ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

前往频道在 Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

显示更多
未指定国家未指定类别
902
订阅者
-424 小时
-167 天
+4030 天
帖子存档
የጀርህ እና የተእድል የእውቀት መሳአላ ኢጅቲሀድ ከሚገባባቸው የዕውቀት ጉዳዮች መካከል ነው። ሰዎች አንዱ ሌላውን የግድ በአንድ የተወሰነ አቋም እንዲከተል የሚያስገድዱበት ጉዳይ አይደለም። እንዲሁም በሙስሊሞች መካከል ጥላቻና መከፋፈል ምክንያት መሆን የለበትም። ጀርህና ተዕዲል ከሐዲስ የኢልም ዘርፎች አንዱ ሲሆን፣ የራሱ መርሆችና መመሪያዎች አሉት። ይህ የሚመለከተውም የዕውቀት፣ የፍትሕ፣ የአላህ ፍራቻና የሰዎችን ሁኔታ የመረዳት ብቃት ያላቸው ብቁ ዑለማዎችን ነው። በዚህ ዘርፍ ዑለማዎች በአንዳንድ ሰዎች ላይ ወይም በአንዳንድ ፍርዶች ሊለያዩ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ማስረጃዎችን በመመርመር፣ የዑለማዎችን ንግግር በመረዳት፣ እንዲሁም ጥቅምና ጉዳትን በመመዘን ላይ የተመሠረተ ነው። ስለዚህ የዕውቀት ሰዎች እንደገለጹት፦ የጀርህና ተዕዲል ጉዳዮች ሁሉ በአንድ ደረጃ አይደሉም። ከእነርሱ መካከል ግልጽና የማይከራከርበት ጉዳይ አለ፤ እንዲሁም የምርመራና የኢጅቲሃድ ቦታ ያለው ጉዳይ አለ። በእንደዚህ ያሉ የኢጅቲሃድ ጉዳዮች ላይ ልዩነት በብቁ ዑለማዎች መካከል ከሆነና በማስረጃ የተመሠረተ ከሆነ አይነቀፍም። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ «ከኢጅቲሃድ ጉዳዮች ውስጥ አንድ ሰው ከዑለማዎች አንዱን አቋም ተከትሎ ቢሰራበት አይነቀፍም።» (መጅሙዑል ፈታዋ) እንዲሁም እንዲህ ብለዋል፦ «በኢጅቲሃድ ጉዳዮች ላይ ሰዎችን አንድን የተወሰነ የዑለማ አቋም እንዲከተሉ ማስገደድ ለማንም አይፈቀድለትም።» ስለዚህ በእነዚህ ጉዳዮች ወደ የዕውቀት ባለቤቶች መመለስ ነው ያለብን፤ ወደ ህዝብ ወይም ወደ ግለሰብ ስሜት አይደለም። አንድ ሰው የራሱን አስተያየት ወይም የሸይኹን አቋም ለሁሉም ሰው የሚገደድበት መለኪያ ማድረግ የለበትም፤ ምክንያቱም ማስገደድ የሚሆነው ግልጽ ማስረጃና ትክክለኛ የሸሪዓ እውቀት ሲኖር ብቻ ነው። ኢማሙ ዘሀቢ (ረሒመሁላህ) ከዑለማዎች አንዱ በሌላው ላይ የሚናገረውን ሲገልጹ፦ «የሁለት እኩያ የሆኑ ኡለማዎች ንግግር እርስ በእርሳቸው ላይ የሚነገረው ታጥፎ መተው አለበት።» (ሚዛኑል ኢዕቲዳል) ምክንያቱም በውስጡ የኢጅቲሃድ ልዩነት፣ የአመለካከት ልዩነት ወይም የሰው ልጅ ድክመት ሊገባበት ይችላል። ስለዚህ ትክክለኛው አቋም፦ የጀርህና ተዕዲልን ዕውቀት ማክበር፣ የዑለማዎችን ደረጃ ማወቅ፣ ወደ እነርሱም መመለስ ነው። ነገር ግን የኢጅቲሃድ ጉዳዮችን ለመለያየትና ለጥላቻ መንገድ ማድረግ አይገባም። ጀርህና ተዕዲል ክቡር የሆነ የዕውቀት ዘርፍ ነው፤ ነገር ግን ሰዎችን ለመቆጣጠር ወይም በእያንዳንዱ የኢጅቲሃድ ጉዳይ ላይ ለማስገደድ የሚጠቀሙበት መሣሪያ አይደለም። በዕውቀት፣ በፍትሕና በኢንሳፍ መመዘን አለበት። አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ﴾ “የአንድ ሕዝብ ጥላቻ ፍትሕን እንዳትተዉ አያድርጋችሁ፤ ፍትሕዊ ሁኑ፤ ይህ ለተቅዋ በጣም የቀረበ ነው።” (አል-ማኢዳህ፦ 8) https://t.me/A2mnt

