قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
前往频道在 Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
显示更多未指定国家未指定类别
908
订阅者
-324 小时
-157 天
+4830 天
帖子存档
Repost from Hussein Ali (Durus & Fewa'id)
የድሮ ስርዓት ናፋቂው የከላላ ከተማ ከንቲባው ህገ ወጥ እስርና ወከባ!
የከላላ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ ጥላሁን የክርስትና እምነት ተከታይ ናቸው። ከላላ በአብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ያለበት ከተማ ቢሆንም የህዝበ ክርስቲያኑ መብት ተከብሮ የሚኖርበት አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ በተቃራኒው በሙስሊሙ ማህበረሰብ የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የኢስላማዊ ዳዕዋ ይዘትን ጭምር ካልወሰንኩና ለምን ዳዕዋ ታደርጋለህ በሚል ከንቲባው የመጅሊስ አባል የሆነውን ወንድም ኢዘዲን ሻፊን አስሮና አስፈራርቶ ከለቀቀው በኋላ በድጋሜ ሌሎት 5:00 አፍነው ለመውሰድና ለመግደል ሙከራ ቢያደርጉም አልሳካላቸው ሲል የከለላ ከተማ መጅሊስ ም/ኃላፊ የሆነውን ሸህ ሙሀባ ሰኢድን አስረውት የወገኛሉ።
የከተማው ከንቲባ ይህንን ኢህገመንግስታዊ፣ አሳፋሪና ህዝብን የሚያቃቅር ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ሸህ ሙሀባ ሰኢድን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቁት እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትም በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት አመራር ጋር በመነጋገር መሠል ድርጊቶችን እንዲቃወምና የወንድማችንን መብትና የመጅሊስ ክብር እንዲያስጠብቅ እንጠይቃለን።
ከከላላ ሙስሊሞች
Repost from Daru Sunnah || ዳሩ ሱን'ናህ
ስለ ጀርህ ወተዕዲል ኡለሞች ምን አሉ‼️
=======================
[ ለዚህ ነገር አቅሜ ስለማይፈቅድ የኡለሞችን ንግግር ብቻ ነው የማስቀምጠው]
በዚህ ፅሁፍ ኢንሻ አላህ ስለ ጀርህ ወተዕዲል ኡለሞች ምን እንዳሉ እያንዳንዱን እያነሳሁ ለማሳየት እሞክራለሁ። በአላህ ፍቃድ!። እኔ እንደ አንዳንድ ሰዎች ለስሜቴ የገጠመልኝን ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኡለሞች ያሉትን ለማንሳት ሙከራ አድርጌያለሁ። የኡለሞቹን ንግግር ከታች ባስቀመጥኩት የ"YouTube" ሊንክ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ። ቪዲዮን ለመላክ ሞክሬ ነበር ነገር ግን እምቢ ስላለኝ ትቼው በሊንክ አስቀምጬዋለሁ። አረቢኛውን እየፈጠንኩ ስለፃፍኩት አንዳንድ የቃላት ስህተት ሊኖረው ይችላልና አትውቀሱኝ። ይሄው እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፦
١. علم الجرح والتعديل العلامة صالح بن عبدالله الفوزان حفظه الله
التأصيل العلمي عند السلف الصالح محاضرة
https://youtu.be/zml7VmSdYZ8
٢. من يتكلمون في الدعاة بحجة الجرح والتعديل- العلامة صالح الفوزان حفظه الله
https://youtu.be/aqarKB25HlE
٣. قاعدة الجرح والتعديل- العلامة صالح الفوزان حفظه الله في شرح كتاب تفسير القران الكريم
https://youtu.be/MRylYH6Qh6E
٤. حكم الجرح والتعديل في هذا العصر للشيخ ابن عثيمين رحمه الله
هل سنة الجرح والتعديل ماتت؟ وما حكم الرد على المخالف؟
https://youtu.be/v0SS5PQqHIg
٥. موقفنا من إختلاف العلماء في الجرح والتعديل؟؟
"إذا اختلف بعض من الدعاة في تجريح شخص أو تعديله؛ يعني: بعض الدعاة عدل والبعض الآخر جرح، هل يلزم من ذالك تجريح من عدل؟
جواب الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله
https://youtu.be/HjvrEDC7FnI
٦. وصية الشيخ الألباني لطلبة العلم أن لا يضيعو أوقاتهم في نقد بعضهم بعضا فلان كذا وفلان كذا !!!
كلام قمة الروعة رحمك الله يا شيخنا الألباني وجمعنا بك في الفردوس الأعلى
https://youtu.be/yyocixKbAfw
٧. غلو بعض الطلاب والشباب في الجرح والتعديل وتحذير - للشيخ الوالد فلاح بن إسماعيل مندكار - رحمه الله تعالى
https://youtu.be/PQIneXOyqXE
٨. مسألة مهمة في الجرح والتعديل- الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله تعالى
https://youtu.be/KwPQHHlEtGg
٩. سؤال: إذا اختلف العلماء في جرح شخص أو تعديله ماذا يفعل المقلدون؟
جواب الشيخ عبدالمحسن العباد حفظه الله
https://youtu.be/7fpKz3QNfbo
١٠. بيان ضوابط الجرح والتعديل ودفاع عن العلامة محمد بن هادي للشيخ محمد بازمول حفظهم الله
https://youtu.be/r7GMY1e3zN0
١١. هل صحيح أن علم الجرح والتعديل انتهى وأن هذا الباب قفل؟
الشيخ أحمد بازمول حفظه الله
https://youtu.be/trRHE12RcEw
١٢. نصيحة مهمة حول الجرح والتعديل و ردود السلفيين بعضهم لبعض!
