ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
2 944
المشتركون
-1024 ساعات
+77 أيام
+37930 أيام
أرشيف المشاركات
የአገዛዙ የኮማንዶ አባል ሙሉ ትጥቅ ይዞ የራንቦ ክፍለጦርን ሲቀላቀል፣ የአብይ አህመድ አረመኒያዊ አራዊት ሰራዊት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የቤተክርስቲያኑን አገልጋይ ካህን በግፍ ገድሏል!!          ቀን 11/9/2018 ዓ.ም ​በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአሳምነው ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር "የራንቦ ክፍለጦር"   የብልፅግናው 104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር የጋንታ መሪ የነበረው የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ ፶ አለቃ ገመቹ ፈይሳ ሙሉ ትጥቁን በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀለ።በዚህም ፶ አለቃ ገመቹ የማለዳዋን ፀሐይ ተገን በማድረግ፦ ​👉,አንድ ዘመናዊ የክላሽንኮቭ መሳሪያ ​👉,አንድ የደረት ትጥቅ፣ 👉 ​150 የክላሽ ጥይቶች፣ ​👉ሶስት የጥይት መጋዘን/ካርታዎች 👉​ሁለት የእጅ ቦምቦችን ይዞ የራንቦ ክፍለጦርን ተቀላቅሏል።​የክፍለጦሩ አመራሮች ለውስጥ አርበኛው ፶ አለቃ ገመቹ ፈይሳ ደማቅና ተገቢውን አቀባበል አድርገውለታል። በሌላ ዜና ብልፅግና መራሹ ስርዓት አማራን የማጥፋት ዘመቻውን ዛሬም ​በንጹሃን ላይ  አሰቃቂ ግድያ  ፈፅሟል። ​ሆኖም በአካባቢው የሚገኘው የብልፅግና የጦር አባላት እየከዱ ፋኖን መቀላቀላቸውን ተከትሎ፣ የመከላከያ 112ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ ሻለቃ በንጹሃን ዜጎች ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ​ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገረማርያም ከሰም ወረዳ፣ ሁለት የአገዛዙ አመራሮች ከድተው ፋኖን መቀላቀላቸውን ተከትሎ፣ የሰራዊቱ አባላት መረጋጋት በማጣታቸው በአካባቢው በሚገኙ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽመዋል። ​ከወረዳው መዲና ሾላገበያ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው "መሲዎሥ" በተባለው ጎጥ፣ እጅግ የተከበሩት የሃይማኖት አባት ቄስ አለማየሁ ሸንቁጤ የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል። ንጋት 11:30 ላይ ለአገልግሎት ወደ ቤተክርስቲያን በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ በቤተክርስቲያኑ ደጃፍ ላይ በአየር ወለድ ኮማንዶ ሰራዊት አባላት አማካኝነት በጩቤ በመውጋትና በጫማ በመረጋገጥ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ተገድለዋል፡፡ አገዛዙ ሽንፈቱን ለመሸፈን በንጹሃን አባቶች ላይ የሚፈጽመው ግፍ ትግሉን አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኝነትን የሚጨምር ነው። ​"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!" "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ​የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!!

