ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

🌱📖"بناء الذات بنور الوحي

🌱📖"بناء الذات بنور الوحي

前往频道在 Telegram

🌱📖 ራስን በወህይ ብርሃን መገንባት ቁርኣንና ሐዲስን የሕይወታችን መሪ በማድረግ፣ ማንነታችንን የምንቀይርበትና በእውቀት አብረን የምናድግበት ልዩ መድረክ! 📖🌱 📖 የቁርኣን አንቀጾችንና ውብ የነብዩን  ሐዲሶች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ እንዴት እንተገብራቸዋለን? 🌱 እስላማዊ ስነ-ምግባርን እንዴት እንላበስ? 🤝 በጋራ የምንማማርበትና አብረን የምንለወጥበት

显示更多
未指定国家未指定类别
500
订阅者
-324 小时
-77 天
+3430 天
帖子存档
መጣት 💔 ~ የመጣትን ህመም የሚመስል እዚህ ምድር ላይ የለም ...ህመሙ እጅግ ያየለ ነው ለመሻርም ብዙን ግዜ ይፈጃል! ~የማጣት ህመም የሚያቀው ታማሚው ብቻ ነው መድሃኒት ማግኘት ካበድ ነው .... ከዛ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ባጣነው ነገር ላይ ሰብር ማድረግ ላይ የአላህን ውዴታ እናገኛለን 🥰 〰🤲🏻አላህ ላጣናቸው ቤተሰብ ወዳጅ ዘምድ ሁሉ መተኪያውን ይስጠብ ላጣናቸው ሁሉ መልካም ሀያት ያድርግላቸው! ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

وَمَا جَعَلَهُ اللَّهُ إِلَّا بُشْرَىٰ وَلِتَطْمَئِنَّ بِهِ قُلُوبُكُمْ ۚ وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ [....................]
Anonymous voting

🌎አለም ለፈተና ያላት እይታ... 〰በህይወት ጉዞ ላይ መከራ ሲገጥመን፣ አለማዊ አስተሳሰብ ነገሮችን በጠባብ መነፅር ብቻ እንድንመለከት ያደርገናል። ብዙ ጊዜ "መንገዱ ተዘግቷል፣ ከእንግዲህ አማራጭ
🌎አለም ለፈተና ያላት እይታ... 〰በህይወት ጉዞ ላይ መከራ ሲገጥመን፣ አለማዊ አስተሳሰብ ነገሮችን በጠባብ መነፅር ብቻ እንድንመለከት ያደርገናል። ብዙ ጊዜ "መንገዱ ተዘግቷል፣ ከእንግዲህ አማራጭ የለም" በሚል ተስፋ ቢስነት እና ጨለማ ውስጥ እንዋጣለን። አለምም በዙሪያችን ያሉትን ጫናዎች እንደ መጨረሻው ምዕራፍ አድርገን እንድንቆጥርና እንድንሸነፍ ትገፋፋናለች። ቁርአን: – فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ۝ إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا «ከችግር ጋርም በእርግጥ ምቾት አለ። በእርግጥም ከችግር ጋር ምቾት አለ።» (ሱረቱ አል-ኢንሺራህ 94:5-6) 📌የሰማዩ ብርሃንና የምድሩ ጨለማ... የአላህ ጥበብ ከሰው ልጅ ውስን እውቀት "በላይ" ነው። መከራ ሲበዛ መውጫው እንደራቀ በሚሰማን ቅጽበት፣ እፎይታው እዚያው አጠገባችን መሆኑን ቁርአን ያረጋግጥልናል። ችግርና ምቾት ተከታትለው የሚመጡ ተቃራኒዎች ሳይሆኑ፣ በአላህ እቅድ ውስጥ አብረው የተቆራኙ መሆናቸውን መረዳት ትልቅ መንፈሳዊ ጥንካሬ ነው። እውነተኛው ድል የሚገኘው በሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን፣ በማይለወጠው የፈጣሪ ቃል ላይ በመተማመን ነው። ✔ፈተናን እንደ እንቅፋት ሳይሆን ወደ አላህ መቃረቢያና የውስጥ ማንነትን መገንቢያ ድልድይ አድርገን እንየው። በጭንቅ ውስጥ ሆነን በእርሱ ሰፊ እዝነት የምንተማመንና በትዕግስት ወደ ላቀ ከፍታ የምንሸጋገር ያድርገን🤍!
ከእድገት ማዶ 🌱....
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

. وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا [....................]
Anonymous voting

🫀🧠 ቁርአን ሲያናግረኝ part 44 እኔ: – «ብዙ አቅዳለሁ፣ እደክማለሁ፤ ነገር ግን ያቀድኩት ሁሉ ባለመከናወኑ ተስፋ እቆርጣለሁ። ለምን እቅዶቼ ሁሉ አልሳካ አሉ? የአላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይነትስ🥹 የእኔን እቅድ ለማሳካት ጋር እንዴት ያንሳል! ቁርአን: – «وَلَا تَقُولَنَّ لِشَيْءٍ إِنِّي فَاعِلٌ ذَٰلِكَ غَدًا ۝ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ» (“ለማንኛውም ነገር «እኔ ይህንን ነገ አድራጊ ነኝ» አትበል፤ አላህ ካሻ በቀር።”) (ሱረቱ አል-ካህፍ፡ 23-24)            💡 ተደቡር: – ... እቅድህ ባልተሳካና ተስፋ በተሰማህ ቅጽበት ሁሉም ነገር እየከሰመ ባለ ሰአት እያተነገረህ ያለው እቅድ ማቀድህን እንድታቆም ሳይሆን እንዲህ ልብህ በሚያረጋጋ አያህ ነው; 〰 አላህ በሁሉም ነገር ላይ ሙሉ ቻይ ነው! ነገር ግን የሰው ልጅ የሚያቅደው ሁሉ የሚሳካው በራሱ "ፍላጎት" ብቻ ሳይሆን በአላህ ፈቃድና ጥበብ ነው። አንተ ጥረትህን አድርግ፣ አቅድ፤ ነገር ግን የነገሩን ፍጻሜ ለአላህ ውሳኔ ስጥ። ያቀድከው ሳይሳካ ሲቀር አላህ ከእቅድህ በላይ የተሻለና የሚጠቅምህን ነገር ስላዘጋጀልህ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በራስህ እቅድ ላይ ብቻ አትመካ፤ አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑን አምነህ ጥረትህን ቀጥል—ውጤቱ የሚወሰነው እሱ ላንተ በሚመርጥልህ መልካም ነገር ነውና! 🤍✨
ከእድገት ማዶ🌱
       ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ሰው ሲያያቹ ምትፈሩ ሰዎች.... 🍂ስንትሺህ አይን ያለው እንጀራ ሳታቅማሙ ሳትፈሩ እየበላቹ ሁለት አይን ያለውን ሰው እንዴት ትፈራላች 🤭 እኔ አደለሁም ያልኩት ላጤያን አብሽሩልኝ 😉 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

🍂ሳንተያይ ሳንገናኝ የአላህ ዲን ላዋደደን ፣ብእርና ቃላት ላስተሳሰሩን ፣የእስልማና የኢማን ጉዳይ ላገናኘን ሁሉ ሰባሐል ኸይር ❤‍🩹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

📜ከሀዲስ ገፅ ....part 10 〰ስንቶቻችን ነን ትርፍ ሰዓታችንን በአግባቡ የምንጠቀመው? ...ነፃ ጊዜ ሲኖረን በዚክር፣ ስለ ነገው "አኼራችንና ስለ መጨረሻችን (ስለ ኻቲማችን) "በማሰብ ነው ወይስ በሶሻል ሚዲያ ማለቂያ በሌለው ዝውውር እንዲ አለ ተባለ ሆነ ....በማለት ጊዜያችንን እያቃጠልን...!? ሁላችንም እናቀዋለን 🥹... ዛሬ ላይ ስልካችን ላይ የምናጠፋው ውድ ሰዓት #ሳናውቀው ህይወታችንን እና እድሜያችንን እየሰረቀው ይገኛል! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ይላሉ: «نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ: الصِّحَّةُ وَالفَرَاغُ» (ሁለት ጸጋዎች አሉ፤ ብዙ ሰዎች በእነሱ ይሸወዳሉ (ይከስራሉ)፦ ጤና እና ትርፍ ጊዜ ናቸው።) — (ሶሒህ አል-ቡኻሪ) 📌 ...ቀደምቶች እንደሚሉት፦ «الوقت كالسيف، إن لم تقطعه قطعك» "ጊዜ ልክ እንደ ሰይፍ ነው፤ አንተ ካልቆረጥከው (በመልካም ካልተጠቀምክበት) እርሱ ይቆርጥሃል!" ሶሻል ሚዲያን ለአኼራችንና ለዱንያችን በሚጠቅም መልኩ ካልተጠቀምንበት ሳናውቀው ህይወታችንን በመጥፎ ያበላሸዋል፤ ጊዜያችንን ይበላዋል። ትርፍ ሰዓታችንን በዚክር፣ ኢስቲግፋር በማድረግ እና ነፍሳችንን በመገምገም ልማድ እናድርገው፤ ጊዜ ተመልሶ የማይገኝ ውድ ሀብት ነው⏳! አላህ ቀልብ ይስጣን🤲🏻
ከእድገት ማዶ🌱
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

