ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 389
المشتركون
+2924 ساعات
+2547 أيام
+1 45030 أيام
أرشيف المشاركات
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ህዳር 29/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ቀትር 6:30 ሰዓት ድረስ በወሰደው የደፈጣ ጥቃት አይና ቡግና ከአይና ቅዱስ ሐርቤ መውጫ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የአገዛዙ ተላላኪ የሆነውን መከላከያን እና ሚሊሻን በደፈጣ ሶራ ሜዳ ላይ ሲያራግፉት ውለዋል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት የክፍለ ጦሩ 2ኛ ሻለቃ፣4ኛ ሻለቃ እና 3ኛ ሻለቃ አንድ ሻምበል በመናበብ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም ጠላት አንድ የፖሊስ መኪናና አምቡላንስ ቁስለኛ ይዞ ሲመለስ ከ12 በላይ ሲደመሰስ እዲሁም ሰባት ጥቁር ክላሽ 836 የብሬን ተተኳሽ እና 659 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል።
የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ሰራዊት በቡግና ወረዳ 03 መሰቀለ ክርሥቶስ ቀበሌ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ላይ የከብት ሳር ወይም መኖ እየተሸከመ ያገኘውን የ16 አመት ህፃን ከሁለት ቦታ ላይ በክላሽ በማቁሰል፣አውድማ በማለቅለቅ ላይ የምትገኝን የ17 አመት ልጃገረድ በክላሽ በማቁሰል፣በአዉድማ ላይ የተከማች እህል በማቃጠል፣መስቀለ ክርስቶስ ቀበሌ ላይ ቤት ለቤት በመዞር ህዝቡን ገንዘብ በመዝረፍ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የጭካኔ በትሩን አሳይቶ ሄዷል።
በዚህ ያላበቃው የአገዛዙ ሰራዊት አይና ከተማ ላይ ህዝቡን በየቤቱ በመግባት አስገድዶ በማስወጣት፣መነሀሪያ የሚገኝን ደንብ አስከባሪና ተሳፋሪን እንዲሁም በትምህርት ገበታቸው የሚገኙ ተማሪዎችን አስገድዶ በማስወጣት ስብሰባ ሰብስቦ ከልጆቻችሁ ጋር አስታርቁን እና አስታራቂ ሽማግሌ መልምሉ እንዲሁም የሦስት አመት ግብር ትከፍላላችሁ ሲሏቸው ህዝቡም ሽማግሌ አንመለምልም ልጆቻችን የወጡት እውነትን ይዘው ነው ከዚያ ውጭ ቡግና በጦርነት፣በድርቅና በወረርሽኝ ሲሰቃይ የነበረ ህዝብ የት አምጥቶ ግብር ይከፍላል እናንተ እኛን የፈለጋችሁን ገንዘብ ለመሰብሰብ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በመጨረሻም ጠላት ክንዳችን ያውቀዋል፣ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የብልፅግናንና ጄሌዎቹን እስትንፋስ ለመቁረጥና የህዝባችንን ዕምባ የምናብስበት ቀን ቅርብ መሆኑንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ሲሉ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ሃምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙሉዬ አሳስበዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሽፈራው አለልኝ መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ
+2
የአፈብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ የህዝብ አስተዳደር ስራዎችን የጦር አደረጃጀት ከማህበረሰብ አስተዳደር በተለየት በአዲስ መልኩ እያደራጀ ይገኛል ።
የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቴዎድሮስ እዛ 206ኛ ኮር በስሩ ያሉትን ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን መልሶ በማደራጀት የጊዚያዊ መንግስት መዋቅር እየዘረጋ ይገኛል።
በዛሬው እለት በ206ኛ ኮር ከሚያስተዳድረው ነፃ ቀጠና አወበል ወረዳ ማህበረሰብ ጋር የትግሉ መነሻ እና መዳረሻ እንዲሁም አዲሱን የጊዚያዊ መንግስት አወቃቀር ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
ሰውነት ቢተው ቢያዝን📷📷📷📷
አመራሮች ላይ የደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ!!
