ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

前往频道在 Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

显示更多
未指定国家未指定类别
193
订阅者
-224 小时
-47 天
-630 天
帖子存档
ሸይኸ ኢድሪስ ሙሃመድ አፋር አላህ ይጠብቃቸው

ለሱና ደዕዋ የእውነት መቆርቆር ያላችሁ ወገኖች! ~ ደዕዋው በጩኸት፣ በግርግር፣ በፍጥጫ፣ በንትርክ እንዲታወቅ አናድርግ። አላህን እንፍራ። እንዲህ አይነት አካሄድ ደዕዋው ላይ ከባድ ጠባሳ ነው የሚጥለው። * እርጋታ፣ ስክነት ይኑረን። በትንሽ በትልቁ ከመጯጯሁ እንውጣ። * ለደዕዋው መልካም ስም እንጨነቅ። መልካም ስም ዋጋው ከምናስበው በላይ ዋጋው ትልቅ ነው። ለራሳችን ክብር ስንል ያለፈ ያገደመው ላይ የምንጮህ ከሆነ ደዕዋውን እንጎዳለን። * ወገናችንን ከስር ጀምሮ በስርአት በዒልም መኮትኮት ላይ ቅድሚያ ሰጥተን ተግተን እንስራ። * ክፉ አመላችንን እንግራ። ጀብደኝነት፣ ከዚያም ከዚህም ጋር መላተም ይጎዳናል እንጂ አይጠቅመንም። * በየ አካባቢያችን በተቻለን አቅም ማህበራዊ ተሳትፎ ቢኖረን መልካም ነው። የተቸገረን መርዳትና ማስተባበር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ማሳከም፣ መሻይኾችን ማክበር፣ ማገዝ፣ ወዘተ. ተግባር ከንግግር በላይ ይጣራል። የቴሌግራም ቻናል፡- = https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ዘመነ ኢህአዴግ (ወያኔ) እና የራያ ሙስሊሞች ጭቆና(ከባለፈው የቀጠለ ) ሠ.መስጆዶች እንዳይሰሩ ማድረግ ራያ ላይ መንግስት ወሀብያ ብሎ እንቅስቃሴ ከጀመረበት 2000 ዓ/ል ጀምሮ አዲስ መስጂድ አልተሰራም ምክንያቱም መስጂድ የሚያሰሩ የመስጂድ አባቶችት እስር ቤት ተወርውረው መስጂዶች በፖለቲከኞች እጂ ወድቀዋል። እነዚህ ስዎች ለስሙ ሙስሊሙ ቢሆኑም መስጂድ እንዲሰራ አይፈልጉም ፤ ከቻሉ የተሰራው ቢፈርስ ደስታቸው ወደር የለውም። በእርግጥ ሙስሊሙ ከዚህ በፊት ተሰተው ያረጁ መስጂዶችን እንዳዲስ የገነባ ቢሆንም ለአዲስ መስጂድ ግንባታ የተሰጠ ቦታ የለም።ሙስሊሙበአላማጣ፣ኮረም፣ማይጨውና መኾኒ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም። በትግራይ ስር የሚገኛው የራያ ክፍል መዲና የሆነችው የማይጨው ሁለት መስጂዶች ብቻ ያላት ሲሆን ተጨማሪ መስጂድ ለመጠየቅ የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ሊሳካ አልቻለም። በአላማጣም ቀይ አፈርና ሀያት ሰፈር መስጂድ ጥያቄ መልያስ ያላገኙ ናቸው። የሀያት መስጂድ ጥያቄ የመጂሊሱ ሴራና ድክመት በድንብ ሰለሚያሳይ በምሳሌ እንየው ሀያት ሰፈር በብዛት ሙስሊሞች የሚኖሩበት ቢሆንም በአቅራብያቸው መስጂድ ባለመኖሩ በጣም ሲቸገሩ ነበር፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በ1996 ከኮኮብ ፅባሕ አጣገብ በሚገነው የቀድሞ የሙስሊሞች መቃብር አጣገብ ያለዉን መስጂድ ለማሰራት በሱዳናዊ አህለል ኸይር 400,000 ብር ድጋፍ እንቅስቃሴ ቢጀመርም በወሀቢ ብር መስጂድ አይገነባም በማለት በመጅሊሶች ምክንያት እንዲቀር አድርገዋል፡፡ ፎርማል በሆነ መንገድ ከ1998 ጀምሮ በተከታታይ ጥያቄዎች ቢቀርቡም ምላሽ ሊገኝ አልቻለም፡፡ በ2005 ዓ.ል አስተዳደሩ አጠቃላይ የሙስሊሙን ቁጥር መዝግባቹህ አምጡ ከ500 የሚበልጥከሆነ መስጂድ እንደሚሰጥ ቃል ሲገባ የአከባቢው ሙስሊሞች ባጠቃለይ ከ6000 በላይ መሆናቸውን በዝርዝር ቢያቀርቡም መስጂድ ሊሰጥ አልቻለም፡፡ ለዚህም ዋነኛ ምክንያት መጅሊሶች ናቸው፤በ2005 የሀያት ሰፈር ተከራይተው በሚሰግዱበት ቢላል መስጂድ ላይ የመጅሊስ ተወካዮች ሙስሊሙን በመሰብሰብ መስጂዱን በአጭር ግዜ ዉስጥ እንደሚረከቡ በመግለፅ ህዝበ ሙስሊሙ በትግስት እንዲጠብቁ በማሳሰብ አጭበርብሯቸዋል፡፡ ቢሆንም ግን የሀያት ሰፈር ሙስሊሞች ወኪል ሀጂ አሊ ጉሎ ከባልደረቦቹ በመሆን መስጂዱ እንዲሰጥ ብዙ ጥረት አድርገው፣ ጥረቱ ዉጤት ሊያፈራ በቀረበበት ማግስት በመጅሊሶች በመካከል በተከሰተው ሹኩቻ ተጨናግፏል፡፡ በመጅሊሶች መካከል የተከሰተው ሽኩቻ የጥቅም እንጂ ኡማውን ለማገልገል የተደረገ አይደለም፤ የሽኩቻው መንስኤ የመስጅዱን ግንባታ ሀላፊነት በእኔ ላይ ይሁን ከሚል ገንዘብ ለመዝረፍ ከመሽቀዳደም የተነሳ ነው፡፡ በመጨረሻም የሀያት ሰፈር ሙስሊም ወኪሎችን በመጥራት ለመስጂዱ የሚሆን ገንዘብ ምን ያክል ነው ያላቹህ ከማን ጋር ነው ያለው ብለው ጠየቋቸው ወኪሎችም እኛ ጋር ምንም አይነት ገንዘብ የለም ቦታው ከተገኘ ሙስሊሙ አዋጥቶም ቢሆን እንገነባዋለን በሚል ነው እንቅስቃሴዉን የጀመርነው ሲሉ መልስ ሰጡ፡፡ ይህንን የሰሙ መጅሊሶች የመስጂዱን ጉዳይ እርግፍ አድርገው ተውት!! ምክንያቱም ሲሯሯጡ የነበረው እንዲሁም በማሀላቸው ሽኩቻ የተፈጠረው ለመስጂድ ማሰርያ ተብሎ የሚመጣዉን ገንዘብ ለመዝረፍ ነበር ገንዘቡ ስለለለ የመስጂዱን ጉዳይ ተረሳ፡፡ የሀያት ሙስሊሞች በመጅሊሱ ክህደት ሳይበገሩ ጥያቄዎቻቸውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ሙሰሊሙ በቀጥታ ከአስተዳደር ጋር መገናኘት ስለማይችል ማናቻዉም ጥያቄ በመጅሊስ በኩል መምጣት ስላለበት የታሰበዉን ዉጤት ሊያመጣ አልቻለም፡፡ በመጨረሻ የሙስሊም ጠላት የሆነው መጅሊስ ሙስሊሙ የመስጂድ ችግር የለበትም እንኳን አዲስ መስጂድ ያለውም ሚሰግድበት የለም ስለዚህ የመስጂድ ጥያቄ የለንም ብለው በመደምደም የ10 አመታት የኡማው ልፋት ከንቱአስቀረተዉታል፡፡ በዚህ ቀስሙ የተሰበረው ሙስሊሙ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ተጋባ፡፡ ሙስሊሙ ተስፋ ሳይቆርጥ ጥያቄዉን አጠናክሮ በመቀጠል በ2011 ዓ.ል 1700 ካሬ ቦታ እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት ቦታዉን ለመከለል ማሀንዲስ ሲመጣ በአካባቢው ባለ ቄስ አመካኝነት ችግር በመፈጠሩ ተጓተተ፡፡ አስተዳደሩም በአከባቢው ያሉ ክርስትያኖችን አስፈቅዱ ከፈቀዱላቹህ እንሰጣቹህ አለን በማለት መሬቱን እና ስልጣኑን ለአንድ እምነት አስረከበ፤ በሙስሊሞች ላይ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም መጅሊስ ቁሞ ከመመልከት ሌላ የሰራው አልነበረም፡፡ ሙስሊሞቹ መስጂድ ለመገንባት የክርስትያኖች ፍቃድ መጠየቅ የለብንም ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው ይሰጠን ቢሉም በመጅሊስ ደካማነት ምክንያት ሊሳካ አልቻለም፤ በመጨረሻም ቄሱ ለአስተዳደሩ ያስገባው ደብዳቤ ይህ ቦታ ለሙስሊሞች መሰጠት የለበትም ምክያቱም ልጆቻችን የሚጫወቱበት እና እኛ ቤተክርስተያን የምንሄድበት መንገድ ነው የሚል ሲሆን ለቄስ ልጆች መጫወቻ ተብሎ የሙስሊሙ ጥያቄ ቁማርተጫውተዉበታል፡፡ ቀልድ በሚመስል አንዲት ደብዳቤ መስጂድ እንዳይሰራ ያገደዉን ቄስ ከህግ አንፃር በመክራከር እና ሙስሊሙን አስተባብሮ ከመንቀሳቀስ ይልቅ መጅሊስ ዝምታን በመምረጡ የሀያት ሙስሊሞች አሁን ድረስ በተከራዩበት ቢላል መስጂድ እየሰገዱ ይገኛሉ፡፡

