የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 303
订阅者
-624 小时
-247 天
-9030 天
帖子存档
4 301
🇪🇺🇺🇦 የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እርሱላ ቫን ዴር ሌየን፡
ከዘለንስኪ ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ ነገ ሌላ $4.3 ቢሊዮን ዩሮ ለሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ምርት ወደ ዩክሬን እናስተላልፋለን።*-*- ፈጣሪ ጣልቃ ካልገባ፣ ይቅርታ፣ ሩሲያ አታሸንፍም! ሩሲያ ዩክሬንን መደምሰስ እየቻለች አልደመስስም ስትልና በሁለት ልብ ሆና (ድርድር እና ውጊያ) እየተዋጋች ስትንደፋደፍ፣ እንግዲያውስ እኛ እንደመስስሻለን ያሏት ይመስላል። እነሱ የሚዋጉት በአንድ ልብ ነው፣ ድርድር የሚሉትም ከአንገት በላይ፣ ሩሲያን ሳያኮሎጂካሊ ለማምታታት ነው። ገብቷታል ይሄ? አሁንም ደግሜ እላለሁ፡ አውሮፓ እስካለ ጦርነቱ አይቆምም፣ ዩክሬን እስካልተደመሰሰች ጦርነቱ አይቆምም! አሁን ያለው የሩሲያ አያያዝ ደግሞ ያንን ማድረግ የሚችል ነው ብዬ አላስብም። አውሮፓዊያን ከራሳቸው ዜጎች ላይ እየነጠቁ ለዩክሬን የሚያወጡት የገንዘብ መጠን የማይታመን ነው። ነገ ሩሲያ ተሸንፋ የሚዝቁትን ሀብት በሕልማቸው እያለሙ ለሃጫቸውን አዝረብርበዋል። ሩሲያ አውቃ ይሆን የምታስወጣቸው ጦርነቱን በማርዘም? ካዝናቸውንም መጋዘናቸውንም ልታደኸየው? ይሆን እንደዛ? ትችላቸዋለች 1 ለ 40 ?
4 301
🇪🇺🇺🇦 የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እርሱላ ቫን ዴር ሌየን፡
ከዘለንስኪ ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ ነገ ሌላ $4.3 ቢሊዮን ዩሮ ለሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ምርት ወደ ዩክሬን እናስተላልፋለን።*-*- ፈጣሪ ጣልቃ ካልገባ፣ ይቅርታ፣ ሩሲያ አታሸንፍም! ሩሲያ ዩክሬንን መደምሰስ ስትችል አልደመስስም እያለች በሁለት ልብ ሆና (ድርድር እና ውጊያ) ስትንደፋደፍ፣ እንግዲያውስ እኛ እንደመስስሻለን ያሏት ይመስላል። እነሱ የሚዋጉት በአንድ ልብ ነው፣ ድርድር የሚሉትም ከአንገት በላይ፣ ሩሲያን ሳያኮሎጂካሊ ለማምታታት ነው። ገብቷታል ይሄ? አሁንም ደግሜ እላለሁ፡ አውሮፓ እስካለ ጦርነቱ አይቆምም፣ ዩክሬን እስካልተደመሰሰች ጦርነቱ አይቆምም! አሁን ያለው የሩሲያ አያያዝ ደግሞ ያንን ማድረግ የሚችል ነው ብዬ አላስብም። አውሮፓዊያን ከራሳቸው ዜጎች ላይ እየነጠቁ ለዩክሬን የሚያወጡት የገንዘብ መጠን የማይታመን ነው። ነገ ሩሲያ ተሸንፋ የሚዝቁትን ሀብት በሕልማቸው እያለሙ ለሃጫቸውን አዝረብርበዋል። ሩሲያ አውቃ ይሆን የምታስወጣቸው ጦርነቱን በማርዘም? ካዝናቸውንም መጋዘናቸውንም ልታደኸየው? ይሆን እንደዛ? ትችላቸዋለች 1 ለ 40 ?