የአብይን ፍላጎት ለማሟላት ሙሉ የአማራን ህዝብ እያስጨረሰ ያለው የብአዴን አመራር ህዝብ እሰበስባለሁ በማለት ከግንደወይን ተነስተው ደብረወርቅ ለመሰብሰብ በዙ23 እና በ6 ዲሽቃ እየታጀበ ፈለገብርሃን ከተማን አልፎ ጥቂት ርቀት እንደተጓዘ ጭየ ወንዝ እና ባድማ ጫካ ላይ የ74ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ አባላት ከባድ የደፈጣ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሲሆን
ሞጣ መገንጠያ ላይ የሻለቃ 5 አባላት ሌላ ተጨማሪ ደፈጣ እንደተጣለበት ሲያውቅ ሙት እና ቁስለኛውን በመያዝ ከሽፈሬ ጀምሮ ሁሉም የብልፅግና ቅጥረኛ አመራር ከነሰራዊቱ በእግረኛ አንደኤሌ እየተጎተተ ደብረ ወርቅ በመድረስ የህዝብ ስብሰባ የሞከረ ሲሆን ጀግኖቹ እየተከታተሉ በስለት ደብረወርቅ ገብቶ የጀመረውን ስብሰባ በሞርተር አደባይተው በትነውበታል።
ውሎውን በልቅሶ ያገባደደው የብልፅግና ጉዳይ አስፈፃሚ ምሸት ላይ ጥቂት ደጋፊዎችን ይዞ ስብሰባውን በድጋሜ ለማካሄድ ደፋቀና እያለ ሲሯሯጥ ውሏል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስተስፋ፣አዲስ አስተሳሰብ
ህዳር 28/3/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የጠላትን ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ በነበረው የሰራዊት አባል ላይ እርምጃ መውሰረዱን 206ኛ ኮር አስታወቀ።
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
በመልሶ ማደራጀት ትግበራው ሰራዊቱን በተቀናጀ መልኩ እያደራጀ የሚገኘው 206ኛ ኮር በሰራዊቱ መካከል የተሰገሰጉ የጠላት እጆችን እየቆረጠ ሲሆን በ14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ አባል በነበረው አንተነህ ናዴ ላይ ክትትልና ምርመራ ከተደረገበት በኋላ ወንጀለኛ ሁኖ በመገኘቱ የድርጅቱን መመሪያና ደንብ መሰረት በማድረግ ኮሩ እርምጃ ወስዶበታል።
ከጠላት ዋና አጀንዳዎች መካከል ሰራዊቱን እርስ በእርስ ማጋጨትና ማስከዳት ፣በፋኖ ስም ፀያፍ ተግባራትን መስራት በዋናነት የተቀበለው አንተነህ ናዴ ፦
1ኛ .የጅበላ ሙተራን ሻለቃ ሰራዊትን በማጋጨት
2ኛ .በአስገድዶ መድፈር
3ኛ . አባላትን በማስከዳት
4ኛ.ወታደራዊ ሚስጢሮችን ለጠላት አሳልፎ በመስጠት
5ኛ. ከማህበረሰቡ በማስገደድ ገንዘብ በመቀበልና በመዝረፍ
6ኛ. ከጠላት ኃይል አመራሮችና ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተልዕኮውን ጨርሶ በፋኖ አመራሮች ላይ ግድያ ፈፅሞ ወደ ጠላት ለመቀላቀል ሲነጋገር በተገኘ የስልክ ልውውጥ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ከላይ የተዘረዘሩ ወንጀሎችን ፈፅሞ በመገኘቱ ኮሩ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