الشيخ صالح السحيمي حفظه الله تعالى
https://youtu.be/tOkmCSswPNs
١٣. فتاوى الوالد الشيخ عبدالمحسن العباد حفظه الله تعالى عن الجرح والتعديل
https://youtu.be/yeSNHJ4rr50
١٤. حكم الجرح والتعديل للدعاة وطلبة العلم عن طريق وسائل التواصل الإجتماعي؟
لفضيلة الشيخ عبدالعزيز آل الشيخ حفظه الله
https://youtu.be/ytIEENpyhwo
١٥. حكم التقليد في الجرح والتعديل - الشيخ عبدالعزيز الريس حفظه الله
https://youtu.be/15cqC3dXXkE
١٦. منهج الجرح والتعديل للشيخ مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله تعالى
https://youtu.be/Yvfe_zfPmqs
١٧. سؤال مهم جدا عن الجرح والتعديل- العلامة عبدالعزيز بن باز رحمه الله تعالى
https://youtu.be/vursG6tSpXY
١٨. فتنة الجرح والتجريح
للرد على من صار شغلهم الشاغل الطعن في الدعاة والعلماء واصطياد زلاتهم -العلامة المحدث محمد ناصر الدين الألباني -رحمه الله تعالى
https://youtu.be/k9j4I8MULcU
١٩. إذا كان الرد من باب الجرح والتعديل فهو واجب شرعي - الشيخ العلامة محمد امان الجامي
https://youtu.be/wguAUPfkDjQ
٢٠. حقيقه الجرح والتعديل لفضيلة الشيخ المحدث صالح اللحيدان حفظه الله تعالى
https://youtu.be/l8dyoqKWlDw
٢١. شهر بن حوشب وبيان حاله علماء الجرح والتعديل- للعلامة محمد بن آدم الإتيوبي رحمه الله تعالى
https://youtu.be/fAXaFCer7p4
٢٢. كلام مهم جدا.....الفرق بين الجرح والتعديل والغيبة
الشيخ محمد سعيد رسلان حفظه الله تعالى
https://youtu.be/t9wnGgyxb9w
الدرس تعارض الجرح والتعديل
https://youtu.be/c_PVcUD373E
~~~~~
ይህን ፅሁፍ "ለዛ ሰፈር ሰዎች አድርሱ" ምናምን አልልም። ብቻ ዋናው የኡለሞችን ሀሳብ መሠረት እያደረግን በዛ ብንጓዝ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። ወሏሁ አእለም!
ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ
https://t.me/Daru_Sunnah
https://t.me/Daru_Sunnah
Repost from قناة الشيخ عبدالمحسن العباد
🔊 الدروس الصوتية 🔊
▪️دروس الحديث
1. شرح رسالة أبي داود إلى أهل مكة في وصف سننه
2. شرح بلوغ المرام
3. شرح كتاب الصيام من اللؤلؤ والمرجان فيما اتفق عليه الشيخان
4. شرح الأربعين النووية وتتمة ابن رجب
5. شرح ألفية السيوطي في علم الحديث
6. شرح عمدة الأحكام من كلام خير الأنام
7. شرح سنن ابن ماجه
8. شرح سنن الترمذي
9. شرح سنن النسائي
10. شرح سنن أبي داود
11. شرح صحيح مسلم
12. شرح صحيح البخاري (الجديد 1431هـ-1441هـ):
13. شرح موطأ الإمام مالك
▪️دروس الفقه
14. شرح شروط الصلاة وأركانها وواجباتها
15. الإختيارات الفقهية من فتاوى الشيخ عبد العزيز بن باز:
-أ- كتاب الزكاة -ب- كتاب الصيام
16. شرح كتاب آداب المشي إلى الصلاة
17. تبصير الناسك بأحكام المناسك - عام 1429هـ
▪️دروس العقيدة
18. شرح الصدور بتحريم رفع القبور
19. شرح مقدمة رسالة القيرواني
20. شرح كتاب تطهير الاعتقاد من أدران الإلحاد
▪️محاضرات عامة
21. المحاضرات العلمية والتوجيهات المنهجية
ا〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
إذا واجهتك أي صعوبات في الصوتيات تفضل بزيارة هذه الصفحة: اضغط هنا
ا〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
Repost from ፈዋኢድ
አህባሾች ኢብኑ ተይሚያን ከሚከሱበት ነጥብ አንዱ ጀሀነም(ጀነት አላልኩም) ትጠፋለች ብሏል ሚለው ነው።
ኢብኑ ተይሚያ በፈታዋቸውና በሌሎችም ኪታቦቻቸው ጀሀነም እንደማትጠፋ በግልፅ ያስቀምጣሉ። አህባሾቹ ክሳቸውን ከሚወስዱባቸው ኪታብ መካከል ቀጣይ ከታች ያለችው ሪሳላ ነች።
ሚገርመው በኪታቡ ኢብኑ ተይሚያ ጀሀነም ትጠፋለች ሚለው ቀውልን ነው ረድ ያደረጉበት። በመፅሀፋ በተወሰነው ክፍል የዚህን ቀውል ባለቤቶች መረጃ ስለዘረዘሩ ብቻ የእሳቸውም ቀውል ነው ብለው እንደመረጃ ያመጣሉ። (በምን እንክሰሳቸው ነው እንግዲህ 😆😆)
ከሰለፎችስ ይህ ቀውል አልተገኘም? ቢድዐ ነው? ሚለውን መመልከት ይቻላል።
በተጨማሪ መስዐላው በሸርህ ጠሀዊያ በጥሩ ሁኔታ ተብራርቷል።
እንድታነቧት እጋብዛለው። ከስር ዳውንሎድ ማድረግ ትችላላችሁ
https://t.me/fewaidabdurazaq/10
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አዎ እንቁጣጣሽ በዓላችን አይደለም!
