قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
前往频道在 Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
显示更多未指定国家未指定类别
912
订阅者
-224 小时
-127 天
+5130 天
帖子存档
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሀገሬ ወሎ ሲናፍቀኝ እፍፍፍፍ
«እንደዚህ ነው ወሎ»
፧
፧
የዘር ጂኒ-ጃንካ አይደርስም ከደጁ፡
ሁሉንም አክባሪ እንደዚህ ነው የጁ፡
እኔም ወደዛው ነኝ #ወሎዬ ነኝ ልጁ፡
፧
፧
ከሰፊው ሜዳ ላይ ተጫውቶ ገራዶ፡
ከወሎ ከተማ #ደሴ ላይ ተወልዶ፡
ከእንቅልፉ ሲነቃ #ጦሳን ያዬ ማልዶ፡
ፍቅር ነው መለዮው ይኖራል ቀልዶ፡
ፈገግ ይላል ፊቱ #በሙሀባ ነ'ዶ
🎙✍️ በኑረዲን አል-ዓረቢ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from هَذِهِ عَقيدَتُنَا
ይሄ ውብ አፕልኬሽን ተጋበዙልኝ ውድ ቤተሰቦቼ
የፈለጋችሁትን የቁረአን አያ ከነትርጉሙ በዚህ መልኩ በፈለጋችሁት ከለር ኢሜጅ ማውጣት ትችላላችሁ በድምፅም አለው ምቹ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ነው ለወንድማችን አላህ ሰደቀተል ጃሪያ ያርግለት ገብታችሁ አውርዱ
Repost from N/a
ቁርአን ትርጉም.apk20.42 MB
Repost from Abu Hayder Aliy
🔥 ወዳጆቼ ሆይ ከእሳት እንጠንቀቅ!
ውድ የአላህ ባሮች ሆይ! ይህች በዓለም ላይ የምናያት እሳት ምንም እንኳን ኃይለኛ ብትሆንም፣ የጀሀነም እሳት ከዚህ በእጅጉ የከፋች ናት። ስለዚህ ወደ ጀሀነም እሳት ከሚያደርሱ ኃጢአቶችም መጠንቀቅ ይገባል።
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦
﴿فَاتَّقُوا النَّارَ الَّتِي وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ﴾
“ነዳጇ(መቀጣጠያዋ) ሰዎችና ድንጋዮች የሆኑትን እሳት ተጠንቀቁ።”
[አል-በቀራህ፡ 24]
እንዲሁም አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا﴾
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ።”
[አት-ተሕሪም፡ 6]
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«اتَّقُوا النَّارَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ»
“እሳትን ተጠንቀቁ፣ የተምርን ግማሽ በመስጠት ቢሆንም እንኳን።”
[ቡኻሪና ሙስሊም]
اللهم أجرنا من النار، اللهم أجرنا من النار، اللهم أجرنا من النار، وأدخلنا الجنة مع الأبرار، برحمتك يا عزيز يا غفار.
አላህ ሆይ! ከእሳት አድነን፤ ከእሳት አድነን፤ ከእሳት አድነን፤ ከበጎዎች ጋር ጀነት አስገባን። አንተ በምሕረት የተከበርክ እና ብዙ ይቅር ባይ ነህ አደራህን ይቅር በለን ! አሚን።
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
Repost from Ferhan’ M Official Channel
አይናስ እውነት ነው አለ!
==
"ቀደርን የሚቀድም ነገር ቢኖር ኖር አይንናስ ይቀድም ነበር ፣ታጠቡ በተባላችሁ ጊዜ እጠቡ"
ምልክቶቹ
==
~ለብቻ መቀመጥን መምረጥ
~ዝም ብሎ ማልቀስ
~የሰውነት ክብደት መቀነስ
~በትንሽ በትልቁ መቆጣት፣መናደድ
~የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጥፋት
~ዝምምም ማለት
~የሆነ ሰአት መደሰት፣የሆነ ሰአት መቆጣት
===
ፍቱን መፍትሄዎቹ በአላህ ፍቃድ ይለቃል!
