Mohammed Seid - Miftah
前往频道在 Telegram
🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
显示更多未指定国家未指定类别
2 480
订阅者
-124 小时
+1177 天
+35130 天
帖子存档
አበቃበት የተባለው አፕል በiPhone Duo ተከስቷል! 😍
አፕል የመጨረሻውን የቴክኖሎጂ አቅሙን በመጠቀም የመጀመሪያውን ተጣጣፊ ስልክ "iPhone Duo" ይፋ ማድረጉን አስታውቋል። ይህ ስልክ ሲታጠፍ 5.4 ኢንች እንዲሁም ሲከፈት ወደ 7.6 ኢንች ግዙፍ OLED ስክሪን የሚቀየር ሲሆን፣ በኃይለኛው A20 Pro ቺፕሴት እና በታይታኒየም ማጠፊያ መዋቅር የተገነባ ነው።
#Apple #iPhoneDuo
በ No-Code AI ብቻ ሙሉ መተግበሪያ (App) መስራት ይቻላል? 🤖📱
አሁን ባለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን እንደ GitHub Copilot, FlutterFlow, Cursor, Replit, Bubble, v0, Google Al Studio እና Bolt.new ባሉ No-Code AI መሳሪያዎች አፕሊኬሽን መስራት በጣም ቀላል ሆኗል። ነገር ግን "ዝም ብሎ በPrompt (በትዕዛዝ) ብቻ ውጤታማ መተግበሪያ መስራት ይቻላል?" ካላችሁኝ... መልሴ አይቻልም! ነው፡
AI ጥሩ ረዳት እንጂ ሙሉ በሙሉ አእምሯችንን የሚተካ አይደለም። በትዕዛዝ ብቻ የሚሰራ አፕ ውጫዊ ገጽታው (UI) ያማረ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን እውነተኛ ቢዝነስ የሚሆን አፕ ለመስራት ከPrompt ባሻገር እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ማወቅ ግዴታ ነው።
1️⃣ የዳታቤዝ ዲዛይን (Database & Logic): መረጃዎች እንዴት እንደሚቀመጡ፣ እንደሚገናኙ እና እንደሚሰረዙ የዳታ ፍሰቱን ማቀድ የራሳችን ድርሻ ነው።
2️⃣ API እና Integrations: አፑ ከሌሎች ሲስተሞች ጋር (ለምሳሌ ከቴሌብር/Chapa ለክፍያ ወይም ከSMS Gateway) እንዴት እንደሚገናኝ መረዳት።
3️⃣ የUI/UX ህጎች: አፑ ለተጠቃሚዎች ቀላል እና ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ።
4️⃣ Debugging (ስህተትን ማረም): AI Error ሲሰራ ስህተቱን ተረድቶ መልሶ ለማሻሻል መሰረታዊ እውቀት ማካበት። ቀለል ለማድረግ እንጅ ብዙ አሉ ስለ Framwork እና የሶፍትዌር ልማት ሂደቶችንም ጭምር ማወቅ ግድ ነው።
ራሱንም AI ምንድን ነው? እንዴት ይሰራል የሚለውንስ ማወቅ ግዴታ አይደለም? ስለ prompt engineering ስ ማወቅ ግዴታ አይደለም? መልሱን ለእናንተ ትቻለሁ።
በአጭሩ በ No-Code AI መሳሪያዎች የፕሮግራሚንግ ኮድ የመጻፍ ድካምን ይቀንሱልናል እንጂ የሶፍትዌሩን Logic (ሎጂክ) የማሰብ ኃላፊነት የራሳችን ነው።
አፕ ለማልማት ኮድ ማወቅ አያስፈልግ ይሆናል፤ የሲስተም ሎጂክ ማወቅ ግን ግዴታ ነው! 😉
ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ቀላል ዘርፍ አይደለም እያስፈራሗችሁ አይደለም በዘርፉ ለመቀጠል ፍላጎት ካላቸሁ መሰረቱን ማወቅ ግድ ነው።
በእኔ ግምት የበለጠ ውጤታማ (productive) የሚሆኑት አሁንም የዘርፉ ባለሙያዎች ናቸው ብዬ አስባለሁ።
No-code Al ልምምድ ጎን ለጎን የዘርፉን መሰረታዊ እውቀት እንማር የሁልጊዜም መልእክቴ ነው።
ሀሳቤን የመንቀፍ ሆነ የመደገፍ መብታችሁ የተጠበቀ ነው።
ኮሜንት ላይ ተጨማሪ ይቻላል!⤵️
📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ፣ AI እና የሶፍትዌር ልማት መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉 https://t.me/miftahcode
ያለ እውቀት መናገር አይቻልም ፤ ያለ እውቀት መስራትም አይቻልም!