~
እንደ ሙስሊም እንቁጣጣሽን ማክበር አይፈቀድም። ይሄ አጉል ማክረር ጋር የሚገናኝ ነገር አይደለም። አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ግን ማክበር ያለብንንና የሌለብንን በዓላት ሊመርጡልን ይፈልጋሉ። አክራሪነት ማለት በሌሎች እምነት ውስጥ ዘው ብሎ በመግባት የእምነታችሁን ህግጋት ካላሰመርንላችሁ፣ እኛን ካልመሰላችሁ ማለት ነው።
አንዳንዶቹ ሳዑዲ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ያከበረችበት ነው እያሉ ፎቶ ይቀበላሉ። ማስረጃ ማቅረባቸው ነው በነሱ ቤት። ሸሪዐዊ ህግጋትን የምንወስደው ከቁርኣንና ሐዲሥ እንጂ ከሳዑዲም ይሁን ከሌላ ሃገር አሰራር፣ ወግና ልማድ አይደለም። የመውሊድም ጊዜ በያመቱ ተመሳሳይ ከሸረሪት ድር የደከሙ "ማስረጃዎችን" የሚለቃቅሙ አሉ። የሆነ ጊዜ መካ ካለው አብራጀ ሳ0ህ ላይ የረቢዕን መግባት ተከትሎ መብራት ለቀዋል መውሊድን ማክበር ጀመሩ ይላሉ። የሆነ ጊዜ እለቱን በካላንደር ዝግ እንደሆነ አሳወቁ ይላሉ። የሆነ ጊዜ ከዓመታዊ የዲን ትምህርት ፕሮግራሞች ውስጥ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲራ የሚመለከተው ክፍል በረቢዕ ወር ላይ መደልደሉ መውሊድን ማክበር መጀመራቸውን ያሳያል ይላሉ። ወደፊትም የሆነ መንጠላጠያ መፈለጋቸው አይቀርም።
ከዚህ ሁሉ መንጠላጠያ ፍለጋ ኋላ ያለ አንድ ብልሹ እምነት አለ። በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የሳዑዲን መንግስት ነው የሚከተሉት የሚል እምነት አላቸው። ይሄ ራሳቸው ጮኸው ራሳቸው ያመኑት ባዶ ሙግት ነው። አንዳንዶቹ በግልፅ በመምጣት "እናንተ ዘንድ የሳዑዲ መንግስት ሐላል ያለውን ሐላል፣ ሐራም ያደረገውን ደግሞ ሐራም ታደርጋላችሁ" የሚል የለየለት ቅጥፈት ያራግባሉ። ይህንን ውሸት ደጋግመው በማስተጋባታቸው የተነሳ አንዳንድ የዋሆች እውነት እስከሚመስላቸው ደርሰዋል። ለማንኛውም መመሪያችን ቁርኣንና ሐዲሥ ብቻ ነው። የሳዑዲ መንግስት ሐላል ያለውን ሐላል፣ ሐራም ያደረገውን ደግሞ ሐራም አድርጎ የሚያምን አንድ ሙስሊም የለም። አንድ እንኳ! ሲጀመር በዚህ መልኩ እያመኑ ሙስሊም መሆን አይቻልም። እንኳን የሳዑዲ መንግስት፣ የሳዑዲ ዑለማኦች እራሱ የሐላል ሐራም መወሰኛ አይደሉም። በዚህ መልኩ የሚያምን ሰው ሙስሊም ሊሆን አይችልም።
ወደተነሳሁበት ነጥብ ስመለስ በኢስላም የሌሎች እምነት በዓላትን ማክበር ቀርቶ "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት አይፈቀድም። ይሄ ኢጅማዕ ያለበት ጉዳይ ነው። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
وأما التهنئة بشعائر الكفر المختصة به فحرام بالاتفاق، مثل أن يهنئهم بأعيادهم وصومهم، فيقول: عيد مبارك عليك، أو تهنأ بهذا العيد ونحوه، فهذا إن سلم قائله من الكفر فهو من المحرمات، وهو بمنزلة أن يهنئه بسجوده للصليب، بل ذلك أعظم إثمًا عند الله، وأشد مقتًا من التهنئة بشرب الخمر وقتل النفس وارتكاب الفرج الحرام ونحوه
" የበክህ ^ደት (ኩ^ፍር) ሃይማኖታዊ መገለጫዎችን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ ማለት በዑለማኦች ሙሉ ስምምነት ሐራም ነው። ይኸውም በበዓሎቻቸውና በጾማቸው ወቅት እንኳን አደረሳችሁ በማለት፤ ለምሳሌ፦ 'መልካም በዓል ይሁንልህ' ወይም 'በዚህ በዓል ደስ ይበልህ' እና የመሳሰሉትን አባባሎች በመጠቀም ነው። ይህን ያለው ሰው ራሱ ከኩ ^ፍር ቢተርፍ እንኳ፣ ድርጊቱ ከሐራም ነገሮች አንዱ ነው። ይህም ልክ ለመስቀል ሲሰግድ 'እንኳን ሰገድክ' ብሎ ደስታውን እንደመግለጽ ያህል ነው። እንዲያውም ይህ በአላህ ዘንድ አልኮል መጠጥ በመጠጣት፣ ነፍስ በማጥፋት እና ዝሙት በመፈጸም እንኳን ደስ አለህ ከማለት የከበደ ወንጀልና የከፋ ቁጣን የሚያስከትል ነው።" [አሕካሙ አህሊ ዚመህ፡ 1/205]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
✅ ቁጣን (በቀልን) መተዉ ያለው ትሩፋት!