عن ابن عباس رضي الله عنهما قال : كُنْتُ خَلْفَ رَسُولِ اللهِ ﷺ يَوْمًا فَقَالَ : "يَا غُلَامُ ، إنِّي أُعَلِّمُكَ كَلِمَاتٍ ، احْفَظِ اللهَ يَحْفَظْكَ ، احْفَظِ اللهَ تَجِدْهُ تُجَاهَكَ ، إذَا سَألْتَ فَاسْألِ اللهَ ، وَإذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللهِ ، وَاعْلَمْ أنَّ الأُمَّةَ لَوِ اجْتَمَعَتْ عَلَى أنْ يَنْفَعُوكَ بِشَيْءٍ لَمْ يَنْفَعُوكَ إلَّا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللهُ لَكَ وَلَوْ اجْتَمَعُوا عَلَى أنْ يَضُرُّوكَ بِشَيْءٍ لَمْ يَضُرُّوكَ إلَّا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللهُ عَلَيْكَ .. رُفِعَتِ الأقْلَامُ وَجَفَّتْ الصُّحُفُ". [مسند الإمام أحمد (واللفظ من جامع الترمذي)].

የ አለማዊ ሙሁሮች ሆይ! ማወቅ ደግ ነገር ስለሆነ እንኳን አወቃቹህ እንኳን ደስ አላቹህ የምር መማር ጥሩ ነገር ነው። ነገር ግን እኛን የአለማዊ እውቀት ያልተማርን ወንድሞቻችሁን አትናቁን አታንጓጡን መቼምኮ እኛም እንደናንተው እናሰላስላለን እናስተውላለን ወጥተንም እንገባለን ቤትሰብም ጀመዓም እንመራለን ባለመማራችን ምክንያት ላንድያችን ድፍን ቅል ሁነን አልተቀመጥንም። እንደው ከናንተጋ ውለን መግባታችን ሽሮም በልተን ቢሆን ቤትሰብ መመስረታችን አያስመሰግነንም እንዳለመማራችን? ከተማረውም ውስጥኮ የቀን ስራ እየሰራ ለእለት ጉርሱ ያልበቃ አንደበቱን ከፍቶ ሀሳቡን መግለፅ ያልቻለ ቡዙ ወገን አለ ያው መማር ለቅርቢቱ ዓለም ነው የሚያገለግለው ይባል የለ ግን ያልተጠቀመ ነፍ ህዝብ አለ። ለአኺራ ከሆነ የአለማዊ እውቀት አያጋድድም አሏህም እንድህ ሲል ይናገራል إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡ https://t.me/abumuazhusenedris

