ar
Feedback
Ethiopian University Freshman Information

Ethiopian University Freshman Information

الذهاب إلى القناة على Telegram

Information service for Ethiopian university freshmen. Admissions • Registration • University Updates • Academic Information

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Ethiopian University Freshman Information

تُعد قناة Ethiopian University Freshman Information (@freshmanunion) لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 23 082 مشتركاً، محتلاً المرتبة في فئة اخرى.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 23 082 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 30 سبتمبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -230، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -27، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 54.61‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 31.54‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 12 610 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 7 282 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 25.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“Information service for Ethiopian university freshmen. Admissions • Registration • University Updates • Academic Information”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 01 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة اخرى.

23 082
المشتركون
-2724 ساعات
-2097 أيام
-23030 أيام
أرشيف المشاركات
#MoE በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይ
#MoE በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። @FreshmanUnion ✔️

ከላይ ከቀረቡት ዲፓርትመንቶች በመቀጠል በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተፈላጊነት እና ተስፋ ያላቸው የሚቀጥሉት 10 (ከ11-20) ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች)፦ 11. ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ (Mechanical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የማሽነሪዎችን፣ የሞተሮችን፣ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎችን እና የኃይል ማመንጫ አሰራሮችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት እና የመንከባከብ ሳይንስን የሚያጠና ነው። የሥራ እድሎች፦ በአቪዬሽን እና አየር መንገድ (እንደ Ethiopian Airlines) የማሽን ጥገና እና ኦፕሬሽን ኢንጂነር በማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች (የሲሚንቶ፣ የምግብ እና መጠጥ) የምርት ማኔጀር በአውቶሞቲቭ እና ከባድ ማሽነሪ ተቋማት የቴክኒክ ባለሙያ 12. አርክቴክቸር (Architecture / Urban Planning) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (EiABC / 5 ኪሎ) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የህንፃዎችን ውበት፣ ቅርፅ፣ የውስጥ ክፍል አቀማመጥ (Interior Design) እና የከተሞች ማስተር ፕላን ንድፍ በፈጠራና በቴክኖሎጂ አስደግፎ የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በግል እና በድርጅቶች የህንፃ አርክቴክት እና ንድፍ አውጪ (Architect) የውስጥ ዲዛይን እና የቦታ ውበት አማካሪ (Interior Designer) በከተማ ልማት እና ፕላን መሪያ ተቋማት የከተማ ፕላነር (Urban Planner) 13. አግሪካልቸራል ኢንጂነሪንግ እና ባዮሲስተምስ (Agricultural Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የዘመናዊ መስኖ ቴክኖሎጂዎችን፣ የትራክተርና አዝመራ ሰብሳቢ ማሽኖችን እና የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሰፊ የንግድ ግብርና (Commercial Farming) እና የግብርና ፕሮጀክቶች የመስኖ እና ማሽነሪ ኢንጂነር በዓለም አቀፍ የግብርና ድርጅቶች (FAO, USAID) የቴክኒክ እና የምግብ ዋስትና አማካሪ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም በክልል ግብርና ቢሮዎች የውሃ ሀብት ባለሙያ 14. ኢኮኖሚክስ (Economics) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን፣ የገበያ ሁኔታዎችን፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እና የዳታ ትንተናን (Data Analysis) የሚያጠና የማህበራዊ ሳይንስ ንጉስ ነው። የሥራ እድሎች፦ በባንኮች እና ፋይናንስ ተቋማት የኢኮኖሚና ገበያ ተነታኝ (Economic Analyst) በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ አውጪና ተመራማሪ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች (World Bank, IMF, UN) የልማት ፕሮጀክት አማካሪ 15. አኔስቴዥያ (Anesthesia) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (በቅድሚያ በመጀመር የሚታወቅ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ታካሚዎች ቀዶ ህክምና (Surgery) ከመደረጋቸው በፊት እና በሚደረግበት ወቅት የማደንዘዣ መድኃኒቶችን መስጠት፣ የህመም ማስታገስ እና ምልክቶችን የመከታተል የጤና ሳይንስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና ክፍል አኔስቴቲስት (Anesthetist) በአደጋ ጊዜ እና በፅኑ ህሙማን መከታተያ ክፍል (ICU) የህክምና ባለሙያ በህክምና ማሰልጠኛዎች እና ምርምር ማዕከላት አስተማሪና ተመራማሪ 16. ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ (Radiology Technology) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ በዘመናዊ የመመርመሪያ መሳሪያዎች (እንደ X-ray, Ultrasound, CT Scan, MRI) በመጠቀም የበሽታዎችን መንስኤ እና የሰውነት ክፍል ምስሎችን (Medical Imaging) የሚያነሳ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና በምርመራ ማዕከላት (Diagnostic Centers) የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት በግል ምስል ማንሻ ማዕከላት ስራ አስኪያጅነት እና የኢሜጂንግ ባለሙያ የራዲዮሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት እና ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ 17. ማርኬቲንግ ማኔጅመንት (Marketing Management) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ንግድ ስራ ትምህርት ቤት / Commerce) ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የምርቶችና አገልግሎቶችን ገበያ ማናት፣ የዲጂታል ማርኬቲንግ ስትራቴጂዎችን መንደፍ፣ የደንበኞች ፍላጎት ማናት እና የሽያጭ መጠንን ማሳደግ ላይ የሚያተኩር የቢዝነስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በቴሌኮም፣ ባንኮች እና ትልልቅ ኩባንያዎች የማርኬቲንግ እና ብራንድ ማኔጀር የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የማህበራዊ ሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት (PR) ስፔሻሊስት በማስታወቂያ እና ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች የፈጠራ እና የስትራቴጂ ዳይሬክተር 18. ኬሚካል ኢንጂነሪንግ (Chemical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ጥሬ እቃዎችን ወደ ተለያዩ ጠቃሚ ምርቶች (እንደ ፕላስቲክ፣ ሳሙና፣ መድኃኒት፣ መጠጦች) ለመቀየር የሚደረጉ የኬሚካል እና የፊዚካል ሂደቶችን የሚያጠና መስክ ነው። የሥራ እድሎች፦ በምግብና መጠጥ፣ በስኳር፣ በሲሚንቶ እና ሳሙና ፋብሪካዎች የሂደት (Process) ኢንጂነር በፔትሮኬሚካል እና ፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች የቴክኒክ ማኔጀር በጥራት ቁጥጥር (Quality Control) እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣናት ተቆጣጣሪ 19. ነርሲንግ / ክሊኒካል ነርሲንግ (BSc Nursing) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ለህሙማን የቅርብ እንክብካቤ መስጠት፣ የህክምና ትዕዛዞችን መፈፀም፣ የታካሚዎችን ሁኔታ መከታተል እና በጤና ኤክስቴንሽን ማህበረሰብን ማገልገልን የሚያጠና ህይወት አድን ሙያ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች ክሊኒካል ነርስ (Clinical Nurse) በአለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች (Red Cross, MSF) የህክምና እንክብካቤ አቅራቢ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ (የውጭ ሀገር የነርሲንግ የሥራ እድሎች) ሰፊ የሥራ እድል ያለው 20. ጋርመንት እና ቴክስታይል ኢንጂነሪንግ (Textile & Garment Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (በቴክስታይል እና ፋሽን ኢንስቲትዩት - EiTEX የሚታወቅ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የጨርቃ ጨርቅ፣ የፈትል፣ የልብስ ስፌት ቴክኖሎጂ እና የፋሽን ዲዛይን ማኑፋክቸሪንግ ሂደትን በኢንዱስትሪ ደረጃ ማምረትን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አልባሳት ፋብሪካዎች የምርት እና የጥራት ቁጥጥር ኢንጂነር በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዲዛይን ኩባንያዎች የቴክኒክ አማካሪ የራስን የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ መፍጠር @FreshmanUnion ✔️

