ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

前往频道在 Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

显示更多
未指定国家未指定类别
318
订阅者
-424 小时
-77 天
+5430 天
帖子存档
👑እማዬ የኔ ጨረቃ👑 🎉እናት ማለት ለልጇ ስትል ራሷን የምትሰዋ ልብ ናት። በእርግዝና የተሸከመችን ሸክም ተቋቁማ በምጥ ህመም ወልዳን ከዚያም በእንቅልፍ ማጣት በድካም በስጋት እና በትዕግስት አሳደገችን። አላህ ﷻ ስለ ወላጆች በተለይም ስለ እናት ያሳለፈችውን መከራ አስታውሶናል፦ ﴿حَمَلَتْهُ أُمُّهُ كُرْهًا وَوَضَعَتْهُ كُرْهًا﴾ “እናቱ በችግር ተሸክማው በችግርም ወለደችው።” [አል-አሕቃፍ 15] 🌷እናት ስትራብ ልጇን ታስቀድማለች። ስትደክም ልጇን ታሳርፋለች። ልጇ ሲታመም እንቅልፏን ትታ ትንከባከበዋለች። በራሷ ላይ ያለውን ችግር ተሸክማ ለልጇ ደስታን ትመኛለች። ለዚህም ነው ረሱል ﷺ እናትን ማክበር በተለየ መልኩ ያስተማሩን። አንድ ሰው “ከሰዎች መካከል ለመልካም አጠባበቅ በጣም የሚገባው ማነው?” ብሎ ሲጠይቃቸው ረሱል ﷺ “እናትህ” አሉ። እንደገናም “እናትህ” አሉ። ሶስተኛ ጊዜም “እናትህ” አሉ። ከዚያም “አባትህ” አሉ። ስለዚህ እናትህ በሕይወት እያለች ዕድሉን ተጠቀም። ቃልህን አሳምርላት። አትጩኽባት። አትናቃት። አግዛት። ዱዓ አድርግላት። ﴿وَقُلْ رَبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا﴾ “ጌታዬ ሆይ በልጅነቴ እንዳሳደጉኝ ሁለቱንም ማርላቸው በላቸው።” 🤲🏻 እናት አላህ የሰጠህ ታላቅ ኒዕማ ናት። ኒዕማውን ከማጣትህ በፊት ዋጋውን እወቅ። ለውድ እናቶቻችን ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን የሞቱትንም አላህ ይማርልን ያረብ🤲 t.me/qdemiy_letwuhide

«ዲነኛዋን አግባ» በማንኛውም ጉዳይ ከስሜታችን ይልቅ የረሱልንﷺ ትዕዛዝ ብናስቀድም ኑሮ እንዴት ያለ ደስተኛ ህይወት መኖር በቻልን ነበር። ብዙ ጊዜ ግን ወንዶች የትዳር አጋር ምርጫ ላይ ውጫዊ ውበት ላይ ብቻ በማተኮር፣ አንዳንዴም የቤተሰብን ምርጫ ተቀዳሚ በማድረግ ከባድ ስህተት እንፈፅማለን። በዚህም የተነሳ እረፍት እናገኝበታለን ያልነው ትዳር ይበልጥ ፈተና ይሆንና የተመሰቃቀለ ህይወት ለመግፋት እንገደዳለን። በጣም የሚደንቀው ደግሞ በሌሎች ስህተት አለመማራችንና ህይወታችንን ቤተ ሙከራ ማድረጋችን ነው። ወንዶችየ ምናልባት ከሰማቹህኝ ልምከራቹህ "የረሱልንﷺ ትዕዛዝ አክብርና ዲነኛዋን አግባ" ሰላም ታገኛለህ። ትዳር ትልቅ የህይወት አዳራሽ ነውና በምርጫና በውሳኔህ መስመር ስተህ፣ አላስፈላጊ ዋጋ ከመክፈልህ በፊት ቆም ብለህ አስብ። ወንድማዊ ምክሬ ነው። فَاظْفَرْ بِذَاتِ الدِّينِ تَرِبَتْ يَدَاكَ = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