ዘመነ ኢህአዴግ (ወያኔ) እና የራያ ሙስሊሞች ጭቆና(ከባለፈው የቀጠለ ) መ. ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ችግር መፍጠር ሙስሊሙ እንዳይማር ከአፄ ሀይለስላሴ ጀምሮ የተለያዩ ሴራዎች እንደነበሩ ይታወቃል። የራያ ሙስሊሞች በሁሉም ዘርፍ ለማዳከም የሚደረገው ዘመቻ ተማሪዎችን እንኳን አልተወም። የራያ ሙስሊም ትምህርት እንዳይማር አያሌ ችሮች ነበሩ፤ከችግሮቹ ውስጥ ትምህርት ከኢስላም ጋር አብሮ እንደማይሄድና የመጨረሻ አላማውም ከኢስላም ማሰወጣት እንደሆነ በመስበክ ሙስሊሙ እንዳይማር ተደርጓል። ለምሳሌ የኔ ትምህርት መማር በአራቱም አያቶቼ ቅሬታ ፈጥራል። በእረፍት ለገጠር በምሄድበት ግዜ የማስታወሰው ሁሌም ለትምህርት የነበረቸው ጥላቻና አባትና እናቴ ሰፈር (ለኢስላማዊ ትምህርት የሚደረግ ጉዞ) ሳይልኩ ትምህርት ማስገባታቸው አንድም ቀን አስደስቷቸው አያውቀም። ምክንያቱም ትምህርት መማር ከኢስላም ለማሰወጣት የመጣና ለሙስሊሞች የሚበጅ እንዳልሆነ ስለተነገራቸው ነው። በተጨማሪም ሙስሊም በሚበዛባቸው የራያ አከባቢዎች አንድም ትምህርት ቤት አለመኖሩ እነዲሁም ት/ቤት የተገነባባቸው አከቢዎች ት/ት በአግባቡ አይሰጥም እነዚህና ሌሎች ተግባራት ሙስሊም እንዳይማር እየተሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው። ይህንን ሴራ በመቋቋም ትምህርት በሚማሩ ልጆች ደግሞ ከፍተኛ ችግር ይፈጠርባቸው ነበር። ከነበረው ችግሮች አንዱና ዋነኛው ደግሞ ሰላትና ሂጃብ ነው። በመላ ኢትዮጵያ የተፈቀደው ትምህርት ሚኒስተር ባወጣው መመርያ ሳይቀር የፈቀደውን ሂጃብ በመከልከል ሙስሊሙ ተረጋግቶ እንዳይማር በማድረግ ከትምህርት እንዲቀር አድርገዋል። ተማሪዎች ሲደረግባቸው የነበረው ጭቆና በተለያዩ ግዝያት ለመታገል ሞከራዋል።ሙስሊም ሴቶችሂጃባቸው እየተገፈፈ ሲቃጠል በአይናችን ተመልክተናል፤ እስካሁን ድረስ ይህንን ሳስታውስ ይሰቀጥጠኛል። ከነበረው ጭቆና የአላማጣን እንመልከት 2000 ዓ.ል በታዳጊዋ ኢትዮጵያ ሂጃብ በመከልከሉ ምክንያት ተማሪዎች ጥያቄ አነሱ። ጥያቄውን በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ተማሪዎችን በማሰቃየተና በማስፈራራት ለመቀልበስ ቢሞከረም ሊሳካ አልቻለም። ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው አጠናክረው በመቀጠላቸው በሽብር ማነሳሳት ተከሰው ሁለት ተማሪዎችና ሁለት መምህራን ታስረው ስድስት ወር ከተፈረደባቸው ቡሃላ ተማሪ ስለሆኑ በገንዘብ እንዲቀጡ ተወሰነባቸው። የሚገርመው ደግሞ በተመማሪዎቹ ላይ የአቃቢ ህግ ምስክር የነበሩት ሙስሊሙን ስያሳስርሩ፣ተቋሙን ስያፈርስ የነበሩ የመስጊድ ኮሚቴዎች ነበሩ። አስረኞቹም ከሁለት ሳምንት እስር ቡሃላ በቅጣት ተለቀዎል። በ 2003 ዓ.ል የታዳጊዋ ኢትዮጵያ እና የህዳሴ ፕሪፓራቶሪ ተማሪዎች በተቀናጀ መልኩ የሂጃብ እና የሰላት ጥያቄዎችን አንግበው መንቃሰቀስ ጀመሩ፡፡ በተማሪዎች መካከል ምክክር እና ወይይት እየተደረገ የታዳጊዋ ት/ቤት ስታዲዮም ይሰገድ ነበር ሴቶችም ህጃብ ሲለብሱ ነበር፡፡ የመምህራን ጫና እየበረታ ሲመጣ ሙስሊሙ ተጠራርቶ በብዛት ስታዲዮም ላይ ሰገደ፤ ይሄኔ ገብረስላሴ የተባለ ፖሊስ ተጠርቶ ካሰላመቱ ቡኋላ እንዲህ አለ ‹‹ ይህ ት/ቤት ነው ፤የህይማኖት ቦታ አይደለም ስለዚህ እዚህ መስገድ አይቻልም፡፡ በዚህ ሀሳብ ምትስማሙ ከሆነ እዚሁ ያልቃል ካልሆነ ግን ፖሊስ ጣብያ እንወስዳቹህ አለን፡፡›› የሚል ዛቻ አዘል ንግግር በቁጣ ታናገረ፡፡ተማሪዎችም በዚህ ሀሳብ እንደማይስማሙ እና ቢታሰሩ እንኳን ምንም እንደማይመስላቸው ተናገሩ፡፡ ሙስሊሙ ተማሪ ሀሳቡን ሊቀይር ስላልቻለ ወደ ፖሊስ ተውሰደው ከአንድ ኢንስፔክተር ጋር ዉይይቱ ተጀመረ፤ እንደተለመደው