ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

前往频道在 Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

显示更多
未指定国家未指定类别
193
订阅者
-224 小时
-47 天
-630 天
帖子存档
ዶ/ር ኑሩ መካከለኛ ክሊንክ ባለን ፅዱ የህክምና ከባቢ በተመጣጣኝ ዋጋ የምንሰጣቸው አግግሎቶች 1⃣ኛ:–አጠቀላይ የአዋቂዎች እና የህፃናት ህክምና 2⃣ኛ:–መለስተኛ ቀዶ ህክምና ግርዛትን ጨምሮ 3⃣ኛ:
ዶ/ር ኑሩ መካከለኛ ክሊንክ
ባለን ፅዱ የህክምና ከባቢ በተመጣጣኝ ዋጋ
           የምንሰጣቸው አግግሎቶች
1⃣ኛ:–አጠቀላይ የአዋቂዎች እና የህፃናት ህክምና 2⃣ኛ:–መለስተኛ ቀዶ ህክምና ግርዛትን ጨምሮ 3⃣ኛ:– የላብራቶሪ አገልግሎት
4⃣ኛ:– የአልትራሳውንድ አገልግሎት 5⃣ኛ :–መንጃፍቃድ ለሚያወጡ እና ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዶ  ሙሉ ምርመራ እንሰጣለን
አድራሻ:ደሴ ተቋም ታክሲ ተራ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ ግራውንድ  የድሮው ወሎ ጠቢብ መካከለኛ ክሊኒክ
ሰልክ ቁጥር:0911121155
ወይም0901173317
ደሴ እና በደሴ ዙሪያ ያላቹህ ሁሉ የተቀላጠፈ አግልግሎት ለማገኘት ዶ/ር ኑሩ መካከለኛ ክልኒክን ምርጫዎ ያድርጉ በአሏህ ፍቃድ ይደሰታሉ

تـفــسيــر الــقـ📖ـرآن الكـــريــــم #الدرس_الجديد   #سورة النحل ٧٢_٧٩ 🎙 للشيخ أبي عمار أول بن أحمد الخميسي  «حفظه الله» https://t.me/DurusSheikhAwol

🎙ታላቅ የዳዕዋ ጥሪ የፊታችን እሁድ ⏰ እሁድ ከምሽቱ 3፡00 ይጠብቁን ተጋባዥ እንግዶቻችን/ኡስታዞቻችን 🎤1 ኡስታዝ አቡል አባስ ሙሃመድ ናስር ባኮ ሃፊዘሁላህ ርዕስ~ጠቅላላ ምክር ነሲሃቱል ዓማ
🎙ታላቅ የዳዕዋ ጥሪ የፊታችን እሁድ ⏰ እሁድ ከምሽቱ 3፡00 ይጠብቁን ተጋባዥ እንግዶቻችን/ኡስታዞቻችን 🎤1 ኡስታዝ አቡል አባስ ሙሃመድ ናስር ባኮ ሃፊዘሁላህ ርዕስ~ጠቅላላ ምክር ነሲሃቱል ዓማ 🎤2 ኡስታዝ አብዱ ሽኩር አቡ ፈውዛን ሃፊዘሁላህ ርዕስ~የባልና የሚስት ሃቅ 🎤3 ኡስታዝ ተውፊቅ ሙሀመድ ሃፊዘሁላህ ርዕስ_ በስዓቱ ይገለፃል 🎤4 ኡስታዝ ሙርሰል ሰይድ ሃፊዘሁላህ ርዕስ _ስለ ሰደቀቱል ጃሪያ ቱርፋቶች ውድና የተከበራችሁ ወንድም እህቶች እነሆ የፊታችን እሁድ ሞቅ ደመቅ ያለ ፕሮግራም አዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ ነው ! ሁላችሁም ጥሪያችሁን በማክበር ኢስላማዊ ግደታዎን ይወጡ  ! መርዳት ባይችሉ ለሚረዱን ወንድምና እህቶች ሸር በማድረግ ይተባበሩን ! ታህሳስ 5/2018 E.C "ወደመልካም ያመላከተ እንደሰሪው ነው " ነብዩ ሰለለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ፕሮግራሙ የሚተላልፍበት የቴላግራም አድራሻ ሊንክ! ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/YeZemzemMesjidJemea https://t.me/YeZemzemMesjidJemea/28226

