قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
前往频道在 Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
显示更多未指定国家未指定类别
901
订阅者
-424 小时
-167 天
+4030 天
帖子存档
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሙሓደራ 192
አዲስ ሙሓደራ ክፍል 04
"" ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ ""
የተዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት
👉 እውነት የ አቋም ለውጥ ( የመንሓጅ ለውጥ) የተከሰተው ከማን ነው ???
👉 የአብዱልሐሚድ እንዲሁም መሰል የተገጫጨውን ንግግር ሲቀርብ የግንዛቤ ድክመት ተከስቶአልን እንደሚባለው ?
👉 ስለ ኢልዛም ሰፋ ባለ መልኩ እንዲሁም የአቋም ለውጥ ባመጡ በሆኑ ሰዎች ላይ አጥጋቢ ምላሽ ።
👉 ሀሰን ገላው ፣ አቡ
ዘር እንዲሁም ባህሩ ተካ ከነበራቸው አቋም በግልፅ መገልበጣቸውን ከድምፅ መረጃ ገር የተደገፈ ንግግር
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ ( አቡ ሐቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኹጥባ በተቻለ መጠን፡
* ቃላቱ የተከሸነ፣
* መጠኑ የተመጠነ፣
* መልክቱ ወቅቱን ያማከለ፣
* አቀራረቡ ታዳሚውን ያልዘነጋ ቢሆን መልካም ነው።
ኸጢቦች ሆይ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ሰዎች ውጭ ላይ ከባድ የቀትር ፀሐይ ቃጠሎ ሲያንቃቃቸው ወይም ዝናብ ሲዘንብ እንኳ ርህራሄ ቢኖራችሁ መልካም ነው። ሰዎች እየተከፉ ዒባዳቸውን እንዲፈፅሙ አታድርጉ። "ከናንተ ውስጥ አስበርጋጊዎች አሉ" የሚለውን ሐዲሥ አስታውሱ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
ማስተማር ላይ እንበርታ
~
ዐብዱላህ ብኑል ሙባረክ ረሒመሁላህ "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ነበር የምትሰራው?" ተብለው ቢጠየቁ "ሰዎችን አስተምር ነበር" ብለው መለሱ።
[አልመድኸል፣ ሊልበይሀቂይ፡ 2/45]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ليس الغريب غريب الشام واليمن إن الغريب غريب اللحد والكفن.
النجاة والمصلحة والخيرات في الكلام بعلم ، والسكوت بحلم ، ورد كل أمر إلى أهله ، فليس السكوت دائما محمودا ، فقد يكون في السكوت انتشار الباطل أو إظهاره أو غش العامة أو التدليس عليهم فيكون الكلام محمودا ولكن بعلم , وقد يكون في الكلام تقوية للفتنة أو نشر لها ، أو نشر لما لا يحصل به صلاح ولا يدفع به فساد ، ونحو ذلك فيكون السكوت محمودا ولكن بحلم ، فلو لم يتكلم إلا عالم حيث يحسن الكلام أو يجب ، وسكت من لم يعلم بحلم ، وعَرف فضل من علم وتكلم بعلم ، ورُدَّ كل أمر إلى أهله ، وأمسك كل إنسان عن الخوض فيما لايعنيه أو فيما لم يحط بعلمه ، لظهر الصلاح في البر والبحر ، وقل الشر واندحر ، وانطفأت الفتن ، وكثر الخير ، واستراح الناس ، وصلحت الأحوال .
✍الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله ورعاه
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me/Abulabas1444
http://t.me/Abulabas1444
كلام الشيخ ربيع في الحدادية
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
تحذير الشيخ العلامة سليمان الرحيلي من المدعو محمد بن شمس الدين.
