ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 387
المشتركون
-324 ساعات
+2587 أيام
+1 43630 أيام
أرشيف المشاركات
+2
ሕዝብ ላቡን ጠብ አድርጎ የሰራቸው የቀበሌ ተቋማት በአረመኔው ሰራዊት እንዲህ እየነደዱ ነው። በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ወርቅማ ቀበሌ የሚገኘውን የቀበሌ አዳራሽ በትናንትናው ዕለት የአብይ አህመድ ሰራዊት እንዲህ አውድሞታል። ይህ ጨካኝ አንባገነን ስርዓት  አማራንና የአማራ የሆነውን ሁሉ እያጠፋ ነው ያለው ። ላለመጥፋት በሚደረገው የህልውና ትግል ሁሉም አማራ የራሱን ድርሻ ሊወጣ ይገባል።

=====ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል====== ################################### ድርጅታችን አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ይፋ ባደረገው አዲስ መዋቅር መሰረት በአዲስ በተደራጀው 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለ ጦር እና በስሩ ባሉት የወረዳ ጊዜያዊ መስተዳድሮች የድርጅታችንን ቁመና ፣ አዲሱን መዋቅር ማስረዳትና ማደራጀት እንዲሁም ህዝባችንን ማወያየት ቀጥለናል። ዛሬ በቀን 07/03/2018 ዓ/ም በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ነባርና በቅርቡ ከጠላት ነፃ የወጡ ሰኞ ገበያ ንዑስ ወረዳንና እኔሳ ቀበሌን  የጊዜያዊ መንግስቱ አመራሮች በቀጠና በመከፋፈል አወያይተናል። በውይይታችንም፦ የቀበሌ መዋቅር የሌላቸውን አዋቅረናል፣ የድርጅታችንን ወቅታዊ ቁመና አስረድተናል፣ የግል ታጣቂውን በሻለቃ አደራጅተን የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅና በወል  መሬትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን የመጨረሻ እልባት ሰጠናል፤ ማህበረሰቡም አጥቶት የነበረውን ነፃነቱን በማግኘቱ ደስታውን ገልፆ ይህንን ነፃነት ለማፅናት የትኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርግና መስዋዕትነትንም ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ ገልፆልናል። አማራ ያሸንፋል!! ድል ለአማራ ፋኖ! ! የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሚዲያና ኮምኒኬሽን ሀላፊ ፋኖ ይበልጣል ጥሩነህ

⛔️በቀን14/03/2018 በሰው በላው የአብይ አህመድ ወራሪ ሀይል የተጨፈጨፉ ንጹሀን ስም ዝርዝር‼️ =========== 1.አቶ ደሴ ካሳ፤ እድሜ 60፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ ድማማ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር 2.አቶ ወርቄ ገረም፤ ዕድሜ 45፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ ድማማ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር 3.ተመስገን በላይነህ፤ ዕድሜ 30፤የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር 4.ዋሴ መኩሪያ፤ ዕድሜ 26፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር 5. አለኸኝ ክንዴ፤ ዕድሜ 27፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር 6. አማኑኤል አዲስ፤ ዕድሜ 20፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር 7. ቻሌ ፈንታሁን፤ ዕድሜ 24፤ የትውልድ ቦታ ቲሊሊ ወረዳ አሽፋ ማርያም ቀበሌ ስራ ባጃጅ ሹፌር