ዘመነ ኢህአዴግ (ወያኔ) እና የራያ ሙስሊሞች ጭቆና(ከባለፈው የቀጠለ ) ሀ. ሙስሊሞችን ማለያየትና ማጥቃት ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው አፄ ሀይለስላሴ የራያ ሙስሊሞችን በጣም ሊያዳክሙት የቻሉት በመካከላቸው ልዩነት እንዲፈጠር በማድረግ ነበር። ኢህአዴግም ሙስሊሙን የመከፋፈል በተራቀቀ መልኩ በማስቀጣል ኡማው ሊወጣው ወደ ማይችለው አዘቅት ከቶቷል። ኢህአዴግ ሙስሊሙን ለመከፋፈል በኢትዮጵያውያን ብቻ አልተገደበም፤ይልቁንስ ለመንግስት በሚመቸው መልኩ የሚያስተምሩ ፣ የመድረሳዎችና የመስጂዶች መፍረስ ደንታ የለላቸው አስተማሪዎች ከሊባኖስ በማስመጣት ፕሮፓጋንዳ ሰራ። ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል በተለየ መልኩ ቱክረት የተሰጠው ራያ ነበር። ለዚህም ምክንያት ሊሆን የሚችለው ሙስሊሞች ስያደርጉት የነበረው የዲን እንቅስቃሴ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊም ለሀይማኖቱ ያለው ቦታ ክፍ እያለ በመምጣቱ በተጨማሪም ራያ በኢትዮጵያ እስልምና ታሪክ ከፍትኛ ድርሻ ያላት በመሆኑ፣ከፊሉ የራያ ክፍል ደግሞ በትግራይ ክልል ስር በመሆኑ ራያን ማዳከም ግዜ ሊሰጠው የማይገባ በመሆኑ ዘመቻው 2001 ዓ/ል ነው የተጀመረው። ይህም በመላ ኢትዮጵያ ከመጀመሩ ከ3 አመት በፊት ማለት ነው። በ2001 ዓ/ል ሸይኽ ሀሳም አል-ሀሊቢ የተባለ ሊባኖሳዊ አስተማሪ በማምጣት ራያ ኩቤጃብሌ በተባለ ቦታ 80 ለሚሆኑ ስዎች ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናው በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች ጠበቂነትና ስፖንሰርነት የተደረገ ነው። በስልጠናው ከተነሱ ጉዳዮች መካከል «ወሀብዮች» የኢስላም ፀር እንደሆኑና አሁን ላይ መስጂድም፣መድረሳም የሚገነቡት በትክክል ለሙስሊሞች በማሰብ ሳይሆን ኢስላማዊ መንግስት በመመስረት ህዝበ ሙስሊሙና መንግስትን ለማጋጨት እንድሆነ ወዘተ ይገኝበታል። ሌላው ደግሞ እነዚህ ስዎች የአባቶቻችሁን መንገድ ለማጥፋት ተልዕኮ የተሰጣቸው በመሆኑ ሁላቸውም ሊታገሏቸ እንደሚገባ አበክረው ገለጹላቸው። አስተማሪዎችን ከሊባንስ በማምጣት ብቻ ሳይሆን 3 የራያ ልጆችን ሊባኖስ የትምህርት እድል እንድያገኙ በማድረግ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው አላማው እንድያሳኩ ተደርጓል። ራያ ላይ ቀድሞ የመጣው ሙስሊሞችን የመከፋፋልና የማለያየት ሴራ 2003 ዓ/ል መጨረሻ አከባቢ ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ ተጀመረ። ለድጋሚ ስልጠና የተመረጡት የራያ ሰዎች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም4 2014 ዓ/ል ጀምሮ ለተተከታታይ 15 ቀን ስልጠና ተሰጠ። በስልጠናው የክልል ሰላምና ፅጥታ ሀላፊዎችና ሌሎች ባለስልጣናት በተገኙበት «ወሀብያ» የተባለው ቡድን መወገድ እንዳለበት ለዚህም መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግና ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጭምር በማሳሰብ ስልጠና ስጡ። የባህርዳሩ ስልጠና ብዙ ተቃውሞ የደረሰበት ሲሆን ያታሰበዉን ሊያሳካ አልቻለም። የመቀሌው ስልጠና በከፍተኛ ሁኔታ የተሳካ ሲሆን ተመርጠው የሂዱትም ከፊሉ የህወሓት አባል ሌላው ደግሞ ለሀይማኖቱደንታ የለለው የመጅሊስን ወንበር የሚፈልግ ስለሆነ ተቃውሞ ሳይገጥመው ተገባደደ። በመቀጠልም ወጣቶችን በመመልመል በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአዲስ አበባ በሸይኸ አሊ ስልጠና እንዲወስዱአስደረጉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ቀጣይ ለሚደረጉ እርምጃዎች ዝግጂት ነው። ችግሩ በመላ ኢትዮጵያ ተባብሶ የሙስሊሙ ትግል እንዲፈጠር አድርጓል። በስልጠናው መሰረት የመጀመርያ ስራ «ወሀብያ» በተባሉት ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማድረግ ነበር። «ወሀብያ» የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ከላይ የጠቅስኳቸው መስጂዶችና መድረሳዎችን ያስገነቡ፣ የቲሞችንና የሀይማኖት አባቶች እንዲረዱ ያደረጉ ሙስሊም ክርስትያኑ በመልካምነታቸው የሚመስክርላቸው ስዎች ናቸው። ወጥመድ ውስጥ የገቡበት ምክንያት እስልምናን ለማጠናከር በሰሩት ስራ ነው። ለኢስላም የሚሰራና ጠንካራ ሙስሊም ሁሉ ወህብያ የሚል ስያሜ ሰጡት! ኢስላምን ማዳከም የሚቻለው ለኢስላም የሚሰሩ ስዎችን በማዳከም መሆኑ ግልፅ ነው። ይህን ተከትሎ በስልጠና የወሰዱትን ፕሮፓጋንዳ ለህዝበ ሙስሊም ማድረስ ይመቻቸው ዘንድ መጀመርያ ያደረጉት ለኢስላም የሚቆሩቆሩ ኢማሞችን ማባረር ነበር። እነሱን ከመስጂድ ካባረሩ በኋላ ዘመቻ ጀመሩባቸው። ዘመቻው ከአላማጣ ጀምሮ እስከ መሆኒ እና ከኮረም እስከ ማይጨው ድረስ በሁለት ቡድን የተከፈለ ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ሊባኖስ ሰልጥነው በመጡ ስዎችና በአከባቢ ተሰሚነት ያላቸው ስዎች ነው የተደረገው። የዘምቻው ዋና አላማ «ወሀብያ» ብለው የሰየሟቸው ሰዎች ሙስሊም እንዳልሆኑና ካፊር በመሆናቸው ህዝበ ሙስሊሙ ሊጠነቀቃቸው እንዲሚገባ ነበር። በዚህ ፕሮፓጋንዳቸው ማህበረሰቡ በተለይ የገጠሩ ክፍል መደናገር የፈጠረ ሲሆን ያላመነዉን ደግሞ የሀይል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጁ። ፕሮፓጋንዳው ሁሉም ባይሆንም አብዘሀኛው ሰው በውድም ሆነ በግድ እንዲቀበል ማድርግ ችሏል።ከዚህ ቡኋላ የቀጠለው በመንግስታዊ መዋቅር በመታገዝ ማጥቃት ነው።

ዘመነ ኢህአዴግ (ወያኔ) እና የራያ ሙስሊሞች ጭቆና የኢህዴግ 1983 ዓ/ል ወደ ስልጣን በመጣበት ማግስት የራያ ሙስሊም ነፃነት ተጎናጽፏል። የራያ ኡለሞች ይህንን እድል በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቅምዉበታል። በውጭ ሀገር የነበሩትም ወደ ሀገራቸው በመግባት ከፌደራል መጂሊስ ጋር በመተባበር አላማጣ ከተማ ላይ ለመጀመርያ ግዜ መጂልስ አቋቋሙ። ሸይኸ መሀመድ ነጅብ ሊቀ መንበር ፣ ፀሀፊ ደግሞ ዘይኑ አረቡ እንዲሁም ሸይኽ ሱልጣን አህመዳልሃዲ በመሆን መጂሊሱን አቋቁመው እንቅሰቃሴ ጀመሩ። የራያ መሻኺኮች ሰለራያ ሙስሊም ሁኔታ በኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሱ ማህበራት፣ኢስላማዊ ተራድኦ ድርጂቶች በማስተዋወቅ ከፍተኛ ስራ መስራት ችለዋል። በራያ አጠቃላይ 16 የግንብ መስጂዶች እንዲገንቡ ሲያደርጉ 6 መስጂዶች ደግሞ በጭቃ እንዲሰሩ አድርገዋል። ቁርአንም በተለያዩ ከተሞች እንዲቀራ ሁኔታዎች አመቻችተዋል፤ ለምሳሌ በአላማጣ ሉቅማን አል-ሀኪም መድረሳ እንዲሰጥ በማድረግ ብኋላም ዘመናዊ የሆነ መድረሳ በአላማጣ ከተማ ስታድየም ፊትለፊት በመግንባት ለተማሪዎች በነፃ ዩኒፎም በማደል ቁርአን በተሻለ መልኩ እንዲቀራ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ የራያ ክፍል የቲሞችና ሚስኪኖች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች ድጋፍ እንዲያገኙ አድርገዋል። የተለያዩ ፈተናዎች እተጋረጠባቸው ቢሆንም ፈተናዉን ተቋቁመው ለውጥ ለማምጣት ችለዋል። የራያ ሙስሊሞች የተጎናፀፉት ነፃነት እንደተመኙት አልቀጠለም፤ በእርግጥ ከመጀመርያዉም አልጋ በአልጋ ባይሆንም የተሻለ ሁኔታ በመኖሩ አያሌ ስራዎች መስራት ተችሏል። ሙስሊሙ ማሰዳድና ጫና መፍጠር የተጀመረው በ1989 አከባቢ ነበር። በሙስሊሙ መካከል ያለው ልዩነት በማስፋት እርስበርስ እንዲጋጩ መንግስት ማሴር ጀመረ። በሙስሊሙ መካከል የነበረው ችግር እንደምክንያት በመጠቀም ዲኑን ለመርዳት የሚንቀሳቀሱ ኡለሞችን በመለየት ተፅኖ አደረሱ። አንዳንዶቹ በአላማጣ መጅሊስ በማቋቋምና ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ብዙ ስራዎች በመስራታቸው አይን ውስጥ ያደረጋቸው ሲሆን የቤተሰቦቻቸውን መስጂድ በኢማምነት ስያስግዱ የነበረ ቢሆንም በደረሰባቸው ጫና አላማጣን ጥለው ወልድያ በመሄድ ለ6 አመታት ኢማም በመሆንና በማስቀራት አሳልፈዋል። ከ1995 አከባቢ በመስጂዶች ዙርያ የሚከራዩ ግንባታዎችን በመገንባት መስጂዶች ራሳቸው እንዲችሉ እንቅሰቃሴ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በመንግስት ተፅኖንና ህዝበ ሙስሊሙን በማይውክሉ አካላት እንዲቆም ተደርጓል። የ02 መስጂድ ከፊትለፊት ለግንባታ የተዘጋጀው መሰረት እስከቅርብ ግዜ መኖሩ ሁላችን የምናውቀው ነው። ከዚህ በተጨማሪ 3/30/1996 ዓ/ል በኩኩፍቶ ከተማ መስጂድ በሀይል በመቀማትና ከዚህ በፊት መስጂዱን ያስገነቡት እንዲሁም ኢማም የነበሩትን በማባረር መንግስት ጭቆናውን አጠናክሮ ቀጥሏል። መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰው ጫና በአይነት እየጨመረና እየተወሳሰብ መጣ፤ የነበሩ ችግሮች አጠር አድርገን ለማየት በርዕስ ከፋፍለን እንየው፡

የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ይመዝገቡ! ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 02-12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡

መልካም ዜና፡ "መብሩክ"ባልትና፡የተለያዩ የቤት ምሮቶችን ለተጠቃሚዎች የምናቀርብበት የስራ ቦታችን ነው።እናማ የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን ይዘን ተከሰተናል በመሆኑም፡በመግዛትም ሆነ ማስታወቂያ ሸር በ
መልካም ዜና፡ "መብሩክ"ባልትና፡የተለያዩ የቤት ምሮቶችን ለተጠቃሚዎች የምናቀርብበት የስራ ቦታችን ነው።እናማ የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን ይዘን ተከሰተናል በመሆኑም፡በመግዛትም ሆነ ማስታወቂያ ሸር በማድረግ አበረታቱን።እናመሰግናለን የምንይዛቸው አቅርቦቶች፦ >ምጥን ሽሮ >ነጭ ሽሮ >በርበሬ >ድፍንና ክክ ምስር >የሾርባ እህሎች >አተር ክክና የፉል ባቄላ >የገንፎ ዱቄትና የአጥሚት ዱቄት፦ *ፓስታ መኮሮኒና ሌሎችም።እናንተ ጠይቁን እናቀርባለን።በብዛት ለምትፈልጉ ወደ ወሎና አካባቢዋ እንልካለን። አድራሻ፡ኬሚሴ//ስልክ፡+251914466875፡ይደውሉ እንታዘዛለን። የቴሌግራም አድራሻችን፦ t.me/+juaC6nCRCcdkNWQ8

አፄ ሀይልስላሴ ባሴሩት ሴራ ሙስሊሙ አንድ ሁኖ ጠላቶቹ ላይ እንዳይነሳ በማድርገ ተከፋፍሎ እርስበርሱ እንዲባላ ማድረግ በመቻላቸው እስልምናን ስልታዊ በሆነ መልኩ ማዳከም ችለዋል። ሙፍቲ ራያ በሚያስተምሩበት ዳንሳ ከፍተኛ ችግር ሲደርስባቸው የነበረ ቢሆንም የምያስቸግሯቸው ስዎችን ለመገሰፅ ቁርአንና ሀዲስን መሰረት አድርገው ለማስተማር ቢሞክሩም ስዎቹ ሊያቆሙ ባላመቻላቸው ዳንሳን ጥለው ወደ ኩቤጃብሌ ሂደዋል።............

