قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
前往频道在 Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
显示更多未指定国家未指定类别
914
订阅者
-324 小时
-177 天
+5330 天
帖子存档
በሰፈሩበት ቁና..!
ማነህ ልጅ ከዛ ማዶ ሸይኽ አቡ ዘር ስለ ሰሞነኛው ጉዳይ (ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን በሰይድ ቁጥብ ዙሪያ) ስለተናገረው ነገር ያደረገውን ረድ ላክልኝማ። ወይንስ አላደረገም? ለምን? አይ ከዚህ በፊት ሰለ ሰይድ ቁጥብ ማንነት ቀደም ብሎ ተናግሯል ብለህ እንዳታስቀኝ ብቻ! ጥያቄየና መልስህ አይገናኝም እኔ የጠየኩህ ስለ ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን የተናገረውን ነው አንተ የመለስክልኝ ስለ ሰይድ ቁጥብ ያወራውን ነው። አራንባና ቆቦ። ስለ ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን ሌሎች ተናግረዋል ረድ ማድረግ ደግሞ "فرض الكفاية" ነው ልትለኝ ባልሆነ¡ ደፍረህ አዎ ካልከኝ፡ መልሴ ለሌሎች ያጠመዳችሁት ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብላችሁ ገብታችሁበታል ነው። ከዛ ቡሃላ እኔም እናንተው እንዳመጣችሁት "አዩሃል ሙመይዑን" ማለት እንድ ጀምር ይፈቀድልኝ⸘ ማነህ ልጅ ባለፈው titok ስፈር ላይ ሂደህ ኡስታዝ አቢኑ ሙነወር በሰሞነኛው ጉዳይ ስላወራው ነገር አንስተህ፡ "ሙመይዑ ኢብኑ ሙነወር" የሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንን ስም አላነሳም ያልከው ልጅ ግን በጣም ነበር እንዴ የታመምከው! ያልከውን የረሳሁልህ መስሎህ ነዋ? አሁን በል "ሙመይዑ አቡ ዘር" ስለ ሸይኽየው የተናገረውን ላክልኝማ‽ በሰፈሩበት ቁና ይሉሃል እንዲህ ነው።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
በነገራችላይ አቡ ሙዓዝ የስነ-መግባር ሰው ቢሆን በማስተማሩና በአንዲበቱ እሱጋ የቀረበን አካል ተፅኖ ማሳደር የሚችል ሰው ቢሆን ኑሮ
ከሱጋ የአኽላቅና የመረጃ ንጥቀት ቢኖረው ኑሮ ወንዲሜ አቡ ሹራን ይዞ መሄድ ይችል ነበር
ሁሉም በተወበት ሰአት አኽላቁንና አላማውን በተገነዘብንበት ሰአት ማንነቱን ሳያውቅ በመልካም ጥርጣሬ አብሮት የነበረው ገራ ገሩ ወንዲሜ አቡ ሹራ ነበር
ተከትሎት ግን አልሄደም !!!
በቻለው ከመከረ ካስመከረው ቡሃላ ምንገዱን ጨርቅ ያርግልህ ብሎ ነው የሸኘው
ምልል ፈልጌ ነው ከአቡ ሙዓዝ ጋ ከተነቃቃን ውለን አድረናል ብዙም አልደነገጥን አልባባንምም ጫው ለራስ ብለህ ጣፍጥ ካልሆነ ዲንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል ይባላል
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
ዐፍወን የአቡ ሙዓዝን ጉዳዩ ተወት ብታደርጉት መልካም ነው ብየ አምናለሁ።መሄዱ ቡዙ የሚፈጥረው አድስ ሽቡሃ ይኖራል ብየ አላምንም።ያው ድሮ ተቦክቶ የተጋገረ ነው።ይሄን እንደ አድስ አንስቶ መመዛመዝ ደግሞ ጊዜ ማባከን እንዳይሆን።ገና ዘሎ እዛ ከመግባቱ ሙመይዓ ብሎ መናገሩ አለያም በተምይዕ መወንጀሉ፡ከዛ ሰፈር የሞጠለው ስለሆነ የሚጠበቅ ነው።ምናልባት የተለየ ነገር ይፈጠራል ተብሎ ከተሰጋ አድስ ነገር ማምጣጡ ከተደረሰበት የዛኔ ከመልስ ምት እስከ ወይይት ድረስ እየተገባበዝን እናወራለን።አይሻልም?ለእኔ ይሄ የሚበጅ ይመስለኛል።
አላህ በአቡ ሙዓዝ መቀናት ውስጥ መልካምን ካወቀ ወደ ቅኑ ይመልሰው።እርሱን ብቻ አይደለም ሌሎች ከእውነታ የሸሹን ሁሉ አላህ ቅኑን ያሳውቃቸው።
ወንድማችሁ አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
📌አምኛችሁ ያላመናችሁኝ፣
ወድጃችሁ የጥላቻን ጥግ ያሳያችሁኝ፣
በሌለሁበት የተናገራችሁኝ፣
ያሳዘናችሁኝ፣ ልቤንም የሰበራችሁኝ ሁሉ…
ከልቤ ይቅር ብያችኋለሁ።
📍ምናልባት ያደረጋችሁትን ሁሉ ልረሳው አልችልም፤ ግን በልቤ ቂም ይዤ መኖር አልፈልግም። የሰውን ጥላቻ ተሸክሜ ልቤን ማድከምም አልፈልግም።
📍እኔም ፍጹም ሰው አይደለሁም፤ ሳላውቅ ወይም አውቄ ያሳዘንኳችሁ፣ የበደልኳችሁ ወይም የተሳሳትኩባችሁ ነገር ካለ፣ እኔም ዐፍውታን እጠይቃለሁ።
ያለፈውን በይቅርታ እንዝጋው፤ የወደፊቱን በሰላም እንመልከተው።
ልቤ ከቂም ነፃ ነው፤ እናንተንም ከልቤ ይቅር ብያችኋለሁ።
ነገ እሞታለሁ የሚል ዐፍው ሊባባል ይገባል
አላህ እኔንም እናንተንም ይማረን፣ ልባችንን ከጥላቻና ከቂም ያጥራልን፣ በመካከላችንም ፍቅርን፣ ይቅርታንና ሰላምን ያስፍን።
አሚን‼️
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሽርክ ነው ዒሬቻ !!