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَن كَظَمَ غيظًا وهو قادرٌ على أن يَنْفِذَه دعاه اللهُ عزَّ وجلَّ على رؤوسِ الخلائقِ يومَ القيامةِ حتى يُخَيِّرُه اللهُ مِن الحُورِ ما شاءَ.﴾
“ቁጣውን ለመወጣት (ለመበቀል) አቅም እያለው ቁጣውን የዋጠ ሰው፤ አላህ (🤍) በቂያማ እለት በሕዝቦች ሁሉ ፊት ይጠራዋል፤ ከሁር አል-አይን (ከጀነት ሴቶች) ያሻውን መርጦ እንዲያገባ ምርጫ ይሰጠዋል።”
📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 4777
🟧🟧🟧🟧🟧🟧🟧
🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
📱 Telegeram 📱 Whatsup
📱 Facebook 📱 Instagram
📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok
አልተፈታም ህልሜ
/=====================/
አንደበቴ አፍታቶ ሲሳነው መናገር፡
ጊዜው ተራመደ ሳልሰራ ቁም ነገር፡
ጎዳናው ጠፋብኝ ካደባባይ ቆሜ፡
ዲብቅ ሚስጥር ሆኖ ሳይፈታ ህልሜ፡
ኑሮ ትርጉም ሲያጣ ሲሆን እንቆቅልሽ፡
አነባሁ አምርሬ ህይወት አዘንኩብሽ፡
ሳልኖር እየኖርኩኝ ሳያመኝ ታምሜ፡
አለሁ እስከ ዛሬ አልተፈታም ህልሜ፡
_
ውስጤ እየተከፋ አንጀቴ እያረረ፡
ለሰወች እያልኩኝ የግል ሀሳቤ እየተቀየረ፡
እንደ እኔ አስተሳሰብ ህይወት መች ተኖረ፡
በበቂ ምክንያት ችግር ሆኖ ይፋ፡
እኔ እያለቀስኩኝ ሰው እንዳይከፋ፡
በሀሳብ ማዕበል ውስጤ እየተገፋ፡
የነገን እያሰብኩ አለሁኝ በተስፋ፡
ሀሳቤ ነበረ እምነቴን ማስፋፋት፡
ጀግና ወጣት መሆን ጥንቁቅ ከኹኀራፋት፡
በፍቅር ለመኖር የፍቅር ሰው ሆኘ፡
አዕምሮየ አስቦ ልቤ እንደተመኘ፡
ሆነብኝ በዐክሱ ዛሬ ምን ተገኘ፡
ተስፋ አልቆርጥም ዛሬም ምኞቴ ይሳካል፡
የዛሬው መከፋት በደስታ ይተካል፡
ውስጠቴ ንፁህ ነው እያልኩ አስባለሁ፡
አላህ እስከሚሻ በተስፋ እኖራለሁ፡
ተውሒዲ ሱናን ይዠ ምን ያስጨንቀኛል፡
የውስጥ ስሜቴ አይዞህ ይለኛል፡
ጓደኛ ቢጠፋም ውስጤ ያፅናናኛል፡
ውስጤ ይመክረኛል፡
እንዲህም ይለኛል፡
የትናንት ወዳጂህ ዛሬ ቢሆን ባዳ፡
በየ ደረሰበት ስላንተ መጥፎነት ወሬውን ቢነዳ፡
ቆም ብለህ አስብ አሰታውስ ያላህን ቃል፡
በእምነትህ ጠንክር ሀዘንህ ይርቃል፡
ትክክል ነህ በነገር መወጋት ያማል!
ያስጨንቃል ልብንም ያደማል!
ግን ከወሬኞች በላይ አንተ ራዕይ አለህ፡
እነርሱ ሲያወሩ አንተ ተለይተህ፡
ለአላማህ ስራ የተግባር ሰው ሆነህ፡
የነገረኞች ቃል እንደ እሬት ቢመርም፡
ለሚጮኸው ሁሉ አይወረወርም፡
ዛሬ ያስተከዘህ ነገ ላይ ይፈካል፡
አብሽር አትጨነቅ ምኞትህ ይሳካል፡
ኢንሻ አላህ
አብሽር ጠንከር በል ራስህን አፅናና፡
ከጌታህ በስተቀር ባይተዋር ነህና፡
ሰው ያለውን ይበል በተውሒዲህ ፅና፡
የልቤ ትርታ ይህንን ሲመክረኝ፡
እኔም ተረጋጋሁ ውስጤንም ደስ አለኝ፡
ትልቅ ተሰፋን ጫንኩኝ ከሀዘን ርቄ፡
በወደፊት እቅድ ደስታየን ናፍቄ፡
ህልሜ እውን ይሆናል ቆርጨ ወሰንኩኝ፡
አዛኙን ጌታየን እየተማፀንኩኝ፡
ነገር ግን ዛሬ ላይ!
በወደፊት ህልሜ እጂጉን ብደሳም፡
በአላህ ተወክየ እንደሚስተካከል ወስኘ ብነሳም፡
ፈተናወች በዝተው ብተኛም ታምሜ፡
በችግሬ ጊዜ ቢርቀኝ ወንድሜ፡
ተስፋ አልቆርጥም እንጂ አሁን ባለሁበት
አልተፈታም ህልሜ፡
17- 07- 2011 አ.ል
(ኑረዲን አል_አረቢ)
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
♦️♦️♦️እህቶች በግዜ አግቡና ወለዱ አላህ መልካሙን ባል ይውፍቃችሁ በታሪኩ ተማሩ
📌قال الشيخ أحمد بن يحيى النجمي رَحِمهُ الله :
فَالْمَرأَة مَهْمَا حَصَلَ لَهَا مِن شَهَادَاتِ ، فَإِنَّ الْحَيَاة لا تطيب لَهَا إلا بالبنين والبنات ، ولقد سمعت أَنَّ امرأة دَرَسَتْ وتَدَرَّجَتْ فِي الشَّهَادَاتِ حَتَّى أخذت أعلاها ، وفي النهاية قالت : خُذُوا شَهَادَاتِي كُلها ، وأعطوني طفلاً ألاعبه .
ولقد خلق الله النساء ليكُنَّ أُمَّهَاتِ مُرَبَيِات وحاضنات ماهرات ، فَإِذَا خَرَجَت عن هذه الوظيفة وتركتها ؛ ندمت بعد ذلك ، وحنت إليها بعد أن ذَهَبَ الزَّمَن وبَلِيَ الشباب ، فالله الْمُسْتَعَان.
ሴት ምንም ያህል ትምህርት ብትማርና ብዙ የትምህርት ዲግሪዎችን ብታገኝም፣ ሕይወቷ ያለ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ሙሉ በሙሉ ደስተኛ አይሆንም።
አንዲት ሴት ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምራ በትምህርት ደረጃዎች ሁሉ እየተማረች እስከ ከፍተኛው የትምህርት ድረስ እንደደረሰች ሰምቻለሁ። በመጨረሻም እንዲህ አለች፦
“ሁሉንም የትምህርት ዲግሪዎቼን ውሰዱ፤ እኔ ግን የማጫውተውና የምንከባከበው አንድ ሕፃን ስጡኝ።”
አላህ ሴቶችን
እናቶች፣ ልጆቻቸውን በመልካም ሥነ-ምግባር የሚያሳድጉ አስተማሪዎችና ብቁ አሳዳጊዎች እንዲሆኑ ፈጥሯቸዋል።
ስለዚህ ሴት ከዚህ የእናትነትና የልጆችን የማሳደግ ተፈጥሯዊ ሚናዋ ብትወጣና ብትተወው፣ በኋላ ትጸጸታለች። ጊዜው ካለፈ፣ ወጣትነቷም ካለቀ በኋላ ወደዚያ ሚና ትናፍቃለች።
አላህ ረዳታችን ይሁን።
📚 تأسيس الأحكام (ج ٢ ص ٣١٢).
አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from Abu_Oubeida~channel
ይቅርታ!
ሰዎች ሲበድሉን፣ ይቅርታ ሲጠይቁን «ለምን ወዲያው ይቅር አልኳቸው?» እያልን ራሳችንን እንወቅሳለን። ጤናማና ሰብአዊ ስሜት ያለው አእምሮ እንኳ ሳይቀር የጥፋተኛውን ይቅርታ ወዲያውኑ መቀበል አቅቶት ሲቸገር ይስተዋላል።
ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት የጥፋቱ ስሜት ከቃሉ ይልቅ በውስጣችን ጥሎት ያለፈው ቁስል ከባድ ስለሆነ ነው።
የጥፋቱ ስሜት ውስጣችንን እንዲህ ይጎዳዋል፦
መተማመን ሲሰበር
በሰዎች ግንኙነት ውስጥ ዋጋው ከፍተኛው ነገር መተማመን ነው። አንድ ሰው ሲበድለን፣ የጥፋቱ ክብደት ብቻ ሳይሆን ያመነበትና የተመካበት ልባችን መክዳቱ ዋነኛው ጉዳት ነው። ይቅርታ መጠየቅ የጠፋውን ነገር በቅጽበት መልሶ መገንባት አይችልም። መተማመን እንደ አበባ ቡቃያ ነው፤ ጊዜ፣ እንክብካቤ እና ታጋሽነት ይፈልጋል።
የተፈጠረው ክፍተት እና ድካም
እያንዳንዱ ስህተት እና በደል በሰው ልብ ላይ የስነ-ልቦና ድካም ይፈጥራል። «ለምን እንዲህ አደረገ?» የሚለው ጥያቄ፣ ያሳለፍነው መመረር እና ውስጣዊ ጭንቀት አእምሯችንን ያደክሙታል። ይቅርታን ለማድረግ ሲሞከር እንኳን ውስጣችን ዝግጁ የሚሆነው ያ የደረሰን ድካም ሲቀልና አዕምሯችን እረፍት ሲያገኝ ነው።
ጊዜን የሚጠይቅ የፈውስ ሂደት
ቁስል ሲነካ ወዲያው እንደማይድን ሁሉ፣ የልብ ስብራትም የራሱ የሆነ የፈውስ ጊዜ አለው። ይቅርታ የሚጠይቅ አካል «ይቅርታ አድርግልኝ» ሲል፣ የተበዳዩ አካል ውስጣዊ ሰላም ግን ወዲያውኑ ሊመለስለት አይችልም፤ ልቡ የደረሰበትን ጉዳት አብጥሮ ለማየትና ያንን ስሜት ለማስተናገድ ጊዜ ይሻል።
ይህ ሁሉ ሆኖ፣ ይቅርታ ማድረግ የደካሞች ሳይሆን የጠንካሮች መለያ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ያንን ይቅርታ ከመቀበል በፊት ውስጣችንን ማዳመጥ ቅንጦት ሳይሆን የግድ የሚል ፍላጎት ነው። ቁስሉ ሳይደርቅና ውስጣችን ሳይረጋጋ የሚሰጥ ይቅርታ ባዶ ሊሆን ይችላል።
በመሆኑም፣ ይቅርታችሁን ከመቀበል በመዘግየታችን እንዳያማችሁ—እራሳችንን እስከምናስታግስ እንጂ ይቅርታችሁን ሳንቀበል አንቀርም።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
ሳይሸማቀቁ ችላ ሊሏቸው የሚገቡ አምስት ሰዎች ፡-
1- የደረሰበትን ችግር እንደፈተና ቆጥሮ የአንተን ግን እንደቅጣት የሚያይን ሰው።
2- ስህተቱን እንደጥረት ተመልክቶ ስህተትህን ደግሞ የምትቀጣበት ኃጢአት አድርጎ የሚያስብን ሰው።
3- ክብርህን ነክቶ ይቅርታ እንድትጠይቀው የሚጠብቅን ሰው።
4- ይቅርታ አድርገህለት እንደፈራኸው የሚያስብህን ሰው።
5- ጥፋቱን ችላ ስትለው ቂል አድርጎ የሚመለከትህን ሰው።
https://t.me/Abulbuhari.
بسم اللــــه الرحمـــــــــن الرحيم.
الســــــــــــؤال :-
ما صحة هذه القاعدة: (من لم يبدع المبتدع فهو مبتدع) أو (من توقف في تبديع المبتدع فهو مبتدع)؟
الإجـــــــــابة :-
بسم الله الرحمن الرحيم، الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله، أما بعد:
فما يتعلق بالبدع التي في أصول السنة الواضحة الجلية التي لا يحتاج فيها إلى إقامة الحجة لمن ابتدع فيها؛ لبيانها ووضوحها؛ فهذه القاعدة صحيحة فيما يتعلق بذلك. وعلى سبيل المثال: بدعة القول بخلق القرآن، وبدعة القدر، وبدعة تعطيل الله من صفاته، وما أشبه ذلك.
وأما ما يتعلق بالبدعة والأخطاء الخفية التي قد يحصل فيها الخفاء النسبي، فمثلها لا يصلح أن يبدع فيها العالم المجتهد المتحري للحق؛ فضلًا عن أن يقال فيها: (من لم يبدع المبتدع فهو مبتدع)، أو (من توقف في تبديع المبتدع فهو مبتدع). إلا في حالة أن يتبين له فيها الحق، فيقدم هواه ويعاند الحق.
ففي هذه الحالة يلتحق بالصورة الأولى؛ إذ أن من أصول أهل السنة تقديم أدلة الكتاب والسنة على العقل والهوى، وتقديم الحق على كل شيء سواه.
