ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 134
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4247 أيام
+1 14930 أيام
أرشيف المشاركات
#የሥርዓት_ማክተም_እና_የለውጥ_መባቻ
በታሪክ ሂደት ውስጥ ማንኛውም የሕዝብን የለውጥ ፍላጎት መሸከም ያቃተው ድርጅት የመውደቂያው ጊዜ መድረሱ የማይቀሬ ነው። ብአዴን ላለፉት አሥርት ዓመታት ሲከተለው የነበረው የአንባገነንነት ጉዞ እና የሕዝብን ብሶት ችላ የማለት ልምድ፣ ዛሬ ለደረሰበት የፖለቲካዊ ሞት ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
የውድቀቱ መገለጫዎች
#የሕዝብ_አመኔታ_ማጣት፡ ድርጅቱ ከወከለው ሕዝብ ጋር ያለው ትስስር ተበጥሷል። ሕዝቡ ድርጅቱን እንደ ጠባቂ ሳይሆን እንደ ጫና ፈጣሪ ማየቱ የሞራል የበላይነቱን እንዲያጣ አድርጎታል።
#የመጨረሻው_ትግል (The Death Throes)፦ ማንኛውም እየወደቀ ያለ ኃይል ህልውናውን ለማቆየት የመጨረሻ ሙከራ ማድረጉ የተለመደ ነው። አሁን የሚታዩት ግትርነቶችና ጥረቶች የጥንካሬ ምልክት ሳይሆኑ፣ የሕይወት እስትንፋስን ለማቆየት የሚደረጉ የሽንፈት ትግሎች ናቸው።
#የማይመለስ_ጉዞ፡ ታሪክ ወደ ኋላ አይጓዝም። የጭቆናና የፍርሃት ዘመን እንዲያበቃ ሕዝቡ የወሰነው ውሳኔ፣ ብአዴን ወደነበረበት የአንባገነንነት መንበር ተመልሶ እንዳይመጣ የመቃብር ድንጋይ አስቀምጦበታል።
#መደምደሚያ
የአንድ ድርጅት መሞት ማለት የአንድ አዲስ ተስፋ መወለድ ነው። ብአዴን በገዛ እጁ በፈጠረው ስህተት እና በሕዝብ የለውጥ ማዕበል ተሸንፏል። ከዚህ በኋላ የሚኖረው ጉዞ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ ወደነበረው የአንባገነንነት አዙሪት የሚመለስ አይሆንም። የብአዴን ዘመን አብቅቷል፤ ቀጣዩ ምዕራፍ የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበትና እውነተኛ ነፃነት የሚሰፍንበት ይሆናል።
ከምን ተነስተን የት እንደደረስን እናውቀዋለን እኛ ከጅምሩ ገብቶን መንግስትን አፍርሰን የመጣን እንጅ ድንገት ሳናስበው መንግስት ፈርሶብን ወደ ትግል የወጣን አደለንም። ደብረ ማርቆስ ይመስክር !!
ከሃዲዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እና ውጥናችንን ለማሳካት ከእውነተኛ ታጋዮች የሚጠበቀው እልህ፣ቁጭት፣ጀግንነት፣የአላማ ፅናት እና አሸናፊነት ነው። ብድሩን ያልመለሰ ወንድ ልጅ ደግሞ አይፈጠር !!!
አሳምነው ፅጌን ለምን ገደሉት ?
ስጋውን ላይበሉት ደሙን ላይጠጡት 😭
አንድ ሁኑ ስላለ ድንገት ቢፈሩት ::
አንድ ሁኑ 🫵 የአደራ ቃሉ ነው 🙏
አንድነት ኃይል ነው !!!