#የእነማይ_ወረዳጊዜያዊ_መንግስት_የህዝብ #ውይይቶችንአካሂዷል። ህዳር 15/2018 ዓ.ም የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት በእነማይ ወረዳ ዲማ ከተማና እና ደብረፅሞና ቀበሌ ማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት በማካሄድ:- ➣የቀበሌ ሊቀመንበር ➣የቀበሌ ም/ል ሊቀመንበር ➣የቀበሌ ፀሀፊ ➣የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ (3) ➣የቀበሌ ገቢና ሀብት አሰባሰብ ➢የቀበሌ አስተዳደር ፀጥታ ➢የቀበሌ ወጣት ጉዳይ ➣የቀበሌ የሀገር ሽማግሌ (7) ➣የቀበሌ የጎጥ ሽማግሌ (3) ህዝብ ያመነባቸው አዋቅሯል። የውይይት መድረኩን የመሩት የ201ኛ ኮር አመራሮች እና የጊ/መንግስትአመራሮች ሲሆኑ በመበመድርኩ ለተገኙት የህብረተሰብ ክፍል አገዛዙ አረመኔው ሰራዊት በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ድርጅቱ ያለበትን ወቅታዊ ቁመና በተመለከተ ሰፊ የፖለቲካ ግንዛቤ በመስጠት ቴዎድሮስ ዕዝ እያደረገ ያለውን የጊ/መንግስት አደረጃጀት ሰረተዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ! ህዳር 15/2018 ዓ.ም ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

የአቋም መግለጫ ==========+ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ለመላው የአማራ ህዝብ ፣ ለመላው የትግሉ ደጋፊ እና ለመላው የአማራ ፋኖ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋብኃ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጅ አዝማች ኮር በአምስት ክፍለ ጦሮች  ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ በታላቅ ተጋድሎ ጎዳና ይገኛል። ፋሺስት ፣ ወራሪው የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ሁሉን ዓቀፍ መዋቅራዊ ግፍ እና በሌሎችም ብሔርብሔረሰቦች ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ እያደረሰ ይገኛል። በአማራ ህዝብ ላይ ዘርን መሠረት ያደረገውን ጭፍጨፋ የአማራ ህዝብ እንደህዝብ  በሠላማዊ መንገድ ጭፍጨፋዊ እንዲቆም ቢጠይቅም አገዛዙ ጭፍጨፋውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ጠያቂውን ደግሞ በአፈሙዝ ምላሽ ሰጥቶታል። ሁሉም የሰላማዊ መንገድ አማራጮች በአገዛዙ መዘጋታቸውን ያየው ፋኖ ዱር ቤቴ በማለት ጨፍጫፊዎችን በመጡበት አግባብ እያስተናገደ ይገኛል። የአፋብኃ እና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለኮርና ለክፍለ ጦር አመራሮች ከጥቅምት 20/02/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 13/03/2018 ዓ /ም ለተከታታይ 23 ቀን ሲሰጥ የቆየው አጫጭር ተቋማዊ ስልጠናዎች ማለትም ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ  ስልጠናዎችን የወሰድን ሲሆን እንዲሁም ከዚህ በፊት በነበረ የትግል ጉዟችን የነበሩትን ጠንካራ እና ተግዳሮቶቻችንን በመገምገም  ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ፣ ከአፋሪካ እና ከዓለም ዓቀፍ ሀገራት ጋር የሠራውን ዲፖሎማሲ በመገምገም እና በቀጣይ ለምናደርጋቸው ጉዟችንን አቅጣጫ በመስጠት ባለ 9 ነጥብ የአቋም በመግለጫ በማውጣት መድረኩ ተጠናቋል። 1ኛ. እኛ የኮርና የክፍለ ጦር አመራሮች በአፋብኃ እና በዕዝ ከፍተኛ አመራሮች የተሠጡንን ተቋማዊ ግዴታዎች፣ ተልዕኮዎች ለመፈፀም እና ድርጅታችንን አፋብኃን ለመጠበቅ በሙሉ ዝግጅት ላይ እንገኛለን። አጠናክረንም እንቀጥላለን። 2ኛ. ከፍተኞ አመራሮቹ በተከታታይ ሲሰጡት የሰነበቱትን ስልጠናዎች እስከ ብርጌድ አመራሮች ፣ ሻለቃ አመራሮች እና አባላት በማድረስ አንድ አይነት አመለካከት ፣ ግንዛቤ እና እውቀት እንዲኖረን እናደርጋለን። 3ኛ. ፋሺስቱ፣ ወራሪው ፣ ዘራፊው የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን መዋቅራዊ የዘር ማፅዳት ዘመቻ ከህዝባችን ጋር በመሆን እኛ ፋኖዎች እንመክታለን። 