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (በቴክስታይል እና ፋሽን ኢንስቲትዩት - EiTEX የሚታወቅ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የጨርቃ ጨርቅ፣ የፈትል፣ የልብስ ስፌት ቴክኖሎጂ እና የፋሽን ዲዛይን ማኑፋክቸሪንግ ሂደትን በኢንዱስትሪ ደረጃ ማምረትን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አልባሳት ፋብሪካዎች የምርት እና የጥራት ቁጥጥር ኢንጂነር በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዲዛይን ኩባንያዎች የቴክኒክ አማካሪ የራስን የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ መፍጠር

ከላይ ከቀረቡት ዲፓርትመንቶች በመቀጠል በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተፈላጊነት እና ተስፋ ያላቸው የሚቀጥሉት 10 (ከ11-20) ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች)፦ 11. ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ (Mechanical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የማሽነሪዎችን፣ የሞተሮችን፣ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎችን እና የኃይል ማመንጫ አሰራሮችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት እና የመንከባከብ ሳይንስን የሚያጠና ነው። የሥራ እድሎች፦ በአቪዬሽን እና አየር መንገድ (እንደ Ethiopian Airlines) የማሽን ጥገና እና ኦፕሬሽን ኢንጂነር በማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች (የሲሚንቶ፣ የምግብ እና መጠጥ) የምርት ማኔጀር በአውቶሞቲቭ እና ከባድ ማሽነሪ ተቋማት የቴክኒክ ባለሙያ 12. አርክቴክቸር (Architecture / Urban Planning) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (EiABC / 5 ኪሎ) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የህንፃዎችን ውበት፣ ቅርፅ፣ የውስጥ ክፍል አቀማመጥ (Interior Design) እና የከተሞች ማስተር ፕላን ንድፍ በፈጠራና በቴክኖሎጂ አስደግፎ የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በግል እና በድርጅቶች የህንፃ አርክቴክት እና ንድፍ አውጪ (Architect) የውስጥ ዲዛይን እና የቦታ ውበት አማካሪ (Interior Designer) በከተማ ልማት እና ፕላን መሪያ ተቋማት የከተማ ፕላነር (Urban Planner) 13. አግሪካልቸራል ኢንጂነሪንግ እና ባዮሲስተምስ (Agricultural Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የዘመናዊ መስኖ ቴክኖሎጂዎችን፣ የትራክተርና አዝመራ ሰብሳቢ ማሽኖችን እና የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሰፊ የንግድ ግብርና (Commercial Farming) እና የግብርና ፕሮጀክቶች የመስኖ እና ማሽነሪ ኢንጂነር በዓለም አቀፍ የግብርና ድርጅቶች (FAO, USAID) የቴክኒክ እና የምግብ ዋስትና አማካሪ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም በክልል ግብርና ቢሮዎች የውሃ ሀብት ባለሙያ 14. ኢኮኖሚክስ (Economics) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን፣ የገበያ ሁኔታዎችን፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እና የዳታ ትንተናን (Data Analysis) የሚያጠና የማህበራዊ ሳይንስ ንጉስ ነው። የሥራ እድሎች፦ በባንኮች እና ፋይናንስ ተቋማት የኢኮኖሚና ገበያ ተነታኝ (Economic Analyst) በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ አውጪና ተመራማሪ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች (World Bank, IMF, UN) የልማት ፕሮጀክት አማካሪ 15. አኔስቴዥያ (Anesthesia) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (በቅድሚያ በመጀመር የሚታወቅ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ታካሚዎች ቀዶ ህክምና (Surgery) ከመደረጋቸው በፊት እና በሚደረግበት ወቅት የማደንዘዣ መድኃኒቶችን መስጠት፣ የህመም ማስታገስ እና ምልክቶችን የመከታተል የጤና ሳይንስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና ክፍል አኔስቴቲስት (Anesthetist) በአደጋ ጊዜ እና በፅኑ ህሙማን መከታተያ ክፍል (ICU) የህክምና ባለሙያ በህክምና ማሰልጠኛዎች እና ምርምር ማዕከላት አስተማሪና ተመራማሪ 16. ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ (Radiology Technology) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ በዘመናዊ የመመርመሪያ መሳሪያዎች (እንደ X-ray, Ultrasound, CT Scan, MRI) በመጠቀም የበሽታዎችን መንስኤ እና የሰውነት ክፍል ምስሎችን (Medical Imaging) የሚያነሳ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና በምርመራ ማዕከላት (Diagnostic Centers) የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት በግል ምስል ማንሻ ማዕከላት ስራ አስኪያጅነት እና የኢሜጂንግ ባለሙያ የራዲዮሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት እና ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ 17. ማርኬቲንግ ማኔጅመንት (Marketing Management) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ንግድ ስራ ትምህርት ቤት / Commerce) ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የምርቶችና አገልግሎቶችን ገበያ ማናት፣ የዲጂታል ማርኬቲንግ ስትራቴጂዎችን መንደፍ፣ የደንበኞች ፍላጎት ማናት እና የሽያጭ መጠንን ማሳደግ ላይ የሚያተኩር የቢዝነስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በቴሌኮም፣ ባንኮች እና ትልልቅ ኩባንያዎች የማርኬቲንግ እና ብራንድ ማኔጀር የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የማህበራዊ ሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት (PR) ስፔሻሊስት በማስታወቂያ እና ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች የፈጠራ እና የስትራቴጂ ዳይሬክተር 18. ኬሚካል ኢንጂነሪንግ (Chemical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ጥሬ እቃዎችን ወደ ተለያዩ ጠቃሚ ምርቶች (እንደ ፕላስቲክ፣ ሳሙና፣ መድኃኒት፣ መጠጦች) ለመቀየር የሚደረጉ የኬሚካል እና የፊዚካል ሂደቶችን የሚያጠና መስክ ነው። የሥራ እድሎች፦ በምግብና መጠጥ፣ በስኳር፣ በሲሚንቶ እና ሳሙና ፋብሪካዎች የሂደት (Process) ኢንጂነር በፔትሮኬሚካል እና ፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች የቴክኒክ ማኔጀር በጥራት ቁጥጥር (Quality Control) እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣናት ተቆጣጣሪ 19. ነርሲንግ / ክሊኒካል ነርሲንግ (BSc Nursing) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ለህሙማን የቅርብ እንክብካቤ መስጠት፣ የህክምና ትዕዛዞችን መፈፀም፣ የታካሚዎችን ሁኔታ መከታተል እና በጤና ኤክስቴንሽን ማህበረሰብን ማገልገልን የሚያጠና ህይወት አድን ሙያ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች ክሊኒካል ነርስ (Clinical Nurse) በአለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች (Red Cross, MSF) የህክምና እንክብካቤ አቅራቢ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ (የውጭ ሀገር የነርሲንግ የሥራ እድሎች) ሰፊ የሥራ እድል ያለው 20. ጋርመንት እና ቴክስታይል ኢንጂነሪንግ (Textile & Garment Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦

📣 ለ2019 የFreshman ተማሪዎች በሙሉ! በዝግጁ (Zegju) መተግበሪያ ላይ የPhysics እና Anthropology ትምህርቶች ግልጽ፣ ማራኪ እና ለማንበብ እጅግ ምቹ የሆኑ ለፈተና አጋዥ ማስ
📣 ለ2019 የFreshman ተማሪዎች በሙሉ! በዝግጁ (Zegju) መተግበሪያ ላይ የPhysics እና Anthropology ትምህርቶች ግልጽ፣ ማራኪ እና ለማንበብ እጅግ ምቹ የሆኑ ለፈተና አጋዥ ማስታወሻዎች ተካተዋል! የመጀመሪያ ዓመት ኮርሶቻችሁን፣ በየቻፕተሩ የተከፋፈሉ ጥያቄዎችን እና ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎችን በነፃ (FREE) ዝግጁ አፕ ላይ አግኙ። 🔎 እንዴት እንደምትመዘገቡ ለማየት ማስታወሻ፦ Password የረሳችሁ መመዝገቢያ ቦት ላይ "Change Password" የሚለውን ቁልፍ ተጫኑ ወይም /recover ብላችሁ ይላኩ። ለመመዝገብ - @Zegju_registration_bot ▶️ Android (Play Store) 🛒 iOS (App Store)

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ነባርና አዲስ ተማሪዎቹን ለመቀበል አስፈላጊዉን ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳወቀ መስከረም 20/2019 ዓ/ም ላለፉት 50 ዓመታት ተማሪዎችን በተለያዩ የሙ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ነባርና አዲስ ተማሪዎቹን ለመቀበል አስፈላጊዉን ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳወቀ መስከረም 20/2019 ዓ/ም ላለፉት 50 ዓመታት ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ተቀብሎ፣አሰልጥኖ ሲያስመርቅ የቆየዉ አንጋፋዉ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎቹን ለመቀበል ልዩ ዝግጀት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ አሳዉቀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ ክወትሮዉ በተለየ መልኩ ሰፊ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዉ፣ ሰፋፍ የመማሪያ ክፍሎችና የተማሪዎች መኝታ ቤቶች ዕድሳት መደረጉን ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ነባርም ሆኑ አዲስ የሚመደቡ ተማሪዎች የተሻሉ መማሪያና መኝታ ክፍሎች ላይ ሆነዉ ትምህርታችዉን እንዲከታተሉ ለማድረግ ያለመ ለትምህርትና ተማሪ ትኩረት የሰጠ መጠነ ሰፊ የዕድሳትና ማስዋብ ስራ መሰራቱ ዩኒቨርሲቲዉ ለትምህርት ጥራትና ለተገልጋዮች እርካታ ልዩ ትኩረት ስለመስጠቱ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡ @FreshmanUnion ✔️

በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው 10 ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች) ፦ 1. ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ኮምፒውተር ሳይንስ (Software Engineering / Computer Science) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT / 4 ኪሎ) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን ማልማት፣ የሞባይል መተግበሪያዎችን (Apps) መስራት፣ የዌብሳይት ግንባታ፣ የዳታ አያያዝ እና የዳታቤዝ ደህንነትን የሚያስተምር ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ የሶፍትዌር እና አፕሊኬሽን አልሚ (Software / Mobile App Developer) በፊንቴክ እና በባንኮች (እንደ ቴሌብር፣ ቻፓ፣ ንግድ ባንክ) የሲስተም ኢንጂነር ከሀገር ውጭ ላሉ የውጭ ኩባንያዎች በሩቅ (Remote Work / Freelancing) መስራት 2. ህክምና (Doctor of Medicine - MD) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ (በማህበረሰብ አቀፍ ህክምና የሚታወቅ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የሰው ልጅ አካል አወቃቀርን፣ በሽታዎችን የመመርመር፣ የመታከም፣ የቀዶ ህክምና የማድረግ እና የህክምና ሳይንስ ምርምሮችን የሚያጠና አንጋፋና ጥልቅ የትምህርት ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ የመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች ጠቅላላ ሀኪም (General Practitioner) በስፔሻላይዜሽን ትምህርት በመቀጠል የልዩ ህክምና ስፔሻሊስት (እንደ ቀዶ ሀኪም፣ የህጻናት ሀኪም) በአለም አቀፍ የጤና ድርጅቶች (WHO, UNICEF, NGOs) የህክምና አማካሪና ተመራማሪ 3. ኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ (Electrical & Computer Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትና ማሰራጨት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ኔትወርኮች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የመቆጣጠሪያ ሲስተሞች (Automation/Hardware) ንድፍን የሚያጠና መስክ ነው። የሥራ እድሎች፦ የቴሌኮም ኢንጂነር (በኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮም) የኃይል እና ኤሌክትሪክ ኢንጂነር (በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል/አገልግሎት) የኔትወርክ እና የሃርድዌር ሲስተምስ አድሚኒስትሬተር 4. ሲቪል ኢንጂነሪንግ (Civil Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የህንፃዎች፣ የመንገዶች፣ የድልድዮች፣ የደብዳቤና የውሃ ግድቦች ንድፍ (Design)፣ የግንባታ ሂደት እና የፕሮጀክት አስተዳደርን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ኩባንያዎች የሳይት ኢንጂነር (Site Engineer) የመንገድ፣ ውሃ እና ህንጻ ፕሮጀክት መሃንዲስና ዲዛይነር የግንባታ አማካሪ (Consultant) እና የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ 5. ህግ (Law - LL.B.) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ የህግ ኮሌጅ) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የሀገሪቱንና የአለም አቀፍ ህጎችን፣ የህገ-መንግስት መርሆዎችን፣ የንግድና የወንጀል ህጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን የሚያጠና ዲፓርትመንት ነው። የሥራ እድሎች፦ የህግ ጠበቃ እና አማካሪ (Attorney / Legal Advisor) ዓቃቤ ህግ (Prosecutor) እና ዳኛ (Judge) በባንኮች፣ በድርጅቶች እና በአለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ተቋማት (NGOs) የህግ ጉዳዮች ኃላፊ 6. ፋርማሲ (Pharmacy) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የመድኃኒቶችን ውህደት፣ ዝግጅት፣ የጎንዮሽ ጉዳት፣ የመድኃኒት አሰራጭነትን እና ለታካሚዎች የሚሰጡ የመድኃኒት ህክምናዎችን የሚያጠና የጤና ሳይንስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በግል እና በመንግስት ሆስፒታሎች ክሊኒካል ፋርማሲስት የራስን የግል መድኃኒት ቤት (Community Pharmacy) ወይም የመድኃኒት পাইክስ (Wholesale) ከፍቶ ማስተዳደር በመድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች እና አስመጪ ድርጅቶች ውስጥ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ 7. አካውንቲንግ እና ፋይናንስ (Accounting & Finance) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (የንግድ ስራ ትምህርት ቤት / Commerce) ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የድርጅቶችን የገንዘብ እንቅስቃሴ መመዝገብ፣ የበጀት ዝግጅት፣ የኦዲት ምርመራ፣ የታክስ አሰራር እና የፋይናንስ እቅድ ማውጣትን የሚያስተምር ትምህርት ነው። የሥራ እድሎች፦ በባንኮች፣ በሚክሮፋይናንስ እና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሂሳብ ሹም/ኦዲተር በግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ማኔጀር የውጭ ኦዲት እና የታክስ አማካሪ (Tax & Audit Consultant) 8. ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ (Biomedical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ጅማ ዩኒቨርሲቲ (JiT) ዲፓርትመንቱ፦ የቴክኖሎጂ እና የህክምና ሳይንስ ውህደት ሲሆን፣ የህክምና መሳሪያዎችን (እንደ CT Scan, MRI, Ultrasound) ዲዛይን ማድረግ፣ መገጣጠም እና መጠገንን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች ውስጥ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና እና ቁጥጥር ኢንጂነር የህክምና መሳሪያዎችን በሚያስመጡ እና በሚሸጡ ድርጅቶች የቴክኒክ ስፔሻሊስት በምርምር ማዕከላት የሰው ሰራሽ አካላት (Prosthetics) እና የህክምና ቴክኖሎጂዎች አልሚ 9. ቢዝነስ ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ / MIS (Business Information Systems) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እና በንግድ ስራ ማኔጅመንት መካከል ያለውን ድልድይ የሚያጠና ሲሆን፣ መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ለንግድ ውሳኔዎች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያስተምር ነው። የሥራ እድሎች፦ የቢዝነስ ኤአይ / ዳታ አናሊስት (Data / Business Analyst) በባንኮች እና በድርጅቶች የዳታቤዝ እና የሲስተም አድሚኒስትሬተር የኢአርፒ (ERP) እና የሶፍትዌር ትግበራ አማካሪ (IT Consultant) 10. ሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት (Logistics & Supply Chain Management) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (የንግድ ስራ ትምህርት ቤት) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የዕቃዎች እና አገልግሎቶች እንቅስቃሴ ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ ያለውን የትራንስፖርት፣ የመጋዘን፣ የጉምሩክ እና የእቃ አያያዝ ሂደት የሚያስተዳድር ትምህርት ነው። የሥራ እድሎች፦ በወጪና ገቢ (Import/Export) ድርጅቶች የሎጅስቲክስ ማኔጀር በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ፋብሪካዎች የአቅርቦት እቅድ አውጪ (Supply Chain Officer) በጉምሩክ፣ በትራንስፖርት ኩባንያዎች እና በማላኪያ/ሺፒንግ ኤጀንሲዎች የኦፕሬሽን ኃላፊ