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ 🫰
የኢትዮያንና የአማራ የሕዝብ ድምፅ ⚖️📷 ነው። ዴቭ
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
ሰበር ዜና
**
የብልፅግና ሰራዊት የፋኖ አንድነት ሲሰማ እየፈረሰ እንዲህ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። የአፋብን ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦርን የተቀላቀሉ የ11ኛ ዕዝ 16ክ/ጦር የግለሰብ ዙፋን ጠባቂ አንሆንም ብለው ከመጡት መካከል እነኝህ ይገኙባቿል።
ሰበር ዜና
4ኛ ደጃዝማች ኮር በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ።
በቀን 11/05/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12 ላይ ከማእከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ወረዳ ጃንሱማ ቀበሌ ሽመል በር በተባለ ቦታ ላይ የኮሩ ልዩ ዘመቻ እና የተከዜ ክፍለ ጦር በጥምረት በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት እርምጃ ከፍተኛ በጠላት ላይ ኪሳራ ደርሶበታል።
የፋሽሽቱ ወንበር አስጠባቂ የሆነዉ የ92ኛ እና 78ኛ ክፍለ ጦር 2ሬጅመንት እና አንድ የሻለቃ አድማ በተን ወደ 70 የሚሆን ሰላም አስከባሪ በጥምረት ያሰማራዉን ሃይል ክፉኛ ተመቷል።
በሽመል በር (ጎጥ) በጠላት በኩል ከ70 ሲደመሰስ ሲሆን ከ40 በላይ ቁስለኛ ሁኗል።ለጊዜዉ ስማቸዉ ያለታወቀ ከፍተኛ አመራሮችም ተመተዋል።
በፋኖ ምት የተበሳጨዉ የጠላት ኦህዴድ/ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃን ወገኖቻችን ኢላማ በማድረግ የአርሶ አደሮችን ህይወት ሲቀጥፍ ቤት ንብረትም አውድሟል።
ጥር 12/2018 ዓ.ም
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
#ራሳችንን_ለአገዛዙ_አሳልፈን_አንስጥ‼️
ኃይማኖታዊ በዓል (የተለያዩ ፕሮግራሞች) ሲካሄዱ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራን ፋኖ ወይንም አርበኛ ዘመነ ካሴንና ሌሎች አርበኞች ስም በመጥራት ወጣቶች ሲያወድሱ ይስተዋላል። ትናትና ዛሬም የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ #በፋኖ_አንድነት የተደሰተው ህዝባችን ስሜቱን በጭፈራ ሲገልፅ አርበኛ ዘመነ ካሴን ሲያወድስ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች ጭፈራ ላይ የነበሩ ወጣቶች #በአገዛዙ_ታፍነዋል። ለአብነትም በደብረማርቆስ ከተማ 1 ወጣት በከተራ በዓል ላይ #ዘመነ_ካሴ ብለህ ጨፍረሀል ተብሎ #በአሰቃቂ_ሁኔታ_ተረሽኗል‼️
በዛሬው ዕለትም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ጨፍራችዋል የተባሉ በርካታ ወጣቶች ከታች ዝርዝር መረጃ ባስቀመጥነው ፀረ አማራ ባንዳ አማካኝነት ታስረዋል።
አሳሳሪው #ይታያል በተባለ የንጉስ ተክለኃይማኖት ክፍለ ከተማ ደህንነት (የቀበሌ 05 ፖሊስ የነበረ ቀበሌ 09 ሚካኤል በታች የነበረ መኖሪያ ቤቱ ሾላንብ እድር ቤቱ ጋር የሆነ ባለቤቱ ድሮ ቀበሌ የምትሰራ አሁን ክፍለ ከተማ የገባች ሲል የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል‼️