የሰራዊቱን የውስጥ አንድነትና የትግሉን ህልውና ለማስቀጠል በትኩረት እየሰራ የሚገኘው 206ኛ ኮር በጅበላ ሙተራ ሻለቃ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በመፍታት ሰራዊቱ አንድነቱን በማፅናት ማንኛውንም ግዳጅ መወጣት በሚያስችልበት ቁመና ላይ መገኘቱንም ኮሩ አክሎ ገልጿል።
በቀጠናው እረጅም እጆቹን አስገብቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ጠላት መሰል እርምጃዎችን ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሰ ሲሆን አንተነህ ናዴ ላይ እርምጃ ከተወሰደ በኋላ ወደ ቸርተከል ከተማ የተንቀሳቀሰውን ጠላት የጅበላ ሙተራ ሻለቃ ወደ ኋላ መመለሷም በመረጃው ተመላክቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የትግሉን ህልውና ለማስቀጠል የሰራዊቱን አንድነትና ደህንነት ማስጠበቅን የቅድሚያ ቅድሚያ አድርጎ እየሰራ የሚገኘው 206ኛ ኮር አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በወንጀለኞች ላይ ድርጅታዊ እርምጃ መወሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
የሰራዊታችን ደህንነት ለማይቋረጠው ትግላችን!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
"....እጅህን ስጥ አለኝ ጠላት፤እጅ ተይዞ ሊዎሰድ፣ምን እጅ አለኝና የእሳት ሰደድ፤አያውቅም እንዴ ክንዴ እንደሚያነድ።"
እኛ የአጤ #ቴዎድሮስ የመንፈስ ልጆች ነን። እጅ መስጠት በአማራ ባህል እጅግ ፀያፍና ነውር ነው። ለቤተሰብ፣ለልጅ፣ለልጅ ልጅና ለዘመድ አዝማድ ደግሞ አንገት የሚያስደፋ፤የባንዳ የካሃዲ ልጅ የሚያስበል ነው።
አጤ ቴዎድሮስ ለእንግሊዞች እጅ አልሰጡም። ይልቁንስ "እጄን ለጠላት ከምሰጥ፣ሞቴን እመርጣለሁ" ብለው ሽጉጣቸውን ጠጥተው፣ምን ያህል ለቃል፣ለአገር፣ለእምነትና ማንነት መታመንን በደማቸው ዋጅተው የወጡበትን ማኀበረሰብ በደማቅ የታሪክ ቀለም አስፍረዋል።
አጤ ምኒልክ ለጣሊያን እጅ መስጠት ቀርቶ በኋላ ቀር መሳሪያ ድል አድርገው፣ለዓለም ጥቁሮች የነፃነት ቀንዲል ሆነዋል።ንጉሱ በጠላት እጅ ከመውደቅ ይልቅ ሸሽተው በመሄድ በሰሩት ዲፕሎማሲያዊ ስራና የእርሳቸው የመንፈስ ልጆች በዱር በገደሉ ባደረጉት ተጋድሎ ድልን ተቀዳጅተው ተመልሰው ዙፋናቸውን ይዘዋል።በላይ ዘለቀ ለጣሊያንም ይሁን ለሌሎች ባዕዳን እጅ አልሰጠም።ይልቁንስ ድል አድርጓቸዋል።የኛ ዘመን ምልክት ጀግናው ብርጋደር አሳምነው ፅጌ ለአብይ አገዛዝ እጅ ከምሰጥ በሚል ብቻውን ተዋጋቶ በደሙ ይህንን ትውልድ አፍርቷል።
ታዲያ አንተ ከእኛ ወገን የሆንክ ሁሉ ከየት የተማርከውንና ያየኸውን ነው ለጠላት እጅህን አሳልፈህ የምትሰጠው??? ለመስጠትስ የምትቋምጠው??? እንግዲያውስ ከኛ ወገን አይደለህም። ይጠየቁ ቤተሰቦችህ፣ይጠና ማንነትህ።
Wogderes Tenaw ወግደረስ ጤናው
+1
የትዳር አጋሬን ነጠቁኝ ቀኑ ጨለመብኝ! ወ/ሮ ጎጃም ታፈረ
***//
ምዕ/ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ ኮኪ ቀበሌ በአብይ መሩ ጨፍጫፊ ሠራዊት ህዳር 22/2018 ዓ ም በግፍ የተገደለው የአቶ ፈንታሁን ቸኮል ባለቤት ቀኑ ጨለመብኝ የማነው አቤት የምል ትልለች!!