مسألة الجرح والتعديل من المسائل العلمية التي يدخلها الاجتهاد، وليست من المسائل التي يُلزم فيها الناس بعضُهم بعضًا باتباع قولٍ معيّن، ولا يجوز أن تكون سببًا للتنازع والتباغض بين أهل الإسلام. فالجرح والتعديل بابٌ من أبواب علوم الحديث، وله قواعده وأصوله، وهو من اختصاص العلماء المتأهلين الذين جمعوا بين العلم والعدل والورع ومعرفة أحوال الرجال. وقد يختلف العلماء في بعض الأشخاص أو في بعض الأحكام؛ لأن هذا الباب مبنيٌّ على النظر والاجتهاد في ثبوت الأسباب، وفي فهم كلام العلماء، وفي تقدير المصالح والمفاسد. ولهذا قال أهل العلم: إن مسائل الجرح والتعديل ليست كلها على درجة واحدة؛ فمنها ما يكون ظاهرًا قطعيًّا لا يختلف فيه أهل العلم، ومنها ما يكون محلَّ نظرٍ واجتهاد، فيختلف فيه العلماء، ولا يُنكر في مسائل الاجتهاد ما دام الخلاف صادرًا من أهله وبأدلته. قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله: «ومسائل الاجتهاد من عمل فيها بقول بعض العلماء لم يُنكر عليه» (مجموع الفتاوى). وقال رحمه الله: «ليس لأحد أن يلزم الناس باتباع قول عالمٍ بعينه في مسائل الاجتهاد» (مجموع الفتاوى). فالواجب أن يُرجع في هذه المسائل إلى أهل العلم، لا إلى العوام، وألا يجعل الإنسان رأيه أو رأي شيخه ميزانًا يُلزم به جميع الناس، لأن الإلزام لا يكون إلا بدليل واضح، ومعرفة صحيحة بأحكام الشرع. وقد قال الإمام الذهبي رحمه الله في بيان حال كلام العلماء بعضهم في بعض: «كلام الأقران بعضهم في بعض يُطوى ولا يُروى» (ميزان الاعتدال)، لما قد يدخل فيه من اجتهاد أو اختلاف نظر. فالموقف الصحيح هو: احترام علم الجرح والتعديل، ومعرفة قدر العلماء، والرجوع إليهم، مع حفظ الأخوة، وعدم تحويل مسائل الاجتهاد إلى أبواب للفرقة والخصومات. فالجرح والتعديل علمٌ معتبر، لكنه ليس بابًا للتسلط على الناس، ولا وسيلة لإلزامهم في كل مسألة اجتهادية، وإنما يُعامل بميزان العلم والعدل والإنصاف، كما قال الله تعالى: ﴿وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ﴾ [المائدة: 8] https://t.me/A2mnt

አኺል ከሪም! ~ ሰለፎች ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ብርቱዎች ነበሩ። ይህ ማለት ባልተረጋገጠ ወሬ ሰዎችን ይከሱ ነበር፣ በእውር ድንብር ተብዲዕ ያደርጉ ነበር ማለት አይደለም። ሰዎችን ከሱና ለማስወጣት አትቸኩል ስትባል አይክፋህ። የዚህ መልእክቱ ለቢድዐም ለሙብቱዲዕም ጥብቅና እንቁም የሚል አይደለም። እንደዚያ አድርገህ ብትረዳ ራስህን ነው የምትጎዳው። ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ጠንካራ መሆን ይገባል። ለዚህም የሰለፎችን ብርቱ ማሰጠንቀቂያዎች ማሰራጨት ሁነኛ አማራጭ ነው። ይህንን ስናደርግ ግን ሌላ መልክ ያለው ቡድንተኝነት፣ ጥላቻን መሰረት ያደረገ ፍረጃና ዘመቻ፣ የሰዎችን ንግግር ሆነ ብሎ ገልብጦ እየተረጎሙ ወከባ ማብዛት አይገባም። ይሄ ከሰለፎች አካሄድ ያፈነገጠ ግና በሰለፎች ስም እየተፈፀመ ያለ የስነ ምግባር ዝቅጠት ነው። የራሳችንን የረከሰ ስነ ምግባር ወደ ሰለፎች ከማስጠጋት መቆጠብ አለብን። ከአጥፊዎች ጥፋት ባልተናነሰ የኛ ባህሪ ራሱ ሰዎችን ከሱና እያስበረገገ ነው። መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን ለማረም ሌላ ፅንፍ መርገጥ አያስፈልግም። በሌላ ጫፍ ለትክክለኛው ኢስላማዊ ዐቂዳ ዋጋ የማይሰጥ፣ ሺርክና ቢድዐ የማይጎረብጠው፣ የቢድዐ አጫፋሪዎች መነካት ምቾት የሚነሳው አካል እንዳለ ይታወቃል። ይህንን ብኩን አካሄድ የምናኮላሸው ራሳችን ጤነኛ አካሄድ ሲኖረን ነው። በዙሪያው ካለ ህዝብ የተኳረፈ፣ እርስ በርስ በመዘራጠጥ የሚታወቅ፣ መስለሐና መፍሰዳ የማይገባው፣ አልፎ አልፎ ሌሎችን ለመክሰስ መረማመጃ ለማድረግ ያክል ብቻ ከሚያነሳቸው የቢድዐ አንጃዎች በበለጠ የተሻለ ለሚቀርቡት የከፋ ጥላቻ ያረገዘ፣ አብይ መታወቂያው ሃሰተኛ ክስና ፍርደ ገምድል ውንጀላ የሆነ ስብስብ የክፋት አካሄዱን በሰለፎች ስም ሲያቀርብ ያሳፍራል። እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን ጣት ከምንሰነዝርባቸው አካላት ባልተናነሰ ወይም በባሰ ተበክለናል። ራሳችንን አንዘንጋ። መልእክቱ ለራሴም ጭምር ነው። በመጨረሻም አደራ! ያልተፃፈ እንዳታነብ! ራስህን ነው የምትጎዳው። = የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/Abulabas1444 http://t.me/Abulabas1444