ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 486
المشتركون
+3524 ساعات
+997 أيام
+94030 أيام
أرشيف المشاركات
"መድረሻችን ጨረቃን ስንጠቁማችሁ የእናንተ አይን የሚያዬው ከፍ ያለውን መድረሻችን ሳይሆን የጠቆምንበት ጣታችን ጫፍ ነው።
ግራ የምትጋቡትም የማይገባችሁም ለዚህ ነው። እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ግባችን ላይ ስንደርስ ይገባችኋል‼️"
አብዮታዊው መሪያችና ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ከተናገራቸው ንግግሮች መካከል የተወሰደ....
እኛም እንላለን፦
በእያንዳንዱ ቀን፣ሰአትና ደቂቃ አዲሱ ትውልድ በየወንዙ፣ጋራና ሸንተረሩ አዲስ ታሪክ በመፃፍ ላይ ይገኛል ።አብዮታዊው ትውልድ ጣና ቀለም ምድር ብራና ቢሆኑ ተፅፎ የማያልቅ ደማቅ ታሪክ በመፃፍ ላይ ይገኛል ። ትውልዱ ካሰበው ይደረሰ ዘንድ ግድ ነውና ወደ ምንፈልገው ግብ ለመድረስ ሁልጊዜም በቅንነት እንሰራለን።እንተጋለን!
ቅንነት የአዲሱ ትውልድ የትግል መመሪያ ነው። ተራራ የሚያህል እውቀት ቢኖረን ቅንነት ከሌለን ከንቱ ነው።
ቅን እንሁን!
ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ሃይለሚካኤል ባየህ
ንጉስ ሚካኤል ኮር አደም አሊ ክፍለጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ መቅደላ ወረዳ ላይ ተጋድሎ በማድረግ ድል አደረጉ‼️
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር አደም አሊ ክፍለጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ መቅደላ ወረዳ 015 እና 028 ቀበሌ የፋኖዎችን ይዞታ ለማስለቀቅ ከመቅደላ ከደብረዘይት ከተንታና ጊንባ በርካታ ሃይሉን ይዞ በኮማንዶ ኡመር ምሳው የምትመራውን ይችን ሻለቃ ለማጥቃትና ለመክበብ የመጣ ጠላት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ይዞታቸውን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ጦር ለመስከረም 10/2018 ዓ.ም ሌሊት 7:00 ማጥቃት ያደረገ ሲሆን እስከ ቀን 8:00 በንስሮቹ ተመክቶና መልሶ ማጥቃት ተደርጎበት በርካታ ሃይሉ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ወደመጣበት የተመለሰ ሲሆን በተጋድሎው ጠላት ጥሎት የሸሸ እስከ 10 የሚደርስ አድማ ብተናና ሚሊሻ ፋኖ ህዝብ አስተባብሮ አስቀብሯቸዋል::
በተጋድሎው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ የቃታ መሳሪያዎች ወታደራዊ ሻንጣዎችና የዝናብ ልብሶች ማርኳል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም በፋሽስቱ ሰራዊት ታፍነው የነበሩ ሶስት ወጣቶችን ያስለቀቀ ሲሆን አገዛዙ አሁንም በየ አካባቢው መምህራኖችን ከፋኖ ጋር ትወያያላችሁ ትመክራላችሁ በሚል እያዋከበ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
13/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሕዝባዊ ስብሰባ በበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ማይ አንገታም ቀበሌ!
መስከረም 13/2018 ዓ.ም
ሁሉ ነገሩን ሳይሰስት ለሚሰጠን ሕዝባችን ያለንን እንሰጠዋለን!
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ከማይ አንገታም ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ።
በውይይቱ የክፍለ ጦሩ የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ አረፋይኔ ተጎድና የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊው ፋኖ አበባየሁ ባንታምላክ የተገኙ ሲሆን በአማራ ትግል መሠረታዊ ጉዳዮችና የትግላችንን አሁናዊ ልዕልና አስመልክቶ ለማሕበረሰቡ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የቀበሌ መዋቅሩንም በመፈተሽ የአመራር ሪፎርም ሰርተዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሕዝባችን!