4 301
🇸🇦🇺🇸⚡️ — በዋሽንግተን የሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ፡-
የታቀደው የኤፍ-35 ሽያጭ፣ የሳዑዲ-አሜሪካን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ጥንካሬ እና ዘላቂ ባህሪ እና የመከላከያ ትብብራችንን ቀጣይ እድገት ያሳያል። ለበርካታ አስርት ዓመታት፣ የሳዑዲ-አሜሪካ የጸጥታ ትብብር፣ ለአካባቢው መረጋጋት አስተዋጾ አበርክቷል፣ የጋራ የመከላከል አቅማችንን ያጠናክራል፣ እንዲሁም የጋራ የደህንነት ፍላጎቶቻችንን ያሳድጋል።
4 301
🇺🇸/🇺🇳 ዛሬ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በይፋ ወጣች። የተጠቀሱት ምክንያቶች፣ በእስራኤል ላይ አድልዎ ያደርጋል፣ ግብዝነት ያጠቃዋል እና እንደ ኢራን ላሉ የሽብር አገዛዞች ድጋፍን ይሰጣል፣ የሚሉ ናቸው።
4 301
🇵🇰🇸🇦⚡️ — የፓኪስታን ጦር ቃል አቀባይ ሌተናል ጀነራል አህመድ ሸሪፍ ቻውድሪ፡
ፓኪስታን ከሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት ጋር በዲፕሎማሲያዊም ሆነ በአካል ሙሉ በሙሉ ትቆማለች። ለሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት ደህንነት በማንኛውም ደረጃ እንሄድበታለን። የፓኪስታን ሕዝብ ከሳውዲ ወንድምና እህቶች ጋር ትከሻ ለትከሻ መቆሙ ግልጽ መሆን አለበት። በአጭር አነጋገር፣ እኛ እዚያ ነን፣ እናም የሳውዲ ዓረቢያን መንግሥት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ተዘጋጅተናል።
4 301
🇺🇦🇷🇺⚡️የዩክሬን STING ኢንተርሴፕተር ድሮን፣ የሩስያ ድሮን ከመሬት ወደ አየር በተወነጨፈ የዩክሬን ሚሳዬል በተደመሰሰበት ቅጽበት፣ ያስቀረው ምስል።
4 301
🇸🇦⚡️🇾🇪 በሳዑዲ ዓረቢያ ደቡባዊ ግዛት፣ ግዙፉ የያንቡ ወደብ፣ በአሁኑ ሰዓት የየመንን የምሽት ጥቃት ተከትሎ በእሳት እየነደደ ይታያል ።
4 301
🇺🇸🇶🇦🇮🇱⚡- ሌላ ሰበር፡ ኳታር ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ከቱርክ በመቀጠል የኤፍ-35 ጀቶችን ግዥ ጥያቄ በማቅረብ ከመካከለኛው ምስራቅ አዲስ አባል ሆናለች።
እስራኤል ኤፍ-35 አውሮፕላኖችን ለዶሃ መሸጥን በመቃወም፣ ከቱርክ ጥያቄ ጋር እንዳደረገችው ተቃውሞዋን አሰምታለች።
*-*-*-
አማሪካ… አማሪካ እኮ ከልቡ ሀገር ነው፣ አላህ የምድር ገዥ አድርጓቸው … ቸብችበው!