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
አል-ኢማም ሐሰን አል-በስሪ(رحمه الله)እንድህ ተብለው ተጠየቁ፦
﴿هَلْ يَنَامُ إِبْلِيسُ؟ قَالَ: لَوْ نَامَ لَوَجَدْنَا لِذٰلِكَ رَاحَةً﴾
“ኢብሊስ ይተኛል እንዴ? እንዲህ አሉ፦ በተኛማ ኖሮ እኛ እረፍት ባገኝን ነበር።አዝሁድ ሊኢማሙ አህመድ፡ (1506)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me/Abulabas1444
http://t.me/Abulabas1444
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (41)
~
የብዙ ፈተናዎችና ብጥብጦች ሰበብ ሶብር ማጣት ነው። በሚገጥሟቸው ፈተናዎች ተበሳጭተው ወደ ሃይልና ብጥብጥ በመግባታቸው የተነሳ ስንቶች ህይወታቸውን አጥተዋል?! ስንቶች አካላቸው ጎድሏል?! ስንቶች ንብረታቸው ወድሟል?! ስንቶች ለረጅም የወህኒ ቆይታ ተዳርገዋል?! ስንቶች ቤተሰቦቻቸውን አጥተው የቁጭት እሳት እየለበለባቸው ነው?! ስንቶች አገራቸውን ጭምር አጥተዋል?! ስንቶች መስጂዳቸውን፣ ደዕዋቸውን፣ ዲናቸውን አጥተዋል?! በሶብር ማጣት ስንቶች ትዳራቸውን አጥተዋል?! ስንቶች የተሻለ ስራቸውን አጥተዋል?! ሶብር ማጣት ብዙ ነገር ነው የሚያሳጣው።
ብዙዎች ከሶብር የሚርቁት ወደ ዓላማቸው ለመድረስ ካላቸው ጉጉትና ችኮላ የተነሳ ነው። ነገር ግን የሚዘነጉት ነገር ሶብር በራሱ ወደ ዓላማ መቃረቢያ ሁነኛ መንገድ መሆኑን ነው። በሶብራቸው ደካሞች ካለሙበትት ደርሰዋል። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِینَ كَانُوا۟ یُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَـٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَـٰرِبَهَا ٱلَّتِی بَـٰرَكۡنَا فِیهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِیۤ إِسۡرَ ٰۤءِیلَ بِمَا صَبَرُوا۟ۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ یَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُوا۟ یَعۡرِشُونَ }
"እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆቿንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው። የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስ ^ራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች። ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን።" [አልአዕራፍ፡ 137]
ፈተና ሲገጥመን ሶብር፣ ዱዓእ፣ ጥረት ላይ መበርታት ይገባል። ያኔ ፈተናው በአላህ ፈቃድ ይገፈፋል። ኸባብ ብኑል አረት ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦
شَكَونا إلى رَسولِ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم وهو مُتَوسِّدٌ بُردةً له في ظِلِّ الكَعبةِ، فقُلنا: ألا تَستَنصِرُ لنا، ألا تَدعو لَنا؟ فقال: قد كان مَن قَبلَكُم يُؤخَذُ الرَّجُلُ فيُحفَرُ له في الأرضِ، فيُجعَلُ فيها، فيُجاءُ بالمِنشارِ فيوضَعُ على رَأسِه فيُجعَلُ نِصفَينِ، ويُمشَطُ بأمشاطِ الحَديدِ ما دونَ لَحمِه وعَظمِه، فما يَصُدُّه ذلك عن دينِه، واللهِ لَيَتِمَّنَّ هذا الأمرُ، حتَّى يَسيرَ الرَّاكِبُ مِن صَنعاءَ إلى حَضرَمَوتَ، لا يَخافُ إلَّا اللهَ، والذِّئبَ على غَنَمِه، ولَكِنَّكُم تَستَعجِلونَ.
