ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 615
المشتركون
+1324 ساعات
+4187 أيام
+1 05630 أيام
أرشيف المشاركات
የደጋው መብረቅ ኮር በአንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር በመቄት ወረዳ በሁለት ግምባር የብልፅግና ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ድል ተጎናፅፈዋል:: አንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር ከሲሲጊ እስከ መቅረጫ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ሰዓት ላይ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ የፋሽስቱን ሰራዊት 360° ከበባ ውስጥ አስገብተው ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሰውበታል፤ውሀ ውሀ እስኪል ድረስ ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል ተጎናፅፈዋል:: በሁለቱም ግምባር ላይ የክፍለ ጦሩ ግስላ ፋኖዎች ጥላት ከመሸገበት ጉሬ ድረስ ዘልቀው በመግባት የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ከአስራ ሰባት (17) በላይ እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆኑ፤ በውል ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ በመኪና ጭኖ ወደ ፍላቂት  ሆስፒታል ሲያጉዝ አምሽቷል። በተጋድሎው 15 ክላሽ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል:: የብርሀኑ ጁላ መልክተኞችም ጨለማን ተገን በማድረግ ሙትና ቁስለኛ ሰራዊታቸውን ወደ ፍላቂት ከተማ ሲያመላልሱ ማምሸታቸውን ከአባባቢው ማህበረሰብ የተገኘ መረጃ ጭምር የታወቀ ሲሆን በሌላ መልኩ ፍላቂት ላይ ተወሽቆ የድሀን ልጅ እየላከ እሳት አረር ላንቃ ላይ የሚወረውረው የጁላው ኮሎኔል ለበላይ ጋግስተር አለቆቹ ደውሎ "ድረሱል አስበላችሁኝ! በፋኖ ተከብቢያለሁ"ቢልም ዙር ግጠም የጥላት በሮች ተከርችመው ተገርፏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል የካቲት 26/2018 ዓ.ም

በዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ (አባ ደርምስ)       ገደብየ ከተማ የነበረ ጠላት ተመታ!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው  የግዙፋ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  አሀድ የሆኑት ይታየሁ እና ምስጋናው አጣኔ  ብርጌድ  አባላት በጥምረት  የካቲት 25/2018 ዓ/ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ  እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት  ድረስ  በገደብየ ከተማ ዙሪያ ዳራ በተባለ ቦታ  ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ  በማድረግ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል ። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በዘመቻ አርበኛ ማንዴላ እያዩ ስም እየተደረገ ባለው ዘመቻ  ንቁ  ተሳትፎ በማድረግ ጠላትን በመደምሰስና በመማረከ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል  ። የሁለቱ ብርጌድ ጀግኖቻችን ዛሬ በወሰዱት ኦፕሬሽን በደጎማ ከተማ ለተሰውብን አርበኛ ደመላሽ ስመኝ እና ሌሎች አርበኞች መሰዋትነት  የበቀል እር፣ምጃ  ነው ሲሉ  ጠላትን በማደን የሚታወቀው ጎንደሬ በጋሻው  ክፍለ ጦር  ሳይውል ሳያድር  ደም መላሽነቱንም አረጋግጧል  ። በተደረገው አውደ ውጊያ በጠላት በኩል 7  በሞት የ*ተ*ደ*መ*ሰ*ሰ ሲሆን  በርካታ ቁስለኛን ደግሞ ወደ ዳባት ሆስፒታል አስገብቷል። በጀግኞች እጅ  በምርኮ  2 ክላሽንኮቭ መሳሪያ  400 የክላሽ ተቸኳሽ 2 ቦንብ 2 የወገብ  ትጥቅ  ገቢ ሁኗል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የአገዛዙን ስልጣን ለማስቀጠል እየሰሩ  ያሉ ተላላኪ ባንዳዎችን አንገት እና እጅ  መቁረጡን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን መሰዋት የሆኑ  የጀግኖቻችን አላማ ግቡን ይመታል ።      አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!! አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ            የካቲት 26/2018 ዓ/ም

የኢራን ሚሳኢሎች ብዙ ነገር ለውጠዋል። በሚሳኢሎቹ ምክንያት ኢማራት የአየር ክልሏን በመዝጋቷ የአማራ ህዝብ ላይ የድሮን ቦንብ ለሚያዘንቡ ወታደሮቿ ከዱባይ እና ከአቡዳቢ ደብረ ዘይት እና ባህር ዳር ድረስ በአውሮፕላን የሚመጡ ትኩስ ምግቦች በግዜው መድረስ አልቻሉም። ጀነራል ሐሰንን ጨምሮ የኢማራት ድሮን ተኳሾች እና ቴክኒሻኖች ለሰሞኑ የኢትዮጵያን ምግብ መልመድ ግድ ሊሆንባቸው ነው። ወደ ገራህ ቆፍር እንደሚባለው ወደ ቀናው የሚጓዘው የአብይ አህመድ ወራሪ ጦር ለሳምንታት ተጉዞ ከተከማቸበት የትግራይ እና የአማራ ክልል ድንበር አካባቢ በከፊል ተቀንሶ ወደ መሃል አገር ጉዞ ጀምሯል። በነገራችን ላይ አብይ ወደ ቆቦ፣ ሰቆጣ፣ ወደ ደባርቅ ኃይል ያጠራቀመው ሰሜኖች ከበው ሊያጠፉኝ ስለሆነ መከላከል አለብኝ ብሎ እንጅ አቅዶ ያደረገው ስምሪት አይደለም። በዛው አጋጣሚም እያስፈራራ ሽምግልና ሊቀመጥ ነበር ሰሚ ጠፋ። አሁን ከምርኮ የተረፈውን ሰራዊቱን እያንከራተተው ነው። ሰውዬው ሀገር እና ኮሪደር፣ ሰራዊት እና አራዊት ተምታቶበታል። አሰብም ወደ ሃሳብ ተለውጧል፤ የቀይ ባህር ምኞትም እንደ ጉም ተኗል። ጌታቸው ረዳ፣ ደመቀ ዘውዱ፣ ሜላት ኃይሉ እና አገኘው ተሻገር የተባሉ አገልጋዮቹን በአንድ መዝገብ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ ያገናኘው አብይ አህመድን አምኖ የሚከተል ሁሉ እጣ ፋንታው መክሸፍ ብቻ ነው። አስርስ ማር

ያልተነገረለት ጀግና የክብር መንገድ ከአጣዬ ሰማይ ስር እስከ ደመላሽ ሻለቃ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ፋይናስ ኃላፊው አርበኛ ከበደ ሀብቴ ​የአጣዬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኘው የዋርካ ዛፍ ጥላ ለብዙዎች እረፍት ነበር። ለሱ ግን የሀሳብ ማዕበል መናገሻ ሆነ። በክፍል ውስጥ መምህሩ ስለ ታሪክ ሲያስተምር፣ የእሱ አእምሮ የሚመላለሰው በአሁኑ ጊዜ እየተፈጠረ ባለው መሪር እውነት ላይ ነበር። በየቀኑ የሚሰማው የንጹሃን እምባ፣ በአጣዬ አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚታየው የጭስ ዳመና እና ከወለጋ የሚመጣው የጭካኔ ዜና ደሙን ያፈላልገው ጀመር። ​ደብተሬ ላይ ታሪክ ከመጻፍ ይልቅ፣ በታሪኩ ውስጥ ታሪክ ሆኜ መገኘት አለብኝ የሚል ጽኑ እምነት በውስጡ በቀለ። የጁንታው ሴራና በየቦታው የሚታየው ግፍ የአባቶቹን