مَاتُوا وَعِشْنَا فهُم عَاشُوا بِمَوْتِهمُ وَنَحْنُ__في صُوَرِ الأَحْيَاءِ أَمْوَاتُ

ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ዱዐ የሚያደርግላቸው ሷሊሕ ልጅ ትተው አላለፉም። ነገር ግን ዱዐ የሚያደርግላቸው ብዙ ህዝብ ጥለው ነው የሞቱት። ረሒመሁላህ ረሕመተን ዋሲ0ህ! ደረጃቸውን ከፍ ያድርግላቸው። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

«አንተ አቡል ዐስ ሆይ፤ ለመሆኑ የእኛ መለያየት እንዲህ ቀለለህ?» አለችው... ይህች ቃል የነብዩ(ﷺ) ውድ ልጅ ዘይነብ፣ ለትዳር አጋሯ ለአቡል ዐስ ኢብኑ ረቢዕ የሰነዘረችው የናፍቆት ቃል ናት። የ
«አንተ አቡል ዐስ ሆይ፤ ለመሆኑ የእኛ መለያየት እንዲህ ቀለለህ?» አለችው... ይህች ቃል የነብዩ(ﷺ) ውድ ልጅ ዘይነብ፣ ለትዳር አጋሯ ለአቡል ዐስ ኢብኑ ረቢዕ የሰነዘረችው የናፍቆት ቃል ናት። የዘይነብ የሞት ሰዓት ሲቃረብ፣የአቡል ዐስ ዓለም በድቅድቅ ጨለማ ተዋጠ። የምድር ሕይወት ትርጉም አጥታ ታየችው። ሞቷን ሲሰማ የመነጨው ከባድ ለቅሶና ጩኸት፣ ልቡ ውስጥ የነበረውን ጥልቅ ፍቅርና የደረሰበትን የውስጥ ስብራት የሚያሳይ ነበር። ያዩትን ሁሉ የሚያዝኑት ታላቁ ነብይ (ﷺ) በአማቻቸው ከባድ ስቃይ ልባቸው ተነክቶ፣ በሩህሩህ እጃቸው እየዳበሱ ሊያፅናኑት ሞከሩ። እርሱ ግን እንባው እየጎረፈ፣ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለ፦«ወላሂ አንተ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ያለ ዘይነብ ይህችን ዱንያ መኖር አልችልባትም!» አላቸው። በእርግጥም ያለ እርሷ መኖር አልቻለም። የልብ ስብራት፣ የናፍቆት እሳትና የፍቅር ቁስል ሰውነቱን ቀስ በቀስ አደከመው። ዘይነብ በሞተች በዓመቱ፣ እርሱም ይህችን ዓለም ተሰናብቶ ተከተላት። ◈ምን ማለት ፈልጌ መሰላችሁ...በፍቅር መጎዳትንና የመለያየትን ስቃይ መቼም ቢሆን ቀላል አድርገን ልንመለከተው አይገባም።ቀስ በቀስ ሰውን የሚያደክም፣ አልፎ ተርፎም ለህልፈት የሚዳርግ ኃይል አለው። አላህ በሃላሉ ያብቃቃችሁ! -- t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