#ማሳሰቢያ በነገው ዕለት ለሚከበረው አመታዊ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል እንደዚህ አይነት ነገሮች እንዳይፈጠሩ አገዛዙ በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ወጣቱ #ሙያ_በልብ በማለት ከትግል ጭፈራ ራሱን በማራቅ ከአልተፈለገ መስዋትነት እንዲጠብቅ ንስር አማራ ከወዲሁ ጥሪዋን እያስተላለፈች በግፍ ለተረሸነው ወንድማችን ነፍሱን እንዲምርልን ፣ ለወዳጅ ዘመድ መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን🙏
ለትግሉ በስሜት ሳይሆን በስሌት እንደግፍ‼️
11/ዐ5/2018 ዓ.ም
‼️‼️ሰበር ዜና‼️‼️
አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ወደ ፊስ ቡክ የትግሉን እንቅስቃሴ ይዞልን መጣ፡፡ መረጃዎችን ጎልጉሎ በማውጣት ታማኝ የመረጃ ምንጭ ሁኗል ይወዳጁቱ መልክታችን ነው አጋርነታቸውን ስለ አሳያችኋለሁ እናመሰግናለን አንድ ስንሆን አሸናፊ መሆናችንን አሳይተናል ፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://www.facebook.com/share/p/1Au51Q8uKK/
‼️‼️ሰበር ዜና‼️‼️
አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ወደ ፊስ ቡክ መጣ መጣ፡፡ መረጃዎችን ጎልጉሎ በማውጣት ታማኝ የመረጃ ምንጭ ሁኗል፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://www.facebook.com/share/v/17sYEJidzf/
"በትዝብት አይተን ፈገግ ብለን ያለፍናቸው ብዙ ነገሮች አሉ።
"ትናንት ጠላቶቻችን አማራዉ መቼም በታሪክ አጋጣሚ አንድ ሆኖ መታገል አይችልም" እያሉ ሲዘባበቱብን በተናጠል ሲገሉን" ሲያፈናቅሉን"ሲደፍሩን " ሲያኮላሹን የፈሪ ብትር ማሳረፊያቸው አማራው ላይ ሲያደርጉ ቆይተዋል ። ሆኖም በትኩ የአማራ አንገቱ አንድ እንደሆነ ዛሬ ላይ በአንድነታችን በተግባር ስናሳያቸው ከውስጥ እስከ ዉጪ ወዳጅ መሳይ የአማራ ታሪካዊ ጠላቶች ድረስ የሀዘን ድንኳን ጥለው ለቅሶ ላይ ይገኛሉ"።
" ብዙ ጊዜ እንል ነበር አማራው አንድ የሆነ ቀን ጠላቶቻችን ይሸበራሉ። ከመሸበርም አልፈው ይፈረጥጣሉ። ምክንያቱም አሸናፊነታችን ያለው አማራ ከሚለው ሀያሉ ስም ላይ ነው።
"ከመቅረት ይሻላል በሚለው መርህ መሰረት ዘግይቼም ቢሆን "እንኳን ደስ አላችሁ አለን" ለማለት እዉዳለሁ ለማላዉ የትግል አጋሮቻችን በሙሉ።
"የጀነራል አሳምነው ፅጌን የአንድ ሁኑ የአደራ ቃልን በተግባር ላሳያችሁን መሪዎቻችን በሙሉ ክብር ይገባችኋል🙏gechoo sisay
Yoseph Asmare Et
ትግል ይቀጥላል .......
ፋኖ አብርሃም ብርሌ አማራው
#ጠላትን_ለመምታት_ሁሌም_ዝግጁ_ነኝ
ከቀደምት አማራነቱን የተላበሰ የአባቶቻችን ጀግንነትን በመውረስ የወጣለትን ዓላማ በደም እና አጥንት ዳር የሚያደርስ የወጣለትን ዓላማ ጠንቅቆ የሚያውቅ የዓላማ ጽናት ያለው በተራ ጥቅም አማራነቱን የሚያስከብር ከህዝቡ በፊት ለመሞት ዝግጁ የሆነ ፋኖ ነው፡፡
የአማራን አንድነት ለመበታተን የሚሯሯጥ ሳይሆን ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚታገል ሴረኛዎችን ፊት ለፊት የሚገጥም በየትኛውም ግዜና ቦታ ጠላትን እረፍት በመንሳት የአገዛዙን ስራዊት በማፈራረስ ድንቅ ኦፕሬሽን የሚሰራ የታሪክ ባለቤት ፋኖ ነው።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ_ክፍለ_ጦር ግዙፍ ሰራዊት
ከአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ለጥምቀት በዓል እና ለአማራ ፋኖ አንድነት መመስረት የእንኳን አደረሳቹህ እና የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት አስተላልፏል‼️
በመጀመሪያ ለዓመታት በናፈቅነዉና በደማችን በገነባነዉ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስረታ እንኳን አደረሳቹህ እንኳን ደስ አላቹህ !!