የጀግንነት ታሪክ እንዲያስታውስ አስገደደው። አረበኛ ከበደ ራስን የመከላከልና የህልውና ጥያቄ ከትምህርት ጥራት በላይ ሆኖ አገኘው። ​አንድ ቀን ጎህ ሳይቀድ የትምህርት ቦርሳውን አውርዶ የመታገያ ስንቁን አዘጋጀ። ቤተሰብ፣ ትምህርትና የወጣትነት ምቾት በዚያች ሌሊት ተሸኙ። ወደ ጫካው ሲገባ መድረሻው የነጻነትና የፍትህ አደባባይ እንደሆነ ያውቅ ነበር። ​በመጀመሪያዎቹ የትግል ቀናት እንደ ማንኛውም አዲስ ታጋይ ከታች ጀምሮ ራሱን አዘጋጀ። ቅሬታ አያውቅም፤ ድካም አይበግረውም። የተሰጠው ግዳጅ ምንም ይሁን ምን በዝናብ ወይም በበረሃ ሐሩር በጥቁር ዓለት ላይ እንደተቀረጸ ጽኑ ቃል በታማኝነት መወጣት ጀመረ። በጓደኞቹ ዘንድ የማይበገረው የዲሲፕሊን አምድ የተባለለት ከበደ የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የደመላሽ ሻለቃ ምክትል​ አልፎም ዋና መሪ ጊዜውን በፈተና አሳልፎ እየሰራ የሚገኝ ታታሪው ጀግና አርበኛ ከበደ ሀብቴ። እስናይፕር ተኳሹ አርበኛ ከበደ ሀብቴ የትግሉ ሜዳ ጀግናን ከፈሪ፣ ታማኝን ከከዳተኛ የሚለይበት ወንፊት ሆነ። እሱ ግን በውጊያ መካከል የሚያሳየው መረጋጋትና ስልታዊ ብልህነት በከፍተኛ አመራሮች ዘንድ አመኔታን አተረፈለት። ​ያ የአጣዬው ተማሪ አሁን የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የፋይናንስ ኃላፊ ዋልታ ሆኗል። የደመላሽ ሻለቃን በምክትል እና ዋና መሪነትን እንዲመራ ሲታዘዝ፣ በትከሻው ላይ የወደቀው የኃላፊነት ክብደት አልከበደውም። ይልቁንም፣ የሚመራቸው ታጋዮች ደህንነትና የሚጠበቅባቸው ድል የዕለት ተዕለት ስንቁ ሆነ። ደመላሽ የሚለው ስም ዝም ብሎ ስያሜ ሳይሆን፣ ለተበደለው ህዝብ የፍትህ አምሳያ እንዲሆን ያደረገ። የቁርጠኝነት ዋጋ ​ዛሬ ጀግናው አርበኛ ከበደ ሀብቴ በታሪክ መዝገብ ውስጥ ስሙን በደመቀ ቀለም እየጻፈ ይገኛል። ከክፍል ውስጥ ትምህርቱን አቋርጦ የወጣው ወጣት፣ ዛሬ በሜዳው ላይ ለሺዎች ተስፋ ሆኗል። ትግሉ ገና ቢሆንም፣ የእሱ ጽናት ግን ለአማራ ህዝብ ህልውና የተከፈለ ትልቅ መስዋዕትነት ሆኖ ይቀጥላል.....! ​ ​

👉የአማራ ብሔርተኝነት ከአምላክ ቀጥሎ ብቸኛው መዳኛችን ነው🔥 👉የአማራ ብሔርተኝነት የህልውናችን መቀጠል ብቸኛው ዋስትናችን ነው🔥 👉አማራው መጠቃት የጀመረው አማራዊ ብሔርተኝነቱን ያላላ ቅፅበት ነው🔥 👉አማራዊ ብሔርተኝነታችን አምላክ የሰጠን መሰባሰቢያችን፣የጥቃት መመከቻችን፣የህልውናችን መሰረት የዘላለዊ ጌጣችን ነው🔥 👉የአሁኑ ፋኖ ትግል መገፋት ወልዶት በአማራ ብሔርተኝነት የሚመራ የህልውና ተጋድሎ ነው🔥 👉የአማራ ብሔርተኝነት ትግል ሲከፋን የምንይዘው ሲደላን የምንተወው ሳይሆን ከማንነታችን ጋር ከአምላክ የተሰጠን ፀጋ ነው🔥 👉 አማራውያን በየመክሊታችን ለምንከፍለው ዋጋ ሁሉ መልሱን በቅርብ የምናየው፣ እንዲሁም ትሩፋቱ ለቀጣይ የአማራ ትውልድ የሚተርፍ ይሆናል🔥 👉የአማራ አንገቱ አንድ ነው🔥 በአለም ታሪክ በተለያየ ዘመናት በርካታ ሃገራት እና ህዝቦች እራሳቸውን እና ሃገራቸውን ከጠላቶቻቸው የተከላከሉት ብሔራዊ ህብረታቸውን እና ብሔርተኝነታቸውን ተጠቅመው መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው። እንደ ምሳሌ በሃገረ እስራኤል አስራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች ከሦስቱ ብሔራዊ ሃይማኖቶቻቸው ጋር በጠንካራ አንድነት ጠርንፎ ያቆማቸው፣ ከመጥፋት ያዳናቸው፣ ከእልቆመሳፍርት ጠላቶቻቸው ጠብቆ ያቆያቸው፣ እንዲሁም ከ2500 አመታት ስደት ጀምሮ እስከ የ1948ቱ የአገረ እስራኤል ዳግም ምስረታ ድረስ ያሉትን የስደት፣ የመከራ እና የጭለማ አመታት ፅናት እና አንድነት ለግሷቸው፣ ከህልውና ጥፋት ተከላክሎ ለዚህ አለማቀፋዊ ስኬት ያበቃቸው የእስራኤላውያን ብሔርተኝነት ወይም ፅዮናዊነት(Zionism) ይባላል። አማራም ከእስራኤል ብሔርተኝነት ባልተናነሰ መልኩ ጠንካራ ብሔርተኝነት ለበርካታ ሺህ ዘመናት ገንብቶ ኖሯል። ለዚህም ነው አማራው ማንነቱን ጠብቆ ልጆቹን ሰባት ቤት እየቆጠረ፣ ለአማራ(ለጨዋ) እየዳረ ደማዊ አማራ ማንነቱን ሃይማኖቱን(ሁሉን ምሃይማኖቶች) ታሪኩን እና እሴቲን ጠብቆ ለሚቀጥሉት ትውልዶች የሚያስረክበው። እነሆ ይህ ወርቃማ ማንነት ነው፣ በተድላም በክፉ ቀንም አልፎ በቅብብሎሽ እኛ ትውልድ ጋር የደረሰው። ሆኖም አማራ ላይ በደረሰው እጅግ ከባድ የሃገር ውስጥና የውጭ ጠላቶች ርብርብ ይህ ወርቃማ ማንነት ላለፉት ሰባ እና ስልሳ አመታት በተወሰነ መጠን ተመቶ ተዳክሞ ሰገባ ውስጥ ገብቶ ነበር። የዚህ ትውልድ አማራ ይህን ከሰገባው የገባውን ብሔርተኝነት አሁን አውጥቶ ለህልውናው አደጋ መድህን አድርጎታል። ጠላቶቹን በሙሉ አበራይቶም ህልውናውንም በብቃት ይጠብቃል። ህልውናችንን ካስጠበቅን በኋላ የእኛው አለአዋቂ ምሁራን ተብየዎች እንደሚደሰኩሩት፣ ብሔርተኝነቱን እንተዋለን ማለት ግን በፍፁም አይደለም። እኛ አማራዎች ከንግዲህ በኋላ ብሔርተኝነታችን የኑሮ ዘይቤያችን፣ ጌጣችን፣ መከበሪያችን፣ መሰባበቢያችን፣እና መጠናከሪያችን ሆኖ ከአማራ ነገድ ጋር አብሮ ይቀጥላል። ይህ ሲሆን ብቻ ነው አማራውም ሆነ ኢትዮጵያ በዘላቂነት ለህልውናቸው ዋስትና የሚያገኘት። ባለፉት ዘመናት የሰራናቸውን ስህተት ማለትም በዘመነ መሳፍንት ወቅት እንደነበረው አካባቢያዊነት፣ በ1960ዎቹ ወቅት እንደነበረው የተማሪ ፖለቲከኞች የድንቁርና ተግባር እና የነሱ ርዝራዥ ከሆኑት ያሁኖቹ ብአዴናዊ ልሂቃን ከሃሳዊ-ኢትዮጲያኒስቶች ጋር አብ'ረው አማራን የማዳከም ስራ እና የመሳሰሉትን ስህተት ዳግም መፈፀም፣ አማራው ልክ እንደ ጋፋት ህዝብ ታሪክ ሆኖ መቅረት ብቻ ነው ትርፉ። ከንግዲህ የአማራው ጠላቶች ማለትም:- የውጭና የውስጥ ታሪካዊ ጠላቶች፣ ሃሳዊ ኢትዮጵያኒስቶች፣ በዚህ የህልውናን የማስከበር ትግል ጉዳይ መንጫጫታቸው አይቀርም። ግን የአማራን ብሔርተኝነት ትግል የማክሰም ሴራቸው አይሳካም። የአማራው አባቶች አገር ሰርተው፣ መንግስት አቁመው የሃገር ድንበርና ባንዲራ ተክለው ባቆዩን አገር መጤዎች ከመሸ መጥተው በደምና አጥንት የተሰራችውን አገር እንደ ገል ሰባብረው ተከፋፍለው አማራውን እንደ ኩርድ ህዝብ አገር አልባ ለማድረግ የውስጥ ባንዳዎች ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብረው ስራ ከጀመሩ እነሆ ከሁለተኛው የጣልያን ወረራ ጀምሮ ሰማንያ አመታትን ደፍነዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አማራው በልበሰፊነት አገሩ እንዳትፈርስ ሁሉን ችሎ እየሞተም እየተሰደደም ቢያንስ የውስጥ የቅናት ፖለታካ አራማጅ ባንዳዎች ልብ ይገዛሉ በሚል ያን ሁሉ መከራ በትእግስት አሳልፏል። አሁን ግን የጠላት ጥቃት ተባብሶ የአማራውን የመኖር ህልውና ስለተፈታተነ እና ትግሉ ወደ ህልውና ትግል ስለተቀየረ አማራው ተወት አርጎት የነበረውን የአማራ ብሔርተኝነት ትግል እንደአዲስ አቀጣጥሎታል። አዲሱ የአማራ የብሔርተኝነት አብዮት ለየት የሚያደርገው ከሃይማኖት እና ጎጥ ነፃ የሆነና ከዘመኑ ጋር የዘመነ ሲሆን አማራነትን ብቻ ርዕዮት ያደረገ፣ ያደገ እንቅስቃሴ ነው። በፍራማውሮ የመካከለኛው ዘመን የአለም ካርታ በግልፅ እንደሚታየው፣ በ1400 ዓም ገደማ ከነበረው በራራ-አዲስአበባን ማዕከል ካደረገው የዐዔ ዳዊት ቀዳማዊ(1382-1413) የአማራ መንግስት ዘመን ከነበረውም የአማራ ብሔርተኝነትም የሚመጣጠን ሆኗል። የዐፄ ዳዊት ቀዳማዊ አስራሶስተኛ ትውልድ ልጅ የሆነው ዐፄ ዳዊት ዳግማዊ(ልብነ ድንግል 1507-1540) በግራኝ እና ኦሮሞ ወረራ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር "ወደ አባቶቻችን አማራ ነገስታት መነሻ እንሄዳለን፣እሷን እየጠበቅን በአማራ ደጅ እንሞታለን።" በዘመነ መሳፍንት ዘመን የነበሩት የአማራ አከባቢያዊ መሳፍንት የሰሩትን "አማራን ፍፁም አንድ ማድረግ አልመቻል" ስህተት ታርሞ አማራን ወደ ፍፁማዊ አንድነቱ እየተመለሰም ይገኛል። የዘመነመሳፍንቱ ቆሻሻ ጎጣዊ መጠሪያ ማለትም ጎጃሜነት፣ወሎዬነት፣ሸዋዬነት፣ጎንደሬነት ተደምስሶ በፍፁም አማራዊ አንድነት ወደ ቀደመ ክብሩ ማለትም "አማራነት" ከፍ ብሏል።

64ኛ ክፍለጦር አንድ ስናይፐርን ጨምሮ 11 ክላሽንኮቭ መሣሪያ በመማረክ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት መወጣቱን አስታወቀ! በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር በጃዊ ግንባር የካቲት 23/2018 ዓ/ም የጠላት አከርካሪን በመስበር የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት መወጣቱን ክፍለጦሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። በምዕራብ አማራ ጃዊ ቀጠና ድርጅቱ የሰጠውን ተልዕኮ በልዩ ብቃትና ጀግንነት የፈፀመው 64ኛ ክፍለጦር፡ የጠላትን አከርካሪን በመስበር አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅቷል። በግዳጁ በ206፣ 105 እና  201ኛ ኮሮች ስር ከሚገኙ ክፍለጦሮች ጋር በመቀናጀት መብረቃዊ ጥቃት የፈፀመው 64ኛ ክ/ጦር፡ አንድ ስናይፐርን ጨምሮ 11 ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከጠላት ማርኮ ታጥቋል። በተጨማሪም፡ ስድስት የእጅ ቦምብ፣ ሰባት ካዘና፣ 1ሺ የክላሽ ተተኳሽ፣ አንድ የራዲዮ መገናኛ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርኮ መታጠቁን ክፍለ ጦሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል  በላከው መረጃ አስታውቋል።

አገዛዙ በድሮን የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ነው‼️ የካቲት 25/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ በጎጃም ጃዊ ቀጠና ቀዝቃዚት ቀበሌ ከተማዋ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን
+4
አገዛዙ በድሮን የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ነው‼️ የካቲት 25/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ በጎጃም ጃዊ ቀጠና ቀዝቃዚት ቀበሌ ከተማዋ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን መገደላቸው እና መቁሰላቸው ታዉቋል። የአካባቢው ማህበረሰብ የለት ከለት ኑሮውን ለማሸነፍ ለስራ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ምንም አይነት ተኩስ በሌለበትና የፋኖ አባላትም በአካባቢው በሌሉበት ሁኔታ ሆን ተብሎ የአማራን ህዝብ በጁምላ ኢላማ አድርጎ በድሮን እየጨፈጨፈ ይገኛል ሲል የ66ኛ ክ/ጦር አስታውቋል።😭 አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በአሁኑ ሰዓት በዳንግላ እና አካባቢው ድሮን እየቃኘ ይገኛል !
በአሁኑ ሰዓት በዳንግላ እና አካባቢው ድሮን እየቃኘ ይገኛል !

የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር ከጭምት ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ሕዝባዊ ውይይት አካሂዷል። የአማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል በተሳካ ሁኔታ ከግቡ ለማድረስና የ
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር ከጭምት ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ሕዝባዊ ውይይት አካሂዷል። የአማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል በተሳካ ሁኔታ ከግቡ ለማድረስና የሕዝባችንን ዘለቄታዊ ዋስትና ለማረጋገጥ የሕዝባችን ሁለንተናዊ ድጋፍ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። በዚህም የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የጎዛምን ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች ከጭምት ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ የአማራ ሕዝብ ትግል አሁናዊ ቁመና ምን እንደሚመስል፤ በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች፤ በፋኖና ሕዝብ መካከል ስላሉ የእርስ በእርስ መስተጋብሮችና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን የተመለከቱ ጉዳዮች ተዳሰዋል። ድል ለአማራ ፋኖ! የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

የምሽቱ ፀጥታ በገደላገደሉ ላይ በሚሰማው የቆቅ ጩኸትና አልፎ አልፎ በሚስተጋባው የተኩስ ድምፅ ይረበሻል። በደጋው ቅዝቃዜ ውስጥ የፋኖ አባላት በትንሽ የባትሪ ብርሃን ፍኖተ አማራ ሚዲያ የሚያስተላልፈውን ዜና ለማዳመጥ ተሰባስበዋል። መሬት ላይ ተቀምጠው፣ አቧራ የለበሰውን ዩኒፎርማቸውን እያራገፉ በትኩረት ያዳምጣሉ። ​ ለፋኖ ሚዲያ አባላትና ለመላው የአማራ ፋኖ ደጋፊዎች ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከግንባር ካለችበት ተጨባጭ መሬት ላይ ሆና ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ ለመሆን ሌት ተቀን እየባዘነች ነው። ነገር ግን አሁን ሰማዩ ጠቁሯል። የጠላት ወጥመድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዘርግቷል። አብይ አህመድ ከሰላሳ(300003 ሺህ በላይ የሳይበር ወታደሮችን አዝምቶ፣ በትግላችን መካከል የጥርጣሬና የክህደት ዘር ለመዝራት እየተጋ ነው። ​ሰሞኑን በትግሉ መሪዎች ላይ አላስፈላጊ ስም መስጠትና የስም ማጥፋት ዘመቻ ተጀምሯል። ይሁንና፣ መረዳት ያለብን ሀቅ አለ የትኛውንም ፋኖ በመሳደብ ወይም ስሙን በማጥፋት ትግሉን አንድ እርምጃ ወደ ፊት ማራመድ አይቻልም። ይልቁንም እኔ ካልመራሁት' በሚል እልህ መሪዎቻችንን ማጥቃት፣ ለጠላት መረጃ አሳልፎ እንደመስጠት ይቆጠራል። ​የተከበበችው አማራዊያን ​ዛሬ አማራ በአራት አቅጣጫ እንዲታረድ በጠላት ተፈርዶበታል። አጣዬ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ወለጋና ደራ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲጠቃለሉ የአረመኔው አገዛዝ መመሪያ አስተላልፏል። ምድሪቱ የደም እምባ እያለቀሰች ነው። ስለዚህ ወንድሞቻችን እህቶቻችን ድርጅታችንንና መሪዎቻችንን እንደ አይን ብሌናችን የምንጠብቅበት ሰዓት አሁን ነው። አንድነታችን ካልጠነከረ፣ ጠላት በከፈተው የክፍተት በር ገብቶ ይበላናል።"

#አስቸኳይ‼️ ምስራቅ ጎጃም #ማቻክል ወረዳ #አማኑኤልና አካባቢው የመሸገው የአብይና የቀንድ አውጣ ሰራዊት ከአመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የትራንስፖርት እቀባ አድርጎ ሰፋ ያለ ደፈጣ ይዟለ መረጃ