4ኛ. ደመኛ ጠላቶቻችን ፋኖ ገዳይ ነው፣ ፋኖ ዘራፊ ነው፣ ሌሎች ብሔርብሔረሰቦችን ገፊ ነው ፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂ ነው እያለ የሚሠራውን ትርክት የሀሰት ትርክት ሲሆን በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረው ሁሉን ዓቀፍ ወረራ በመግደልና በማፈናቀል ሌሎችም ብሔርብሔረሰቦች በእቅድ የሚያስቀጥልና ራሱ ገዳይ መሆኑ የጊዜ ጉዳይ እንጅ በራሱ ጊዜ ይገለጣል። ስለዚህ ይሄን ስርዓት ከስረ መሠረቱ ነቅሎ ለመጣል ከፋኖ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እያስተላለፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል ዓይን የሚያይ  ስርዓተ መንግስት እናቆማለን። 5ኛ. በፋሺስቱ፣ በወራሪው፣ በዘራፊው የብልፅግና አገዛዝ መዋቅር ውስጥ እያገለገላችሁ የምትገኙ ከተራ አባል እስከ ላይኛው ወታደራዊ እርከን ያላችሁ ከህዝባችሁ ይልቅ ለጊዜአዊ ጥቅም ብላችሁ ባንዳነትን የመረጣችሁ ከዚህ በፊት ባደረግንላችሁ ጥሪ መሠረት በርካቶች  ፋኖን ተቀላቅላችሁ እየተገላችሁ ያላችሁ ሲሆን አሁንም በጠላት መዋቅር ውስጥ ያላችሁ የበደላችሁትን ህዝብ ለመካስ ፋኖን ተቀላቅላችሁ እንድትታገሉ ጥሪ እናስተላልፋለን። 6ኛ. በውጭና በሀገር ውስጥ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የትግላችን ደጋፊዎች በሙሉ የፋኖ ትግል በአጭር ጊዜ ይቋጭ ዘንድ በፋይናንስ፣ በዲፕሎማሲ እና በእውቀት ሽግግር እንድታግዙ ጥሪ እናስተላልፋለን። 7ኛ. ለሚዲያ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ሙሁራኖች፣ አንቂዎች ፣  ለሚዲያ ተጠቃሚዎች በሙሉ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መዋቅራዊ  ሰብአዊ ፣ ቁሳዊ  እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በአንድነት ሁናችሁ  እንድታሳውቁ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን። 8ኛ. ከወራሪው፣ ከጨፍጫፊው፣ ከዘራፊው የብልፅግና አገዛዝ የፀጥታ መዋቅርና የፖለቲካ ክንፍ  ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እና ተልዕኮ በመቀበል በየአውራ መንገዶች ህዝባችንን  የምትዘርፉ፣ የምታግቱ፣ የምታንገላቱ በውስጣችን ያላችሁ እንዲሁም " አፈንጋጭ" የሚል የዳቦ ስም ያላችሁ የመዋቅራችን  የመረጃ ክፍል  ባከሄደው ጥናት አረጋግጧል። በትልልቅ ከተሞች ማለትም በባህርዳር በጎንደር ከተማ ሳይቀር ከአገዛዙ ጋር ተናባችሁ የእገታ፣ የዘረፋ፣ የግድያ ወንጀል እንደሚፈፅሙ ተደርሶባቸዋል። ይህን የምታደርጉ  አካሎች ከፋሺስቱ አገዛዝ በላይ ጠላት መሆናችሁን በማመን ከድርጊታችሁ በማትታቀቡት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን። 9ኛ. በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ አንድ ጎጆ እንዲሠራ እንጅ ሁለት አማራ ስለሌለ እንድ ቤት እንድንገነባ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን። ድል ለአማራ ህዝብ ድል  ለአማራ ለፋኖ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር

ግባ በለው የአገዛዙ ሰራዊት እየተናደ ነው ፩ ቻላቸው ድረስ----መከላከያ ፪ ጌትነት ታደሰ ----መከላከያ አባላት ፫ እንዳላማው ፈንቴ ---ሚሊሻ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ መሽጎ ከሚገኘው ከ59ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት የአረመኔውን ስርዓት በመክዳት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ዮሐንስ አለማየሁ ሻለቃን ተቀላቅለዋል

​⚠️ WARNING: This video should not be viewed by children, pregnant mothers, or anyone who is easily startled/nervous.