===
~ሱረቱል ፋቲሃን እየደጋገሙ መቅራት
~አይናስ ጥቃት ያደረገው ሰው ከታወቀ ሙሉ ሰውነቱ የታጠበበትን ለታማሚው ሰው መስጠትና እንድታጠብ ማድረግ፣
~ሱረቱ አል ፈለቅን ፣አል ናስን ደጋግሞ ደጋግሞ መቅራት ፣ሱረቱ አል ፈለቅ ላይ ስለ ሂስድ የሚያወራውን ደጋግማችሁ ቅሩበት።
~ስለ ቅጣት፣ስለ ጀሀነም የሚያወሩ የቁርአን አንቀፆችን እየመረጡ በደንብ መቅራት በደንብ ተጠቀሙበት።
~ነጭ ሽንኩርት አይወድምና መብላት፣ በተነሳ ጊዜ ደግሞ ነጭ ሽንኩርቱን ድቅቅ አድርጎ አፍንጫ ላይ ማድረግ እንድሸተው ማለት ነው።
~የወይራ ዘይት መቀባት።
t.me/FerhanMufti
t.me/FerhanMufti
Repost from ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
ባለንበት ዘመን ሁሉም ነገር በፍጥነት እየተቀያየረ ነው። አስተውላችሁ ከሆነም አብዛሀኛው ነገር ሁሉም በሚባል ደረጃ ከቴክኖሎጂ ጋር እየተጣመረ ነው። በዚህ ሰአት ቴክኖሎጂን በደንብ የተዋወቁና መጠቀም የሚችሉ ሰዎች እንዲሁም ተቋማት ናቸው ከመንጋው ተለይተው የተሻለ ውጤታማ መሆን የሚችሉት።
እኛም እንደሙስሊም ኡማ ወደኋላ ልንቀር አይገባም። ይህን ዘርፍ ተቀላቅለን
ኢስላማዊ እሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ
ራሳችንን ቤተሠባችንን እንዲሁም ሙስሊሙን ኡማ ልንጠቀምበት ይገባል።
ሙስሊም ቀውይ ነው መፍዘዝና ወደኋላ መቅረት አያምርብንም።
ሀይማኖታዊ እሴቴን ባከበረ መልኩ
የት ልማር ብላችሁ ካሠባችሁ አንድ ተቋም ልጠቁማችሁ
Riseup tech Solution ይባላሉ
ሴቶችን በሴት እንዲሁም ወንዶችን በወንድ መምህራን
🖥 Fullstack(MERN)
💻 Python Programming
🖥 Basic Computer Skill
🎨 Graphic Design
🎬 Video Editing
🇬🇧 English
🇸🇦 Arabic
እና ሌሎች ተፈላጊ ክህሎቶች ያስተምራሉ።
የቴሌግራም ቻናላቸውን @riseuptech ቤተሠብ በመሆን ሙሉ መረጃ እንዲሁም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ጠቃሚ ሀሳቦችን ታገኛላችሁ።
አሁን ላይ ለ10ኛ ዙር ምዝገባ ላይ ስለሆኑ ሳይሞላባችሁ ፈጥናችሁ በመመዝገብ በአካል ወይም በኦላይን በተመቻችሁ አማራጭ በመማር የቴክኖሎጂውን አለም ተቀላቀሉ።
Repost from فوائد أ.د. صالح سندي
🔰 شبهة خطيرة
🎙️ لفضيلة الشيخ صالح سندي حفظه اللّه
رابط المحاضرة كاملة (قواعد في معرفة الشرك) https://youtu.be/YWDcUBSVdrs?si=BGgWf7jqPy8UDdGJ