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ በከዕባ ጥላ ስር ኩታቸውን ተንተርሰው ሳሉ ስለሚደረስብን መከራ አቤቱታ አቀረብንላቸው፤ ‘እርዳታን አትለምንልንምን? ዱዓእ አታደርግልንምን?’ አልናቸው።
እርሳቸውም እንዲህ አሉ። ‘ከእናንተ በፊት በነበሩት ህዝቦች ዘንድ አንድ ሰው ተይዞ መሬት ይቆፈርለትና በውስጧ ይገባ ነበር፤ ከዚያም መጋዝ መጥቶ በራሱ ላይ ይደረግና ለሁለት ይከፈል ነበር። በብረት ማበጠሪያዎችም ሥጋው ከአጥንቱ ይበጠር ነበር። ይህ ሁሉ ግን ከሃይማኖቱ አይመልሰውም ነበር። በአላህ እምላለሁ! ይህ ጉዳይ (እስልምና) ሙሉ ይሆናል! ተጓዥ ከሰንዓ ተነስቶ እስከ ሐድረመውት ድረስ፣ ከአላህና በበጎቹ ላይ ከሚመጣ ተኩላ በስተቀር ምንም የሚያፈራው ነገር ሳይኖር የሚጓዝበት ጊዜ ይመጣል። ነገር ግን እናንተ #ትቸኩላላችሁ።’ " [አልቡኻሪይ፡ 6943]
አስተውሉ! ያ ሁሉ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ስሞታ ቢያሰሙ ነው "ትቸኩላላችሁ" ብለው የገሰጿቸው። ከዚህ የማይቀርቡ ፈተናዎችን መታገስ አቅቶን ለስንት የባሰ መከራ ተደርገናል?! ይልቁንም አስፈላጊ ሰበቦችን በማድረስ እንደታዘዝነው በመታገስ ፈረጃን ከአላህ እንጠብቅ። ካልሆነ ግን የሚቀረው ምርጫ የከፋና የመረረ ይሆናል። አዎ! ሶብርን መልቀቅ ለከፋ ፈተና መጋለጥ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
عامة الفتن التي وقعت من أعظم أسبابها: قلة الصبر؛ إذ الفتنة لها سببان: إما ضعف العلم، وإما ضعف الصبر
"የደረሱ ፈተናዎች (ሁከቶች) እንዳለ ከዋና መንስኤዎቻቸው ውስጥ አንዱ የትዕግሥት ማነስ ነው። ምክንያቱም ለፈተና ሁለት መንስኤዎች አሉት፡ ወይ የእውቀት ማነስ ወይም ደግሞ የትዕግሥት ማነስ ናቸው።" [አልፉሩዕ፡ 10/181]
||
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 16 /1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from مَنَارُ السَّلَفِيِّينَ (መናሩ ሰለፍይይን)
ውሸትን የደዕዋ መሳሪያ ከማድረግ መጠንቀቅ
~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~
ወንድሜ ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቅ! ሙብተዲዕ ነው ብለህ በምታምነው ሰው ላይ እንኳ ፈፅሞ አትዋሽ። ደዕዋ ላይ የተሰማራህ ስትሆን ደግሞ ይበልጥ ጥንቃቄ ይኑርህ። የዳዒያህ ውሸታም አደጋው ከሌሎች ውሸታሞች የከፋ ነው።
1- ውሸት ልፋቱን ከንቱ ያደርጋል። ለደዕዋ እየለፋ ዞሮ በየመሀሉ ሆነ ብሎ ውሸትን የሚሰነቅር ከሆነ እየፈጩ ጥሬ ነው የሚሆው።
2- ውሸት መቋጫ የሌለው ድርብርብ ወንጀል ላይ ይጥላል። በተለይ ውሸቱ በደዕዋው ላይ የሚንፀባረቅ ከሆነ (ለምሳሌ፦ ሰዎችን ዋሽቶ የሚወነጅል ቢሆን) ያ ውሸቱ ባሳደረው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል። በሱ ውሸት የተነሳ ደዕዋ ቢደናቀፍ፣ የሰዎች ስም ቢጎድፍ፣ ሰዎች ለኢስላም ወይም ለደዕዋው ያላቸው እይታ ቢበላሽ፣ ሰዎች ከኸይር ቢርቁ፣ በቀጥታ በራሱ ውሸችም ይሁን በሱ የውሸት ውንጀላ በተሸወዱ ሰዎችም ይሁን በየትኛውም መልኩ ሌሎች ላይ ጉዳት ቢደርስ የውሸቱ ጠንሳሽ ላይ ድርብርብ ወንጀል አለበት።