#የአገዛዙ_ሰራዊት_በሽንዲ_ከተማ_ተቀበረ...‼️
አፋብኃ ምዕ /አ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር (መስከረም 13/2017 ዓ.ም)
የወምበርማ ብርጌድ በሽንዲ ከተማ መሽጎ የተቀመጠውን ሰውበላ ስርዓት የአብይ ወምበር አስጠባቂዎችን በዛሬው ዕለት መስከረም 13/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ሲወቀጥ አርፍዷል።
አይበገሬዎቹ የወምበርማ ብርጌድ ሶስቱን ሻለቃዎች በማሰለፍ ማለትም ንስር ሻለቃ፣ ቆምጥ ሻለቃ እና ነበልባል ሻለቃ በሚሊኒየም ትምህርት ቤት ፣ በሙስሊም ሠፈር ፣ መነሐሪያ በሶስቱም አቅጣጫ በመግባት ከተማዉን እስከ መነሃሪያው ተቆጣጥረዉ ጠላትን አይቀጤ ቅጣት ቀጥተውታል።
በውጊያውም የድል ናፋቂው ስርዓት ጠባቂዎች ከተማውን ለቀው እስከ መነሃሪያ ድረስ በአይበገሬዎቹ የወምበርማ ብርጌድ በቁጥጥር ስር አርፍዷል።
በኦፕሬሽኑም ከፍተኛ አመራሮች እና ፖሊሶችም ወደላይኛው ሲሸኙ 6 ተላላኪ ሚኒሻዎች ሲደመሰሱ እንዲሁም ባንዳ ሞላ አጥናፍ፣ ባንዳ መልካሙ ፈረድ እና ባንዳ ደሳለው ይታይህ እና አንድ ስሙ ያልታወቀ ባንዳ ለአረመኔው ስርዓት በመረጃ እና ደህንነት ሲያገለግሉ የቆዩ በድምሩ 4 ባንዳዎች በከባድ ቁስል ላይ ናቸው።
እንዲሁም በርካታ መከላከያዎች ሲደመሰሱ ቀሪዎች ደግሞ በከባድ ቁስል ላይ መገኘታቸውን እና ያልተነሱ ቁስለኞችን፣ እሬሳዎችን በፓትሮል እየለቃቀመ እንደሚገኝ እንዲሁም ህዝቡን ገመናዉን እንዳያዩ እየደበደበ ወደ ቤት እየረስገባ እንደሚገኝም የውስጥ ምንጮቻችን መረጃውን አድርሰውናል።
የአረመኔው ስርዓት ወምበር ጠባቂዎች እንደ ተርብ በሚናደፉት የወምበርማ ብርጌድ ውጊያ በሽንዲ ከተማ በርካታ ሰራዊቶችን ቀብሯል።
የወምበርማ ብርጌድ አይበገሬነታቸውን እና ጀግንነታቸውን በሽንዲ ከተማ አስመስክረዋል ሲል የወምበርማ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መረጃውን አድርሶናል።
በተጨማሪም መስዋዕትንትን የተቀበለው በጀግንነቱ የሚታወቀው ''ሻለቃ አባይ አንዷለም'' የጠላትን ኃይል እሬሳ በሬሳ አድርጎ ከፍተኛ ድልን ለወገን አቀዳጅቶ ውድ ህይወቱን ለአማራ ህዝብ መስዋዕትነት ከፍሏል።
ጠላትን እንደተርብ የሚናደፈው ተምዝግዛጊዋ ቆምጥ ሻለቃ መሪ ሻለቃ አባይ በርካታ ተላላኪ ባንዳዎችን እና ግፈኛ ሰራዊቶችን እረፍርፎ የጀግናው የበቀለ ካሳ ልጅ መሆኑን አስመስክሮ በጀግንነት ተሰውቷል።
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ኢንጅነር ካሳሁን አማን ህ/ግንኙነት
13/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ የበለጠ ጓዳዊ ዝምድና ለማጠናከር ሁሉም የብርጌድና የፋኖ አባላት አባላት በተገኙበት ተሃድሶ አካሔደ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክ/ጦር የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ የበለጠ ጓዳዊ ዝምድና ለማጠነካር ከፍተኛ የእዝ፣የክፍለጦር እና ሁሉም የብርጌድና የሻለቃ አመራሮችና አባላት በተገኙበት ደማቅ ተሃድሶ አካሒዷል።
የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ አርበኛ ደመላሽ አድነው በመረሃግብሩ ተገኝተው እንዳሉት እኛ የምንታገለው ጠላትን ለመግደል፣ ለመደምሰስ ፣ የሀገረ መንግስት ባለቤት ለመሆን ፣የቀደምት አባት አያቶቻችን ዙፋን የስልጣን ባለቤት ለመሆን፣ አማራን የተደቀነበትን የመጥፋት ዘመቻ ለመታደግ ብቻ ሳይሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አረንቋ ለማላቀቅ ስለሆነ የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሁላችንም በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ጠላቶቻችን ፀረ አማራ ዓላማ አንግበው የተነሱ በመሆኑ ጠላቶቻችንን ሳንደመስስ ማረፍ ስለሌለ የጋራ ጠላታችንን በአንድነት በመሆን ማሸነፍ ይገባናል ብለዋል።