ሰላሃዲን አል-አዩቢ ለምን የመስቀል ጦረኞችን አትዋጋም ሲባል " ጀርባዬን ለሺአ አጋልጬ የውጭ ጠላትን አልዋጋም!" ነበር መልሱ። ምክንያቱም ሺአዎች ከነ ቀንዘላቸው ምድርን ከረገጡ ሴረኛ እና ተንኮለ
ሰላሃዲን አል-አዩቢ ለምን የመስቀል ጦረኞችን አትዋጋም ሲባል " ጀርባዬን ለሺአ አጋልጬ የውጭ ጠላትን አልዋጋም!" ነበር መልሱ። ምክንያቱም ሺአዎች ከነ ቀንዘላቸው ምድርን ከረገጡ ሴረኛ እና ተንኮለኛ ፍጥረታት ቁንጮዎቹ መሆናቸውን ጠንቅቆ ገብቶታል። ኢስላምን ከውስጥ ሆኖ ለመጣል ከደጃል ጋር እንደሚያብሩ ጠንቅቆ ያውቀዋል! በግዜያችን የኢራቅ፣ የየመን፤ የሊብያ፣ የሶርያ፣ የአፍጋኒስታን መውደም የሺአዎች እንብርት ኢራን እጅ ከፍተኛ ነው። እያንዳንዱን ሀገራት ሲያፈርሱ አሜሪካ እስራኤ እና ኢራን እጅ እና ጓንት ነበሩ! የአሁኑም ግዜ የጦር አላማቸው መካ ነው! ሁለቱን ሀረመይኖችን (ካእባን እና የነብዩን መስጅድ) መካ እና መዲናን ማወድም። ከአሁን ቀደም እንዳደረጉት ሰጋጆችን መጨፍጨፍ፣ እንደ ሀጀረል አስወድ ያሉ ቅዱስ ነገራቶችን ማራከስ! ይኸው በራሳቸው አንደበት👆👆

ما لا يُنالُ بالأسباب يُنال بالدُعاء...

ስናድግ ዝምታም አብሮን ያድጋል። ለሰዎች ከምናወራው በበለጠ ወደውስጥ የምናወራው መብዛት ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የምንመላለሰው የውይይት ሀሳቦች መሀል የሚገራርሙ መመሰጦች ውስጥ እንገባለን። የመገለል ፍላጎት ይቆጣጠረናል። ለብቻ የመሆን። ብዙም ቅልቅል አለመውደድ። ጥሩ ስሜት አለው። ከነዚህ ምልልሶች  ባሻገር ግንኙነትህን ሚያስውቡ  ስሜትህን ሚያዳምጡ ዲንህ ላይ ጥንካሬ ሚሰጡህ ውብ ሰዎች አሉ አላህ ይጠብቃቸው