ተውሒድን ስበኩ ከዘር ቅርቃር ውጡ፡
ሐቅን ግልፅ አድርጉት በቃ ተለወጡ፡
ከዒሬቻ ኮተት ህዝቡን አስጠንቅቁት፡
ሐቅን አሰራጩ ከጥመት አርቁት፡
ይህንን ትልቅ ህዝብ የዋሁን ይዛችሁ፡
እሱ እናንተን ወዶ እያከበራችሁ‼️
ኢሬቻን ሲያከብር ዝም ትላላችሁ⁉️
አወ ነገ አሏህ ፊት ትጠየቃላችሁ‼️
የኦሮሚያ ሙስሊሙ እውነት ለመናገር፡
ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል ለዚህች ሀገር፡
ለኦሮሞ ህዝቦች አለኝ ልዩ ፍቅር፡
ሙስሊም አይወክልም #ኢሬቻ ግን ይቅር፡
የጥመት አዝመራ የሽርክ ጥንቅር፡
......ኢሬቻ ግን ይቅር‼️
ኢስላም ዖሮሚያ ላይ በነፃነት ነግሷል፡
ለብዙ ዘመናት ታሪኩ ታድሷል፡
ለእስልምና ሲባል ብዙ ደም አፍስሷል፡
በሙስሊምነቱ በጠላት ተወቅሷል፡
በተውሒድህ ፅና በሱናህ ላይ ክተት፡
ሁሌም ከሚፈፀም ከመጥፎ ስህተት፡
በእምነትህ ፅና በቃ አትንሸራተት፡
ለሀቅ የሚቆሙ ኦሮሚያ አሏት ጀግኖች፡
የተውሒድ መምህር የሱና ልሳኖች፡
የትኛውም ቦታ ሀቅን የሚሰብኩ፡
የሰወችን ሀሳብ በሁጃ እሚለኩ፡
ቅጥፈትና ውሸት የማይፈበርኩ፡
እናም ጀግኖቻችን አሁንም በርቱልን፡
ከኢሬቻ በአል ህዝቡን ከልክሉልን፡
ተናገሩ በግልፅ ህዝቡን አስጠንቅቁት፡
ከሽርክ እንድጠበቅ ሐቁን አሳውቁት፡
በእውቀት አንፁት ከተኩላ አርቁት፡
በግልፅ ንገሩት ህዝቡ ሀቅ ይሰማል፡
ውቅያኖስ ላይ ሆኖ ውሀ እንደት ይ'ጠማል፡
ተውሒድ እያለለት ሰው በሽርክ ይከስማል⁉️
ኢስላም አያውቀውም ሽርክ ነው ካላችሁ፡
አሏህ አጂራችሁን በእጥፍ ይክፈላችሁ‼️
ዒስላም የማያውቀው የባዕድ አምልኮ፡
#እንጨትን_ዘይሮ_ድንጋይ_ግንድ ታኮ፡
የለም በዕምነታችን ከአሏህ ውጭ አማላጂ፡
ማን ነው የፈቀደው ማን ነው በድን ቀላጂ‼
አናመልክም #ዋቃን ዛፍ ቅቤ እየቀባን፡
ሽርክ ነው እንራቅ አይሆንም ለቁርባን፡
ስሜት ነው በስህተት ገደል የሚያስገባን፡
ሽርክን እንፀየፍ ተውሒድ ብቻ ይግባን፡
በእስልምናችን ይህ አይፈቀድም፡
ይህን ያፀደቀ ደሊል የለም አንድም፡
አሏህ ከልክሎናል ከቶ አይወደድም፡
ፈፅሞ አይቻልም ዒስላም አያውቀውም፡
ይህም ጭካኔ እንጂ እዝነት አንለውም፡
ህዝቡ እንድሰባሰብ ካስፈለገ ደግሞ፡
ተውሒድን መስበክ ነው ደጋግሞ ደጋግሞ፡
....ከዚህ ውጭ...
ወንዝ ዳር በመሄድ ሳርን በመበተን፡
ሰይጣን ተከትሎ ጥመት በመተንተን፡
አይሆንም ይህ ተግባር እሳት ነው ፍፃሜው፡
ከኢሬቻ እራቁ ሔዋንም አዳሜው፡
....ለኦሮሚያ ዱዓቶች....!!