ولكن الذي يحكم على العالم بأنه قد صار يتابع هواه، ويقدمه على الحق في مثل هذه القضايا الخفية هم العلماء الراسخون؛ لأنهم هم الذين يميزون الحق من الباطل، ويميزون صاحب الهوى من صاحب السنة، ويعلمون الأعذار الشرعية التي يعذر بها العالم، وقد ألف شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله كتابا سماه: (رفع الملام عن الأئمة الأعلام)، ذكر فيه جملة من الأعذار الشرعية للمجتهدين، ننصح بقراءته والاستفادة منه.
ثم بعد ذلك كيف تطبق القواعد المذكورة لو حصل خلاف بين علماء أهل السنة في ذلك العالم، أهو متبع لهواه أم له عذر شرعي.
فإذا كان الخلاف موجودا بين العلماء في الاعتذار لعالم، فكيف يسوغ أن تطبق مثل هذه القواعد المجملة.
ولو كان أكثر العلماء لا يرون لذلك العالم عذرا شرعيا، وحكموا عليه باتباع الهوى، وتردد بعض العلماء عن الحكم عليه بذلك، لا تصويبا لخطئه، ولا اتباعا للهوى ، ولكن لاحتمالهم العذر الشرعي السائغ لذلك العالم، فكيف يسوغ أن تطبق عليهم القواعد المذكورة.
فالحقيقة أن كثيرا من الغلاة والمبتدئين الحماسيين ينزلون هذه القواعد في غير موضعها مما سبب جناية عظيمة على الدعوة السلفية وعلمائها.
ثم يأتي رجل جاهل، أو متعالم فيحكم على العالم باتباع الهوى، ويكتب الملازم نصيحة وإقامة للحجة فيما يزعم؛ فهذا من العجائب.
فإن هؤلاء المتعالمين قد يحكمون على بعض الأخطاء بأنها بدع، وليست كذلك، بل قد يحكمون على بعض الكلام الصحيح بأنه مخالف لمنهج السلف، وهم المخالفون لمنهج السلف رضوان الله عليهم.
وكم من عائب قولًا صحيحًا ** وآفته من الفهم السقيم
ثم يبنون على أفهامهم السقيمة أنها بدع، وأنهم قد نصحوا، وأن العالم قد خالف نصيحتهم وعاند؛ فيبدعون علماء السنة الأبرياء، ثم يبدعون من لا يوافقهم على تبديعهم، بحجة أنهم قد نصحوا، وفي الحقيقة أن ملازمهم مليئة بالبهتان، والطعن في النوايا، وتحميل الكلام ما لا يحتمل، والإلزامات الباطلة.
فهؤلاء الأصناف آلة هدم للدعوة السلفية شعروا أو لم يشعروا، ولذلك لا تجد لهم جهودًا ظاهرة في العلم والتعليم ونشر العقيدة الصحيحة والتوحيد والسنة، وتجدهم يظهرون عند الفتن، نسأل الله العظيم أن يسلم الدعوة من ضرر هؤلاء الغلاة المتعالمين، وأن يكبتهم، وأن يحفظ دينه وحملته والمدافعين عنه بالحق.
والحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين.
الشيج محمد بن حذام
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
..ዛሬ ግን.....
--------------
ማን እየጣለኝ ነው የበዛው መውደቄ፡
የእምነት ምልክቴ የት አለ ሰንደቄ፡
መቼ በምን ዘመን እንደጠፋ ሳቄ፡
ማን እንደ ሰረቀኝ እኔ ምን አውቄ፡
ግና ልጅ እያለሁ መሳቅ ያምርብኛል፡
ለክፉም ለደጉም ፈገግታ ያምረኛል፡
በዚህች አለም መተት ገና ሳልሰበር፡
ፈገግታ እያበዛሁ ጨዋታ አውቅ ነበር፡
አሁንማ ደግሞ...
በምን ለምን ከሰው እንደሸሸሁ፡
ከብቸኝነት ጋር የት ቦታ እንዳመሸሁ፡
ከማን አጭበርብሬ ከማንን እንደሸሸሁ፡
እንደዚህ ነው ብዬ ባላውቀውም ቅሉ፡
እያደከመኝ ነው ህይወት ምስቅልቅሉ፡
አወ....
በአዕምሮዬ ሀሳብ ስደግን፡
የመከራ ቆሎ ስዘግን፡
ፈገግታ ራቀኝ ዛሬ ግን....
✍ኑረዲን አል አረቢ
http://t.me/nuredinal_arebi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (48)
~
መጅሊስ በታሪኩ ከመንግስት ተፅእኖ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ለዚህ ዋናው ምክንያት መጅሊሱ ላይ የሚቀመጡ አካላት ባህሪ ሳይሆን የፖለቲከኞቹ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህሪ ነው። ከዚያ የሚቀመጡ ሰዎች ድባቡን ያዩና ከ "አየር ንብረቱ" ጋር ራሳቸውን ያስማማሉ። የ1987ቱ የአንዋር መስጂድ ብጥብጥ ምክንያት ከጥቅም ግጭት ባለፈ የመንግስት አካላት ፍላጎት ከጀርባ ነበር። በሁለቱም ጎራ የተሰለፉ አካላት የተሻለ የመንግስት ድጋፍ እንዳላቸው ያስቡ ነበር። ኋላ ላይ አሕ^ባሽ ከሊባኖስ ተጋብዞ የገባውም ከመጅሊስ ሰዎች ፍላጎት ባለፈ የመንግስት ፍላጎት ስለነበር ነው።
ዛሬ ላይ ያለው የፖለቲካውን ነፋስ ተከትሎ የመጣው የመጅሊስ ለውጥም ያለቀለትና የማይነካ አይነት አይደለም። ነገ ሊቀየር ይችላል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ አንዳንድ ደስ የማይሉ ሽታዎች ያሉ ይመስላል። መጅሊስ ላይ በየመዋቅሩ ያሉ አካላት ይህንን ተገንዝበው ለህዝባችን ዐቂዳውን ማስተማር ላይ ወይም ለማስተማር ምቹ ድባብ እንዲኖር ማድረግ ላይ መሬት የረገጠ ስራ ሊሰሩ ይገባ ነበር። ነበር የምለው በተግባር እየሆነ ስላላይደለ ነው። በተለይ አማራ ክልል ላይ ከ'ኮስሞቲክ' ስራዎች በመውጣት ዛሬ ላይ ቆፍጠን ብሎ መስራት ይሻል ነበር። ነገሮች ቢቀያየሩ ተፅእኖው ከሌሎች አካባቢዎች ይለያል።
