ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )

ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 057
المشتركون
+6824 ساعات
+3957 أيام
+1 39230 أيام
أرشيف المشاركات
ሁሌም በአራቱም ማዕዘን ጎጃም ሽዋ ወሎ እና ጎንደር እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ያሉትን መረጃ 24 ስዓት በማድርስ የሚታወቀው  የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ አዲሱን አካውንት ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ አማራዊያን እና ኢትዮጵያውያን https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973

ዝንታለም የማይረሳ ጀግንነትን ተላብሶ ለአማራ ህዝብ ደፋ ቀና ሲል ኖሮ የእውነት ትግል ታግሎ በእውነት የተሰዋው ሻለቃ አስቻለው ደሴ፤ የአሳምነው ግልገል! ጭንቅ የሚገላግል! የአስቻለው ደሴ ቀኝ! ለወዳጁ ታማኝ! የጎቤ ደም መላሽ! የጭቁን እንባ አባሽ! ሻለቃ አስቻለው ደሴ የኛ ዘመን አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ነው:: ሻለቃ አስቻለው ደሴ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ ምትክ ነው። የጦሩ ሙሽራ፣ እውነተኛው የነፃነት ታጋይ፣ ምሉዑ አማራ እና ሞት አይፈሬው ጀግና ወንድማችንን ያጣነው ባለመደራጀታችን ብሎም የጄኔራል አሳምነው ፅጌን "አንድ ሁኑ" የሚለውን ቃል ባለማክበራችን ነው። አንድ የሆነ ህዝብ ጀግኖቹን አሳልፎ በቀላሉ አይሰጥም። የተደራጀ ህዝብ መሀል ገብቶ ጀግናን ለይቶ ማጥቃት የሚችል አካል ሊኖር አይችልም። የመደራጀትን ጥቅም ለማወቅ የሻለቃ አስቻለው ደሴን ቤተሰቦች የደበደበው ግለሰብ አምና ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በፋኖ በአፍጢሙ መደፋቱ አስረጅ ነው። ሻለቃ አስቻለው ደሴ ከተሰዋ በኋላ ግለሰቡ "የእናንተ ልጅ በድሎናል" በሚል የሻለቃው ወላጆች ላይ ድብደባ በመፈፀም የዓይን ብርሃናቸውን እንዲያጡ አድርጓል የተባለው የወረዳው የሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና ሌሎች የወረዳው አመራሮች ናቸው አምና ከዚህ ምድር የተሰናበቱት። ይህ የመደራጀት ውጤት ነው። የተደራጀ ህዝብ አሸናፊ ነው። ነፍስ ኄር ወንድምሰው። የሞትክለትን አላማ ከዳር እናደርሳለን።

photo content

ሁሌም በአራቱም ማዕዘን ጎጃም ሽዋ ወሎ እና ጎንደር እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ያሉትን መረጃ 24 ስዓት በማድርስ የሚታወቀው  የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ አዲሱን አካውንት ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ አማራዊያን እና ኢትዮጵያውያን https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973

ሁሌም በአራቱም ማዕዘን ጎጃም ሽዋ ወሎ እና ጎንደር እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ያሉትን መረጃ 24 ስዓት በማድርስ የሚታወቀው  የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ አዲሱን አካውንት ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ አማራዊያን እና ኢትዮጵያን https://www.facebook.com/share/19D9uBuBwa/

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ የሽብር ወንጀል ተከሳሾች የሰነድ ማስረጃ አስተያየት በጽሁፍ አቅርበዋል ፤ ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረቡ አቤቱታዎችና የመብት ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥር 28/2018 ቀጠሮ ይዟል። ከአማራ ማንነታቸው ጋር በተያያዘ ታፍነው በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ከ300 በላይ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን ጉዳይ ሲመለከቱ የከረሙት ሶስት ዳኞች በሌላ ሶስት አዳዲስ ዳኞች ተቀይረው ነው የእለቱ ችሎት እንዲታይ የተደረገው። በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ ከአማረ መለሰ እና ደሳለኝ እጅጉ በስተቀር 14 ተከሳሾች በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጥር 19/2018 በነበረው ችሎት ከማ/ቤት ተገኝተዋል። ተከሳሽ አማረ መለሰ በአዋሽ አርባ እና በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከምርመራ ጋር በተያያዘ በደረሰበት ግፍ እና በደል የአዕምሮ ሕመም አጋጥሞት በአማኑኤል ሕክምና እየተከታተለ ስለሚገኝ ዛሬን ጨምሮ ለበርካታ ወራት ፍ/ቤት እየተገኘ አይደለም። ተከሳሽ ደሳለኝ እጅጉም ከአልባሳት ጋር በተያያዘ ከማ/ቤቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በችሎት ሳይገኝ መቅረቱ ተገልጧል። ጥር 19/2018 በነበረው በዚሁ ችሎት በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በቀደመ ቀጠሯቸው መሰረት የሰነድ ማስረጃ አስተያየት በጽሁፍ አቅርበዋል። በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፣ የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ እና የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ተሻገር በኩል የተለያዩ አቤቱታዎችና የመብት ጥያቄዎች ለችሎቱ ቀርበዋል። የም/ቤት አባልነት ያለመከሰስ መብታቸው ከመነሳቱ በፊት ሊከሰሱ እንደማይገባ በመግለጽ መብታቸው ተነስቶ ከሆነም ሕጉን በጠበቀ መልኩ ስለመነሳቱ ፍ/ቤቱም ሆነ ተከሳሾች በቃለ ጉባኤ ጭምር ተረጋግጦ ሊያውቁት እንደሚገባ በመጥቀስ ማስረጃው ይሰጣቸው ዘንድ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። በተያያዘም በስልክ ጠለፋ ተገኘ የተባለው የድምፅ ሪከርድ በሕጋዊ መልኩ በፍ/ቤት በኩል ሂደቱን ጠብቆ የተከናወነ ስለመሆኑ የክሱ እና የክርክር መዝገቡ እንዲመጣልን በማለት ትዕዛዝ ጠይቀዋል። በዐቃቤ ሕግ በኩል አሁን በከሳሽ በኩል ማስረጃ የሚቀርብበት እንጅ ተከሳሾች ማስረጃ የሚያቀርቡበት አይደለም ፤ ተከላከሉ ከተባሉም ያኔ የሚፈልጉትን መረጃ ከተለያዩ ተቋማት ጠይቀው ሊያስመጡ ይችላሉ ፤ በመሆኑም ማስረጃው ለምን እንደተፈለገ ግልፅ ባልሆነበት አስተያየት ለመስጠት ይቸግረናል የሚል ምላሽ ሰጥቷል። የስልክ ጠለፋውን በተመለከተ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ከሰጠ ተፈጻሚ እንደሚያድርግ ነው ከሳሽ የገለፀው። ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረቡ አቤቱታዎችና የመብት ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥር 28/2018 ቀጠሮ ይዟል። ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾች በሰጡት የሰነድ አስተያየት ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት ፍ/ቤቱን የጠየቀ ሲሆን ችሎቱም የተከሳሾችን የሰነድ አስተያየት ተመልክቶ ምላሽ ያስፈልገዋል ብሎ ሲያምንበት ትዕዛዝ እንደሚሰጥ ገልጧል። ተከሳሽ አማረ መለሰን በተመለከተም ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ተወስዶ እንዲታከም ለቀረበው አቤቱታ መጀመሪያ ተቋሙ በተሻለ የሕክምና ተቋም እንዲያሳክመውና ማሳከሙንም ሪፖርት እንዲያደርግ ያለው ፍ/ቤቱ አቤቱታውን ከዛ በኋላ የምናየው ይሆናል ሲል ገልጧል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረቡ አቤቱታዎችንና የሰነድ አስተያየቶችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥር 28/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል። በተመሳሳይ በእለቱ ፍ/ቤት ከቀረቡ የሽብር ተከሳሾች መካከል ንብረት ሕብስት አንዱ ነበረ። ዐቃቤ ሕግ በንብረት ላይ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽሎ እንዲቀርብ በሚል ትዕዛዝ የተሰጠው ቢሆንም አሻሻልኩት ያለው ክስ ገና አልተሻሻለም ከመባሉ ጋር ተያይዞ ፍ/ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 21/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። (አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥር 19/2018)