▰▶22ኛ ክፍለጦር መሸንቲ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በጠላት ላይ እርምጃ ወሰደ!!! ▰▭▰▭▰▭▰▭▰▭▰▭▰▭ ➛ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር አካል የሆነችው በድሮ የጣናው መ
+1
▰▶22ኛ ክፍለጦር መሸንቲ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በጠላት ላይ እርምጃ ወሰደ!!! ▰▭▰▭▰▭▰▭▰▭▰▭▰▭ ➛ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር አካል የሆነችው በድሮ የጣናው መብረቅ ብርጌድ አደረጃጀት መሸንቲ ሻለቃ በሻለቃ ታርቆ መሪነትና እቅድ አውጭነት በ10,09,2018ዓ.ም ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ሌሊት ሰባት ስዓት መሸንቲ ከተማ ሰርጎ በመግባትና የአጫደርን የጠላት ኬላ ቀድሞ በመያዝ  26 በመሆን በገልባጭ መኪና የመጣውን የአድማ ብተናና የመከላከያ የጠላት ሀይልን "ኦ"  ቅርፅ በማስገባት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ በተወሰደው መብረቃዊ ጥቃትም 18 የጠላት ሀይል እስከወዲያኛው ሲሸኝ አምስቱ ከባድ ቁስለኛ ሲሆን ሶስት የጠላት ሀይል እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። ➛ አፍንጫው ስር በተፈፀመበት ድንገተኛ ጥቃትና በሁኔታው የተደናገጠው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት አመራር ያለ የሌለ ሀይሉን አግበስብሶ በማንቀሳቀስ ቁስለኛና አስከሬኑን ይዞ ተመልሷል። ➛ ሻለቃ ታርቆን ወደ ጠላት ገብቷል(ለአገዛዙ እጁን ሰጧል) በማለት ማህበረሰቡንና ታጋዩን ለማደናገር የብለፅግና የሳይበር ሚሊሻ ፕሮፓጋንዳ መስራቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። ነገር ግን ዛሬ የሰራው አስደማሚ ኦፕሬሽን የአገዛዙን ቅስም የሰበረ ምት ሁኗል። 22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት! ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!   ግንቦት 11,2018 ዓ.ም

በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በእብናት ከተማ ትናንት ግንቦት 10/18 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ባደረገው ተጋድሎ ከ8 በላይ የኮንክሪት ምሽጎችን ሰብሮ አን
በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር በእብናት ከተማ ትናንት ግንቦት 10/18 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ባደረገው ተጋድሎ ከ8 በላይ የኮንክሪት ምሽጎችን ሰብሮ አንፀባራቂድ ድል አስመዝግቧል። አገዛዙ እብናት ከተማ ዙሪያ ከ8 በላይ ኮንክሬት ምሽግ ቢገነባም የ204ኛ ወንዱ አስቻለው ደሴ ኮር አርበኞች ግን የጠላት ምሽግን በመደረማመስ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅተዋል። ከተሰበሩ ምሽጎች ውስጥ ➞ ገብርኤል ምሽግ! ➞ ቋሊሳ መውጫ ምሽግ! ➞ ጥንጁት በር ምሽግ! ➞ ክልቢ አቦ ምሽግ! ➞ ፖሊስ ጣቢያ ምሽግ! ➞ ከንቲባው ምሽግ! ➞ ሀይስኩሉ ምሽግ! ➞ አስተዳደር ምሽግ! ጀብደኞቹ የ204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አርበኞች በጠላት ላይ ከፍተኛ የበላይነት ተቀዳጅተው በርካታድሎችን አስመዝግበዋል። በድሉም የተገኙ ውጤቶች ➞በተሰበሩት ምሽጎች የጠላት ሀይል ከፍተኛ ሙት እና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮ ተደርጓል። ➞ከ45 በላይ ክላሽንኮፍ መሳሪያ 8 ቃታ መሳሪያ ገቢ የሆነ ➞ በርካታ ተተኳሽ ➞ሌሎች በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ገቢ ተደርገዋል። ምንጭ፦ በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!

የጥንቃቄ መልክት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ቀጠና ደብረ ማርቆስ ዙሪያ የቦቅላን ጨምሮ ከንጋቱ 11:00ጀምሮ አገዛዙ የድሮን አሰሳ እያደረገ ስለሆነ የወገን ሃይል የሁልጊዜው ጥንቃቄ አይለያችሁ!!!

