የክርስቶስ ፈለግ
前往频道在 Telegram
የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። 1ኛ የጴጥሮስ 2:21 #የክርስቶስን-ፈለግ እንከተል #Jesus is love✞.! #
显示更多未指定国家未指定类别
271
订阅者
+324 小时
+217 天
+2330 天
帖子存档
271
Repost from ቅዱስ ማኅበር
የማይሞላ ጉድጓድ
የሥጋ ምኞት በቃኝን አያውቅም! መቼም እንደማይሞላ ሲኦል፣ የፍጻሜ ወለል እንደሌለው ጥልቅ ጉድጓድ አይጠረቃም። እንኳን ከሌሎች 7 ቢሊዮኖች ሰዎች ጋራ ተካፍለናት ይቅርና ዓለም ራሷ ተጠቅልላ የእኛ ብትኾን እንኳን የምኞት ጉድጓዳችንን አይሞላውም።
እግዚአብሔር ልባችንን የሠራው ነውና የሰራው በራሱ ልክ ነውና ከ እሱ ሌላ አንድ ሊሞላ የሚችል ነገር የለም። እሱ ሲገባበት ግን ጢም፣ ልክክ ይላል፣ ከአፍ እስከ ገደቡ ይሞላል። ያኔ ሰው ስለሚረካ ለራሱ "ኑሮዬ ይበቃኛል!" ይልና የሌሎችን ጉድለት ለመሙላት ያስባል፣ እጁን ይዘረጋል።
ጌታ ሆይ፥ ምኞት የኃጢአት እናት፣ የሞት አያት፣ የአሮጌው ሰው መገልገያ፣ የውድቀት ጥግ ማሳያ ናት። እባክኸን ኃጢአተኛ ተፈጥሮዬን ከምኞቴ ጋር ሰቅዬ በትንሳኤህ ሕይወት በአንተ የረካ ኑሮ እንድመራ እርዳኝ።
እውነተኛ አምልኮ ከዝማሬ ባለፈ በአንተ ተደስቶ፣ በማንነትኸ ረክቶ መኖር ነውና አንተ ብቻ እርካታችን ኹነልን።
አሜን !🙏
ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን
እፎይታ ሣልሳይ
271
Repost from የክብሩ ነፀብራቅ✨
.
ለነፍሳችን "ስኬት ምን ማለት ነው? መኖርስ ምንድነው?" ለሚለው ጥያቄ ቁርጥ ያለ መልስ እስካልሰጠን ድረስ እረፍት ምን ማለት እንደሆነ አናውቅም።
እግዚአብሔር አምላክ ከሃሳቡ ጋር ያገናኘን! 🙌🏾✨ @ShekinnahKBR
271
..
የሕይወት ትርጉም ፣ እግዚአብሔር ለዓላማዉ እንድጠቀምብህ መፍቀድ እንጅ ፣ ለራስህ ዓላማ እርሱን መጠቀሚያ ማድረግ አይደለም።
ሪክ ዋረን ( ከዓላማ መር ሕይወት)!
..
271
....
Morning! Family 👨👩👧👧🙌
ገደም ስንል እንደ ዕሾክ በምወጋን በዓለም ክፋት ሥር ቁጭ ብለን "እግዚአብሔሔር መልካም ነዉ!" ስንል ኸረ እንዴት ይላል..? በእናታችሁ። በሉ ለነፍሳችሁ።
እግዚአብሔር መልካም ነዉ🙌።
ቸር ሰምብቱ🥰! መልካም ቀን!
...
271
.....