4 301
🇸🇦🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ 48 የኤፍ-35 ተዋጊ አውሮፕላኖችን እና 49 የፕራት ኤንድ ዊትኒ ሞተሮችን ለሳዑዲ ዓረቢያ በ$24.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሸጥ አጸደቀ።
4 301
🇸🇦🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ 48 የኤፍ-35 ተዋጊ አውሮፕላኖችን እና 49 የፕራት ኤንድ ዊትኒ ሞተሮችን ለሳዑዲ ዓረቢያ በ$24.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሸጥ አጸደቀ።
4 301
🇺🇸 ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኳታር፣ ባሕሬን፣ ኩዌት እና ኦማን መሪዎች ጋር በማክሰኞ እንደሚገናኙ AXIOS ዘግቧል።
ትራምፕ፣ "የት እንዳሉና እንዴት እንደሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ። ደህና ናቸው ወይ? እኛ ለእነሱ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረግን ነው" ብሏል።
ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ወይም በኋላ፣ በጦርነቱ ዙሪያ ውሳኔ ይወስን እንደሆን ለተጠየቀው፣ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።
አንዳንድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት፣ የአሁኑን "ጦርነትም፣ ሰላምም ያልሆነውን" ሁኔታ አደገኛና አሜሪካን የሚጎዳ ፖሊሲ አድርገው ይመለከቱታል፣ እናም ስምምነት ካልተደረሰ መጠነ ሠፊ ሌላ ዙር ጦርነት እንደገና ሊጀመር ይችላሉ ብለው ይፈራሉ ።
4 301
አጀብ! ስንት ሀገር ለእርዳታ ተለመነ! የስንቱ ደጅ በልመና ተጠና … በጎረቤት ሀገር ያሉን ሽምቀኞች ለመዋጋት… ኧረ ተወኝ!
ይታያችሁ እስቲ፣ ሳዑዲ እድሜ ዘመኗን የኖረችው የአሜሪካን መሳሪያ ስትገዛ ነው። (ትናንት ትናንት፣ በዕለተ- እሮብ፣ $24 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ መሳሪያ ከአሜሪካ አዝዛለች፣ አሜሪካኖች ግዢውን ገና አላጠደቁትም እንጂ።) ስታግበሰብስ እና ስትሰበስብ፣ ስታከማች እና ስትከዝን ነው የኖረችው።
ከማንም ሀገር በላይ፣ 'ያድኑኛል' ያለቻቸውን መሳሪያዎች ከሮማዊያን (ከፈረንጆች) ላይ በመግዛት፣ ሳዑዲ ዓረቢያን የሚደርስባትም ሆነ የሚወዳደራት ሌላ ሀገር በዓለም የለም። ታዲያሳ… የት ነው ያ ሁሉ ብረት አሁን ላይ? ምን ውጦት ነው ያ ሁሉ የሰበሰበችው የሮማዊያን ቴክኖሎጂ? ራሷን እንዲህ መጠበቅ እስኪያቅጣት ተአማጢያኖች?
ከመጀመሪያው እኮ የቀጠናው ተመልካቾች ተይይ…አይሆንም ብለናታል። ተማጥነናታል በተቻለን … ይቅርብሽ ብለን ተናግረናል! አሁን ምን ይደረጋል? አንዴ ገብተውበታል፣ የሚወጡበትን መንገድ ቁጭ ብለን እናያለን!
እንደ እኔ፣ ሳዑዲ የመንን ሙሉ በሙሉ እርግፍ አድርጋ መተው አለባት። ከየመን ሙሉ በሙሉ መውጣት አለባት። ከዚያ ነገሮች ይስተካከላሉ፣ ባሕሩም ይከፈትላታል።
ሳዑዲ የመን ውስጥ ምንድነው የምትሠራው? በዚያ ያለችው ለምን ዓላማ ነው? በየመን፣ በሰው ሀገር፣ የሙጥኝ ማለት፣ ምን ፈልጋ ነው? ምን ድነው ጎሏ? የሷ በየመን መገኘት እኮ ምንም ጥቅም የለውም፣ አንገብጋቢ የሆነ የሚያገባት ጉዳይም የለም። አላስፈላጊ እኮ ነው።
ነው ወይስ ሳዑዲ በቅጥረኝነት የጽዮናዊያንን ጦርነት ነው በዚያ እየተዋጋች ያለችው?