የነፃነት ድምፅ አርበኛው ኢሳያስ ደመቀ እና የሸዋው ዕዝ ግስጋሴ!! የአማራ ልጅ... የታሪክ ምስክር፣ የነፃነት ህያው ሀውልት! ንግግሩንና ጀግንነቱን ይቅርና፣ ጠላት ቀና ብሎ መልኩን እንኳ ሲያየው ፍርሃት የሚወርሰው ያ የነፃነት ኃይል ፋኖ ነው! ​ዛሬ በታሪክ ሌላ አዲስ ምዕራፍ እየተፃፈ ነው። ታሪካዊውን ጥሪ ያስተጋባው፣ ሸዋን ከከስም እስከ ማጀቴ፣ አልፎም እስከ አዲስ አበባ ድረስ በአንድ ወጥ ድምፅ የጠራው የነፃነት ድምፅ ጥሪው ተራ ድምፅ አልነበረም፤ የትውልድ መነቃቂያ እንጂ! አማራ ሆይ... አሁን ተነስ! ራስህንና ወገንህን የምታድንበት ወሳኙ ሰዓት አሁን ነው!" የሚለው ይኸው ጥሪ፣ የሸዋውን አንበሳ ከወሎ ጎበዞች፣ ከጎጃም ቁርጠኞችና ከጎንደር ጀግኖች ጋር እጅ ለእጅ አያያዘው። ​ዛሬ አስፈሪና ግዙፍ የነፃነት ኃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራጅቶና ታጥቆ ወደ ፊት እያስገሰገሰ ይገኛል። ይህንን ታሪካዊ ግስጋሴ ከወንድሞቹ ጋር እየመራ ያለው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ #አርበኛ #ኢሳያስ ደመቀ ነው! ​ አሁን ፍልሚያውና ስልቱ ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ለአራቱ ኪሎ እጅግ ቅርብ ከሆነችው ስትራቴጂካዊ ስፍራ ላይ ሆኖ፣ የአፋብን ሽዋ ጠቅላ ግዛህ አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ጓዶቹን አስከትሎ ፊቱን ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ አድርጓል። ምድሪቱን በሚያናውጥ የቆራጥነት ድምፅ "አዲስ አበባ ይሰማል?!" እያለ ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው! ይህ የዛሬዋ መልዕክት ለአዲስ አበባ ወጣቶች ነው! የነፃነት አየር የሚናፍቃችሁ፣ የወንድሞቻችሁን ኮቴ የምትሰሙ የከተማዋ ጀግኖች... የወንድሞቻችሁን የነፃነት ጉዞ ለመቀበልና ታሪክ ለመስራት ዝግጅታችሁን ማጠናቀቃችሁን ለዓለም የምታሳዩበት ወሳኙ ሰዓት አሁን ነው! የነፃነት ድምፅ አይታፈንም! ታሪካዊው ግስጋሴ ወደ ፊት…!#Dawit #Amhara

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ የግዳጅ ግምገማና የጀግኖች ሽልማት ሥነ-ሥርዓት አካሄደ!! ይህ በእንዲህ እንዳለ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ በጋራና በተቀናጀ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ግዳጅ ሲፈጽሙ የቆዩ ክፍለ ጦሮቹን የስራ አፈጻጸም የገመገመበትና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዘመቻ መመሪያ ኃላፊዎች የክብር ባንዲራ የሸለመበት ደማቅ መድረክ አካሄደ። ​በዚህም ባለፉት ወራት በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ስር የሚገኙ በርካታ ክፍለ ጦሮች እርስ በርስ በመናበብና የተቀናጀ የጋራ ኦፕሬሽን በመስራት ደማቅ ገድል ሲያስመዘግቡ መቆየታቸው ይታወቃል። በዚህም መሰረት ​በአፄ ዘርአ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ስር የሚገኙት ሁለቱ ክፈለ ጦሮች ሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር እና አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር እንዲሁም በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ​መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ስር የሚገኘው አስቴ ጉማ ተራራ ክፍለ ጦር፤ እነዚህ ሶስት ክፍለ ጦሮች በጋራ የከረሙበትን ወታደራዊ ግዳጅ በስኬት በማጠናቀቅ፣ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የገመገሙ ሲሆን ለቀጣይ ግዳጅ ዝግጅትም አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ​ይህንኑ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ የግዳጅ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የመሩት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ፣ ዋና የዘመቻ መመሪያ ኃላፊው  ምክትል የዘመቻ መመሪያ ኃላፊው ጋር በመሆን መድረኩን በበላይነት መርተውታል። በዕለቱም ክፍለ ጦሮቹ ባሳዩት አስደናቂ የግዳጅ አፈጻጸም ልክ፣ በየክፍለ ጦሮቹ ለሚገኙ የዘመቻ መመሪያ ኃላፊዎች በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ አመራሮች አማካኝነት የጀግንነት መገለጫ የሆነው የክብር ባንዲራ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ይህ ሽልማት ሰራዊቱ ላሳየው ፅናትና ተጋድሎ የተሰጠ እውቅና መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ መላው የጦር አባላት ለቀጣዩ ግዳጅ ያላቸውን ዝግጁነት ይበልጥ ያጠናከረ ክስተት ሆኖ አልፏል።      ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''    ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ       ግንቦት 10/2018ዓ.ም

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አሃዶች በሰሩት ከፍተኛ የደህንነት ስራ የብልፅግናውን አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮች በሥቦ ማስካዳት ውጤታማ ተግባር መፈፀሙን ኮሩ አስታወቀ። አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ ከአዲስ አበባ መናገሻ ቤተ-መንግሥቱ ደጅ አፍ ላይ የሚገኘው የከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የፋኖ ሰራዊት የአገዛዙን ዙፋን አሥጠባቂ 112ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮችን ሥቦ በማሥከዳትና ከፍተኛ የውጊያ ሽፋን በመስጠት የአገዛዙን ወታደራዊ ቁልፍ አመራሮች ማስኮብለሉን ኮሩ በምስል አስደግፎ በላከው የግንባር መረጃ አስታወቀ። ጠላት የከዱትን አመራሮቹን ለመያዝ ከንጋቱ 10:00 እስከ 12:00 ድረስ ባደረገው የውጊያ ሙከራ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አናብስቶች በአገዛዙ ወራሪ ሰራዊት ላይ የአፀፋ እርምጃ በመውሰድና ፋኖን አምነው የመጡ ሁለት ከፍተኛ የ112ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮችን ከነሙሉ የደህንነት ጥበቃ ጋር መቀበሉን ዕዙ በመረጃው አረጋግጧል። ጀግናው የአማራ ፋኖን የተቀላቀሉት የአገዛዙ አየር ወለድ ቁልፍ አመራሮች:- 1ኛ. ፻ አለቃ ዋቆ አባድባ ✅ማዕረግ ፻ አለቃ ✅ ኅላፊነት ሻለቃ መሪ ✅(1) መገናኛ ሬዲዎ ✅ (1) ሀዲድ ክላሽ ከ120 በላይ የክላሽ ተተኳሽ ✅(03) ቦምብ በመያዝ ፋኖን ሲቀላቀል 2ኛ. ፶ አለቃ ግርማ አበረ ✅ማዕረግ ፶ አለቃ ✅ ኅላፊነት ጋንታ መሪ ✅ (01)ሀድድ ክላሽ ✅160 የክላሽ ተተኳሽ ✅(03) የክላሽ ካዝና እና ሙሉ የደረት ትጥቅ በመያዝ የኃ/ማርያም ማሞ ክፍለ ጦርን ሲቀላቀሉ በየደረጃው ባሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል ሲል የከሰም ፪ኛ ኮር በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሬማ ከተማ የመሸገው የብልፀግናው 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት መካከል ትላንት ምሽት በተፈጠረ አለመግባባት በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ጥቂት የማይባሉ የሰራዊቱ አባላት መጎዳታቸውን የውስጥ አርበኞች መረጃውን ያደረሱ ሲሆን በአገዛዙ ሰራዊት መካከል ከፍተኛ አለመተማመን መፈጠሩን ጠቁመዋል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 10/2018ዓ.ም

በወግዲ ወረዳ ሸመኔ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኝ የአገዛዙ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈፀመ ስኬታማ የሞርተር ድብደባ በርካታ ወታደሮች መደምሰሳቸው ታወቀ‼️ ከኢላማቸው የተነሳ "#የሞርታር_ቅምቡላን #ከጥላት_ኪስ ውስጥ መክተት ይችላሉ" የሚባልላቸው በሃጂ ንጉሤ ሃሚድ በሚመራው የ45ኛ ክፍለጦር ውስጥ የሚገኙት የሞርታር ምድብተኞች በተከታታይ ሁለት ጊዜ በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በፈፀሙት በዚህ ድብደባ፡ የግዳጅ መመሪያ ለመቀበል በአንድ አከባቢ ተሰባስቦ የነበረ የጠላት ስብስብና ከግዳጅ መልስ በሰልፍ ወደ ካምፕ በመግባት ላይ የነበረ የጠላት ኃይል ዳሽቆ እንዲቀር መደረጉ ተረጋግጧል። በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር #በሃጂ_ንጉሤ_ሃሚድ የሚመራው የ45ኛ ክፍለጦር የሜካናይዝድ ምድብተኞች ትናንት ግንቦት 09/2018 ዓ/ም በወግዲ ግንባር #ሸመኔ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የጠላት ካምፕ ላይ በፈፀሙት የሞርታር ድብደባ የጠላት አከርካሪን በመስበር አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅተዋል። የሞርታር ጥቃቱ የተፈፀመው በተከታታይ ሁለት  ጊዜ ሲሆን በካምፑ ውስጥ በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ አርፎ የጠላትን ኃይልና ወታደራዊ ንብረት ዳሽቆ እንዲቀር አድርጎታል። በመጀመሪያው የሞርታር ድብደባ በሸመኔ ቀበሌ ፒያሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው የጠላት ካምፕ ውስጥ የግድጅ መመሪያ ለመቀበል ተሰባስበው በነበሩ የጠላት ኃይሎች ላይ ሲሆን፡ የሞርታር ቅምቡላው በመኃላቸው ላይ አርፎ ዶግ አመድ አድርጓቸዋል። ሁለተኛው የሞርታር ድብደባ ደግሞ በዛው በሸመኔ ቀበሌ ፒያሣ ከሚገኘው ካምፕ በስተጀርባ ከግዳጅ ውለው በሰልፍ ወደ ካምፑ እየገቡ በነበሩ የጠላት ወታደሮች ላይ አርፎ ብርቁስቁሳቸውን አውጥቶታል። ከኢላማቸው የተነሳ "የሞርታር ቅምቡላን ከጥላት ኪስ ውስጥ መክተት ይችላሉ" በሚል የሚሞካሹት የ45ኛ ክፍለጦር ሜካናይዝድ ክፍል ውስጥ የሞርታር ምድብተኞች በተከታታይ ሁለት ጊዜ በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በፈፀሙ በዚህ ጥቃት፡ ከ15 በላይ የሚደርሱ የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን፡ ከቁስለኞቹ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በጥቃቱ እጅና እግራቸው የተቆራረጠ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል። መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ©አፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ 10/ዐ9/2018 ዓ.ም

ጀግናው የነጎድጓድ ከፍለጦር ዛሬም በብልፅግናው የግል ወታደሮች ላይ እርምጃ ሲወስድ በሀገረማርያም ከሰም ወረዳ እየተደረገ ባለው ውጊያ ሁለት የኮማንዶ አመራሮች ከግንባር ከድተው ፋኖን ተቀላቀሉ። ፍኖተ አማራ ሚዲያ አፋብን ሸዋ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ዛሬም እንደተለመደው የአገዛዙን ዘራፊ ሰራዊት ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ዙሪያ በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ስር በሚገኘው ቀበሌ ልዩ ስሙ ሞዬአማንጉልት በተባለ ቦታ ከሌሊቱ 11:30 ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 01:30 ድረስ የክፍለጦሩ 2ኛ እና 4ኛ ሻለቃ የተቀናጀ ጥቃት ፈፅመዋል። ሰራዊታችን በፈፀመው ተጋድሎ በአገዛዙ ኃይሎች ላይ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የብልፅገናው ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ በመሆን ቀሪው እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጦ መመለሱን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃው ገልጿል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በሀገረማርያም ከሰም ወረዳ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የከሰም ፪ኛ ኮር አሃዶች እያደረጉት ባለው የተቀናጀ አውደ ውጊያ ሁለት የ112ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮች የያዙትን የሬዲዮ መገናኛ ጨምሮ ከነሙሉ ትጥቃቸው የተለያዩ የአገዛዙ ምስጥራዊ ሰነዶችን በመያዝ ከውጊያ ግንባር ከድተው ፋኖን መቀላቀላቸውን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል። በከሰምና አካባቢው ቀጠና እየተካሔደ ያለውን ዝርዝር የአውደ ግንባር መረጃ እንዲሁም ከውጊያ ቀጠና ከድተው ፋኖን የተቀላቀሉ የአየር ወለድ ክፍለጦር አመራሮችን በምስል አስደግፈን ዕዙ አጠናቅሮ የሚመለስ መሆኑን እየጠቆምን፣ ድል ለጀግናው ሰራዊታችን እንመኛለን። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 10/2018ዓ.ም