ሌላው ቢቀር ለተሻለ መስለሓ ብላችሁ የገባችሁ ወገኖች ራሱ ከልብ በመመካከር ህዝብ ላይ ብትሰሩ መልካም ነው። ጊዜው አሁንም አልረፈደም። ብዙ መራመድ የሚያስችላችሁ አቅም ባይኖራችሁ እንኳ በአቅማችሁ ልክ የምትችሉትን ሳትሰሩ ጊዜው እንዳያልፍ ብታስቡበት ይሻላል። እውነት ለመናገር በተበላሸ ዐቂዳውም ቢሆን ሳይልፈሰፈስ ቆፍጠን በማለት እና መሬት የወረደ ስራ በመስራት በኩል ከመጅሊስ ተቋማት የተባረረው አሕ^ባሽ የተሻለ ትጋት አለው። አሕ^ባሽ የመጅሊሱ መዋቅር በእጁ ሳለም ያለምንም ይሉኝታ ህዝብን ለመለወጥ እስከ ደም ጠብታ ታግሏል። የያዘው ዐቂዳ ክር^ፋትና የመንግስት ዓይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ነው ወደ ህዝብ ልብ ከመግባት እንቅፋት የሆነበት።
ከመሆኑም ጋር ለብልሹ ዐቂዳው በመዋደቅ ላይ ከመጅሊሱ ደጅ ርቆም አልቆመም። ዳግም ከተመለሰም ከቀደመው የበለጠ እንደሚጠቀምበት ይጠበቃል። ያ እንዳይሆን ወይም እውን ቢሆን እንኳ ጉዳት ለመቀነስ ደግሞ ፖለቲከኛ ተደግፎ መተኛት ሳይሆን ህዝብን ትክክለኛውን አስተምህሮት ማስታጠቅ ነው የሚገባው። የሹማምንትን ጫና ለመጋፈጥ ወይም ለመቀነስ ትክክለኛው መንገድ ደሞ ከአላህ በታች ህዝብን ማንቃት ነው ሁነኛው ስራ። አላህ ልብ ይስጠን።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
አላህ ከጎንህ ከሆነ ምንም አይነት ጭንቅ ቢኖር መጨረሻው ሁሌም ቀላል ይሆናል።
_1. ኢብራሂም (ዐለይሂሰላም) ከእሳት_
ንጉሡ በላያቸው ውስጥ በጣለበት ጊዜ አላህ እሳቱን
يا نار كوني برداً وسلاماً ብሎ በረዶና ሰላም አደረገለት።
_2. ኑህ (ዐለይሂ ሰላም) - ከጦፋን_
ህዝቡ አላመነም፣ አላህ ታላቅ ጎርፍ ሲያመጣ እሱን እና አማኞችን በመርከብ አዳናቸው።
_3. ዩኑስ (ዐለይሂሰላም) - ከዓሣ ሆድ_
ከህዝቡ ተቆጥቶ ሲሄድ ዓሣ ዋጠችው። በጨለማው ውስጥ لا إله إلا أنت سبحانك ብሎ ሲያወድስ አላህ ከሆዷ አወጣው።
_4. ዩሱፍ (ዐለይሂሰላም) - ከጉድጓድ እና ከእስር_
ወንድሞቹ በጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፣ ከዚያም በሀሰት ክስ ታሰረ። በመጨረሻ ግን አላህ የግብጽ ንጉሥ አደረገው።
_5. ሙሳ (ዐለይሂሰላም) - ባህር ተሰንጥቆ_
ፊርዐውን ሲያሳድዳቸው አላህ ባህሩን ከፍሎላቸው አሻገራቸው፣ ጠላቶቻቸውን ደግሞ አሰጠማቸው።
_6. ሙሐመድ ﷺ - ጋረ-ሠውር (የሠውር ዋሻ)_
ከመካ ወደ መዲና ሲሄዱ በዋሻው ውስጥ ተደብቀው ሳሉ አላህ በሸረሪት ድር እና በርግብ እንቁላል አዳናቸው።
አላህ ሁሉንም ፈተና ያቃልልልን! 🤲💦💦💦መሰናክል በበዛ ቁጥር መንገዱ ይረዝማል እንጂ መዳረሻውን አይለውጠውም። ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዘን ስንጓዝ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ተስፋ ሊያስቆርጡን ሳይሆን፣ ለድል የምንሰጠውን ዋጋ ከፍ አድርገው ሊያስተምሩን የመጡ ምዕራፎች ናቸው።
ነፋሱ ኃይለኛ ሲሆን ጀልባው ትንቅንቅ ይፈጥራል፤ ነገር ግን ማዕበሉን አልፎ ወደቡ የሚደርሰው በጽናት የገሰገሰ ብቻ ነው። ስለዚህ፣ እምነታችንን አጽንተን፣ ቆራጥነትን አንግበን፣ እያንዳንዱን እክል ደረጃ በደረጃ ልንወጣው ይገባል።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
ክብር ለዑለሞቻችን!
ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲ አል–ዓባድ ሐፊዞሁላህ፦ በዚህ ዘመን ከታላላቅ የሰለፊያ ዑለሞች መካከል በዒልምም ሆነ በእድሜ ከግንባር ቀደም የሚቆጠሩ ታላቅ የሐዲስ ሊቅ ናቸው። አይደለም ሸይኽ ዐብዱልሙሐሲን ይቅርና ተማሪዎቻቸው በዚህ ዘመን በእድሜም ሆነ በዒልም አቻ የሌላቸው ናቸው። ከተማሪወቻቸውም መካከል፦
1.የየመኑ ሙሐዲስ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል–ዋዲዒይ ረሒመሁላህ
2.ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ ረሂመሁላህ
3.ሸይኽ ዑበይድ አል–ጃቢሪይ ረሂመሁላህ
4.ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሱሐይሚይ ሐፊዘሁላህ ይገኙበታል።
✍🏻 ኢብኑ ሙሐመድዘይን
📍 تفريغ دورة دراسات في المنهج (بصيغة pdf)
للشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله
ዐረበኛ የምትችሉ ኪታቡን አውርዳችሁ ብታነቡት በአላህ ፍቃድ እጅግ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ።
የተዳሰሱ ነጥቦች፦
1, መንሀጀ ሰለፍ
2, በዘመኑ ያሉ ጠማማ አንጃዎች
👉 ተብሊግ
👉 ኢኽዋን
👉 ዳዒሽ
3, ኢስላምን ያስጠሉ ግለሰቦች
(ሐሰን አል–በና፣ሰይድ ቁጥብ፣አቡ አዕላእ አል–መውዱውዲ) እና ሌሎችም የጥመት መሪዎች ረድ የተሰጠበት ዳሰሳ አካቶ ይዟል።
ኪታቡ ከላይ እተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰፋ ባለሁኔታ ስለመንሀጅ የተዳሰሰበት ጥሩ ትምህርት ነው።
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን። አሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ማነው ፖለቲካ የገባው?
