ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد2 976
المشتركون
+2324 ساعات
+367 أيام
+41430 أيام
أرشيف المشاركات
+6
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም ድል ተቀዳጅቷል ።
ክፍለጦሩ ባደረገው ትንቅንቅ 44ኛ ክፍለ ጦር
68 ጥምር ጦር (ሚኒሻ፣ አድማ ብተና፣ መከላከያ ፣ፖሊስ ሲደ*መሰስ፡)
2 ብሬን
55 ክላሽ
3 መገናኛ ሬዲዮ
5000 በላይ ክላሽ
3000 የሚደርስ የብሬንና
2 አስቃጥላ የድሽቃ ተተኳሽ ሲማረክ
5 መከላከያና
2 አድማ ብተና ተማርኳል።
በተመሳሳይ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከደብረ ማርቆስ ከተማ የካድሬዎች መገልገያ ፒካፕ መኪና ማርኳል ።
ድል ለጀግናው አማራ
ድል ለጀግናው ፋኖ !!
+1
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም ድል ተቀዳጅቷል ።
ክፍለጦሩ ባደረገው ትንቅንቅ 44ኛ ክፍለ ጦር
68 ጥምር ጦር (ሚኒሻ፣ አድማ ብተና፣ መከላከያ ፣ፖሊስ ሲደ*መሰስ፡)
2 ብሬን
55 ክላሽ
3 መገናኛ ሬዲዮ
5000 በላይ ክላሽ
3000 የሚደርስ የብሬንና
2 አስቃጥላ የድሽቃ ተተኳሽ ሲማረክ
5 መከላከያና
2 አድማ ብተና ተማርኳል።
በተመሳሳይ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከደብረ ማርቆስ ከተማ የካድሬዎች መገልገያ ፒካፕ መኪና ማርኳል ።
ድል ለጀግናው አማራ
ድል ለጀግናው ፋኖ !!
ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤክርስቲያንን እንዲታደግ የቢቡኝ ወረዳ የኮርብታና አካባቢው የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ።
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ሚያዚያ29/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ ጀነራሎች በአደባባይ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ምሽግ በማድረግና ፀበሏን መዳኘዋን ለሻወርና ለመጠጥ በመጠቀም ልዕልናዋን እንደገፏት የቢቡኝ ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ተናግሩ።
በአማራ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወረራ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጥታ ጥቃት እየተፈፀመባት ነው ያሉት የሐይማኖት አባቶች በበኩላቸው ካህናት፣ ቀሳውስት ፣ የአብነት ተማሪዎችና ዲያቆናት እየተገደሉ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየተስተጓጎለ ይገኛል ብለዋል፤ አክለውም የወረዳዋ ድጎፅዮን ጫፍ ላይ ሉባ አዲሱ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለአገዛዙ ምሽግ፤ ማደሪያ ብሎም ጥንታዊቷን ድጓፅዮን ቤተክርስቲያንን አጥሯ ተደፍሮ ምሽግ አድርጓል በማለት ተናግረዋል። እንዲሁም የወረዳዋ ታዳጊ ከተማ የሆነችው ወይንውሃ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ጦር ፋሲለደስ ቤተክርስቲያንን ምሽግ ማድረጉን በቁጭት ገልፀዋል።
ከዚህ በፊት በድምቀት የሚከበሩት ዓመታዊ ሐይማኖታዊ በዓላት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመመሸጉና የሐይማኖት አባቶችን በማሳደዱ በተለመደው መልኩ ማክበር አለመቻሉንም አስታውቀው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቅርሷ እየተዘረፈ፤ ስርዓቷ እየተገፈፈ፤ አገልጋዮቿ እየተገደሉ በመሆኑ ፀበሉን እንደ ውሀ እየቀድ እየጠጡት ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ከመጥፋት እንዲታደጋት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህም 201ኛ ኮር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!፥
