ch
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

前往频道在 Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

显示更多
未指定国家未指定类别
4 290
订阅者
+124 小时
-157 天
-8430 天
帖子存档
🇪🇹🇬🇧⚡️እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀች። ዋና ከተማው ሲቀር፣ መላው ሀገሩ ለደህንነት አስጊ እና አደገኛ ነው ብላለች። ማስጠንቀቂያው፣ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ለጉዞ
🇪🇹🇬🇧⚡️እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀች። ዋና ከተማው ሲቀር፣ መላው ሀገሩ ለደህንነት አስጊ እና አደገኛ ነው ብላለች። ማስጠንቀቂያው፣ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል ለጉዞ አደገኛ አድርጎ በመጥቀስ፣ ዜጎቹ ወደ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች ሙሉ በሙሉ እና ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በምትዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች ከአሥር እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ እንዳይንቀሳቀስ አሳስቧል።

🇪🇹⚡️የዐማራ ፋኖ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ አስረስ ማረ ዳምጤ፡- 'ሠራዊቱ ከጅምሩ ስለ አገዛዙ ምርጫ ይዞት የነበረው አቋም ትክክለኛ እንደነበር በተግባር ተረጋግጧል።' 1️⃣ BBC 2️⃣ The Eco
🇪🇹⚡️የዐማራ ፋኖ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ አስረስ ማረ ዳምጤ፡- 'ሠራዊቱ ከጅምሩ ስለ አገዛዙ ምርጫ ይዞት የነበረው አቋም ትክክለኛ እንደነበር በተግባር ተረጋግጧል።'
1️⃣ BBC 2️⃣ The Economist 3️⃣ Reuters 4️⃣ Foreign Affairs 5️⃣ Al Jazira 6️⃣ Bloomberg 7️⃣ Netherlands Medias 9️⃣ Africa Report 🔟 Democracy Journal 11. Africa News 12. The conversation 13. Ethiopian Insight 14.DW(Deutsche Welle) 15. France 24 16. Amnesty International 17. African Intelligence እና ሌሎችም፣ የአብይ አህመድን የምርጫ ድግስ ውድቅ አድርገውታል። በኢትዮጵያ ከምርጫ ጋር በተያያዘ በዚህ ልክ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የተነፈገው እና ተቃውሞ የቀረበበት የፖለቲካ ክንውን ታይቶ አያታወቅም። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በዘንድሮው ምርጫ ጉዳይ የያዘው አቋም ትክክለኛ እንደነበር በተግባር ተረጋግጧል። በታንክ እና በድሮን ታግዞ እንኳን አንድ ሐሙስ የቀረውን ስልጣን በምርጫ ስም በተዘጋጀ የደም ድግስ ለማስቀጠል መሞከር የብልፅግናን የፖለቲካ ፆመኛነት ከማሳዬት ያለፈ ፋይዳ የለውም።

• አዲስ አበባ ሰላም ኖ ኣ…?
• አዲስ አበባ ሰላም ኖ ኣ…?

🇸🇩🇨🇳🇦🇪⚡- የሱዳን መንግሥት ጦር ኃይሎች፣ ከኢትዮጵያ የተነሳ ነው የተባለ እና ባለቤትነቱ የኤሜሬት የሆነ ቻይና ሰራሽ CH-95 ድሮንን፣ መትቶ መጣሉን አስታወቀ። *** የኤሜሬት ሼክ እ
+2
🇸🇩🇨🇳🇦🇪⚡- የሱዳን መንግሥት ጦር ኃይሎች፣ ከኢትዮጵያ የተነሳ ነው የተባለ እና ባለቤትነቱ የኤሜሬት የሆነ ቻይና ሰራሽ CH-95 ድሮንን፣ መትቶ መጣሉን አስታወቀ። *** የኤሜሬት ሼክ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር፣ ጃንጃዊድ (RSF) የተባለውን እና በዘር ማጥፋት በተደጋጋሚ የተከሰሰውን አማፂ ቡድን እንደሚደግፉ ይታወቃል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የመንግሥት ኃይሎች በአማፂው ቡድን ላይ የበላይነት እየተቀዳጁ ናቸው።