በዒልም ጉዞ ብዙ አመታትን አሳልፈን ካልተጠቀምን ችግሩ ከኛው ነው። ከደርሱ የተማርናቸውን #ፈዋዒዶች ምንድናቸው ብለን #ሙጧለዓ ካላደረግናቸው የምናገኘው ጥቅም እምብዛም ወይም ምንም ነው የሚሆነው። ከቻልን ርእሱ ላይ በራሳችን Reflect ማድረግ፤ ለሌሎችም ማስተላለፍና ማስተማር።
እዉቀት በተቃሩት ባስተማሩት ቁጥር በልብ #እየሰረጸ ይመጣል ።
يزيد بكثرة الإِنفاقِ مِنه ** وينقصُ إن به كفًّا شَددتا
«ከሱ (ከእውቀት) ነፈቃ ባደረግክ ቁጥር (በሰጠህ ቁጥር) ይጨምራል። እጅህን ሰብስበህ ራስህ ጋር ካቆየሀው ግን እየጎደለ ይሄዳል።
፨ ይህ ግንዛቤን የሚጨምር ነገር ነው። ጧሊበል ዒልም ትኩረት ሊስጠው ይገባል።
حياة العلم مذاكرته
🎙 ሸይኽ ሷሊህ ሲንዲይ ሐፊዘሁሏህ
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«እንቁ ሚስት ሁኝ»
------------------
....በርግጠኝነት መልካም ሚስት የመሆን ህልም አለሽ አይደል «በቃ ፀባይሽን ብቻ አስተካክይ»ሰምተሻል።
«ሚስት መሆንና እስስት መሆን»
«ማራኪ መሆንና አነካኪ መሆን»
«ታዛዥ መሆንና አደንዛዥ መሆን»
«ኸይረኛ መሆንና ነገረኛ መሆን»
➯አብረው የማይሔዱ የትዳር መዳኒትም በሽታወችም ናቸው።
ውበት ቁንጂናሽ ጋር ቢታጀብም በስም፡
ፀባይ ከሌለሽ ግን ትዳርን አይቀምስም፡
ውብ መልክሽ ብቻውን ሁሌ አያቀናጣም፡
ውበት ላይ አትልፊ ቢመጣም ባይመጣም፡
ቁንጂናሽ ቢታይም ከአባት ቤት ቢያሶጣሽ፡
ፀባይሽ ነው ደግሞ መልሶ እሚያመጣሽ፡
ስለዚህ ልንገርሽ ክፉት አትሰብስቢ፡
በንፁህ ልቦና ሰላም ሆነሽ አግቢ፡
«ቀድሜ ያስጠነቀቅኩሽ መልካም ሚስት በወንዶች ዘንድ ከመልከኛ በላይ ስለምትፈለግ ነው...ለምን መሰለሽ አብዛኞቹ ቆንጆ ነን የሚሉት ትዳር መያዝ እየተሳናቸው ፀባይ ያላቸው ግን ሸበላ ወንድ ጋር አስደናቂ ህይወት የሚመሩት...ሚስጥሩ ትዳር ፀባይ እንጂ መልክ ስላልሆነ ነው ገባሽ!?
➯መልካም ሴት የወንድ ልጅ ስኬት ነች።
......መልካም ሚስት የደስታ መሠረት በቤት ውስጥ የሀሴት ቁልፍ፣ የስኬት አጋር እና ባለቤቷን የምትረዳ እና የበፈገግታ የምትቀበል ሰው ተደርጋ ትቆጠራለች።
A good wife is considered the foundation of happiness, the key to happiness in the home, a partner in success, and someone who supports and welcomes her husband with a smile.
