ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 303
المشتركون
+824 ساعات
-47 أيام
-7130 أيام
أرشيف المشاركات
🇺🇸⚡️ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት በር ላይ፡
እንዴ CNN፣ በጣም ይገርማል! እዚህ ምን ትሰራላችሁ? እዚህ ምን ትሰሪያለች አንቺ? ትናንት ሽፋን አንሰጥህም ምናምን ብላችሁኝ አልነበር እንዴ? እ? አትስጡኝ ሽፋን!

🇺🇸⚡️ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላይ "ትልቅ ውሳኔ" እንደሚጠብቀው ተናግሯል።
"ከኢራን ጋር ስምምነት ይደረጋል?  ወይስ ኢስላማዊውን ሪፐብሊክ አጥፍቼ ቶሎ ልገላገለው? በገሃነም ውስጥ እንዲኖሩ ገፍትሬ ልጨምራቸውና ለወደፊቱ ትውልዶች ታላቅ የመሆን ተስፋቸውን ላጨልመው? እኔን የሚያንገበግበኝ ጥያቄ ይሄ ነው በአሁኑ ሰዓት።

🇨🇺 ትራምፕ ስለ ኩባ፡ ኮሚውኒዝም ወደ አሜሪካ በፍፁም አይመጣም፣ ነፃነት ግን ወደ ኩባ ይመጣል።

🇷🇺🇺🇸 ቭላድሚር ፑቲን በማያሚ ፍሎሪዳ በሚካሄደው የG20 ስብሰባ ላይ በትራምፕ ተጋብዞ የነበረ ቢሆንም፣ ይዘለዋል ተብሏል። በዚያ ምትክ በ APEC ጉባኤ ላይ ይሳተፋል። የዚህን ዓመት ጉባኤ
🇷🇺🇺🇸 ቭላድሚር ፑቲን በማያሚ ፍሎሪዳ በሚካሄደው የG20 ስብሰባ ላይ በትራምፕ ተጋብዞ የነበረ ቢሆንም፣ ይዘለዋል ተብሏል። በዚያ ምትክ በ APEC ጉባኤ ላይ ይሳተፋል። የዚህን ዓመት ጉባኤ ቻይና የምትመራው ሲሆን ከህዳር 18 እስከ 19 በሼንዘን ይካሄዳል። የሩሲያ መሪ እንደ ፈረንጆች ከ2017 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል በመገኘት በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አቅዷል.

🇻🇪 ከዛሬ 20 ዓመት በፊት በዛሬው ዕለት፣ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ላይ ንግግር ሲያደርግ፣ ከዕለቱ አንድ ቀን በፊት ንግግር ያደረገውን ጆር
🇻🇪 ከዛሬ 20 ዓመት በፊት በዛሬው ዕለት፣ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ላይ ንግግር ሲያደርግ፣ ከዕለቱ አንድ ቀን በፊት ንግግር ያደረገውን ጆርጅ ቡሽን፣ "ዲያብሎስ" በማለት ጠርቶት ነበር። እራሱን ከተሳለመ በኋላም፣ "አሁንም ቢሆን የድኙ (Sulfer) ሽታ ይሸተኛል" በማለት ተናግሯል። *-*-*-*- አዎን! መሪዎች አሉ፤ የመሪዎች መሪዎች ደግሞ አሉ። ቬንዙዌላ ከቻቬዝ ሞት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጣለች።

🇷🇺📞🇸🇦 ቭላድሚር ፑቲን፣ ከሳዑዲ አልጋወራሽ ልዑል አቶ መሀመድ ቢን ሰልማን አል ሳዑድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። በመካከለኛው ምስራቅ፣ በተለይም በፋርስ ባሕረ ሰላጤ እና በየመን አካባቢ ስላለው ሁኔታ መወያየታቸውንም፣ ክሬምሊን ተናግሯል። *-*-*-  ወደ ሩሲያ ደግሞ መጣችሁ እናንተ ሰዎች? ኧረ ተዋት እሷን እንኳ

🇷🇺📞🇸🇦 ቭላድሚር ፑቲን፣ ከሳዑዲ አልጋወራሽ ልዑል አቶ መሀመድ ቢን ሰልማን አል ሳዑድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። በመካከለኛው ምስራቅ፣ በተለይም በፋርስ ባሕረ ሰላጤ እና በየመን አካባቢ ስላለው ሁኔታ መወያየታቸውን ክሬምሊን ተናግሯል። *-*-*-  ወደ ሩሲያ ደግሞ መጣችሁ እናንተ ሰዎች? ኧረ ተዋት እሷን እንኳ

🇪🇹⚡️ዛሬ፣ ​መስከረም12 ቀን 2019 ዓ.ም፣ ከማለዳ ጀምሮ፣ በራያ አላማጣ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች ላይ፣ በብልጽግና ጦር ሰራዊት እና በሕዝባዊ ጥምር ጦሩ መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲደረግ ውሏል። በዚህ ውጊያ፣ የብልጽግና ጦር 19 የሚደርሱ የድሮን ጥቃቶችን፣ ሕዝባዊ ጥምር ጦር 'የሚገኝባቸው' በሚል በሲቪሊያ መገልገያ ተቋማት ላይ ፈጽሟል፣ እንደ አካባቢው የዓይን እማኞች ገለፃ። ​ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ቦታዎች፡ 📌​ዋጃ መውጫ - ሓውጃኖ ትምህርት ቤት 📌​ፋጫ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 📌​ንጉስ ቸኮለ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 📌​አላማጣ ቴክኒክ ትምህርት ቤት 📌መሆኒ ጤና ጣቢያ ላይ መፈፀሙ ታውቋል። ​ አለማጣ ከተማ ከማለዳ የተጀመረው ውጊያ አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ለማወቅ ችያለሁ።

🇺🇦🇷🇺⚡️ምሽቱን፣ ኪየቭን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን ከተሞች፣ በከፍተኛ የሩስያ ጥቃት ሥር ናቸው።
+2
🇺🇦🇷🇺⚡️ምሽቱን፣ ኪየቭን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን ከተሞች፣ በከፍተኛ የሩስያ ጥቃት ሥር ናቸው።

🇺🇸 ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከዋይት ሃውስ ለሰራተኞች ንግግር እያደረገ ነበር፣ ነገር ግን ድምጹ አልተሰማም። ይሄም የሆነበት ምክኒያት የዜና ማሰራጫዎች ከዋይት ሃውስ በመታገዳቸው ምክኒያት ነው። ማይክ የለም። ይህን ያስተዋለችው የ Newsmax ጋዜጠኛ፣ ፕሬዝዳንቱ በሚዲያዎች ላይ የወሰደው እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እራሱን እንደጎዳው ስትናገር ትሰማለች። *-*-*- Newsmax በአሜሪካ የኮንሰርቫቲቭ እና የትራምፕ ደጋፊ ሚዲያ ነው። ያም ሆኖ …

🇺🇸 አብዛኞቹን ዋና ዋና የዜና ማሰራጫዎችን ከከለከለ በኋላ፣ ፕሬዝዳንቱ እና ዋይት ሃውስ ሁሉንም የፕሬዚዳንት ትራምፕን መግለጫዎች እና እይታዎች ለመሸፈን፣ አዲስ 'Trump TV' የተባለውን የመ
 🇺🇸 አብዛኞቹን ዋና ዋና የዜና ማሰራጫዎችን ከከለከለ በኋላ፣ ፕሬዝዳንቱ እና ዋይት ሃውስ ሁሉንም የፕሬዚዳንት ትራምፕን መግለጫዎች እና እይታዎች ለመሸፈን፣ አዲስ 'Trump TV' የተባለውን የመንግሥት ቻናል አስተዋውቋል።

🇮🇶 🇸🇦 ⚡️ — ሳዑዲ ዓረቢያ፣ በሳውዲ-ኢራቅ ድንበር አቅራቢያ የስለላ ራዳሮችን እና ፊኛዎችን መትከል ጀምራለች። *-*-*- ማን ይወራታል በመሬት? ይሄ ፍራቻዋስ ከየት መጣ? ካለፈው ሳምንት ጀምሮ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ በኢራቅ በሚያዋስናት ድንበር በኩል፣ በመሬት፣ ሊወራት ያለ ኃይል በዝግጅት ላይ ነው የሚል ወሬ ነበር። ያው ከጭምጭምታና ከመላምት የዘለለ አልነበረም። ወራሪዎቹ ማን ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውም ግልጽ አልነበረም። አንዳንድ ጭምጭምታዎች የኢራቅ ሚሊሾች የሚሉ ነበሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ የኢራን ጦር ይሉ ነበር። እንዳልኩት በወሬ ደረጃ እንጂ የታየ ወይም የተያዘ ተጨባጭ ነገር አልነበረውም። ዛሬ ግን ሳዑዲ፣ ምናልባትም የደረሰችበት ነገር ይኖር ይሆናል፣ የስለላ መሳሪያዎችን በድንበሯ እየተከለች ነው። ይሄ የተረጋገጠ መረጃ ነው