በአፄ ሃይሌ ስላሴ (1930-1974) ዘመነ መንግስት አጼው በራያ ሙስሊሞችን ላይ ሲፈጽም የነበረው እስልምናን የማዳከም ተንኮልና ሴራ ይህን ይመሥል ነበር። አፄ ሀይሌስላሴ ለሙስሊሞች ከመጀመርያው ጀምሮ ከፍተኛ ጥላቻ እንደነበራቸው ይታወቃል። አፄ ሀይሌስላሴ በራያ ሙስሊሞች ያደረሰው ጉዳት ከሌሎች አንፃር ሲታይ እንጅግ በጣም የከፋና ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሁኖ አልፏል። ይህም የሆነው አፄ ዮሃንስና አፄ ምኒሊክ ግልፅ ጦርነት በማወጃቸው ሙስሊሙ በቻለው መጣን እየታገለ ራሱን ለማዳን ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። በአንፃሩ አፄ ሀይሌስላሴ ግልፅ ጦርነት ከማወጃቸው በተጨማሪ በሴራና ተንኮል ሙስሊሙን በመከፋፈል እርስበርስ እንዳይተማመን በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እድርሰዋል። አፄ ሀይሌስላሴ ሙስሊም ያልሆነን ሰው አዝሀር ድረስ አረብኛና የኢስላም ትምህርት እንዲወስዱ በማድረግ ሙስሊሙን ሲከፋፍሉና ስያለያዩ እንድነበር ይታወቃል። እነዚህ ስዎች በውስጣቸው ክርስትያን ቢሆኑም የሙስሊም ሀይማኖት አባት በመመሰል ኢስላማዊ መፅሐፎችን እስከማዘጋጀት ደርሰዋል። አፄ ሀይሌስላሴ በ1923 ዓ/ል ከነገሱበት ግዜ ጀመሮ ሙስሊሙን ስያጠቁና ስያሳድዱና ስጨፈጨፍ ነበር፤ ይህንን የተገነዘበው ጣልያን በ1935 እ.ኤ.አ ራያ ላይ በራሪ ወረቆችን በትኗል። የራያ ህዝብ ሙስሊሙ በመሆኑ በሸዋ ክርስትያኖች ከፍተኛ ስቃይና መከራ እየደረሰበት እንደሆነና የጣልያን መንግስትም ከጎኑ የሚሰለፉ ከሆነ የጦር መሳርያ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውና አከባቢውን ሲቆጣጠር የሀይማኖት ነፃነት እንዲምያጎናፅፋቸው የሚገልጽ በራሪ ወረቀት ራያ ላይ እንዲበተን አድርጓል። ጣልያን ከዚህ በፊት በአፄ ምኒሊክ ግዜ ካስታጠቃቸው የጦር መሳርያ በተጨማሪ የተለያዩ የጦር መሳርያ ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንዲሰለፉ አድርጓል። ራዮች በአፄ ሀይለስላሴ ሰራዊትም ቢሆንም በጣም እንደሚፈሩና በአንደ አከባቢ ብቻ ከ10 ሺህ ሰራዊት በላይ የአፄውንሰራዊት እየጠበቁ እንደሆንና እነሱን አሽንፎ ማለፍ የማይታሰብ መሆኑን የሀበሻ ጀብዱ ፀሀፊ ግልጿል። በ1928 ዓ/ል ማይጨው ጦርነት የአፄ ሀይለስላሴ ጦር ሽንፈት ገጥሞት ወደኋላ ስያፈገፍግ ራዮች ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዉባቸዋል። የራስ ሙሉጌታ ጦር ከጣልያ ጦር ሽሽተው ሀሼንጌ አከባቢ ሲደርሱ በራያ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ሽንፈት የገጠማቸው አፄ ሀይለስላሴ በዋግ አድርገው ወደ ጁቡቲ በማቅናት ወደ እንግሊዝ ሀገር ተሰድተዋል። ጣልያን ኢትዮጵያን ለ5 አመታት ከ1928-1933 ዓ.ል ገዛ። ራዮች ከጠልያን ጋር እንዲተባበሩ ያደረጋቸው ክህድት ወይም ባንዳነት ሳይሆን በሸዋ ሹማንምንቶች የሚደርስባቸው ግፍና መከራ ነው። አፄዎቹ እስልምናን እንዳይማር፣ እንዳያስተምር መስጂዶቹን በማቃጠልና ኡለሞችን በመግደልና በማሰር ሲደረግ የነበረው ግፍ በመቃወም ሀይማኖታቸውንና ክብራቸውን ለመጠበቅ ያደረጉት ተጋድሎ እንጂ እንዳንዶቹ እንደሚሉት የባንዳነት ስሜት ስለነበራቸው እንዳልሆነ ጣልያን ከገባ ብኋላ የተፈጠሩ ክስተቶች ማሳያ ናቸው። በሸዋ ሹማምንቶች ከፍተኛ በደል ምክንያት ራዮች ለነገስታትቱ ጥላቻ እንደነበራቸው የሀበሻ ጀብዱ ደራሲ አውስቷል። ጣልያን ኢትዮጵያን በተቆጣጠረበት 5 አመታት ራዮች ከዚህ በፊት ያላገኙት ነፃነት ተጎናጽፈዋል፤ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከኦሮምያ፣ ሀረር፣ ስልጤ ሳይቀር ወደ ራያ በመምጣት ከሙፍቲ መሀመድ ሲራጅ (ሙፍቲ ራያ) መማር ችለዋል። በግዜው አያሌ መስጂዶች መገንባትና እየተንቀሳቀሱ ኢስላማዊ አስተምህሮቶች መስጠች ችለዋል። እነዚህ 5 አመታት ለራያ ሙስሊሞች ከአፄዎቹ አንፃር ሲታይ የእፎይታ ግዜ ነበሩ። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ራዮች ሙስሊም በመሆናቸው ሲድርስባቸው በነበረው ግፍን በመቃወም እንጂ ጣልያንን ወደውና ደግፈው እንዳልነበረ ከምያሳዩት ክስተቶች ዉስጥ ሂጅራ የሚገኝው ታሪካዊ መስጂድ ጣልያን በወቅቱ ለነበሩት የጀማሉድን አል-አኒይ የልጅ ልጂ እንዲሁም የሙፍቲ ራያ ተማሪ ለሆኑት ሽይኽ አብዱሰመድ መስጂድ ገንብቶላቸዋል። ጣልያን የሀይማኖት ነፃነት ያጎናጻፈቸው ቢሆንም ጣልያን በሰራው መስጂድ እንዳይሰገድ በማድረግ ለጣልያኖች ያላቸውን ጥላቻ አሳይተዋል። ከዚህ አልፈውም የራያ ኡለሞች ጣልያንን መታዘዝ አግባብ አለመሆኑን አስተምረዋል በዚህም ምንክያት ጣልያን ከሙስሊሞች ጋር ቅራኔ ውስጥ የገባ ቢሆንም ከሌሎች መንግስታት አንጻር ሲታይ የራ ህዝብ ሰላም አግኝቷል ማለት ይቻላል። በ1933 የጣልያ ጦር ኢትዮጵያን ለቆ ሲወጣ የአፄው ሰራዊት በራያ ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰድ ጀመረ። የሚደርሰው ግፍና መከራ እየባሰ በመምጣቱ በ1935 ዓ/ል አመፁ ተቀጣጣለ፤ ከቆቦ የጀመረው የራዮች አመፅ እየተጠናከረ በመሄድ ወጀራት ብሎም እንደርታን አዳረሰ ይህም «ወያነ» ተብሎ የሚጠራውን ትግል ፈጥሯል። አመፁ ጥቅምት 1936 ዓ/ል በቁጥጥር ስር ከዋለ ብኋላ በራዮች ላይ ከፍተኛ ስቃይና መከራ ደረሰ። ከአመጹ መክሽፍ ብኋላ ራያ በወታደራዊ ስር እንድተዳደር በማድረግ ብዙ መስጂዶች እንዲቃጠሉና ኡለሞችም እንዲታሰሩ አድርገዋል። በአፄ ዮሃንስና አፄ ሚኒሊክ ከተቃጠሉ መስጂዶች ይልቅ አፄ ሀይለስላሴ ያቃጠሉት በቁጥር ይበልጣል። ከመስጂዶች መቃጠል በተጨማሪ ብዙ በኡለሞችቻን የተጻፉ መጽሐፎች ተቃጥለዋል። ከአፄ ዮሃንስና ምኒሊክ ጥቃት ለመታደግ በራያ ጋንዳባ ጡባ አከባቢ አሁንም ድረስ «መሸኮዒ ኽታብ - የኪታብ መደበቅያ» ተብሎ በሚጠራው ዋሻ በመደበቅ መታደግ ቢቻልም የሚበዙት በአፄ ሀይልስላሴ ተቃጥለዋል። መስጂዶችንና መጽሐፎች ከማቃጠል በተጨማሪ ሙስሊሙን ከሁለት በመክፈል አፄው ስጋት ይሆኑብኛል በለው የሚያስቧቸው የሀይማኖት አባቶች ስም በማጠልሸት መምታት ችለዋል። የሙስሊሙ እንድነት ለመሸርሸር የተጠቀሙት መንገድ እሳቸውን ለሚደግፍ የሀይማኖት አባቶች ድጋፍ በማድረግ በሌሎች ላይ ችግር እንዲፈጠር አድርገዋል። አሁን ላይ «ወሀብያ» ተብለው መከራና ስቃይ እንደሚያዩት በአፄ ሀይልሰላሴ ግዜ ደግሞ «ሙዕተዚላ» የሚል ታፔላ በመለጠፍ ኡለሞችን አሰቃይተዋል። የዚህ ሴራ ሰልባ ከሆኑት መካከል ታላቁ አሊም የሀበሻው ሙፍቲ መሀመድ ሲራጅ ነበር። ሙፍቲ መሀመድ ሲራጅ በተለያዩ የአለማችን ክፍል በመጓዝ ከፍተኛ እውቀት የቀሰሙ በመጨረሻው ሙፍቲ ተብለው ከፍተኛ ማዕረግ የተሰጣታቸው ታላቅ አሊም ቢሆኑም አፄ ሀይስላሴ በአይነቁራኛ ሲከታተላቸውና በራሱ ስዎች ፕሮፓጋንዳ ስያስነዛባቸው ከቆየ ብኋላ በ1366 ሂጅራ ማለትም 1937 ዓ/ል መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ በሚል በመቀሌ ወታደራዊ እስርቤት እንዲታሰሩ በማድረግ በመጨረሻም መፈንቅለ መንግስት ከተለያዩ የውጭ ሀገራት በመሆን ሞከረዋል በማለት የሞት ፍርድ ተፈዶባቸዋል። የሞት ፍርድ ቢፈርድባቸውም በአላህ እገዛ ቀጥሎም ራስ ስዩም ሙፍቲ ራያ ላይ የሚወራው ውሸት እንደሆነና ከፖለቲካ ጋር ንክኪ እንደሌላቸው በመመስክራቸው ምክንያት ሀይለስላሴ የሞት ፍርዱ እንዲቀር በመወሰን 7 አመታት እንዲታሰሩ አድርጓል። ሙፍቲ ራያ ከሞት ፍርድ ቢተርፉም በእሳቸው ላይ ሲደርስ የነበረው መከራና ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ችግር ሲደርስባቸው የነበረው ቀጥታ ከሀይልስላሴ ሳይሆን ከራሳቸው ወገን ሙስሊሞች በመሆኑ እጂጉን ከባድ አድርጉታል።

አፄ ምኒሊክ (1989-1913) እና የራያ ሙስሊሞች የመከራ ዘመን የራያ ሙስሊሞች በአፄ ዮሃንስ የተጀመረው ግፍ በአጼ ሚኒልክም ቀጥሏል። ሸይኽ ጦልሀ ጃዕፈር በዓሳውርታ ሰራዊት ለመመልመል በተጓዙበት ከጀማሉዲን አል-አሊይ ጋር ቃልኪዳን አድርገዋል (በአረብኛው ባይዓ ማለት አብሮ ለመዋጋት፣ለመተጋገዝ መስማማት Military alliances ማለት ነው) ፤ በቃልኪዳኑ መሰረት ሽይኽ ጠልሀ ከራያ ብዙ ተዋጊዎች እንዲቀላቀሉ በማድርግ ራያን በተለይም ሀሼንግን እንደዋና ምሽግ ተጠቅመዉበታል። ሸይኽ ጠልሀ አፄ ዮሃንስ በወሎ ሙስሊሞች ላይ ሲያደርሰው የነበረው ግፍ በመቃውም ሲዋጋ እንደነበር ይታወቃል።በአፄዮሃንስ ላይ በሸይኽ ጠልሀ የሚደረገው የደፈጣ ውግያ በ1884 እ.ኤ.አ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሸይኽ ጠልሀ ሰራዊት አብዘሀኛው ከራያና ዓሳ ዉርታ የተመለመሉ ነበሩ። ጣልያን በአፄዎች የሚደርስባቸው ግፍና መከራ ለመቋቋም ከፍተኛ ትግል ስያደርጉ የነበሩ የራያና ወሎ ሙስሊሞች ለመጠቀም (exploite ለማድረግ) ከፍተኛ እንቀሰቃሴ አድርጋለች። ኢትዮጵያን ቀኝ ለመግዛት ፍላጎት ያላት ጣልያን ጭቁን ሙስሊሞችን ከራሷ ጋር በማሰልፍ በቀላሉ ኢትዮጵያን ለማሰተዳድር የጦር መሳርያ ድጋፍ አድርጋለች። ሙስሊሞች ከጣልያን ጋር ስምምነት ያደረጉት ባንዳ ሁነው አልያም ሀገራቸውን ጠልተው አይደለም ይልቁንስ በስው ልጅ ሊፈፀም የማይገባው ጭካኔ የተሞላው ዘመቻ ስለተደረገባቸው ነው። አፄ ዮሀንስ በሙስሊሞች ያደረሰው በደል እንዲሁም ሚኒሊክ እያደረሰው የነበረው ግፍ ታግሎ ለመቀልበስ የግድ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ሙስሊሞቹ ከጣልያን ያገኙት ድጋፍከጣልያን ጋር በማበር ሀገራቸውን ለመውጋት እንዳልሆነ የተከሰቱ ሁነቶች አስረጂ ናቸው። አፄ ሚኒሊክ ጣልያንን ለመውጋት ሲመጣ ሰራዊቱ በደረሰበት ያራያ አከባቢዎች መስጂዶች፣ቤቶች፣ሰብሎችን በማቃጠል ሀብትና ንብረት በመዝረፍ ነበር። የራያ ህዝብ በሚኒልክ ጦር ከፍተኛ ስቃይ ደርሶበታል። በአፄ ሚኒሊክ የሚደርሰው ግፍ ለመታገል በሸይኸ ጠልሀ የሚመራው የሙስሊም ሰራዊት ተራራማው የራያ ክፍል ተቆጣጥረው ሀሸንገን የጦሩ መዕከል አድርገዋል። ከእምባ አላጄ ጦርነት በፊት በሸይኽ ጠልሀ የሚመራው የሙስሊሙ ሰራዊት ሀሼንጌ ላይ ከ300-350 በማስፈር የሚኒልክ ጦርን መጠባበቅ ጀመሩ። ጦርነቱ በተጀመረ ግዜ ሸይኽ ጠልሀ ያጣልያንን አላማ ወደጎን በመተው ከውግያው ወጥተዋል። ይህም ትግላችው ሀይማኖታቸው ለማስጠበቅ እንጂ ሀገርን ለመካድ አልያም ሌላ አላማ እንዳልነበረው የሚያሳይ ነው። አፄ ሚኒሊክ በሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰው ግፍ አጠናክሮ ቀጥሏል፤ አያሌ ሙስሊሞች ተገድለዋል፣ መስጂዶቻቸውና ቤታቸው ተቃጥሏል በዚህም የራያ ህዝብ ቂም አድሮበታል። በጣልያኖች ድጋፍ የታጠቀው የራያ ህዝብ አፄ ሚኒሊክ አድዋ ላይ ድል ቀንቷቸው ወደ ሸዋ በሚመለሱበት ወቅት ከፍተኛ ጥቃት በመፈፀም ሲደርስባቸው የነበረውን ግፍ ተበቅለዋል። የታሪክ ፀሀፊያን አፄ ሚኒልክ አድዋ ላይ ካጡት ስራዊት ይልቅ ራያ ላይ ያጡት በቁጥር እንደሚበልጥ ገልፀዋል። አፄ ሚኒሊክ እንደ አፄ ዮሃንስ የማጥመቅ ዘመቻ ባያውጁም በራያ ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ጉድት አድርሰዋል።

ኧረ እንዲህም ታስቧልን?