🌎አለም ስለ ትዳር እና ሀብት ... 〰በህይወት ስንኖር አብዛኛው ማህበረሰብ የሚያስበው ትዳር ከመያዝ በፊት ቤት፣ መኪና፣ የሞላ አካውንትና የተረጋገጠ ሀብት ማሟላት ግድ እንደሆነ ነው። "ያለ በቂ
🌎አለም ስለ ትዳር እና ሀብት ... 〰በህይወት ስንኖር አብዛኛው ማህበረሰብ የሚያስበው ትዳር ከመያዝ በፊት ቤት፣ መኪና፣ የሞላ አካውንትና የተረጋገጠ ሀብት ማሟላት ግድ እንደሆነ ነው። "ያለ በቂ ገንዘብ ትዳር ድህነትን ያወርሳል፤ አስቀድመህ ሀብታም ካልሆንክ አታግባ" በሚል ፍርሃት ወጣቱ እድሜውን ሙሉ ሲሮጥና ትዳርን #ሲያሸሽ ይኖራል። ቁርአን: – وَأَنكِحُوا الْأَيَامَىٰ مِنكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ ۚ إِن يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ "ከናንተም ያላገቡትን፣ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ደጋጎቹን አጋቡ። ድሆች ቢሆኑ እንኳ አላህ ከችሮታው ያበለጽጋቸዋል። አላህም ችሮታው ሰፊ፣ ዐዋቂ ነው።" 24:32 📌የአለም ሂሳብና የአላህ ቃል ፈጽሞ አይገናኙም... ብዙዎች "ትዳር ወጪን ያበዛል፣ ኑሮን ያከብዳል" ብለው ሲያስቡ፣ ቁርአን ግን ትዳርን ራሱን "የሀብትና የሲሳይ መክፈቻ በር" አድርጎ ያስቀምጠዋል። እውነተኛ ብልጽግና በባንክ ደብተር ብዛት ሳይሆን በትዳር ውስጥ በሚወርድ "በረካ" ይገኛል። ✔ሀብታም እስክንሆን ድረስ ትዳርን ማዘግየት ሳይሆን፣ የለንንን ይዘን አግብቶ በአላህ በረካ ውስጥ መበልጸግ "የነቢያቶች ፈለግ" ነው። በሀላል ተጣምረው በረካን ከሚጎናጸፉት፣ በችሮታውም ከሚከብሩት ያድርገን🤍!
ከእድገት ማዶ 🌱....
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

وَاللَّهُ أَيَّدَهُ بِجُنُودٍ لَّمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ الَّذِينَ كَفَرُوا السُّفْلَىٰ ۗ وَكَلِمَةُ اللَّهِ هِيَ الْعُلْيَا ۗ وَاللَّهُ [..................]ٌ
Anonymous voting

ኑረ ሰባህ 🩵
ዛሬ እያንዳንዷ የምትስራት ከይር ስራ አቅለህ አትየው ....ነገ ላይ ትልቅ ሽልማት እያዘጋጀህ ነው ለራስህ ስለዚህ .... ኩን ቀወየን ሊአጅሊክ በሰላት ፣በዚክር ፣በሰደቃ ፣በመልካም ንግግር وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا كَبِيرًا....♡♡ ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