🇬🇧🇸🇦🇾🇪⚡️ — የሁቲ (አንሷራላህ) ጥቃቶች እየተጠናከሩ በሄዱበት እና በየመን ቀይ ባሕር ኃይሏን በይበልጥ ለማጠናከር በማሰብ፣ እንግሊዝ ለሳዑዲ ዓረቢያ ተጨማሪ "የመከላከያ" ወታደራዊ ድ
🇬🇧🇸🇦🇾🇪⚡️ — የሁቲ (አንሷራላህ) ጥቃቶች እየተጠናከሩ በሄዱበት እና በየመን ቀይ ባሕር ኃይሏን በይበልጥ ለማጠናከር በማሰብ፣ እንግሊዝ ለሳዑዲ ዓረቢያ ተጨማሪ "የመከላከያ" ወታደራዊ ድጋፍ ልትሰጥ መቃረቧን ብሉምበርግ ዘግቧል። ሳውዲ ዓረቢያ የኦፕሬሽን እና የመከላከያ እርዳታን ከብሪታንያ ጠይቃለች። ዩናይትድ ኪንግደምም ወታደራዊ አማካሪዎችን ለማሰማራት ተስማምታለች ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃም ተጨማሪ ድጋፍን እያጤኑ እና ሌሎች ሀገራትም እንዲረዱ ለማበረታታት አቅደዋል። *-*-* ስንተኛዋ የተጠየቀች ሀገር ናት እንግሊዝ? ሳዑዲ አሁን የታደለች ይመስላል። እንደ ሀገር፣ የሀገሩን ስም ሳይቀር ከነበረበት (ሂጃዝ) ወደ ሳዑዲ የለወጠችላት፣ አዲሲቷን 'ሳዑዲ' የምትባል ሀገር ያዋለደችዋ እና ንጉሦቹን ወደ ሥልጣን ያመጣቻቸው እንግሊዝ፣ ልትረዳት ነው። ነጣ ያወጣቻች፣ አሁንም ደግማ ነጣ ልታወጣት ነው። ይቅናቸው ውይ።

🇬🇧🇸🇦🇾🇪⚡️ — የሁቲ (አንሷራላህ) ጥቃቶች እየተጠናከሩ በሄዱበት እና በየመን ቀይ ባሕር ኃይሏን በይበልጥ ለማጠናከር በማሰብ፣ እንግሊዝ ለሳዑዲ ዓረቢያ ተጨማሪ "የመከላከያ" ወታደራዊ ድ
🇬🇧🇸🇦🇾🇪⚡️ — የሁቲ (አንሷራላህ) ጥቃቶች እየተጠናከሩ በሄዱበት እና በየመን ቀይ ባሕር ኃይሏን በይበልጥ ለማጠናከር በማሰብ፣ እንግሊዝ ለሳዑዲ ዓረቢያ ተጨማሪ "የመከላከያ" ወታደራዊ ድጋፍ ልትሰጥ መቃረቧን ብሉምበርግ ዘግቧል። ሳውዲ ዓረቢያ የኦፕሬሽን እና የመከላከያ እርዳታን ከብሪታንያ ጠይቃለች። ዩናይትድ ኪንግደምም ወታደራዊ አማካሪዎችን ለማሰማራት ተስማምታለች ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃም ተጨማሪ ድጋፍን እያጤኑ እና ሌሎች ሀገራትም እንዲረዱ ለማበረታታት አቅደዋል። *-*-* ስንተኛዋ የተጠየቀች ሀገር ናት እንግሊዝ? ሳዑዲ አሁን የታደለች ይመስላል። እንደ ሀገር፣ የሀገሩን ስም ሳይቀር ከነበረበት (ሂጃዝ) ወደ ሳዑዲ የለወጠችላት፣ 'ሳዑዲ' የምትባልን አዲስ ሀገር አዋልዳ የፈጠረቻት እና ንጉሦቹን ወደ ሥልጣን ያመጣቻቸው እንግሊዝ፣ ልትረዳት ነው። ነጣ ያወጣቻች፣ አሁንም ደግማ ነጣ ልታወጣት ነው። ይቅናቸው ውይ።

🇸🇾🇮🇱⚡️ — ደማስቆ በእስራኤል ላይ፣ ምንም እንኳን በአደባባይ የከሰሰችው ነገር ባይኖርም፣ የጦር መሳሪያ ማከማቻዎች ላይ በተከሰቱት ባልታወቁ ፍንዳታዎች ውስጥ ተሳትፎ ሊኖርባት እንደሚችል እ
🇸🇾🇮🇱⚡️ — ደማስቆ በእስራኤል ላይ፣ ምንም እንኳን በአደባባይ የከሰሰችው ነገር ባይኖርም፣ የጦር መሳሪያ ማከማቻዎች ላይ በተከሰቱት ባልታወቁ ፍንዳታዎች ውስጥ ተሳትፎ ሊኖርባት እንደሚችል እየመረመሩ ነው። ትናንት ማምሻውን ከአሌፖ በስተደቡብ በሚገኝ የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘን ላይ የደረሰው ፍንዳታ በሶሪያ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሶስተኛው ነው። *-*-*-