እናንተ ሌላ ተልዕኮ ተሰጥቷቹህ የምትንቀሳቀሱ እንጂ እውነትም ለሀይማኖታቹህ አይደለም ሲል ተማሪዎችን ለማሸመቀቅ ሞከረ፡፡ ተማሪው በአቋሙ ስለ ፀና ዉይይቱ ባለመግባባት ሊጠናቀቅ መሆኑ ሲታወቅ አንድ ተማሪን ክፍኛ ደበደቡት እሱን አስረው የተቀሩት ተማሪዎችን እንዲሄዱ ቢያዟቸውም ተማሪዎቹ ያለሱ አንደማይሔዱ በመናገር ከፖሊስ ጣብያው ግቢ አልወጣም በማለታቸው ልጁ ተፈታ፡፡ ጉዳዩም ከተማሪዎች ጋር ሳይሆን ከሙስሊም መሪዎች ጋር ተነጋግረው መፍትሔ እንደሚፈልጉ ተናገሩ፡፡ ተማሪዉም በዚህ ሀሳብ ተስማምቶ ወደ ቤቱ አቀና፤ ከመጀመርያዉም ለሙስሊም ተማሪዎች ትኩረት የማይሰጠው መጅሊስ አደገኛ የክህደት በትሩን አሳረፈ፡፡ ሶላት ከት/ቤት ሲመለሱ ይሰግዳሉ፤ ሂጃቡ ደግሞ እድሚያቸው ገና ስለሆነ ግዴታ አይሆንባቸውም ሲሉ ተስማሙ፡፡ ተማሪው ጥያቄዉን በድጋሚ ሲያነሳ እናንተ ሌላ ተልዕኮ ይኖራችኋል እንጂ የእናንተ መሪዎች ችግር የለዉም ያሉትን ጉዳይ እናንተ ማራገባቹህ በሰላም አይደለም ሲሉ ተማሪዉን አሸማቀቁት፡፡ ሂጃብ ለብሰው የመጡ ተማሪዎች ሂጃባቸ እንዲቃጠል ተደረገ፤ ከዚያን ወዲህ ሙስሊሙ ተማሪ ሂጀብ ሆና ሰላት ተከለከ፡፡ በ2006 ዓ.ል ጥያቄው በእያሱ በርሄ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች በአዲስ እና በተደራጀ መልኩ ተነሳ ፤ ጥያቄው ሂጃብ መልበስ አለብን ባሉ ሴት ተማሪዎች ተቀጣጠለ፡፡ ለሁለት ሳምንታት ከትምህርታቸው የተከለከሉት ተማሪዎች ትግላቸዉን አጠናክረው ቢቀጥሉም አብሽሩ የሚላቸው አንድ የሙስሊም መሪ አልነበረም፡፡ ሙስሊሙ ተማሪ በመደራጀት ጥያቄዉን ለማቅረብ በሉቅማን አልሀኪም(01) መስጂድ ተሰባሰበ በዚሁ ስብሰባ ላይ የመጅሊስ ወኪል በመገኘት የሙስሉሙ ጥያቄ አግባብ እንዳልሆነ እና ተማሪዎቹ ሳያስፈቅዱ መሰብሰብ አንዳልነበረባቸው በመናገር ተማሪዎቹን ለማሸማቀቅ ሞከረ፡፡ ተማሪዎቹ በጥያቄ ስለፋጠጧቸው ወይይቱ ባለ መግባባት ተጠናቆ ተማሪው ተበተና፡፡ በመስጂድ እንዲሰበሰብ ጥያቄ ያቀረበው ተማሪ በመጅሊሱ መስጂድ ላይ መሰብሰብ እንደማይችሉ ተነገራቸው፡፡ ለሙሰሊሙ ጠበቃ ነኝ የሚለው መጅሊስ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ችግሩ እንዳይፈታ እንቅፋት ሆነ፡፡ ተማሪው ተሰባስቦ የሚነጋገርበት ቦታ ለግዜው ባያገኝም ጥያቄዉን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ጂሃን ላይ ያለዉ የሸይኸ መሀመድ አሚን መስጂድ መጠቀም አንድንችል ፈቀዱ፡፡ተማሪው ጂሃን መስጂድ ላይ እየተሰባሰበ እና እየተወያየ ትግሉን አጧጧፈው፤ ይህ በእዲህ አንዳለ ሴቶቹም ሂጃብ ካላወለቃቹህ አትገቡም ሲለተባሉ ለሁለት ሳምንታት ክላስ ሳይገቡ ቀሩ፡፡ በመጨረሻው ትግሉ እንደማይቆም የተረዳው ት/ቤቱ ከዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ቆብ እንዲለብሱ ፈቀደ፡፡ ተማሪው ደግሞ እኛ የታዘዝነው ሂጃብ እንጂ ቆብ አይደለም በማለት ይህንን ዉሳኔ እንደማይቀበሉ አሳውቁ፡፡ ይህንን ሁሉ ትግል በሚደረግበት ግዜ አንድም የመጅሊስ ሰው ያገዘ የለም፡፡ ትግሉ እየተፋፋመ ሲመጣ የሙስሊም ተወካዮች ይምጡና እነሱ ጋር ተወያይተን ዉሳኔው እናሳልፋለን አሉ። ሙስሊሙን ወክሎ የመጣው ከመጅሊስ ነበር፡፡ አንድም ቀን አግዟቸው የማያውቀው ሰው፤ ከዳይሬክተር ጋር በመነጋገር ዋናው ነገር ፀጉራቸው መሸፈኑ ስለሆነ ቆብ ሆነ ሂጃብ ችግር የለዉም የሚል ፈትዋ በመስጠት ተስማምቶ ወጣ፡፡ በዚህ ኩፍኛ የተከፋው ተማሪው ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ተጋባ በመጨረሻም ግዜው እየነጎደ ተማሪዎቹ ደግሞ ክላስ እያለፋቸው ስለሆነ ተማሪዎች ባልተስማሙበት በመጅሊስ ዉሳኔ ፀና ሴት ተማሪዎችም ቆብ በማሰፋት ለበሱ፡፡

📚المنظومة الرائية في السنة ✍لأبي القاسم سعد بن علي بن محمد بن علي بن الحسين الزنجاني 📚ሽም ኪታብ:መንዙመቱ ራኢያ 🎤ደርሲ ዝሃቦ:ሸይኽ ሙሓመድ መ
📚المنظومة الرائية في السنة ✍لأبي القاسم سعد بن علي بن محمد بن علي بن الحسين الزنجاني 📚ሽም ኪታብ:መንዙመቱ ራኢያ 🎤ደርሲ ዝሃቦ:ሸይኽ ሙሓመድ መኪን ሙሓመድ 🔊በዝሒ ቕዳሕ ድምፂ 7⃣ ➷➴➷ ናይ ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/Alikhlasderstat

تـفــسيــر الــقـ📖ـرآن الكـــريــــم #الدرس_الجديد   #سورة النحل ٨٠_٨٨ 🎙 للشيخ أبي عمار أول بن أحمد الخميسي  «حفظه الله» https://t.me/DurusSheikhAwol

🔖ተከታታይ  ደርስ 📚 ሪያዱ ሷሊሒን 📄ክፍል:- 274   👈كتاب الجهاد 👉ሐዲስ ቁጥር:- 1354 - 1360 🎙አቅራቢ:-ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም 🕌የሚሰጥበት ቦታ፦ ፋሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ 📖የኪታቡ ሶፍት ኮፒ (በ pdf ):- https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/7959 🗓 ዛሬ ሐሙስ ጁማደል ኣኺር 20,1447 ሂጅሪ 02-04-2018) * የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት :-ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከሱብሒ ሰላት በኃላ *የቴሌግራም ቻናሎች፡- @SheikhMuhammedZain @SheikhMuhammedZainadam @abuhuzeyfashaikhmohammedzeyn

የአራቱ አዒማዎች ሱናን መከተልና ንግግሮቻቸው ያን የሚቃረን ከሆነ መተው እንደሚገባ ከራሳቸው አንደበት! አል‐ኢማም አቡ ሐኒፋ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ ﴿إذا صح الحديث فهو مذهبي﴾ “ትክክለኛ የሆነ ሐዲስ፤ እርሱ የኔ መዝሀቤ (አቋሜ) ነው።” 📙 ኢብን አብደይን ፊይ አልኻሺይ: 1/23 አል‐ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ ﴿ليس أحد بعد النبي (ﷺ) إلا ويؤخذ من قوله ويترك إلا النبي (ﷺ)﴾ “ከነብዩ  (ﷺ) በኋላ አንድም ሠው የለም ንግግሩ (ታይቶ ትክክል ከሆነ) የሚያዝለት፤ (ትክክል ካልሆነ) የሚተው ቢሆን እንጂ ነቢዩ (ﷺ) ሲቀሩ” 📙 ኢብኑ አብዱልበር በጃሚዕ ውስጥ ዘግበውታል፡ 2/91 አል‐ኢማሙ አህመድ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ ﴿لا تقلدني ولا تقلد مالكا ولا الشافعي ولا الأوزاعي ولا الثوري وخذ من حيث أخذوا﴾ “እኔን በጭፍን አትከተሉኝ፡፡ ኢማሙ ማሊኪን፣ ሻፊዒይን፣ አውዛዒንም ሆነ ሰውሪ በጭፍን አትከተሉ፡፡ እኛ ከያዝንበት (ከተማርንበት) ያዙ።” 📙 አል‐ፉላኒይ፡ 113 አል‐ኢማሙ ሻፊዒይ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ ﴿أجمع المسلمون على أن من استبان له سنة (ﷺ) لم يحل له أن يدعها لقول أحد﴾ “ከአላህ መልእክተኛ (ﷺ) የተረጋገጠ ሱና እርሱ ዘንድ የደረሰው ሰው በሙሉ፤ ለየትኛውም የሰው ንግግር ብሎ (ሱናን) መተው እንደሌለበት ዑለማዎች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።” 📙አል‐ፉላኒይ: 68