⭕️👉ለውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ አፍያ ያድርገውና አድርሱልኝ።✅             <<አንተን ክፉ አይንካህ>> የነብያት ወራሽ ዳዒ ነህ ታታሪ፤ የኢስላም ወታደር ባጢል አባራሪ። የሱና ሳተና የቢዲዓ ጠላት፤ በሁጃ ተውበህ ሀቅን ያፀናሀት፤ ባጢልን አባረህ አጭደህ የወቃሀት። በእኔ ጭልፍ ሆሄ በአጭር አማረኛ፤ ሊደርስህ ባይችልም ተራ ፈረሰኛ፤ ላንጎራጉር ብየ እንደመንገደኛ፤ ሲሰማኝ ቋጠርኳት ከውስጤ ማደኛ። የኔ ጀግና ብየ ባወሳህ አልጠግብም፤ አንበሰና ነህ ብልህ አንጀቴ አይገግብም። የሀበሻው ኮከብ ስጦታው ይደንቃል፤ በማራኪ አንደበት ዒልምን ያስታጥቃል ። #አህባሽ ግሳንግሱ ብቅ ሲል ሀበሻ፤ በሎጅክ ለማጥመቅ ሲያሳጣ መድረሻ፤ ወገቡን ሰበረው በሁጃ መዶሻ። ተዕዊል እና ተዕጢል አንግቦ በውስጡ፤ ሹብሀ እየነዙ ምድር ሲቀውጡ፤ የሱናን ሰው ጠልተው ከሀገር ሲያስወጡ፤ ሲያስገርፉ አሳስረው ዋሽተው ሲያናውጡ። የነብዩን መንገድ ገርሳሹ ሲበዛ፤ ውሸትን ተዋጋው ቆልቶት እየነዛ፤ ቁርአን ሀድስን ከሰለፎች መቅጃ፤ ኢጅማዕን አስፍሮ አጣቅሶ ማስረጃ፤ አበረከተልን ሹብሀን ማስወገጃ፤ ጀግናው የኔ ዑስታዝ ድንቅ ኢብኑ ሙነወር፤ ኢላማው አይስትም ሁጃው ሲወረወር። ሱፍያን፣አህባሽን ድባቅ ያስገባቸው፤ ከአርሹ በላይነው ብሎ ፃፈባቸው። የአህባሾች መሪ "ሀሰን ታጁ" ሲዋሽ፤ ከኢኽዋኖች መጥቶ  በመውሊድን ሲቀረሽ፤ እርምት አረገበት የታሪኩን ግድፈት፤ በማስረጃ አድርጎ ውሸትን ቀበራት። በሱና ስም ሰርገው ፊልም ለሚሰሩ፤ ተገቢ ያልሆነን ተግባር ላሰመሩ፤ አደብ አስያዛቸው በውብ መነፀሩ። ሀጃዊራ ዘልቃ ያለ አግባብ ስትቀረሽ፤ የሁጃ ጦር ስሎ በደሊሉ ጥንቅሽ። አልበያንን ከትቦ እያሰጣ ቀንጣሽ፤ ከታላላቆቹ ማስረጃን አጣቃሽ፤ አንተኮ ነህ ጀግናእውነትን አስታዋሽ። አካሄዱ በሳል ንግግሩ ቁጥብ፤ ምክሩ አንጀት አርስ ነው ልብን የሚያረጥብ፤ በምን ፊደል ላውሳው በምን ቃላት ነጥብ፤ ብቻ ማር ያዘንባል ጀግና ነው እንደ ንብ። ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ፤ ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ፤ ወዳሴም አይሻ የማንንም ታርጋ፤ አፉን የለጎመው የለተሞን መንጋ፤ ያላግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ፤ ድምፅ ባለው ፅሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ፤ የሙነወር ልጅ ነው የባጢል አለንጋ ፤፦ የተክፊርን ቅሪት ወገቡን የቀጨው፤ በአንድ ንግግሩ መንጋውን ያጋጨው፤ አንድ ኳስ ወርውሮ "ሽ" ያነጫነጨው። ለሀቅ ዘብ ቆሞ ለፍትህ የሚኖር፤ ለሱና ኻድም ነው የኢስላም መምህር። ልክ እንደ ፔንዱለም ፊትና ሲያናውጠን፤ ድንገት ተከስቶ አካቦ ሲውጠን፤ ፈጥነህ በመመከት እረፍት የምሰጠን። አላህ ይጠብቅህ ከመከራ ከጭንቅ፤ ከሴረኞች ተንኮል ከአይሁድ ከሙናፊቅ። ሻፊ ነው ጌታችን በቶሎ ያሽርህ፤ ወንጀልክን አብሶ በኸይር ያበሽርህ። የአንተን ሀላፊነት የለም የሚተካህ፤ የሀበሻው ኮኮብ አንተን ክፉ አይንካህ። ✍بقلم أبي شورى أحمد https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ~ እንዴት ናችሁ ወንድሞች እህቶች? ሰሞኑን ከደርስ የራቅኩት ባለቤቴ በወሊድ ምክንያት ሆስፒታል ገብታ ስለነበር ነው። ማታ ከመግሪብ በኋላ በሰላም ወደ ቤት ገብተናል አልሐምዱ ሊላህ። ደርስ እየገባሁ ያልነበረው ከቤት ራቅ ስላልኩ በሚመች ሁኔታ ላይ ስላልነበርኩ ነው እንጂ ህመሜ ተመልሶብኝ አይደለም። ያሰባችሁልኝ በሙሉ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን። አላህ ከክፉ ይጠብቃችሁ። አሁንም ጠንከር ያለ ጉንፋን ድምፄን ስለዘጋኝ ምናልባት ለውጥ ከሌለኝ ጥቂት ተጨማሪ ቀናት ላልገባ እችላለሁ። እናንተን የሰጠኝ ጌታ አልሐምዱ ሊላህ። ጁዚቱም ኸይረን፣ ወኩፊቱም ሸረን። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

رَبِّي إِنَّهُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ، خَيْرُ الْأَيَّام عِنْدَكَ, فَاكْتُبْ لَنَا الْخَيْرَ فِيهِ، وَأَسْعِدْ قُلُوبَنَا، وَيَسِّرْ لَنَا أُمُورَنَا كُلَّهَا يَا اللَّهُ. ጌታዬ ሆይ! ይህ የጁምዓ ቀን ነው፤ አንተ ዘንድ ከቀናት ሁሉ በላጩ ነው። ስለዚህ በውስጡ ለእኛ መልካሙን ጻፍልን፤ ልቦቻችንንም አስደስት፤ ጉዳዮቻችንንም በሙሉ አግራራልን ያ አላህ። የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

عِيشُوا مَا شِئْتُمْ فَإِنَّكُمْ مَيِّتُونَ، وَأَحِبُّوا مَنْ شِئْتُمْ فَإِنَّكُمْ مُفَارِقُوهُ، وَاعْمَلُوا مَا شِئْتُمْ فَإِنَّكُمْ مَجْزِيُّونَ بِهِ. የፈለጋችሁትን ያህል ዘመን ኑሩ #ሟቾች ናችሁ። የፈለጋችሁትን ሰው ውደዱ #ትለዩታላችሁ። የፈለጋችሁትንም ስራ ስሩ፤ #ትመነዱበታላችሁ። የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/DeewaSelefyya1448 https://t.me/DeewaSelefyya1448

~የተውሒድ መምህር......!      ~ ተውሒድን እንዳትሰብክ  ኡማው አልተስማም፡ ሽርክን ተውሒድ አርጓል ድምፅህ አይሰማም፡ በአርሶ አደሩ ክልል በሚያርቀው ሞፈር፡ ተውሒድ አሥተምረን ናማ በኛ ሰፈር፡ ወይ ደግሞ ላኩልን የተውሒድ መምህር፡ copi   