በሚል መሪ ቃል ቢቡኝ ወረዳ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት
+8
#እጅ_ያልሰጡት_ተደምስሰዋል
ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ ጀብድ እየፈፀመ ሲሆን #እጅ_አንሰጥም ያሉት የተደመሰሱ ሲሆን እድለኞች ተማርከዋል 💪
ንስር አማራ የምርኮ ዝርዝር ይዛ የምትመለስ ይሆናል ይጠብቁን....‼
በኤፍራታና ግድም ወረዳ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ የሚኖሩ የሙስሊም እምነት ተከታይ አማራዎች በከሀዲው ብልፅግና አመራሮች ከፍተኛ ዘረፋ ሲፈፀምባቸው፣የአገዛዙ 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሩ ፋኖን ተቀላቅሏል።
ሚያዚያ 29/2018ዓ.ም
በጉባ ዋጮ የሚኖሩ ሙስሊም አማራዎች ሁለት ቋንቋ በመናገራቸው ካሁን በፊት ቤታቸው በብልፅግና አስተባባሪነት በልዩ ዞኑ የኦሮሞ ብሔረሰብ አመራሮች ቤታቸው ተቃጥሎባቸውና ንብረታቸውም ተዘርፎ ሸራ ጥለው የሚኖሩ ነበሩ።
ብልፅግና የሚባል ነውር ጌጡ መሬታቸው ለረጅም ጊዜ አድሮ የሚገኘውን ሱካይ ቆላ "ኑ እረሱ" በማለት ስንዴ ዝሩ በማለት አርሰው፣አለስልሰው ደክመው አዝምረው አጭደው ወቅተው ለልጆቻቸው ዳቦ ሊያቀምሱ ሲሉ በፎቶው ላይ በሚታየው ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል አንስቶ ይጠቀምበታል።
የለመደውን ዝርፊያ አይገባችሁም በማለት በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሰንበቴ መሬት አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አብዱ ሽሮ ከግብረ ሀይሎቹ ጋር በመሆን ወደ ወረዳቸው በመኪና በመጫን እጃቸውን እያርገበገቡ እህል እህል ሲሉ በአደባባይ ተዘርፈዋል።
በሌላ የግንባር መረጃ የብልፅግናው 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር የሻለቃ አመራሩ ከነ ሙሉ ትጥቁና የሬዲዮ መገናኛ በመያዝ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን በይፋ ተቀላቀለ።
ለመውደቅ እየተንገዳገደ ላለ አንባገነን ስርዓት ከንቱ የህይዎት ዋጋ አልከፍልም፣የህዝቤንም መከራ ከዚሕ በላይ ማየት አልፈልግም፣የአማራን ህዝብ ከዚሕ በላይም አልበድልም በማለት የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦርን የተቀላቀለው የሻለቃዋ አመራር ከዛሬ ጀምሬ የበደልኩትን ህዝብ ከፋኖ ወንድሞቸ ጋር ተሰልፌ ውድ መስዋዕትነት ለመክፈል ቃል ገብቻለሁ በማለት የተናገረ ሲሆን በፋኖ አመራሮች ለተደረገለት ደማቅ አቀባበልም ምስጋናውን አቅርቧል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 29/2018ዓ.ም
ማያዚያ 29/2018 ዓ.ም
ደቡብ ጎንደር የቀጠለ የድል ዜና‼️
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ባለፉት 24 ሠዓታት ከስማዳ እስከ ወለላ በሀር ባደረጉት ትንቅንቅ ተጨማሪ ድል ተገኝቷል። በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች ተገድ*ለዋል፣ ተማርክዋል።
የጠላት ሃይል አንድ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ በተደመሰሰበት በዚህ ውጊያ ከተገደሉት መካከል:-