ስንዴ እናጭዳለን ሠራተኛ በጥዋት መያዝ አለብኝ ብሎኝ ነበር ከንጋቱ 12:00 ሠዓት ከቤት የወጣው። የስራ ሰው ነው ባለቤቴ ምን ይኑር ምን የሚያውቀው ጉዳይ አልነበረም። ሳይደውል ሲዘገይ ሠራተኛ ማግኘት አለማግኘቱን የጋራ ልጃችንን ደውለህ ጠይቀው እህል ላበሳስል የመከላከያ ኃይልም መጧል ይባላልና ዝም ያለ ለምድነው ብየ ስልክ አስደወልኩኝ ስልኩን ሌላ ሠው አነሳው። መከላከያ መጧል ተባልኩኝ ወጥቸ ሳይም አየኋቸው ግቢ በለው ወደ ቤት አስገቡኝ ጨነቀኝ የማደርገውን አጣሁ በጣም ፈራሁ የፈራሁት አልቀረም ምሽት 12 ሠዓት አካባቢ ልጁን ደግመህ ደውል ስለው ...................... እሬሳውን አንሱ የሚል ምላሽ ሠጡን።
የ3 ልጆቸን አባት ልጅ አሳዳጊውን ባሌን፤ ከቤቱና ከማሳው ውጭ የማያውቀውን የስራ ሠው የሆነውን ባሌን ................ ክፉዎች ነጠቁኝ። ዛሬ ቀኑ ጨልሞብኛል። .................. ከባድ ሀዘን ቤቱ ላይ ነግሷል።
የአብይ አህመድ አማራ ጠል ቅጥረኛ ሠራዊት አማራን አማራ በመሆኑ ብቻ ይገድላል፣ ይዘርፋል፣ ሐብት ንብረት ያወድማል። የዚህ እኩይ ድርጊቱ አርሶ አደር ፈንታሁን ቸኮልን የግፉ ሠላባ አድረጎታል። ወምበርማ ወረዳ ብቻ ከሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ እድሜ፣ ፆታ፣ ሐይማኖት ሳይለይ መነኳሳት ጨምሮ በአማራነታቸው ብቻ በግፍ ገሏል፣ ዘርፏል ሐብት ንብረት አውድሟል።
የ88ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
ህዳር 29/2018
የድል ዜና
የከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር በመጣመር ታላቅ ጀብዱ ፈጸመ
===========
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም 2ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር ተቀናጅቶ ሸኖ ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሷል::
የኃይለ ማርያም ክ/ጦር አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር ከአዲስ አበባ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሸኖ ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት የብልጽግናን አራጅ ሰራዊት ረፍርፎታል::
የብልጽግና ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት የሸኖ ከተማን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ አስገድዶ ለስብሰባ እያስወጣ ባለበት ወቅት የኃይለ ማርያም ማሞ አራተኛ ቦጋለ ሬጅመንት ከአባት አርበኞች ጋር ሰርጎ በመግባት ሶስት የጠላት ኃይል እስከወዳኛው ሸኝተው አምስቱን ደግሞ አቁስለዋል::
