላይ ይሮጥ ነበር።
አንድ ቀን ጎረቤቱ ገበሬውን፣ "ለመሆኑ ውሻህ መኪና ደርሶ የሚይዝ ይመስልሃል?" ብሎ ጠየቀው።
ገበሬውም፣ "የሚያስጨንቀኝ እሱ አይደለም። የሚያስጨንቀኝማ አንድ ቀን መኪናውን ቢይዘው ምን ሊያደርገው ነው?" ብሎ መለሰለት።
በህይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች ልክ እንደ ውሻው በትርጉም የለሽ ግቦችን ይኖራሉ።
270
"ጠንካራ ስዎች ግን እንዴት ደስ ይላሉ የማንም ሙገሳ የማንም ወቀሳ ከፍ ዝቅ የማያደርጋቸው እራሳቸዉን ሆነው የሚኖሩ ከመጣዉ መአበል ጋር የማይሽራተቱ ጀግኖች ያስድስቱኛል::🌸💜🦋
270
አንዳንዱ ጋር ቸኩዬ አንዳንዱ ጋ ዘግይቼ ዋጋ ከፍያለሁ ።
አንዳንዱ ጋር ጥጋቤ አንዳንዱ ጋ ትህትናዬ አስገምቶኛል።
አንዳንዱ ጋር መጠየቄ አንዳንዱ ጋ ዝምታዬ ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ አንዳንዱ ጋ ግዴለሽነቴ አስመርምሮኛል ።
አንዳንዱ ጋር ጨዋነቴ አንዳንዱ ጋ ብልግናዬ ረብሿል።
አንዳንዱ ጋር አማኝነቴ አንዳንዱ ጋ አህዛብነቴ አጠያይቋል።
አንዳንዱ ጋር ቸርነቴ አንዳንዱ ጋ ስስቴ አስገርሟል !!
270
እኛው ነን ጠላትሽ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሀገሬ ዘመንሽ በጠመንጃ ገዝፎ
ሰክኖ በመነጋገር ሰላም ፍቅር ሰንፎ
ሁሉም ለወንበሩ ሲሞተና ሲገደል
በየቦታው ሲወድቅና ሲጣል
ጠላቶችሽ ሁነን ልጆችሽ በጋራ
ከሩቅ ሳይሆን ፍዳሽ የቅረቡ ጎመራ
ዘመን እየሄደ ዘመን እየመጣ
ቢለያይም ቅሉ ሁሌም ያንቺ ጣጣ
ከእኛ ነው መነሻው የሰላምሽ ጥልመት
ከጎራዴም አያልፍም የሩቅማ ጠላት ።
እኛ ነን ጠላትሽ🇪🇹🇪🇹😢
270
ናፍቀሺኛል ብየ
ናፍቀሺኛል ብየ ለመጮህ አልወጣ ሰውም ቢያፌዝ እንጂ አንቺን ይዞ አይመጣ ናፍቀሺኛል ብየ እኔም ግጥም አልፅፍ ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ ብቻ ናፍቀሺኛ.....ናፍቀሺኛል በጣም
270
270
ህይወት ስታስጠላህ እና ስትሰለችህ ታሪክህን ለሁሉም አትዘርዝር።ነገር ግን ለእውነተኛ ጓደኛ አማክር። ሲደብርህ የፊትህ ፈገግታ ጠፍቶ ሴለሚታይ ብዙ አስመሳይ ሰወች ምን ሁኖ ነው አያሉ ሊስልሉህ ይችላሉ በዚያ ስአት የህይወት ታሪክህንና ገመናህ ለሁሉም ሰው አትዘርዝር የሳቁልህ ሁሉ ከውስጥ አይደለም። ይሉቁን ያንተን ዋጋ ለሚያውቅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለሚረዳህ ለአንድ እውነተኛ ወዳጅ ወይም ለቤተሰብ ደውለህ ተጨዋውት ልብህን በፈገግታ ከሚመርዙ ሳይሆን ካንተ ጋር በቁርጠኝነት ከሚቆሙት ጋር አድርገው።
270
የፍላስፎቾ ንግግር... 🗣️
ሀብታም የደከያል ሀኪም ይሞታል
ጎበዝ ይሸነፋል ብልህ ይሳስታል
የበራውን ጠፍቶ የሰሩትን ይፈርሳል
የቆመው ወደቆ የሳቀ ያለቅሳል
ግጥም ሆነ #ጥበብ 💫
ውበት ሆነ ክብርም
ያማረበት ነገር ማስቀየሙ አይቀርም ✨