በክብር እንግዳ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአረንዛው ዳሞት ብርጌድ ሰብሳቢ አርበኛ ቻሌ ዘመን እንዳሉት ገረመው ወንዳውክና አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ሁለቱ መትዮች ተብሎ የተመሰከረላቸው ብርጌዶች በመሆኑ ከዛሬ በፊት የምናደርጋቸውን ግንኙነቶችን በማጠናከር ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስና በጋራ በመስራት የጋራ ጠላታችን ለመደምሰስ ዝግጁ ነን ብለዋል።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ የኔአለም ዘለቀ በተሃድሶ መረሃ ግብር ተገኝተው እንዳሉት አንድ ወታደር ማድርግ ያለበትና የሌለበትን በማወቅ ማንኛውም ወታደር ከግላዊ ስሜት በመውጣት የወጣበትን አለማ በመገንዘብ ነበልባሉ ገገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ገናና ታሪኩን በማስቀጠል ጠላትን አከርካሪውን መስበር ይገባል ብለዋል ሲል ፋኖ በላይ ሞገስ የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ተወካይ ህዝብ ግንኙነት ተናግሯል።
( መስከረም 13/2018ዓ.ም)
፲/አ ኢ/ር ዘመኑ አማረ
የ5ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሰበር የድል ዜና‼️
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ሺ አለቃ ጋሪ ቶላን ጨምሮ ከመቶ በላይ የአገዛዙን ሰራዊት ደመሰሰ።
==============
መስከረም 12/2018 ዓ ም ከጧቱ 12:00 ጀምሮ በአራት ግንባር ወረራ የፈጸመው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በአጼ ዘርዓ ዓይቆብ አንደኛ ኮር ከመቶ በላይ ሲደመሰስ ከመቶ ሀምሳ በላይ ደግሞ ቁስለኛ ሁኗል::
በወዠድ ግንባር በተካሄደው አውደ ውጊያ የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሺ አለቃ ጋሪ ቶላ ይዞት ከገባው የሰራዊት አባል ጋር በአጼ ዘርዓ ዓዕቆብ አንደኛ ኮር ነጎድጓድ ክ/ጦር እ፣ ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ፣ ናደው ክፍለጦር እና ብሩኬ ደምሴ ብርጌድ በተውጣጡ ሻለቆች ተደምሷል::
የሸዋን ቀጠና ለመቆጣጠር ከተራ ሚሊሻ ፣ ኮማንዶ እስከ አየር ወለድ ያሰማራው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን በገባበት አውደ ውጊያ በፋኖ ጥይት እየተቀነደበ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል::
በአራት ግንባር የፋኖን ጠንካራ ይዞታ ለመቆጣጠር በካራ ቆሪ ግንባር የገባው 102ኛ በካራ ለጎማ ግንባር 103ኛ በመስቀል በር አርብ ገበያ 104ኛ ኮማንዶ እና በወዠድ 105ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ ልፍለጦር ከአድማ ብተና እና ሚሊሻ ጋር ጥምረት ፈጥሮ ለወረራ ቢንቀሳቀስም በነበልባሎቹ የአማራ ፋኖ ተቀንድቦ ከ200 በላይ የሚሆኑት በመሀል ሜዳ ሆስፒታል ገብቷል::
ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ያስተናገደው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ያለ የሌለ ተጨማሪ ኃይል እያሰባሰበ ለማስገባት ቢሞክርም የፋኖ ኃይሎች ገዥ ቦታዎችን በመያዥ ስቦ ለማስገባት የወሰዱትን እርምጃ በመፍራት ባለበት ለመቆም ተገዷል::