የማለዳ መልእክት ~ * የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአንድ ወቅት : "የከሰረ ሰው ማለት ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?" ብለው ጠየቁ። - ሶሐቦችም ፡ "ከእኛ መካከል የከሰረ ማለት ገንዘ
የማለዳ መልእክት ~ * የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአንድ ወቅት : "የከሰረ ሰው ማለት ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?" ብለው ጠየቁ። - ሶሐቦችም ፡ "ከእኛ መካከል የከሰረ ማለት ገንዘብ እና ንብረት የሌለው ሰው ነው" ብለው መለሱ። * ነብያችን በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦ «إن المفلس من أمتي من يأتي يوم القيامة بصلاة وصيام وزكاة، ويأتي وقد شَتَمَ هذا، وقذف هذا، وأكل مال هذا، وسَفَكَ دم هذا، وضرب هذا، فيعطى هذا من حسناته، وهذا من حسناته، فإن فنيت حسناته قبل أن يُقْضَى ما عليه، أخذ من خطاياهم فَطُرِحتْ عليه، ثم طُرِحَ في النار». "ከሕዝቦቼ መካከል በእውነት የከሰረ ማለት፤ በቂያማ ቀን የሶላት፣ የጾም፣ የዘካ፣ ... (ምንዳ) ይዞ የሚመጣ ነው። ነገር ግን ይህንን ሰድቦ፣ ይህንን በዝሙት ወንጀሎ፣ የዚህን ገንዘብ (በግፍ) በልቶ፣ የዚህን ደም አፍስሶ፣ ይህንን መትቶ፣ ... ይመጣል። ከዚያም ለዚህኛው ከመልካም ስራው ይሰጠዋል፤ ለዚያኛውም ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። በእርሱ ላይ ያለበት (የበደል) እዳ ተከፍሎ ሳያልቅ መልካም ስራዎቹ ካለቁበት፣ ከእነርሱ (ከበደላቸው ሰዎች) ወንጀል ተወስዶ በእርሱ ላይ ይጫንና ከዚያም ወደ እሳት ይወረወራል።" [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2581] ይህ ሐዲሥ በኢስላም ውስጥ እጅግ አስፈሪ እና ትልቅ ማስጠንቀቂያ ከያዙ ሐዲሦች ውስጥ አንዱ ነው። ከሐዲሡ ከሚወሰዱ ቁም ነገሮች ውስጥ ጥቂት ለማንሳት ያህል፦ = 1- የኪሳራ ትርጉም፡ ሰዎች በተለምዶ ኪሳራ ሲባል የሚያውቁትና የሚያስደነግጣቸው የገንዘብና የንብረት ማጣት ነው። ይህ ዓይነቱ ኪሳራ ግን በዱንያ የሚያልቅ ቀላል ኪሳራ ነው። ከባዱ ኪሳራ የቂያማ ቀን ኪሳራ መሆኑን ከሐዲሡ እንማራለን። 2- ዒባዳ ብቻውን ዋስትና አይደለም፡ አንድ ሰው ሶላት ቢሰግድ፣ ፆም በያይነቱ ቢጾም፣ ዘካ ቢያወጣም፣ ሌሎች ዒባዳዎችንም ቢፈጽም፤ ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት (ስነ-ምግባሩ) የተበላሸ ከሆነ ለአደጋ የተጋለጠ ነው። ኢስላም ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነት (ዒባዳ) እና ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት (ሙዓመላ) ያጣመረ ሃይማኖት ነው። 3- የቂያማ ቀን መገበያያ፡ በዚያ ቀን ብር ወይም ወርቅ አይሰራም። መገበያያው "ሐሰናት" (መልካም ስራ) እና "ሰይኣት" (ወንጀል) ብቻ ነው። የሰው መብት የነካ ሰው መልካም ስራውን ለበደላቸው ሰዎች ይከፍላል። መልካም ስራው ካለቀበት ደግሞ የእነሱን ወንጀል ተሸክሞ ወደ እሳት ይወርዳል። 4- የሰዎች ሐቅ፡ ይህ ሐዲሥ የሰዎችን ደም ማፍሰስ፣ ገንዘብ መብላት፣ ስም ማጥፋት እና መሳደብ ምን ያህል ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ያሳያል። አላህ የሰዎችን መብት ከመንካት፣ የዚያን ቀን ከሳሪዎች ከመሆንም ይጠብቀን። * ይሄ ሁሉ ሰልፈኛ ሐቃቸውን ከኛ ለመውሰድ የተሰለፉ ቢሆኑ ብለን እናስብ እስቲ። አላህ ልብ ይስጠን። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