〰ለዚች አጭር ዱንያ ስንቱ መከራ ሰቃይ አየነው አላህዬ ካቲማችን ብቻ አሳምርልን!🥹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ [....................]
Anonymous voting

✏ኢሊፍ ስለ ረሱል ሁብ ...🫶🏼 〰ከከባዱ የጣራ ህመም ሞት ጀርባ የነበረው የማይታሰብ ከባድ ፍቅር ራስን ዘንግቶ ስለኔ ስላንተ ስላንቺ ሚጨነቅልብ አንድ ግለሰብ አለ! ሀቢቡና🥹 ሞት አፋፍ ላይ
✏ኢሊፍ ስለ ረሱል ሁብ ...🫶🏼         〰ከከባዱ የጣራ ህመም ሞት ጀርባ  የነበረው  የማይታሰብ ከባድ ፍቅር  ራስን ዘንግቶ  ስለኔ ስላንተ ስላንቺ ሚጨነቅልብ አንድ ግለሰብ አለ! ሀቢቡና🥹 ሞት አፋፍ ላይ ሆነው "ላ ኢላሀ ኢለላህ፣ ኢነ ሊል መውቲ ለሰከራት" (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ በእርግጥ ለሞት የራሱ የሆነ ጭንቀት/ህመም አለው።) [ቡኻሪ ዘግበውታል] ~ግን ስለሰኛ ከማሰብ  ስለኛ በማልቀስ  አልቦዘኑም ፊዳካ አቢ ወኡሚ የረሱለላህ 🥹 ስቃይ ላይ ሆነው ስለኛ ከማውሳት ያልተዘናጉት ... ታዲያ በሳቸው ላይ ሰላም ሆነን የነሱን ስም ለማውሳት ምንሳሳው? 😔 ♡    ♡الهم صل وسلم عل نبينا محمد.♡

🥀ከሰዎቹ ሁሉ ቆንጆዎቹ ትላልቅ ህፃናት ናቸው ....🫶🏼 〰ትላልቅ ህፃናት በእድሜ ትልቅ ናቸው።አርጅተዋል ፣ ሸብተዋል ።ግና ቀልባቸው እንደ አምስት አመት ህፃን ነው ..ለሰው ያዝናሉ ፣ስለ ሰው ይጨነቃሉ 🥹 እዝነት በመጥፋቱ በአለም ላይ "ሞት ፣ችግር፣ርሃብ...#ስደት ፣ጦርነት በዛ "ተሳሳትኩ? 🤲🏻አላህ ሆይ ለባሮችህ አዛኝ የሆነችን ቀልብ ስጠን ፤ከጨካኞችም አታድርገን ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِأَعْدَائِكُمْ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَلِيًّا وَكَفَىٰ بِاللَّهِ [....................]
Anonymous voting

~ዛሬም እስትንፋሳችን ኖሮ ዳግም ተነስተን የዱንያ ከስብ ፍለጋ እንድንሳተፍ አደረገን! ሹክረንሊላህ ❤‍🩹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ዛሬ ላይ ባልዋልክበት ስም ለሰጡህ ሁሉ..... ✍🏽መልስ በመስጠት ግዜህን አትግደል የግዜ ጉዳይ ነው አላህ ሂክማውን ያሳያቸዋል! ይልቁንም በንግግራቸው ማንነታቸው ለካ እና የራስህን ሰው ፈልግ! ~እኛ ባንናገራቹ ግዜ ያናግራቹሃል! ❤‍🩹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

~ተመልሰናል ጌታዬ ....♡♡ ✍🏽እኛ ሰዎች እይታችን ቅርብ ፣ ዕውቀታች አናሳ ፣አስተውሎታች ጥቂት በመሆኑ ባንተ ውሳኔ ባደረግ ነው "ማጉረምረም ፣መካፋታችን ትክክል አይደለም ለዛም .... ተመልሰናል ጌታዬ❤‍🩹 ጥቁር መነጽር አውልቀናል ።ክፋውን እይታ አንስተናል ያደረከው የምታደርገው ሁሉ ትክክል ፍትሃዊ ፍርድህ ያልተዛባ በመሆኑ አሁን ተመልሰናል ኢላህዬ 🥹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat