የክብሩ ነፀብራቅ✨
前往频道在 Telegram
ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]
显示更多未指定国家未指定类别
357
订阅者
无数据24 小时
+127 天
+9330 天
帖子存档
357
Repost from የክርስቶስ ፈለግ
....
የበለጠ እንወቀው.....!
አቤት፣ መታወቅ ግን ምኔኛ ደስ የምል ነገር ነዉ! ስማችን ሲጠራ፣ በስም ተጠርተን ሰላም ስንባል ፥ የነፍስ ዕርካታዋ የሚነገር አይደለም። የእግዚአብሔር አሠራርማ ግሩም ነው! "እንቶኔ" ተብሎ በስም መጠራትና መታወቅ የሚፈጥረው ደስታ ለነፍሳችን ልዩ ነዉ። የምያዉቀንን አካል ባወቅን ዕለት፥ በልባችን ሞገስንና ልዩ ትኩረትን ያገኛል። የፈጣሪ አሠራር ድንቅ ነውና ለሠሪው ክብር ይግባው። ይበልጥ መታወቅና መጠጋት በጨመረ ማግስት ድካም ጎልቶ የምታይባት የሰዉ ነፍስ እንኳ እንደዚህ የምትሻ ከሆነ፤ ታውቆ የማያልቅ፣ ባወቅነው ልክ ወደር የለሽ ብርታቱን የሚያሳይ እግዚአብሔር ምንኛ ለመታወቅ ይፈልግ ይሁን?
ሆሴዕ 6፡6«ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እሻለሁና።»እግዚአብሔር የአጽናፈ ዓለም (Universe) ፈጣሪ ነው። እግዚአብሐርን በመልካምነቱና በቁጣዉም የማያቅ ጥቅት ነዉ። ሀሉም ፈጣሪ ይለዋል። በዕውነቱ ፈጣሪውን የማያውቅና "ፈጣሪ ይመስገን" የማይል ሰው ይገኝ ይሁን? አላውቅም። እግዜር የሌሽ (Atheist) ካልሆነ በስተቀር፣ በማኅበረሰባችን ውስጥም ይሁን በዕለት ተዕለት ሕይወት ይህንን የማይል ሰው የለም ብል አልሳሳትም። ታዲያ ይህ ሁሉ እግዚአብሔርን አዉቋልን? ካልሆነስ እግዚአብሔር በቃሉ የሚሻው እውቀት የትኛው ነው? በዚያ ዘመን እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብን ያውቁ ነበር፤ መሥዋዕቱንም አዘውትረው ያቀርቡ ነበር። ነገር ግን ራሱን እግዚአብሔርን አያውቁትም ነበር። ይገርማል። ሆሴዕስ ምን ይላል? እግዚአብሔርስ ምን እያላቸው ነው? እግዚአብሔር የሚፈልገው፤ በመረጃ፣ በአዕምሮ ብቻ የሚተነተን፣ ወይም ለሰዎች ለማብራራት የሚመች የደረቀ የንድፈ ሀሳብ እውቀት አይደለም። ከጣዖት አምልኮ ጋር ያልተላቀቀ፣ ዕርሾ የሞላበትን ልምምድም አይደለም። እርሱ የሚፈልገው—መነካካት፣ መደማመጥ፣ መነጋገር፣ የፍቅሩን ቅምሻ ማጣጣም፣ የልጅና የአባት ምና የተወጣበት ፣ ከእርሱ ጋር መዋል፣ መቆየት እና እግዚአብሔርን በውኑ መፈለግ የታከለበት የሕይወትና የልምምድ እውቀት (Experiential Knowledge) ነው። በዘመናችንም ክርስትናችን ከዕውቀት የዘለለ፣ የሕይወትና የኃይል ድርሻውንም የሚያሳይ ይሁንልን። እግዚአብሔርን ከእለት ተዕለት ኑሯችን ጋር አብረን እንወቀው! አሜን! ተባረኩልኝ። 🥰
እግዚአብሔርን እንወቀው፤የበለጠ እናውቀው ዘንድ እንትጋ፤እንደ ንጋት ብርሃን፣በእርግጥ ይገለጣል! — ሆሴዕ 6፡3.......
357
ያለ ኢየሱስ እንዴት መኖር ይቻላል ግን?!..
አንዳንድ ጊዜ ሰው ከክርስቶስ ውጪ በእውነት ምንን ታምኖ ምንንስ ተደግፎ ነው ሚኖረው ብዬ አስባለሁ?!!
