ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 632
المشتركون
+124 ساعات
+3977 أيام
+1 06030 أيام
أرشيف المشاركات
የአማራ ህዝብ የህልውና ታጋድሎ ተተርኮ የማያልቅ ገድል እና ጀግንነት የተፈፀመበት ነው። በእያንዳንዱ ድል ጀርባ አስደናቂ ተጋድሎ አድርገው የወደቁ ጀግኖች አሉ። ከእነኝህ መካከል የፋግታ ለኮማዋ ፋኒ
የአማራ ህዝብ የህልውና ታጋድሎ ተተርኮ የማያልቅ ገድል እና ጀግንነት የተፈፀመበት ነው። በእያንዳንዱ ድል ጀርባ አስደናቂ ተጋድሎ አድርገው የወደቁ ጀግኖች አሉ። ከእነኝህ መካከል የፋግታ ለኮማዋ ፋኒት ዘመናይ ደጉ አንዷ ነች። የካቲት 07 ቀን 2018 ዓ/ም አዲስ ቅዳም አቅራቢያ ሰምቡ ግሸን ተራራ ላይ ከጓዶቿ ጋር በጠላት የተከበበችው ፋኒት ዘመናይ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በማድረግ ጥይቷ ሲያልቅ የመጨረሻዋን ጥይት ወደራሷ ተኩሳ እራሷን በክብር ሰውታለች። ራሷን በጀግንነት የሠዋችው ድንቅ አማራዊት ፋኒት ዘመናይ ደጉ የ105ኛ ክፍለ ጦር 44ኛ ክፍለ ጦር አርበኛዋ ወደ ራሷ ከመተኮሷ በፊት '"ሚጣ ተይ እራስሽን አታጥፊ ብትማረኪ ይሻላል..." የሚሉ ድምፆች ወደ ጆሮዋ ቢመጡም በጠላት ከመማረክ ይልቅ በራሷ እጅ ሰማዕት የመሆንን ክብር አስቀድማለች። ትውልዱ የፋኒት ዘመናይ እና መሰሎች እዳ አለበት። ብዙወች በተራ ነገር ትግሉን በሚሸጡበት ሁኔታ ውስጥ ዓላማቸውን ከህይወታቸው ያስቀደሙ ጀግኖች በሚከፍሉት መስዋዕትነት የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ግቡን ይመታል።

አገዛዙ የራሱን ሚሊሻና ከድማ በትን ላይ የድሮን ጥቃት አደረሰ ================ አገዛዙ ደልጊ ላይ ተደጋጋሚ በፈፀመው የድሮን ጥቃት ከፋኖ ጥይት የተረፈውን የራሱን አድማ ብተናና ሚሊሻ ወደ
አገዛዙ የራሱን ሚሊሻና ከድማ በትን ላይ የድሮን ጥቃት አደረሰ ================ አገዛዙ ደልጊ ላይ ተደጋጋሚ በፈፀመው የድሮን ጥቃት ከፋኖ ጥይት የተረፈውን  የራሱን አድማ ብተናና ሚሊሻ ወደ አመድነት ቀይሮታል። ጎንደር በለሳ ላይ ብልጽግናን አምነው በተሰበሰቡ ሚሊሻዎች ላይ በተቀነባበረ ሴራ በአደረሰው የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሚሊሾች መሞታቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። በአማራ ሚሊሾችና አድማ ብተና ላይ ተደጋጋሚ በሚደረግባቸው ክህደት ብዙ ሚሊሾች መሞታቸው ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ብልጽግና የሌቦች የሴረኞች የሀገር ሻጮች ስብስብ ነው። ስለዚህ ሚሊሻ፣ፖሊስ፣አድማበትን እና መከላከያ የወረደላችሁን የምህረት ሲሳይ በቶሎ መጠቀም ብልጠት ነው። ⛔️የብልጽግና ክፋቱ ክህደቱ፤ የካቲት 19/2018 ዓ.ም

​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በታሪካዊት ማጀቴ ህዝባዊ ወይይት አካሔደ!! ​በታሪካዊቷና የጥንታዊቷ ስልጣኔ መገኛ በሆነችው ማጀቴ ከተማ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና  አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ከከተማዋና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረገው በዚህ ውይይት የፋኖ ወቅታዊ ቁመናና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። 1, ድርጅቱ የተመሰረተው በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስና ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባትም ነው ሆኖም የአማራ ህዝብ የታሪክ አደራን ለመሸከም ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች የድርጅቱን ስርወ-መሠረትና ጽኑ ዓላማ ለሕዝቡ አስረድተዋል። ​2, ​በወታደራዊ ረገድ ፋኖ አሁን ካለበት   መከላከል ወደ ማጥቃትና ቁልፍ ይዞታዎችን ወደ መቆጣጠር" መሸጋገር ላይ ይገኛል። 3, የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በማጀቴና በዙሪያዋ ባሉ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎች ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር ያሳየበትና ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ  የሕዝብ ጋሻ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል። ፋኖ አሁን ላይ ዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስን የታጠቀና የተቀናጀ ዕዝ ያለው ኃይል መሆኑ በዝርዝር ቀርቧል። ​4, ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን ግልጽ ፖለቲካዊ ራዕይ እንዳለው ለነዋሪው ተብራርቷል፦ ​ፖለቲካዊ ሁሉንም ያካተተ፣ የአማራን ሕዝብ ጥቅምና ክብር የሚያስከብር የፖለቲካ ስርዓት በመገንባት ላይ ያለውን ቁመናም ተገልጿል። በመጨረሻም ​በአሁኑ ሰዓት ፋኖ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን ያጠናከረ፣ በዲሲፕሊን የታነፀና ከሕዝብ ጋር በደም የተሳሰረ በመሆኑ። ፋኖ የሕዝብ ልጅ ነው በማለት ዛሬ በማጀቴ የተደረገው ውይይት በሕዝብና በታጋዩ መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ አጠናክረዋ። ሆኖም ይህ ውይይት ለቀጣዩ ድል ትልቅ ስንቅ ነው በሚል በአካል ከማህበረሰቡ አስተያየት ተሰጥቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 19 /06/2018 ዓ.ም

በዚህ ትግል ሁሉም ታጋይ የራሱን የማይረሳ ጀብድ ሰርቷል ከጀብዶች ጀብድ ግን ያች ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የባሕር ዳር ሰባታሚቱ እስር ቤት አትረሳኝም። በነ ማንችሎት የሚመራ ከቋሪት፣ ከአዴት፣
በዚህ ትግል ሁሉም ታጋይ የራሱን የማይረሳ ጀብድ ሰርቷል ከጀብዶች ጀብድ ግን ያች ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የባሕር ዳር ሰባታሚቱ እስር ቤት አትረሳኝም። በነ ማንችሎት የሚመራ ከቋሪት፣ ከአዴት፣ ከጭስ አባይ፣ ከባሕርዳር ከተማና ዙሪያ ኃይል እየመጣ ነው። ከሰዓታት በኋላ ይሰበራል ዛሬ ትወጣላችሁ ተባልን። በወቅቱ አሁን የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራር የሆነው አርበኛ አበበ መልኬ "ኧረ ወዲያ ከጎንደር የመጣ ኃይል ካልሆነ እኔ የነ ማንችሎትን ኃይል አላምንም ወሬ ብቻ ነው" አለ። ይችን አሁንም አቤ አይክድም😁 የሆነው ሁኖ እነ ማንቼ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁን ፣ ድንጋይ እንዳትወረውሩ ፣ እንዳትንጫጬ፣ እኛ ወደ ግቢው ሳንገባ ለመውጣት እንዳትሞክሩ ብለው በቀጠሯቸው ሰዓት መጠው በአናት በአናቱ ላይ ያዘንቡት ጀመር። ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አማራ በግፍ ከታጎረበት ከትልቁ የክልሉ ሰባታሚት ማረሚያ ቤት የአማራን ወጣት የእስር ቁልፍ ሰብረው የነፃነትን ቁልፍ አስረከቡን።

የአገዛዙ ሀይል ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት ============== በትናንትናው ዕለት በቀን18/06/2018 አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛክ/ጦር ከደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ወደ
የአገዛዙ ሀይል ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት ============== በትናንትናው ዕለት በቀን18/06/2018 አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛክ/ጦር  ከደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ወደ አረፋ ደብተራ ለመንቀሳቀስ ሙከራ ያደረገውን  የአብይ አህመድ አረመኔውን ሰራዊት እሳት በሚተፉት ሻለቃ-4  የፋኖ አባላት  ሰላም አምባ በተባለ ቦታ  መብረቃዊ ጥቃት በመሰንዘር ወደ መጣበት እንዲፈረጥጥ ማድረግ ተችሏል። ከቀኑ 10:00-12:00 በቆየው አውደውጊያ በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። #መረመረጃው  የ99ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት የካቲት 19/2018 ዓ.ም

የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 8:10 በፈፀመው የቦምብ ጥቃት ም/ኢኒስፔክተር ወረታውን ጨምሮ 3 ፖሊሶች ሲገደሉ 2 (ሁለት) ፖሊሶች ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። የካቲት 19/2018 ዓ.ም ==================================== የ206ኛ ኮር አነፍናፊ አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከቀናት በኋላ በድጋሚ ከሌሊቱ 8:10 በዩኒቨርስቲው መስመር ከቀበሌ 02 ወደ ቀበሌ 01 በሚወስደው አውራ ጎዳና ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ፖሊሶች ላይ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት ም/ኢንስፔክተር ወረታውን ጨምሮ 3 (ሶስት) ፖሊሶች ሲገደሉ 2(ሁለት) ፖሊሶች ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። አዳኝ ቡድኑ በተከታታይ በሚያደርጋቸው ጥቃቶች ተጋላጭነትን ለመቀነስ በእግረኛ ከተማዋን በሚቃኙ ፖሊሶች ላይ የተደረገው የቦምብ ጥቃት ስኬታማ የሆነ ሲሆን የመንቆረር ክ/ከተማ ፖሊሶች ከተገደሉት መካከል እንደሚገኙበት ተረጋግጧል። በሌሊት የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መቋቋም ያቃተው የአረመኔው ሰራዊት አስክሬኖችን እየሰውረ በወታደራዊ ካምፖች መቅበር መፍትሔ ያደረገው ጠላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኞችን እንዲሁ ወደ ሆስፒታል መውሰድ አቁሟል። ከቀናት በፊት አስክሬን በመሰወሩ ምክንያት የሟች ቤተሰቦች በፈጠሩት ጫና በየ ከተሞች መርዶ እያደረሰ ሲሆን በደጀን ወረዳ ብቻ አምስት አድማ ብተናና ፖሊሶች ቤተሰቦቻቸው መርዶ እንደተረዱ ታውቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት 👇

ሰበር መረጃ የአገዛዙ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ነው!!! አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አፄ ፋሲል ክፍለ ጦር የአገዛዙን ወ
+1
ሰበር መረጃ የአገዛዙ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ነው!!! አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)  ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አፄ ፋሲል ክፍለ ጦር  የአገዛዙን ወታደሮች በመቀበል ላይ ነው። የክፍለ ጦሩ አዛዥ  አርበኛ ዝናው አያናው ጋር በተደረገ ንግግር  አንድ የሻንበል መሪውን ጨምሮ 11 የአገዛዙ አድማ ብተና አባላት ከ 1 ብሬን እና 11 የነፍስ ወከፍ ክላሽ ኮፕ ትጥቆች ጋር  ክፍለ ጦራችንን በሰላም ተቀላቅለዋል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!! የካቲት 19/ 2018 ዓ.ም 👇 Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር መረጃ የአገዛዙ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ነው!!! አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አፄ ፋሲል ክፍለ ጦር የአገዛዙን ወ
ሰበር መረጃ የአገዛዙ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ነው!!! አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)  ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር አፄ ፋሲል ክፍለ ጦር  የአገዛዙን ወታደሮች በመቀበል ላይ ነው። የክፍለ ጦሩ አዛዥ  አርበኛ ዝናው አያናው ጋር በተደረገ ንግግር  አንድ የሻንበል መሪውን ጨምሮ 11 የአገዛዙ አድማ ብተና አባላት ከ 1 ብሬን እና 11 የነፍስ ወከፍ ክላሽ ኮፕ ትጥቆች ጋር  ክፍለ ጦራችንን በሰላም ተቀላቅለዋል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!! የካቲት 19/ 2018 ዓ.ም 👇

ማርቲን ፕላውት ባስተላለፈው መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የመንግሥት መከላከያ ሠራዊት (ENDF) በተከታታይ ሽንፈቶች ከገጠሙት በኋላ በአማራ ክልል መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ገልጿል
ማርቲን ፕላውት ባስተላለፈው መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የመንግሥት መከላከያ ሠራዊት (ENDF) በተከታታይ ሽንፈቶች ከገጠሙት በኋላ በአማራ ክልል መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ገልጿል።

​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በታሪካዊት ማጀቴ ህዝባዊ ወይይት አካሔደ!! ​በታሪካዊቷና የጥንታዊቷ ስልጣኔ መገኛ በሆነችው ማጀቴ ከተማ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና  አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ከከተማዋና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረገው በዚህ ውይይት የፋኖ ወቅታዊ ቁመናና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። 1, ድርጅቱ የተመሰረተው በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስና ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባትም ነው ሆኖም የአማራ ህዝብ የታሪክ አደራን ለመሸከም ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች የድርጅቱን ስርወ-መሠረትና ጽኑ ዓላማ ለሕዝቡ አስረድተዋል። ​2, ​በወታደራዊ ረገድ ፋኖ አሁን ካለበት   መከላከል ወደ ማጥቃትና ቁልፍ ይዞታዎችን ወደ መቆጣጠር" መሸጋገር ላይ ይገኛል። 3, የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በማጀቴና በዙሪያዋ ባሉ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎች ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር ያሳየበትና ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ  የሕዝብ ጋሻ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል። ፋኖ አሁን ላይ ዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስን የታጠቀና የተቀናጀ ዕዝ ያለው ኃይል መሆኑ በዝርዝር ቀርቧል። ​4, ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን ግልጽ ፖለቲካዊ ራዕይ እንዳለው ለነዋሪው ተብራርቷል፦ ​ፖለቲካዊ ሁሉንም ያካተተ፣ የአማራን ሕዝብ ጥቅምና ክብር የሚያስከብር የፖለቲካ ስርዓት በመገንባት ላይ ያለውን ቁመናም ተገልጿል። በመጨረሻም ​በአሁኑ ሰዓት ፋኖ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን ያጠናከረ፣ በዲሲፕሊን የታነፀና ከሕዝብ ጋር በደም የተሳሰረ በመሆኑ። ፋኖ የሕዝብ ልጅ ነው በማለት ዛሬ በማጀቴ የተደረገው ውይይት በሕዝብና በታጋዩ መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ አጠናክረዋ። ሆኖም ይህ ውይይት ለቀጣዩ ድል ትልቅ ስንቅ ነው በሚል ከአካል ከማህበረሰቡ አስተያየት ተሰጥቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 19 /06/2018 ዓ.ም

በምድር የተሸነፈው ጨቅላው እና ጅምላ አውዳሚው አብይ አህመድ ፍኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠና ከUAE በተዋሰው ድሮን የአማራን ሀብት እና ንብረት በዚህ መልኩ እያወደመ ይገኛል።
በምድር የተሸነፈው ጨቅላው እና ጅምላ አውዳሚው አብይ አህመድ ፍኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠና ከUAE በተዋሰው ድሮን የአማራን ሀብት እና ንብረት በዚህ መልኩ እያወደመ ይገኛል።

#የአገዛዙ_ሰራዊት_እየተናደ_ነው‼️ የአገዛዙ 6 የአድማ ብተና አባላት የምህረት አዋጁን በመጠቀም ከእነሙሉ ትጥቃቸው አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ እዝ እስቴ ደንሳ ብርጌድን በዛሬው ዕለት ተቀላቅለዋል‼️ 19/ዐ6/2018 ዓ.ም