እንቁጣጣሽ ማን አመጣሽ❓ 🔭 "ጳጉሜ" የሚለው ቃል "ኤጳጉሚኖስ" ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ "ተጨማሪ" ወይም "የተጨመረ" ማለት ነው። 🔜 ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው። 🔜 ይህም ወር በነሐሴ እና በመስከረም መካከል የሚገኝ የመጨረሻው ወር ነው። 🔜 ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዘመነ ዮሐንስ ስድስት ቀናት ሲኖሩት በዘመነ ሉቃስ ዘመነ-ማቴዎስ እና በዘመነ -ማርቆስ ደግሞ አምስት ቀናት ይሆናል። 🔜 ልብ በሉ ይህ ወር ከግሪክ ሄለኒዝም ጊዜ ከአሌክሳንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እንጂ በዕብራውያን አቆጣጠር ላይ 12 ወራት ብቻ ነው ያለው። ♻️ አላህም የወሮች ቁጥር በእርሱ መጽሐፍ በለውሀል መህፉዝ ማለትም በጥብቁ ሰሌዳ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው፦ 📖 قال الله تعلى:- ﴿ ﺇِﻥَّ ﻋِﺪَّﺓَ ﭐﻟﺸُّﻬُﻮﺭِ ﻋِﻨﺪَ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﭐﺛْﻨَﺎ ﻋَﺸَﺮَ ﺷَﻬْﺮًۭﺍ ﻓِﻰ ﻛِﺘَٰﺐِ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﻳَﻮْﻡَ ﺧَﻠَﻖَ ﭐﻟﺴَّﻤَٰﻮَٰﺕِ ﻭَﭐﻟْﺄَﺭْﺽَ ﻣِﻨْﻬَﺂ ﺃَﺭْﺑَﻌَﺔٌ ﺣُﺮُﻡٌۭ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﭐﻟﺪِّﻳﻦُ ﭐﻟْﻘَﻴِّﻢُ ۚ ﻓَﻠَﺎ ﺗَﻈْﻠِﻤُﻮﺍ۟ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﺃَﻧﻔُﺴَﻜُﻢْ ۚ ﻭَﻗَٰﺘِﻠُﻮﺍ۟ ﭐﻟْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ ﻛَﺂﻓَّﺔًۭ ﻛَﻤَﺎ ﻳُﻘَٰﺘِﻠُﻮﻧَﻜُﻢْ ﻛَﺂﻓَّﺔًۭ ۚ ﻭَﭐﻋْﻠَﻤُﻮٓﺍ۟ ﺃَﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﻣَﻊَ ﭐﻟْﻤُﺘَّﻘِﻴﻦَ ﴾ سورة التوبة [ 9:36] 📖  አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን  አሥራ  ሁለት # ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤ [ሱረቱ ተውባህ 9፥36] 🔜 ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያው ዘመን መለወጫ በልምድ ከግሪክ የመጣ ሰርጎገብ እንጂ አገር በቀል አይደለም። 🔜 ከዚያም ባሻገር መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ሳይሆን ሰው ሰራሽ ቢድዓ ነው ዓመተ-ምህረትን ያማከለ ዘመነ-ሉቃስ ዘመነ-ዮሐንስ ዘመነ-ማቴዎስ እና ዘመነ -ማርቆስ ሰው ሰራሽ ትምህርት ነው። ♻️ በዛ ላይ የባእድ አምልኮ የሚፈፀምበት ቀን ነው። 🔭 በጳጉሜ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች ዶሮዎች ድመቶች ጥንቸሎች ወዘተ... ታርደው ይጣላሉ። 🔜 በደም የተነከሩ ሳንቲሞች ብሮች ጌጣ-ጌጦች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ♻️ ይህ ቀን ሲያልቅ የቀኑ መጨረሻ በጉጉት ስለሚጠበቅ "እንቁ" ተባለ። ♻️ የሚያመጣው ጣጣና መዘዝ ደግሞ "ጣጣሽ" ተባለ በጥቅሉ "እንቁ-ጣጣሽ" ተባለ። 📌 ጥንቆላና ድግምት ከትልቁ ሽርክ የሚመደቡ የፈጣሪያችንን የአላህን ሃቅ የሚነካ ትልቅ በደል ነው። 📖 قال الله تعلى:- ﴿ واتبعوا ما تتلو الشياطين على ملك سليمان وما كفر سليمان ولكن الشياطين كفروا يعلمون الناس السحر وما أنزل على الملكين ببابل هاروت وماروت وما يعلمان من أحد حتى يقولا إنما نحن فتنة فلا تكفر فيتعلمون منهما ما يفرقون به بين المرء وزوجه وما هم بضارين به من أحد إلا بإذن الله ويتعلمون ما يضرهم ولا ينفعهم ولقد علموا لمن اشتراه ما له في الآخرة من خلاق ولبئس ما شروا به أنفسهم لو كانوا يعلمون ﴾ . سورة البقرة [2:96] 📖 አላህም እንዲህ አለ:- በነብዩ ሱለይማን (ዐለይሂሰላም) ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም ድግምት ተከተሉ ሱለይማን ግን አልካደም ድግምተኛ አልነበረምና ግን ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ..... 📖 قال الله تعلى:- ﴿ قال فإنا قد فتنا قومك من بعدك وأضلهم السامري ﴾ سورة طه [20:69] 📖 አላህም እንዲህ አለ:- ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም አልን  ይላል። ሱረቱ ጧሀ [20፥69] 📌 እንቁጣጣሽን ማክበር አቆጣጠሩ አገራዊ ሳይሆን እምነታዊና ባህላዊ መሰረት ያለው ሲሆን ከእርሱ ጋር የተያያዙት ባእድ አምልኮ አስበን ከዚህ ሰው ሰራሽ በአል እራሳችንን እንጠብቅ። የተወሰደ