🇱🇧🇱🇧❌🇮🇱 —ሂዝቦላ በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የጋሊሊ ፎረስት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሁለት የIDF ወታደሮችን በቀጥታ ሲመታ የሚያሳይ የFPV ድሮን ቪዲዮ ዛሬ አውጥቷል።

— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'ኢራን በጣም መጥፎ አቋም ላይ ትገኛለች። አየር ኃይል የላቸውም፣ የባሕር ኃይል የላቸውም፣ ምንም የላቸውም። ያላቸው ንግግር እና የውሸት ዜና (fake news) ብቻ ነው።'

— 🇺🇸/🇮🇷 ትራምፕ ኢራን ለቅርብ ጊዜ ሀሳቡ ምላሽ ለመስጠት ሦስት ቀናት ያህል እንደሚወስድባት ተነግሮታል፤ አንድ ባለስልጣን 'ቃል በቃል በዋሻ ውስጥ ናቸው፣ ኢሜይል አይጠቀሙም' ብሏል – Axios

🇮🇷⚡️— የኢራን IRGC የባሕር ኃይል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በIRGC የባሕር ኃይሎች በተደረገ ቅንጅት እና ደህንነት የነዳጅ ታንከሮችን፣ የኮንቴይነር መርከቦችን እና ሌሎች የንግድ መርከቦች
🇮🇷⚡️— የኢራን IRGC የባሕር ኃይል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በIRGC የባሕር ኃይሎች በተደረገ ቅንጅት እና ደህንነት የነዳጅ ታንከሮችን፣ የኮንቴይነር መርከቦችን እና ሌሎች የንግድ መርከቦችን ጨምሮ 28 መርከቦች በደህና ሁኔታ የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋርጠዋል ብሏል።

+5
🇮🇱❌🇱🇧— የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ዛሬ ቀኑን ሙሉ በደቡብ ሊባኖስ በሚገኘው በታይር ከተማ ላይ በተከታታይ ኃይለኛ የአየር ጥቃቶችን አካሂደዋል።

⚡🇺🇳 ቻይና ክፍያዎቿን እያዘገየች በመሆኑ እና አሜሪካ ማንኛውንም ነገር ለመክፈል ፈጽሞ ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ የተባበሩት መንግስታት ገንዘብ እያለቀ ነው፣ በነሐሴ አጋማሽ የተባበሩት መንግስታት የገንዘብ አቅርቦቱ ያልቃል።

🇮🇷— በቴህራን ኤንግሌሃብ አደባባይ በተካሄደ የመንግስት ደጋፊ ሰልፍ ወቅት፣ IRGC "27 Rajab" የሚባል አዲስ ፈጣን የጥቃት ጀልባ አሳይቷል። የኢራን ሚዲያ፣ 27 Rajab፣ እስከ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ዒላማ መምታት የሚችሉ ሁለት የክሩዝ ሚሳይሎችን የመተኮስ፣ በሰዓት እስከ 200 ኪ.ሜ የመጓዝ እና እስከ 3 ሜትር ከፍታ ያላቸውን ማዕበሎች የመቋቋም አቅም እንዳለው ዘግቧል።

+1
🇮🇱⚡️🇱🇧 'የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ቤን-ግቪር ስለ ሊባኖስ፦ 'እነሱን የሚጎዳው ዳሂየህ ነው፣ ዳሂየህ መደምሰስ አለበት… ዳሂየህ ጥፍጥፍ ጥፍጥፍ ብሎ መጥፋት አለበት— ጥፍጥፍ፣ ጥፍጥፍ፣ እንደገና ጥፍ ጥፍ!' ** ዳሂየህ በስተ ደቡብ ያለ የቤሩት ከተማ ክፍል ነው።