የዋሁ ወገንህ በሽርክ እያለቀ፡
ቄጠማ ጎዝጉዞ እደተደለቀ፡
ከወንዝ ዳር ወርዶ ወሀ እየተራጨ፡
ሽርክ እየፈፀመ ተውሒድ ካቀጨጨ፡
የት አለ መረጃህ ከየትስ መነጨ⁉️
አንተ ኦሮሚያ ውስጥ ምን ነበረ ስራህ⁉️
ሽርክን ካላወገዝክ ተውሒድ ካልተጣራህ፡
ለሐቅ የሚፋለም ጀግና ካላፈራህ፡
#በአሏህ_ይሁንብኝ__‼
አዕምሮ ያለው ሰው ይህንን አይሰራም፡
ሽርክ ስትፈፅም አሏህን አትፈራም⁉️
የኢስላም ወገኖቼ #ዖሮሚያ ያላችሁ፡
ሽርክ ላይ ሲወድቅ የዋሁ ህዝባችሁ፡
ዒሬቻን ሲያከብር ምን ትሰራላችሁ⁉️
አሏህን ያውቃሉ አሊም ተብላችው፡
ኸረ አሏህን ፍሩ ጥያቄ አለባችሁ⁉️
#ሙስሊሞች_ሆይ_ንቁ__‼
ከዒሬቻ በዐል አማኞች እራቁ፡
ይህን መጥፎ ተግባር በጣም ተጠንቀቁ፡
በአቅራቢያው ካላችሁ ከቦታው ልቀቁ፡
የአምልኮን ተግባር ስጡ ለአሏህ ብቻ፡
የጥመት ጥርቅም የሽርክ ግትቻ፡
ባዕድ አምልኮ ነው የወንጀል ሽልቻ፡
ቢዲአ ኹራፋት ኮተት አራሙቻ፡
የክህደት ተግባር ሽርክ ነው ዒሬቻ፡
#በኑረዲን_አል_አረቢ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
🤎►▸ሰው ሞተ◂◄🤎
በፊት ድሮ ያኔ
ሞተ ሲባል ሰው፣
ሁሉ ያዝን ነበረ
ምንም ባያቀው፣
አሁን አሁንማ
ሞት እንደቀልድ ሆኖ፣
በጅምላ ሰው አልቆ
ሜዳ ተበትኖ፣
ልክ እንደ በፊቱ
ማዘኑ እንኳን ቢቀር፣
እንዴት ይጠየቃል
የሞተ ሰው ብሄር✅
✍✍️
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
Repost from ተቀርተው ያለቁ ደርሶች
የዐቂዳ ኪታብ ደርሶች፦
1- ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ
2- አልዐቂደቱ አጦሓዊያ
3- አልዐቂደቱል ዋሲጢያ
4- ላሚየቱ ኢብኒ ተይሚያህ
5- ሓኢየቱ ኢብኒ አቢ ዳውድ
6- አልኢርሻድ ኢላ ሶሒሒል ኢዕቲቃድ
7- ቀዋዒዱን ሀማ ፊል አስማእ ወሲፋት
8- ኢዕቲቃዱ አህሊ ሱና ሊል ኢስማዒሊ
9- ፈትሑ ረቢል በሪያ ቢተልኺሲል ሐመዊያ
10- ሪሳለቱ ኢብኒ አቢ ዘይድ አልቀይረዋኒ
11- ሙዘኪረቱን ዐለል ዐቂደቲል ዋሲጢያ
12- ሚን ኡሱሊ ዐቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወልጀማዐ
13- አብዋቡን ሙኽተሶረቱን ፊል ዐቂዳ
14- ዐቂደቱ ሰለፍ አስሓቢል ሐዲሥ
15- አልኢቅቲሷድ ፊል ኢዕቲቃድ
16- በያኑ አህሊ ሱንና ወልጀማዐ
17- አልወጂዝ ፊ ዐቂደቲ ሰለፍ
18- ሸርሑ ሱና ሊል በርበሃሪ
19- አልሙዕተቀዱ ሶሒሕ
20- አልቀዋዒዱል ሙሥላ
21- ሸርሑ ሱና ሊል ሙዘኒ
22- ሶሪሑ ሱንና ሊጦበሪ
23- ተቅሪቡ ተድሙሪያ
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ ዲኑ ሰፊ ነው!
በጥመት ሰዎች ላይ ሸሪዓዊ እርምት በሚሰጥ ጊዜ "በቃ ሱንና የግል ንበረታቹህ አደረጋቹህት!?" "ዲኑ ሰፊ ነው" እና መሰል የሆኑ ንግግሮችን ከአንዳንድ የእርጎ ዝንቦች መስማትና መመልከት የተለመደ ነው። አዎ ሱንና አዛኙ ጌታ በእርሱ ችሮታ የሰጠን ተወዳዳሪ የሌለውና ህይወታችንን የምንሰጥለት ቤታችን ብሎም የማንደራደርበት ቀይ መስመራችን ነው።
ማንም ይሁን ማን ሱንና ተቃርኖ ከተገኘ ክብሩ አያስጨንቀንም። ጥመቱን በማስረጃ እናጋልጣለን። የወቃሽ ወቀሳና የዘላፊ ዘለፋ ግድ አይሰጠንም። ዲኑም ልክ ነው ሰፊ ነው። ነገር ግን በጣም ሰፊ ይሁን እንጅ ሽርክና ቢድዓን የሚያስተናግድበት የአንዲት ፀጉር ያክል ክፍት ቦታ የለውም። ሰፊ ከመሆኑም ጋር እጅግ ንፁህና የጠራ መንገድም ነው። ይህን ንፁህ ዲን የሚያቆሽሽ ቆሻሻ ተመልክተን ማለፍ ደግሞ ህሊናችም ዲናችም አይፈቅድልንም።
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉ለኦሮሚያ ሙስሊሞች ይድረስ አደራ‼️
እኛ የዋቄ-ፈና እምነት ተከታዮች ነን በእምነታችን ውስጥ ማንም እንድስተናድ አንፈልግም ።
👉ሙስሊሙ የራሱ የሆነ በዓል አለው ራሱን ይቻል ብለዋል።
....ይህን እያሉ በግልፅ «እንከባበር»እያሉን ሳለ በግድ ሔጀ «ዋቆ-ጉራቻን»አመልካለሁ ካልክ ይሔ እምነትህን እንደማታውቅና ለእስልምናህ ክብር እንደሌለህ ማሳያ ነው።
➢ሙስሊሙ‼️
ሙሀመድም ሰይድ ጫላም ሆንክ ባልቻ፡
በኢስላም ሀይማኖት ሽርክ ነው ኢሬቻ፡
ማምለክ አሏህን ነው አንዱን ጌታ ብቻ፡
ጌታችን የለውም«ዋቆ» .ሚባል አቻ!?
