ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 011
المشتركون
+2324 ساعات
+367 أيام
+41430 أيام
أرشيف المشاركات
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ በ102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም ድል አስመዘገቡ::
በምርጫ ስም እራሱን ብቻ በእጩነትና በመራጭነት ያቀረበው የብልፅግና አገዛዝ ህዝብን በማስገደድና በማዋከብ የምርጫ ካርድ እንድወስዱ በቀዩ ጋሪያ፣ በተኩለሽና በጮቢ በር ለመሰብሰብ ሙከራ ቢያደርግም በጀግኖቹ ክንድ ተበትኗል።
በደም የጨቀየው ለሲቪሊያን ህይወት የማይጨነቀው ቆሞ ቀሩ የብልፅግና አገዛዝ አለም አቀፍ ህጎችን ሙሉ ለሙሉ በመጣስ የአማራ ክልል ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት በመፈፀም በግዳጅና በማስፈራራት የምርጫ ካርድ አውጥተው አንዲመርጡት በከፍተኛ እንእስቃሴ ላይ ይገኛል።
ግትርና ቆሞ ቀሩን አገዛዝ በውል የተረዱት የ12ኛ ክፍለጦር አሀዶች በጠላት ላይ የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ አካባቢውን የወገን ሀይል ተቆጣጥሮ ውሏል።
በመሆኑም ጠላት በጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም በ12ኛ ክፍለ ጦር የሚመሩት አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ቀጠናውን ለወገን ሃይል አስረክቦ ወጥቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 25/2018 ዓ/ም
21ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ልዩ ስፍራው አጣጎይ ከተባለ ቦታ ደፈጣ በመስራት ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 21ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ በአንጎት ወረዳ ከዥጣ ወንዝ እስከ አሁንተገኝ ከተማ መንገድን ግራና ቀኝ የጠላት ጦር በመወጠር ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ህዝብን ግዴታ ተመዝግባችሁ የምርጫ ካርድ አውጡ በማለት ገበያ የሚሄደውን ሰላማዊ ነዋሪ እና የግብረ ሰናይ ድርጅት እርዳታ ሊያደረግላቸው ጥሪ የተደረገላቸውን የ012 ቀበሌ ነዋሪዎች ሲያሰቃይ ውሏል።
ህዝብን ሲያንገላታ የዋለውን የብልፅግና ሰራዊት የ21ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ፋኖዎች ልዩ ስፍራው አጣጎይ በተባለ ቦታ ደፈጣ በመስራት ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ስድስት የስርዓቱ ጠባቂ ወታደር ሲደመሰሱ ሰባት የሚሆኑት ቆስለው በአንቡላንስ ተጭነው ወደ ህክምና የተወሰዱ ሲሆን ወጥሮ የነበረው ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ አሁንተገኝ ከተማ ተመልሷል በወገን በኩል ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰ መሆኑን የተከዜ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል።
ህልውናች በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 25/2018 ዓ/ም
ላስታ ወረዳ ወደ 025 ቀበሌ ድብኮና አከባቢው የሃሰት ምርጫ ለማካሄድ ካርድ ለመበተን የተንቀሳቀሰው የጁላ ሰራዊት ተቀጥቅጦ ተመለሰ!
ሚያዚያ:- 25/ 2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን /ወሎቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፍ አሳምነው ኮር የሚገኙት 19ኛ ክፍለጦርና 16ኛ ነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ በጋራ በሁለት አቅጣጫ የመጣውን የብርሃኑ ጁላን ሰራዊትአይቀጡት ቅጣት ቀጥተውታል።
ከላሊበላ ከተማ እና ከጋሸና ከተማ በከባድ መሳሪያ ታጅቦ ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ከጧቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ግለቱን የጠበቀ አውደ-ውጊያ የተካሄደ ሲሆን በተለይም ደግሞ ቆጋ፣ አለምከተማ እና መደነቢያ በተባሉቦታዎች ላይ የአገዛዙ ዘብ ጠባቂ ወታደር ከፍተኛ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራን አስተናግዷል።
በዚህ አውደውጊያ 17 የጠላት ሃይል ሲደመሰስ ከ23 በላይ ቁስለኛውን በአንቡላንስ ይዞ ወደ ላሊበላ ከተማ እና ወደ ጋሸና ከተማ እያንጠባጠበ ይዞ ተመልሷል።
የሃሰት ትርዕክትን ተልዕኮ ተቀብሎ የመከላከያ ሰራዊት ብልፅግና ፖርቲ እስኪመስል ድረስ የማጭበርበሪያ የምርጫ ሰነድ የይምረጡኝ የመፎክር ፕርፖጋንዳን ለማካሄድ ያሰበው የጁላ ጦርና አመራሮቹ ባልጠበቁት እና ባልገመቱት ልክ መብረቃዊ ጥቃት ወርዶባቸዋል።
በተለየ መንገድ ውጊያው የጠላትን ምሽግ ከማስለቀቅ ወደ ሙሉ ማጥቃት የተሸጋገርንበት የትስስር ውጊያና የስብጥር ውጊያ ነው ያሉት የ19ኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌና የ16ኛ ነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንዶ ፍቃዴ ቢተው የጠላትን ሃይል በመገርሰስ የበላይነትን ያሳየንበት ትልቅ አኩሪ ድል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በዚህ የተበሳጨው የብርሃኑ ጁላ ጦር አለኝ በሚለው ከባድ መሳሪያ በዙ-23 የ አርሶ አደር አበባው ተሾመን ቤት ቆጋ አምባ የተባለ ቦታ ላይ አቃጥሎ ተመልሷል፤ በተከታታይ በስድስት የዙ-23 ጥይት ቤት ንብረቴን አውድመውታል ያለው አርሶ አደሩ አቶ አበባው ተሾመ አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ ያሉት ተረት ከኔ ደረሰ ብሏል።
በመጨረሻም በዚህ መብረቃዊ ምት የተደናገጠው የአገዛዙ ሰራዊት መንገድ ላይ የሚያገኛቸውን ንፁሃን ግለሰቦች ላይ አሰቃቂ ግፍ የሽንፈት ምዕራፉን አሳይቶ ከፊሉ ወደ መጣበት ተመልሷል
መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ም/ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ አርበኛ መምህር ሙላት አላምረው መረጃውን አድርሷል ።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ:- 25/ 2018 ዓ'ም።
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የአማራን ሕዝብ ሲሳደብ የነበረው ባለስልጣን ክስ ሊመሠረትበት ነው!
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ የሕሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ሲደበድብና የአማራን ሕዝብ በጅምላ ሲሳደብ የነበረው የማረሚያ ቤቱ ጥበቃና ደህንነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ፡ በፈፀመው ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክስ ሊመሰረትበት መሆኑን መረብ ሚዲያ አረጋግጧል።
በአቶ ዮሐንስ ቧያሌውና በአቶ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ ስር የሚገኙት የቁርጥ ቀን የአማራ ልጆች ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ፡ የፌዴራል ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን ለፍርድ ቤት አስታውቋል።
በሽብር ስም በማረሚያ ቤት የሚገኙትን የፖለቲካ እስረኞች መብት በመርገጥ የሚታወቀው ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ፡ ተከሳሾችን ከመደብደብ አልፎ ጠያቂ ቤተሰቦቻቸውን በማዋረድና የአማራን ሕዝብ ማንነት የሚነኩ የጅምላ ስድቦችን ሲሰነዝር መቆየቱ ይታወቃል።
ይህ ግለሰብ የአገዛዙን የጥላቻ ፖለቲካ በማረሚያ ቤት ውስጥ ተግባራዊ ሲያደርግ የነበረ ቢሆንም፡ የእስረኞቹ ጠንካራ አቋምና ያቀረቡት ሕጋዊ አቤቱታ ለክስ እንዲበቃ አድርጎታል።
ሚያዚያ 22/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት፡ ፍርድ ቤቱ በኢንስፔክተሩ ላይ የተጀመረው ምርመራ የደረሰበትን ደረጃ የጠየቀ ሲሆን፡ የፌዴራል ፖሊስ ከረጅም ጊዜ መጓተት በኋላ ጉዳዩን አጣርቶ ክስ እንዲመሰረትበት መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ መላኩን አረጋግጧል።
በዚህም መሰረት ዐቃቤ ሕግ በቅርቡ በኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ላይ ክስ ይመሰርታል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንም እንኳ አገዛዙ የራሱን ባለስልጣናት ለይስሙላ ክስ ሊያቀርብ ቢሞክርም፡ ይህ እርምጃ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚፈፀመውን ስር የሰደደ ግፍና ጭካኔ የሚያጋልጥ ነው ብለዋል መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው ጉዳዩን በቅርብ የተከታተሉ እማኞች።
የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች በማረሚያ ቤት ሆነው ለሕዝባቸው ክብርና ለማንነታቸው የሚያደርጉት ተጋድሎ፡ የአገዛዙን የግፍ መጋረጃ እየቀደደው ይገኛል።
ሰበር የድል ዜና
በቀን 24/8/2018ዓ.ም የአፋብን ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር አካል የሆኑት የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና ነበልባሉ 23ኛ ክፍለጦር በጋራ በሰሩት የተናበበ ውጊያ
የተገኙ ድሎች፦
✅01 ጥቁር ሥናይፐር በውጊያ ከጥቅም ውጭ ሆኖ የተማረከ
✅48 የነብስ ወከፍ ክላሽንኮቭ የተማረከ
✅ 35 የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት ተማርኳል
✅501 የዲሽቃ ተተኳሽ፣ 05 የዲሽቃ ሸንሸሎች ከነተተኳሾቻቸው ተማርከዋል።
✅01 ብሬን ከነተተኳሹ ተማርኳል።
ፋኖ ይችላል🤞
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር በጠላት ሀይል ላይ ድል ተቀዳጅቷል!!
ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር በይፋት አውራጃ አንፆኪያ ገምዛ፣ ግሽ ራቤልና በዳዋ ጨፋ ወረዳዎች ጠላትን ለበርካታ ሳምንታት ቁም ስቅሉን ሲያሳዩት በመቆየታቸው ዛሬ ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም በድል አሸናፊነታቸውን አረጋግጠዋል።
የአገዛዙ ሀይል በአንፆኪያ ገምዛ አገረ ማሪያም ከጠዋቱ 12:00 በአራት ቦታ የተጀመረው አውደ ውጊያ ቀኑን ሙሉ ዘጠኝ ጊዜ የማጥቃታ ሙከራ ቢያደርግም ከሶስት ሻለቃዎች የተውጣጡት ክንደ ብርቱዎቹ ሰራዊትና አመራር በሞርተርና በአርቢጂ በታገዘ መካናይዝድ አውደ ውጊያ በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ብትር አሳርፈው አሰከሬንና ቁስለኛውን ከነመሳሪያው ጥሎ እዲፈረጥጥ አድርገውታል።
በኩሬ የጎደል ቀበሌ ሸሃደብስና እሁድ ገበያ የገባውን የጠላት ሃይል ከሁለት ሻለቃ የተውጣጡ ሻንበሎች በጋራ በመቀናጀት በጠላት ላይ ብዙ ኪሳራ አድርሰውበታል።
የፋኖን ውጊያ መቋቋም ያቃተው የጠላት ሃይል ተጨማሪ ሰራዊት ከግሽ ራቤል ፥ግሾጌና ሸበቶ ቀበሌ ሶስት መኪና መከላከያ ቢያመጣም የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር አናብስቶች የመጣውን ሃይል እዳይወጣ አድረገው 12 የአገዛዙ ሀይል ሲደመሰስ ከ16 በላይ ከባድ ቁስለኛ አድርገውት አስከሬኑን ማንሳት ሳይችል አዘረክርኮ ፈርጥጧል። በዚህም ጠላት መሽጎባቸው የነበሩ ወታደራዊ ገዢ ቦታዎችን ክ/ጦሩ መቆጣጠር ችሏል።
የአስቴ ጉማ ነበልባሎች 5 የጠላትን አስከሬን በህዝብ በማስነሳት በአማራው ባህልና ወግ በቀርቀሃና ሃገረ ማርያም ስርአተ ቀብራቸውን አስፈፅመዋል።
ከጠላት የተገኘ ምርኮ
1. ሁለት (2)ጥቁር ጥርጥር ክላሽ
2. ስምንት (8) የክላሽ ካዝና
3. ሶስት መቶ አስራ ሁለት (312)የክላሽ ጥይት
4.አምስት (5)ወታደራዊ ሻንጣ
5.ሁለት(2)ወታደራዊ ሳንጃ በመማረክ መታጠቅ ችለዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ
+4
201ኛ ኮር ሰዴ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች ጋር መክሯል
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
=========================== ማያዚያ 24/2018 ዓ.ም
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የመንግስት ሰራተኞች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ማካሔዱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ እና የማህበራት ተጠሪዎች በንቃት ተሳትፈውበታል ።
አማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ሰብሮ ለመውጣት የመንግስት ሰራተኞች ሚና በጉልህ የሚገለጽ ሲሆን ትግሉን በተባበረ ክንድ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
🛑 የብዕር ጩቤና የቁም መቃብር
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ትልቁን ፈተና አልፏል። ትናንት በጎጥና በመንደር ተከፋፍሎ፣ "የእኔ ቀጠና ይበልጣል" በሚል ሽኩቻ ደም የተቃባው ፋኖ፣ ዛሬ በጋራ ዓላማ ስር ተሰልፏል። በጦር ግንባር ግንባር ለግንባር ተጋጥመው የነበሩት ጀግኖች ቂማቸውን በይቅርታ አጥበው፣ በአንድ ጥይት ጠላትን እየመከቱ ነው።