ዕድሜ ልካቸውን ነብስ ለማዳን የሚሰሩት ወንድም እህቶቻችን ነብሰ በላው አገዛዝ በአማራነታቸው በግፍ የገደላቸው ዶክተሮች‼️ ------ ኢትዮጵያ ወስጥ አንድ ዶክተር አስተምሮ ለማስመርቅ 27 ዓመት በላይ ይፈጃል። በአጠቃላይ ያሉት ዶክተሮች ለ130 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር  ሲነፃፀር እጅግ በጣም አነስተኛ ይህም በሒሳብ ስሌት ቢቀመጥ አንድ ስፔሻሊስት ዶክተር በአማካይ ለአንደ ሚሊየን ሕዝብ እያገለገለ ነው ያለው  ማለት ነው ። ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት በከፍተኛ ደረጃ የህክምና ባለሞያዎችን አስቀድሞ የመግደል የዘር ማጥፋት ስልት እየተከተለ ይገኛል። እረኛውን ምታው መንጋው ይበተናል የሚል የዘር ጨፍጫፊዎች የዘር ማጥፍት መፈክር እንደ ስልት የሚከተለው አብይ አህመድ አሊ ባለፋት ሰባት ዓመታት ብቻ እጅግ በጣም ብዙ የጤና ባለሞያዎች ተገድለዋል። ዕድሜ ልካቸውን ነብስ ለማዳን የሚሰሩት ወንድም እህቶቻችን ነብሰ በላው አገዛዝ በግፍ የገደላቸው የአማራ ዶክተሮች:- 1 - ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ :- እውቁ የሰርጀሪ ህክምና ባለሙያ ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ እሁድ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ የጠዋት ሩጫ በማድረግ ላይ ሳሉ ግድያ እንደተፈፀመባቸው ታውቋል። 2- ዶ/ር ኤልሳቤት ተሾመ :- በሚያዝያ 14 ቀን 2016፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ (ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ)፣ የአብይ አገዛዝ ሀይሎች (ሚሊሻዎች) ዶ/ር ኤልሳቤት ተሾመ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያ ቤቷ እየተመለሰች ባለችበት በጥይት መተው መግደላቸውን አረጋግጧል። 3- ዶ/ር ገብረ ሚካኤል ወልደ አማኑኤል :- ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ  ከአለም ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ልዩ ስሙ ማጋስ ቀበሌ መሳለሚያ በተባለ  ቦታ መከላከያ በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ ጥዋት 2:30 በከፈተው ጥቃት የአለም ከተማ እናት ሆስፒታል ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ የሆነው ዶ/ር ገ/ሚካኤል ወ/አማኑኤል፣ የ1 ዓመት ጨቅላ ሕፃን እና ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። 4- ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ በጥር 24 ቀን 2017፣ የኦሮሞ ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ የተባሉ ሰላማዊ ሰው መግደላቸውን ማወቅ ችሏል። 5- ዶ/ር ሜሪ አበበ በጎንደር ዩንቨርስቲ ጀማሪ ዶክተር። 6- ዶክተር ጥበቡ አለነ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የ2ኛ ዓመት የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ፕ/ት ሐኪም የነበረው ዶ/ር ጥበቡ አለነ ከሆስፒታሉ በር ፊትለፊት በአገዛዙ ተግድሎ ተጥሎ ተገኝቶል። 7- ዶክተር እስራኤል ጥላሁን በአገዛዙ ተረኛ በመሀል አዲስ አበባ ቦሌ በጥይት ግንባሩ ተመቶ የተገደለ። 8- ዶክተር ሜሮን ደምሌ:- አዲስ የተመረቀች የህክምና ዶክተር በጎንደር ዩንቨርስቲ በጠቅላላ የህክምና ዶክተርነት ስታገለግል የነበረች። 9- ዶክተር ፀጋሁን ስሜን ጥር 26/2018 ዓ.ም የአገዛዙ ቅጥረኛ ወታደሮች ከሚሰራበት ስፍራ እየደበደቡ ወሰዱት። በዕለቱ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ ቤተሰቦቹ ወደ ስፍራው በመሄድ አስክሬኑን እንዲውስዱ በገዳይ ኃይላት መጠየቃቸው ታውቋል። 10- ዶክተር አበኔዘር ጌታቸው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ አመት የቀዶ ህክምና ተማሪ 11- ዶ/ር ሄኖክ ተስፋዬ ህዳር 21 /2016 ዓ.ም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በምትገኘዉ ወገልጤና በተባለ ቦታ በአምቡላንስ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ተገደለ። 12- ዶ/ር በውቀቱ አንዳርጌ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 6ኛ ዓመት የሕክምና ዶክትሬት ነፍስ በሰላም ትረፍ!!

ከአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የፋኖ ሠራዊትን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መሰልጠን የምትፈልጉ ወጣቶች ከታች ባለው መስ
ከአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የፋኖ ሠራዊትን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መሰልጠን የምትፈልጉ ወጣቶች ከታች ባለው መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ወጣት መመዝገብ ይችላል። 1.​ብሔር አማራ የሆነ/የሆነች ​እድሜው ከ18 እስከ 45 ዓመት ድረስ የሆነ/የሆነች 2. ​ጾታ አይለይም ሴቶችን እናበረታታለን 3.​ጤናው ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች 4. ​ህዝቡን እና ድርጅቱን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል የሚፈልግ/የምትፈልግ 5.​የመመዝገቢያ ጊዜ ከቀን 18/06/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ። ​የምዝገባው ቦታ አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር በተቆጣጠራቸው ቀበሌ እና በማጀቴ ቀበሌ እንዲሁም ሠራዊት ባለበት ቦታ መጥተው መመዝገብ ይችላሉ። ​አጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር እና ድርጅቱ መረጃ ከፈለጉ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን 0906039200 0905918609 ​ማሳሰቢያ፦ የቀድሞ የሠራዊት አባል የነበራችሁ በሙሉ በተለያዩ ምክንያቶች ከትግሉ እራሳችሁን አግልላችሁ የቆያችሁ አባላት መለሳችሁ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የምትፈልጉ ከሆነ የመመዝገቢያ ቦታ መጥታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። ​ክብር ለተሰዉት ድል ለአማራ ፋኖ