📣 ለ2019 የመጀመርያ አመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ! ሙሉ በሙሉ ያለምንም ክፍያ የቀረበው ዝግጁ አፕ አዲስ ገጽታ ይዞላችሁ መጥቷል! ከአሁን ጀምሮ የፍሬሽማን እያንዳንዱን ትምህርት በየቻፕተ
📣 ለ2019 የመጀመርያ አመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ! ሙሉ በሙሉ ያለምንም ክፍያ የቀረበው ዝግጁ አፕ አዲስ ገጽታ ይዞላችሁ መጥቷል! ከአሁን ጀምሮ የፍሬሽማን እያንዳንዱን ትምህርት በየቻፕተሩ የተከፋፈሉ አዳዲስ የልምምድ ጥያቄዎች ተሰብስበው ገብተውላቹኋል። 📣 ይህ አዲስ ገጽታ ምን ይጠቅማቹሃል? ➡️ለፈተና 100% ያዘጋጃችኋል፡ ከትምህርቱ ይዘት ጋር የተጣጣሙ ጥያቄዎችን በመስራት ሙሉ በሙሉ ያዘጋጃቹሃል። ➡️ድክመታችሁን ይለያል፡ ክፍተት ያለባችሁን ቻፕተር በግልጽ በማሳየት ትኩረታችሁን የት ማድረግ እንዳለባችሁ ይጠቁማችኋል። ከዚህ በተጨማሪም ለጥናታችሁ የሚረዱ በርካታ አዳዲስ አገልግሎቶችን በቅርብ ቀናት እናስገባላችኋለን! 🔎 እንዴት እንደምትመዘገቡ ለማየት ማስታወሻ፦ Password የረሳችሁ መመዝገቢያ ቦት ላይ "Change Password" የሚለውን ቁልፍ ተጫኑ ወይም /recover ብላችሁ ይላኩ። ለመመዝገብ - @Zegju_registration_bot ▶️ Android (Play Store) 🛒 iOS (App Store)

📣 የጥሪ ማስታወቂያ ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ለተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፦ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ፣ የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ፦ • ሁሉም ነባር ተማሪዎች • በ2018 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች • ለ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የፍሬሽማን እና የሪሜዲያል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ጊዜ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ስለሆነ፣ በተጠቀሰው ቀን በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