በቀን 9/ 2018 ዓ.ም የታወጀዉ ይህ ታሪካዊ አንድነት በሁሉም አማራ ምድር ላይ ለምትጋደሉ እና የጀኔራል አሳምነዉ ፅጌን አደራ የተሸከማቹህ አመራር እና አባላት ትልቅ ብስራት ነዉ።
1 ለሁሉም ለአማራ ፋኖ አመራር እና አባላት :_ በትግሉ ሂደት ዉስጥ ያሳየህዉ ፅናት ፣ቅንነት እና ለህዝብ አንድነት የነበረዉ ቁርጠኝነት ዛሬ ለደረስንበት መሰረት ሁኗል። በመላዉ አማራ ምድር በከፍተኛ መሰዋትዕነት ጠላትን ስታንቀጠቅጡ የቆያቹህ አመራሮች እና ታጋዮች ፣ዛሬ በአንድ ተቋም ስር መጠቅለላችንን ለጠላቶቻችን የሞት ደብዳቤ ለህዝቦቻችን ደግሞ የነፃነት ቁልፍ ነዉ። ገና ከጥንቱ ጀምሮ ክፍለ ጦሮች እና ኮሮች ሲመሰረቱ የነበራቹህ ቅንነት እና ለህዝባቹህ ያሳያቹህት ፍቅርና ቁርጠኝነት ዛሬ ለደረስንበት ታላቅ መሰረት ሁኗል። በአማራ ምድር ላይ የጀግንነት ታሪክ የሚታደሱ ፣ የአማራ ክብር ለማስመለስ በብርቱ ፅናት የቆማቹህ አመራሮችና አባላቶች ፣በእናተ ላይ ያለን ክብር እና እምነት እጀግ የላቀ ነዉ።
የአንድነታችን ትርጉም ለጠላት እና ለህዝባችን የአማራ ልጆች ሃሳብ የላቸዉም፣ ቢኖራቸዉም ተቀባይነት የለዉም።
አማራዉን ጨፍልቀን ቆሻሻ ሳጥን ዉስጥ ከተነዋል እያለ ከፍተኛ በጀት እየመደበ እና የጥፋት መረብ እየዘረጋ ለሚፎክረዉ ለቀነጨረ ስርዓት ፣ይህ ዛሬ ያሳየነዉ አንድነት የመጨረሻዉ የሞት ደብዳቤ ነዉ። በተቃራኔዉ ደግሞ ላለፉት አመታት መከራን ለገፋዉ በትናንት የፈጠራ ትርክት ሲሳደድ እና ሲታረድ ለኖረዉ ገራገሩ የአማራ ህዝባችን ፣ይህ የመላዉ ቤተ አማራ አንድነት ከባርነት ቀንበር ወጥቶ ወደ ነፃነት እና ወደ ክብር የሚሻገርበት የነፃነት መግቢያ ቁልፍ ነዉ። ይህ አዲስ ንቅናቄ የተመሰረተዉ እንደ አንድ ህዝብ የመጥፋት አዳጋን ለመቀልበስ እና የአማራን ህልዉና በዛላቂነት ለማረጋገጥ ነዉ። የአማራ ፋኖ ብሄራዉ ንቅናቄ አባላት ይህ አንድነት ትርጉሙ ትልቅ ነዉ። ምክንያቱም :-
* የላቀ አቅም :- የተበታተነ ትግል አብቅቶ በወጥ መዋቅር ዉስጥ በመሆናችን ለቀጣይ ወታደራዊ ድሎች ዝግጁ ያደርገናል።
* የጠላት ዉድቀት:- አማራ አይሰባሰብም ብሎ ሲፎክር የነበረዉ አባገነን ስርዓት በሃሳብ እና በአደረጃጀት አሸንፈነዋል።
* ታሪካዉ ኃላፊነት :- ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ የተሰዋለትን የአማራ ብሄርተኝነትን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሚያስችል ብሄራዊ ግንባርን ፈጥረናል።
# የታሪክ ምስክርነት እና ጥሪ
ጊዜዉ እና ቦታዉ ሲደርስ፣ ይህንን ታላቅ የቤት ስራ የሰሩ ፣ለህዝባችን አንድነት ደምና አጥንታቸዉን የሰጡ አባላትና አመራሮች የሚገባቸዉ የታሪክ ክብር እና ምስጋና እንደሚያገኙ ጥያቄ የለዉም። አማራ በታሪክ ጀግና የማታጣ ለክብሯ የማትንበረከክ ምድር እንደመሆኗ መጠን ዛሬ የአማራ ትንሳኤ ዕዉን ማድረግ ችለናል።
በመላዉ ዓለም የምትገኙ የትግል ደጋፊወች እና የዲፕሎማሲ ስራ የምትሰሩ ወገኖቻችን ፣ይህ አንድነት ዳር እንዲደርስ ላደረጋቹህት ደከመኝ ሰለቸኝ የማይባል ድጋፍ እያመሰገንን አሁንም ጠላትን ባዶ እጁ እና ምላሱን ብቻ እንዳስቀረነዉ አዉቃቹህ ርብርባቹህን አጠናክራቹህ እንድትቀጥሉ ጥሪየን አቀርባለሁ።
በቀጣይም መላ የአማራ ህዝብ ባለበት ቦታ ሁሉ የነፃነት ቀንዲል ሁኖ እንደሚቀጥል ጥርጥር የለኝም ።
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ።
ለአማራ ድል ለፋኖ !!