➯ምርጥ ሚስት ስትታይ የምታስደስት፣ ፈገግታ ከፊቷ የማይጠፋ ፣ቅንነት የሞላባት፣ሁሉን በእኩል የምታይና የምታከብር....ግና ባሏን የምታነግስ ልቧ ለባሏ ብቻየተከፈተ ማንም የማይገባበትንፁህ አፍቃሪ ነች።
መልካም ሚስት በፈቃደኝነት ያለምንም ከልካይ በደስታ ባሏን የምትንከባከብ፣ባሏ ባዘዛት ጊዜም በቅንነት የምትታዘዝ ሴት ነች።
ጥሩ ሚስት ባል በሌለ ጊዜ ንብረትና ክብሯን ለባሏ የምትጠብቅና የምታስጠብቅ ውብ ሴት ነች።
እንቁ ሚስት ራሷን፣ባሏንና ንብረቷን ለማንም አሉባልታ አሳልፋ የማትሰጥ የባሏ ጠበቃ እና በድክመቱ ገብታ ብርታት የምትሆን የባሏ ቀኝ እጅ ነች።
እንቁና መልካም ሚስት ማለት ከባሏ ውጭ የማታመነታ እና አይኗም ልቧም የማያማትር ግና ማንም ወንድ ሁሉ በጥንቁቅነቷ በጥብቅነቷ በሙያዋና ለትዳሯ ባላት ክብር የሚመኛት ውብና ቆንጆ ሴት ነች።
እንቁ ሚስት ውድ ጌጥ ነች ቤቷን አሰማምራ በንፅህና የምትይዝ በውበቷና በፍቅሯ ባሏን የምትማርክ ምድራዊ የሰላም ሰገነት ነች።
እንቁ ሚስት➯ ውኃህ ናት፦ ስሜትህን ጥማትህን ታረካለች።
ቆንጆ ሚስት➯ፀኃይህ ነች ሲበርድህ ታሞቅኃለች።
ትሁት ሚስት ➯ ብርኃንህ ነች ጎጆህን ታደምቃለች።
መልካም ሚስት ➯አይንህ ብሌንህ ነች ትመራሃለች ያላየኸውን ታሳይሃለች።
አፍቃሪ ሚስት➯ መስታውትህ ነች አይንህን ባይንህ ታሳይሃለች።
.....በዚህ ክስተት በሚንጠው ዘመን የመከራ ወጀብ በቀኝ በግራ ሲያዋክብህ በቤትህ ውስጥ የደስታ ቁልፍ መልካም ሚስት የስኬት አጋር ካለህ አንተ የዱንያን የመከራ በሀር መቅዘፍ የምትችል ልዩ ሽልማት ያለህ ወንድ ነህ።
.....#ወንድ_ሆይ_ስማ ምንም ባለፀጋ ብትሆን ሞልቶህ ብትተረፈረፍ ያለ ሚስቴ ጎዶሎ ነህና ማንን እንደት በምን መምረጥ እንዳለብህ አስበህ አሁኑ ሙሉ ሰው ሁን።
....አቡ-ፋሩቅ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
لا تجعل عمرك يمر بلا فائدة
تعلم ما ينفعك في دينك ودنياك
تعلم شيئا جديدًا
عليك بالخطوة الأولى وبعدها ستجد الأمر سهلا
بتوفيق الله.
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቢድዐን መናቅ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል
~
በስራ ከተማ ደቡባዊ ዒራቅ ውስጥ የምትገኝ ጥንታዊ ከተማ ነች። በተለያዩ ዘመናት አደገኛ አንጃዎች አልፎ አልፎ ቢያቆጠቁጡባትም እንደ ጥቅል ግን ከሶሐቦች ጀምሮ ታላላቅ ዑለማኦች የወጡባት የሱና ከተማ ነበረች። ዛሬስ? ዛሬ ላይ በስራ ውስጥ ሱኒዮች አናሳ ናቸው። ከጠቅላላው ሕዝብ ከ9% እስከ 15% አካባቢ ብቻ ይገመታሉ። ሺዐዎች ዛሬ በስራ ላይ ብዙሃን ናቸው። በርግጥ አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት እስከ 2003 ድረስ የሱኒዮች ቁጥር 40% አካባቢ ነበር። በጉልበት ስላፈናቀሏቸው ነው ተመናምነው ዛሬ የደረሱበት ዝቅተኛ ቁጥር የደረሱት። ከኋላ የመጣው ሺዐ ዛሬ በስራ ላይ ከ86% በላይ ይሆናል።