መነካት....🫳🫴
የክርስትናን ጉዞ ከጌታችን ከኢየሱስ ጋር ከጀመርን ሕይወት ሰምበትበት ብሏል። አጽናኙ መንፈስ መሪ መሆኑን ስናስብ ዕርግጠኝነታችን ይህ ነዉ አይባልም🔥። አቤት! የኑሮ ጣዕም ፣ የተስፋ ጸዳል ፣ የመኖር ጉጉትና ሕይወትን መዉደድ እንዳልላሱት ማር በጽኑ ያስጎመጃል ። ያላየናቸዉን ቀኖቻችንን ናፍቀናቸዋል ነዉ ምላችሁ...🙌! በዚህ ክቡር ሕይወት ጎዳና ዉስጥ የተጓዦች አቅም የምወሰነዉ፣ ጉልበታቸዉ የምጎለብተዉ ፣ ለጉዞአቸዉ ቀና አመለካከትና ትጋት የምኖራቸዉ ከመሪዉ መንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት(intimacy) ልክ ነዉ። በዉስጣችን ካለዉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥልቅ ሕብረት የምንጀምርበት፣ በነፍስ ዕዉቀት የገባዉን በሕይወት ልምምድ የምናጎላበት ፣ የጉዞአችንን ቀለብ ሰንቀን የምንነሳበት፣ እግዜር ልባችንን የምያሰናዳበት ትልቁና የተለየ ክስተት መነካት(Encounter) ነዉ። ከጩኼትም ዝም ከማለትም ፤ ከመንከባለልም ስሜት ከታከለበት ከአንድ ቀን ዕምባም ያለፈ ነገር ነዉ ባይ ነኝ መነካት። በርግጥ የሥጋችን ምላሽ መሆን ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን አይገልጹትም። በአዕምሮችን እንደዛ ስለን እነደሆነን ፣ ከመፈለግ እንጎድላለን የረካን ስመስለን።
ቃሉ ያፈራዉ እዉነተኛ መነካት፦ የእግዚአብሐርን መነጽር አጥልቆ አጽናፈ ዓለሙን መመልከት ነዉ።ለእግዚአብሔርና ለራሳችን፣ ለወንድሞቻችንና ለክርስቶስ አካል ፤ ለዓለምም እንኳን ባለን ዕይታ የእግዚአብሔርን አዕምሮ(Godly mind) የምንጋራበት ድንቅ ክስተት ነዉ። የሕይወት ዘመን ጉዞ እንጅ ሰሞነኛም አይደለም ። ቀምሰዉ እንዳዩ ምላሶች ፥ የቃሉ ርሃብ ፣ የጸሎት ጥማት ያኃይላል። የወንድማማች መዋደድና የቤተ ክርስቲያን መታነጽ እንደዶፍ ይዘንቡብናል። መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ፍቅር በልባችን ያፈስብናል። ፈቃዱን ያስረዳል። መንበርከክ ያጓጓል፣ ነገሮች እንደድሮ normal አይሆኑም። "ኢየሱስ የወደኛልኮ" ማለት ለቀናት የምናነባበት የምያሳርፈን እዉነት ይሆናል። የነካዉን ለመንካት ርሃብ ይጸናል ፣ ፍለጋውም ይብሳል። ዓለም በጉዳት ትተመናለች ፤ ነፍሱም መሪዉጋር ትከርማለች። ጉዞ ይጣፍጣል ነዉ ምላችሁ...🙌። ካልሆነማ! ምን ልበላችሁ?...👐 በጣም አዳጋችና ታማኝነትን የምጎድል ቁልቁለትና ዳገት ይሆናል ። በዚህ ምድር ከባዱ ሸክም ተደርጎ ይሰላል። ቀድሞ የገባ ዕዉቀት ሁሉ የቤቱ ራስ ይሆናል። የእዉነት መሌክያ የአመክንዮ(logic) ልህቀት ሆኖ ይቀራል። መንፈሳዊ ልምምድ "ለእኔ ዕገለ" ጎራ ይሰጣል።
ሥጋ በብዙ ሰበብ በድሎት ሰፈነጥዝ ፣ ነፍስ ግን ከነጬኼቷ በርሃብ ትጠወልጋለች👐 አድነን!..🙌ባለ ብዙ መንገድ የሆነ አምላክ በምገባላችሁ መንገድና ቋንቋ ለቀሪ ዘመናችሁ ስንቅ በምሆን መነካት ይንካችሁ....🙌🥰🔥! https://t.me/followhistrace ....
271
Repost from የክብሩ ነፀብራቅ✨
ገና እንጭጭ ሳለ ኅጢአትን አንገቱን አንቀህ ደም ስሩን ዝጋበት:: ነገ ላይ ደልቦና ፈርጥሞ እንዳይዳፈርህ::
@ShekinnahKBR
271
https://t.me/theeternalwaymark
Join this telegram channel for your spiritual growth and end days gospel mission readiness.
271
...
ስጋቴን ታንኳ አስምጦ ውጦታል🙌
ነገዬ ስል ሁሌ ኢየሱስ ይቀድማል
የለም የገዘፈ በፍርሀቴ ጎልቶ
አለ ስል መኖሩ እውነቴን አጥርቶ
..
271
...
ቤተሰቦቼ ዕዉቀታችን ሙሉ ወደምሆንበት ፣ ኃጢአት ያጎደለዉን ዕዉቀት በጸጋዉ የምንሞላበት ፤ ከኹላችሁም ጋር በደምብ የምተዋወቅበትን የሰማዩን ጉባዔ እመኛለሁ🥺።
በክርስቶስ በጣም ነዉ ምወዳችኹ🥰🙌!
መልካም ቀን🙌!
...
271
....