🇺🇸⚡️ትራምፕ፦ አያችሁ፣ እነሱ የእልፍኝ አዳራሽ አላቸው — የቻይና ታላቅ አዳራሽ ተብሎ ይጠራል! በጣም ትልቅ እና ውብ ነው። ሰዎች የተሻለ ነገር ለመሥራት በማሰቤ ለምን ይቃወሙኛል? Dumboክራ
🇺🇸⚡️ትራምፕ፦ አያችሁ፣ እነሱ የእልፍኝ አዳራሽ አላቸው — የቻይና ታላቅ አዳራሽ ተብሎ ይጠራል! በጣም ትልቅ እና ውብ ነው። ሰዎች የተሻለ ነገር ለመሥራት በማሰቤ ለምን ይቃወሙኛል? Dumboክራቶች እብድ ናቸው!

+2
🇫🇷 የፓሪስ ከተማ ክለብ የአውሮፓ ዋንጫ አሸነፈ ብለው በደስታ ከተማ የሚያቃጥሉት የሦስተኛው ዓለም ስደተኞች፣ በሩጫ ላይ።

🇲🇦 🇿🇦 ጥቁር አፍሪካ በአፍሪካ አንደኛነቱን ተቀማ። ሞሮኮ ደቡብ አፍሪካን በማለፍ የአፍሪካ ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ሆናለች።

🇺🇸🇺🇦🇷🇺 የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እንዳሉት አሜሪካ ዩክሬን በጦር ሜዳ የምትፈልገውን ሁሉ እንድታገኝ የጦር መሳሪያ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ አቅዳለች። ** ፑቲን ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ ጦርነቱን በበላይነት ከማጠናቀቅ ይልቅ ፈራ ተባ ሲል፣ እንዲያውም እንገፋበታለን አሉ ጠላቶቹ። ጫናውን ይችለዋል? የኾነ ቦታ ቋ ብሎ ጦሩ እስኪሰበር እየጠበቁት ነው። ይፍጠን! ያለበለዚያ ታሪካዊ ውርደት ይመጣ ይመስላል!

🇺🇸 ⚡️Discombobulated ትርጉም፡ እጅግ ግራ መጋባት፣ መወዛገብ፣ መደነጋገር … እኔ ብቅ ስል፣ ዓለሙ የሚገባበት ጠፋው፣ እያለ ነው ትራምፕ።
🇺🇸 ⚡️Discombobulated ትርጉም፡ እጅግ ግራ መጋባት፣ መወዛገብ፣ መደነጋገር … እኔ ብቅ ስል፣ ዓለሙ የሚገባበት ጠፋው፣ እያለ ነው ትራምፕ።

🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶሻል ገጹን በፖስት አጥለቅልቆታል። 'ቤተሰብ መመስረት እና ልጅ መውለድ ኋላ ቀር ነው ተብሎ እናንተን ለማሳመን በቢሊዮኖች ፈሰስ ተደርጓል' እያለ ነው በአንዱ ፖስቱ።
+3
🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶሻል ገጹን በፖስት አጥለቅልቆታል። 'ቤተሰብ መመስረት እና ልጅ መውለድ ኋላ ቀር ነው ተብሎ እናንተን ለማሳመን በቢሊዮኖች ፈሰስ ተደርጓል' እያለ ነው በአንዱ ፖስቱ። በአሜሪካ በአሁኑ ሰዓት መውለድን ለማበረታታት በሚወለድ ልጅ $1000 ሺ ዶላር ይሰጣል። ይህን ትራምፕ፣ ወደ $5000 ሺ ዶላር ለማሳደግ እቅድ ይዟል። ልጅ ማስወረድ በአሜሪካ ወንጀል ተደርጎ ተደንግጓል፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ መቃምም ቢሆን እንዲሁ፣ እንደ ልብ እንዳይገኝ ተደርጓል። የጠንካራ ወንድ መገለጫ ልጅ ማስወለድ እና አባት ሆኖ በኃላፊነት ማሳደግ የሚለው ሲሆን ለሴት ደግሞ እናትነት ከምንም በላይ የሚያስከብራት እንደሆነ፣ በአሜሪካ በአሁን ጊዜ በየ ሚዲያው የሚነገር ጉዳይ ነው። ይህን 'ተፈጥሯዊ ሕግና ውነታ'፣ መጥፎ ነገር እንደሆነ እና በዚህም ቤተሰብን ሆን ተብሎ ለማፍረስ እና ማሕበረሰብን ለማጥፋት፣ ሰይጣናዊ አጀንዳ ያነገቡ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሆን ብለው ሲሰሩበት የኖሩት ነው፣ ብለው ዛሬ ብዙዎች፣ በተለይ ሪፐብሊካኖች፣ ይከሳሉ። በአፍሪካ እና እንደ ኢትዮጵያ ባሉ 'የደሃ ደሃ ሦስተኛው ዓለም' ሀገሮች ግን፣ የወሊድ መቆጣጠሪ እና 'የቤተሰብ ምጣኔ'፣ ያለ ውይይት፣ ያለ ገደብ እና ያለ ምርጫ፣ በሴት እህቶቻችን እና በእናቶቻችን ላይ በግድ ሲጫኑ እናያለን። የጨነገፈው ህፃን እና የመከነው ፅንስ ቢቆጠር፣ በራሱ፣ በሕዝብ ላይ የተፈጸመ ዘር ማጥፋት ወይም ጀኖሳይድ ሊባል ይችላል። የአፍሪካ መሪዎች የማይወዱትን የሕዝብ ዘር ለማጥፋት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ ይሄ ነው። ወሊድ ቁጥጥር እና ቤተሰብ ምጣኔን እንደ መሳሪያ ይጠቀሙበታል በዚህ ጉዳይ በሰፊው ወደ ፊት እንመጣበታለን።

🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቶማስ ማሲ፣ በማርጀሪ ቴይለር ግሪን፣ በራንድ ፖል፣ በተከር ካርልሰን፣ በካንድስ ኦዌንስ እና በሎረን ቦበርት ላይ ሙድ ይዟል።
🇺🇸⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቶማስ ማሲ፣ በማርጀሪ ቴይለር ግሪን፣ በራንድ ፖል፣ በተከር ካርልሰን፣ በካንድስ ኦዌንስ እና በሎረን ቦበርት ላይ ሙድ ይዟል።

🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇷 የሳዑዲ ዓረቢያ ኤክስፐርት ሙባረክ አል አቲ ለCNN ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወረቀት ላይ ነብር ነው። ሳዑዲ፣ ትራምፕ ወደ ጦርነት ተመልሶ የጀመረውን እንዲጨርስ እና 'እስላማዊ'
🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇷 የሳዑዲ ዓረቢያ ኤክስፐርት ሙባረክ አል አቲ ለCNN ፕሬዝዳንት ትራምፕ የወረቀት ላይ ነብር ነው። ሳዑዲ፣ ትራምፕ ወደ ጦርነት ተመልሶ የጀመረውን እንዲጨርስ እና 'እስላማዊ' የሚባለውን የአያቶላዎችን ሲስተም እንዲያወድም ትፈልጋለች። ያንን ማድረግ ባለመቻሉ ግን፣ በዓለም አቀፍ መድረክ አሜሪካ ደካማ መስላ እንድትታይ ምክኒያት ሆኗል። ለሳዑዲ እና ለገልፍ ሀገሮች የአሜሪካ ደካማ ሆኖ መታየት፣ ለወደፊቱ ህልውናችንን እና ደህንነታችንን በእሷ ላይ እንዳንጥል አደጋ ጋርጧል። ትራምፕ ጠንካራ ቢሆንና ጦርነቱን መጨረስ ቢችል ኖሮ፣ ሳዑዲ ከእስራኤል ጋር በፍቅር እና በትብብር በተመሠረተ ወዳጅነት ላይ፣ በአብርሃም ስምምነት ጥላ ሥር ለመደመር አታቅማማም ነበር።