ጠቃሚ የፈትዋ ጥያቄና መልሶቻቸው ከሸይኽ ፈውዛን ጋር

የራያ ሙስሊሞች የጭቆና ቀምበር 1. በኢማም ጀማሉዲን አኒይ ላይ የተሞከረው የመጀመርያ ጥቃት ጀማሉዲን አል-አኒይ ለማጥቃት እንደ ሂጅራ አቆጣጠር በ1296 ማለትም 1871 ዓ.ል(እ.አ.አ 1878) አፄ ዮሃንስ ከመቀሌ መደ ራያ ተጓዘ፡፡ነገር ግን ጉዞው ወደ ራያ እንዳልሆነና ወደ ሸዋ ለመሄድ እንደመጣ አስነገረ ለዚህም ራያን አልፎ በሰቆጣ ከዝያም ላስታ አደርጎ ወሎ ገባ፤ ይህንን ያደረገበት ምክንያት የራያ ሰዎች እንዲዘናጉ ለማድረግ ነው፡፡ ወሎ ግዛት ከደረሰ ቡኃላ ሌሊት በመመለሰ ወልዲያ አጣገብ በሚገኘው ጉባ ላፍቶ ላይ አረፈ፡፡ ጉባ ላፍቶ ላይ ሆኖ ሸይኹን ማርኮ አልያም ገድሎ የሚመጣ ሰራዊት ላከ፡፡ የአፄ ዮሃንስ ሰራዊት ወደ ራያ መዝመቱን የሰሙት ሸይኽ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ የሚከታተል ሰው አደረጉ፤ ከዋጃ በስተደቡብ በኩል መድረሱን መረጃ የደረሳቸው ተማሪዎቹ ሸይኹን ከመስጂድ ሲያስወጧቸው የዮሃንስ ሰራዊት ሂጅራ መስጂዳቸው ላይ ደረሰ፡፡ መስጂዱ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ዉግያ ሶስት ሰዎች ከሸይኹ ሲከላከሉ ተሰው፤ቢሆንም ግን የሸይኽ ጀማሉዲን አልአኒይ ተማሪዎች ሸይኹን ከመስጂድ አውጥተው ደብቀዋቸው ስለነበር ጉዳት ሳይደርስባቸው ቀረ፡፡ ከታመሪዎቹ መካከል በእድሜ ትንሹ የሆነው ሸይኽ አሊ ዳንዳ ‹‹ ኢንጆሌ አባ አልቃሲም›› ‹‹ ኢንጆሌ በድር›› በማለት ፎክረው የተማሪዉን ሞራል አነሳሱት በኦሮምኛ ትርጉምም «እኛ የአቡ አልቃሲም ወጣቶች›› ‹‹ እኛ የበድር ወጣቶች›› ነን በማለት ለጠላት እጅ እንደማይሰጡ ተምሳሌታቸው ደግሞ የአቡ አልቃሲም ማለትም የነብዩ( የአላህ ሰላት እና ሰላምበእሳቸው ላይ ይሑን) ባልደረቦች የሆኑት የበድር ወጣቶች እንደሆኑ በማበሰር ወጣቱን በከፍተኛ ሞራል አነሳስትው የአፄውን ሰራዊት ድል ነስተዉታል፡፡ የተሰዉት የሚከተሉት ነበሩ 1) አብደላህ አል-ሙኣዚን ፡- የሸይኽ መስጂድ መአዚን፤ ሙአዚን ማለት የሰላት ጥሪ የሚያደርግ ሰው ማለት ነው፡፡ 2) ሸይኽ ቡዳላ ከራያ ትላልቅ አባገሮች አንዱ ነበሩ፡፡ አባጋር ማለት የሀገር ሽማግሌ እንደማለት ሲሆን ሰዎችን፣ ጎሳዎች ሲጣሉ የሚያስታርቁ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡ 3ኛው ከሸይኹ ተማሪዎች መካከል ነው፡፡ የጀማሉዲን አል-አኒይ የልጅ ልጂ ሸይኽ አብዱልጀሊል ይህንን ክስተት እንዲህ ሲሉ ገልፀዉታል፡ ‹‹ ሰራዊቶቱ ጁምዓ ቀን ደረሱ፤ ሸይኽ አል-አኒይ ድንገተኛ የሆነ ዱበዕዳ ወረደባቸው፡፡ አላህ ሸይኹን እና ተማሪዎቹን ከጥቃት ቢጠብቃቸውም በተደረገው ዉግያ ሶስትባልደረቦቻቸው ተሰው፡፡ ሸይኹ ራቅ ብለው ከከፊል ተማሪዎቻቸው ጋር በመሆን ተደበቁ፤የአፄው ወታደሮች ለ15 ቀናት በተከታታይ ሸይኹን ለመያዝ ሙከራ ቢያደርጉም የሸይኹ ፈረስ እናእቃዎቻቸዉን እንጂ አኒይን መያዝ አልቻሉም፡፡ ሁለተኛው ጥቃት የመጀመርያው ጥቃት ስላልተሳካ ሁለተኛውን ጥቃት በሚስጥር በማድረግ ሙስሊሞቹ በማይጠብቁን በኩል ማለትም በአፋር ሔርቶ ግዛት በምስራቅ ራያ ጨርጨር አድርገው ሃዳ አልጋን በማቋረጥ በሚስጥር ጋባተ ደረሱ፡፡ እዚህ ቦታ ላይ የታላላቅ ኡለሞች መቃብር ይገኛሉ፤ ሰራዊቶቹ መቃብሩ አከባቢ ሲደርሱ ሰዎች እዚህ አከባቢ እንደሚኖሩ የሚያመላክቱ ምልክቶች የሰው ኮቴ፣ የተሰበረ ስኒ እና እቃዎች ተመለከቱ፡፡ ከዚህ በመነሳት ሸይኹ እዚህ አከባቢ ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገመት የእግር ኮቴ እየተከተሉ ጉዛቸዉን ቀጠሉ፡፡ ኩቤ ጥና ተብሎ የሚጠራው ኮረብታ ላይ ደረሱ ኩቤ ጥና ማለት ትንሽ ኮረብታ ማለት ሲሆን ኩቤ ባግኤ በመባልም ይታወቃል፡፡ ኩቤ ጥና ላይ የአፄ ዮሃንስ ሰራዊት እና የሸይኹ ተማሪዎች ተገናኙ ባልተጠበቀ ሁኔታ መራር ዉግያም ተደረገ፡፡ ከዮሃንስ ሰራዊቶች አንፃር የሙስሊሞች ቁጥር እጅግ በጣም ጥቂት እና ከትጥቅ አንፃር የማይወዳደሩ ቢሆንም ፍልምያው ተጀመረ፡፡ ፍልሚያው በጣም አስጨናቂ የነበረ ቢሆንም በሃጂ ዓልዩ በሚመራው በሙስሊሞች ድል ተገባደደ፤ የአፄው ሰራዊት አብዛኛው ተገድሎ ደጃዝማች ተላ እና ሌሎችም ሸሽተው አመለጡ፡፡ ከዚያ ቀን ቡኋላ ኩቤ ጥና ተብሎ የሚጠራው ቦታ ኩቤ ጃሃዳ ማለትም የጂሃድ ኮረብታ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት እስካሁን ድረስ ቢዘህ ስያሜ ይጠራል፡፡ ስለ ኩቤ ጃሃዳ ሲወሳ ሙስሊሞች በኩራት የአያቶቻቸው ጀግንነት ያወሳሉ የአያቶቻቸዉን ጀግንነት በትግርኛ፣አረብኛ እና ኦሮምኛ በግጥም መልኩ ያንጎራጉራሉ፡፡ ኩቤ ጃሃዳ የሙስሊሞች የድል ተምሳሌት!!! ሀይማኖትን፣አገርን እና ክብርን ለመጠበቅ በተደረገው መራራ ጂሃድ ከሙስሊሞች 12 ሰዎች ተሰው (አላህ ጀነት አልፊርደዉስ ይወፍቃቸው)፡፡ የአሰራ አንዱ አስከሬን ተገኘ አንዱ አስክሬን ግን ሊገኝ አልቻለም፤ ሸይኹ የጠፋው የማን አስከሬን እንደሆነ ሲጠይቁ የሀቢብ ያዮ እንደሆነና ምናልባች ዉግያዉን ትቶ ሸሽቶ ሂዶ ሊሆን እንደሚችል ነገሯቸው፡፡ ሸይኹም ሀቢብ ያዮ በፍጹም ይህንን አያደርግምና ፈልጉት ሲሉ አዘዙ፤ በተደገረው ፍለጋ ሀቢብ ያዮ የአፄ ዮሃንስ ሰራዊት ሀያ ሬሳዎች ተደራርበዉበት ከስር ተገኘ፡፡ በዉግያ ከተሱዉት መካል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- 1) ቡሽራ ወራቄ 2) ሀምዴ በቅጥያ ስሙ ሀምዴ ጥና መባል ይታወቃል 3) ሸይኽ ሀሰን አሊ የሙፍቲ መሀመድ ሲራጅ የእናታቸው ወንድም 4) ሀቢብ ያዮ ቆስለው ከዉግያዉም ቡኋላ የሞቱት ደግሞ:- 1) የሙስሊሞች መሪ የነበሩት ሀጅ አልዩ 2) ሸይኽ ቡሽራ ወራቄ አል-ማርስይ ናቸው፡፡ 3) ሸይኽ ዙበይር የሀጅ አልዩ ወንድም በዉግያው ላይ የቆሰሉ ቢሆንም አልሞቱም፡፡ በጅሃድ ላይ የተሰዉት ጦርነት በተደረገበት ቦታ ኩቤ ጃሃዳ ላይ ተቀበሩ፡፡ የሙስሊሞች የጦር መሪ የነበረው ሀጂ አልዩ ቆስለው ነበር፤ ሰዎችን ሸይኹ እንዴት ናቸው ስሉ ጠየቁ፤ ሸይኹ ደህና እንደሆኑ ሲነገራቸው አሁን ብሞትም ምንኛ ያማረነው አሉና ላኢላህ ኢለሏህ የሚለዉን የመጨረሻ ቃላቸው በማድረግ ወደ አኺራ ሄዱ፡፡ ሸይኽ ቡሽራ ወራቄ አልመርሲይእንዲሁ ወደ አኺራ ሄዱ፡፡ ኩቤ ባግኤ ጋንዳ ጋሮ በሚባለው ቦታ ተቀበሩ ይህ ቦታ አሁን ድረስ የሀጂ አልዩ ቀብር በመባል ይታወቃል፡፡ የኢማም ጀማሉዲን አል-አኒ ቆራጥነት እና ጀግንነት የራያ ዓዘቦ ሙስሊሞች በሀሼንግ፣ በቴንቤን፣አክሱም፣ በወሎ ሙስሊሞች ላይ የደረሰው አይነት ክርስትናን እንዲቀበሉ የማስገደድ ዘመቻ ሳይካ ቀርቷል። አፄ ዮሃንስ በራያ ዓዘቦ ድል ሳይቀዳጅ፣ መስጂዶችም ሳያቃጥል፣ አብያተ ክርስትያናትም ሳይገነባ ዉርደት ተከናንቦ ተመልሷል፡፡ ይህን የአባቶቻቸዉን ጀግንነት በራያ አሁን ድረስ ይወሳል በመንዙማዎች፣ በግጥሞች፣ ሰርግ ላይ በሚደረጉ መፈክሮች፣ መውሊድ ላይ እና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ ጀግንነታቸው በኦርምኛ፣ በትግርኛ እና አረብኛ ይነገራል፡፡ የአፄ ዮሃንስ ሙስሊሙን የማጥመቅ ዘመቻ እንደተፈለገው ሳይሳከ የቀረ ቢሆንም በተቆጣጠሩት ደጋማ የራያ ክፍል ማለትም ከማይጨው እስከ ሀሼንጎ አከባቢ ከትግራይ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችን በማስፈር የዲሞግራፊ ለውጥ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል። ቆላው የራያ ክፍል ራያ ዓዘቦ ግን 100% ሙስሊሙነቱን አስጠብቆ ቆይቷል።................

