Ethiopian University Freshman Information
前往频道在 Telegram
Information service for Ethiopian university freshmen. Admissions • Registration • University Updates • Academic Information
显示更多未指定国家未指定类别
📈 Telegram 频道 Ethiopian University Freshman Information 的分析概览
频道 Ethiopian University Freshman Information (@freshmanunion) 是活跃参与者。目前社区聚集了 22 647 名订阅者,在 其他 类别中位列第 。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 22 647 名订阅者。
根据 23 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -646,过去 24 小时变化为 -45,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 40.54%。内容发布后 24 小时内通常能获得 21.29% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 9 182 次浏览,首日通常累积 4 822 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 25。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“Information service for Ethiopian university freshmen.
Admissions • Registration • University Updates • Academic Information”
凭借高频更新(最新数据采集于 24 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 其他 类别中的关键影响点。
22 647
订阅者
-4524 小时
-1517 天
-64630 天
帖子存档
የ1ኛ ዓመት የትምህርት ማቴሪያሎች
ለ2019 ዓ.ም የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች የቀደሙ ፈተናዎችን፣ አሳይመንቶችን እና የኮርስ ሞጁሎችን በየኮርሱ አዘጋጅተንላችኋል።
📖 የፍረሽማን ኮርሶች፦
🔵Anthropology
🔵Applied Math
🔵Biology
🔵Chemistry
🔵Civics
🔵Critical Thinking and Logic
🔵Economics
🔵Emerging Technology
🔵English
🔵Entrepreneurship
🔵Geography
🔵History
🔵Inclusiveness
🔵Math for Natural Science
🔵Math for Social Science
🔵Physics
🔵Psychology
📘Modules
በሴሚስተሩ ውስጥ ለሚኖሯችሁ አሳይመንቶች፣ ሚድ እና ፋይናል ፈተናዎች ለመዘጋጀት እነዚህን ማቴሪያሎች ተጠቀሙባቸው።
➡️ ሌሎች የ1ኛ ዓመት ተማሪዎችን ታውቃላችሁ? ለትምህርቶቻቸው የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን ማግኘት እንዲችሉ ይህንን መረጃ ላኩላቸው።
@FreshmanUnion✅️
📣 #HaramayaUniversity | ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የትራንስፖርት እገዛ
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች አስተባባሪዎችን በመመደብ የትራንስፖርት እገዛ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
📞 እገዛ እንዴት ማግኘት ይቻላል?
በምስሉ ላይ የተቀመጡትን የስልክ ቁጥሮች በመጠቀም ከዩኒቨርሲቲው አስተባባሪዎች ጋር በመገናኘት እገዛ ማግኘት ትችላላችሁ።
📅 የሪፖርት ማድረጊያ ቀናት፦ ጥቅምት 05–08/2019 ዓ.ም
ማሳሰቢያ፦ የትራንስፖርት እገዛ ለማግኘት በምስሉ ላይ የተጠቀሱትን ቁጥሮች ብቻ ተጠቀሙ።
➡️ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ይህን መረጃ ለሌሎች ተማሪዎች ሼር አርጉ።
@FreshmanUnion ✔️
Repost from Aviation University Info Center
📣 የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የጽሁፍ ፈተና ጥሪ
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በCabin Crew እና በ AMT (Aircraft Maintenance Technician) ዘርፍ አመልክታችሁ ለነበራችሁ አመልካቾች በሙሉ፡
📅 የፈተና ቀን፡ ጥቅምት 7 - 8 ቀን 2019 ዓ.ም.
📍 የስም ዝርዝር እና የመፈተኛ ቦታ፡ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን የመፈተኛ ቦታችሁንና ስምችሁን ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/results
⚠️ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች:
"ሳንመዘገብ እድሉ አመለጠን" እያላችሁ ለምትገኙ ተማሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲው ድጋሚ ጥሪዎችን የሚያደርግ ስለሆነ መረጃዎችን በጥንቃቄ እና በትግስት እንድትከታተሉ እናሳስባለን።ታማኝ እና ፈጣን የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን የተቀላቀሉ፡ Telegram: @aviation_et
Repost from Aviation University Info Center
⤴️ የጽሑፍ ፈተና ጥሪ የተደረጋችሁ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በET-Sponsored Trainee Cabin Crew የስልጠና ፕሮግራም የተመዘገባችሁ የአዲስ አበባ አመልካቾች ስም ዝርዝር።
ማስፈንጠርያውን ከፍታችሁ ስም ዝርዝራችሁን መመልከት ያልቻላችሁ ስማችሁን እና የመፈተኛ ሰዓታችሁን እዚ ፋይል ውስጥ ፈልጉ።
@Aviation_Et ✔️
📣 #WolkiteUniversity
በ2019 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
➡️ መረጃው ለሚጠቅማቸው ጓደኞቻችሁ Share አድርጉ።
@FreshmanUnion ✔️
📣 #DireDawaUniversity | የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ማስታወቂያ
በ2019 ዓ.ም ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የRemedial ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆናቸው ተገልጿል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
• ከ9ኛ–12ኛ ክፍል Transcript — ዋናውና ኮፒው
• የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት — ዋናውና ኮፒው
• 4 የ3×4 መጠን ፎቶግራፎች
• ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)
• አንሶላ፣ የሌሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ
የመልሶ ቅበላ ማስታወቂያ
በተለያዩ ምክንያቶች የ1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ፣ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ጥቅምት 10 እና 11/2019 ዓ.ም ለመልሶ ቅበላ ማመልከት ትችላላችሁ።
➡️ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ሌሎች ተማሪዎችም መረጃውን ሼር አድርጉ።
@FreshmanUnion ✔️
አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ
በ2019 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም የማካካሻ (Remedial) ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የቅበላ ቀን ረቡዕ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም፣ የምዝገባ ቀናት ሐሙስ እና ዓርብ ጥቅምት 5 እና 6/2019 ዓ.ም፣ ትምህርት የምጀመረው ቀን ሰኞ ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚህ መሠረት በ2018 ዓ.ም የማካካሻ (Remedial) ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም የማካካሻ (Remedial) ትምህርት በተማራችሁበት ካምፓስ እንድሁም በ2019 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በምደባው መሠረት ኩልፎ (Kulfo Campus)፣ አባያ (Abaya Campus)፣ ጫሞ (Chamo Campus)፣ እና ዋናው ግቢ (Main Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ኩልፎ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ እና ዋናው ግቢ ካምፓሶች፣ ሳውላ ካምፓስ (Sawula Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጂስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንዲታደርጉና ምዝገባ እንዲትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡
ሊንክ፡- https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement
ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርቴፍከት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንድሁም የፋይዳ መታወቂያ ካርድ፣ አንሶላ፣ ትራስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
📣 #BoranaUniversity
በ2019 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ (Freshman) መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቦረና ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
ያቤሎ ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት 3X4 መጠን ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡
@FreshmanUnion✅️
#DebreTaborUniversity
በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ (Freshman) መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3X4 መጠን የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID)፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡
በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ምዝገባ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
@FreshmanUnion✅️
📣 #BongaUniversity
በ2019 ዓ.ም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● ፋይዳ መታወቂያ፣
● ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ፡፡
@FreshmanUnion✅️
#BahirdarUniversity
📣 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ አዲስ እና 2018 Remedial ለተማሩ ተማሪዎች ጥቅምት 9-10 ጥሪ አድርጕል
ሁሉም የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በግሽ አባይ (ደቡብ) ግቢ እንዲሁም
ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በሰላም ግቢ
በአካል በመገኘት ከጥቅምት 9-10 ቀን 2019 ዓ.ም ምዝገባ እንድታካሂዱ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።
ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በተለያዩ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
@FreshmanUnion✅️
#SalaleUniversity
📣 በ2019 ዓ.ም ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3×4 መጠን የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፎች፣
● National ID፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የምዝገባ ቦታ
ጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ
@FreshmanUnion✅️
# MizanTepiUniversity
በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች እና በ 2018 በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲያችን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ
የ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 09 እና 10 መሆኑን እየገለጽን፤
የመመዝገቢያ ቦታ :-
1ኛ. ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ሚዛን-አማን በሚገኘው ዋናው ግቢ
2ኛ. ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ
በዩኒቨርሲቲያችን በሪሜዲያል/እርምጃ "ማሻሻያ"ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች መመዝገቢያ ወቅት ወደፊት ሌላ ጥሪ ማስታወቂያ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እየገለጽን፤
ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@FreshmanUnion✅️
+1
📣 ዲላ ዩኒቨርሲቲ | 2019 ዓ.ም የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ
በ2019 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች፣ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፦
የምዝገባ ቀን
ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም
አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች፦
የምዝገባ ቀን
ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም
ለምዝገባ ይዛችሁ የምትሄዱት
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሄዱ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፦
• ከ9ኛ–12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች — ዋናውና ኮፒ
• የ8ኛ ክፍል ፈተና ካርድ — ዋናውና ኮፒ
• 8 የ3×4 ፎቶግራፎች
• አንሶላ
• የትራስ ጨርቅ
• ብርድ ልብስ
• የስፖርት ልብስ
• 1 የሰነድ መያዣ ክላሰር
📍የምዝገባ ቦታ
ኦዳያኣ ግቢ
→ የሬጅስትራር ሕንፃ ቁጥር 609
→ በአካል
የምዝገባ ቀናችሁን እና ለምዝገባ የሚያስፈልጓችሁን ሰነዶች በቅድሚያ አረጋግጡ።
➡️ ለሌሎች የዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች Share አድርጉ።
@FreshmanUnion✅️
📣 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ | 2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች
በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች፣ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች፦
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን
ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም
በተመሳሳይ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎችም የመግቢያ ቀናችሁ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ መስፈርቶች
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፦
• ከ9ኛ–12ኛ ክፍል Transcript — ዋናውና ኮፒ
• የ12ኛ ክፍል Certificate — ዋናውና ኮፒ
• 4 የ3×4 ጉርድ ፎቶግራፎች
• አንሶላ
• ብርድ ልብስ
• ትራስ ልብስ
• የስፖርት ልብስ
📍 የምዝገባ ቦታ
ማኅበራዊ ሳይንስ
→ ማራኪ ግቢ
ተፈጥሮ ሳይንስ
→ አጼ ቴዎድሮስ ግቢ
ድኅረ-ምረቃ
→ በግቢው የሚገኙ የረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
Online Registration
የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ከመሄዳችሁ በፊት Online Registration ማጠናቀቅ አለባችሁ።
🔗 Registration.uog.edu.et
📌 የOnline Registration ሂደቱን በቅደም ተከተል ለማየት ከዚህ ፖስት ጋር የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።
➡️ ለሌሎች የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች Share አድርጉ።
@FreshmanUnion✅️
በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
@FreshmanUnion✅️
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት የቻይንኛ ቋንቋ ስልጠና ፈላጊዎች (Chinese Language Certificate Program) ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም (ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ3:00-5:00 ሰዓት)
ስልጠናው ከጥቅምት 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ሳምንታት፣ ቅዳሜ ከሰዓት ከ7:00-9:00 ሰዓት ይሰጣል፡፡
የስልጠና ደረጃ፦ Level 1
የምዝገባ ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፎረም ህንፃ፣ 8ኛ ወለል፣ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ (ያሉ ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ።)
@FreshmanUnion✅️