3- የውሸት ፀያፍነት ሰዎች ዘንድ ቀልሎ እንዲታይ ያደርጋል። ሸይኽ ወይም ኡስታዝ እከሌ እንዲህ የሚዋሸው ጉዳዩ ያን ያህል ከባድ ባይሆን ነው የሚል ሸፋፋ ሂሳብ የሚሰራ ሊያጋጥም ይችላል።
4- ውሸታም ሌሎች የዳዕዋ ሰዎችን ያስንቃል። የጥፋት አንጃዎች ዘንድ መሳለቂያ ያደርጋል። የዑለማእ፣ የዱዓት መናቅ ደግሞ ትምህርታቸው ተቀባይነት እንዲያጣ ያደርጋል።
5- ውሸታም ለሌሎች ክፉ ምሳሌ ይሆናል። አስተማሪው ሲዋሽ የተመለከተ ሰው ነፍሲያ በጎተጎተው ቁጥር ያለምንም ጥንቃቄ ሊዋሽ ይችላል። ውሸታም አስተማሪ ውሸታም ተማሪዎችን ያፈራል። ይሄ ደግሞ አጠቃላይ ደዕዋው ላይ ከባድ ጉዳት ነው የሚያደርሰው። ምክንያቱም የተቀየመውን ሁሉ በረድና ተሕዚር ስም ዋሽቶ ለማጠልሸች የማይመለስ መንጋ ይተካልና።
ወንድሜ ሆይ! አስተውል! ተውሒድ በሺርክ፣ ሱና በቢድዐ፣ እውነት በሀሰት አይታገዝም። ዲንን ለማስተማር ብለህ አታዋሽ። ዲንህ የውሸትን እርዳታ የሚፈልግ አይደለምና። አጥፊን ለማስጠንቀቅ ብለህ አትዋሽ። ሳትዋሽ ከአጥፊ ማስጠንቀቅ ካልቻልክ ከምታለማው የምታጠፋው ይበዛልና ይቅርብህ። አትሸወድ! የበደለኛን በደል በሌላ በደል አስቆማለሁ ማለት አጥፎቶ መጥፋት ነው። ተያይዞ ገደል! የትም ቦታ ቢሆን ፍትህ መጠበቅ አለበት። አላህ እንዳስፈላጊነቱ ከሀ*ዲዎችን ከፍ ስል በመሳሪያ ዝቅ ሲል በደዕዋ እንድንዋጋቸው አዞናል። ከመሆኑም ጋር ፍትህ እንዳናዛባ አሳስቦናል። ይሄውና አደራው፦
(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰمِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ህዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡" [አልማኢዳህ፡ 8]
እወቅ! ውሸት ተራ መስሊሞችም ላይ ቢሆን ፀያፍ ከመሆኑ ጋር ነገር ግን የሙስሊም መሪዎችና ዑለማዎች ላይ ሲሆን ክብደቱ ይጨምራል። ምክንያቱም በተራ ሙስሊሞች ላይ ከመዋሸት የከፋ ውጤት ያስከትላልና። ውሸቱ በአላህና በነብዩ ﷺ ላይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ አደገኛ ይሆናል። የአንድን ሙስሊም ክብር የሚያጠለሽ ውሸት ተሻጋሪ ጉዳት ከሌለው ውሸት የከፋ ነው። በህዝብ ላይ፣ በደዕዋ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ውሸት ደግሞ በግለሰብ ላይ ጉዳት ከሚያደርሰው ውሸት የከፋ ነው። ስለዚህ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
እና እልሃለሁ! ለሱና እከላከላለሁ ብለህ አትዋሽ! ቢድዐን እዋጋለሁ ብለህ አትዋሽ። ያለበለዚያ ይበልጥ ቆሻሻ ጥፋት ውስጥ እየተነከርክ ነው። ሸይኽ ረቢዕ - ሐፊዘሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
الكذب أخبث من البدع يا إخوان والكذَّاب أخبث عند أهل السنة من المبتدع المبتدع يروى عنه, رَوَوْا عن القدرية رَوَوْا عن المرجئة ورَوَوْا عن غيرهم من أصناف أهل البدع ما لم تكن بدعة كفرية ما لم يكن كذابا. لو كان ينتمي إلى أهل السنة كذَّاب فهو عندهم أحط من أهل البدع .
ومن هنا عقد ابن عدي-رحمه الله- في كتابه "الكامل" حوالي تسعة وعشرين باباً للكذَّابين([1]) وبابًا واحداً لأهل البدع .
وقَبِل أهل السنة رواية أهل البدع الصادقين غير الدعاة .