በተጨማሪም ዛሬ ማለትም መስከረም 13/2018 የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በፋኖ ሸጋው ግርማ የሚመሩት የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ቃኝወች በኤፍራታ ግድም ወረዳ ካራለጎማ ቀበሌ ፈረስ ጎጥ ላይ ባደረጉት የሽምቅ ውጊያ ከአጣዬ ከተማ ሊዘርፍ የመጣውን ባንዳ ሚሊሻ እና ምእከላከያ ሙሉ በሙሉ ደምሰውታል። በብልጽግናው ሰራዊት ላይ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የተከታተልን ተደራሽ የምናደርግ ይሆናል::
መረጃውን አጠናክሮ ያደረሰን አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፄ ዘራዓ ያዕቆብ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ነው።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
መስከረም 13/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የፋኖ_አንድነት
እንደው ዝም ብለን አንድነት አንድነት እያልን እንጮሀለን እንጂ ትግላችን እኮ ታሟል። በጣም በጣም ታሟል። በምን ታመመ ብትሉኝ - በጎጠኝነት። ጎጠኝነት እንዲህ ስር ሰድዶ እያየን አንድነትና ውስጣዊ ጥንካሬ ይኖራል ብሎ ማለት ዘበት ነው፡፡
አሁን የአፋብኃ ደጋፊዎች ነን የምንለው ሰዎች እኮ ከቋራ የአፋብኃ ምስረታ በፊት ቲክቶክ ላይ አብረን ቁጭ ብለን ታፕ ታፕና ኮፒሊንክ እያረግን ለሁሉም የፋኖ አደረጃጀት ፕሮፓጋንዳ ስንሰራና ገንዘብ ስናሰባስብ ነበር። ከቋራ በኃላ ግን ልክ በሀይለኛ ሞገድ ተመታ እንደተበታተነች መርከብ ብትንትናችን ነው የወጣው። አሁን አንድ ላይ የምንሰባሰብበት አንድም መርከብ የለንም። 😩
ቋራ ላይ ምን ተፈጠረ የሚለውን ባጭር አረፍተነገር ስገልፀው - የፋኖ አመራሮች እርስበእርስ መተማመን ስላልቻሉ ለአፋብኃ መሪ መምረጥ አቅቷቸው ተበተኑ ነው። ችግራችን ጎጠኝነቱ የወለደው #አለመተማመን ነው። ብንተማመን ኖሮ ስለሴራ፣ ስለሶስተኛ አካል ጣልቃገብነት፣ ስለስልጣን ጥመኝነት፣ ስለትግል ጠላፊነት ምናምን እያወራን አንሻኮትም ነበር። "የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል" እንደሚባለውም ቃልኪዳን ስናፈርስና ስናድስም አንኖርም ነበር።
አሁን ማን ይሙት ነገ መሪዎች ተመራርጠው የአመራር ቦታዎችን ድልድል አድርገው ቢነግሩን ይህ ጎራ ለጎራ ለይቶ መነቋቆሩ፣ አንዱ የአንዱ ስም ማጠልሸቱና ጠልፎ ለመጣል መሞከሩ ይቀራል ትላላችሁ? እኔ አይመስለኝም። እያንዳንዱ ከጎጡ ያልሆነው ሰው ላይ እንደተለመደው ይዘምትበታል። የሴራ ድርሰት ደራሲዎቹም ከነሱ ጎጥ የሚፈልጉት ሰው የሚፈልጉት ቦታ እስካልያዘ ድረስ አሁንም ሴራ አለ ብለው አንድነቱን ይበትኑታል። ለምን? አንተማመንማ።
ከጎጠኝነት የፀዳ ጤነኛ ብሔርተኝነትን ገንብተን መተማመንን አዳብረን ቢሆን ኖሮ ይህ ሀሉ ችግር ባልኖረ ነበር። አሁን ላይ አንዳንዶች ጎጣቸው ውስጥ ተደብቀው በአብን ጊዜ የተፃፉ የአማራ ብሔርተኝነት ፅሑፎች ከArchive አውጥተው ሊያስነብቡን ሲሞክሩ እያየሁ አስቃለሁ። 😀 መጀመሪያ ከጎጥህ ውጣ። አሁን የሚያስፈልገው ብሔርተኛ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ የፋኖ መሪዎችም ጭምር ከጎጠኝነት ራሳቸውን ማፅዳት ነው።
ወደ ሀሳቤ ስመለስ አንዳንዶች ብቃት ላይ መሰረት ያደረገ የመሪዎች ምደባ ከተደረገ ሁሉ ነገር አሸወይና የሚሆን ይመስላቸዋል። I doubt it. እንዲህ ዋልታ ረገጥ ጎጠኝነት ገንግኖና እርስ በእርስ #መተማመን በሌለበት ሁኔታ "ብቃት ላይ ብቻ መሰረት ባደረገ መስፈርት መሪዎችን መምረጥ" የሚለው ሀሳብ ideal እንጂ ሊተገበር የሚችል ነው ብዬ አላስብም። ትቀልዳላችሁ? የኛ ሰው እኮ ከባድ ነው። መሪዎቻችን በመስፈርቱ ላይ ተስማምተው ቢመራረጡ እንኳን "መስፈርቱ መጀመሪያም የወጣው የአንድን ቡድን ጥቅም ለማስከበር ነው" ብሎ እሪ የሚል በእርግጠኝነት አይጠፋም። ለምን? አንተማመንማ።
እውነት ለመናገር ብቃትን ስንለካ ቅንነትንም መለካት ቢቻል ጥሩ ነበር። አገራችን እዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ውስጥ የገባችው ቅን ባልሆኑ ነገር ግን የተማሩና "ብቁ" ናቸው በተባሉ ሰዎች ስለሆነ። Honestly የአንዳንድ ፋኖ መሪዎችን ቅንነት እኔ ራሴ እጠራጠራለሁ። 😮
ነጥቤ ምንድን ነው? እርስ በርስ መተማመን መጀመሪያ እስካልመጣ ድረስ ማንኛውም የሀላፊነት ምደባ በጥርጣሬ ይታያል፤ ይህም ወደ የማያቋርጥ ንትርኮች፣ የወገኝተኝነት ውንጀላዎች እና በመጨረሻም አንድነቱ እንዲፈርስ ያደርገዋል። መተማመን ከሌለ "ብቃት" የምንለው እንኳን አከራካሪና ውጤት አልባ ነው። ትግላችን ደግሞ የትጥቅ ትግል በመሆኑ #መተማመንን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።
ጤነኛ ብሔርተኝነትና መተማመን ሲኖር በፋኖ መዋቅር የመሪዎች ምደባ ተደርጎ ከሀላፊነት ጋር የሚመጣው የመወሰን አቅም በአንድ ሰው ወይም ከአንድ አካባቢ በመጡ ሰዎች ቢያዝ እንኳ አቧራ አይነሳም። #መተማመን ከሌለ ግን ጥርጣሬን መጫሩ አይቀርም። ጥርጣሬ ደግሞ አድጎ መከፋፈልን ይወልዳል።
እና ምን ለማለት መሰላችሁ .. አሁን ላይ ብቃት ብቃት እያልን ብንደሶኩር እንኳ ነባራዊ ሁኔታው የሚነግረን ወደድሽም ጠላሽም representation matters ነው። ስለዚህ አመራር ሲመርጡ ብቃትን ያስቀደመ እና የአካባቢንም ውክልናን ደሞ ያልገፋ አሰራር ቢከተሉ፣ ወይንም የተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ ሃላፊነትን ለአንድ ሰው ብቻ ከመስጠት ይልቅ ከሌላ አንድ ሰው ጋር መጋራት ቢቻልና በመግባባት ውሳኔዎችን ማሳለፍ ቢቻል ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። Shared responsibility ሲኖር የጋራ ተጠያቂነትም ይኖራል፣የግል ፍላጎቶችንም ይገድባል፣ መተማመንን ያዳብራል።
እንግዲህ እንዲህ አርገን ጀምረን መተማመንን እያሳደግን ትግሉን ያለምንም የጎንዮሽ ሽኩቻ ማስኬድ ከተቻለ ሌላውን ሌላውን አራት ኪሎ ስንደርስ እንጨነቅበታለን። ኢንሻአላህ 🙏
አይ ከሌላው አካባቢ ጋር አንድነት አያስፈልገኝም ፣ ብቻዬን እንደ ምድረ በዳ ዛፍ መቆም እችላለሁ ካልክ ደሞ ኃላ የትግል መሰረት ስርህ ደርቆ፣ በድል ጥም ተቃጥለህ፣ እዚያው ጫካ ውስጥ ከሚሊሻና ከአድማ ብተና ጋር አባሮሽ ስትጫወት መክረምህ ነው።
የያዝነው ትግል የህልውና ትግል ስለሆነ የፋኖ አንድነት ግድ ነው።
#የፋኖ_አንድነት
#አፋብኃ
+4
በድጋሜ የተለጠፈ
ትግሉ በሰርጎገቦች ተወሯል ብቻ አይደለም "#ተውጧል" ለማለት አስደፋሪ እየሆነ ነው።
በ4ቱ ክ/ሀገሮች የጎጥ ዋሻ ምሽግ የያዙ መስለው ፀረ አምሓራ አንድነት ከፋፋይ ለመናጆዎቻቸው መርዛማ መኖ የሚያቀብሉትን በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። እነዚህን መሰሎች የትግል ቃል አቀባይ አድርጎ የሚራመድ የትግል ቡድን ለህዝብ እየሰራ አለመሆኑ ይሰመርበት።
ይልቁንስ አውራጃዊ ግጭት፣ ጎጣዊ የፖለቲካ ትርክት ለመፍጠር እየተጣደፈ ነው።
የብልፅግና የልቡ ልብ ሰጭዎች እነኝህ መሰሎች፣ በትግሉ ውስጥ ሰርገው ገብተው ሚስጥራዊ የሆኑና የአመራር በትር እስከመጨበጥ የደረሱት ናቸው።
ነገር ግን ፍኖተ-አማራ ሚዲያ እነዚህን አረመኔያዊ አስተሳሰብ ያላቸውን በሙሉ በመከታተል ከትግል አጋሮቻችን ጋር በመሆን ከትግል ሚዳ እየሰራን እንገኛለን።
ሆኖም የተከበራችሁአማራዊያን በማነኛውም ቦታ የምትገኙ አማራዊያን እና የትግል ደጋፊዎቻችን ኢትዮጵያዊያን ቻናላችን በቀና ልቦና ሸርና ጆይን በማድረግ እንድትተባበሩን ስንል በአክብሮት እንገልፃለን!
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ በሶስት ግንባር ተጋድሎ በማድረግ ድል ተጎናፀፈ::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ መስከረም 12/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በሶስት ግንባር በጓሜዳ ከተማ፣ መለስ ሳንቃ በር፣ እና እዋ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
ተጋድሎው በተደረገበት ሶስት ግንባር በጓሜዳ ወንድም መልኬነው ሻለቃ፣ ያምረው አለሙ ሻለቃ አንድ ሻምበል፣ እና የብርጌድ ቃኝ በጥምረት አንድ ፓትሮል የጠላት ሃይል ሲደመስሱ ከዚህ በተጨማሪም 15 ሚሊሻ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም ሶስት ክላሽ በመማረክ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::
በሌላኛው እዋ ከተማ ግንባር ሳተናው ሻለቃ እና ነብሮ ሻለቃ በጥምረት ከተማው ላይ መሽጎ የነበረ አድማ ብተናና ሚሊሻ ጋር ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ በርካታ ሆድ አደር በመደምሰስና ቀሪውን በመበታተን ከተማዋን ተቆጣጥረዋል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ጠላት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን እስካሁን አስከሬኑን በማንሳት ላይ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 13/2018 ዓ.ም
ፋኖ በጎንደር ከእንፍራንዝ እስከ አርኖጋርኖ ቀጠና በሜካናይዝ የታገዘ ውጊያ ማድረጉን አስታወቀ!
ከማክሰኝትና ከእንፍራንዝ እስከ አርኖ ጋርኖ ደረስ ዘልቋል በተባለው በዚህ ውጊያ በርካታ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ወታደሮች መገደላቸውን መረብ ሚዲያ ከአፋብኃ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዕዝ ስር ከሚገኘው ከ5ኛ ኮር ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
በጥቂት የሰው ኃይልና በጥቂት የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች የተጀመረው የአማራ ሕዝብ ትግል አሁን ላይ በኮርና በዕዝ ከመደራጀት አልፎ በሜካናይዝድና በኮማንዶ ደረጃ መዋቀር ከጀመረ ዋል አደር ማለቱን ጣቢያችን ምስል ጭምር አስደግፎ ለአድማጭ ተመልካቾቹና ለአንባቢዎቹ ማድረሱ አይዘነጋም።
በአራቱም አቅጣጫ ያለው የፋኖ ኃይል በዘመናዊ ከባባድ መሣሪያዎች ላይ የሚራቀቁ፡ ሲተኩሱም ቅምቡላቸውን ከጠላት ኪስ ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ተኳሽና የከባድ መሣሪያ ባለሙያዎችን በገፍ እያፈራ ነው።
ሰበር ||
ባሕር ዳር ላይ የዞን አመራሩ በፋኖ ተወሰደ
በደሴና በጎንደር በሞርተር የታገዘ ውጊያ
ስለ ኢሬቻ አከባበር የተሰማው አዲስ ነገር
https://youtu.be/9UsALexVt-A
ለአማራው ያልሆነች ኢትዮጵያ ትፈርሳለች እንጂ በአማራ ደም አትበለፅግም
🔺የክርስቲያን ታደለ ጥፋቱ አማራ መሆኑ ብቻ ሌላ ወንጀል ምን ሰርቶ ያዙት እውነተኞች ቢሆኑ የሰራውን ወንጀል እሄን እሄን ወንጀል ሰርቷል ብለው እስከ መረጃዎች በነገሩት ነበር ግን እሄ ጊዜ ያልፋል ይብላኝ ለግፈኞች ከአብይ ጋር ሁነው ለአስገደሉን ለአሳሰሩን ለአፈናቀሉን ለወረፉን ማየት የምፈልገው እኔ አብይ ከተባረረ በኋላ ያለችውን ኦሮሚያ ..!!!
🟢ጦማሪ ዘርይሁን ገሠሠ፣ በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ አድሎአዊነት አጋልጣለሁ ባለበት አዲስ ጽሑፍ፣ በአቶ አብነት ገብረመስቀል እና በምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ የእስር ጊዜ መካከል ያለውን ከፍተኛ ልዩነት በማነጻጸር ጠንካራ ትችት አቅርቧል።
🟡ጦማሪው ከአቶ አብነት ጋር በአጋጣሚ አብሮ እንደታሰረ በመግለጽ፣ የእሳቸው እስር "የይስሙላ" እንደነበር ተናግሯል።
🔴ዘርይሁን እንደሚለው፣ አቶ አብነት "በህክምና ሰበብ" ከእስር ቤት እየወጡ ለቀናት የፈለጉትን አድርገው ይመለሱ ነበር።
የፓርላማ አባላት ሳይቀሩ ፌደራል ፖሊስ ድረስ በመምጣት ያደራድሯቸው እንደነበርም ጽፏል። በመጨረሻም "በጤና ችግር" ክሳቸው ተቋርጦ መለቀቃቸውን በማስታወስ፣ "ተደራድረህ ትፈታለህ!" ሲል የሥርዓቱን አሰራር ይተቻል።
⭕️በአንጻሩ በእስር ላይ የሚገኘው የምክር ቤት አባል #ክርስቲያን_ታደለ የሚደርስበትን ስቃይ ይጠቅሳል። ጦማሪው እንደሚለው አቶ ክርስቲያን ተገቢውን ህክምና፣ የቤተሰብ ጠያቂ
እና እንክብካቤ የተነፈገው "ከግፍና ከግፈኞች ጎን ባለመቆሙ" እና "በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመታገሉ" ነው።
🔵ጦማሪ ዘርይሁን ገሠሠ ጽሑፉን ሲያጠቃልል፣ በኢትዮጵያ ውስጥ "የእስር ገመድ የሚጠብቀው እውነትን ስትናገር ብቻ ነው" ሲል ይሞግታል።
✅"ፍትህ በሌለበት ሀገር ፍትህ እያልኩ አልጮህም" ያለው ጦማሪው፣ ነገር ግን እንደ ክርስቲያን ታደለ ያሉ እስረኞች ለሁላችንም "መሪር መስዋዕትነት" እየከፈሉ መሆኑን ህዝቡ እንዲገነዘብ ጥሪ አቅርቧል።
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
♦ በፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው
#በቅርብ ቀን.....!!!!
በአማዞን (amazon) እና በሌሎች ከ10 በላይ በሚሆኑ ዲጅታል ገበያዎች በ online ሽያጭ እና በበሕትመት Hard Copy(Paperback)ይጠብቁን!!
#የፋኖን በሁሉም መስክ ስኬታማነት እና ከውጊያ ባለፈ በሁለንተናዊ ተሳትፎው ረገድ አቻ የማይገኝለት መሆኑንን የሚያሳይ"የአማራ ፋኖ ግቡን እንዲመታ" በሚል ርዕስ፣ ከትግል ሜዳ በፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ምክር አዘል መፅሐፍ ተዘጋጅቷል።
መፅሐፉ፦
#የአማራ ፋኖ የፖለቲካ ትጥቅ ትግል ባለቤት ከሆኑት ባሻገር የትጥቅ ትግሉ ያገባናል ለሚሉ ሁሉ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
#በ7 ምዕራፎች እና በ170 ገፆች የተቀነበበ ነው።
#በበቂ መረጃዎች እና የግርጌ (Footnote) ዋቢ/ማሥረጃዎች የተደገፈ ነው።
"አድማ ብተና ግልገል ፋኖ ነው፡ ካሁኑ መጥፋት አለበት" የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች!