በፍፁም እንዳትሔድ ከባህር ዳርቻ፡
ሁልህም አዳምጠው ይህን ማመልከቻ፡
አደራ ሙስሊሙ የኦሮሞ ቄሮ፡
በእስልምናህ ፅና ጠንክር እንደ ዱሮ፡
ለእምነትህ ክብር ስጥ ሽርክን አትጠጋ፡
በተውሒድህ ፅና አትውደቅ ለአደጋ፡
በአሏህ ተመካ ሲመሽም ሲነጋ፡
በእምነትህ ድመቅ የሰው እምነት አክብር፡
አንበሳ ይይዛል ጠንክሮ ድር ሲያብር፡
በኢሬቻ ቦታ አትገኝ ከእንግድህ፡
በእምነትህ ፅና ሁሉም እንድወድህ፡
የራስክን አስከብር የሌሎች አትንካ፡
በውድ አገርህ ላይ ግዘፍ እንደ ዋርካ፡
በቃ ቆፍጠን እንበል አንሁን መሳቂያ፡ አዳምጠን እንቁም ይህን ማስጠንቀቂያ፡የኢሬቻ አክባሪዎች በጥብቅ አስጠንቅቀዋል። እንከባበር ብለዋል። ክርስቲያኑም ሙስሊሙም የራሱ ቦታ ስላለው፤ የኛን ቦታ አይንካብን ብለዋል።
«እኛም ሰምተናል በምስጋና መልዕክቱን ተቀብለናል ብለን ከአሁን በኋላ ኢሬቻ ላይ መገኘት እንደሌለብን መወሰን ግድ ነው።»ወገኖቻችን በግልፅ እንደዚህ እያሉት በግዴታ የሚገኝ ሼም የማይዘው ሙስሊም ይኖረናል ብዬ አላስብም። «ስለሆነም ይህችን መልዕክት በተለይ ለኦሮሚያ ጀግና ሙስሊሞች የነዚህን ሰዎች መልዕክት በማሰራጨት ድምፅ እንሁናቸው። ኑር t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi
በእኔ ዘመን የነብዩ ናፍቆትና ፍቅር ህይወቱን የሰዋዉ ወጣት!
በተከበረው ረውዳ አጠገብ፣ የጸጥታውን መንፈሳዊ አየር የሚቀድ ድንገተኛ ሁከት ተፈጠረ። አራት የፖሊስ አባላት የአንድን ወጣት እጆች እንደ ወንጀለኛ ወደ ኋላ አጣምረው በገመድ አሰሩት። ወጣቱ በተሰበረ አንደበት፣ «ምን አጥፍቼ ነው? እኔ እኮ ሌባ አይደለሁም… ወንጀል አልሰራሁም! ለምን እንዲህ ትጨክኑብኛላችሁ?» እያለ በዕንባ ይማጸናል፤ መልስ ግን አልነበረም።
ይህን ገጽታ ከርቀት ሲከታተሉ የነበሩ አንድ አረጋዊ፣ ህመሙ ቢበላቸው ወደ ፖሊሶቹ ቀረቡ። «ይህን ወጣት እኔ አውቀዋለሁ» አሏቸው። ፖሊሶቹም በመገረም «ከየት ታውቀዋለህ?» ሲሉ ጠየቁ።
አረጋዊውም በዕንባ በተሞላ ዓይን «እኔ እኮ ሁልጊዜም እዚህ ረውዷዉ ፊት ለፊት ሲቆም፣ በስስት ሲቀመጥ፣ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋትና ሰላምታ ሲያወርድ፣ በውቅያኖስ ዕንባ ፊቱን ሲያርስና ሲያቀረቅር ነው የማየው! ለመሆኑ ይህን የነቢ ወዳጅ ሰው ለምን ታስሩታላችሁ? ሌባ ነው እንዴ?» አሏቸው።
ወጣቱ የአልባንያ ብቸኛ እንግዳ ነበር። ዕድሜው ከ35-36 የማይሻገርን ሙሒብ ፖሊሶቹም «አይደለም፣ ሌባስ አይደለም! ነገር ግን ከአልባንያ መጥቶ ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ በዚህች የተቀደሰች ከተማ ለስድስት ዓመታት ኖሯል። ልንመልሰው ያላደረግነው ጥረት የለም፤ ነገር ግን በያዝነው ቁጥር ከእጃችን አምልጦ እንደገና እዚሁ የነቢዩ መስጂድ ውስጥ ይከሰታል። ዛሬ ግን ሳናስረው ልንተው አልቻልንም» ብለው መለሱ።
«አሁንስ ወዴት ልታደርሱት ነው?» ሲሉ አረጋዊው ጠየቁ። ፖሊሶቹም «ሕጉን እናስፈጽማለን፤ አሁኑኑ ወደ ኤርፖርት ወስደን ወደ አገሩ በሚበር አውሮፕላን ላይ እንጭነዋለን» አሏቸው።
በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ዓለም ተናጋ። የፍቅርና የሰላም ምንጭ፣ የነቢዩ ጠረንና ትዝታ ከሞላባት ከተማ ለዘላለም ሊያባርሩት መሆኑን ሲረዳ፣ የልቡ ስብራት በዓይኖቹ ላይ እንባዉ እንደ ጐርፍ ፈሰሰ።
በተቆራረጠ ድምፅ እንዲህ ሲል ተማጸናቸው፦
«እባካችሁ የልቤን ሕመም ተረዱኝ… እኔ ማንንም አልበደልኩም፣ አልሰረቅኩም፣ የሰው መብት አልነካሁም። እዚህ የመጣሁት ለምድራዊ ጥቅም ወይም ለዱንያ አይደለም፤ ለአላህ መልእክተኛ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ብቻ ነው!»