🔹ሃምሳ አለቃ ተክሌ የተባላ ሻለቃ መሪ፣
🔹መቶ አለቃ ጌታሁን ተስፋዬ የተባለ ሻንበል መሪ፣
🔹አምሳ አለቃ አፓሳ የተባላ ሻንበል መሪ
🔹እና አምሳ አለቃ ቡፊያ የተባለ ዲሽቃ ተኳሽ ይገኙበታል።
ከ17 ሰዓታት በላይ በወሰደው በዚህ አውደ ውጊያ ዲሽቃ፣ ብሬን፣ ስናይፐር፣ ክላሽ ኮቭ፣ በርካታ ተተኳሽ እና ወታደራዊ ቁሳቁስ መማረክ ተችሏል። በዚህም መሰረት:-
➜ 106 ክላሽ ንኮቭ
➨ 4 ብሬን
➨ 2 ስናይፐር
➨ 1 ባለክሻፋ ዲሽቃ ከናሸንሸሉ
➨1 ፖትሮል ተተኳሽ
➨ 2 መኪና ወታደራዊ ቁሳቁስ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ተማርከዋል።
🔸ሃምሳ አለቃ በቀለ ዘለቀ፣
🔸ሃምሳ አለቃ ወንድወሰን ሀብታሙ፣
🔸ሃምሳ አለቃ ከማል ከድር የተባሉ ወታደራዊ መኮንኖችን ጨምሮ 83 የመከላከያ አባላት ተማርከዋል።
ይቀጥላል...
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለ ጦር ታቦር ተራራ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቁ::
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 47ኛ ክፍለ ጦር ታቦር ተራራ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን ምልምል ፋኖዎች በማስመረቅ ለህልውና ትግሉ አስፈላጊ ከሆነው አንዱና ዋነኛውን አደረጃጀትን በሰው ሃይል ማጠናከር ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ::
በዚህም ታቦር ተራራዎች የ47ኛ ክፍለ ጦር የ105ኛ ኮር እንዲሁም በየ ደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራዊት በተገኙበት ምልምል ሰልጣኝ ፋኖዎችን በደማቅ ሁኔታ ያስመረቁ ሲሆን ከፍተኛ አመራሮችም የእንኳን ደስ አላችሁ በማለት የተጣለባቸውን ብሔራዊ ሃላፊነት በታማኝነትና በቁርጠኝነት እንዲወጡ መልክት አስተላልፈዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም
+2
በጃማ ወረዳ አህያ ፈጅ ቀጠና ከተለያዬ ተቋማት ከተወጣጡ የመንግስት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቃቄ ባስቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፣ ህልውናውም ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል በምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ከሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከተውጣጡ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።
ትናንት ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም በተካሔደው መድረክ የጃማ ወረዳ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች ጋር ውጤታማ ውይይት መደረጉን ነው የ33ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ያስታወቀው።
ለውይይት በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ከተሰብሳቢዎቹ ተነስተዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች መድረኩን በመሩት የ33ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
ምንጭ፦በአፋብ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ 33ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!