አንድነት ኃይል ነዉ!!
ጥር 11 / 2018 ዓ.ም
11/ዐ5/2018 ዓ.ም
#ፋኖ፦ #የክብር_ዘብ፣ #የነጻነት_አርማ
እነሆ! በታሪክ አደባባይ ላይ የቆመው አማራ ፋኖ—የአንበሳ ግርማ፣ የንስር እይታ። እርሱ ለጠላት መብረቅ፣ ለወዳጅ ደግሞ ጥላና ምርኩዝ ነው። ከጥንት አባቶቹ የወረሰውን የጀግንነት ካባ ተላብሶ፣ የግፍን አጥር ለመስበር የተነሳ የትውልድ አለኝታ ነው።
#የህዝብ_መከታ፦ እንደ ተራራ የጸናው ፋኖ፣ የህዝቡን እንባ ሊያብስና ክብሩን ሊመልስ ቆርጦ ተነስቷል። እርሱ የደካሞች ኃይል፣ የጭቁኖች ድምፅ ነው።
#የነገው_የድል_ብርሃን፦ በጨለማ ውስጥ ለሚጓዘው ትውልድ እርሱ ፋና ወጊ ነው። መንገዱ የእውነት፣ ዓላማው የነጻነት በመሆኑ የነገዋን ታላቅ ሀገር በደሙ ይጽፋል።
#የህዝብ_ፍቅር_ማኅተም፦ ፋኖ በጠመንጃው ብቻ ሳይሆን በምግባሩ የህዝብን ልብ ገዝቷል። ህዝቡም ቤቱን ከፍቶ፣ ስንቁን አጋርቶ "አንተ የእኔ ነህ" ብሎ አትሞታል።
የፋኖ ጉዞ የፍትህ ጉዞ ነው፤ ድምፁ የነጻነት መዝሙር ነው። ከእውነት ጋር የቆመ፣ በህዝብ ፍቅር የታጀበ ኃይል ደግሞ መጨረሻው ድልና ታላቅነት ብቻ ነው!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኑአምላክ ክፍለ ጦር በታሪካዊቷ ከተማ ማጀቴ ብርሃነ ጥምቀቱን በደማቅ ሁኔታ አከበረ!!
ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አስተምህሮ ጥምቀት ማለት ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ መውለድና የክርስቶስ ቤተሰብ ወይም አባል መሆን ማለት ነው።ዳግመኛ መውለድ ማለት ደግሞ በመጀመሪያ በሥጋ ከእናትና ከአባት መውለድ ቀጥሎም በ40 እና በ80 ቀን ከውኃና ከመንፈስ በጥምቀት የክርስቶስ ልጅነትን ማግኘት ማለት ነው።ደግሞ ከውኃና ከመንፈስ ለመውለድና የክርስቶስን ልጅነት ለማግኘት መጀመሪያ በሥጋ ከእናትና አባት መውለድ ያስፈልጋል።
በመጀመሪያ የአማራ ፋኖ ከዚህ አምስት እና ስድስት ዓመታት በፊት የህልውና ትግል ሲጀምር በየሰፈሩ እና በየአካባቢው የትግል መንፈስን ብቻ ይዞ ከእናቱና ከአባቱ ከጀግናው ሕዝብ ከአማራ አብራክ ተወለደ። በመጨረሻም ከብዙ ውጣ ውረድ እና ከብዙ ድካም በኋላ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ተወልዶ የክርስቶስን ልጅነት እንደምትጎናጸፍ ነፍስ ድርጅታችንም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ከበፊቱ በላቀ የልዕልና ደረጃ ከፍ ብሎ እንዲሁም ፍፁም ትህትናን በተላበሰ መልኩ እንደ ንስር ታድሶ ዳግመኛ ተወልዷል።
ከብዙ ድካም በኋላ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አንደ መሪ አንደ የማታገያ ድርጅት ፈጥሯል። በዚህ የአንድነት ዋዜማ ላይ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል መከበሩ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል። በመሆኑም ለመላው የአማራ ሕዝብ እንኳን ደስ አለህ ማለት እወዳለሁ። በመቀጠልም በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት እንዲሁም የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን እየተመኘሁ በዓሉን ለማክበር ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጣው ሕዝበ ክርስቲያን ራሱን ለአደጋ ከሚያጋልጥ ስፍራ እንዲጠብቅ እያልኩ ጥብቅ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
አርበኛ አቡሽ ጌታሁን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር የዓፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር ዋና አዛዥ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
ጥር 11/05/2018 ዓ.ም
በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኑአምላክ ክፍለ ጦር በታሪካዊቷ ከተማ ማጀቴ ብርሃነ ጥምቀቱን በደማቅ ሁኔታ አከበረ!!
ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አስተምህሮ ጥምቀት ማለት ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ መውለድና የክርስቶስ ቤተሰብ ወይም አባል መሆን ማለት ነው።ዳግመኛ መውለድ ማለት ደግሞ በመጀመሪያ በሥጋ ከእናትና ከአባት መውለድ ቀጥሎም በ40 እና በ80 ቀን ከውኃና ከመንፈስ በጥምቀት የክርስቶስ ልጅነትን ማግኘት ማለት ነው።ደግሞ ከውኃና ከመንፈስ ለመውለድና የክርስቶስን ልጅነት ለማግኘት መጀመሪያ በሥጋ ከእናትና አባት መውለድ ያስፈልጋል።
በመጀመሪያ የአማራ ፋኖ ከዚህ አምስት እና ስድስት ዓመታት በፊት የህልውና ትግል ሲጀምር በየሰፈሩ እና በየአካባቢው የትግል መንፈስን ብቻ ይዞ ከእናቱና ከአባቱ ከጀግናው ሕዝብ ከአማራ አብራክ ተወለደ። በመጨረሻም ከብዙ ውጣ ውረድ እና ከብዙ ድካም በኋላ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ተወልዶ የክርስቶስን ልጅነት እንደምትጎናጸፍ ነፍስ ድርጅታችንም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ከበፊቱ በላቀ የልዕልና ደረጃ ከፍ ብሎ እንዲሁም ፍፁም ትህትናን በተላበሰ መልኩ እንደ ንስር ታድሶ ዳግመኛ ተወልዷል።