ፖሊሶቹ ግን ልባቸው አልራራም፤ «ሕግ ሕግ ነው፤ ያለ ፈቃድ እዚህ መቆየት አትችልም» ሲሉ ወሰዱት።
ከመስጂደ ነበዊይ ደጃፍ ሊያወጡት ሲሉ፣ ወጣቱ በመጨረሻው አቅሙ አንድ የመጨረሻ ዕድል ለመናቸው። ፈቀዱለት።
ዞር ብሎ ያንን አረንጓዴ ጉልላት በስስት አየ💔። ልቡ በአንዴ ተሰበረ፣ ነፍሱ በናፍቆት ተቃጠለች። በሚያሳዝን ድምፅ ወደ ረውዷው እየተመለከተ በቃጠሎ ጮኸ፦
«هل هكذا كان الاتفاق بيننا؟!»
«የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የነበረን ቃል ኪዳን እንዲህ ነበረን?»
«የእርስዎ ጎረቤት ሆኜ እንድኖር ብዬ ንግዴን፣ ቤተሰቤን፣ አባትና እናቴን — ሁሉንም ነገር ትቼ መጣሁ… አሁን ግን ከጎንዎ እንድቆይ አልፈቀዱልኝም!» ሲል በቃታ ተናገረ።
እነዚህ የእሳት ቃላት ከአንደበቱ እንደወጡ፣ የነፍሱ ገመድ ተበጠሰ፤ ህሊናውን ስቶ መሬት ላይ ተዘረረ። ፖሊሶቹ አሁንም ለማምለጥ የሰራው ተንኮል መስሏቸው ነበር። ነገር ግን አንስተው ውኃ በፊቱ ላይ ሲረጩ፣ የዚያ አፍቃሪ አካል ምንም ምላሽ አልሰጠም። አንደኛው ፖሊስ እየተንቀጠቀጠ «ወዮልን! የልብ ድካም ሳይይዘው አልቀረም… አምቡላንስ ጠሩ!» ሲል ጮኸ።
አምቡላንሱ ደርሶ ወደ ሆስፒታል ወሰደው። ሐኪሙ ግን አካሉን መርምሮ በከባድ ኃዘን እንዲህ አለ፦
«ይህ ሰው እኮ ህይወቱ ካለፈ ከአንድ ሰዓት በላይ ሆኖታል…»
የፖሊሶቹ ጉልበት ተነቀለ፤ እያነቡም «በአላህ ይሁንብን! እኛ ተግባራችንን ስንወጣ፣ የዚህ ሰው ለአሏህ መልእክተኛ ያለው ፍቅር እስከ ሞት የሚያደርስ እንደሆነ በፍጹም አልተረዳንም ነበር…» እያሉ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። ከህክምና ሲረጋገጥም በጥልቅ ስሜትና በልብ ምት መጨመር ህይወቱ ማለፉ ከሐኪሞች ተነገረ😭😭
ያ አፍቃሪ ሰው በክብር ታጠበ፣ ተከፈነ፣ ሶላት ተሰገደበት። በመጨረሻም ወደ አልባንያ ሊወስዱት ያሰቡትን ሰው፣ አሏህ ወደ ተከበረው ጀነት አል-በቂዕ መራው—ከሚወዳቸዉ ከዓይኑ ማረፊያ ከዉዱ ሰዉ ሀገር እዚያው መስከኛዉ ሆነ።
ወደ አልባንያ ሊበር የነበረው ወጣት፣ ይልቁንም የፍቅርን ጥልቀት፣ የናፍቆትን መስዋዕትነት ለዓለም አሳይቶ ወደ ዘላለም እረፍቱ አቀና።
በፍቅራቸዉ ኖረን በሐገራቸዉ መዲና መሞትን አሏህ ይወፍቀን💔።
Repost from የአብዱረሕማን አቡ ዑሠይሚን ሙሐደራዎች ስብስብ ቻናል
✺ የጁሙዓህ ~ ኹጥባ
──────⊱◈◈◈⊰───
❑ርእስ፦ « በሰላት ዙሪያ ማስገንዘቢያ »
🎙 አብዱረሕማን አቡ ዑሠይሚን
⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍
t.me/MuhaderahChannel/1376
Repost from N/a
«ሕመምህን ሰው እንዲረዳህ ማስረዳት አለብህ፤ አላህ ግን ሳይነገረው የልብህን ሕመም እና የውስጥህን ጭንቀት ያውቃል።»
አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ በቃላት ልንገልጸው የማንችለው፣ ለሰው አውርተንም ቀላል የማይሆን ከባድ የውስጥ ሕመም ያጋጥመናል።
ለቅርብ ሰው እንኳን ለማስረዳት ቃላት ያጥሩናል፤ አሊያም ደግሞ "ሰው አይረደኝም" በሚል እጣፋንታ ዝምታን እንመርጣለን።
ሰው ሕመምህን እንዲረዳህ በረጅም አብራርተህ ማስረዳት አለበት፤ ያን ያህል ደክመህ አብራርተህ እንኳን አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ ሊረዳህ አይችልም።
አላህ ግን እንዲህ አይደለም!