በዘመቻ ሰማዕታቶቹ፦
✅አርበኛ ፍቃዴ አለባቸው፣
✅አርበኛ አበበ አንለይ እና
✅አርበኛ አንደበት ክንድዓለም ሥም ከጠዋቱ 02:00 11:45 ለተከታታይ 08 ሠዓታት በተደረገ የቅንጅት አውደ ውጊያ ደማቅ ድል ተመዝግቧል❗
[ሚያዝያ 28/2018ዓ.ም]
አፋብን፦
✅ሰሜን ዓምሐራ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር/ጉና ክ/ጦር እና
✅ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር/ 👉አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር እና
👉ጀነራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክ/ጦር የጋራ አውደ ውጊያ አድርገዋል።
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ሬሽን ለመቀባበል ከራሥ ጋይንቱ ነፋሥ መውጫ እና ከሥማዳው ወገዳ ከተማ ተነሥቶ ከራሥ ጋይንቱ ''ወለላ ባሕር'' ከተማ ሬሽን ከተቀያዬሩ በኋላ ከራሥ ጋይንት የመጣው ሬሽኑን አቀብሎ ወደ ራሥ ጋይንት ሲመለሥና ከሥማዳ የመጣው ሬሽኑን ተቀብሎ ወደ ሥማዳ ለመመለሥ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ከሁለቱም ኮሮች ከየአቅጣጫው ፈጣን የሆነ ማጥቃት ተደርጎበታል። በዚህ ውጊያ ወደ ሥማዳ በመመለሥ ላይ የነበረውን የጠላት ኃይል፦
✅የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ ከአጎና እሥከ ሐረር፣ ከደገዛ እሥከ ደብረ ሲና፣ እና ከወለላ ባሕር እሥከ ባዝራ መገንጠያ የአገዛዙን አራዊት ሰራዊት ሲያሳድዱት በሌላ አቅጣጫ ጠላት ለሆድ ዘመዱ ለመድረሥ ከሥማዳ ወገዳ በኩል ወደ አጎና ሲመጣ የነበረውን የጠላት ኃይል ''ሐገረ ቢዘን ብርጌድ'' ሸረፍ ጎዴና አሥፋ ሜዳ ላይ ጠላትን አምበርክከውታል፤ የተረፈውንም ወደ ወገዳ ከተማ ፈርጥጦ እንዲገባ አድርገውታል።
✅በ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር፦
👉ሥር ያለው የሰማዕቱ አርበኛ አንደበት ክንድዓለም ክፍለ ጦር(አንበሳው ጋይንት ክ/ጦር) ደግሞ ከወለላ ባሕር ጀምሮ እሥከ ሳሊ፣ ማዶዬ፣ ጥርጥራ፣ መገንጠያ እና ውኋ ምድር ድረሥ ከፍተኛ ድልን ያሥገኙ አውደ ውጊያዎችን ሲያከናውኑ
👉ጀነራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክ/ጦር በወገዳ ከተማ ዙሪያ አውደ ውጊያ አድርገዋል።
የአንበሳው ጋይንት የምርኮ ቁጥራዊ መረጃዎች በ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ሕ/ግ ዘርፍ በኩል የሚቀርብ ይሆናል።
በጉና ክ/ጦር የተገኙ ዕንቁ ድሎች ለጊዜው የተሰበሰቡ(ሙሉው ቁጥራዊ መረጃ እንደደረሰ የምናቀርብ ይሆናል)፦
01.እሥቴ ዴንሳ ብርጌዴ፦
✅ 50 ክላሽንኮቭ
✅02 ብሬን
✅02 ሥናይፐር
✅01 ዲሽቃ ባለ መነጽር(ክሻፋ) ከነ ሸንሸሉ
✅01 FSR ሙሉ ተተኳሽ
✅01 ፓትሮል እሥከ ተተኳሹ
✅40+ ምርኮኛ መከላከያ
✅30 ቁሥለኛ
✅01 ሬጅመንት የተደመሰሰ(ሙት) ቁጥሩ ያልታወቀ
👉የሬጅመንት ዘመቻ መሪ የተደመሰሰበት
👉ዲሽቃ ተኳሽ(ሐምሣ አለቃ) የተደመሰሰበት
👉ሻምበል መሪ(ሐምሣ አለቃ) የተደመሰሰበት
02. ሐገረ ቢዘን ብርጌድ
✅01 ብሬን
✅22 AK-47 ክላሽንኮቭ
✅21 ምርኮኛ መከላከያ
✅ወታደራዊ ሎጅስቲክና ቁሳቁስ መጠናቸው ያልታወቀ
✅ቁጥሩ ያልታወቀ የተደመሰሰ
በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት የታጨደበት፣ የተወቃበት፣ በሚገባው ቋንቋ የተነገረበት፣ የዓምሐራ ፋኖ የአሸናፊነት ሥነልቦናን ተላብሶ ምርኮ በምርኮ የሆነበትና አራዊት ሰራዊቱ ቁሥና አካላዊ ኪሳራን የተከናነበበት አኩሪ ድል ሲሆን የድሉን መታሰቢያም ለሰማዕታቶቹ አንደበት ክንዳለም፣ ፍቃዴ አለባቸውና አበበ አንለይ ተደርጓል።
ክብርና ሞገሥ ለትግሉ ሰማዕታት❗
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊✊
አፋብን ሰሜን ዓምሐራ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው
በጌምድር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
ቋሚ ምሥል፦ በሥማቸው ዘመቻ የተደረገላቸው ሰማዕታት ዓምሐሮች
በየቀኑ በጠናከረ መንገድ ስቦ የማስከዳት ስራው ቀጥሏል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
.....ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም
በዛሬው እለትም አራት የመከላከያ አባላት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው 201ኛ ኮር 54 እና 74 ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
1.አብርሀም በየነ ....መከላከያ ከ25ክ/ጦር 54ኛክ/ጦርን የተቀላቀለ
2.ንሮዝማን ናስር...መከላከያ ከ25ክ/ጦር 54ኛክ/ጦርን የተቀላቀሉ
3.አብርሀም አለሙ...መከላከያወደ 74ኛክ/ጦር የተቀላቀሉ
4.ደጀኔ ብርሀኑ.....መከላከያወደ 74ኛ ክ/ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በሦስት አቅጣጫ የመጣው የብልፅግና ጦር በሦስቱም አቅጣጫ ተመትቶ ሽንፈቱን ተከናንቦ ተመለሰ!
ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 30ኛ ክፍለ ጦር በሦስት አቅጣጫ የመጣውን የብርሐኑ ጁላ ግብስብስ ሠራዊት በመጣበት ሁሉም አቅጣጫ ገርፈው ክንደ ነበልባሎቹ አሳፍረው መልሰውታል።
ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ጠላት በሜካናይዝድ ማለትም በአየር መቃወሚያ (ዙ-23)፣ ሞርተር፣ ድሽቃና በሌሎች የቡድን መሳሪያዎች ታግዞ ለሙሉ ቀን በቀጠለው አውደ ውጊያ በአሞራ በር አቅጣጫ፣ በአርባዕቱ እንስሳ አቅጣጫና በትኩርዛ ኪዳነ ምህረት አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ጦር በመጣበት ገትረው በመያዝና በመልሶ ማጥቃት ጠላትን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወደ መጣበት አፍሮ ወደ መደበቂያ ጉድጓዱ እንዲመለስ አድርገውታል።
በዚህ ለሙሉ ቀን በቀጠለው አውደ ውጊያ 27 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ 34ቱን በማቁሰልና 15 የደረትና የወገብ ትጥቅ እንዲሁም በርካታ ደረቅ ሬሽን በመማረክ አመርቂ ድል አስመዝግበዋል።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ:- 28/2018 ዓ/ም
ሰበር የግድያ መረጃ!
በደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ይወደድ የነበረው ወጣት ሐይሌ ያለው በአረመኔው ሰራዊት አባላት ከምሽቱ 2:15 በመኗሪያ ቤቱ መገደሉ ተረጋግጧል።
ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም
=======================================
እንደወትሮው ቁኑን በስራ አሳልፎ ማምሻውን ወደ ቤቱ የተመለሰው የደብረ ማርቆስ ከተማ ተወላጅ የሆነውን ወጣት ኃይሌ ያለውን ተከታትለው መኗሪያ ቤቱ በመግባት የአረመኔው ሰራዊት አባላት በግፍ እረሽነውት ወጠዋል።
የጠላት ጥይት በሰውነቱ ከማረፉ በፊት 5 የሚደርሱ ወታደሮች ገንዘብ እንዲሰጣቸው አፈሙዝ ደቅነው እያስፈራሩ ቢጠይቁትም ወጣት ኃይሌ ያለው የተጠየቀውን ገንዘብ መክፈል ባለመቻሉ በአሰቃቂ ሁኔታ በደብረ ማርቆስ ከተማ ፍቅር ተራ ተብሎ ከሚጠራው ሰፈር በሚገኘው መኗሪያ ቤቱ ተገድሏል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት
+2
ልማደኞቹ የ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር እና 1ኛ ውባንተ አባተ ኮር በጥምረት ተዓምር ሰርተዋል።
ደቡብ ጎንደር ላይ ሊያንሰራራ የሞከረው ጠላት ወገቡ ተሰብሯል፤ የሻለቃ አንደበት ክንዳለም ወንድሞች ምድሩን በጠላት አስከ*ሬን በመሙላት እና የጠላትን ሎጅስቲክስ ሙሉ በሙሉ በመረከብ የወንድማቸዉን ደም መልሰዋል።
ዝርዝሩ ተሟልቶ ይቀርባል...