photo content

206ኛ ኮር ከጠላት የሚሰነዘር ማንኛውንም ጥቃት በመመከት አስፈላጊውን አጣፋዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችለውን የወትሮ ዝግጁነት ማጠናቀቁን አስታወቀ ጥር 19/2018 ዓ.ም =================================== የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የቀጠናውን ትግል በማቀጣጠል በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል የተቀናጀ ሲሆን ኮሩ በተመሰረተ ጥቂት ወራት በሁሉም ክ/ጦሮች በተደረገ ማጥቃት በተለያዩ ግንባሮች በጠላት ላይ የበላይነት መውሰዱን የኮሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል። ኮሩ የሚንቀሳቀስበት ቀጠና የጠላት የሎጀስቲክ፣ የሰው ኃይልና የካድሪ ማመላለሻ በመሆኑ ከፍተኛ ሜካናይዝድ ድጋፍ የሚሰጠው የጠላት ሰራዊት መንቀሳቀሱን መምሪያው የገመገመ ሲሆን የጠላትን የኃይል አሰላለፍ የሚመጥን የትግል ስልት መንደፉንም መምሪያው ገልጿል። ከደጀን -ሞጣ መርጡለ ማርያም እና ከደጀን ደንበጫ ባሉ ሁለት አውራ ጎዳናዎችን ተጠቅሞ ሎጀስቲክ እና ወታደራዊ ድጋፍ የሚሰጥበት የትኖራ ወታደራዊ ካምፕ በኮሩ ቀጠና መገኘቱን የጠቀሰው ኮሩ፤ የ602ኛ እና 501ኛ ኮር ዋና ማዘዣ መሆኑ የጠላት ኃይል ክምችትና እንቅስቃሴ በስፋት እንዲኖር ማድረጉን ጠቅሷል። የጠላት ሰራዊት የመዋጋትና የማድረግ አቅም ዝቅተኛ መሆን የአዋጊዎችና ወታደራዊ መኮንኖች ጦርነቱን ለግል ጥቅም ማካበቻ እያዋሉት መሆኑን የገመገመው 206ኛ ኮር ጠላት የሚያደርገውን ማንኛውንም ትንኮሳ በመመከት ከባድ አጠፋዊ ምላሽ መስጠት የሚያስችለውን የወትሮ ዝግጁነት ማጠናቀቁን አስታውቋል። የአረመኔው ሰራዊት ከዚህ ቀደም ባደረጋጀው ትንኮሳዎች እና በወገን ኃይል ፍላጎት የተደረጉ ግዳጆችን የተመለከተው 206ኛ ኮር በደጀን፣ በጃማ፣ በስናን ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረ ኤልያስና ጎዛምን አካባቢዎች በተደረጉ ግንባሮች ክ/ጦሮች ባስመዘገቡት ትልቅ ድል የቀጠናውን ትግል ያቀጣጠለና የጠላትን የድንኳን ፕሮፓጋንዳ የበጣጠሰ መሆኑን ኮሩ አክሎ ገልጿል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

photo content
+3

ሁለንተናዊ ህዝባዊ ንቅናቄ  ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል‼️        ****            19/05/2018 ዓ.ም የዋድ አዲስ ዓለም ከተማ የህዝብ መድረክ በመፍጠር የማህበረሰብ  ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ የ99ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አመራሮችና የደምበጫ ወረዳ ጊዜዊ መንግስት አመራሮች ተገኝተውበታል። በህዝባዊ መድረኮቹ ስለ ትግሉና ድርጅቱ ወቅታዊ ሁኔታ  እና ተዛማጅ ጉዳዮች በዋድ አዲስ ዓለም ከተማ  ህዝብ ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም የከተማው ህዝብ የተጀመረውን የህልውና ትግል አንድነቱን ያበሰረው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መደሰታቸውን ገልፀው  በውጊያም በሎጀስቲክም ድጋፋቸውን  አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል። በውይይቱ  ያለፉ ችግሮችን በጥልቀት ሀሳባቸውን በመግለፅ፣ ስለቀጣይ ፋኖ እና ህዝቡ  መስተጋብር እንዲሁም የትግል ድርሻ ዙሪያ በዝርዝር ተነስተው በዋድ አዲስ ዓለም ከተማ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ቀጣይ  አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል። በህዝባዊ መድረኮቹ ከውጊያ ጎን ለጎን  የህዝባዊ አስተዳደር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተመላክቷል። ዓመታት ያስቆጠረውን የህልውና ትግል በውስጣችን ያለውን ባንዳ አስወግደን ህይዎታቸውን ሰጥተው፣አካላቸውን አጉድለው ፣ግንባራቸውን ሰጥተው ፀሀዩ ብርዱ ያልበገራቸው እንቁ የአማራ የህልውና ታጋይ ወንድሞቻችን ከጎናቸው ነን በማለት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም የተጀመረው የአንድነት ብስራት የህልውና ትግላችን ምሰሶ መሆኑን በመረዳት አማራ የሆነ ሁሉ አማራዊ ስሜት አንገብግቦት ድርጅቱን መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል። አዲስ ትውልድ !!አዲስ አስተሳሰብ !!አዲስ ተስፋ !! ድል ለአማራ ፋኖ!! የደምበጫ ወረዳ ጊዜዊ መንግስት ሚዲያ ግንኙነት ክፍል