እሱ የልብህን ትርታ፣ የዓይንህን ዕንባ፣ እና በውስጥህ የሚመላሰውን ጭንቀት ሁሉ ሳይነገረው ያውቃል።
በልብህ ውስጥ የተቀበረውን ስቃይ ለመግለጽ ቃላትን ማደራጀት አይጠበቅብህም።
ዝም ብለህ በዓይንህ ዕንባና በልብህ ስብራት ወደ እሱ ስታዞር፣ እሱ የውስጥህን ስቃይ ሰምቶ መልስ ይሰጣል።
የሰው ረዳትነት ወሰን አለው ሰው ሊያዝንልህ ይችላል፣ ሊያዳምጥህ ይችላል፤ ነገር ግን የልብህን ክብደት ከውስጥህ አውጥቶ ሊቀንስልህ አይችልም።
የአላህ እውቀትና እዝነት ግን ወሰን የለውም ያልተናገርከውን ያውቃል፣ ያላወጣኸውን የውስጥ ቁስል ያክማል፣ የልብህንም ስብራት ይጠግናል።
ስለዚህ፣ ሰው አልተረዳኝም ብለህ አትጨነቅ። የልብህን ጭንቀትና ሕመም የሚያውቅ፣ ሳይናገሩ የሚያዳምጥ፣ ሲለምኑት ደግሞ የማይሰለች ጌታ አለህ።
ውስጣችሁን በእሱ ላይ ጣሉ፤ በዝምታችሁ ውስጥ ያለውን ድምፅ እሱ ብቻ በትክክል ይሰማዋል!
@BerhanFelega
@BerhanFelega
Repost from Abu~Mahi Channel
🔥 ቆፍጠን በል! በሐቅ ላይ አቋም ይኑርህ!
ወንድሜ ሆይ! ሃይማኖትና መንሐጅ የጨዋታ እቃ አይደሉም። ዛሬ ላይ ትልቁ ፈተና የዒልም ማነስ ብቻ ሳይሆን የጽናትና የአቋም መሸርሸር ነው።
ለሰው ብለህ አታዳላ፤ ለማንም ብለህ አትለሳለስ! ሐቅ አንድ ብቻ ናት—እሷም በነቢዩ ﷺ እና በሶሐቦች መንገድ (በሰለፎች አሰረ-ፍኖት) ላይ መጓዝ ብቻ ናት።
እዚያም እዚህም የምትለከሰከሰዉ እስከ መቼ ነው?
"ሰለፊይ ነኝ" እያልክ በቃላት እየተጫወትክ፡
በአንድ በኩል ከሐቅ መንገድ ጋር፣ በሌላ በኩል ደግሞ አየር በነፈሰበት አቅጣጫ ከሚነዱት ጋር አብረህ አትወዝወዝ!
የሰዎችን ወገንተኝነትና ሙገሳ ፍለጋ ስትል ሐቅን አታደብዝዝ፤
ለሆድህ፣ ለስምህ ወይም ለጥቅምህ ብለህ የያዝከውን ቀጥተኛ መንሐጅ አትሸጥ!
ወንድ ከሆንክ በሐቅ ላይ ቆፍጠን በል!
የሰለፊያ መንገድ የጽናት መንገድ እንጂ የአጋጣሚዎች መጠቀሚያ አይደለም።
ዱኒያ አጫጭርና አታላይ ናት። ዛሬ በሰዎች ዘንድ ለመወደድ ብለህ የምታደርገው መለስለስና ማቻቻል፡ ነገ አላህ ፊት ሲቆም አንዳች አይጠቅምህም።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይላል፡
«በታዘዝከው ነገር ላይ ቀጥ በል!» (ሁድ፡ 112)ተውሂድን ይዘሃል? ቀጥ በል! ሱናን ጨብጠሃል? አትወዝወዝ! ቢድዓንና ጥመትን ትተሃል? አትለሳለስ! ሰው ቢደሰትም ቢጠላም፤ ዓለም ቢከተልህም ቢተውህም—አንተ ግን በሐቅ ላይ እንደ ተራራ ጸንተህ ቁም። ዱኒያ በቅርብ የምታልፍ ህልም ናት፤ አታላይ ሽንገላዋ አይዝጋህ። ወንድሜ ሆይ! ራሰህን ፈትሽ… ዛሬውኑ አቋምህን አስተካክል! @Abu_Mahi_Ibnu_Idris @Abu_Mahi_Ibnu_Idris
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
➥ኡዝር ቢል ጀህልን የተመለከቱ ወይይቶች እና ሙሓዶራዎች ለማግኘት በዚህ በኩል ይግቡ
🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ ያደረገውን ውይይት
🎙ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ስለ ዑዝር ሙሓዶራ
🎙በኡስታዝ አቡ ዒምራን ተከታታይ በያን ስለዚህ መስዓላ
ወደ ድምፆች ለማግኘት 👇👇
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/4774
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/4774
Repost from قَناةُ وفَوا ئِد أبي فَوزان الْحَبَشِيِّ
የኡስታዝ ሳዳት ከማል ከፊል ስራዎች በአፕልኬሽን
👇👇👇
🍃https://t.me/abujemila25
🍃https://t.me/abujemila25
