ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 208
المشتركون
+18224 ساعات
+2627 أيام
+63730 أيام
أرشيف المشاركات
አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ጉዳት አደረሱ!!      64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ በመነሳት ወደ ደጀን ከተማ በጉዞ ላይ የነበር የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ ላይ በጣሉት ደፈጣ በየዕዱውኃ አካባቢ የምጥጭ ጎጥ ላይ #አበዛው ደምል እስከ ወዳኛው ሲሸኝ ስማቸውን በውል ያላወቅናቸው የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል። በሸበል በረንታ የዕድውኃ አካባቢው በተጣለው ደፈጣ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በየምጥች ጎጥ:- 1ኛ. ማሙሽ ይበልጣል የተባለ ንፁሃን አርሶ አደር በግፍ እረሽኗል። 2ኛ. አቶ አንዳርጌ ጫኔ የድውኃ ነዋሪ 1 በሬ ፣5 ከረጢት የህል ማዳበሪያ፣ የቤት እቃ በሙሉ ወድሟል። 3ኛ.አቶ ዳምጤ ጫኔ ሙሉ ንብረት የቤት እቃ አውድሟል 4ኛ. ጌታሰው ዳምጤ የተባለ ግለሰብ እና በሰረግ ላይ የነበረ የሙሽራ ቤተሰቦች እየደበደቡ አስረዋል። በየምጥች ጎጥ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍል በመደብደብ የአካል ጉዳት አድርሰዋል። በሌላ መረጃ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም በእነማይ ቀሸምሽ ቀበሌ በአገዛዙ ዘራፊ ሰራዊት ከተዘረፈባቸው ንፁሀን መካከል:- 1ኛ. ፋኖ ሀብቴ ቢሴ 3 ኩንታል ሽንብራ፣ 2 ማዳበረያ ድቄት፣ ፋራሽ 2ኛ. ፋኖ ካሳሁን ዳኜ 20 ኩንታል ጤፍ፣10 ኩንታል ስንዴ እና ሙሉ የቤት ዕቃ 3ኛ. 1 ሞተር ዘረፈዋል። 4ኛ. በቀሸምሽ ቀበሌ የንፁሀን አርሶ አደሮችን ቤት በመግባት ሌጥ እና ዱቄት ሳይቀር ደፍተዋል። በቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችንና መገልገያ እቃዎችን አውድመዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአፋብን ቴዎድሮስ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ ቀሸምሽ ቀበሌ የገባው የጠላት ኃይል ለማስወጣት በጠልማ ቀበሌ ከሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ውጊያ በመክፈት በቀሸምሽ ቀበሌ ለዝርፊያ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት አስወጥቷል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ጉዳት አደረሱ!!      64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ በመነሳት ወደ ደጀን ከተማ በጉዞ ላይ የነበር የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ ላይ በጣሉት ደፈጣ በየዕዱውኃ አካባቢ የምጥጭ ጎጥ ላይ #አበዛው ደምል እስከ ወዳኛው ሲሸኝ ስማቸውን በውል ያላወቅናቸው የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል። በሸበል በረንታ የዕድውኃ አካባቢው በተጣለው ደፈጣ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በየምጥች ጎጥ:- 1ኛ. ማሙሽ ይበልጣል የተባለ ንፁሃን አርሶ አደር በግፍ እረሽኗል። 2ኛ. አቶ አንዳርጌ ጫኔ የድውኃ ነዋሪ 1 በሬ ፣5 ከረጢት የህል ማዳበሪያ፣ የቤት እቃ በሙሉ ወድሟል። 3ኛ.