የወገን ምት ያበሳጨው የብልጽግና ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ያለ የሌለ ግትልትል ኃይሉን ከሰንቦና ጫጫ አግተልትሎ በሶስት ግንባር አውደ ውጊያ ቢያካሄድም በሚገባው ቋንቋ በማናገር ልክ አስገብተውታል::
ይህ ግትልትል ሰራዊት በፊጦ አላ መሥኖ ቀበሌ ግንባር÷ በጫጫ መንደር በአራጌቻ ግንባር እና በሸኖ ከተማ ዳር ለማጥቃት ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እና ተዋርዶ ወደመጣበት ጥሎ ፈርጥጧል።
በመጨረሻም የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አራተኛ የቦጋለ ሬጂመንትና የአባት አርበኞች ጠላት ያቀደውን የሥብሠባ አጀንዳ እንዲቋረጥ በማድረግ በሰላም ወደ ምድብ ቦታቸው ተመልሰዋል።
መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ ጌታሁን ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
ከድሮን የተረፈው የት/ቤት ንብረቶች #ወደሙ።
=======
የአረመኔው #አብይ አህመድ እና #የሎሌዎቹ ስርዓት
በማቻክል ወረዳ የግራቅዳምን መሰናዶ እና ፕሪፓራቶሪ ት/ቤት ሙሉ በሙሉ #አወደመ።
የአማራ ህዝብ ለሃገረ ግንባታ #ለሉዓላዊነት የከፈለውን መስዋዕትነት #በማሳነስ እና ወደኃላ በመተው እንደጨቋኝና ተስፋፊ በመቁጠር የቻሉትን #በመግደል ያልቻሉትን ማህበራዊ #እረፍት በመንሳት የአማራን ህዝብ የማጥፋት አላማቸውን እየፈፀሙና እያስፈፀሙ ይገኛሉ።
አላማቸውን ለማሳካት #ግራቅዳምን መሰናዶና ፕሪፓራቶሪ ት/ቤት በመግባት ሪከርድ እና ማህደር ክፍል ፣ ንብረት ክፍል ፣
የር/መምህራን ቢሮ፣ ሂሳብ ክፍል፣ ግዥ ክፍል፣ የፕላዝማ ማሰራጫ ሪሲቨር ክፍል፣ ላብራቶሪ ክፍል፣ የመማሪያ ክፍል ፕላዝማዎችን ..... ወዘተ ሙሉ በሙሉ #አው*ድመዋል።
ለአማራ ህዝብ ሆነ ለመጭው ትውልድ የሚጨነቅ ስርዓት ቢሆን በጦርነቱ ምንም ተሳትፎ የሌላቸውን እና በፋኖ የተጠበቁ #ተቋማትን ባላወደመ ነበር።
እንዲህ አይነት ጥላቻ ተሸክመው ሃገር #መምራት እንደማይችሉ #ማሳየት ይኖርብናል።
አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ፤
ኅዳር 28/ 2018 ዓ/ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት
ውስጥን በማጥራት ለላቀ ስኬት እየተጋ የሚገኘው አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ሜ/ጀ/ ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር✅
በትጋት ላይ...
የአፋብኃ ሰሜን አምሐራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሥራ አሥፈጻሚ አርበኛ አንተነህ ድረሥ ዕውነታን እንዲህ ይገልጣል፦
✅ያሰባሰበን ነገደ አምሐራ ብሔርተኝነታችን ነው።
✅ያሰባሰበን ጠላቶቻችን በከፈቱት መዋቅራዊ ዘርፈ ብዙ የሕልውና ጥቃቶች ነው።
✅ቋሚ ወዳጅም ቋሚ ጠላትም የለም።
✅የፈለገው ተዓምር ቢፈጠር በሕዝባችንና በተቋማችን ጥቅም ልንደራደር አንችልም።