#አስቸኳይ‼️ ምስራቅ ጎጃም #ማቻክል ወረዳ #አማኑኤልና አካባቢው የመሸገው የአብይና የቀንድ አውጣ ሰራዊት ከአመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የትራንስፖርት እቀባ አድርጎ ሰፋ ያለ ደፈጣ ይዟለ መረጃው ለወገን ኃይል ይድረስ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል‼️ 25/ዐ6/2018 ዓ.ም

🔥የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ወልድያና መርሳ ዙሪያ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ‼️ የምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር እና 101ኛ ኮር አሃዶች በጥምረት ወልድያና መርሳ ዙሪያ ዛሬ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል:: የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ከወልድያ በመነሳት ወደ መርጦ ለማጥቃት አስቦ ቢንቀሳቀስም 101ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር በመርጦ ሚካኤል እና 35ኛ ክፍለ ጦር በቱላባ ማርያም እንዲሁም ከመርሳ በመነሳት ወደ ቡሆሮ ማጥቃት ያደረገውን ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር በጉባራ በመከላከልና መልሶ ማጥቃት በማድረግ አሃዶቹ በጥምረት ድል አስመዝግበዋል:: የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በምድር በከፍተኛ መካናይዝድ ድጋፍና በአየር ሃይል በድሮንና በጄት ታግዞ ፋኖን መዋጋት የለመደና ከዛ ውጭ ከመደምሰስና ከመማረክ ውጭ አማራጭ እንደሌለው የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው የወልድያና መርሳ ዙሪያ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ዳመናና ጉም በመሆኑ የተደረገበትን መልሶ ማጥቃት መቋቋም አቅቶት ተመልሶ ወደ ምሽጉ ገብቷል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 25/ዐ6/2018 ዓ.ም

ፅናት ክፍለ ጦር በሁለት ወረዳዎች ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገበ‼️ አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር የካቲት 25/2018 ዓ/ም በደላንታና አምባሰል ምድር ድል አድርገዋል! የፅሀይን ወጋገን መነሻ ተገን ተደርጎ እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት የዘለቀው ጥላትን ስቦ የማስገባት ቅጥቀጣ በደላንታ ወረዳ ተምበኮ ቀበሌና እና በአባሰል ምድር ዘሜት ቀበሌ ላይ ያለ ጥጋት ደራሽ የፋሽስቱ ሰራዊት ተቀጥቅጧል። በዚህ አውደ ዊጊያ ላይ በጥላት ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ከሞት እስከ አመራር ማቁሰል የደረሰ ሲሆን በዚህም መጠን በ19ኙ ብሬንና እስናይፐር ተኳሾቹን ጨምሮ ወደማይቀረው የድምሰሳ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ 23ቱን እና ሻምበል መሪውን ጨምሮ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል። ሞትን አነፍንፎ የመጣው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ከፋኖዎቹ በደረሰበት ቅጥቀጣ ወደኋላ በድበራ ነፍስ አውጭኝ ሲፈረጥጥ የንፅሀኖችንና የእንስሳቶችን ህይዎት ቀጥፏል። ከንፁሀን ቤት በመግባት የአንድ ቄስ ህይዎትን በአረመኒያዊ ተግባር ሲነጥቁ ከአምስት በላይ እንስሳቶችንም ጭምር ገድለዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል የካቲት 25/2018 ዓ.ም 25/ዐ6/2018 ዓ.ም