@ShekinnahKBR
357
ህልውናህ ህይወቴ ነው መገኘትህ 🔥
እኔ አልችልም ከቶ መኖር ያለአብሮነትህ
የአንተ መኖር መኖሬን ወስኗል🫠🫠🫠
ልቤም አንተን አንተን ይላል🙇♂🙇♂🙇♂🙇♂
☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️☁️
🌩🌩🌩 † 🌩🌩🌩
🧎♂️➡️🧎🏻♂️➡️🧎🏽♂️➡️🔥🧎🏿♂️🧎🏽♂️🧎♂️
@ShekinnahKBR
357
የአንዲት የደከመች ነፍስ ፀሎት 🧎♂️
አባ በፊትህ ተንበርክኬ ቃላት ገጣጥሜ ድምፀን ከፍ አድርገ በብዙ ልሳኖች አንተን ማውራት አቅቶኝ... በታላቅ ፀጥታ ብምበረከክም እባክህ ከእግርህ ስር የምቆይበትን ፀጋ አብዛልኝ🥹🙏
✒️ኑ እንታደስ
@ShekinnahKBR
357
ቤተሰቦቼ.....
ጌታ ብረዳኝ በቅርቡ፡ የተነካሁባቸውን Devotional የሆኑ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳቦችን በ Voice [ድምፅ] ማስቀመጥ እጀምራለሁ። እስከዛው Channel ለብዙ ሰው እንዲደርስ Share በማድረግ ተባበሩኝ😊
Coming Soon..@ShekinnahKBR
357
ያ በግርማው የሚያስፈራው ልንቀርበው በማንችል Presence ውስጥ ያለው ትልቁ እግዚአብሔር ለእኛ ሲል ከክብሩ ወረደልን😭
እንዴት ቢወደኝ ነው? እንዴት ቢወደን ነው?
ተወደናል ቤተሰቤቼ🤍
Have a Lovely Day👌
357
ነገ 🤌
ትዝ ይለን የለ ሰዎችዬ እስራኤላውያኖች እንደ እግዚአብሔር ቃል ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፈው ነበር እነዛን ፈተናዎች ሁሉ አልፎ እግዚአብሔርም ደግሞ በባህር መካከል በየብስ ካሻገራቸው በኋላ የረሃብ ፈተና በድጋሚ ወረደ በዚያም ጊዜ ሁሉም ፊታቸውን ወደ ሙሴ አዙረው የሀዘን እንጉርጉሯቸውን ሲያንጎራጉሩ ሙሴም እንዲህ ሲል ተናገራቸው" እኔ ማን ነኝ?ችግር ሲያጋጥማችሁ ፊታቸውን የምታዘሩብኝ ፊታችሁን ወደ እግዚአብሔር አዙሩ "ብሎ ሙሴ ከተነገራቸው በኋላ እግዚአብሄርም ጩኸታቸውን ሰምቶ እንዲህ ሲል ለሙሴ ተናገረ በማታ ስጋን በቀንም እንድትጠግቡ እንጀራና አዘንባለሁ ካለ በዃላ እግዚአብሔር ለሙሴ ደግሞም እንዲህ ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጠ "ስትሰበስቡ ለእለት የሚሆናችሁም ብቻ ሰብስቡ" ሲል አሳሰበው.....እንደኔ ያሉ እስራኤላውያን ለነጋቸው ከነጋቸው ፈጣሪ በላይ የሚጨነቁና የሚያስቡ የሚመስላቸው ሰዎች ነበሩና ለነገ ብለው ከእለታቸው በላይ አብዝተው የሰበሰቡ ነበሩ..በነዛ ሰዎች ላይም እንዲህ ሆነ......ዘፀአት 16:20 ነገር ግን ሙሴን አልሰሙትም፤ አንዳንድ ሰዎችም ከእርሱ ለነገ አስቀሩ፥ እርሱም ተላ ሸተተም፤ ሙሴም ተቈጣቸው።.....እነዚህ ሰዎች ለነገ ብለው ባስቀመጡት ነገር ላይ ችግር የገጠማቸው ስለነገአቸው በማሰባቸው ብቻም ሳይሆን ዛሬን እንደ እግዚአብሔር ቃሉ ባለመኖራቸው ነው....ለነጋችን ነገን የሚፈጥረው አምላክ እንዴት እንደሚሰራው እና እንደሚያበጃጀው ያቅበታልና ነገን እናሳምራለን ብለን ዛሬ የተሰጠንን ስጦታ እንዳናበላሸው...
አስተውሉ ሰዎችዬእንደ እግዚአብሔር ፀጋ ለነገ መዘጋጀትና ስለነገ አብዝቶ መጨነቅ is so different ....የኔ አምላክ ስለሰጠኸኝ ዛሬ ስለ ሰጠኸኝ ስጦታ አመሰግንኸለሁ ለነገ አንተ ስለ ቃልህ ስትል ታማኝ ነህና አምንኸለሁ።ዛሬን እንደቃልህ ልኑርልኽ‼️
ከTikTok መንደር
@ShekinnahKBR