photo content
+3

photo content
+6

598 የአብይ አህመድ ሰራዊትን ደምስሶ 200 ምርኮን የተጎናጨው ተወርዋሪው የአፋብን ጦር ይህ ነው:: ነግሬሽ ነበረ ባጥር ተንጠልጥዬ ከፋኖ መሳሪያ አታመልጪም ብዬ። ብልፅግና በቃታ መሳሪያ ሁሉ በአ
598 የአብይ አህመድ ሰራዊትን ደምስሶ 200 ምርኮን የተጎናጨው ተወርዋሪው የአፋብን ጦር ይህ ነው:: ነግሬሽ ነበረ ባጥር ተንጠልጥዬ ከፋኖ መሳሪያ አታመልጪም ብዬ። ብልፅግና በቃታ መሳሪያ ሁሉ በአንዳንድ ግንባር ማሸበር ጀምሯል ሌላውን እማ ፎጣ ለባሹ በከዘራ እየማረከ ተረከበው። በነገራችን ላይ ለነገይቱ በእጃችን ለምትወሰነው ኢትዮጲያ በማለት እንጂ ታንክም መታጠቃችንን ጠላት ያውቃል። እስካሁን እየሰራን ያለነው መከላከያን ከእልቂት የማትረፍ ስራ ነው። አብይ ድሮንን የራሱን ወታደር መደምሰሻ አድርጎታል😂😂😂😂

አፋብን ከቀጠናዊ ጉዳዮች አንፃር /////////////////////////////// ምስራቅ አፍሪካን እያመሰው ያለው የውክልና ጦርነት አሁን ደግሞ ፊቱን ወደ ሰሜን ኢትዮጲያ ሃይሎች እያዞ ይገኛል። በቀጠናው ያለው የሃይል ፍላጎት ከሃገራት ብሔራዊ ጥቅም አኳያ ውስብሰብ እና ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ጦርነት ተደቅኗል!! የምስራቅ አፍሪካን ሰላም እያወከ ያለው የመካከለኛው ምስራቅ ፍላጎት ደግሞ በዓይነቱ ለየት ያለ ጦርነትን የወለደ ሲሆን በተለይም ሱዳን የገባችበት ቀውስ በእጅጉ አሳዛኝ ሰብአዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን የፈጠረ ሲሆን ሃገራት ከብሔራዊ ፍላጎታቸው ተነስተው ምስራቅ አፍሪካን የሚያተራምሰው የገልፍ ሃገራት ጦርነት ሱዳንን፣ኢትዮጲያን፣ኤርትራን፣ሶማሊያን፣ጅቡቲን እና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ሌሎች ቀጠናዎችን ጨምሮ ሰፊ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ሁለቱ ሃብታም የገልፍ ሃገራት በውክልና ጦርነት የመንን ጨምሮ ሶማሊያን እና ኢትዮጲያን ጨምሮ ለማፈራረስ እየሰሩ ይገኛሉ። የቀጠናው ቀውስ ጠማቂ የሆነው ብልፅግና ባጋጠመው ድፕሎማሲያዊ ክሺፈት እና የኢኮኖሚ ጫና አድስ ጦርነት በመፍጠር አድስ ሃገር ለማዋለድ የጀመሩት እንቅስቃሴም ሌላው ፈተና ይሆናል!! ስለዚህ አይቀሬው ጦርነት በኤርትራ እና በኢትዮጲያ መካከል ሆኖ ሃገራት እንደ ብሔራዊ ጥቅማቸው ከሁለት ጎራ ተሰልፈው ወታደራዊ ሎጀስቲክሶችን በመደገፍ ላይ ተጠምደዋል!! ስለሆነም የምስራቅ አፍሪካው ቀውስ ቀጠና ውስጥ የአማራ ህዝብ እና የአማራ ፋኖ ትግል ምን ማድረግ አለበት የሚለውን በትግላችን ውስጥ ያጋጠሙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶችን በመተንተን ፣የሚያመጣውን ስጋት እና ዕድል ታሳቢ በማድረግ ማዘጋጀት ያስፈልጋል!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መጭው ዘመንን ታሳቢ ያደረገ ድፕሎማሲ፣ወታደራዊ አቅም እና የስትራቴጅክ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይጠበቅበታል!! ድርጅታችን መሬት ላይ ጠንካራ የሃይል ሚዛን ሊፈጥር ይገባል። በየቀኑ የሚለዋወጠውን የቀጠናውን አሰላለፍ ታሳቢ ያደረገ አማራዊ ዝግጅት ማድረግም እንድሁ ተቀደሚ ስራችን ሊሆን ይገባል🙏❤