​Extremely Tragic Massacre❗ ​Six innocent people were killed by the ruling regime's soldiers in Agut Kebele, Sekela Woreda! ​The anti-Amhara Prosperity Party group's Defense Force abducted six innocent people from Agut Kebele in Sekela Woreda and brutally murdered them inside the compound of Ditilim School in the Kebele. They did this in a cruel manner, after cutting off their genitals and tongues. ​The fate of all Amharas is this. ​When you delve into this video, there is a narration of those who found the bodies. Since this is full evidence, I urge those involved in advocacy work to inform the international community. ​Let this be recorded for history‼️ May God have mercy on the souls of our people who were massacred unjustly 😭 ​We are following the Fano battlefronts in all four directions and are working 24 hours a day. Join us using the Telegram link below: ​https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ማሳሰቢያ:- ይህን ቪድዮ ህጻናት ወይም እርጉዝ እናቶች እንዱሁም ድንጉጥ የሆነ ሰዉ እንዳያየዉ። እጅግ_አሳዛኝ_ጭፍጨፋ❗ በሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ስድስት ንፁኋን በአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ! የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን መከላከያ ሰራዊት ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ስድስት ንፁኃንን አፍኖ በመውሰ በቀበሌው ድጥልም ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ፣ ብልታቸውንና ምላሳቸውን ከቆረጠ በኋላ ገድሏቸዋል። የሁሉም አማራ እጣ ፋንታ ይህ ይህ ነዉ። ይህ ቪድዮ በዉስጡ ገባ ስትሉ ሬሳቸዉን ያገኙ ንግግር አለ። ሙሉ ማስረጃ ስለሆነ በአድቮኬሲ ስራ ለተሰማራችሁ ለአለም አቀፋ ህብረተሰብ እንድታሳዉቁ አደራ እላለሁ። ለታሪክ_ይቀመጥ‼️ በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ነፍስ ይማር😭

#እስከመቸ_ሁሉም_አማራ_እራሱን_ማደራጀት_እና #መመከት_አለብን መተከል ቡለን ወረዳ ላይ 50 የሚደርሱ ንፁኋኖች ተገደሉ!‼️ በቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ በኩጂ በተባለ አከባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በፈፀ
+8