🇷🇺🇺🇦⚡️ — የዩክሬን ጥቃቶች ቀጣይነት ባለው መልኩ የሀገሪቱን የነዳጅ ማጣሪያዎች በማወካቸው፣ ሩሲያ በአብዛኛዎቹ የናፍጣ ምርቶች ላይ የጣለችውን እገዳ ከሴፕቴምበር ወር መጨረሻ በላይ ልታራዝ
🇷🇺🇺🇦⚡️ — የዩክሬን ጥቃቶች ቀጣይነት ባለው መልኩ የሀገሪቱን የነዳጅ ማጣሪያዎች በማወካቸው፣ ሩሲያ በአብዛኛዎቹ የናፍጣ ምርቶች ላይ የጣለችውን እገዳ ከሴፕቴምበር ወር መጨረሻ በላይ ልታራዝም ነው፣ ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ፣ ገደቦችን ቢያንስ ለሌላ ወር ለማራዘም እያሰቡ ነው።

🇺🇦❌🇷🇺 — በጋዝፕሮም ባለቤትነት የተያዘው የሩሲያ የሞስኮ የነዳጅ ማጣሪያ፣ ድፍድፍ ማቀነባበር አቁሟል ሲል፣ ሮይተርስ ዘግቧል። ግዙፉ ማጣሪያ፣ ከትናንት በስትያ በዩክሬን ድሮኖች ጥቃት ሁለቱ
🇺🇦❌🇷🇺 — በጋዝፕሮም ባለቤትነት የተያዘው የሩሲያ የሞስኮ የነዳጅ ማጣሪያ፣ ድፍድፍ ማቀነባበር አቁሟል ሲል፣ ሮይተርስ ዘግቧል። ግዙፉ ማጣሪያ፣ ከትናንት በስትያ በዩክሬን ድሮኖች ጥቃት ሁለቱ ዋና ዋና የድፍድፍ ማጣሪያ ክፍሎቹ የወደሙ ሲሆን፥ ጥገናው የሚመች ከሆነ ወደ ነበረበት ለመመለስ በርካታ ወራት እንደሚወስድ ይጠበቃል።

🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ እና በየመን የሳዑዲ ዓረቢያ ቅጥረኞች (PLC), ለሁለት ሳምንታት በሁቲዎች (አናሷራላህ) ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻን ሲያዘጋጁ ቆይተዋል፣ ነገር ግን የሁቲ ጥቃት ፋታ
🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ እና በየመን የሳዑዲ ዓረቢያ ቅጥረኞች (PLC), ለሁለት ሳምንታት በሁቲዎች (አናሷራላህ) ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻን ሲያዘጋጁ ቆይተዋል፣ ነገር ግን የሁቲ ጥቃት ፋታ ስላሳጣ፣ ዘመቻው በተደጋጋሚ መዘግየቱን AXIOS ዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁቲዎች በሳውዲ ዓረቢያ ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረዋል።

🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ እና በየመን የሳዑዲ ዓረቢያ ቅጥረኞች (PLC), ለሁለት ሳምንታት በሁቲዎች (አናሷራላህ) ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻን ሲያዘጋጁ ቆይተዋል፣ ነገር ግን የሁቲ ጥቃት ፋታ
🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ እና በየመን የሳዑዲ ዓረቢያ ቅጥረኞች (PLC), ለሁለት ሳምንታት በሁቲዎች (አናሷራላህ) ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻን ሲያዘጋጁ ቆይተዋል፣ ነገር ግን የሁቲ ጥቃት ፋታ በማሳጣት፣ ዘመቻው በተደጋጋሚ መዘግየቱን AXIOS ዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁቲዎች በሳውዲ ዓረቢያ ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረዋል።

🇺🇸⚡️ የዋይት ሃውስ የቴሌቪዥን ቡድኖች እና ግዙፎቹ የአሜሪካ ሚዲያዎች፣ FOX, ABC, CBS, እና NBC፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ CNN እና MSNBC ሚዲያዎችን ከዋይት ሃውስ ማገዱን በመቃወም፣
🇺🇸⚡️ የዋይት ሃውስ የቴሌቪዥን ቡድኖች እና ግዙፎቹ የአሜሪካ ሚዲያዎች፣ FOX, ABC, CBS, እና NBC፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ CNN እና MSNBC ሚዲያዎችን ከዋይት ሃውስ ማገዱን በመቃወም፣ ለፕሬዝዳንቱ እና ለሚከውናቸው መንግሥታዊ ሥራዎች ሽፋን እንደማይሰጡ ገለጹ። በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሚያደርገውን ንግግር ጨምሮ፣ የበርካታ ዝግጅቶችን የቀጥታ ሽፋን እንደሚገድቡ ይጠበቃል።