ወደ ሃገራችን ስመጣ የሃገራችን ሙስሊም የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሐቦችን የሚወድና የሚያከብር ቢሆንም የሺዐ ተከታዮች ግን ከውስጡ አንዳንድ ማለት ጀምረዋል። ስራ መስራት ያለብን ዛሬ ነው። ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም። በዚህ ጉዳይ ላይ መስራት እንደ ተቋም መጅሊስን ይመለከት ነበር። እሱ ቢቀር ዱዓቶች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባ ነበር። ሁሉም ግን ፀጥ ረጭ ብሏል። ይሄ በየሁዳው ዐብደላህ ኢብኑ ሰበእየተጠነሰሰ ቡድን ስር ሳይሰድ በፊት በጊዜ ስራ ልንሰራ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🫀 ልብ ልክ ሁሉም ነገር በአላህ ቁጥጥር ስር መሆኑን ስትረዳ ትረጋጋለች።አንተ የምትችለውን አድርግ፤ የተቀረውን ለአላህ ተወው። ምክንያቱም የምትፈራው ነገር ከአላህ ዕውቀት ውጭ አይደለም፤ የምትጠብቀውም ነገር ከአላህ ዕውቀት ውጭ አይደለም። የዛሬ ጭንቀትህ የነገ መጨረሻህን አይወስንም። የዛሬ መዘግየት የአላህ ውሳኔ እንደተረሳህ አያሳይም። አንድ በር ሲዘጋ ሁሉም በሮች ተዘግተዋል ማለት አይደለም። 🌿 ኢብኑ አባስ رضي الله عنهما እንዲህ ይላሉ፦ «وَاعْلَمْ أَنَّ مَا أَخْطَأَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُصِيبَكَ، وَمَا أَصَابَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُخْطِئَكَ.» “ያመለጠህ ነገር ሊደርስብህ አልተፃፈም፤ የደረሰብህም ነገር ሊያመልጥህ አልተፃፈም።” ይህን በልብህ በጥልቀት ስትረዳ፣ ሰዎች ከአንተ ሲርቁ አትፈራም፤ አንድ ነገር ሲዘገይ አትፈርስም፤ የፈለግኸው ነገር ሳይሆን ሲቀርም አላህ እንደሚያውቅ ታምናለህ። ⚠️ ኡመር ኢብኑል-ኸጧብ رضي الله عنه እንዲህ ብለዋል፦ «لَوْ كُشِفَ الْغِطَاءُ مَا ازْدَدْتُ يَقِينًا.» “መጋረጃው ቢነሳ እንኳ ያለኝ እርግጠኝነት አይጨምርም። እርግጠኝነት ማለት ሁሉንም ነገር አስቀድመህ ማወቅ አይደለም፤ ሁሉንም ነገር የሚያውቀውን አላህን ማመን ነው። 🫀 ●ስለዚህ የልብህን ጭንቀት አላህ ፊት አውጣ። ●ሰዎች ላይ ያልተቻለውን ከአላህ ጠይቅ። ●የሚያስፈራህን ነገር ለእርሱ አስረክብ። ●የምትፈልገውን በዱዓ ጠይቅ፤ ከዚያም “አላህ የሚመርጥልኝ ከእኔ ለራሴ ከምመርጠው ይሻላል” ብለህ ልብህን አሳርፍ። ⚠️ ምናልባት የምትለምነው ነገር ይዘገይ ይሆናል፤ ግን አላህ አልረሳህም። ⚠️ ምናልባት የምትወደው ነገር ከአንተ ይርቅ ይሆናል፤ ግን አላህ እያየህ ነው። ⚠️ ምናልባት የምትጠላው ነገር በሕይወትህ ይመጣ ይሆናል፤ ግን አንተ የማታየውን ጥበብ አላህ ያያል። «وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ، وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ، وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ» 🌿 “ምናልባት እናንተ የሆነን ነገርን ትጠላላችሁ እርሱ ግን ለእናንተ ኸይር ይሆናል፤ ምናልባትም የሆነን ነገርን ትወዱታላችሁ እርሱ ግን ለእናንተ ሸር ይሆናል፤ አላህ ያውቃል፣ እናንተ ግን አታውቁም።” 🥀 ስለዚህ ልብህ ይረጋ። ● አላህ ሁሌም ካንተ ጋር ነው። ● አላህ ሁሉንም ያውቃል። ● አላህ ሁሉንም ያያል። ● አላህ ሁሉንም ይሰማል። ● አላህ ያዘጋጀልህ ነገር አይሳሳትም። የአላህ ውሳኔ ከአንተ ፍላጎት ጋር ባይመሳሰልም፣ የአላህ ምርጫ ሁሌም ከአንተ ዕውቀት ይበልጣል። 🫀 ልብ የሚረጋው የሚፈልገውን ሁሉ ሲያገኝ አይደለም፤ የሚያገኘውም ሆነ የሚያጣው ሁሉ በአላህ ዕውቀትና ጥበብ ስር መሆኑን ሲያምን ብቻ ነውና ጉዳዮችህን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋ። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለፈገግታ
~
ከወሎ ወደ አዲስ አበባ የመጣች ሙስሊም ናት። ክርስቲያን ዘመዶቿ ልጃቸው ትምህርት ጨርሶ ተመርቆ ኖሮ ድል ያለ ድግስ አዘጋጅተዋል። እቤታቸው እንደገባች ግድግዳ ላይ የተሰቀለ "የእየሱስን" ምስል ተመለከተች። "ይሄ ነው የተመረቀው ልጃችሁ?" ብላ ጠየቀቻቸው። እሷ እንዴት ብላ የ"ፈጣሪያቸውን" ምስል ይሰቅላሉ ብላ ታስብ?
እውነተኛ ገጠመኝ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
⓵:- ፌስቡክ 🗂
👇👇👇 ተቀላቀሉ
https://www.facebook.com/abw.mran.alathry
m/abw.mran.alathry
⓶:- ቴሌግራም🗂 👇
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy
⓷:- የ አረበኛ ደርሶች ትምርት መስጫ👇
https://t.me/Al_arebiyeh
⓸:- የአረበኛ ትምርቶች ኦዲዮ ማስቀመጫ👇
https://t.me/Adurusu_alarebiyeh
⓹ :-በአህሉል አሰር የሚሰጡ ደርሶች ኦዲዮ ማስቀመጫ👇
https://t.me/Abu_im_ran
⓺:- ስለ ኡዙር ቢል ጀህል መረጃ ማስቀመጫ👇
https://t.me/Al_ouzru_biljehl
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from درر العلامة المحدث-ربيع بن هادي المدخلي
ندوة علمية بعنوان أصول أهل السنة في العقيدة
ضيوف الندوةفضيلة الشيخ العلامة المحدث ربيع بن هادي المدخلي-رحمه الله- فضيلة الشيخ العلامة علي بن ناصر الفقيهي-رحمه الله- فضيلة الشيخ العلامة صالح بن سعد السحيمي-حفظه الله-
المقدمفضيلة الشيخ الدكتور عبد الرزاق البدر حفظه الله تعالى https://t.me/DrRabeeM/3127 الدال على الخير كفاعله
Repost from Abu useymin (Mohammed Ali)
✅ አብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ ዐ) እንዲህ ብለዋል፡-
አላህ የወሰነውን ነገር “ባያደርገው ኖሮ” ብዬ ከምናገር ይልቅ የሚነድ ፍም እሳትን እስኪቀዘቅዝ ድረስ ነክሼ ብይዝ እመርጣለሁ።
📚الزهد لأبي داودt.me/MohamedAliEdris
Repost from Abu Hayder Aliy
اللَّهُمَّ أَصْلِحْ قُلُوبَنَا، وَاسْتُرْ عُيُوبَنَا، وَاغْفِرْ ذُنُوبَنَا، وَأَحْسِنْ خَاتِمَتَنَا، يَا رَبَّ الْعَالَمِينَ.
አላህ ሆይ! ልቦቻችንን አስተካክልልን፣ ጉድለቶቻችንን ሸፍንልን፣ ኃጢአቶቻችንን ማርልን፣ መጨረሻችንንም አሳምርልን መልካም አድርግልን! 🤲
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