አቶ ዳምጤ ጫኔ ሙሉ ንብረት የቤት እቃ አውድሟል 4ኛ. ጌታሰው ዳምጤ የተባለ ግለሰብ እና በሰረግ ላይ የነበረ የሙሽራ ቤተሰቦች እየደበደቡ አስረዋል። በየምጥች ጎጥ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍል በመደብደብ የአካል ጉዳት አድርሰዋል። በሌላ መረጃ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም በእነማይ ቀሸምሽ ቀበሌ በአገዛዙ ዘራፊ ሰራዊት ከተዘረፈባቸው ንፁሀን መካከል:- 1ኛ. ፋኖ ሀብቴ ቢሴ 3 ኩንታል ሽንብራ፣ 2 ማዳበረያ ድቄት፣ ፋራሽ 2ኛ. ፋኖ ካሳሁን ዳኜ 20 ኩንታል ጤፍ፣10 ኩንታል ስንዴ እና ሙሉ የቤት ዕቃ 3ኛ. 1 ሞተር ዘረፈዋል። 4ኛ. በቀሸምሽ ቀበሌ የንፁሀን አርሶ አደሮችን ቤት በመግባት ሌጥ እና ዱቄት ሳይቀር ደፍተዋል። በቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችንና መገልገያ እቃዎችን አውድመዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአፋብን ቴዎድሮስ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ ቀሸምሽ ቀበሌ የገባው የጠላት ኃይል ለማስወጣት በጠልማ ቀበሌ ከሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ውጊያ በመክፈት በቀሸምሽ ቀበሌ ለዝርፊያ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት አስወጥቷል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

በተለያዩ መዝገቦች ተካተው በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ፍ/ቤት ቀርበዋል ፤ ተከሳሽ ተመስገን አቤ ተከላከል ተብሏል። በተለያዩ መዝገቦች ተካተው በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ሚያዝያ 15/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። አማራነትን እና ፋኖነትን እንደ ወንጀል በቆጠረው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በሽብር ወንጀል ተከሰው በግፍ እስር ላይ ከሚገኙት መካከል አንዱ የሆነው ተከሳሽ ተመስገን አቤ ጥፋተኛ በሚል ተከላከል ተብሏል። መዝገቡ የቀጠረው የዐቃቤ ሕግ ምስክር እና የሰነድ ማስረጃ አስተያየትን መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ችሎቱ ተከሳሹን በሁለት ክሶች ጥፋተኛ በማለት በአንቀጽ 3 (2) ተከላከል ብሎታል። በሽብር እና በሕገ ወጥ መታወቂያ ይዞ መገኘት በሚሉ ክሶች ነው ተከላከል ያለው። ተከሳሹ አሉኝ ያላቸውን አስር ተከላካይ ምስክሮችን ሀምሌ 8 እና 9/2018 አቅርቦ እንዲያስመሰክር ሲል ቀጠሮ ተሰጥቷል። አካሉ ላይ ጉዳት የገጠመው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ሽፍን ጫማ እንዲገባለት ፍ/ቤቱ ያዘዘለት ቢሆንም ማ/ቤቱ ተፈጻሚ አለማድረጉ ተገልጧል። በተመሳሳይ የፖለቲካ እስረኛ የኋላሸት ዘነበ በችሎት የተገኘ ሲሆን መዝገቡ የተቀጠረው ተከሳሹ ተከላካይ ምስክሮችን እንዲያሰማ በሚል ነበር። ነገር ግን በማ/ቤት ከሚገኙ ምስክሮች መካከል ተስፋዬ ከበደ ብቻ የቀረበ ሲሆን ሌሎች ምስክሮች ያሉት መንግስታዊ ጦርነት ባልተለየው አማራ ክልል በመሆኑ እና ሀገራዊ ችግር ከሆነው ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ የትራንስፖርት ችግር በመኖሩ ለመምጣት አለመቻላቸው ተገልጧል። በተከሳሽ ጠበቃ አስማማው እንደተገለፀው የችግሩን ስፋት ታሳቢ በማድረግ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። ፍ/ቤቱም ለሀምሌ 7/2018 ቀጠሮ ሰጥቷል። በተያያዘ በግፍ ከታሰሩት መካከል ተከሳሽ ታዴ በቀለም በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ቀርቦ ነበር። ምስክሮች ስላልመጡ ለግንቦት 18/2018 እንዲያስመሰክር ቀጠሮ ተይዞለታል። ©መረጃው የአውሎግሶን አንድነት ነው።

እነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፍ/ቤት ቀርበዋል ፤ የዐቃቤ ሕግ ምስክር እና የሰነድ ማስረጃ ክርክሩን መርምሮ ለመበየን ፍ/ቤቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ ቀጠሮው ለግንቦት 28/2018 ተራዝሟል። እነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ጉዳያቸውን በእስር ቤት ሆነው የሚከታተሉ 16 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች ሚያዝያ 15/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ፍ/ቤት ቀርበዋል። የዐቃቤ ሕግ ምስክር እና የሰነድ ማስረጃ ክርክሩን መርምሮ ለመበየን ፍ/ቤቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ ቀጠሮው ለግንቦት 28/2018 ተራዝሟል። መዝገቡ የተቀጠረው ፦ 1. የዐቃቤ ሕግ ምስክር እና የሰነድ ማስረጃ ክርክርን መርምሮ ብይን ለመስጠት እና 2.የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊ እና ፌደራል ፖሊስ በተከሳሾች ለቀረበባቸው አቤቱታ በችሎት ተገኝተው የሚሰጡትን ምላሽ ለመቀበል ነበር። በእለቱም የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊ በችሎት አልተገኙምም ይልቁንስ የማ/ቤቱ የጥበቃ እና ደህንነት አስተባባሪ መሆናቸውን የገለፁት  ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ወክለው ምላሽ ለመስጠት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም። ችሎቱም የጠራናችሁ የፍ/ቤት ትዕዛዝ እየፈፀማችሁ ስላልሆነ ነው " እርስዎን ግን አልጠራነዎትም ፤ አንፈልግዎትም" ብሏል። ነገር ግን የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ተሻገር አፅንዎት እንዲሰጥልኝ እፈልጋለሁ በሚል በግል ሆስፒታል ተኝተው የልብ ሕክምና እንዲሰጣቸው እና ከታማሚ ልጃቸው ጋር የመገናኘት ጊዜ ጋር በተያያዘ ላነሱት አቤቱታ ኢ/ር ድሪባ አጭር ምላሽ እንዲሰጡበት ተደርጓል። ኢ/ር ድሪባም ለጉዳዩ አዲስ መሆናቸውን ገልፀው የፍ/ቤት ትዕዛዝ እስከደረሰ ድረስ እንደሚያስፈጽሙ ተናግረዋል። ፌደራል ፖሊስ በተወካዩ በኩል ከሰብአዊ መብት ጥሰት እና በተከሳሾች በኩል በኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ላይ ከቀረበው ክስ አንጻር ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጾ ከፊል ተከሳሾች ወደ አባ ሳሙኤል ማ/ቤት የተጫኑ በመሆኑ ገብተን ተከሳሾችን ለማነጋገር እንችል ዘንድ ትዕዛዝ ይሰጥልን ብሏል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ የሚከተለውን ትዕዛዝ ሰጥቷል ፦ 1. የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊ በችሎት ፊት ተገኝተው ምላሽ እንዲሰጡ በድጋሜ ታዟል። 2. ሶስተኛ ተከሳሽ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ተኝተው ለመታከም ይችሉ ዘንድ ማ/ቤቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ፤ 3. ፌደራል ፖሊስ ከሰብአዊ መብት ጥሰት አንጻር እያደረገ ላለው ምርመራ አባ ሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማ/ቤት ከተከሳሾች ጋር ከማገናኘት አንጻር አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ታዟል። 4. ፌደራል ፖሊስ ተከሳሾች ከተወሰደባቸው ንብረት ጋር በተያያዘ ፍ/ቤቱ ሚያዝያ 8/2018 በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ፈጽሞ ምላሹን ለችሎት እንዲያቀርብ ታዟል። 5. 