ታለበለዚያ ግን፣ አልወጣም ብላ በየመን የውስጥ ጉዳይ መፈትፈቷን የምትቀጥል ከሆነ፣ ሳዑዲን የሚሰባብሩት የመኖች ይሆናሉ።
አዎ! ሳዑዲን የሚሰባብሩት የአቢሲኒያዊያን (የሰሜኖች) ደም ያላቸው የኛው ዘመዶች ይሆናሉ።
4 301
🇸🇦/🇮🇷/🇾🇪/🇨🇳 ሳዑዲ ዓረቢያ ከቻይና እርዳታ መጠየቋ ተሰማ።
የባብ አል መንደብ ወሽመጥ እና የቀይ ባሕር ዳርቻዎች በሁቲዎች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ቻይና ሁቲዎችን በመቆጣጠር ላይ ኢራንን እንድትለምንላት ተማጽናለች፣ ሦስት የኢራን እና የቻይና ምንጮች እንደተናገሩት።
ቻይና መልእክቱን ለኢራን አስተላልፋለች፣ ነገር ግን ምንም አይነት ማስፈራሪያ አልሰጠችም ወይም ደግሞ በቴህራን ላይ የኢኮኖሚ ኃይሏን ተጠቅማ ጫና ስለማሳደር አላነሳችም፣ ብለዋል።
ኢራን በበኩሏ፣ በጉዳዩ ምንም አይነት ዋስትና ከመስጠቷ በፊት፣ አሜሪካ እና እስራኤል የጁመሩትን ሕገ-ወጥ ጦርነት ሊያቆሙ ይገባል ብላለች።
"የቀጠናው መረጋጋት የተመሠረተው የአሜሪካ እና የእስራኤል ጦርነት በማስቆም ላይ ነው በማለት ምላሽ ሰጥታለች። - ሮይተርስ
4 301
🇸🇦⚡️🇾🇪 ሰበር ዜና፡ ሳውዲ ዓረቢያ ከሁቲ ጋር ለመደራደር ፍላጎቷ እንደሆነ ገለጸች። ኦማንን ሽማግሌ አድርጋ ልካለች።
በኦማን በኩል ከአንሷረላህ (ሁቲዎች) ጋር ለሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ጠይቃለች።
ኦማን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ጥያቄውን ያቀረበችው ትናንት ምሽት መሆኑን ተናግራለች።
4 301
AXIOS:
🇺🇸🇸🇦🇦🇪🇶🇦 🇵🇸🇴🇲🇯🇴 ትራምፕ ከጦርነቱ በኋላ ከኢራን ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ስትራቴጂ ሀሳቦችን ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት ያብራራሉ።
*-*-*-
ቁጭ ብለህ ተማር ከፕሮፌሰር ትራምፕ። ሳዑዲ፣ ክላስ እንዳትቀሪ።
4 301
🇺🇸🇮🇱⚡️ጄዲ ቫንስ፡
የመካከለኛው ምሥራቅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን ለእስራኤል መንግሥት አጎብዳጅ እንዲሆን ልንፈቅድ አንችልም … ከኔቶም ጋር እንዲሁ፣ ለማንም ብለን አናጎበድድም።
ከሰዎች ጋር ስንሠራ አብረን እንሠራለን። ባልተስማማንበት ጊዜ ደግሞ፣ አንስማማም!
4 301
🇸🇦⚡️ሳዑዲ ዓረቢያ ከየመን ሁቲዎች (አንሷሩላህ) ጋር ያለው ግጭት እየቀጠለ በመምጣቱ፣ የአየር መቃወሚያ ሚሳዬሎቿ እንደተሟጠጡባት ገልፃ፣ ተጨማሪ የአየር መከላከያ ድጋፍ ከቀጠናው እና ከምዕራባውያን አጋሮች እንድትፈልግ አስገድዷታል፣ ሲል AP ዘግቧል።
ሳዑዲ ዓረቢያ ፈረንሳይን፣ ብሪታንያን፣ ፓኪስታንና ግብጽን፣ መንግሥቷን ለመጠበቅ የአየር መከላከያ ድጋፍ እንዲያደርጉላት ጠይቃለች።
እስካሁን ሊረዳት የፈቀደ አልተገኘም።
የሳዑዲ ዓረቢያ ዋነኛ ወታደራዊ አቅራቢ የሆነችው አሜሪካም፣ ከኢራን ጋር ለስድስት ወራት በነበረው ጦርነት ምክንያት፣ የኢንተርሴፕተር ሚሳዬሎች ክምችቷ እንዳሽቆለቆለና ለመስጠት የምትችልበት ዕድል እንደሌለ ታውቋል፣ እንደ ሕትመቱ ዘገባ።