"ውሸት ከቢድዐ ይበልጥ ቆሻሻ ነው፣ ወንድሞች። ውሸታም የሱና ሰዎች ዘንድ ከሙብተዲዕ የከፋ ቆሻሻ ነው። ሙብተዲዕ ከሱ ይዘገባል። (የሐዲሥ ምሁራን) ከቀደሪያ ዘግበዋል። ከሙርጂአ ዘግበዋል። ከሌሎች የቢድዐ አራማጅ አይነቶችም እንዲሁ። ይህም ቢድዐው ክህደት የሚደርስ እስካልሆነና ዋሾ እስካልሆነ ድረስ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ውሸታም እራሱን ወደ አህለ ሱና የሚያስጠጋ ቢሆን እንኳ እሱ እነሱ ዘንድ ከቢድዐ ሰዎች በታች ናቸው። ለዚህም ነው ኢብኑ ዐዲይ - ረሒመሁላህ - አልካሚል በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ሙሸታሞችን በተመለከተ ሃያ ዘጠኝ ርእሶችን ሲሰጡ፣ የቢድዐ ሰዎችን በተመለከተ ግን አንድ ርዕስ ብቻ መስጠታቸው።"
ልብ በሉ! ውሸትና ውሸታሞች ፀያፍ የሚሆኑበትን ገፅ አጉልተው ለማሳየት እንጂ ይህን ማለታቸው እንዳጠቃላይ ቢድዐውን እንደ ኢስላም መቃረቢያ አድርጎ የሚቆጥረው ሙብተዲዕ የከፋ ወንጀለኛ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
ፅሁፌን የምቋጨው በተከታዩ የነብዩ ﷺ ሐዲሥ ነው፦
"وإيّاكم والكذِبَ، فإنّ الكَذِبَ يَهْدِي إلَى الفُجُورِ، وإِنّ الفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النّارِ وَمَا يزَالُ العبْدُ يَكْذِبُ وَيَتَحَرّى الكَذِبَ حَتّى يُكْتَبَ عِنْدَ الله كَذّابا".
"ውሸትን አደራችሁን (ተጠንቀቁ)። ውሸት ወደ አመፅ ይመራልና። አመፅ ደግሞ ወደ እሳት ይመራል። አንድ ሰው ከመዋሸትና ውሸት ላይ ከማተኮር አይወገድም አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስከሚመዘገብ ድረስ!" [ቡኻሪና ሙስሊም]
==
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from قناة شيخ جمال الذهبي الصباح
🔗 📌 بِسْــــمِ ﷲِ الرَّحْمـٰــــــــنِ الرَّحِيمِ 📌
🎁በሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ተቀርተው የተጠናቀቁ ቂርአቶች
في العقيدة1📚الأصول الثلاثة https://t.me/SheikhJemalZehabi/130 2📚الأصول الستة https://t.me/SheikhJemalZehabi/139 3📚القواعد الأربعة https://t.me/SheikhJemalZehabi/139 4📚أصول السنة للإمام أحمد https://t.me/SheikhJemalZehabi/160 5📚لمعة الإعتقاد https://t.me/SheikhJemalZehabi/173 6📚العقيدة الواسطية https://t.me/SheikhJemalZehabi/199 7📚العقيدة الإسلامية https://t.me/SheikhJemalZehabi/226 8📚 شروط لا إله إلا الله ونواقض الإسلام https://t.me/SheikhJemalZehabi/287 9📚شرح القواعد المثلى في صفات الله وأسمائه الحسنى https://t.me/SheikhJemalZehabi/508 10📚قواعد في أسماء الله وصفاته لبن القيم من كتاب بدائع الفوائد(ملحق بشرح قواعد المثلى) https://t.me/SheikhJemalZehabi/859 11📚شرح السنة للبربهاري مع شرح شيخ صالح الفوزان حفظه الله https://t.me/SheikhJemalZehabi/944 12📚كتاب التوحيد لشيخ صالح الفوزان حفظه الله https://t.me/SheikhJemalZehabi/1089 13📚محاضرة المتتابعة من كتاب معالم في طريق طلب العلم https://t.me/SheikhJemalZehabi/1080 14📚 نُورُ التَّوحِيدِ وظُلماتُ الشِّركِ في ضَوْءِ الكِتابِ والسُّنَّة https://t.me/SheikhJemalZehabi/1192 15📚 هَذِهِ دَعْوَتُنَا وَعَقِيدَتُنَا https://t.me/SheikhJemalZehabi/1223
في المصطلح الحديث16📚 شرح المنظومة البيقونية https://t.me/SheikhJemalZehabi/340 17📚 تيسير المصطلح https://t.me/SheikhJemalZehabi/419
في الفقه18📚 منهج السالكين https://t.me/SheikhJemalZehabi/1144 📚 19 الفقه الميسر https://t.me/SheikhJemalZehabi/1362
في أصول الفقه20 📚 شرح متن الورقات لشيخ عبد الله بن صالح الفوزان https://t.me/SheikhJemalZehabi/1296 📚 21 شرح نظم الورقات لبن عثيمين https://t.me/SheikhJemalZehabi/1582
تفسير القرآن العظيمእየተቀራ ያለ https://t.me/SheikhJemalZehabi/1705 =ሪከርዶችን በነዚህ ሊንኮች ታገኙታላቹህ 🔗 https://t.me/SheikhJemalZehabi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
* ሰበብ እየፈለገ ሌሎችን ከሱና የሚያስወጣ አካል መጨረሻ ላይ ሌሎችን ባስወጣበት በር ራሱ ይወጣል።
* እወቅ! ሌሎች ላይ የመዘዝከው የኢልዛም ሰይፍ ወዳንተም ይዞራል። እቆርጥበታለሁ ያልከው ይቆርጥሃል።
* ሰለፊያ የወደድከውን የምታስገባበት፣ የጠላሀውን የምታስወጣበት ያ'ባትህ ግቢ አይደለም። ሰለፊያ ኢስላም ማለት እንጂ ሌላ ቡድን አይደለም። ይህንን ከቃላት ባሻገር በተግባር አስረግጥ።
* በዚህ ዘመን በመንሀጅ ስም ተጠቅልሎ ያለው አብዛኛው ጩኸት የአመል ችግር ነው። ያለበለዚያ ሰው እንዴት እስ'ካፍንጫው በተነከረበት ጥፋት ሌሎችን ሊከስ ይደፍራል?