45ኛ ተከሳሽ ደሳለኝ እጅጉ ሕክምናን በተመለከተ ከሰብአዊ መብት ጥሰት አንጻር ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ምርመራ አድርጎ ውጤቱን እንዲያሳውቅ ኢሰመኮ ታዟል። በተያያዘ መሪጌታ በላይ አዳሙ በአባ ሳሙኤል ማ/ቤት እየተስተዋለ ነው ካሉት ከውሃ እና የምግብ አቅርቦት እንዲሁም ከቤተሰብ ግንኙነት ጋር ለተያያዘው ችግር አቤቱታው በጽሁፍ ይግባ መርምረን ትዕዛዝ እንሰጣለን ብሏል ችሎቱ። በመጨረሻም ለቀረቡት አቤቱታዎች የትዕዛዝ አፈጻጸምንና ምላሽን ለመቀበል በሚል ለሚያዝያ 22/2018 እንዲሁም የዐቃቤ ሕግ ምስክር እና የሰነድ ማስረጃ ክርክርን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለግንቦት 28/2018 ቀጠሮ ተይዟል። ©መረጃው የአውሎግሶን አንድነት ነው

#የድልና_የዝግጅት_ብስራት_ከድብ_ፀለምት ​በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር ስር የሚንቀሳቀሰው የቀድሞው ድብ-ፀለምት ክፍለ ጦር ላለፉት ሦስት ሳምንታት በከፍተኛ ትጋት ሲያከናውን የቆየውን ኃይልን የማብቃት፣ የማጥራትና የሬጅመንት አደረጃጀትን የማጠናከር ተግባር በላቀ ውጤት ማጠናቀቁን በዛሬው ዕለት በይፋ አብስሯል። ይህ የወታደራዊ ዝግጅት ምዕራፍ፣ ክፍለ ጦሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ያለውን ቁመና ይበልጥ ያሳደገበትና ድርጅታዊ መዋቅሩን ያደራጀበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል። ​የቀጠናው የዕዝ ግብረ-ኃይል ሰብሳቢ አርበኛ አስምሮ ፈቃዴ ከሥፍራው በሰጡት መረጃ መሠረት ይህ የዝግጅት ሥራ የተከናወነው ሰላማዊ በሆነ ድባብ ብቻ ሳይሆን ከአገዛዙ ኃይል ጋር ፊት ለፊት እየተፋለሙና የጠላትን እንቅስቃሴ እየመቱ በነበረበት ፈታኝ ወቅት ነው ብለዋል። ፋኖዎቹ በአንድ በኩል ራሳቸውን በስልጠናና በአደረጃጀት ሲያበቁ በሌላ በኩል ደግሞ የተጋረጠባቸውን የጠላት ወረራ በመመከት የተሰጣቸውን ድርጅታዊ ተልዕኮ በብቃትና በጽናት መወጣታቸውን አረጋግጠዋል። ​በዚሁ የማጥራትና የማብቃት ሂደት ጎን ለጎን በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የአገዛዙ ሠራዊት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ተገልጿል። አርበኛ አስምሮ ፈቃዴ እንዳረጋገጡት በቅርብ ቀናት ውስጥ በተካሄደው ፍልሚያ ከ80 በላይ የአገዛዙ ሠራዊት አባላት የተደመሰሱ፣ 40 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ የተማረከ ሲሆን ሌሎች ከ12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በወቅቱ እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸውን ማትረፍ ችለዋል። ይህ ድል የክፍለ ጦሩን ወታደራዊ የበላይነትና የአደረጃጀቱን ጥንካሬ በተግባር ያሳየ ሆኗል። ​ተፈጥሮ በሰንሰለታማ ተራራዎችና አስቸጋሪ መልክዓ-ምድሮች የቸረችው የድብ-ፀለምት ቀጠና ለጀግኖቹ ፋኖዎች ሁልጊዜም የድል ሸማን የሚያለብስ የምሽግ ምሰሶ ሆኖ ይታያል። ይህ ድንቅና ግርማ ሞገስ ያለው መልክዓ-ምድር ለጠላት ሲኦል ለነፃነት ታጋዮች ግን የድል አውድማ በመሆን የታሪክ ምስክርነቱን ዛሬም በተጨባጭ እያስመሰከረ ይገኛል። ጎ/ጠ/ግ/በላይ እዝ 208ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

በመከላከያ ሰራዊትና በአድማ ብተና ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ! አሳምነው ዕዝ እየወሰደ ያለውን ጠንካራ እርምጃ ተከትሎ በአገዛዙ ካምፕ ውስጥ በተ