«ትላንትም ዛሬም ጀግናዬ ነህ» «ሳዳት ከማል» ምንም ቢፈራረቅ ክረምትና በጋ፡ ቢመች ባይመች ቢደቀን አደጋ፡ ሳዳት አቋሙ ላይ ቆሟል እንደረጋ፡ የሒዝብያ መንጋ ሁሌ ሲሽመደመድ፡ አንተ ግን በፅናት ኸደፊት ተራመድ፡ ጨብጠሀልና የሱናውን ገመድ፡ በተቻለው አቅም የነብያት ወራሽ፡ ያወቃትን እውነት ሐቋን ለህዝብ አድራሽ፡ ድሽቃ ነው ቃላቱ ሒዝብዮችን አፍራሽ፡ መረጃውን ታጥቆ በሚናገረው ቃል፡ በሳዳት ንግግር ስንት አሳብ ይወድቃል፡ አሏህ አመላክቶት የኢስላምን ዳና፡ ሰበብ ሆኖልናል ለተውሒድ ጎዳና፡ ደግሞ በፊትና ወቅት ስንቱ ሲጉረመረም፡ ስንቱ በሆይሆይታ በጥመት ሲፈረም፡ ሳዳት ጀግኖቹ ጋር አቋም አልቀየረም፡ ከትላንት አቋሙ ያልተነቃነቀ፡ ተውሒድና ሱናን ሐቁን የሰነቀ፡ ስሜት ተከትሎ እውነትን ያልናቀ፡ ዛሬም በተውሒድ ላይ ተውቦ እንዳማረ፡ የሚያውቃትን እውነት ፀንቶ ያስተማረ፡ አሉባልታ ወሬ የማያሸንፈው፡ ጥመት ተመልክቶ ፈፅሞ እማያልፈው፡ ሰወች በሌለበት ስሙን ቢያጠፉትም፡ ሱና ነው አላማው ከኋላም ከፊትም፡ ሳዳት በሐቅ ላይ አይዘባበትም፡ ስንቱ ጀግና ነኝ ባይ ሲገባ አሰንሰራ፡ በወሬኞች አለም ተግቶ የሚሰራ፡ ጀግናችን ነው እሱ የብርሀን ጮራ፡ አለ እየተታገለ በተውሒድ ጂማሬ፡ አንድ ነው አቋሙ ትላንትናም ዛሬ፡ እወቁት ይሔ ነው የኔ መምህሬ፡ በንፁህ ልብ ላይ ተውሒድ የሚዘራ፡ አንገቱን ሳይደፋ ታጥፎ እንደ ከዘራ፡ ሒዝብያ ቢገፋው የማይገፈተር፡ ቀድሞ የታጠቀ የሱና ድሞፍተር፡ ንፁህ የሱና-ዘብ ጀግና ነው ለሚያውቀው፡ ለዛም ነው ጥመትን የሚያስጠነቅቀው፡ ይህን ውድ ታጋይ አሏህ ይጠብቀው፡ ከተውሒድ መስመር ላይ የሌለበት ክዳት፡ ያምራል በገባው ልክ ሱናን ሲያሰናዳት፡ ንፁህ አብሪ ኮከብ ጀግናዬ ነው ሳዳት። በቅርበት ለሚያውቀው ፈፅሞ አያስፈራም፡ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ለሰከንድ አይኮራም፡ ሰውን ለሐቅ እንጂ ለጥመት አይጠራም፡ ግን ሲወነጂሉት እጂጉን ይገርማል፡ ብዙ መሀይማን ሲከሱት ይሰማል፡ ከሚሉት ግን ጠርቷል ዳዒ ሳዳት ከማል፡ «ትላንትም ዛሬም ጀግናዬ ነህ» «በኑረዲን አል አረብ» http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