አብሽሩ ሰለፍያ የማንም የግል ሀብት አይደልም ቶብቶ የገባን ሁሉ ይቀበላል። ሰዎች ስለሆንን አልማጥፋትና አለመሳሳት አይቻልም በላጭነት ግን ስህተትን አውቆ መመለስ ነው። በሰዓቱ እየሄዱበት ያለው መንሀጅ ትክክል መስሏቸው ሲጓዙበት የነበረው መንገድ ዛሬ ትክክል እንዳልነበራችሁ ከገባችሁ ስህተትን አምኖ ለመቀበልና ትክክለኛውን መንገድ ለመቀላቀል ማንገዳገድ አያስፈልግም። በብሩ ቀልጠፍ ብሎ መግባት እንጂ። ቅጥ ያጣ የሆነውን የተብዲዕና የተጅሪሁን የእነ (ለተሞን) መንገድ እና ምስጦፋ አብደሏህ እየመራው ያለውን የተክፊር ጎዳናም ይሁን የተወሰነ ጊዜ አብረው ከተጓዙ በኋላ ቀና ብለው ሲመለከቱት ልክ እንዳልሆነ ሲገባቸው አሁን ስህተቱ የት እና እነ ማን ጋር እንደ ነበረ እየተረዱ ያሉ ይመስላሉ። ቢረፍድም ጥሩ ጅማሮ ነው። አዎ ጎርፍ ሲመጣ ከፊቱ ያገኘውን ሁሉ እየጠረገ ነው የሚወስደው በተለይ በጠባብ ወንዝ የመጣ ከሆነ። ነገር ግን ዝቅ እያለ ሲሆሄድ በሰፊ ወንዞች ላይ ሲበተን መነሻው እየደረቀ ሲሄድ ጩኸቱ ሲደክም፡ አሁን የሚቀረው ቀድሞ የነበረው በበጋም ሆነ በክረምት የማይጠፋው ንጹሁ የወንዝ ውሃ ነው። በቃ ያኔ ጩኸቱም ስለቀነሰ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ ተገላምጦ ለማዳመጥ አንድ እድል ይሰጣል። በጥሞና የሰማም ትክክለኛውን መልስ ይመልሳል። ከረፈደ በኋላ ቢሆንም የበሳል ሰው ስራ። በቃ አሁን ነገሮች ግልጽ እየሆኑ ይመስላሉ ትላንት በሌሎች ላይ ነውር ተብለው ሲቆጠሩ የነበሩት ሁሉ አሁን በየተራ እራሳቸው መስመሩን ጀምረውታል። ለትልቅ ሰው ለዐሊም ክብር ይኑረን ብሎ ዳዕዋ ማድረግ "ተምይዕ" ተደርጎ የተቆጠረበት ዘመን ተረስቶ አሁን ተከታታይ ዳዕዋ እየተዘጋጀበት ነው። የሸይኽ ረቢዕን ኪታብ የጀመሩት ለግል አካሄዳቸው ተመችቶ ስላገኙት ነው እንዳላሉን ዛሬ ይሄው እነርሱም "ለግል አላማቸው" ሁኖ ሲያገኙት አንድ ብሎ ይማሩት ጀመር። በሰፈሩበት ቁና ለክቶ መስጠት ነው ይሉሃል አሁን ነው። በሂደት ብዙ የምናየው ነገር ስለሚኖር አብረን እናወጋለን።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida.
Repost from Abu_Oubeida~channel
አብሽሩ ሰለፍያ የማንም የግል ሀብት አይደልም ቶብቶ የገባን ሁሉ ይቀበላል። ሰዎች ስለሆንን አልማጥፋትና አለመሳሳት አይቻልም በላጭነት ግን ስህተትን አውቆ መመለስ ነው። በሰዓቱ እየሄዱበት ያለው መንሀጅ ትክክል መስሏቸው ሲጓዙበት የነበረው መንገድ ዛሬ ትክክል እንዳልነበራችሁ ከገባችሁ ስህተትን አምኖ ለመቀበልና ትክክለኛውን መንገድ ለመቀላቀል ማንገዳገድ አያስፈልግም። በብሩ ቀልጠፍ ብሎ መግባት እንጂ። ቅጥ ያጣ የሆነውን የተብዲዕና የተጅሪሁን የእነ (ለተሞን) መንገድ እና ምስጦፋ አብደሏህ እየመራው ያለውን የተክፊር ጎዳናም ይሁን የተወሰነ ጊዜ አብረው ከተጓዙ በኋላ ቀና ብለው ሲመለከቱት ልክ እንዳልሆነ ሲገባቸው አሁን ስህተቱ የት እና እነ ማን ጋር እንደ ነበረ እየተረዱ ያሉ ይመስላሉ። ቢረፍድም ጥሩ ጅማሮ ነው። አዎ ጎርፍ ሲመጣ ከፊቱ ያገኘውን ሁሉ እየጠረገ ነው የሚወስደው በተለይ በጠባብ ወንዝ የመጣ ከሆነ። ነገር ግን ዝቅ እያለ ሲሆሄድ በሰፊ ወንዞች ላይ ሲበተን መነሻው እየደረቀ ሲሄድ ጩኸቱ ሲደክም፡ አሁን የሚቀረው ቀድሞ የነበረው በበጋም ሆነ በክረምት የማይጠፋው ንጹሁ የወንዝ ውሃ ነው። በቃ ያኔ ጩኸቱም ስለቀነሰ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ ተገላምጦ ለማዳመጥ አንድ እድል ይሰጣል። በጥሞና የሰማም ትክክለኛውን መልስ ይመልሳል። ከረፈደ በኋላ ቢሆንም የበሳል ሰው ስራ። በቃ አሁን ነገሮች ግልጽ እየሆኑ ይመስላሉ ትላንት በሌሎች ላይ ነውር ተብለው ሲቆጠሩ የነበሩት ሁሉ አሁን በየተራ እራሳቸው መስመሩን ጀምረውታል። ለትልቅ ሰው ለዐሊም ክብር ይኑረን ብሎ ዳዕዋ ማድረግ "ተምይዕ" ተደርጎ የተቆጠረበት ዘመን ተረስቶ አሁን ተከታታይ ዳዕዋ እየተዘጋጀበት ነው። የሸይኽ ረቢዕን ኪታብ የጀመሩት ለግል አካሄዳቸው ተመችቶ ስላገኙት ነው እንዳላሉን ዛሬ ይሄው እነርሱም "ለግል አላማቸው" ሁኖ ሲያገኙት አንድ ብሎ ይማሩት ጀመር። በሰፈሩበት ቁና ለክቶ መስጠት ነው ይሉሃል አሁን ነው። በሂደት ብዙ የምናየው ነገር ስለሚኖር አብረን እናወጋለን።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
ሳዳት ሆይ ኡስታዝ ብዬ ልጥራህ!?