የሙጃ ማርያም ከተማ ኗሪው ወጣት ባለሐብት በአገዛዙ ሰራዊት በጭካኔ ተገደለ! በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ግዳን ወረዳ መናገሻ ሙጃ ማርያም ኗሪ የሆኑት ወጣት ባለሐብት አራጋው ሲሳይ በአረመኔው ብልፅግና ሰራዊትና አመራሮች ጥር 17/2018 ዓ/ም አመሻሽ 2:00 ሰዓት ላይ በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ አንድያ ህይወቱ ልታልፍ ችላለች። በግዳን ወረደ ብልፅግና አመራሮችና በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት አዛዦች የጦስ ዶሮ የሆነው ወጣት ባለሐብት በተሸረበበት ሴራ 5ሚሊዮን ብር ለአብይ አህመድ ወንበር መፅናት ለሚታትሩ መከላከያ አመራሮች የሐብት ማከማቻ ግዛት እንዲከፍል፣ባይከፍል እንደሚገደል ውሳኔ ተወስኖ እንዲከፍል ሲነገረው እንደሚገድሉት ስላወቀ ካሶኒውን ሽጦ ቢከፍላቸውም የፋኖ ደጋፊ ስለሆነ መረሸን አለበት በሚል ውሳኔ በአረመኔዎቹ የጦስ ዶሮ ሊሆን ችሏል። ይህንን ግድያ ያስተባበሩትና የውሳኔ አካል የሆኑት 1ኛ. እንዳለው አባተ:- የግዳን ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ 2ኛ. አማኑኤል አያሌው:- የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ 3ኛ. ሰማኝ ባዮ:- ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ እና 4ኛ. ሙጃ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሲሆኑ በቀጥታ በጄኔራል አሰፋ ቸኮል ትዕዛዝ ከዚህ በፊት እያንዳንዳቸው 1.5ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉና ካልከፈሉ እንደሚረሸኑ ተነግሯቸው የተጠየቁትን ከከፈሉ በኋላ ወጣቱ ባለሐብት እንዲረሸንና አፈፃፀሙን እንዲያስተባብሩ የተሰየሙ ጥቁር አማራዎች መሆናቸውን የውስጥ መረጃዎች አሳውቀዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው በመሩት የመንግስት ሰራተኞች መድረክ ላይ መንግስት አገልጋዩን ሰብስቦ ሰሞኑን የሚረሸን ሰው አለ በማለት የተናገረ ሲሆን በተናገረ ሁለት ቀን ባልሞላው ውስጥ ወጣቱን ባለሐብት አምስት መከላከያዎች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ደፈጣ ይዘው በአምስት ክላሽንኮፍ ጥይት በሳስተው ከገደሉት በኋላ ለሌሎች ትምህርት ይሆናል በማለት እጅና እግሩን በሳንጃ በመቆራረጥ፣እንዲሁም ብልቱን በመቁረጥ ህዝቡን እንዳሸማቀቁት ታውቋል። ህዝቡም በዚህ ድርጊት ማዘኑንና ከአብራኩ በወጡት የአፉኝት ልጆች እየታረደ፣እየተሳደደ፣እየተደፈረ፣ሐብት ንብረቱ እየተዘረፈ መሆኑን በመረዳቱ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ መግባቱ ታውቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  ህዝብ  ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ     ጥር:-19/2018 ዓ/ም