ኢላሂ!.... በቀን አሰጨንቆ - በሀሳብ የሚያስጉዘኝ በሌሊት ቀስቅሶ - እንቅልፍ የሚነሳኝ ችግርና ጭንቀቴን - ኢላሂ ታውቃለህ ደስታዬን ለግሰኝ - ሀዘን በቃህ ብለህ ያረቢ!... አንጀቴ ቢላወስ - አልችል ቢለኝ ሆዴ ልቤ ደስታ ቢያጣ - ስብርብር ቢል ክንዴ ብትንንትን ብሎብኝ - ባይሳካ ህልሜ ያ... ረቢ! እላለሁ  -  ደግሜ ደጋግሜ ያወዱድ!... ስሞችህን ልጥራ - ደግሜ ደግሜ ኢላሂ!.... ልበልህ - ሁሌ ደጋግሜ ያረሂም! ልበልክ - ሁሌም እንዳቅሜ ፈውስ እንዲሆነኝ - ላልሻረው ህመሜ t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ነፍሴ ሆይ እንዴት አስቻለሽ!? ነፍሴ ሆይ! ጌታችን አላህ በሌሊቱ አንድ ሦስተኛው ክፍል ላይ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወርዶ "የሚጠራኝ—አቤት የምለው፤ የሚጠይቀኝ የምሰጠው፤ ምህረትን የሚከጅል—ይቅር የምለ
ነፍሴ ሆይ እንዴት አስቻለሽ!?
ነፍሴ ሆይ! ጌታችን አላህ በሌሊቱ አንድ ሦስተኛው ክፍል ላይ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወርዶ "የሚጠራኝ—አቤት የምለው፤ የሚጠይቀኝ የምሰጠው፤ ምህረትን የሚከጅል—ይቅር የምለው" እያለ ሲጣራ እንዴት አስቻለሽ? እንደምንስ ተኛሽ!?   እንደ ምንስ ብርድ ልብሱ ሞቀሽ። ለጌታሽ አቤት ማለት ከበደሽ—?! ነፍሴ ሆይ እንዴት አስቻለሽ?! የንጉሶች ንጉስ "የሚጠራኝ—አቤት የምለው" ሲልሽ ምንም ዱአ የለሽም?! አንዳች ሀጃ አላደከመሽም? ነፍሴ ሆይ! ፍላጎትሽ ባህር፤ ፍርሀትሽ ተራራ እንደምን አስቻለሽ አዛኙ ሲጣራ!? ነፍሴ ሆይ! ከተሀጁድ ምን ከለከለሽ?! ስንት ጥያቄ አለሽ? ስንት ህመምን ታመምሽ? ስንት ፈልገሽ አጣሽ? "የሚጠይቀኝ—የምስጠው" እያለ ሲጠራሽ— ከቶ እንዴት አስቻለሽ በህልም ማንቀላፋት። ሀዘንሽ ረጅም፤ ሕይወትሽ የከፋ ጥያቄሽ ከዋክብት፤ ከሰማይ የሰፋ እንደምን አስችሎት፤ ልብሽ አንቀላፋ?! ነፍሴ እንዴት አስቻለሽ ወንጀልሽ በዝቶ፣ አደናቅፎ ጥሎሽ፣ ከማጡ ሲከትሽ፣ ምህረትን ፍለጋ ከጅለሽ ያልወጣሽ፣ ጌታዬ እራሱ "ይቅር ልልሽ" ብሎ ወደ አንቺ ሲመጣ በእንቅልፍ መስጠሙ እንደምን አስቻለሽ። ነፍሴ ሆይ እንዴት አስቻለሽ? የወንጀልሽ እሳት፤ ነበልባሉ ነዶ ሸክሙ ጠናብሽ፤ ከአንሶለው ከብዶ ልብሽ መባተቱ፤ ወንጀልሽ መብዛቱ ልማርሽ ስትባይ መራቅሽ መኼድሽ፤ ምንይሆን ምክንያቱ!? ከጌታሽ ምህረት አመፅሽ ጠፍሮሽ፤ ርቀሽ ከብርሀኑ አንድ ዓለም ሆኑብሽ፤ ምሽቱና ቀኑ የወንጀልሽ ክምር፤ ስፋቱ መጠኑ ከብርዱና ልብሱ፤ ይደፋል ሚዛኑ
ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ። {ቁርዓን 32:16}
ነፍሴ ሆይ! እስቲ ልጠይቅሽ እንደምን አስቻልሽ!? እንዴትስ ሆነልሽ?! በእንቅልፍ መስጠሙ ጌታዬ ሲጠራሽ?! ኢብኑ አይደሩስ

اللهم انصرْ إخواننا أهلَ السنةِ في أرضِ اليمنِ على الروافضِ الأنجاسِ الأرجاسِ، واجمعْ كلمتَهم على الحقِّ، واحقنْ دماءَهم، وثبِّتْ أقدامَهم، وأعدْ إلى أرضِهم الأمنَ والسلامَ.