✅በነገደ አምሐራነታችን አንደራደርም።
✅ከጎጥ እሳቤ የፀዳ ሰራዊትም ሆነ ሕዝብ መፍጠር አለብን።
✅ፖለቲካዊ ንፍቀ ክበቡ ከአምሐራ ምድር እሥከ መላ ኢትዮጵያ፣ ከአጎራባች አገራት እሥከ ዓለም የፖለቲካ ዕሳቤዎች መረዳትና የተሻለውን መምረጥ የትግሉ ባሕሪ ነው።
✅የተሰነዱ ሰነዶቻችን እንደ አምሐራ ወጥ ናቸው።
✅በታሪካዊ ርሥቶቻችንና ታሪኮቻችን ላይ አንደራደርም።
✅አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ተቋም በአሰራርና በመርህ የሚጓዝ ተቋም እንዲሆን መሠረት ያለው ሥራ እየከወንን እንገኛለን።
✅አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሥጋ ዝምድናን ፈጽሞ እንዲጸየፍ ተደርጎ ለአላማው እንዲታመን ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ እየሰራን ነው።
✅ዕድሚያቸው 30 ዓመታትን ያልሞሉ ቀምበጦች መሥዋዕትነት የከፈሉበትን የተቀደሰ ትግል ማንም አካል እንዲያራክሰውና እንዲቀልድበት መፍቀድ የለብንም።
✅ለጎንደር አንድነት እሥከ መጨረሻው ድረሥ ዋጋ ከፍለናል። ተመልከቱ አርበኛ ዮኋንሥ ንጉሱ፣ ኢንጅነር በየነ አለማው፣ አርበኛ ግዛቸው አሌ እና አርበኛ መምሕር ፀዳሉ ሙላት በድሮን ተመትተው በፈጣሪያቸው መሻት ለቁርጥ አለመውደቅ እና 04 አጃቢዎቻቸው መሥዋዕትነትን የተቀበሉት ለአንድነት እየሰሩ ባሉበት ኩነት ነው።
✅አሁን ላይ ትግሉ በወንፊት እየተንሳፈፈ፤ በሰፌድ እየተበጠረ እየተለዬ ነው። ትግሉ እየጠራ ነው።
✅ለአንድነት በራችን ክፍት መሆኑን በመሥዋዕትነታችን አረጋግጠናል።
✅ተወደደም ተጠላ መዳኛችን የምንገደልበት ነገዳችን አምሐራነት ነው።
✅እኛ አምሐሮች በመጽናት ጠላቶቻችን ማምበርከክ ግዴታችን ነው።
✅በአካልም፣ በአእምሮም እንዲሁም በሥነልቦናም የተገነባ የአማራ ሰራዊት መገንባት ግዴታችን ነው።
✅ከዘልማድ አሰራሮች ወጥተን በተቋማዊ አሰራር ለመጓዝ መሰረቶችን እያሥቀመጥን ነው።
✅ተቋማችን አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የወንጀለኞች ምሽግ እንዳይሆን አበክረን መሥራት ውዴታችን ሳይሆን ግዴታችን ነው።
✅በቀጠናችን ላይ የሚደረጉ የማሕበረሰብ እንግልቶችን፣ እገታዎችን፣ ግድያዎችን እና ልክ አልባ ድርጊቶችን የማሥቆምና ወንጀለኞችን የማጥራት ግዴታ አለብን።
✅የአማራ ሕዝብ ትግል እንደ ብአዴን ብልጽግና መሰረተ ድንጋይን ሳይሆን ያሥቀመጥነው ክብርና አንገተ ቅጥል የሆኑ መሰረተ አጽሞችን ነው።
✅ነጻነታችን የሚረጋገጠው በክንዳችን ነው።
✅ዕናምናለን እኛ አምሐሮች እናሸንፋለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊👊
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔐🔑
ፈለገ ውባንተ አባተ ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው ዘ ብሔረ ዓምሐራ
ብልፅግና ዝርፊያውን እና የድብደባ ወንጀሉን አጧጡፎ ቀጥሏል!!!!!!!!!!!
