ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 619
المشتركون
+124 ساعات
+3977 أيام
+1 06030 أيام
أرشيف المشاركات
አሳዛኝ ዜና!!! የአብይ አህመድ አገዛዝ ንፁሀንን ያነፃፀረ የድሮን ጥቃት በሻሁራ ከተማ ላይ ፈፀመ!!! ጨፍጫፊውና አውዳሚው ደም መጣጭ ፀረ አማራ የአገዛዙ ሰርአት በእግረኛ ሜካናይዝድ ጦር የአማራን
+2
አሳዛኝ ዜና!!! የአብይ አህመድ አገዛዝ ንፁሀንን ያነፃፀረ የድሮን ጥቃት በሻሁራ ከተማ ላይ ፈፀመ!!! ጨፍጫፊውና አውዳሚው ደም መጣጭ ፀረ አማራ የአገዛዙ ሰርአት በእግረኛ ሜካናይዝድ ጦር የአማራን ህዝብ ለእልቂትና ለስቃይ መዳረጉ አልበቃው ብሎ፤ አሁን ላይ በየ ሀገራቱ ተንከራቶና ለምኖ በሚያስገባቸው ድሮኖች ንፁሀንን ያነፃፀረ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል። በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ የድሮን ጥቃትና ቅኝት በተለይ በዚህ አንድ ሳምንት በማያቋርጥ መልኩ በቀንም በማታም የተደጋገመ ሲሆን ህዝባችን ለሽብርና ለሞት እየዳረገ ይገኛል። በዛሬው እለት የካቲት 23/2018 ከጧቱ 1:00 ስአት ገደማ ሻሁራ ከተማ ቀበሌ01 ዉሀ የሚቀዱ ንፁሀን ላይ ያነፃፀረ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህ ጥቃት ወ/ሮ አንጓች የሀለም፣ ወጣት ናንየ ደጉ እና አቶ አለሙ አቢታ ለእልፈተ ሞት ሲዳረጉ ዋወይ የሚባል ንፁሀንም ከባድ ቁስለኛ ሆኗል። እንዲሁም አንድ የንፁሀን ቤት ሊወድም ችሏል። ተስፋ ቆራጩ የአገዛዙ ስርአት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶት የጀግኖችን የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ክንድ መቋቋም ሲያቅተው እና ከወረዳው ሰራዊቱን በመደምሰስና በመማረክ አቅመቢስ የሆነው፤ አሁን ላይ እንደ አማራጭ ንፁሀን ህዝባችን ላይ ሂሳብ ለማወራረድ የሚሄድበትን እርቀት ምን ያህል በወታደራዊም ሆነ በፓለቲካዊ ዘርፍ የወረደና የተቀዣቀዠ መሆኑ የአራት ኪሎ እድሜው ያበቃ እንደሆነ ያሳያል። ፈጣሪ የተሰው ንፁሀንን ነብስ ይማር!!! ወዳጅ ዘመዶቻቸውን መፅናናት ይስጥልን። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ የካቲት 23/2018

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ለተከታታይ ሶስት ወራት  ወታደራዊ ፖለቲካዊ ስልጠና ያሰለጠናቸውን ምልምል የፋኖ ወታደሮች  በትላንትናው ዕለት  አስመርቋል። ​የአብይ አህመድ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመው ያለውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እና የህዝቡን ነፃነት ለማስከበር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር እንደ ንስር ተወርዋሪ የፋኖ አባላትን  አስመርቁን ቀጥሏል። ​ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ከአዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅርብ ርቀት ላይ የአብይን አየር ወለድ ኮማንድ በገባበት እየገባ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝቡን ሰላም ለማስከበር  ከሊቅ እስከ ደቂቅ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል። ሆኖም በዛሬ ዕለት ​ከ400 በላይ የሚሆኑ የኮሩ ፋኖ አባላት በስነ ልቦናና በአካል ብቃት የበቁ   ስልጠና የወሰዱ ሲሆን  እንደ ንስር ተወርዋሪ ተዋጊዎቹ የሕዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ በብቃት የተዋጣላቸው ሰልጣኞችን አስመርቋል ሆኖም ሰልጣኞች በቀጣይ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።  ይህ ስልጠና አንድ ይለህልውና አደጋ ላይ ያልን እዝብ ነጻ ለማውጣት ብቻ ነው  ።  ስርዓቱ የሞት ድግስ ደግሶብን ከምድር ገፅ ለማጥፋት እየሰራ ባለበት ስዓት በዱር በገደሉ የህይወት ድልድይ እየገነባን የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በመሆን ሰልጣኞቹ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በሚሰጠን ማንኛውንም ግዳጅ ለመቀበልና በድል ለመወጣት የሀገራችንን  ሉዓላዊነት እና የህዝባቸውን ነፃነት በአጥንታቸው ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል። በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ የከፈሉበት የህልውና ትግል ነው። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪዎቻችንን ከትግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ አለባችሁ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውረድን በማለፍ ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን ሲል የ አሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ እያሱ መልዕክቱን አስተላልፏል። በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት በመላው አማራ  ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአብይ አህመድ የአረመኔዊ ድርጊት  በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ። እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 23/06/2018 ዓ.ም

74ኛ ክፍለ ጦር ላይ የነበሩ ችግሮቻችን ቤታችን ዘግተን በመወያየት ፈተናል በአዲሰ መልኩ ከክፍለጦር ጀምሮ እስከ ሻለቃ ድረስ በአዲስ ሪፎርም በመስራት ተጠናቋል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ መሪያችን አረበኛ ዘመነ ካሴ እንዳለው ቤታችን ዘግተን ችግራችን ፈተናል የበላይ እስትንፋስ ታደሰው እንደንስር መጥተዋል። #የቴወድሮስ_ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እና #_የኮር አመራሮች#የ74ኛ ክፍለጦር አመራሮች#_የሻለቃ አመራሮች እና #_ሻንበል አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ጥያቄዎች የነበራቸው #_በክፍለ_ጦሩ ውስጥ የነበሩ አባላት #_ለ7ቀን የፈጀ ጥልቅ ግምገማ ና ውይይት በማካሄድ የውስጥ ችግሮች በመለየት መፍትሔ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ ተችሏል። ውይይትና ግምገማውን መሰረት ያደረገ አዲስ የስራ ስምሪት በመስጠት ተጠናቋል። በተግባር በዉጊያ የተሸነፈው የአብይ ቡድን በሚዲያ ለመከፋፈል ያለ እረፍት 24ሰዓት ቢሰራም እኛ ግን ቤታችን ዘግተን በመምከር ችግራችን በመፍታታት በአንድነት የወጣንለትን ዓላማ በማሰብ ጦራችን በመሰብሰብ የጠላት ቅስም መስበር ችለናል። ከዚህ በሗላ መሪዎቻችን እና ድርጅታችን የሰጠነን ተልእኮ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ( ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም ) የካቲት 23/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የካቲት 23,06,2018ዓ.ም 102ኛ ኮር ታሪክ ሰርተዋል:: =================== * በዓድዋ ድል መታሰቢያ ቀን የካቲት 23/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ
+2
የካቲት 23,06,2018ዓ.ም 102ኛ ኮር ታሪክ ሰርተዋል:: =================== * በዓድዋ ድል መታሰቢያ ቀን የካቲት 23/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ አንሙት ያዛቸው በኮማንዶ ዳንኤል ካሳሁን የሚመራው የኮማንዶ ሻለቃ ታሪክ ሰርቷል ። * ጠላት በሌሊት ከአዴት ተነስቶ ይልማና ዴንሳ ወረዳ ክልልት ቀበሌ ጨጮ በር ጎጥ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ነበልባሎቹ የ11ኛክፍለ ጦር ልጆች በጠላት ላይ ባደረጉት ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከ12 በላይ የአገዛዙ ሚሊሻን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ የተሳካ የደፈጣ ጥቃት መፈፀም ችለዋል ። * በደፈጣ ጥቃቱ የተዝረከረከው ሚኒሻ ብትንትኑ ወጥቶ እግሩ እንዳደረሰው በመፈርጠጥ ላይ እያለ ከአዴት ተንቀሳቅሶ የአብይ መከላከያ ሠራዊት ሽፋን በመስጠት አውጥቶ ወደ መጣበት ይዞ ተመልሷል። ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

እኔ ሁሌም ግርም ከሚለኝ ነገር....! - እንዴት የአንድን ሰው ስልጣን ለማስጠበቅና ለማስቀጠል ይህን ሁሉ መሰዋትነትን ይከፍላል ?! 🤔 - እንዴት ይህ የማይረባና ሀገር አፍራሽ የሆነ ከንቱ የብል
+3
እኔ ሁሌም ግርም ከሚለኝ ነገር....! - እንዴት የአንድን ሰው ስልጣን ለማስጠበቅና ለማስቀጠል ይህን ሁሉ መሰዋትነትን ይከፍላል ?! 🤔 - እንዴት ይህ የማይረባና ሀገር አፍራሽ የሆነ ከንቱ የብልፅግና ፖለቲካ መረዳት ተሳናችሁ ?! 🤔 - እንዴት ህዝባችሁን ልታሰቃዩ ፥ ልትገድሉ ፥ ልትዘርፉ ፥ ልታጠፉ ፥ ሀገር ልታፈርሱ ወደዳችሁ ?! 🤔 ▪️ሀገሪቷ የምታውቀው "የሀገር መከላከያ ሰራዊት" ዳር ድንበር ጠባቂ ፥ የሀገር ዘብ እንጂ የአንድ ሰው ስልጣን አስጠባቂ ሆኖ ሀገር የሚያፈርስ፤ ሰፍሮ - አደር መከላከያን ተይቶም አይታወቅም ። - አሁንም ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ Amhara Fano National Movement (አፋብን) ወንድሞቻችሁን ተቀላቅላችሁ ሀገራችሁን አድኑ ! ። ይህን የምህረት አዋጅ አሁንም አልረፈደምና አፋብን ተቀላቀሉ !!!