የአላማጣ መድረሳ አሁናዊ ገጽታው
የአላማጣ መድረሳ አሁናዊ ገጽታው

ዘመነ ኢህአዴግ (ወያኔ) እና የራያ ሙስሊሞች ጭቆና(ከባለፈው የቀጠለ ) ለ.የሙስሊሙን ተቋም ማፍረስ በሙስሊሞች ጉዳይ ውስጥ በመግባትና እንዲለያዩ በማድረግ ጠያቂ ሳይኖረው የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት ሁኔታዎች በመፈጠሩና በታማኝነት ጉዳዩን የሚያስፈፀሙለት ሎሌዎች በማደራጀቱ ጥቃቱ ዳግም እንዳያንሰራሩ በሚያድርግ መልኩ ጀመሩ። የሙስሊሙ ዋነኛ ተቋም መጂሊስ ነው ፤ መጂሊስ ከተሰተካከለ የሙስሊሙ ሁኔታ እንድሚስተካከል ምንም ጥርጥር የለዉም። የመጅሊስ መበላሸት ድግሞ ሙስሊሙን እንደሚጎዳ ይታወቃል። ኢስላምን ለማጥፋት የጀመረውን ዘመቻ ጠንካራ፣ስለኢስላም እውቀት ያላቸውና ለሀይማኖታቸው የሚቆረቆሩትን በማሰወገድ የኢስላም እውቀት የሌላቸውና በግልፅ የህወሓት አባል የሆኑ ስዎች እንዲመጡ አድርጓል። መጅሊስ ብቻ ሳይሆን የመስጂድ ኮሚቴዎች ጭምር መንግስት የራሱ ስዎች እንዲሸሙ አድርጓል። እነዚህ የተሾሙ ስዎች ከላይ ያየነው ሙስሊሞችን ማክፈር እንዲሁም ቀጥለን የምንመለከተውን የሙስሊም ተቋማት የማፍረስ ተልዕኮ የተወጡ ናቸው። ከስር የምንመለከተው መከራዎችና ጥፋቶች በእነዚህ ሰዎች አድራጊነት የተፈፀመ ነው። መንግስት እየፈጸም ያለውን ግፍ ሊቃውሙ የሚችሉት የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች በማሰር የሙስሊሙን ተቋም አንድ በአንድ ማፍረስ ጀመር። በመላ ራያ መስጂዶች ማፍረስና መዝጋት የመጀመርያ ስራ ሆነ፤ እንዲፈርሱ ወይም እንዲዘጉ ከተደረጉት መስጂዶች መካከል በአላማጣ ሸይኽ ፈይዱ መስጂድና ኩክፍቶ ይገኝበታል። ሐ.የመድረሳ ወደ መኖርያ ቤት መለወጥ የአላማጣ ሉቅማን አልሀኪም መድረሳ በአጭር ግዜ ዉስጥ ከፍተኛ ለውጥ እና መነቃቃት የፈጠረ ከመሆኑም በላይ ልጆች ቁርአንን በነፃ ተምረው ለዲናቸው መሰረት የጣሉበት ሆኖ አልፏል፡፡ እስከ 2002 ዓ.ል የነበሩ ልጆች አብዛሐኛው ቁርኣንን በደንብ የተማሩ እና ቀጥለው ከመጡ ትውልዶች የተሻለ የዲን ግንዛቤ አላቸው፡፡ መድረሳው ስራዉን የጀመረው በሉቅማን አል-ሀኪም መስጂድ ቅጥር ግቢ ባሉ መማርያ ክፍሎች ሲሆን የተማሪዎች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመምጣቱ እና የአላማጣ ሙስሊሞች በዲናቸው ላይ ያላቸዉን ጥንካሬ ጥሩ ደረጃ በመሆኑ በኢትዮጵያ ደረጃ ከተመረጡ የዲን ማዕከላት አንዷ እንድትሆን አስችሏል፡፡ ለዚህም መስጂድ ላይ ሲሰጥ የነበረው ቁርኣን በልዩ መልኩ እንዲሰጥ ዘመናዊ መድረሳ ተገንብቷል፡፡ የመድረሳዉ ግንባታ ከተጠናቀቀ ቡኃላ የቁርአን ትምህርት ቤቱ ወደ አዲሱ መድረሳ በማዛወር ትምህርቱን በዘመናዊ መልኩ መስጠት ተጀምሯል፡፡ በግዜው ለተማሪዎች ዩኒፎም በነፃ ከመስጠት ጀምሮ ዲናዊ ትምህርት በስርዐት ሲሰጥበት የነበረ ሲሆን መድረሳዉን አንድ ደረጃ ለማሳደግ ተብሎ ከ1-4ኛ ክፍል ትምህርት በመጀመር ቁርአን እና አለማዊ ትምህርት ለመስጠት ኮምፒውተርን ጨምሮ በቂ ዝግጅት አድርጎ መማር ማስተማሩን በተሳካ ሁኔታ ጀምሮ ነበር፡፡ መማር ማስተማሩ በጀመረበት ማግስት ከላይ ውሐብዮች ካፊር ናቸው መድረሳና መስጂድ በመስራት ከሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ጋር ሊያጣሉን ነው ብለው የመሰከሩ ግለሰቦች ችግር መፍጠር ጀመሩ። ሉቅማን አል-አልሀኪም ትምህርት ቤት ኢስላማዊ እንድመሆኑ መጠን የቁርአን፣ሀዲስና ሲራ ኮርስች እንደሚካተትበት ይታወቃል ስለዚህ ሙስሊም ያልሆኑ ስዎች ሊማሩ አይችሉም፤ በእርግጥ መማር ከፈለጉ ይችላሉ ነገርግን ሙስሊም ያልሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው ኢስላም እንድማሩ እንደማይልኩ እየታወቀ ሙስሊም ያልሆኑ ስዎች መማር አለባቸው የሚል ትርክት በማምጣት መድረሳው የተነሣበት አላማ ወደ ጎን በመተው አለማዊ ትምህርት ብቻ እንዲማሩ አድርገዋል፡፡ መድረሳው ኢስላማዊ ሆኖ እንዳይቀጥል በማድረግ ሙስሊም ያልሆኑ ተማሪዎች አንዲማሩ በማድረግ የሉቅማን አልሀኪም ትምህርት ቤት ከአንድ ሰሚስተር የዘለለ ኢድሜ እንዳይኖረው አድርገዋል፡፡ ሙስሊም ወይም ክርስትያን ብቻ የሚማሩባቸው ትምህርትቤቶች በኢትዮጵያ አያሌ ናቸው፤ ወልድያን እንደምሳሌመውሰድ ይቻላል።የትምህርት ቁሳቁሶችኮምፒውተሮች ጨምሮ ተዘርፈው የት እንደገቡ አይታወቅም፡፡ ጠንካራ የነበረው መድረሳ በማዳከም ያሰቡትን እኩይ አላማ አሳኩ አላማው ሙስሊሞች ቁርአን እንዳይቀሩ ማድረግ ስለነበር ቁርአን የሚቀሩ ተማሪዎቸን በማሸማቀቅ መድረሳዉን ለመኖርያ ቤት አከራይተዉታል፡፡ የአላህ ቃል ሊማሩበት፣ ልጆች ስለዲናቸው አንድያዉቁ ተብሎ የተገነባው መድረሳ አሁን ላይ የጋራ መኖርያ ኮንዶሚኔም ሆኗል፡፡ መድረሳው ከተዘጋ ቡኋላ የተወለዱ ልጆች አብዛኛቹ ቁርአን ያልተማሩ ከመሆናቸዉም በላይ አሁን ላይ የሚታየው የሙስሊሙ ስነ ምግባር መጉደል መድረሳው የዘጉት ስዎች ተጠያቂ ናቸው።ለዚህምክንያቱ ደግሞ ስለዲን የሚማሩበት እና ግዝያቸዉን የሚያሳልፉበት መድረሳ ተዘግቶ ለመኖርያ ቤትነትአገልግሎት መዋል ስለጀመረ ነው፡፡ መድረሳው ተዘግቶ ወድ መኖርያ ቤትከተቀየረ ብኋላ በተደጋጋሚ ወደ ተገነባለብት አላማ እንዲመልስ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ሊሳካ አልቻለም።