* በሺርክና በቢድዐ መፈረጅ ከሺርክና ከቢድዐ የማስጠንቀቅ ያህል ቀላል አይደለም። ሁለተኛው ላይ ካለህ ትጋት ይልቅ የመጀመሪያውን መድፈርህ መታመምህን ነው የሚያሳየው። ሳይጠናብህ ታከመው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from አህመድ ፈንታቢል
ሙብተድዕ የሆነን ሰዉ ሰላምታ ማቅረብ እንዴት ይታያል?
ሰላምታ ካቀረበልኝ መመለስ እንዴት ይታያል?
መልስ
ቢድዓ ይለያያል
ቢድዓዉ
ከአሏህ ዉጭ ያለ አካል መለመን
ከአሏህ ዉጭ ላለ ማረድ
ከአሏህ ዉጭ ላለ መሳል
ይሄ ኩፍር ነዉ
ይሄ ሰላምታ አይቀረብም
ቢድዓዉ የማያከፍር ከሆነ ሰላምታ ይቀረባል ምክንያቱም ሙስሊም ከመሆን አልተወገደም
መራቁ ሰላም አለማለቱ ከቢድዓ ከወንጀል ይርቃል ተብሎ ከታሰበ በዚህ ነገር ላይ ተፅእኖ ይወድቃል እስኪ ቶብት ድረስ ተብሎ ከታሰበ
ይሄ መራቁ ሰላምታ አለማቅረቡ ወይም ሰላምታ አለመመለሱ ችግር ይለዉም
👇👇👇
https://t.me/HuzeyfaAhmed
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
.....ፅኑዎች ሆይ አብሽሩ
-----------------------
የዉስጥን ስቃይ ባለቤቱ ብቻ ያዉቀዋል....
በሕይወት ጎዳና ላይ ስንጓዝ ሁላችንም የራሳችን የሆነ ከባድ ደመና ከራሳችን በላይ ያንዣብባል ብዙ የሀሳብና የህፀፅ አበባወችም የሲቃ እንባ ጠጥቶ ያፈራል።
አንዳንዴ እንዚህ ነው የህይወት ገመና፡
የጨለማ ጉዞ የስቃይ ደመና፡
ሁሉም ነገር ከንቱ ሁሉም ነገር መና፡
....ግና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች
የዝናቡን መዉረድ እንጂ... ያ ዝናብ በዉስጣችን የሚፈጥረውን
ቅዝቃዜና የሚቀሰቅሰዉን ትዝታ ፊጽሞ ሊረዱት አይችሉም።
ብዙ ጊዜ ሰዎችን የምንፈርደዉ በምናየው ዉጫዊ ገጽታቸው
ብቻ ነው።
"እሱ/እሷ ምን ይጎድላቸዋል!?" እንላለን።
.......ነገር ግን ከጥሩ ልብሶች፣
ከሚያምሩ ፈገግታዎች እና ከቀን ተቀን
እንቅስቃሴዎች ጀርባ የሚደበቁ ስንት የተሰበሩ ልቦች አሉ⁉️
ስንት የሚደሙ ነፍሳትስ አሉ⁉️
👉ሕመም የምሰማው ለቆሰለዉ ሰው ብቻ ነው።
ሌላው ሰው ሊያዝንልህ፣
ሊያጽናናህ ወይም ሊራራልህ ይችላል፤
ነገር ግን
በጨለማ ክፍል ዉስጥ ብቻህን የምታፈሰዉን የእንባ ዘለላ ትክክለኛ ክብደት ሊሰማው አይችልም።
ያንተን ጫማ ተጭቶ
ያልተጓዘ ሰው፣ መንገድህ ምን ያህል አሰቃቂ እንደነበረ ሊረዳ አይችልም።
የሚያስለቅስህ ነገር ለሌላው ሰው ቀላል መስሎ ሊተይ
ይችላል። "ለዚህ ነገር ነው የምታለቅሰው?" ሊሉህ ይችላሉ።
ምክንያቱም እነሱ የሚያዩት የወደቀውን ጃንጥላና የራሰዉን መሬት
ብቻ ነው፤ በልብህ ዉስጥ የፈረሰውን ዓለም አያዩትም።
.....ነገር ግን ማስታወስ ያለብህ አንድ ታላቅ እዉነት አለ፦