photo content

"ከዚህ በኋላ የአማሮች ችግር በአማሮች ነው የሚፈታው፤ ከሌሎች ቀና ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር አብረን እንሰራለን:: ውስጣዊ ክፍተቶችን እየዘጋን ከሌሎች ጋር ስርዓት ባለው መልኩ እንጓዛለን። የፋሽስቱ አብይ መንግስት እስከምንቀብረው ድረስ ራሱን እያታለለ ይኖራል። ከማን ጋር መገናኘት እንዳለብን የምንወስነው እኛ ነን፤ እነማን ጋር ታክቲካል እና ስትራቴጅክ አሊያንስ እንደምንፈጥር እኛ ነን የምንወስነው። አሁን ድርጅት አለን ከዚህ በኋላ ነው ብዙ ጥያቄዎች የሚመለሱት። እነሱ (ጠላቶቻችን) ቸኩለው ይናገራሉ፤ ጠንከር ያለ ምት ሲመቱ ህወሓት ወጋን ይላሉ። የወጋው ግን ፋኖ ነው። ጄኔራሎች የሚባሉት ግልብ (በላይ በላይ ያለ ብቃት) ማዕረግ ያገኙ ስለሆኑ እነዚህ ኃይላት አንድ ከሆኑ ያልቅልናል በሚል ፍርሀት ውስጥ ስላሉ ብዙ ያወራሉ።" በማለት ጄኔራል ተፈራ ስለ ትብብር እና አጋርነት የሰጡት ማብራሪያም ቅቡልነት ያለው ነው። በዚህ ላይ ሀሳብ ለመጨመር ብሞክር ማበላሸት ይሆንብኛል። ጄኔራሉ በንግግራቸው "ራሳችን እንበቃለን። እኛ ነን ወሳኞቹ ብለን ነው ወደ ትግል የገባነው።" በማለት ራሰ በቅነትን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። አክለውም "በዋነኛነት ብልጽግናን ለመምታት ራሳችን ነን የምንቆመው፤ የጋራ ጠላትን በጋራ መምታት የጋራ ፍላጎትን ለማሳካት ይረዳል። ከሌሎች ጋር የምናደርገው ውይይት ይኖራል። እኛ ጋር ለመስራት ጥያቄ ያቀረቡ አሉ፤ ለምሳሌ የአፋር ኃይል። ሌሎችን ሳንይዝ ኢትዮጵያን መስራት አንችልም።" ከሚል ማብራሪያ ጋር የትብብርን አስፈላጊነትም ጠቁመዋል። "አላማችን ነው ከማን ጋር መተባበር እንዳለብን፤ ማን ጋር እስከየት መሄድ እንዳለብን እንድንወስን የሚያደርገን።" የሚል ሀሳብም ሰንዝረዋል፤ ጄኔራሉ። "አንድ ቁጥር ጠላታችን ብልጽግና ነው፤ በቀኝ በግራ የምናየው ሌላ ጠላት የለንም።" ማለታቸውንም ልብ ይሏል። ይህ ማለት እርብርብ ማድረግ ያለብን ብልጽግና ጋር ነው፤ ጠላት ማብዛት የለብንም ማለት ነው። ሁላችንም ይህንን መገንዘብ አለብን። የእነ ዘሜ ወንድም የጦር ጠበብቱ እና የፋኖ ፊታውራሪው ጄኔራል ተፈራ ማሞ የተናገረው🔥 የላስቴይቱ ልጅ የበጌምድሬው! ሀገር ሲናጋ አለሁ የሚለው!! ተብሎለታል:: የአዳም (አደም) ዘር በሄዋን (ሀዋ) ፊት ክብር እና ሞገስ የሚኖረው ልባም እና ጀግና ሲሆን ብቻ ነው:: በእነ አባ ኮስትር ዘመን ልጃገረዶች:- የእጅጉ ዘለቀ የነ በላይ ነኝ! በርግጎ የሚሸሽ ፈሪም አይነካኝ! ብለዋል:: አንተ ቁመህ ተኩስ እነሱ ይሩጡ! የአባ ኮስትር አሽከር ገብሬ ባለቁርጡ! ሲሉም ነበር:: ይህን ሁሉ ያሉት ሞት አይፈሬዎችን እነዚያን የጋሜ ጦር አባላት እነ ገብሬን ለማድነቅ ነው:: የእነሱ አምሳያው ሸማቂው ኮማንዶ ጄኔራል ተፈራ ማሞ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ጀብዱ ፈፅሟል:: አበባው ታደሰ ሲፈረጥጥ ያስማረከውን ትጥቅ እና የሰው ኃይል በጀግንነት ተፋልሞ ያስመለሰው ጄኔራሉ ነው:: ያኔ በጃንሆይ ዘመን ለጋሜዎቹ ለእነ ገብሬ አንተ ቁመህ ተኩስ እነዚያ ይሩጡ እንደተባለው በኢትዮ ኤርትራ ዘመንም እንደ ጄኔራል ተፈራ ያሉ ጀግኖች ታሪክ ሰርተዋል:: ዛሬም ጄኔራሉ ታሪክ እየሰራ ነው:: እሱን ከፊታችን አድርገን ተከትለነው ስንጓዝ ጠላትን የማናሸንፍበት ምንም ምክንያት የለም:: ይህ ትግል ወታደራዊ ልሂቃንን ይሻል:: ሀቀኛውን ጀግና ማክበር እና መከተል አትራፊ ያደርገናል::