ለኔ ፍቀድልኝ!?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አህባሽና ኢኽዋን ሁሌ እየዛተብህ፡
ሱፍያና ተብሊግ ጫት እየቃመብህ፡
ይሙትልን ብለው እየፀለዩብህ፡
ይህን ሁሉ ጫና ጆሮ ዳባ ብለህ፡
በተውሒድ ስብከት ላይ ዛሬም ድረስ አለህ!?
ከማውቃቸው ጀግኖች አንተ ትለያለህ፡
ታዲያ__!!
ሰዎችን በመልካም-ዘውትር እያዘዝከን፡
ወንጀል እንዳንፈፅም እየከለከልከን፡
በአሏህ ውድ ቃል_ሁሌ እያሳመንከን፡
አሏህን ተገዙ አንዱን ጌታ እያልከን፡
ለተውሒድ ለሱና በቻልከው ከለፋህ፡
ባለህ ትርፍ ጊዜ ሽርክን እያጠፋህ፡
ፕሮግራም አውጥተህ ሱናውን ካስፋፋህ፡
በረድ አንበርክከህ ቢዲአን ከገፋህ፡
ዳዒያችን ነህ ብዬ መስክሬ በእውነቱ፡
ኡስታዝ ሳዳት ብልህ ምንድን ነው ጥፋቱ!?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኡስታዝ አትበሉኝ ካልክ እሽ ግድ የለኝም፡
ግን ፈቃድ ይሰጠኝ እኔ አያስችለኝም፡
በስምህ ስጠራህ አዎ ይጨንቀኛል፡
እደነግጣለሁ ፍርሀት ይሰማኛል፡
አንገት እደፋለሁ ይሰቀጥጠኛል፡
ስለዚህ ኡስታዜ ብልህ ይሻለኛል‼️
የኔ ዘመን ክስተት የወጣቱ ወኔ፡
ችግሬን ተረድተህ ፍቀድልኝ ለኔ፡
የተውሒድ ሰባኪው የሱናው ወገኔ፡
#ሳዳት_አንተ_ማለትኮ_!!
ሱናን ለመዘመር ይሉኝታ አይዝህም፡
የአድናቂህ ጫጫታ አያታልልህም፡
የወቃሽ ወቀሳ አላሸነፈህም፡
ጥቅምና ዝና አላማለለህም፡
#ሰለፍይ ወንድም ነህ #ኢኽዋን አይደለህም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አትፈልግም እንጂ ብዙ ብዙ ባልኩህ፡
የውስጤን እምቅ ሀይል ፅፌ በነገርኩህ፡
ግን አንተ አትፈልግም እንድህ አይነት ነገር፡
እንጂማ ጀግና ነህ እውነት ለመናገር፡
በእናትህ ልጅ ጨከንክ ድምፅህን ሰማሁት፡
አሳማኝ ምክርህን በጥልቀት አየሁት፡
ገረመኝ አቋምህ ደነቀኝ ድፍረትህ፡
ለሐቅ ያለህ ቦታ አመለካከትህ፡
ትላንት ሆነ ዛሬ ተውሒድ ነው ስብከትህ‼️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አሏህ በአንተ ሰበብ ብዙ ሰው አቅንቷል፡
ሳይሰለቹ መምከር ላንተም ፅናት ሰጥቷል፡
ብዙዎች መጥተናል ከሱፍያ ገዳም፡
ዛሬ ለሐቅ እንጂ ለሽርክ አንነዳም፡
ይህንን ሁሉ እውነት አንተ ባትረዳም፡
ለዚህ ነው ስምህን የምናነሳሳህ፡
ሰበብ ሆነኸናል አንችልም ልንረሳህ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንጂማ ፈፅሞ ድንበር አላለፍንም፡
ያለ ቦታህ ቁጭ በል በፍፁም አላልንም፡
ነገር ግን ኡስታዝ ነህ እወቀው እውነቱን፡
ተጨባጩ ክስተት መረጃ ነው ፍቱን፡
ከፍ ከፍ አድርገን አናካብድህም፡
እውነት ሀቂቃን ግን እመን ግደለህም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከኢኽዋን መንጋጋ ከጥርሳቸው መሀል፡
አሏህ ሰበብ አርጎ እኔን አውጥተሀል፡
እኔ ኡስታዝ ብልህ ላንተ ምን ያንስሀል⁉️
#በተቻለህ_አቅም፤
ባረፍክበት ሁሉ ሐቅ አስተላልፈሀል፡
#የሱና_ጠበቃ፤
የጥመት መብረቅ ነህ እኛ ወደንሀል፡
#አሏህ_ይጠብቅህ፤
በተውሒድ ስብከትህ ክብር ይገባሀል፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንባ ተናነቀኝ ምክርህን ሰማሁት፡
ሀሳብ ምኞትህን አሻግሬ አየሁት፡
በኔ ቁንፅል ሀሳብ በትንሿ ማንኪያ፡
መስፈርት አሟልተሀል በኡስታዝ መለኪያ፡
በስምህህ አልጠራም ይህን እወቅልኝ፡
እባክህን ሳዳት ይቅርታ አድርግልኝ፡
ኡስታዜ ልበልህ ለኔ ፍቀድልኝ፡
ሀያዕ ይይዘኛል በስምህ ስጠራህ፡
ዑስታዝ ያስብልሀል የሰራኸው ስራህ፡
ይሔ ተማፅኖዬ ላንተ ይድረስልኝ፡
ዑስታዜ ልበልህ ለኔ ፍቀድልኝ⁉️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#በኑረዲን_አል_አረቢ 02/04/1443
---------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
---------------------------------
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
የኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐዶራዎችን ለማግኘት
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/2989
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/2989