=== ===== ===== ====== =====
ሂዳር 27/2018 ዓ.ም
በምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሳርምድር ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው የብልፅግናው ሰራዊት ዝርፊያወችን እየፈፀመ ይገኛል።
በሰኞ ገበያ እና ድቦ ቀጠና በንፁሃን ላይ ዝርፊያውን እና የድብደባ ወንጀሉን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ከኛ ጋር ሆናችሁ ፋኖን አልወጋችሁም በማለት፦
➦ከ51 በላይ የግል ባለመሳራያ በሬውን ሸጦ የገዛውን መሳሪያ ቀምቷል
➦ ተዘግተው የነበሩ 13 ባለሆቴሎችና መኖሪያ ቤቶች ቁልፍ በመስበር ውስጥ ያሉ ሃብቶችን ሙሉ በሙሉ ተዘርፏል።
➦5 ባለትዳር ሴቶች ባሎቻችሁን አምጡ ተብለው ታስረዋል፤ 4ሰወች አሰቃቂ ድብደባ ተፈፅሞባቸው ሜዳ ተጥለዋል
➦ 28 የአካባቢወ ንፁሃን ከባድ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በእስር ላይ ሲሆኑ ሁሉንም እስረኞ ፋኖ ተኩስ ከከፈቱ ቀድመው እንዲመቱ ለማድረግ እና ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት በማድረስ አረመኔያዊ ድርጊት በመፈፀም ላይ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶ወንጀል የተፈፀመባቸው ግለሰቦችም
ከሰኞ ገበያ ቀጠና
በሬ ሸጠው የገዙት መሳሪያ የተወረሰባቸው
1. ደርብ ጌታቸዉ ክላሽ፣
2. አብይ ዮሀንስ ክላሽ፣
3. ይርሴ ክላሽ እና
በስም ያልተጣሩ 31 እንዲሁም 5 ሴቶች ፤
ድቦ ቀጠና=
1. መርሻ አክሊሉ ክላሽ፣
2. ሀብቴ ክላሽ፣
3. ወጣ ገበየ ክላሽ፣
4. መልካ ዘለቀ ክላሽ፣
5. መሰሉ ይመኑ ክላሽ፣
6. ልየው በላቸው ክላሽ፣
7 ሽፈራው ሙንየ እና ሌሎች 10
በድምሩ 51 መሳሪያ በመዝረፍ
3, የወደመ እና የተዘረፈ ሆቴል እና መኖሪያ ቤት
1. ትርንጎስጦታው =ሆቴል
2. ነበረ መለሰ =ሆቴል
3. አዳሙ አለባቸው =ሆቴል
4. ደርብ አድማሴ =ሆቴል
5. አኔ ይበልጣል =መኖሪያ ቤት
6. ተሜ ይልማ =መኖሪያ ቤት
7. የሹ ፈንታ=መኖሪያ ቤት
8. ጌትነት ይሜ=መኖሪያ ቤት
9. ሻምበል ይሜ=መኖሪያ ቤት
10. ምኒሊክ ይሜ =መኖሪያ ቤት
11. ተስፋው ታደሰ =መኖሪያ ቤት
12. ሙንየ ምሬ =መኖሪያ ቤት
13. መልካሙ አብየ =መኖሪያ ቤት
የተሰበረ ስለጠፋባቸው = ውለታው ወሌ፣
ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሜዳ የተጣሉ
1. ጌታቸው ደርብ፣
2. ደርብ አድማሴ፣
3. በላይነህ ተረፈ
4. መርሻ መሰሉ
ድብደባ ተፈፀሞባቸው የታሰሩ ወጣቶች
1. ማማር መንጋው፣
2. ሙሉቀን ዳምጤ፣
3. ውቡ ተምትም፣ በስም ያልተጠቀሱ ከ25 በላይ ንፁሃን ወጣቶች ናቸው።
ለአማራነት ብዙ ጓዶቼ በፊቴ ሲወድቁ አይቻለሁ፦
( አርበኛ ምህረት ወዳጆ አያሌው(ዋርካዉ)!
"ለአማራነት ብዙ ጓዶቼ በፊቴ ሲወድቁ አይቻለሁ፣ ብዙዎቹ ከህፃናት ልጆቻቸው በላይ አማራነት ዋጋ ሲያስቀድሙ በአይኔ አይቻለሁ። የኔም ሚስት በሆዷ ውስጥ ያለው ልጄም ለአማራነት በእስር ዋጋ እየከፈሉ ነው።
"ይሄ ለአማራነት የሚያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም። የነፍሰጡር ሚስቴ ወንጀሏ እኔን ማግባቷ ብቻ ነው! የኔም ወንጀሌ አማራነትን ማስቀደሜ ነው። ይሄ ወንጀል እንዳልሆነ በተግባር ሳላስተምር አላርፍም።
<<#አማራነት_ወንጀል_አይደለም>>
"ዋርካው ምሬ ወዳጆ በአንድ ወቅት ከተናገረው የተወሰደ !!"