"እንኳን ለመላው አለም የጥቁር ህዝቦች የድል ቀን በአል አደረሳችሁ አደረሰን! ከ130 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያዊያን ያሳኩት የዓድዋ ድል በዘመናት መካከል ሁሌ የሚታወስ አይረሴ የታሪክ ከፍታ ነው። ለዚህም ድል የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአመራር ጥበብ፣ የመንግሥታቸው ጥንካሬና የሀገሪቱ የባሕልና የሃይማኖት ተቋማት ጥንካሬ ነው። ዳግማዊ ምኒልክ ምንም እንኳ በዘመኑ በተፈጠረው ሀገራዊ ችግር ምክንያት ጦርነቱን ባይፈልጉትም የመጣው ወራሪ ኃይል አገርና ሃይማኖት የሚያጠፋ መሆኑን ስለተረዱ “. በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጥህም፤” በማለት ወደ -2ማይቀረው ጦርነት ገቡ፤ የሰውን ልጆች ታሪክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀይር ድልንም ተጎናጸፉ። የዓድዋ የድል በዓል የጥቁር አፍሪካዊያን ቀን ሲሆን አፄ ምኒልክ ደግሞ ጥቁሮችን መርቶና አዋግቶ የጥቁሮችን ሰውነት፣ አሸናፊነት፣ መሪነትና ንጉስነት በዓለም አደባባይ ላይ ከፍ አድርጎ ያስየ የአፍሪካና የመላው ጥቁሮች መሪ ነው። የዓድዋን የድል በዓል ስናስብ ሰውነትን ከቀለም መጋርጃ ያላቀቀውን የመጀመሪያውን የጥቁሮች መሪም እናስባለን፤ ዓድዋን ስናከብር በዓድዋ ላይ ታሪክ የሰሩትን እናከብራለን፤ በዓድዋ ላይ ታሪክ መስራት እንደሚቻል ያሳየውንና ታሪክእንዲሰሩ የመራውንም እናከብራለን። ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የአሸናፊነት ዘመን መጀመሪያ ነው፤ የዘመኑ ፈጣሪ ደግሞ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ይባላል። ውድ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካዊያን እንኳን ለዚህ ታላቅ ቀን አደረሳችሁ!!! ዓድዋ በዓለም ላይ ላሉ የጥቁር ሕዝብ ሀገራትና የጥቁር ሕዝብ መብት ተከራካሪዎች በሙሉ የወኔያቸው መፍለቂያ፣ የንግግራቸው መነሻ ነው። ምንም እንኳ አብዛኞቹ ሀገራት እስከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የነጻነት ትግል ባይጀምሩም የዓድዋ ድልና ኢትዮጵያዊያን በዓለም ላይ የነበራቸው ተሰሚነትና ተሳትፎ ትግላቸውን ማፋፋሚያ ስንቅ ሆኗቸዋል። በዚያ ዘጠና ከመቶ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በቅኝ ግዛት በባርነት በሚኖሩበት ዘመን፣ ጥቁርከአራተኛ ክፍል በላይ እንዳይማር ሕግ ሆኖ በተሰራበት ዓለም፣ በአሜሪካ ጥቁርና ነጭ አንድ ቡና ቤት መጠቀም በአንድ አውቶቡስ መሄድ በማይችሉበት ዘመን፣ መላው አፍሪካ፣ ኤዢያ፣ ላቲን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ በቅኝ ተገዢነትና በድህነት አረንቋ ሰጥመው በነበሩበት ሰዓት ኢትዮጵያ ዘመን ያፈራውን የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ እድገት ተቋዳሽ በመሆን አውሮፕላኖቿ ሰማዩን፣ የንግድና የጦር መርከቦቿ ውቅያኖሶችን፣ ወጣቶቿ ጥቁሮች የማይገቡበት ዩኒቨርሲቲዎች አካል ሆነው ማየታቸው ለጥቁር የመብት ተሟጋቾች የየዕለት የትግል ስንቃቸው ነበር። የዓድዋ ድል በዓል የመሪዎችና የሕዝቡ ትብብር ከነጻነት ፍላጎት ጋር ተዳምሮ የተገኘ ስኬት ነው። ከዚህ ድልና ከዚህ የድል-ፈርጦች አገር፣ ትውልድና ሕዝብ ተገቢውን የታሪክ ስንቅ አግኝቷል፤ ነገር ግን አገራችን ኢትዮጰያ ድሉን እንጅ የድል ባለቤቱን በሚከዱ፣ ታሪኩን እንጅ ታሪክሰሪውን በሚጸየፉ፣ ክቡሩን እንጅ ያስከበሩንን በማያውቁ ሰዎች እጅ ስለወደቀች የድል ቀኑን እናስባለን እንጅ ድል አድራጊዎችን አናከብርም። በተለይ የአማራ ሕዝብ ከአድዋ ድል ጋርተያይዘው በተፈበረኩና ሀገሪቱን መልሶ ለመቆጣጠር በተፈጠሩ የሐሰት ትርክቶች ምክንያት በአገር ውስጥ ባሉ የፖለቲካ ኃይሎችም ሆነ በአንዳንድ የውጭ ፀሐፍት ዘንድ ያለ ስሙ ስም ተሰጥቶት ኖሯል፤ ባለፉት አምሳ ዓመታትም የደረሱበት በደሎች ሁሉ ፅንሰታቸው የሚጀምረው ከዚህ ቀንና ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚፈልጉ ኃይሎች በተፈጠሩ ክፉ ትርክቶችና በደሎች ጋርተያይዞ ነው። የወቅቱ ጠላቶች የቅኝ ግዛት ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም የፈጠሩትን ሐሰተኛ ትርክትና የሀገር ማፍረሻ መንገዶች እንደትግል ስልትና ስትራቴጅ በመጠቀም የዛሬዎቹ የሀገርውስጥ ፋሽስቶች በሕዝባችን ላይ በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በደል እያደረሱብን ይገኛሉ። የሀገሪቱ ዜጎች ስንሆን ለባርነት ተመኙን፤ የዓድዋ ባለታሪኮች ስንሆን ታሪክ እንድንሆን ፈለጉ፤ ስለዚህም በሰማይና በምድር ጦርነትን ከፈቱብን። በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነትን ከፍተው የድል በዓል ያከብራሉ፤ ዳግማዊ ምኒልክ በሰራውና በመራው ድል፣ አብይ አህመድን ያመሰግናሉ። ስለሆነም የአማራ ሕዝብ ከአባቱ ከእምዬ ምኒልክ በተማረው መሰረት ሀገር አልባ ሊያደርገው የተነሳውን የአምባገነኑን የአብይ አህመድ የብልጽግና መንግስት በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጥህም፤" ሊለው ይገባል። አምባገነኑ የብልጽግና ሥርዓት አገር አልባ፣ ባሕል አልባ፣ ሃይማኖት አልባና ታሪክ አልባ ሊያደርግህ ተነስቷልና አገሬን አሳልፌ አልሰጥህም ልትለው ይገባል። በአማራ የሕልውና ትግል ሜዳ ላይ የሚገኝ ማንኛውም የአማራ ታጋይም ከአድዋ ጀግኖች የሚማረው ብዙ ቁም ነገሮች አሉ። ያኔ ይደረግ የነበረው ጦርነት ከውጭወራሪ ለመላቀቅ ነው፤ እሱም በአባቶቻችን ድንቅ ተጋድሎ ተሸንፏል። በድጋሚ እንኳን ለመላው አለም ጥቁር ህዝቦች የድል በአል አደረሳችሁ አደረሰን!

#5_ጥቁር_ክላሽ_እና_1ስናይፕር_ይዘው_የአማራ ልጆች ፋኖን ተቀላቀሉ። የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ሰለሞን አሊ ወንድማዊ አቀባበል አድርጎላቸዋል። #የ1
#5_ጥቁር_ክላሽ_እና_1ስናይፕር_ይዘው_የአማራ ልጆች ፋኖን ተቀላቀሉ። የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ሰለሞን አሊ ወንድማዊ አቀባበል አድርጎላቸዋል። #የ11ኛ_ዕዝ_104ኛ_ኮር_መሃንድሶች_ናቸው። የኮሩ ጭንቅላት የሆኑት ናቸው ሹልክ ብለው የመጡት። ጠላትን ቻው ቼልሲ ብለውታል። የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት እየፈረሰ ለመሆኑ ከዚህ በላይ አስረጅ የለም።

የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም 130ኛውን የአድዋ ድል አስመልክቶ ከአፋብን የተሰጠ መግለጫ አድዋ የነፃነት፣ የአንድነት፣ የአይበገሬነት፣ የራስ በቅነት ውጤት ነው። አድዋ ከግዜያዊ ትርፍ ይልቅ የሀገር ክብር እና ነፃነትን፣ ከፍርፋሪ ይልቅ ኩራትን፣ ከአጎብዳጅነት ይልቅ የሞራል ልዕልናን ያስቀደሙ አባቶቻችን የፈፀሙት ድንቃ የታሪክ ክስተት ነው። አድዋ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ከተከሰቱ የዓለም ስልጣኔወች መካከል አንዷ መሆኗን ያስመሰከረ፣ በደረጀ የአመራር ጥበብ፣ የጋራ በሆነ ብሔራዊ አጀንዳ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የተሰለፉበት መድረክ ነው። ሀገር እና ህዝብ መውደድን አውርተው ሳይሆን ሰርተው፣ ተነግሮላቸው ሳይሆን ተግብረውት ያሳዩት አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ እና ሌሎች የዘመኑ ክስተቶች በፅናታቸው፣ በአመራር ጥበባቸው፣ በአስተዋይነታቸው እና በቆራጥነታቸው እብሪተኛ ወራሪወችን በማሸነፍ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ ድል፤ የቅኝ ገዥወችን የኃይል ሚዛን ያዛቡበት ታሪካዊ ክስተትም ነው አድዋ። የኢትዮጵያን ብዝሃነት ከጭፍለቃ ያዳነው የአድዋ ድል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ተሰሚነት ያላት ሀገር እንድትሆን ከማስቻሉም በላይ ለዓለም የዲፕሎማሲ ህግ የጋራ ደህንነት እና በሉዓላዊነት ጣልቃ ያለ መግባትን መርሆወች እንድታበረክት አድርጓል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአድዋ ድል 130 ኛ ዓመት አደረሳችሁ ይላል።  130ኛውን የአድዋ ድል ስናከብር ኢትዮጵያን ከነታሪኳ የሚጠላው የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመመከት እና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የደቀነውን አደጋም ለመከላከል የሚያበቃ ተጋድሎ በማድረግ ነው። ከአድዋ መንፈስ በተቃራኒ የተሰለፈው የአብይ አህመድ ቡድን የሀገሪቱን የመከላከያ ተቋም አመራር ለአረብ ኢምሬቶች በማስረከብ፣ ኢትዮጵያዊያንን በባዕዳን ወንበዴ ሀገራት ድሮን እና ጀት በማስጨፍጨፍ ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ተግባር በመፈፀም ላይ ይገኛል። ባንዳነትን እና ባዳነትን ከአረመኔነት ጋር የተላበሰውን የብልፅግና አገዛዝ በማስወገድ ሀገራችንን ካልተነገረው የአረብ ኢምሬትስ ቅኝ ግዛት ለማላቀቅ በቁርጠኝነት የምንታገል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ

#ከእዚህ ሰራዊት ፊት የሚቆም የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ አንድም ሰራዊት ሊኖር አይችልም በዘመቻ አባ ናደው አገዛዙ ለሶስት አመት የመሸገበትም ኮንክሬት ምሽግ በመስበር 11 ተሽከርካሪ ኦራል እና ፓትሮል
+1
#ከእዚህ ሰራዊት ፊት የሚቆም የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ አንድም ሰራዊት ሊኖር አይችልም በዘመቻ አባ ናደው አገዛዙ ለሶስት አመት የመሸገበትም ኮንክሬት ምሽግ በመስበር 11 ተሽከርካሪ ኦራል እና ፓትሮል የማረኩ የወንዶቹ ስብስብ የዕዙ ልዩ ዘመቻ ሰራዊት አባላት ክብር ይገባቹሀል 💪 #ዛሬም የደገሙት እነዚሁ ለአማራ ህዝብ ዘብ የቆሙ ልባሞች ናቸው👥 #ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን 👥