photo content

የመዋቅር ግንባታና ተሐድሶ ተጠናክሮ ቀጥሏል!! ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ዛሬም በጠራ የአደራጃጀት መዋቅር ብቅ ብሏል!! ትግል ቅብብሎሽ ነው። በትግል ውስጥ መሰዋት፣ ጉዳትና መክዳት ያሉና የነበሩ ናቸው። ሁሉም የየራሳቸው መገለጫ ቢኖራቸውም በኛ የትግል ምራፍ ደግሞ መክዳት ከማህበረሰባችን ወግና ባህል አንጻር ሲበዛ ሰላቶነት ፣ አቅመ ቢስነትና እና ወዶ ገብነት ነው። ሰሞኑን የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ የነበረ ለአገዛዙ ያደረ በመሆኑ ዳግም አደረጃጀቱን በማስተካከል በሚታወቅበት ጠላትን እረፍት የመንሳትና የህዝባችንን የህልውና አደጋ የመቀልበስ ትግል በአዲስ መንፈስ እራሱን አደራጅቷል። ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር በግለሰቦች ስብዕናና ዝና ያልተመሰረተ በመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደሙ አስደማሚ ግዳጅና ኦፕሬሽኖችን ለመስራት እራስን የማዘጋጀት ቅድመ ስራዎችን ጭምር አከናውኗል በመከወን ላይም ይገኛል ። በመሆኑም ዛሬ ጥር 19/2018 ዓ.ም ክፍለ ጦሩ የሚከተለውን አዲስ አደረጃጀት አዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል። 1. አርበኛ ተመስገን አብርሀም------------ዋና ወታደራዊ አዛዥ 2. አርበኛ ያብባል ፈለቀ-------------ምክትል ወታደራዊ አዛዥ 3.አርበኛ ጌታቸው ሞገስ--------- ዋና ወታደራዊ ዘመቻ ኃላፊ 4.አርበኛ አያና ሆነ -------------ምክትል ወታደራዊ ዘመቻ ኃላፊ 5. አርበኛ ባይነሳኝ እንግዳው-------ፋይናስ ኃላፊ 6.አርበኛ ታደሰ አሰፋ-----------ምክትል ፋይናስ ኃላፊ 7. አርበኛ ባንቲደር እውነቱ ----------ቁጥር እና ኦዲት ኃላፊ 8.አርበኛ ጌትነት ስመኝ------------ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ 9.አርበኛ ገበየሁ አማረ--------ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ 10. አርበኛ ነጋ ሆነልኝ------- የሰው ኃይል ኃላፊ 11.አርበኛ ሻለቃ ታዴ አለባቸው ------------ሎጅስቲክስና ኦርዲናስ ኃላፊ ሆኖ ተደራጂቷል። ስለሆነም ማህበረሰባችንም ሆነ የትግል ጓዶቻችን ትግላችን የህልውና ነውና በግለሰቦች ፍላጎትና ጥቅም ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ የህዝባችንን ህልውና ሳናረጋግጥ እሚዝል ክንድ እሚደክም ጉልበት አልተላበስንምና ከእንደዚህ ቀደሙ በእልህና በቁጭት የምንታገል መሆኑን ጭምር መግለጽ እንፈልጋለን። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር!!! ጥር 19 / 2018 ዓ.ም