ከአንተ አንበልጥምና አብራልን....🙌
ስትወለድ በነቢያት አንደበት የቃልህ ፍጻሜ
ዕዉን እንድሆን ዘንድ በቤተል መገኘትህ ገርሞናል! የነቢዪ የኢሳያስ ጩኼትም ከንቱ አልሆነምና። ቃልህ ተፈጽሟል። ፈጣሪ በፍጡር ተሰዶ ለቃልህ ታማኝነት ናዝራዊ ልትባል በትንሽዬ ከተማ መኖር ከጀመርክበት ፣ ዳግም ያገኘንህ በሙኩራቡ አስተማሪዎች ሥር በመጽሐፍት ጥናት ነበር። በ 12 ዓመትህ እንኳን ለቃልህ ያለህ ርሃብ በእዉነትም ልባችንን ያሞቃል። ራስህን የሰወርከዉ ለዓመታት እዛዉ ሰምብተ ይሆናል ከመጽሐፍት ጋር ። ቃልህን መኖር ያቃተዉን የመጀመርያዉን አዳም የጣለ ባላንጣዉ ፣ ክፉኛ ስፈትንህ አፍህን የከፈትከዉ ከዳዊት መዝሙር አይደል የቃልህን ሰይፍ እየመዘዝክበት። በአገልግሎትህ ጀምሩ በሙኩራብ የተረተረከዉ የኢሳያስ መጽሐፍ የቃልህ ወዳጅ እንደሆንክ በርግጥ ያረጋግጥልናል። "መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ" ያልክበት ይህ ዘመን ያልቀየረዉ እዉነት የአንድ ቀን ምሽት ሕልም እንዳይደለህ አይሣንም። ከዘፍጥረት እስከ ሚልክያስ ራስህን አገኘህ እንጅ። ኸረ ግን ያለ ቃልህ መቼ አገኘንህ?! በትንሣኤዉ ዕለት ለድንጋዩ መንከባለል የዓይን እማኝ ለሆኑ ለዔማዉስ መንገደኞች ፣ በዚያኑ ዕለት ታምራት ከማስደመም ይልቅ የሦስተኛ ቀን ድልህን ከመጽሐፍት አጸናህላቸዉ ።
አጽናፈ ዓለሙ ከተደመመበት ከትንሣኤ ዕለት ታምራት ይልቅ በቃልህ ልበ ሙሉ ነህ።በዚህ ምድር አንተን ያለ መጽሐፍት ፣ መጽሐፍትን ደግሞ ያላንተ አላገኘንም። ምነኛ ብትገልጥለት ይሁን? እንዴት ብትነካዉ፣ ምንስ ቀምሶ ይሁን? ዘማሪዉ ዳዊት በመዝ 119 እንደ አድስ አፍቃሪ😁 176 ቁጥር ስለቃልህ ተቅኝቶ አልርካ ብሏል። የመጽሐፍት ረዥሙ ምዕራፍ። እኛ ብላተናዎች አንተን ፍለጋ ያለ ቃልህ እንዳንዳክር ፣ ፈለግህን እንድንከተል ፣ በቃልህ ልባችን መሉ እንድሆን ፣ ከማንጸጸትበት መምህራችን ከአንተ ሕይወትን እንድንቀዳ ፣ ለሕግ ጊዜ እንድበዛልንና የቃልህ ወዳጆች ታድርገን ዘንድ በፍርሃትና በትህትና በእምነት እንማጸናለን። ያከበርከዉ ቃልህ በልባችንም ይክበድ....!🙌🥰 ተባረኩልኝ! .....
271
...
(NLT) Your word is a lamp to guide my feet and a light for my path. Psalm 119:105
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን!🥰
........
271
....
በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
አሞጽ 9:11
.....
271
.....
ዝምብሎ መኖር አይከብድም። ብዙዎች ኖረዋል ፣ እየኖሩም ነዉ። ወደፍትም ይኖራሉ። ለጌታ መኖር እንደምከብድ ማወቅም እንደዛዉ። ተጠይቆ " መኖር ከባድ ነዉ!" ያላሌስ ማነዉ? ዕዉቀቱ መች ጎደለብን። በከረምን ቁጥር "እየኖርኩ ነዉ"! ማለት አዳገተን እንጅ። ነገር ግን እንድንኖርለት የተዘረጋ የእግዚብሔር ታማኝ ክንዱ "ጸጋዉ" ነዉ። የምንኖር እየመስልን እንዳንዳክር ፣ እንደ ኖኅ ትዉልድ ፤ ወደ ጸጋዉ መረከብ ቶሎ እንግባ። ማኖር ያውቅበታልና ወደ ጸጋዉ በእምነት እንቅረብ። ለጸጋዉ ብርታት ክብር ይግባዉ🙌።
የምያኖር ጸጋ ይብዛልን ወዳጆቼ🥰!
..