🚨 ልዩ እና አስቸኳይ ጥሪ ለሰለፍይ ወንድም እህቶች! ⭕️ጉዳዩ የሁላችንም ነው! እንቅልፍ የሚነሳ እና በጋራ ልንወያይበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ገጥሞናል። በመሆኑም የፊታችን ማክሰኞ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ማንኛውንም ፕሮግራም በመሰረዝ፤ እንዲሁም መደበኛ የቂራአት ፕሮግራሞችን ለአንድ ቀን ቆም በማድረግ ሁላችሁም በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭታችን ላይ እንድትገኙ በአላህ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 👥ፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ ወንድሞች፦ ☑ወንድም አቡ ዒምራን ☑ወንድም አቡ ዑሰይሚን ☑ወንድም አቡ ሻኪራ ☑ወንድም አቡ ሱፍያን ☑ወንድም አቡ ዑበይዳ ☑ወንድም አቡ ሐሳን ☑ወንድም ዐብዱል መሊክ ☑ወንድም አቡ ሉቅማን ☑ ወንድም አቡ ሂበቲላህ ☑ ወንድም አቡ አዩብ ☑ወንድም አቡ ረያን ☑ ወንድም አቡ ሁማም ☑ወንድም ሙሓመድ አያሌው ☑ወንድም አቡ ሀፍሷ ☑ወንድም አቡ ሙስዓብ… እንድሁም ሌሎች ኡስታዞች እና ወንድሞች ይገኙበታል። ⚠️ይህ ቀጠሮ በፍጹም እንዳያመልጥዎ! ለሌሎችም ያስተላልፉ። 📆 ቀን፡ የፊታችን ማክሰኞ(ታህሳስ 7) ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ— 😂የቀጥታ ስርጭት አድራሻ፦⇊ t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

"ወሐብዮች ካፊር ናችሁ ስለዚህ ቶብቱ" በአላማጣ ከተማና ገጠር እስልምና ጉዳይ ጽ/ቤት በ28/5/2005 ዓ/ል በአላማጣ ከተማ መድረሳ ትምህርት ቤት ባደረገው ስብሰባ ያሳለፈው ዉሳኔ ይላል ቃለ ጉባኤው። በስብሰባው የከተማና ገጠር እስልምና ተወካዮች፣ የአላማጣና ገጠር መንግስት አካላት፣የከተማና ገጠር ሸረዓ ፍ/ቤት ተወካዮች፣ የመስጂድ ኮሚቴ ተዋካዮች፣ ሽማግሌዋችና ታዋቂ ሰዎች፣ የሙስሊም እድር(ቅሬ) ወኪሎች እንደተገኙ ይገልፃል። በመቀጠልም «እስልምና በኢትዮጵያ በሰላም ተቻችሎ የኖረ ሀይማኖት ቢሆንም «ወሀብዮች» ከቅርብ ግዜ ወዲህ መስጂድና መድረሳ እናሰራለን በማለት በሙስሊሙና ሌሎች ሀይማኖት መካከል ልዩትና ጥላቻ እንዲፈጠር አድርገዋል። አሁን ላይ ግን ህዝበ ሙስሊሙ ነቅቶ «ወሀብያዎች» ከኢስላም የወጡ (ካፊሮች) መሆናቸውን አረጋግጦ ወስኗል።» ይላል ቃላ ጉባኤው። ቃለ ጉባኤው በውቅቱ የአላማጣ ወረዳ ኡለሞች ሀላፊ በነበሩት ተፍርሞ በአላማጣ እስልምና ጉዳዮች፣በአላማጣ ከተማፖሊስና ፣ የአላማጣ ከተማ ፍትህ አስትዳደር ፅ/ቤት ወጪ የተደረገ ሲሆን በግልባጭ ለ15 ተቋማት እንድያስፈፅሙ ያዛል። ይህ አደገኛ ዉሳኔ ህዝበ ሙስሊሙን ሊጠቅሙ የሚችሉ ታላላቅየሀይማኖት አባቶች ስም በማጠልሸት ለእስርና እንግልት ዳርጓቸዋል። የቀረበው ክስ ስንመረምረው 1. «ወሀብዮች» መስጂድና መድርሳ ለመግንባት ከውጭ ሀገራት ጋር መገናኘት የሚል ነው። በኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ግኙነት በመፍጠር ሀይማኖታዊ ድጋፍ ማድረግ በምንም መልኩ ወንጀል ያልሆነ ሲሆን ካቶሊክ፣ፕሮቴስታንትና ሌሎች ሀይማኖቶች ጭምር ድጋፍ ያገኛሉ። ይህም የተለመደና ህጋዊ ተግባር ሲሆን እነዚህ ተሰብስበው ክስ የመሰረቱት ስዎች ራሳቸው ከሊባኖስ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት የነበራቸው ናቸው። እነዚህ ስዎች በቆቦ መስጂድ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ፣ ጥሙጋ አሊ አል-ቃህጣኒ መስጂድ፣ በአላማጣ ሶስቱን ምስጂዶች፣ በኮረም አንዋር መስጂድ፣ በባላ፣ጨርጨር፣ጋርጃል፣ኩኩፍቶ፣ሀዳ አልጋ፣ዳጋጋ፣ኩቤ ጃብሌ፣ጋንዳሻቦ፣ ጎጎሎ፣መኾኒ ና ማይጨው ትላልቅ መስጂዶች ከውጭ ሰዎች ጋር በመገናኘት መገንባታቸው ነው ጥፋታው? በአላማጣ ባለአንድ ፎቅና 8 ክላስ ያለው ጥራቱ የጠበቀ መድረሳና ት/ቤት መገንባታቸው ነው ጥፋታቸው?? አንዴት አንድ ጤነኛ ሙስሊም መስጂድና መድርሳ መገንባቱ ያበሳጨዋል? መልስ ያጣሁበት ጥያቄ ነው። 2. ከሌሎች ሀይማኖቶች ጋር ማለያየት ሁለተኛ ውንጀላ ነው። የራያ ሙስሊሞች እጂጉን ሰላማዊና ከክርስትያኖች ጋር በሰላም ሲኖሩ፣ በችግር ስዐት ሲደጋገፉ የኖሩ መሆኑ የራያ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው እውነታ ነው። የራያ ሙስሊም በራያ ህዝበ ክርስትያን ዘንድ የተከብሩና እንደራሱ ወንድሞቹ የሚያቸው ናቸው። እነዚህ ስዎች መች ነው ከሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ጋር እንድንለያይና እንድንጣላ የሰበኩት?? መልሱ ለእናንተ ትቸው አለሁ። አንዳንድ ሙስሊሞችን የማክፈርና ከሙስሊሞች የመነጠል ዋነኛ አላማው ኢስልምናን ማዳከም ነው። ከዚህ ክስተት ብኋላ ራያ ላይ አንድም መስጂድ አልተሰራም፣ መድረሳዎችም አልተገነቡም፣ የተገነቡትም እንዳይጠቀሙበት ተደርጓል ለዚህ ሁሉ ሰበብ የሆኑት በታሪክ ተወቃሽ ናቸው። ከዚህ ፍረጃ ብኋላ ሙስሊሞች ከፍተኛ ስቃይና መከራ ደረሰባቸው፤ ስለ ኢስላም ምንም በማያውቁ ክርስትያን የመንግስት አካላት ጭምር ህዝብ በሚሰበሰብበት መድረክ «ቶብት» እያተባሉ ስያሸማቅቋቸውና ሲሳለቁባቸው እንደነበር የሁላችን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው። በመቀጠልም በ23/07/2005 ዓ/ል በ ቁጥር ቁ/ወ/አ/ት/እ14-2005 የተፃፈ በውቅቱ የአላማጣ እስልምና ጉዳዮች ሀላፊ ተፈርሞ በአላማጣ ከተማ ፍትህ አስትዳደር ፅ/ቤትና በአላማጣ እስልምና ጉዳዮች ማህተም የወጣው ከኢስላም ውጭ እንደሆኑ ዳግም በማረጋገጥ በቀጣይ ለሚወሰደው እርምጃ justification ሰጥተዋል። ከዚህ ውሳኔ ብኋላ በሙስሊሞች ላይ የሚድርሰው ግፍ በከፍተኛ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት የሀይማኖት አባቶች በተደጋጋሚ እንዲታሰሩ ሁኗል። አንዳንድ መሻሂኾች መስጂድ ለሰላት በመግባታቸው ምክንያት በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ሁላችን የምናውቀው እውነታ ነው።በራያ ተጽኖ የሚፈጥሩ ሙስሊሞች መስጅድ እንዳይገቡ፣ሀዘንና ሰርግ እንዳይቀላቀሉ ካድረጉ ብኋላ በመላ ራያ የሚገኙ ወጣቶች በተለይ የመንግስት ስራ የሚሰሩ ሙስሊሞች ከፍተኛ ጫና ደረሰባቸው የሚበዙትም ሀገር ጥለው ተሰደቱ። የራያ ሙስሊም አባት አልባ ሁኖ እንዲቧዝን ተፈረደበት።

ደጋግመን ሞተናል ! ርካሹን እያየን ፀያፉ ተነቦ ክፉ እየተወራ ስማርት ባሉት ስልክ ፊስቅ እየተቃኘ ነውሩ ከተሰራ በቀን በጨለማው አመፅ ቀለብ ሆኖ አሏህ ካልተፈራ ከሞታችን በፊት ደጋግመን ሞተናል የዲናችነን ቃል አደራ በልተናል !! https://t.me/msirage4