የ 1 ምላስ እና የ2 ጆሮዎች ጥበብ ገብቷችኋል? ማድመጥ > ከመናገር 2 > 1
የ 1 ምላስ እና የ2 ጆሮዎች ጥበብ ገብቷችኋል? ማድመጥ > ከመናገር 2 > 1

አንደኛ፡- አፄ ዮሃንስ በሙስሊሞች እጅ እንደሚገደል የተነገረው ትንቢት ስላለ በዚህም ሸይኹ ሊሆኑ ይችላል የሚል ስጋት ነበረው፡፡ ሁለተኛ፡-አፄው በሚያስተዳድረው ግዛት በጣም ተሰሚነት ያላቸውና በዘመኑ ታላቅ አሊም ስለሆኑ እንዲሁም በዮሃንስ ላይ ጂሃድ ብያውጁ እንኳን ተከታዮቻቸው የሸይኹን ሀሳብ ከመቀበል ወደኋላ እንደማይሉ ስለተረዳ ኢትዮጵያን በክርስትና ለማስተዳደረ እቅዱን ያደናቅፉብኛል የሚል ስጋት ሰላለው የተለየ ቱክረት አድርጎባቸዋል፡፡ ሶስተኛ፡- የራያ ህዝብ በዉግያ እና ራሳቸዉን በመከላከል የታወቁ ጀግኖች መሆናቸው፤ የስልጣን መቀመጫው ለሆነውመቀሌ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች በመሆናቸው በወሎ፣ጎንደር ሙስሊሞች ላይ ከመዝመቱ በፊት በራያ ላይ እርምጃ መውሰዳ እንዳለበት ስላመነ፡፡ በነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ራያን ለማጥቃት ሸይኹን ማስወግድ አልያም ክርስትናን እንዲቀበሉ ለማድረግ ተቀዳሚ አላማው አድርጓል፡፡ «ፈታዋ ጀማሉዲን አል አኒይ» አፄ ዮሃንስ በሙስሊሞች ላይ እያደረገ ያለዉን ግፍ በማስመልከትና ከእሱ ጋር እርቅ ለመፍጠር እንዴት መሄድ እንዳለባቸው የራያ አሉሞች መከሩ፡፡‹‹ለአፄው አምስት መቶ ከብት በስጦታ መልክ ይዘን እንሂድ›› ሚል ሀሳብ አመጡ ሸይኽ ጀማሉዲን አል-አኒም የሚከተለዉን ተናገሩ‹‹ በጥላቻ የተሞላ ሰው ስለሆነ ይቅርታ ጠይቀን ብንሄድ እንኳን አይቀበለንም፤ ይህን በማድረጋችን አገራችንን እናጣለን ምክንያቱም በጥላቻ፣ቂም እና በቀል የተሞላ ሰው ነው በዚህም ሳብያ ሁላችን እንጎዳለን፡፡ ጦርነት ለማንም አታዝንም፤ እሱን በመዋጋታችን ሰላም እና መረጋጋት ስለሚያጣ እኛን በስርኣት እንዳይገዛ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ከእርቁ ይልቅ በቻልነው ሀይማኖታችንን፣ ሀገራችን እና ክብራችንን መካለከል ይኖርብናል የሚለዉን የሸይኹ ሀሳብ ተቃባይነት አገኘ፡፡ ጀማሉዱን አል አኒይ እንዲህ ይሉ ነበር ‹‹ሞኝ ማለት (ዲኑን) ሀይማኖቱን ለራሱ አለማዊ ጥቅም የሸጠ ነው፤ የሞኞች ሞኝ ደግሞ ለሌሎች ጥቅም ሀይማኖቱን የሸጠ ነው፡፡ ተማሪው እና ማህበረሰቡ ሀይማኖቱን እና ሀገሩን እንዲጠብቅ፤ተዋርዶ ከመኖር ይልቅ በኢስላም በክብር መሞት የበለጠ መሆኑን አስረዱ፡፡ እድሜያቸዉን የዲን እውቀት በመፈለግ ያሳልፉ የነበሩ ወጣቶች፤ ከዚህ በፊት የጦር ልምድ ያልነበራቸውተማሪዎች በትምህርት ብቻ የሚያዉቁትን ጂሀድ ለመተግበር ቆርጠው ተነሱ፡፡ .....