ይህ በእንባ የራሰ መንገድ፣
ይሄ ብቻህን የተሸከምከዉ ከባድ
ደመና ለዘላለም አይኖርም።
አሁን የምታሳልፈው ስቃይ
ጥንካሬህን የምትገነባበት፣
የነገ ማንነትህን የምታንጽበት ነበልባል እሳት ነው።
👉ማንም ባይረዳህ እንኳ፣ የራስህን ሕመም በራስህ ጽናት አክመህ እንደምትነሳ እመን።
"የቁስሉ ሕመም የሚያዉቀዉ ባለቤቱ ብቻ ቢሆንም፣ ከሕመሙ
በኋላ የሚመጣውን ብርሃንና ጥንካሬ የሚያጣጥመዉም ያው
የጸናው ልብ ብቻ ነዉ።"
«አሏህ ሆይ በመከራ ለፀኑ ልቦች ፈረጃውን አቅርቦላቸው አሚን።»
....ኑር....✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ወላጆችህን ከቻልክ አቅምህ በሚፈቅደው አስደስታቸው። ካልሆነልህ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የመከፋታቸው፣ የመጨነቃቸው፣ የመተከዛቸው ሰበብ አትሁን። "አይዟችሁ"፣ "ከጎናችሁ ነኝ" ማለት ቢቀር "አትስጉ፣ ደህና ነኝ" ማለት ልናሳጣቸው አይገባም። ሰርቶ ማገዝ፣ ከጎን መቆም ካቃተ፣ ፊትን ከመከስከስ፣ የሻከረ ቃል ከመናገር መቆጠብ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
Repost from تَحْتَ ظِلِّ الْعَرْش
◾️በውስጡ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔻የሀዳድዮች ባህርይና አደገኝነት
🔻ሀዳድዮች ከሌላው የሚለያቸው
🔻ሀዳድዮች ሸኽ ረቢእን ለምን አምረው ይጠላሉ?
👉አጭር ቆይታ ከሸኽ ረቢእ ጋር
🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ናፈቀኝ ገጠሩ፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ጎራው ሸንተረሩ፤
👉ያደኩበት ሀገር ናፈቀኝ መንደሩ፤
👉የተጫወትንበት ያ የ ድንጋይ ቤቱ፤
👉ናፈቀኝ እቃቃው ያየጭቃ ድስቱ፤
👉ያ የድንጋይ ምጣድ የቅጠል እንጀራ፤
👉በጭቃው ጀበና በጠጠሩ ሲኒ
ቡና ጠጡ ብለን ጎረቤትት ስንጠራ፤
👉ቅጠሉን ጎዝጉዘን አርሂቡ ኑ ብለን፤
👉ቡናውንም ቀድተን ቁርሱንም አድለን፤
👉ያኔ ያ ጫወታ የቀልድ ቢሆንም፤
👉ልዩ #ትውስታ አለው ያለፈ ቢሆንም፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ያ የቦረኩበት፤
👉ያ የወንዝ ውሀ የተራጨንበት፤
👉ቦይ እያበጀን የተጫወትንበት፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ሜዳው ሸንተረሩ፤
👉ሲጠማን ጠጥተን፣
👉የዱር ፍሬበልተን፣
👉ዳቦው ተገመሰ፣
👉ጫወታው ፈረሰ፣
👉ብለን ተባብለን ልክ ስንለያይ፤
👉እንሸኛኝ ነበር ተባብለን ባይባይ፤
👉በደህና እንገናኝ ደህና እደሩ፤
👉ምጣዱ ተሰብሮ ሳትበሉ እደሩ፤
👉የቅጠሉን ጫማ እግራችን ጠምጥመን፤
👉ዱፍ ዱፍ እያልን ስንሄድ ሰልፍ ይዘን፤
👉ያየን ሰው ሁሉ በኛ ሲስቅብን፤
👉ትንንሽእንደሄድን ቁርጥርጥ ሲልብን፤
👉ውሀ ሂዶ ሂዶ ጭረቻው ቀሪ ነው፤
👉ትዝታውን ትቶ ቀን ሁሉ ዘማች ነው፤
👉የወፎቹ ጩኸት ቀዝቃዛው አየሩ፤
👉ሰላሙ የሚያምር ሰው ገራገሩ፤
👉ናፈቀኝ ሀገሬ ሜዳው ሸንተረሩ፤
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
1⃣3⃣ የኢርጃዕ በሽታ አለባችሁ ትሉን አላችሁ ኡዙር የሰጡትን አሊሞች ለምንድነው የማትሏቸው?? አሊሞች የራሳቸው ነው መስዐላው።ኡለማወች እና ከታች ያሉት ተመሳሳይ ባህሪ የላቸውም።
⬇️⬇️
✅ t.me/Umu_Reyan_channel_No1/4007
1⃣4⃣ አህባሽን ተከትለህ አትስገድ አይባልም ፣
አንድን ሰው ካፊር ማለት ባህር ነው
✅ t.me/Multeka_Selefiyin/15716
1⃣5⃣ ለሙስጠፋ ዐብደላህ የቤት ኪራይ የምትችል ሴት ሲፈልጉ
⬇️⬇️
✅ t.me/Abu_lmran_Alaseriy/1892
1⃣6⃣ ኡዝር አለ የሚልበት የተክ^ፊሩ መንጋ -
የተክፊርዮች ቃኢዳ ነው ሀዛ ቃኢደቱል ሀዳዲይን ከዚህ እኛ የጠራን ነን
⬇️⬇️
✅ t.me/Umu_Reyan_channel_No1/4457
1⃣7⃣☑ የተክ^ፊሩ መንጋ - ሸይኽ ሙንተቂል
"አዕምሮው የተጠቀለለበት!!"ገልባጤ ኡዙር የለም ያለበት የድምፅ ፋይል
⬇️⬇️
✅ t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3109
1⃣8⃣ በመጨረሻም:-በኡዙር ቢል ጀህል ዙሪያ
ኡስታዝ አቡኢምራን መልስ የሰጠባቸውን
በአስር ክፍሎች የተዘጋቹ የድምፅ ፋይሎችን አጋራችሁአለሁ ። ምራቻን የፈለገ ለሆነ ሰው አላህ :መመራትን ይወፍቀው።
ሀቅን የፈለገ የሆነ ሰው ኦዶዎችን በደንብ ያዳምጥ ።ተአሱብነት አይወጥራችሁ ሀቅን እንጂ ሰው አትከተሉ። 🎙ዑዝር ቢል'ጀህል ተከታታይ ሙሐደራ፦ለማገኘት የሚቀጥለውን ሊንክ ጠቅ ያርጉ
⬇️
✅ t.me/Abu_lmran_Alaseriy/2090
1⃣9⃣ ዑዝር ቢል ጀህል በሸይኽ ሙሐመድ አማን አል'ጃሚይ ረሒመሁላሁ ተዓላ
⬇️
✅ t.me/Abu_lmran_Alaseriy/2818
2⃣0⃣📱ኡስታዝ አቡ ዒምራን አሏህ ይጠብቀው እና ስለ ዑዙር ቢል ጀህል ሸይኽ ፈውዛን ተጠይቀው መልስ የሰጡበት በፅሁፍ ማብራሪያ የሰጠበትን ማንበብ ከፈለጋችሁ
⬇️
🌐 t.me/Multeka_Selefiyin/16152
2⃣1⃣ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ
⬇️⬇️
1⃣ t.me/IbnuMunewor/5230
2⃣ t.me/IbnuMunewor/4685
3⃣ t.me/IbnuMunewor/2608
4⃣ t.me/IbnuMunewor/2042
5⃣ t.me/IbnuMunewor/7622
6⃣ t.me/IbnuMunewor/7623