እኛስ ለራሳችን አድዋ ግዳጅ ላይ ነን። የትናት አድዋ ! የዛሬ የጥቁር አፍሪካ ህዝብ የነፃነት መሰረት በመስዋትነት የተገኘ ድል ነው። በትናት አድዋ እልፍ አላፍ ጀግና አባቶቻችን እና እናቶቻችን ባርነትን ተጸይፈው ደም አዝርተዋል፣ አጥንት ከስክሰዋል ውድ ህይወታቸውን ገብረዋል። የትናት አድዋ የኛ የማይፋቅ ታሪክ ነው! የትናት አድዋ ለእኛ ዘላለማዊ የማይካድ አለም አቀፍ ድልን ነው። በትናት አድዋ ዛሬ በኩራት ቁመናል። በትናት አድዋ የእምየ ሚኒሊክ፣ የእቴጌ ፀሀይቱ ልጆች አለም አክብሮ ይዞናል። የትናት የአድዋ አባቶች ለነፃነት ለህዝብ ክብርና ለሀገር ህልውና የግል ህልማቸውን ሰውተው በሞታቸው ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ እኛም ለራሳችን አድዋ ግዳጅ ላይነን። ይህ ትውልድ ! የእኛ ትውልድ ! ድጋሚ ያንን የአድዋ ድል ለመድገም የሚችልበት እድል ተፈጥሮለታልና በእልህ እየተፋለመ ይገኛል ትግሉንም በመጨረሻ ያሸንፋል ። እኛ ለእኛ አድዋ ግዳጅ ላይ ነን! ግዳጁ ወደኋላ እንድናማትር የሚያስችለን አይደለም፣ በግል ፍላጎታችን በማይገደበው ህልማችን የሚያባዝተን አይደለም ። ይህ ግዳጅ የትናት የአድዋን ድል ባለቤት ህዝብ ሊያጠፋ የመጣን ጠላት መመከት ነውና ኃላፊነቱ ከምንግዜውም በላይ የከበደ ነው። አወ ግዳጅ ላይ ነን። ለማይቀረው የድል ጉዞ እየተፋለምን ነው። እርሀቡ ፣ጥሙ ፣ድካሙ፣ መቁሰል መሰዋቱ የማይገድበው የማይቋረጥ ግዳጅ ላይ ነን። የኛ አድዋ በራሳችን በቅተን የምንወጣው የአማራ ህዝብ የህልውና አደራ እንደመሆኑ መጠን ኩልል ያለ ንፁህ ደም አፍስሰን በታሪክ መዝገብ ውስጥ እጅግ የደመቀ ታሪክ እንጽፋለን እየጻፍንም ነው ። አድዋን ስናስብ ለራሳችን አድዋ ግዳጅ ላይ ሁነን በመሆኑ እጅግ ከራት ይሰማናል ። የአድዋ ድል ፍሬዎች ለራሳችሁ አድዋ ለምትፋለሙት ጓዶች እንኳን ለአድዋ ድል መታሰቢያ አደረሳችሁ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ Esubalew Bamlak

ቴዴ አፍሮ ንጉሱ
ቴዴ አፍሮ ንጉሱ

የጎንጂ ቆለላ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ሀላፊ የነበረው ባንዳ አለኸኝ እርገጤ አፋብኃን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር አናብስቶች ተሸኝቷል።
+1
የጎንጂ ቆለላ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ሀላፊ የነበረው ባንዳ አለኸኝ እርገጤ አፋብኃን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር አናብስቶች ተሸኝቷል።

የዋርካው ምሬ ወዳጆ አስገራሚ ፮''ት ባህሪያቶች ....... ሁሉም የፋኖ ከፍተኛ አመራር የሆነ ታላቅ ህዝብ መሪ ነኝ የሚል አካል ሁሉ የዋርካው ምሬ ወዳጆ ረቂቅ የሆኑ ባህሪያቶችን ቢላበስ እውነትም የህዝብ ልጅ ይሆናል። ከ፮ 'ቱ የዋርካው ምሬ ባህሪያቶቹ ውስጥ ፩፦ ምሬ ወዳጆ በፍፁም የገንዘብ/ንዋይ ፍቅር የለበትም። ማረጋገጫ ፦ ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ - እስካሁኑ የህልውና ጦርነት በአርበኝነት የመሪነት ዘመኑ በተለያዩ መንገዶች ገንዘብ ሲገኝ ከአጠገቤ አርቁ ፤ ገንዘብ በአጠገቤ አታድርጉ። ፈጣሪ ይመስገን ገንዘብ አጥቼ 'ም አልወጣውም ፤ መንግስት 50ሺ በወር ልክፈልህ ቢለኝ አልፈልገውም ብሎ በአደባባይ ተናግሯል። ፪፦ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለጋስ ፣ ቸርና ሩህሩህ ነው። ማረጋገጫ ፦ በሰሜኑ ጦርነት ጊዜ አንድ ጋዜጠኛ መንግስት ምን ቢያድረግልህ ትፈልጋለህ ብሎ ሲጠይቀው ፤ ዋርካው እኔ ምንም የምፈልገው አንዳች ነገር የለም ለሰራዊቴ ለልጆቼ የሚቀምሱት ሬሽን ፣ ልብስና ተተኳሽ ብቻ ነው የምፈልገው ብሎ ተናግሯል። ፫ ፦ ዋርካው ምሬ ወዳጆ እጅግ ሲበዛ ቅን ሀይማኖተኛ ነው። ማረጋገጫ ፦ በፈጠረው ፈጣሪ እጅጉን ይተማመናል። የገና ፣ ሁዳዴ ና ፍልሰታ ፆም ሲሆን ሁልጊዜ ከአምላኩ ጋ በፆም ፀሎት ይገናኛል። ሌላው ዋርካው ቤተአማራ ምድር እንደመፈጠሩ መጠን በሀይማኖት እኩልነትና ተቻቻሎ መኖር እጅጉን ያምናል። ያደገበት የኖረበት ነው። የሁላችንም አባት የነበሩት ክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ማረፋቸውን ሲሰማ እጅጉን ስቅስቅ ብሎ ነበረ ያለቀሰው። ሌሎችም እነ ኮ/ል ሞገስ ዘገዬ እጅጉን ያዘኑበት ዕለት ነበረ። ፎቷቸውን አሳትመው ከሰራዊቱ ጋ የሻማ ማብራት ፕሮግራም አርገዋል በወቅቱ። ፬፦ ዋርካው ምሬ ወዳጆ በፍፁም ራስ ወዳድ አይደለም። ማረጋገጫ፦ ከሰሜኑ ጦርነት እስካሁኗ ሰአት ድረስ ምሬ በፍፁም በጦርነት ጊዜ እንደ መሪ ከኋላ ሆኖ አዋግቶ አያውቅም። ጦርነቱን በተኩስና ጠላትን በመግ**..ደል ይባር...ካል እንጂ። እንዲያውም ሰራዊቶቹ አንተ ወደ ኋላ ሁን በኋላ አንተ ብትሞት ማን ይመራናል ሲሉት ዘወር በልልኝ ፣ እነ መሀመድ ቢሆነኝ ፣ እነ ሞላ ደስዬ ፣ እነ ይታገሱ አራጋው ፣ እነ ዳኒኤል አለሙ... ሞትን አስተምረውኛል ከፊት እሞትልሃለው ብሎ ሰራዊቱን በአደባባይ ተናግሯል። ፭፦ ዋርካው ምሬ ወዳጆ አድርባይነትንና ተላላኪነትን እጅጉን ይፀዬፋል። ማረጋገጫ፦ የሰሜኑ ጦርነት እንደተገባደደ በአንድ ወቅት የብልፅግና አመራሮች ተሰብስበው መጥተው በቤተአማራ ምድር የበላይ አርገን እንሹምህ የፈለከውን ስልጣን እንስጥህ ሲሉት ፣ ዘወር በሉ ከዚህ ጥፉ ብሎ ከማንም በፊት ራያ ዞብል ምድር ላይ የመጀመሪያውን አብሪ ጥይት ወደ መንግስት የተኮሰ ድንቅ : ጥበበኛ መሪ ነው። ፮፦ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ፈሪ በጣም ይጠላል። ማረጋገጫ ፦ በአንድ ወቅት መድረክ ላይ ቁሞ ለሰራዊቱ ንግግር ሲያረግ "ይሄውልህ ስትመታ ከግንባርህ ተመተህ ካልወደክ ጀርባህን ተመተህ ቆስለህ ከመጣህ እመነኝ አትጠራጠር እኔ ነኝ የምጨር***..ስህ "! ማለቱን ልብ ይሏል። ፈሪ በፍፁም አይወድም። ለዛም ሰራዊቱ ቆስሎ ሲማረክ እና እጅ ሲሰጥ እብዛም የማይታዬው። በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋርካው የሚለውን ስም እንዲወጣለት ሲደርግ ስሙን ስፔሻል ኮማንዶ ዘላለም በነበረበት ሀይቅ ልዩ ቦታው "ሱሉላ " የምትባል ቦታ ላይ ነበረ በምስራቅ አማራ ፋኖ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ተመራቂ ፋኖወች እና አሰልጣኞች ናቸው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ብለው ስሙን ያወጡለት። እውነትም ዋርካው ለአማራ እውነተኛ ዋርካ ጥላ መከታ ሁኗል። ታላቁ ገናናው የዐምሓራ ህዝብ ሆይ ለዚህ ጥበበኛና ድንቅ መሪ 365 ቀን ሙሉ በምታምነው ኃይማኖት ፀሎትና ዱዓ አርግ። አደራ መሪህን ጠብቅ። ለታላቁ የድል ትንሳኤ ያብቃህ ውዱ መሪዬ✊✊✊