ነገር ግን እውነታውን እንጋፈጠው፤ መሬት ላይ ያለው ተዋጊ በደሙ የገነባውን አንድነት፣ እኛ በዲጂታሉ ዓለም ያለን ሰዎች በቃላት ሽኩቻ ልንንዱት አይገባም።
ታሪካችን እንደሚያስተምረን፣ ኢትዮጵያውያን በውጭ ወራሪ ያልተሸነፉት በመሳሪያ ብልጫ ሳይሆን በአንድነት ጉልበት ነው። አፄ ቴዎድሮስ "መቅደላ" ላይ ከመውደቃቸው በፊት የገጠማቸው ትልቁ ፈተና የውስጥ መከፋፈል ነበር። ያኔም እንደ ዛሬው አንዱ ሌላውን "ባንዳ"፣ ሌላው ደግሞ "ከዳተኛ" እያለ ሲወነጅል ጠላት በደጃችን ገባ። ዛሬም እኛ በሚዲያው ያለን ሰዎች በቲክቶክና በፌስቡክ የምናደርገው ንትርክ ለአዞ ጥርስ መሳል እንዳይሆንብን እንጠንቀቅ።
አበው ሲተርቱ "ቤት ሳይሰሩ ማገር፣ አንድነት ሳይፈጥሩ ማክረር" ውድቀትን ያፋጥናል ይላሉ። በጠመንጃ አፈሙዝ የተጋጠመው ወንድሙን ይቅር ብሎ አብሮት ሲሰለፍ፣ እኛ በቁልፍ ሰሌዳ የተጋጨነው ለምን ቂም እንቋጥራለን? ደሙን የሚያፈስሰው ጀግና ታርቆ፣ ወሬውን የምናፈስሰው እኛ ለምን እንናቆራለን?
እናም ጋዜጠኞች አክቲቪስቶችና ሚዲያ ላይ ያላችሁ ሁሉ!! ትግሉን "የቪው" (View) እና "የላይክ" (Like) ማከማቻ አናድርገው። አንድነቱ የደረሰው በመቶ ሺዎች መስዋዕትነት ነው። በብዕራችንና በምላሳችን ልዩነትን የምንዘራ ከሆነ፣ ታሪክ ነገ "የአንድነት እንቅፋቶች" ብሎ በደማቅ ቀለም ይዘግበናል።
የተገዳደለ ተስማምቶ፣ የተሰዳደበ የማይታረቅበት ምንም ምክንያት የለም። የሚዲያ ጩኸታችን ከግንባር ድምፅ ጋር መጋጨት የለበትም። ፋኖን ለመምራት አንሞክር፤ ይልቁንም ፋኖ የፈጠረውን አንድነት እንከተል። አንድነት የህልውናችን መሰረት ነውና ልዩነታችንን በይቅርታ ቋጠሮ እናስረው።
የአማራ ህዝብ በአንድነቱ ይጸናል!
ድል ለፍትህ ፈላጊው ህዝብ!
201ኛ ኮር ሁለት እጅ እነሴ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች ጋር መክሯል
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
=========================== ማያዚያ 24/2018 ዓ.ም
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የመንግስት ሰራተኞች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ማካሔዱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ እና የማህበራት ተጠሪዎች በንቃት ተሳትፈውበታል ።
አማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ሰብሮ ለመውጣት የመንግስት ሰራተኞች ሚና በጉልህ የሚገለጽ ሲሆን ትግሉን በተባበረ ክንድ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+4
201ኛ ኮር ቢቡኝ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች ጋር መክሯል

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝናግሼ አውራጃ ግሼ ክላስተር የሕዝብ ተቋማት ሠራተኞች መድረክ ተካሄደ።
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠረው ግሼራቤል ወረዳ የሚገኙ የሕዝብ ተቋማት ሠራተኞች (የህዝብ ሰራተኛ)የውይይት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ መድረኩ "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በመምከርና አቅጣጫ በማስቀመጥ እንድሁም በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የአቋም መግለጫ በማሰማት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