ያለ እውቀት የሚደረግ ጉዞ ወይም የሚሰራ ስራ መዳረሻው ጥፋትና ውድቀት ብቻ ነው የሚሆነው። እውቀት ለአእምሮ ብርሃን፣ ለውሳኔዎች ደግሞ መሰረት ነው።
በማንኛውም መስክ ቢሆን—በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ፣ በስራ ወይንም በዕለት ተዕለት ህይወት—እውቀት ሲኖረን የምንናገረው ነገር ክብደት ይኖረዋል፣ የምንሰራውም ስራ ጥራትና ውጤት ይኖረዋል!
እናም እውቀት ጥሩ ነው።
ጠቃሚ የሆነ እውቀት ይስጠን!🤲
Alን ተጠቅመን የሞባይል መተግበሪያ ለማበልፀግ ለ Al agent ወይም ቻትቦት እንዴት ትዕዛዝ እንሰጣለን ⤵️
👉 ምሳሌውን በ Google Al Studio መሞከር ትችላላችሁ
📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂና AI መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉 https://t.me/miftahcode
🤖 ከ AI ቻትቦቶች ጋር የምንፈልገውን ምርጥ ውጤት ለማግኘት ቁልፉ ያለው ጥያቄ አጠያየቃችን (Prompt Engineering) ላይ ነው!
ከ AI ጋር ውጤታማ ውይይት ለማድረግ እነዚህን 2 ወሳኝ ነጥቦች ተግብሩ፡
1️⃣ ጥሩ ጥያቄ (Prompt) ማዘጋጀት፡ የምትፈልጉትን ነገር በግልጽ፣ በዝርዝር እና ለ AIው ሚና (Role) ሰጥታችሁ ጠይቁት።
2️⃣ ውይይቱን እዚያው ማሻሻል (Iterate)፡ የመጀመሪያው መልስ ካልረካችሁ አዲስ Chat ከመክፈት ይልቅ፣ እዚያው የጀመራችሁት ውይይት ላይ ጥያቄያችሁን እያስተካከላችሁና እያጠራችሁ ሂዱ።
💡 አስተውሉ፡ AI መልስ የሚሰጠው እኛ በሰጠነው መመሪያ ልክ ነው!
📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂና AI መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉 https://t.me/miftahcode
👉 ምስሉ ላይ ያለውን ጥያቄ ውጤቱን ለማየት በዚህ ሊንክ ማየት ትችላላቸሁ፡ https://share.gemini.google/2mEBqlt51NDC
ብዙ ጊዜ የተለያዩ ጥናቶችን ስንመለከት ወይም ሚዲያ ላይ ስንሰማ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለ White-Collar Jobs ስጋት ነው ይባላል። በመሆኑ ምን ማለት ይሆን? ለምንስ ስጋት ሆነባቸው?
ቴሌግራም⤵️
https://t.me/miftahcode
በጣም የገረመኝ እና ደፋር ሪፖርት ነው።
ጫናው ዘርፈ- ብዙ ነው ፤ ከአሜሪካ ዶላር ጋር በተያያዘ ኢኮኖሚያችንን ጠፍሮ የያዘው ሳያንሰን በዚህ በኩልም ምክረ-ሀሳብ አለኝ እያለ ነው፡፡
በተከታይ እዳስሰዋለሁ!
እስኪ ኮሜንት ላይ እንወያይበት? እውነት የአለም ባንክ ምክረ-ሀሳብ ነው ምርጫችን? ለዚህ የሚሆን ዝግጁነትስ የለንም?