በመከላከያ ሰራዊትና በአድማ ብተና ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ! አሳምነው ዕዝ እየወሰደ ያለውን ጠንካራ እርምጃ ተከትሎ በአገዛዙ ካምፕ ውስጥ በተፈጠረ ከፍተኛ ድንጋጤና አለመተማመን የተነሳ መከላከያ ሰራዊቱና የአድማ ብተና ኃይሉ እርስ በርስ እስከመጨፋጨፍ የደረሰ ማጥ ውስጥ መዘፈቃቸው ተጋልጧል። በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ አርማንያ ዙሪያ በጠላት ካምፕ ውስጥ በተካሄደ የእርስ በእርስ ተኩስ በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል። በተመሣሣይ! የፋኖ ግስጋሴና ፈጣን ማጥቃት ያብረከረካቸውና የበላይ አለቆቻቸው የሚሰጧቸውን <ሕዝብ ጠል ተልዕኮን> የተፀየፉ የአገዛዙ ወታደሮች፡ የጥፋት ቡድኑን በመክዳት ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል።

#እነሆ_ጮማ_ዜና አገዛዙ ፋሽሰቱን ስርዓት በቃን ብለው ጀብድ በመስራት 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀሉ። ሚያዚያ /14/2018 ፍኖተ ሰላም ላይ ከተቀመጠው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልፅግና ስርዓት ሲያገለግሉ የቆዩት ደጀኔ በላይነህ፣አበበ ግዛቸው እና ወርቅነህ የተባሉ ስርዓቱ አማራ ላይ ከሚደረገው ማንነት ተኮርና ጭፍጨፋ ተረድተው ከፍኖ ጋር ሆነን ህዝባቸው ለመካስ በማሰብ ጀብዶ በመስራት ወደ ቆንጆወቹ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ሻለቃ 2 ተቀላቀሉ። በፍኖተ ሰላም አካባቢ የአረመኔውን አገዛዝ ስርዓት ብልፅግና የሚኒሻ ጠርናፊና ዋና መረጃ በመሆን ህዝቡን በመጠቆም ሲያሰቃይ ሲዘርፍ የነበረ ባንዳ ዘላለም ከእነ ቲሙ ከቀኑ 4:30 በጃቢ ጠህናን ወረዳ ልዩ ስሙ ሆዳንሽ ላይ ለደፈጣ በወጡበት ጊዜ ከ109ኛ ኮር በ77ተኛ ክፍለጦር ሻለቃ 2 ጋር በመነጋግር ጥምረት በመስራት መምታት ተችሏል። ጀብደኞቹ እንዳሉት ከሆነ ከተማ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ አማራ ጠሉን ስርዓትን በመደገፍ ከተለያዩ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል ወንጀለኞችን ነፍስ ያጠፉ ወንበዴወችን እንዲሁም አማራን ለማጥፋት የሚሰሩ ሰወች ጋር አብሮ የሚሰራ ቀንደኛ ባንዳ ስለሆኑ እርምጃ ወስደው እነሱ ከያዙት በተጨማሪ የሁለቱን አመራሮች መሳሪያ አንድ 40 ጎራሽ ሁለት ብልፅግና በመደረብ ይዘው የወጡ ሲሆን የ109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለጦር አመራሮች ተቀብለዋቸዋል። አፈሩን ኮንክሪት ያድርግላችሁ ከማለት ውጭ ሌላ ምንስ ልንል እንችላለን። 👉የዐማራ ባንዳ አለበት እዳ🫵🫵🫵 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! አፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ/15/2018

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ በታሪካዊቷ ግሼ ወረዳ በደል ቀበሌ የተጀመረውና መላውን ቀጠና ያነቃነቀው የአፋብን ወንድማማች ዕዞች የትግል ጉዞ ዛሬ አዲስ ምዕራፍ እየተሰራ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል። ባለፈው ሚያዝያ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲተገበር የቆየው ይኸው የመቀናጀት ስትራቴጂ፣ ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀትና በወንድማማችነት ስምምነት ተቋጭቷል። ​​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣ ኮሮችና ክፍለ ጦሮች ዛሬ ባደረጉት ታሪካዊ ስብሰባ፣ ያለፈውን የትግል ጉዞ በመገምገም የወደፊቱን የድል አቅጣጫ ነድፈዋል። ​በዚህም አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር እና ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርአያዕቆብ ፩ኛ ኮር የቡርኬ ደምሴ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አመራሮች በጋራ ባደረጉት ውይይት፣ መርህ አልባ ጥምረቶችን በማራቅ፣ በጓዳዊ መከባበርና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ ፅኑ አንድነት ለመስራት አንድነታችን አፅንተዋል። ​የጋራ ተልዕኮና የትብብር መስኮች ​ሁለቱ ዕዞች ከዛሬ ጀምሮ በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች በተቀናጀ ሁኔታ ለመሥራት ቃል ገብተዋል 1. በፖለቲካዊ አመራር፡ የተቀናጀ የጋራ አቋም መያዝ 2. ​በመረጃ ልውውጥ፡ የጠላትን እንቅስቃሴ በንቃት መከታተል 3. ​በወታደራዊ ዘርፍ፡ በጋራ የሚመሩ ኦፕሬሽኖችን ማከናወን። ​በውይይቱ ላይ የተገኙ ቁልፍ አመራሮች ​በዚህ የቁርጥ ቀን ውይይት ላይ ከሁለቱም ወገን የተሳተፉት አመራሮች ዝርዝር የሚከተለው ነው፡ ​ አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ (104ኛ ኮር) ​ 1. አርበኛ እንዳሻው ጌታሁን (ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ) ​ 2. አርበኛ ሲሳይ ሳተናው (ም/ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ) 3. ​አርበኛ ፶ አለቃ ሞላ አባተ (ም/ወታደራዊ አዛዥ) 4. ​አርበኛ ጌታቸው (የዘመቻ ኃላፊ) 5. ​አርበኛ ሱልጣን የሱፍ (የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ) 6. ​እንዲሁም አርበኛ ዮሐንስ ከተማ፣ አርበኛ ፲ አለቃ እያሱ፣ አርበኛ መላኩ እና አርበኛ ሙሉቀን አያልነህ በስፍራው ተገኝተዋል። ​ ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከአሳምነው ዕዝ 1. ​ንጉስ ይመሩ (የአባላት መብትና ምርኮኛ አያያዝ ኃላፊ) 2. ​ታደሰ ዳምጠው (የፋይናንስ መምሪያ ም/ኃላፊ) 3. ​ሱራፌል ስለሺ ​ከዓፄ ዘርአያዕቆብ ፩ኛ ኮር 1. ​ተስፋዬ አለሙ (የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ) 2. ​አበበ ጥላሁን (የኮር ዘመቻ መሪ) 3. ​ሀብታሙ መሳፍንት (የኮር ሕግ ክፍል ተጠሪ) ​ እነዚህ አመራሮች በመገኘት ይህ ስብሰባ፣ የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያሳይ መሆኑን በጋራ ገልፀዋል።። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ !!!! ​ድላችን በተባበረ ክንዳችን! ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም

ከ80 በላይ ጠላት ተደመሰሰ!!     አፋብን ጎ/ጠ/ግ/በላይ ዕዝ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የቀድሞው ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር (የአሁኑ 208ኛ) ኮር ድብ ጠለምት ተከዜ ክ/ጦር በዛሪማ ከተማ አቅራቢያ የአረመኔውን ሰራዊት በመምታት ድል አስመዝግቧል። ከዛሪማ ብስኒት ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ሰራዊት ላይ የታቀደ ጥቃት የሰነዘሩት የድብ ጠለምት ሬጅመንት 1 እና ሬጅመንት 2 በጥምረት በወሰዱት ቆራጥ የድምሰሳ ውጊያ .... ➧80 የተደመሰሰ ➧40 የተማረከ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ➧28 ሚሊሻ ፈርሶ እጅ ሰቷል ➧15 እጅ ሰቶ የተማረከ ➧ከ5 በላይ የቡድን መሳሪያ እና ቁጥሩ በርካታ ጠላት በድንጋጤ በአቅራቢያ በነበረ ጥልቅ ገደል ገብቷል። ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም በድጋሜ የደረሰበትን የስነ ልቦና ስብራት ለማካካስ በማለም ከደባርቅና ዛሪማ ተጨማሪ ኃይል በማንቀሳቀስ ወደ ዛሪማ ዙሪያ አምበራና መናፈሻ የደረሰው የጠላት ሰራዊት የደረሰበትን ምት መቋቋም ባለመቻሉ ወደ መጣበት አቅጣጫ ሸሽቷል።አካባቢው በሰራዊታችን እጅ ገብቷል።      ህልውናችን በአርበኝነታችን!!           ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