#EPSU የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል። ለምዝገባ
#EPSU የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ 🔵 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 ከ9–12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣ 🔵 የፋይዳ መታወቂያ ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ 🔵 ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፣ 🔵 የስፖርት ልብስ። (ተጨማሪ መረጃ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) @FreshmanUnion✔️

🔥 መልካም የዳመራ ስነ-ስርዓት ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንመኛለን! @FreshmanUnion ✔️
🔥 መልካም የዳመራ ስነ-ስርዓት ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንመኛለን! @FreshmanUnion ✔️

👆👆👆 PLACEMENT RESULT – 2018 batch (2nd Year Students)   We are pleased to announce this year's placement results for 2018 entry students. Please note the following important points: 1. A cut-off point to join each program and a description of the remarks are provided on the last page of this placement document (page 48).  2. Complaints can be submitted until mid-day (11:30 AM or 5:30 LT) on Friday, September 24, 2026. Complaints will be collected ONLY via a complaint form, which can be collected from Pre-Engineering office (NB 205B) and should be valid as per the criteria and cut-off point to join each program.  3. Those who are not placed and didn’t choose program preference (e.g., readmission students, student with NG grade), please use stamped Program Preference Verification Form to present your case until mid-day (11:30 AM or 5:30 LT) on Friday, September 24, 2026.   NB: We don't accept any complaint about placement via email, telegram. phone call, or text messages. The TLS Office @Hsquareedu

የዝውውር ቅድመ-ሁኔታ፡ ዝውውር የሚፈጸመው የላኪ እና የተቀባይ ዩኒቨርሲቲዎች ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፤ ትምህርት ሚኒስቴርም በደብዳቤ ሊያውቀው ይገባል። የትምህርት ቆይታ መስፈርት፡ ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ 1 ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50% በላይ ያላጠናቀቀ መሆን አለበት። የተከለከሉ አሰራሮች፡ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚኒስቴሩ ምደባ ውጭ በራሳቸው ተነሳሽነት ተማሪ መቀበል፣ መመዝገብ ወይም ተቋም መቀየር አይችሉም። ልዩ አስተናጋጅነት የለም፡ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ አሰራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር የተከለከለ ነው። የመንግሥት እና የግል ተቋማት ዝውውር፡ ከመንግሥት ወደ ግል ተቋም መዛወር ይቻላል፤ ነገር ግን ከግል ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ መዛወር አይቻልም። @FreshmanUnion ✔️

📣ስለዩኒቨርሲቲ ዝውውር ጥያቄ ላላችሁ በሙሉ "ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህር
+1
📣ስለዩኒቨርሲቲ ዝውውር ጥያቄ ላላችሁ በሙሉ
"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡
- ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡ ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡ ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም። ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል። የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ @FreshmanUnion ✔️

ነፃ የፍሬሽማን የጥናት አፕልኬሽናችንን ተጠቀሙ 👉
ነፃ የፍሬሽማን የጥናት አፕልኬሽናችንን ተጠቀሙ 👉

የፍሬሽማን ነጻ የጥናት አፕ
የፍሬሽማን ነጻ የጥናት አፕ

AASTU Freshman Student Information Announcement Dear Freshman Students, The AASTU Freshman Student Information Portal is now available. Please visit: https://www.aastu.edu.et/freshmaninfo/ To check your information, enter your: Grade 12 Entrance Exam Admission Number of 6 digit and First Name After submitting the form, you can view your student ID, institutional (AASTU) email address, field of study, dormitory placement such as room, block, floor Please carefully review all displayed information. For any incorrect or missing information, contact the  AASTU Registrar office in person for assistance. @FreshmanUnion✅️

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የፖርታል (Portal) የይለፍ ቃላችሁን (Password) ካረሳችሁ ወይም አካውንታችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ከተዘጋባችሁ (Blocked/Locked)፤ ወደተመደባችሁበት ኮሌጅ የሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት (Registrar Office) በአካል በመቅረብ የይለፍ ቃላችሁን ማስቀየር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃችኋለን። @FreshmanUnion✅️