ለበለጠ ቴሌግራም ቻናሌ ⤵️
https://t.me/miftahcode
ስቴፈን ሃውኪንግን ከዛሬ 10 አመት በፊት ስለ Al የተናገረውን ንግግር ስመለከት በጣም ገረመኝ። 🤔
ዛሬ እኛ የምንገረምበትን የ-AI እድገት ሳያይ ነበር ያኔ ያስጠነቀቀው። 'ካወቅንበት ምርጡ ነገር ነው፣ ካልተጠነቀቅንበት ግን የከፋው አደጋ ነው' ያለው ሃሳብ ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ይበልጥ እውነት ሆኗል!
የሳይንቲስቱን ሀሳብ እንዴት አያችሁት?
ከቴሌግራም ቻናላችን ፋይል ማውረድ ፣ የወደዳችሁትን ሼር ለማረግ መቸገራችሁ ይታወቃል። በሰጣችሁኝ አስተያየት መሰረት ክልክላውን አንስቻለሁ!
ፋይል ማውረድ ፣ ለሌሎቹ ሼር ማድረግ አሁን ይቻላል!
አ መ ሰ ግ ና ለ ሁ!
Stay Connected 🥰
🤖 ChatGPT የኬንያውያንን ወጣቶች ጉሮሮ ዘጋው! 😂
ለዓመታት የአሜሪካና የአውሮፓ ተማሪዎችን የቤት ሥራ እና Essay በገንዘብ በመጻፍ Freelance ዶላር ሲያፍሱ የነበሩ የኬንያ ወጣቶች፣ አሁን ላይ ሥራቸውን በ #ChatGPT ተነጥቀዋል።
«ተማሪዎቹ ከእኛ ይልቅ AIን በነፃ ማዘዝ መረጡ» ያሉት ወጣቶቹ ፣ አሁን ደግሞ አዲስ ሥራ ጀምረዋል፦ “AI የጻፈውን ጽሑፍ የሰው ልጅ የጻፈው ለማስመሰል ማስተካከል!” 🏃♂️💨
አይ ቴክኖሎጂ... ምን እነሱን ብቻ! 😄
ይህን መረጃ ያጋራው The New York Times ነው!
🚀 በነጻ የዲጂታል ማርኬቲንግ ሰርቲፊኬት ማግኘት ይፈልጋሉ?
ዓለም ወደ ዲጂታል እየተቀየረች ባለችበት በዚህ ጊዜ፣ የዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀት ለምንም አይነት ቢዝነስ ወይም ሙያ ወሳኝ ነው!
ታዋቂው እና ልምድ ያለው HubSpot Academy ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጠውን Digital Marketing Certification Course ጥቆማ ልስጣችሁ። በብዙ የገጻችን ተከታዮች የተወደደ ኮርስ ነው።
ከዚህ ኮርስ ምን ያተርፋሉ?
➡️SEO (Search Engine Optimization): ዌብሳይትን በፍለጋ አማራጮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ እንዲታይ ማውጣት
➡️Social Media & Content Strategy: ሳቢ ይዘቶችን በመፍጠር የሶሻል ሚድያ ተከታዮችን ማሳደግ
➡️Email & Ads Strategy: ውጤታማ የኢሜይል እና የክፍያ ማስታወቂያዎችን መስራት
➡️ Inbound Marketing: ደንበኞችን በራስ አቅም መሳብ እና ማቅረብ
🎯 ለማን የሚሆን ኮርስ ነው? የራሳቸውን ቢዝነስ ማሳደግ ለሚፈልጉ፣ ማርኬተሮች፣ የኦንላይን ስራ ጀምረው ገቢ ማግኘት ለሚፈልጉ እና አዳዲስ የዲጂታል ክህሎቶችን ማዳበር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው!
📌 ትምህርቱ በራስዎ ጊዜ የሚወሰድ (Self-paced) ሲሆን ሲጨርሱም ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርቲፊኬት ያገኛሉ።
🔗 አሁኑኑ ይመዝገቡ፦ የምዝገባ ሊንክ⤵️
https://academy.hubspot.com/courses/digital-marketing
ይህንን መረጃ ለሌሎችም Share ያድርጉት! 💡
📚 ለሁለተኛ ደረጃ እና ለኮሌጅ ተማሪዎች የሚሆን ድንቅ የትምህርት መረጃ!
የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ ወይም የጠፈር ሳይንስ (Astronomy) ትምህርቶችን በነፃ እና በከፍተኛ ጥራት ማጥናት ይፈልጋሉ?
OpenStax በታወቀው Rice University የሚዘጋጅ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውን የሳይንስ መጽሐፍት በነፃ (PDF) ማውረድ የሚያስችል ድንቅ ገፅ ነው!
📌 የሚገኙ ዋና ዋና የትምህርት ዘርፎች፡
↗️Physics (Introductory, College & University Physics)
↗️Chemistry (General Chemistry, Organic Chemistry)
↗️Biology (Concepts of Biology, Anatomy & Physiology)
↗️Astronomy
↗️Mathematics
↗️Computer Science እና ሌሎችም
መጽሐፍቶችን በነፃ ለማውረድ እና ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፡
👉 https://openstax.org/
መረጃውን ለወንድም፣ እህቶቻችሁ እና ለተማሪ ወዳጆቻችሁ በማጋራት (Share) ተደራሽ አድርጉት!
📚 Mathematics for Computer Science
ለኮምፒውተር ሳይንስ፣ ለሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ለ-AI/ML መሠረታዊ የሆነውን ሂሳብ (Mathematics) በጥበብ የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ!
በ Massachusetts Institute of Technology ምሁራኖች የተዘጋጀ !
OR
https://ocw.mit.edu/courses/6-042j-mathematics-for-computer-science-spring-2015/mit6_042js15_textbook.pdf
ችግሩ ለምን እንደሚጠቅም መቼ እና የት እንደሚተገበር አልነገሩንም እንጂ ሒሳብ እማኮ ...😍 እናም እንውደደው በቅጡ እንማረው!
ሂሳብ ማለት ቁጥር መደመር ብቻ ነው ወይንስ የአስተሳሰብና የፈጠራ መሠረት? ለዚህ አስተያየት የሚሆን ጠንከር ያለ ምላሽ ያላችሁ የሂሳብና የኮምፒዩተር ሳይንስ ሰዎች ድምፃችሁን አሰሙ!
በነገራችን ላይ ብዙዎች እንደዚህ ያስባሉ በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ሳይቀር !
ነፃ የ Generative AI ኮርስ ከ Microsoft! (Version 3)
የ AI መተግበሪያዎችን ከባዶ መገንባት ይማሩ! በ Microsoft Cloud Advocates የተዘጋጀው Generative AI for Beginners ኮርስ በ 21 ክፍሎች ተሻሽሎ ቀርቧል።
ዋና ዋና ይዘቶች፡
🎥 አጫጭር የማብራሪያ ቪዲዮዎች እና ዝርዝር የፅሁፍ ትምህርቶች
💻 በ Python እና TypeScript የተዘጋጁ የተግባር (Coding) ልምምዶች
🔄 ቲዎሪ ("Learn") እና ተግባራዊ ኮዲንግ ("Build") ያካተተ
🌐 ሞዴሎችን ያለ ኢንተርኔት በራስዎ መሣሪያ ላይ ማስኬድ የሚያስችል Foundry Local አገልግሎት
🤝 የ Microsoft Foundry Discord ማህበረሰብ ድጋፍ እና ለ Startup ፈጣሪዎች የ Azure Credits እድል
🛠 ለመጀመር፡ የ Python/TypeScript መሰረታዊ እውቀት፣ GitHub አካውንት እና የ API መዳረሻ (Azure OpenAI፣ OpenAI API፣ Microsoft Foundry Models ወይም Foundry Local) ያስፈልጋል።
🎯 አሁኑኑ ይጀምሩ፡ GitHub ላይ "Generative AI for Beginners by Microsoft" ብለው ይፈልጉ! ማከማቻውን (Repository) Star (🌟) ማድረግ እንዳይረሱ!
የኮርሱን እና ሌሎች ጠቃሚ ሊንኮችን:
↗️ Generative AI for Beginners (Version 3)
↗️ How to Create a GitHub Account (Step-by-Step for Beginners)Amharic ጊትሃብ አካውንት መክፈት በአማርኛ
↗️ Run local AI on any PC or Mac - Microsoft Foundry Local
↗️ Microsoft AI foundry Discord