~
የሰዎች የኋላ ዳራ (background)፣ ስሜት፣ ፍላጎት፣ የሚከተሉት አስተሳሰብ፣ ቡድናዊ አመለካከት፣ የንቃት መጠን፣ የትምህርት ደረጃ፣ የዲን ግንዛቤና አቋም፣ ወዘተ ይለያያሉ። ይህንን ተከትሎም የሚደግፉትና የሚቃወሙት የፖለቲካ ኃይል ይለያያል። እዚህ ድረስ መግባባት ይቻላል። የምንለያየው ይህንን እውነታ የሚያረጋግጥ ተግባራዊ ማሳያ ስንመዝ ነው።
የሚገርመው እነሱ የሚደግፉትን የማይደግፍ፣ እነሱ የሚጠሉትን የሚወድን አካል "አንተ ፖለቲካ አልገባህም" የሚሉ ሰዎች ሁኔታ ነው። ልክ ፖለቲካ መረዳት ማለት ከነሱ ስሜት ጋር መግጠም የሆነ ይመስል። ስለ ፖለቲካ ብዙ የለቀለቀ ወይም የፈተፈተ ሁሉ ፖለቲካ ገብቶታል ማለት አይደለም። ዝም ያለም ሁሉ አልገባውም ማለት አይደለም። ነጋ ጠባ ዜና መዘገብ ፖለቲካ መረዳት አይደለም። ትንሽ ትልቁን ከሴራ ጋራ እያስተሳሰሩ መጎንጎንም የፖለቲካ ችሎታ ሳይሆን የራስን ስንፍና መሸፈኛ ሰበብ ነው። ይሄ ነገር በጣም ከመብዛቱ የተነሳ "ዐረብ ልጁ ትምህርት ቤት ቢወድቅበት የአይ^ ሁድ እጅ አለበት" ከማለት አይመለስም እስከማለት የተሳለቁ አሉ። ግነቱ በውስጡ የሆነ እውነት አለው።
ለምሳሌ ያክል የሀገራችንን የዘር ፌዴራሊዝም በፅኑ የሚያወግዝ ብዙ ኃይል አለ። አሀዳዊ ስርአትን ከሺርክ በላይ የሚኮንንም ብዙ ወገን አለ። አስቡት እንግዲህ ሁሉም እየተነሳ ሌላኛውን አካል ፖለቲካ አልገባህም እያለ ሲያጣጥል። አተያያችን የተራራቀው በዋናነት በግንዛቤዎችን መበላለጥ ምክንያት አይደለም። ይልቁንም በብልጣብልጥና ስግብግል ባህሪያችን የተነሳ ነው። በትምህርት ዝግጅታቸውና ደረጃቸውም፣ በሚከተሉት እምነትም ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት ከአማራና ከኦሮሞ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዘር ፌዴራሊዝምና በአሃዳዊ ስርአት ላይ ያላቸው ምርጫ ተቃራኒ ነው። ለምን? ግልፅ ነው። ታሪክን የሚረዱት በተራራቀ መልኩ ነው። የዛሬ ምርጫቸውም እንዲሁ የተራራቀ ነው።
ልክ እንደዚሁ እኔና አንተ ዐቂዳችንና መንሀጃችን እስከተለያየ ድረስ በሙስሊም ሀገራትና ቡድኖች ላይ ያለን ፖለቲካዊ አተያያችንና ውግንናችንም ይለያያል። ላንተ የዑመር ጠላት የሆኑ ሺዐዎችን መውደድ ኖርማል ነው። ለኔ ደግሞ ይሄ ፈፅሞ ሊያቀራርበን የማይችል ቀይ መስመር ነው። ላንተ "ሙስሊም" የሚለው ስሙ እስካለ ድረስ የፈለገውን ቢያራምድ ዋናው "ሞት ለአሜሪካ!" ማለቱ ነው። ከአሜሪካ ጋር አይንና ናጫ የሆነችው ሰሜን ኮሪያ ራሱ የአሕመዲያ መዝሀብ ተከታይ ብትሆን ኖሮ ሱኒ ሙስሊሞችን እያነቀች ብትገ ^ድል እንኳ ከመደገፍ አትመለስም ነበር።
ለማንኛውም እንደ ሙስሊም ነገሮችን ሁሉ የምንመለከትበት መነፅር ዲን ሊሆን ይገባል። የዲን መሰረቱ ደግሞ ተውሒድ ነው፣ ዐቂዳ ነው። ወላእና በራአችን ዐቂዳን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል። ይህንን ነጥብ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከኢስላም ቋጠሮዎች ሁሉ ጠንካራው" ሲሉ ነው የገለፁት። የዐቂዳ ጉዳይ ላንተ ውሃ የማያነሳበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ራስህን ጠይቅ፣ ልብህን አድምጥ። ምናልባት ለማስተዋል ከጠቀመህ - እንዲያው ምናልባት - ሺዐ እና ሱኒን ለማቀራረብ በጣም ለረጅም ዘመናት የደከመው ዩሱፍ አልቀርዷዊይ በዚህ ጥረታችን ሺ0ዎች አተረፉበት እንጂ ለሱኒው ዓለም ከጉዳት በስተቀር ያተረፈው ፋይዳ የለውም ማለቱን ያዝ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