የጠላት ሀይል መፍረሱ ቀጥሏል እየመጡ ነው እኛም እየተቀበልናቸው ነው!! ጂጋ ከተማ ልዩ ስሙ ቁልቢጥ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልፅግና ስርዓት ሲያገለግሉ የቆዩት ግርማው ደ
+2
የጠላት ሀይል መፍረሱ ቀጥሏል እየመጡ ነው እኛም እየተቀበልናቸው ነው!! ጂጋ ከተማ ልዩ ስሙ ቁልቢጥ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልፅግና ስርዓት ሲያገለግሉ የቆዩት ግርማው ደሳለኝ ፣አሸብር አዲስ እና በቃሉ መለሰ የተባሉ ፋራ ኮማንዶወች አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር ተቀላቅሏል፡፡ አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ/2018

ጥላቶቻችነን ለመዋጋት እንኳን ጫካ ሊላ ቦታ አያስገባም እደ ጎበዝ ፣ ይሄን እያየህ የማትታጠቅ አማራ አማራ አይደለህም እንደ ጌሾ ከትክተው ጣሻላይ ሲጥሉን እያየህ ዝም ፣ አይዞህ ታጠቅ የታጠቀ አይሞ
+3
ጥላቶቻችነን ለመዋጋት እንኳን ጫካ ሊላ ቦታ አያስገባም እደ ጎበዝ ፣ ይሄን እያየህ የማትታጠቅ አማራ አማራ አይደለህም እንደ ጌሾ ከትክተው ጣሻላይ ሲጥሉን እያየህ ዝም ፣ አይዞህ ታጠቅ የታጠቀ አይሞትም ምክንያቱም እራሱን ይጠብቃል Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር!!

በአንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ወከባ ህግን በጣሰ መልኩ ይበልጥ አደገኛ እርምጃ ወዳለበት ደረጃ መሸጋገሩ ተጋለጠ። የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ፣ መሳሪያ የታጠቁ እና በፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪ የመጡ ታጣቂዎች፣ ሲኤምሲ አካባቢ የሚገኘውን የቴዲ አፍሮ የግል ስቱዲዮ እና ቢሮ በኃይል ሰብረው መግባታቸውን የዓይን እማኞች እና የቅርብ ምንጮች አረጋገጡ። ይህ ህገ-ወጥ የኃይል እርምጃ የተፈጸመው ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ወደ ስቱዲዮው ጥሶ ለመግባት የህንጻውን ጥበቃ (ዘበኛ) በከፍተኛ ሁኔታ መደብደባቸው ተገልጿል። የህግ አስከባሪ አካላት መደበኛውን የህግ አግባብ እና የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ወደ ጎን በመተው፣ በምሽት የዜጎችን የስራ ቦታ እና የግል ንብረት በኃይል መስበራቸው የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት እና የዜጎችን ደህንነት ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ድርጊት ሆኗል። ከዚህ የኃይል እርምጃ ባሻገር የጉዳዩን አሳሳቢነት እጅግ ከፍ የሚያደርገው የተሰበረው ቢሮ ይዘት እና የተወሰዱት ንብረቶች ጉዳይ ነው። ይህ ስቱዲዮ ቴዲ አፍሮ እንደ ዋና ቢሮ የሚጠቀምበት፣ የፈጠራ ስራዎቹን የሚያዘጋጅበት፣ ለህዝብ ጆሮ ያልደረሱ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎቹ እና ግጥሞቹ የሚገኙበት፣ እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦቹን የሚጽፍበት እጅግ ሚስጥራዊ እና ጥብቅ የጥበብ ማህደር ነው። በስፍራው በርካታ እና ውድ የሆኑ አዕምሯዊ ንብረቶች የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን በወጡ አዳዲስ መረጃዎች መሰረት ሰብረው የገቡት የፖሊስ አባላት ከስቱዲዮው ውስጥ ሁለት ላፕቶፖችን፣ ስፒከሮችን፣ የሙዚቃ ማቀናበሪያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የስቱዲዮ እቃዎችን ወስደዋል። እነዚህ የተወሰዱት ላፕቶፖች እና ማቀናበሪያ መሳሪያዎች የድምጻዊውን አዳዲስ ስራዎች እና ሚስጥራዊ የጥበብ ማህደሮች የያዙ በመሆናቸው፣ በድምጻዊው አዕምሯዊ ንብረቶች ላይ የተደቀነውን አደጋ በእጅጉ አጉልቶታል። የህግ እና የጥበብ ዘርፍ ተንታኞች ይህንን ክስተት ተራ የንብረት ዝርፊያ ወይም ብርበራ አድርገው አይመለከቱትም። ከሰሞኑ የቴዲ አፍሮ ምክትል ማናጀር እና የቅርብ ጓደኛ የሆኑት አቶ የሱፍ ያሲን ያለምንም ክስ በፖሊስ መታሰራቸውን ተከትሎ፣ አሁን ደግሞ በድምጻዊው የልብ ትርታ በሆነው ስቱዲዮው ላይ የተፈጸመው ይህ ጥቃት፤ ሆን ተብሎ የጥበብ ስራዎቹን ለማሰናከል፣ ያልወጡ ስራዎቹን ለመውሰድ እና በድምጻዊው ላይ ከባድ የስነ-ልቦና ጫና ለመፍጠር የተቀነባበረ ስልታዊ ጥቃት መሆኑን አጥብቀው እየተቹ ይገኛሉ። መንግስት እና የሚመለከታቸው የፌደራል ፖሊስ ኃላፊዎች፣ የጥበብ ባለሙያው አዕምሯዊ ንብረት ላይ ስለተፈጸመው አደጋ እና በህግ ስም ስለተደረገው የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።

ሰበር የድል ዜና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ቡልጋ ክፍለ ጦር አሥደናቂ  እርምጃ በጠላት ወሰደ!!      ሚያዚያ 15/08/2018 ዓ.ም የቡልጋ ክፍለ ጦር የፋኖ ኮማንዶ ተወርዋሪ ሻለቃ ከሌሎች ሻለቃዎች ጋር  በመሆን ሜጢ ወንዝ ላይ የአገዛዙን ሀይል ደመሰሰ።   የአገዛዙ ሀይል ሬሽን ከምንጃር ለመቀበል ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት   መንቀሳቀሱን መረጃ የደረሳቸው የቡልጋ ክፍለ ጦር ሻለቃዎች ቀድመው ቦታውን በመያዝ  በጠላት ሁለት  ተሽከርካሪዎች ላይ  የነበረን ሰራዊት አራግፈውታል።   ይህም ውጊያ  እስከ ቀኑ  6:00 ስዓት የተካሄደ ሲሆን በጠላት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ደርሶበት  ሁለት መኪና ወዲያውኑ ከጥቅም ውጭ ሲሆን  :የአገዛዙ በርካታ ሰራዊትም  ሙት እና ቁሥለኛ ሆኖ፤ በአልሞ ተኳሾቹ የተራገፉትን በመለቃቀም   ወደ መጣበት ተመልሷል።                                                                               ፤      በሌላ ዜና ታፍሶ ወደስርዓቱ ገብቶ የነበረ አንድ የሚሊሻ አባል ከነሙሉ ትጥቁ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ/ዕዝ የአርበኞች ፋኖ ጦርን በሰላም  የተቀላቀለ ሲሆን የአገዛዙን ገመናና በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘረፋ አጋልጧል።    በተመሳሳይ አንድ የአየር ወለድ አባል አፄ ዘርዓያዕቆብ ኮር 7 ለ70 ክፍለጦርን ሲቀላቀል ፤ከአንኮበር 1 የአድማብተና አባል መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለጦርን ከነሙሉ ትጥቋ በሰላም ተቀላቅላለች። በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ አርማንያ ዙሪያ የአማራ ህዝብን በመክዳት የአገዛዙን ወንበር ለማስጠበቅ ወገኑን እየወጋ ያለው አድማ ብተናና ወደ አማራ ግዛት አማራን ለመጨፍጨፍ የገባው የአየር ወለድ ኮማንዶ ትናንት ሚያዚያ 14  እርስበርስ በመዋጋት በርካታ አድማበታኝና አየር ወለድ ሲቆስል ቀላል የማይባል የአገዛዙ ሰራዊት ሞተዋል ‼️           '' ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''          ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን              ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