በአማራ ሕዝብ ላይ የሚሰነዘሩ አጀንዳዎችን በማስቆም፣ ትኩረታችን በህልውናችን ላይ ሊሆን ይገባል" ​በአሁኑ ወቅት የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ በጋራ ማሸነፍ ሲገባን፣ ግለሰቦችን በስም
በአማራ ሕዝብ ላይ የሚሰነዘሩ አጀንዳዎችን በማስቆም፣ ትኩረታችን በህልውናችን ላይ ሊሆን ይገባል" ​በአሁኑ ወቅት የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ በጋራ ማሸነፍ ሲገባን፣ ግለሰቦችን በስም እየለዩና ሰው ሰራሽ አጀንዳዎችን እየፈጠሩ ማሳደድ ፍጹም ኢ-ሰብአዊና ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው። ​በማንነት ላይ ያነጣጠሩ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በአማራ ሕዝብ ላይ ታሪካዊ ስህተት መፈጸም ሊቆም ይገባል። ሁላችንም እውነትን መሰረት አድርገን ልንኖርና ልንንቀሳቀስ ይገባል፤ ይህንን ማድረግ ካልቻልን ግን ከጥፋት ድርጊቶች ተቆጥቦ በዝምታ መቀመጥን መልመድ ይበጃል።

:-ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አፋብን ሸ/ጠ/ግ አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር። ግንቦት 10/2018 ዓ ም አማራ ፋኖ የገጠመውን የህልውና ትግል ለመቀልበስ ከተነሳባት ቀን አንስቶ በጀግና የቁርጥ ቀን ልጆቹ ጠላትን እየቀበረ ለወገን ጋሻና መከታ በመሆን የያዘውን ትግል ከፍፃሜ ለማድረስ በመታገል ላይ ባለበት ሰዓት  ነበልባል ክፍለ ጦር ፍፁም የማይቀበለውና ከአሁን በፊት እርምጃ በመውሰድ ያስቆምነውን የምሪት ቦታ በዘንድሮው አመት ከምርጫ ጋር አያይዞ ለመምራት መታሰቡ  ፍፅም ስህተትና የማንታገሰው መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ድርጊት ውስጥ እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ባለሞያዎች በሙሉ በአስቸኳይ ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ በጥብቅ ማስገንዘብና ማሳሰብ እንወዳለን። ካልሆነ ግን ብልፅግና እድሜውን ለማራዘም ለምርጫ የምሪትን ቦታ ለድምፅ መቀበያነት ሲጠቀምበትና ለካድሬዎቹና ለወንበር ጠባቂዎቹ ሲያድለው ቆመን የማናይ እና አርሶ አደሩ መሬቱን በግፍ ተቀምቶ የካድሬዎች መጠቀሚያ እንዲሆን ስለማንፈልግ አስፈላጊውን እርምጃ  ነበልባል ክፍለ ጦር እንደ ሚወስድ በድጋሜ እናሳስባለን ከዚሁጋ ተያይዞ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የምሪት ቦታ ለመቀበል በዝግጅት ላይ የምትገኙ ማንኛውም አባላት በሙሉ የሚመራው የዘንድሮው ምሪት ሁሉንም ያካተተ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ የትኛው ወጣት ነው እሱጋር ያለው?  ስለዚህ ይህ የመኖሪያ ቤት ምሪት ሁሉንም  ወጣት ያላሳተፈ እና አብዛኛው ተመሪ ወጣት በዱር ገደሉ ለህልውናው በሚዋደቅበት ሰዓት የሚደረግ ምሪት ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ቀይ መስመራችን እንደሆነ መግለፅ እንወዳለን   ከዚሁጋ ተያይዞ በህዝብ ቅቡልነቱን ያጣው ጨፍጫፊው  የብልፅግናው መንግስት የምሪትን ቦታ ለምርጫ ድምፅ ለመሰብሰቢያነት እያደረገ ያለውን አደገኛ አካሂድ እያጋለጥን በዚህ ጥቅም ተስባችሁ የብልፅግና ቡራኬ ተካፋይ የሆናችሁ  በሙሉ ከ2018 ዓ ም ከብልፅግና የተበረከተላችሁ ማንኛውም ቋሚ ንብረቶች ለምሳሌ    :- የትክ ቦታ በሚል   :- የሊዝ ጨረታ በሚል   :-  የቀበሌ ቦታ የወረሳችሁ እና ከሚሊሻና ከፖሊስ እንዲሁም ከብልፅግና ወንበር ጠባቂ እና አገልጋይ ማንኛውም አካላት ላይ የምትገዟቸውን ንብረቶች ከ2015 ዓ ም ወዲህ የተረከቡት ከሆነ በእኛ በኩል እውቅና የማንሰጥ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ማስገንዘብ እንወዳለን።    ድል ለአፋብን ነበልባል ክፍለ ጦር ግንቦት 10/2018 ዓ ም