የተሸነፈው የአብይ አህመዱ የብልፅግና አገዛዝ ወደ ከተሞች ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ የንፁሃንን ህይወት ቀጠፈ::
ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር እና 104ኛኮር በቅንጅት የአብይ አህመድ ተላላኪ ብአዴን ብልፅግና በመርሳ ከተማ የስርዐቱን ዕድሜ ለማራዘም ምርጫ በሚል ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ሁለት መድረኮችን አዘጋጂቶ ፣ሀሳቡን ሳያሳካ ከሁለቱ ኮሮች በተውጣጡ የቃኝ አህዶች ስብሰባውን ሙሉ ለሙሉ በመበተን ፣የስርዐቱን ካድሬዎች ሀሳብ ቅዠት በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
በአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ታጂበው ህዝባችንን ለማደናገር መርሳ ከተማ ላይ መድረክ አዘጋጂቶ ፣መድረኩን በፖለቲካ ሊህቃን ሳይሆን በስርዐቱ ኮለኔሎች ስለቀጣይ ፣ምርጫ ብለው ለሚያስቡትና የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ተጨማሪ የጭፍጨፋ ጊዜን ህጋዊ ቅቡልነት ለማገኘት የከተማውን ህዝብ በሁለት መድረክ ለመሰብሰብ ያሳበው ጨፍጫፊው ስርዐት ከ101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለጦር እና ከ104ኛ 24ኛ ክፍለጦር ፣ በተውጣጡ የቃኝ አህዶች ስብሰባውን ሙሉ ለሙሉ መበትን ሲችሉና ስብሰባውን ሲመሩት የነበሩት የስርዐቱ ካድሬዎችና ኮለኔሎች በተከፈተባቸው ድንገተኛ ተኩስ ያሰቡትን የጥፋት አጀንዳ ሳያሳኩ ወደ ሀራ መስመር በሚወስደው ወደ ጃሮታ አቅጣጫ ፈርጥጠዋል።
ዛሬ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለጦርና ከ104ኛ ኮር 24 ክፍለጦር በተውጣጡ የቃኝ አህዶች በተጠና እና ኢላማውን በጠበቀ የከተማ ሰርጂካል ኦፕሬሸን ስርዐቱ መርሳ ከተማ ከሚገኘው አዳራሽና በከተማው በ06 ቀበሌ መድሃኒዓለም አካባቢ በሚገኝ የቀበሌ ቢሮ ሊያደርገው ያሰበውን ፕሮፖጋንዳ ሳያሳካ ሀሳቡ ቅዠት የሆነበት የብልፅግናው ስብሰብ፣የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ቀዳሚ አጀንዳው ስለሆነ ሀይቅ ላይ ያጠመደውን ጀኔራል መድፍ ወደ መርሳ ከተማ በዘፈቀደ በማስወንጨፍ አራት /4/ የንፁሀን ቤቶችን ሲያቃጥልና ሲያወድም ፣ሁለት ንፁሀንን በመግደል አንድ ከባድ ቁስለኛ አድርጓል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 28 / 2018 ዓ.ም