የአገዛዙ ወታደሮች በተስፋ መቁረጥ ተሞልተዋል። በለስ የቀናቸው ከስምሪት ቀጠናቸው እየጠፉ ሕይወታቸውን ሲታደጉ፡ ይሄንን ወርቃማ እድል ማገኘት ያልቻሉት ደግሞ እርስ በእርሳቸው ተኩስ ከፍተው እየተገዳደሉ ነው።
መከላከያ ሰራዊቱ የቡድን መሣሪያ ጭምር አዙሮ በመተኮስ በርካታ የሚሊሻና አድማ ብተና አባላትን ገድሏል።
የግጭቱ መነሻ "በተሳሳተ መንገድ እየመራችሁ ወስዳችሁ በፋኖ እንድንጠቃ አድርጋችሁናል" በሚልና "በውጊያ ወቅት በቂ እገዛ እያደረጋችሁልን አይደለም" በሚሉ ምክኒያቶች ነው ተብሏል።
የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችም "አድማ ብተና ግልገል ፋኖ ነው፡ ካሁኑ መጥፋት አለበት" የሚል መመሪያ መስጠታቸው ተሰምቷል።
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥የንጉስ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በየጋግና ቀበሌ ፣ በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ማይ አንገታም ቀበሌ ላይ ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አካሄዱ‼️
መሰከረም 12/2018 ዓ.ም
💥የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ በየጋግና ቀበሌ ከሚገኙ የማሕበረሰብ ክፍሎች ጋር ሠፊ የሆነ ውይይት አካሔደ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ፮ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ከሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ውስጥ አንዱ የጋግና ቀበሌ ነው። የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ግዙፍ ኮማንዶ ባስመረቀበት ዕለት የንጉስ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድም በየጋግና ቀበሌ ከሚኖሩ የማሕበረሰብ ክፍሎች ጋር ሠፊ የሆነ ህዝባዊ ውይይት አካሒዷል፡፡
በውይይቱ በርካታ ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን በዋናነትም
👉አሁናዊ የአማራ ትግል ቁመናን አስመልክቶ ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡
👉ፋኖ ከህዝባችን ጋር ሊኖረው በሚገባው መስተጋብር ላይ በጥልቅ ተወያይተናል:
👉 በቀበሌ ደረጃ የፍትህ አሠጣጥ ሁኔታ ምን ይመስላል ወደፊትስ እንዴት መሰራት አለበት የሚሉት እና ሌሎች ጉዳዮች በጥልቀት ተወያይተን የወደፊት አቅጣጫም አስቀምጠናል።
በውይይቱ የብርጌዱ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ አንሙት አባቴነህ፣ የብርጌዱ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ይታያል ጌታ ፣ የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ባዬ ሽፈራውና የብርጌዱ ም/ሰብሳቢ ፋኖ ምንይዋብ አንበሉ የተገኙ ሲሆን ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ ሠፊ የሆነ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትንታኔዎች ተሠጥተዋል ሲል የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ፋኖ ባዬ ሽፈራው ( ቀኜ) ገልጿል።
💥ሕዝባዊ ስብሰባ በበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ማይ አንገታም ቀበሌ!
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ከማይ አንገታም ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ።
በውይይቱ የክፍለ ጦሩ የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ አረፋይኔ ተጎድና የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊው ፋኖ አበባየሁ ባንታምላክ የተገኙ ሲሆን በአማራ ትግል መሠረታዊ ጉዳዮችና የትግላችንን አሁናዊ ልዕልና አስመልክቶ ለማሕበረሰቡ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የቀበሌ መዋቅሩንም በመፈተሽ የአመራር ሪፎርም ሰርተዋል።
ሁሉ ነገሩን ሳይሰስት ለሚሰጠን ሕዝባችን ያለንን እንሰጠዋለን!
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሕዝባችን!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ6ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
13/ዐ1/2018 ዓ.ም