#እስከመቸ_ሁሉም_አማራ_እራሱን_ማደራጀት_እና #መመከት_አለብን መተከል ቡለን ወረዳ ላይ 50 የሚደርሱ ንፁኋኖች ተገደሉ!‼️ በቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ በኩጂ በተባለ አከባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በፈፀሙት የጅምላ ግድያ 50 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች መገደላቸው ተሰምቷል። በአከባቢው የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ከሁለት ቀናት በፊት አከባቢውን ለቀው ከመውጣታቸው ነው ጥቃቱ የተፈፀመው የሚሉት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ታጣቂዎቹ ከአገዛዙ ሰዎች ጋር በመናበብ የፈፀሙት የጅምላ እልቂት ነው ብለዋል። የጅምላ እልቂት ጥቃቱ የተከፈተው ትናንት ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ሲሆን፡ በዚህም እስካሁን ባለው 50 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል፡ ቀሪው የሕብረተሰብ ክፍልም ሕይወቱን ለማትረፍ ሽሽት ላይ ነው ተብሏል። በዚህ አከባቢ ከዓመታት በፊት የጅምላ ግድያ ተፈጽሞ የሰው ልጅ በግሬደር ታፍሶ የተቀበረበት ልብ ሰባሪ ክስተት አይዘነጋም።

አፋብኃ/ሰሜን አማራ ቀጠና/ በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር ጥልቅ ውይይቱና ስልጠናው በስኬት ተጠናቀቀ❗ የአራተኛ ደጃዝማች ኮር አመራሮችና በኮሩ ስር የሚገኙ የስድስት ክፍለ ጦር አመራሮች በመሪዎች በጥልቀት ሰልጥነው ተልዕኮ ቆጥረው ተቀብለዋል። በአርበኛ ሀብቴ ወልዴና በአርበኛ ሲሳይ አሸብር የተሰናዳው ደጃዝማች ፬ኛ ኮር እና በስሩ ያሉ ክ/ጦሮች በሙሉ ለላቀ ግዳጅ ሰልጥነው ለአዲስ ተልዕኮ ተዘጋጅተዋል። አፋብኃ ሰሜን አማራ በላይ ዕዝ ደጃዝማች 4ኛ ኮር የደረሰን መግለጫ በነገው ዕለት የሚቀርብ ሁኖ ጥልቅ ውይይቱና ስልጠናው በስኬት ተጠናቋል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን ቋሚ ምሥል፦ አርበኛ ኃብቴ ወልዴ፣ አርበኛ ሲሳይ አሸብር እና የ፬ኛ ኮር ውይይት ተሳታፊ ሥራ አሥፈጻሚ የነጻነት ተፋላሚ አምሐሮች ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

ከእግረኛ ሰራዊት ወደ መደበኛ የልዮ ኮማንዶ ሰራዊት እየተቀየረ ይገኛል። እንደ አማራ የመጣብን የህልውና አዳጋ ልንቀለብስ የምንችለው የትግሉ መነሻ እና መድረሻ አላማ ጥንቅቅ አድርጎ የሚያውቅ  የፖለቲካዊ ግንዛቤ ያለው በብቃት እና በንቃት የጠላት ሀይል ሊፈረው የሚችል፣ የጠላትን ሀይል በስሙ እና በስራው ሊያስፈራ የሚችል፣ በወታደራዊ ግዳጆች የጠላትን ሀይል መስበር የሚችል ወታደራዊ ብቃት ያለው የሰለጠነ ወታደራዊ ሀይል መገንባት ስንችል ነው። ወታደራዊ ብቃት ያለው የተደራጀ የሰለጠነ ሰራዊት የድርጅቱን መሪዎች እና ድርጅቱን የሚጠብቅ ህዝባችንን የሚያከብር ሰራዊት የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄዎችንን በሙሉ ያስመልሳል። 64ኛ ክፍለ ጦር የሽፈራው ገርባው ልጆች በሸበል በረንታ

ከመሀል ሀገር ሸዋ ምንጃር እስከ ጎንደር ቋራ ዘላቂ አማራዊ አንድነት እና ወንድማዊ ፍቅርን ፍለጋ። በአማራ ህዝብ የትግል ታሪክ ታሪካዊ ተብለው ከሚዘከሩ እውነታዎች ውስጥ ይህ የአንድነት እና ወንድማዊ ግንኙነትን ለመፍጠር ታስቦ የተደረገ እርጅም አድካሚ ጉዞ አንዱ ነው። ለብዙዎቻችን ይህ ጉዞ ከፖለቲካ ፍላጎት በላይ ቤተሰባዊነቱ ያጋድልብናል። አዎ የአማራ ህዝብ የጀመረውን ፖከቲካዊ የእልውና ትግልን የሚመራ አንድ ድርጅት የመፍጠርን አላማ አንግቦ የተደረገ ጉዞ መሆኑን ሳንዘጋ ይህንንም ለማሳካት ከምንም በፊት በመተሳሰብ እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አማራዊ ቤተሰባዎባዊ ትስስር ማስቀደም ግድ ይል ነበር። ለዚህም ከሸዋ የተነሳው በአርበኛ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የተመራው የልዑካን ቡድን ተቀዳሚ አላማው ለዘመናት በአካባቢዎች አጥር ታጥሮ እና ተለያይቶ የኖረውን የአማራ ህዝብ በስልክ በዋትሳፕ የኮንፈረንስ ውይይቶች ሳይሆን የተከፈለው ዋጋ ተከፍሎ የዚህ ትውልድ መሪዎች በአካለ ስጋ በመገናኘት የህዝባችንን ችግሮች ለመፍታት እንደ ህዝብ አንድነቱንም ለማረጋገጥ እንደ አንድ ቤተሰብ አይን ለአይን እየተያየን መወያየት አለብን የሚል ውሳኔ በማሳለፍ ለጉዞ የተነሳው። እንደ ሸዋ የገጠሙን ውስጣዊ የአንድነት ችግሮች እንደ አማራ ችግር መፍጠር የለባቸውም የሰፊው የአማራ ህዝብ አንድነትን ለማረጋገጥ ውስጣዊ ችግሮቻችን እንቅፋት ሆነው ሊያሰናክሉን አይገባም በሚል ታሪካዊ ውሳኔ የወሰነው በኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ የሚመራው አማራ ፋኖ በሸዋ ከብርጌ እና ክፍለጦሮች እስከ ድርጅቱ ስራ አስፈፃሚዎች እና ምክርቤት ተወያይቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ነው። ይህ ውሳኔ በራሱ ታሪካዊ ነው ለአማራነት ያለን ታማኝነት እና ፍቅር ከአካባቢ እንደሚበልጥ የታየበት ውሳኔ ነው። ይህ ውሳኔ በቀድሞ ኣምራ ፋኖ ሻዋ ዕዝ ውስጥ በየደረጃው ከሻለቃ ኣመራሮች እስከ ክፍለጦር ያሉት አመራሮች በጋራ የወሰኑበትም ነው ለዚህም ነው ዛሬ ፋኖ ያዋቀራቸው ህዝባዊ አደረጃጀቶች ሳይቀሩ ሳይቀር አፋብኃን አታጋይ ድርጅት ብሎ በሙሉ ልብ የተቀበለው። ውሳኔውን ተከትሎ ለዚህ ታላቅ ታሪካዊ ጉዞ በአካልም በመንፈስም ዝግጁ የሆነው በኢንጅነር ደስአለኝ ሲያስብሸዋ የተመራው የሸዋ ልዑክ ይህን ታሪካዊ አማራዊ ቤተሰብን እና ዘላቂ አማራዊ አንድነት ጉዞን መነሻውን ከምንጃር ሸንኮራ በማድረግ ትልቁን ሸዋ ከመሃል ሀገር ግማሽ ለግማሽ ሰንጥቆ ጎጃም የመግባት የመጀመሪያ ምዕራፍ ጉዞ ተጀመረ። ይህ ጉዞ አደገኛ የሚባል ጉዞ ነው ከሸዋ ምንጃር እስከ ጎጃም ያለው ጉዞ የመልክዓ ምድሩ አስቸጋሪነት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢ አደገኛ ቀጠናዎችን ማለትም የብልፅግናን የኦነግን የአፋህድም መገኛ ቀጠናዎች ማቋረጥ ግድ ይል ስለነበር እጅግ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ጉዞ በማድረ ያንን የሸዋ መልክዓ ምድር በማቋረጥ ጎጃም ለመግባት ተችሏል..... በዚህ ጉዞ ሂደት ውስጥ የተደከመውን ድካም የተከፈለውን ዋጋ እኔ በምናብ ልፅፈው አልችልም በእካል ዋጋ የከፈሉ የልዑካን ቡድኑ አባላት በራሳቸው አንደበት ቢገለፁት ይበልጥ ትርጉም ስለሚሰጥ ከእነሱ ብንጠብቅ እመርጣለሁ። ዋናው ቁምነገር ይህ ታሪክ ምንም ያህል ብንናገርለት ያማንጠግበው በእኔ ትውልድ ዘመን የተፈፀመ አኩሪ ታሪክ መሆኑን ለዚህም በህዝብም ሆነ በፈጣሪ የተመረጡ የታሪኩ ፈፃሚዎችን እንደ አንድ ግለሰብ ላማክባር ለማስገን እና ይህ ታሪክ እንዳይረሳም ለማስታወስ ነው። በቀጣይ በራሳችን መረዳት ከዘመቻ ምኒልክ እስከ ብለን እዚሁ መንደር ላይ ለሚሞሪ የምትሆን ነገር እናስቃምጣለን!!