ከብዙ ድካም በኋላ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አንደ መሪ አንደ የማታገያ ድርጅት ፈጥሯል። በዚህ የአንድነት ዋዜማ ላይ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል መከበሩ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል። በመሆኑም ለመላው የአማራ ሕዝብ እንኳን ደስ አለህ ማለት እወዳለሁ። በመቀጠልም በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት እንዲሁም የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን እየተመኘሁ በዓሉን ለማክበር ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጣው ሕዝበ ክርስቲያን ራሱን ለአደጋ ከሚያጋልጥ ስፍራ እንዲጠብቅ እያልኩ ጥብቅ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
አርበኛ አቡሽ ጌታሁን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር የዓፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር ዋና አዛዥ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
ጥር 11/05/2018 ዓ.ም
በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ተጨማሪ መረጃ ባሕር ዳር
በሁሉም የባሕር ዳር ከተማ ታቦት በሚሸኝበት ወጣቱ በቡድን በቡድን እየሆነ በልዩ ሁኔታ የአርበኛ ዘመነ ካሤን ስም እያነሳ እየጨፈረ ነው።
ባንዳው አድማ ብተናና ፖሊስ ሲቪልና ሬንጀር እየለበሰ እየተራወጠ ጭፈራውን ለማስቆም ቢሞክርም አልቻለም። በተደጋጋሚ ታቦት የሚያጅበውን ምእመን በሚያውክ መልኩ በድብደባ እየበተኑ ታቦቱ እርቃኑን እየቀረ ነው። በተለይም አኮቴት አደባባይ ላይ ድብደባው የባሰበት ሕዝብ በጩኸት ድብልቅልቁን ቢያወጣውም ድብደባው ባለመቆሙ ወጣቱ በቀጥታ በወታደሩ ላይ ባገኘው ነገር ሁሉ እርምጃ መውሰድ ጀመረ። ገረዱ ወታደርም አካባቢውን በተኩስ መናጥ ጀመረ። ሕዝቡ ወደ ቤቱ መሮጥ ጀመረ። ታቦት ቆሞ ዲያቆናት የደወል ድምፅ ይዘው በመግባት ተኩሱ ቆመ። የሮጠው ሕዝብ ወደ ታቦቱ አልተመለሰም። በርካታ ሕዝብ ታፍሶ ወደ እሥር ቤት እየተደበደበ ገብቷል። ወታደሩ ፎጣና ጋቢ በመልበስ መሣሪውያው በመሸፈን እየተሹለከለከም ታይቷል። ይኸም አዘናግተው ወጣቱ ላይ ሊተኩሱ ነው። በርካታ ጆሮ ጠቢዎች ከሕዝብ ጋርም ተቀላቅለዋል።
©የብላክ ላዬን ምንጮች ከባሕር ዳር
+2
#ሴት_ፋኖ፦ #የትግሉ_ሞተር፣ #የነፃነቱ_ማገር
የታሪክ ማህደር ሲገለጥ፣ የድል አውድማው ሲቃኝ፣ በጀግንነት ስም ዝርዝር ውስጥ የሴት ፋኖ አሻራ የጎላ ነው። እርሷ ለትግሉ ድምቀት ብቻ ሳትሆን፣ መላውን እንቅስቃሴ ወደፊት የምታስፈነጥር "ሞተር" ናት።
በአንድ እጇ ቤቷን፣ በአንድ እጇ ነጻነቷን የጨበጠችው ሴት ፋኖ፤ በቁጭት ስትነሳ ተራራ የምታንቀጠቅጥ፣ ስትራመድም ምድርን የምታናውጥ የጽናት ተምሳሌት ናት። ሰንቀው ለሚዘምቱት ወንድሞቿ ስንቅ ብቻ ሳትሆን፣ ለውጊያው ወኔ፣ ለድሉም ተስፋ የምትዘራ የብርታት ምንጭ ናት።
የእርሷ የትግል ሞተርነት በሁለት መልክ ይገለጣል፦
#በግንባር፦ እንደ ጥይት ተኳሽነቷና እንደ ስትራቴጂ ነዳፊነቷ፣ ጠላትን የምታስበረግግ ቆራጥ ተዋጊ ናት።
#በጀርባ፦ እንደ እናትነቷና እንደ እህትነቷ፣ የትግሉን ማገዶ አቀጣጥላ፣ ተስፋው እንዳይከስም የምታደርግ የህልውና ዋስትና ናት።
#ሴት_ፋኖ ስትታጠቅ፣ ትጥቁ የብረት ብቻ ሳይሆን የሞራልና የማንነት ጭምር ይሆናል። እርሷ በሌለችበት ትግል ውስጥ ትንፋሽ የለም፤ እርሷ ባልቆመችበት አውድማ ላይም ፅናት አይታሰብም። በእውነትም፣ የነፃነት ጉዞው ጋሪው ህዝብ ከሆነ፣ ያንን ጋሪ አድካሚውን ዳገት አስወጥታ ለድል የምታበቃው ብቸኛዋ ሞተር "ሴት ፋኖ" ናት! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር እና የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ሴት ታጋዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ ለእየሱስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