አዳኙ ፋኖ የአሳምነው ልጅ ✊ አማራ ማለት ለኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት፣ የቋንቋ ድልድይ፣ የነፃነት ጠበቃ፣ የሃይማኖትና የባህል ማዕከል ነው። የብዙኃን መግባቢያ የሆነ ቋንቋን በማፍራት፣ የሀገር ሉዓላ
አዳኙ ፋኖ የአሳምነው ልጅ ✊ አማራ ማለት ለኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት፣ የቋንቋ ድልድይ፣ የነፃነት ጠበቃ፣ የሃይማኖትና የባህል ማዕከል ነው። የብዙኃን መግባቢያ የሆነ ቋንቋን በማፍራት፣ የሀገር ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ እና የኢትዮጵያን ታላላቅ ቅርስ በመጠበቅ ለዚህች ውድ አገር የማይናቅ ውለታ የፈፀመ ሕዝብ ነው። ዴቭ ከትግል ሚዳ በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

⚫️ዘር አጥፊው አረመኔው የመከላከያ ሃይል ስድስት ንፁሃንን ምላስና ብልት ቆርጦ ረሽነ‼ በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በተደረገ ተጋድሎ ብዛት ያላቸዉ ጥቁር ክላሾችና ተተኳሽ ሲማረኩ፣ከሀያ በላይ የአሸባሪው ቡድን አባላት ተወግደዋል ። ዛሬ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ከሰከላና ከቡሬ በሁለት አቅጣጫ በለሊቱ በመንቀሳቀስ ለማፈን የሞከረዉ አረመኔ ቡድን በመልሶ ከበባ ተቀጥቅጧል። ከአጉት እስከ አሽፋ በዘለቀዉ አዉደ ዉጊያ ጨፍጫፊና ዘራፊው መንግስታዊ ቡድን ሙትና ቁስለኛው እያዝረከረከ፣ በየ ጥሻው እየቀበራቸዉ፣ ያሰበዉን ሳያሳካ የጀግናው ፋኖን ምት መቋቋም ባለመቻሉ የጣለዉን እየጣለ ዉንብሪ ማሪያም ተብላ ምትጠራዉ ቅድስት ቤተክርስቲያን ዉስጥ በመመሸግ እንዳይወጣ ሁኖ ተከቦ ይገኛል። በአጽኖት አስበው፣ ትርፍና ኪሳራ አገናዝበው የሚንቀሳቀሱት የግዙፉ 44ኛ ክፍለ ጦር ጀግኖች ጥበብ አማካኝነት ተስቦ የገባዉ ዘራፊ ቡድን በከበባ ተቀጥቅጦ በደርዘን የሚቆጠር ክላሽ አስረክቦ 21 ሬሳና ብዛት ያላቸዉ ቁስለኞቹን ተሸክሞ በቅድስቷ ቤተክርስቲያን መሽጎ ይገኛል። የጀግኖቹን ምት መቋቋም ያልቻለዉ ወንበዴ ቡድን በየአካባቢው ያገኛቸዉን ንፁሐን አርሶ አደር እና የከተማ ወጣቶችን አፍኖ በመዉሰድ ስድስቶችን አይናቸዉን በማጥፋት፣ ምላሳቸዉንና ብልታቸዉን በመቁረጥ አሰቃቄ በሆነ ሁኔታ ረሽኗቸዋል። "በተመታን ቁጥር አማራን የሆነዉን ሁሉ ህፃን አዛውን ሳንለይ እንመታለን" እያለ ሲያውጅ የከረመዉ አረመኔ ቡድን፤ ፎክሮ ወደ ፋኖ ቀጠና ፋኖን ለማጥቃት ቢመጣም ውጤቱ አባሉን እያንጠባጠበ ፣ ንብረቱን እያስረከበ ንፁሃን ላይ ጉልበቱን በማሳየት  የለመደዉን የዘር ማጥፋት እርምጃዉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። #ትግላችን_እስከ_ቀራኒዮ_ድላችን_4ኪሎ_ይዘልቃል‼ ©የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኘነት ፋኖ አለበል አወቀ። 14/ዐ3/2018 ዓ.ም