ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 485
المشتركون
+1124 ساعات
+887 أيام
+88530 أيام
أرشيف المشاركات
‎የሀዘን መግልጫ ‎ ‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በአርበኛ ፋኖ ማሙሽ በላይ ዜና እረፍት የተሰማውን ከባድ ሀዘን መግለፅ ይወዳል። ‎ ‎አርበኛ ማሙሽ በላይ ከአባታቸው ከአቶ በላይ ፈለቀ እና  ከእናታቸው ከወ/ሮ ይርገዱ ሽመልስ በ1968 ዓ/ም በመርሀ ቤቴ አውራጃ ደራ ወረዳ ጉንደ መስቀል ከተማ ተወልደው እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ት/ቤት በመግባት እስከ 10ኛ ክፍል ከተማሩ በኋላ ትምህርታቸውን በማቋረጥ የግል ስራቸውን ሲሰሩ ቆይተዋል። ‎ ‎ከዚያም በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ጦርነት ከአሸባሪው አብይ አህመድ የውንብድና ስርዓት ጎን በመቆም ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ሲዋጉ ከቆዩ በኋላ የሰሜኑ ጦርነት ማክተሙን ተከትሎ በአማራ ህዝብ ላይ ስር የሰደደ ጥላቻ የነበረው የአብይ አህመድ የብልጽግና ስርዓት ወደ ዘብጥያ በማውረድ ከባድ ግፍና መከራ አደረሰበት:: ‎ ‎ከረጅም ስቃይና መከራ በኋላ ከእስር ቤት የተለቀቀው አርበኛ ፋኖ ማሙሽ የስርዓቱን ስር የሰደደ ውንብድና ጠንቅቆ በመረዳቱ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የፍቃዱ በላይ ክፍለጦርን በመቀላቀል ወደ ትግሉ ተቀላቀለ። ‎ ‎ክ/ጦሩን ከተቀላቀለ በኋላ አርበኛው በተለያዩ የስራ መደቦች በፅናት ክ/ጦሩን እያገለገለ የህዝብ ችግሮችን እየፈታ እያለ ባጋጠመው ህመም ምክንያት ተገቢው ህክምና ሲደረግለት ቆይቶ መስከረም 10/01/2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም መሰናበቱ ተከትሎ የተሰማንን ሀዘን በመግለጽ ለመላ ቤተሰቦቹ የትግል አጋሮቹና ወዳጆቹ መጽናናትን እንመኛለን!!! ‎ መረጃውን ያደረሰን ‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር ራፖርተር ነው   " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ‎ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ‎  መስከረም 11/2018 ዓ. ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

እንኳን ደስ አላችሁ ለውድ አማራዊያን በሙሉ ፡፡ ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም “የመዳኛ መሳሪያችንን አንድነትን እና ህብረትን እንታጠቅ! አይናችንንም እንደንስር ጥላት ላይ እንትከል በሚል መሪ ቃል የዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ህብረት ተመስርቷል፡፡ “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የሚባለው የሕብረትንና አንድነትን ፋይዳ ጠቋሚ ነው። የአማራ ማህበራት ህብረት ከመመስረቱ በፊት ባደረጋቸው የዳሰሳ ጥናት መሰረት ሁሉን አቀፍ የአማራ ሞትን፣ መሰደድን፣ መዋረድን እና መናቅን የሚያመጡ የተናጠል መንገዶችን ዘግቶ ኃይልን በጋራ በመጎናፀፍ አማራውን ከችግር በላይ ማድረግ የአማራው ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳዩ ነው፡፡ የአማራ ፋኖ አማራን ለማዳን አንድኛ ሕይወቱን እየገበረ የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ቢሆንም የአማራ ህዝብ፣ መላው ኢትዮጵያውያን ብሎም የአለም ህዝብ የሚጠብቀው የድል ጊዜ እየተራዘመ ይገኛል፡፡ ይህ የድል ጊዜ መራዘም ለህዝባቸው መሰዋዕት የሚሆኑ ጀግኖችን እየጨመረ ሲሆን አንዳንዶችም ተስፋ እየቆረጡ ከአማራ ስነልቦና እና ከፋኖነት ባህሪ ውጪ ለጥላት እጅ በመስጠት በቁማቸው ራሳቸውን ገድለው አማራነትን የማዋረድ ተግባር ላይ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል፡፡ ጥላት የማይቀረው ድል እንደሚመጣ ስለሚያውቅ አማራን ማጠፋት የሚለውን አላማ ለማሳካት የአማራን ትውልድ ከትምህርት ማዕድ እንዲርቅ፣ አዛውንትና ታማሚዎች ህክምና እንዳያገኙ እያደረገ፣ ልጃገረዶቻችንን እየደፈረ የስነልቦና ገደላ እያደረገ፣ ባለሀብቶቻችንን እያደኸዬ፣ ባህላችንን እያጠፋ፣ እምነታችንን እያመነመነ ችግርንና ሞትን እንድንለማመደው እያደረገን ይገኛል፡፡ የድላችን መራዘም ዋና ምክንያተ አንድነት እና ህብረት ማጣት፣ አለመናበብ፣ የከንቱ ጩኸት መበርከት፣ ድርጅታዊ አሰራር አለመከተል፣ በአንድ ማዕቀፍ ሆኖ እና ለሥርአት ተገዢ ሆኖ አለመስራት እንደሆነ ግምገማው ያሳያል፡፡ አለም አቀፍ ህብረቱ ይህን ችግር ለመፍታት እንዲቻል በአለም ዙሪያ ያሉ 20 ማህበራትን በአንድነት በማሰባሰብ አማራ አንድ አይሆንም የሚለውን የጥላትን ምኞት ክንቱ ሊያደርግ የአማራውን ስጋት ሊቀርፍ በአንድነት ትልቅ ማህበር መስርቷል። ህብረቱ ማንኛውም የአማራን ደህንነት የሚፈልግ አካል ሁሉ በአንድነት እና በህብረት ተሰባስቦ መስራት በፅኑ የሚያምን በመሆኑ ከማንኛውም በአማራ ሥም የተሰባሰቡ ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ ነው፡፡ እንሰባሰብ!! እንደራጅ !! በመሆኑም የአማራን ጉዳይ የያዛችሁ ወገኖች በሙሉ ከዚህ ቀድም የተፈጠረ መነቃቀፍ ካለ ስለ አማራ ህዝብ ስትሉ ትታችሁ፣ለብቻዬ ሠርቼ ውጤታማ እሆናለሁ የምትሉ ውጤታማ እንዳልሆንን ተረድታችሁ፣ ትርምሱ እና አሉባልታው አስቀይሟችሁ የተደበቃችሁ የሚታረዱ ወገኖቻችኑን አስባችሁ፣ በማሕበራዊ ሚዲያ ወገንን በመስደብ የጀገናችሁ የሚመስላችሁ ባህሪያችሁን አርማችሁ በህብረት እንድንሰራ እና መላው አማራ በአንድነት እንደንብ ተነስቶ ጥላቱን በአጭር ጊዜ ድል እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። መስከረም 20 ቀን 2025 ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ህበረት ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ነበልባሎቹ የማረጉ ተማረ ልጆች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከፍ ብለዉ ለመብረር 🦅 እንደ ንስር ታድሰዉ እየመጡ ነው። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አ
+3
ነበልባሎቹ የማረጉ ተማረ ልጆች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከፍ ብለዉ ለመብረር 🦅 እንደ ንስር ታድሰዉ እየመጡ ነው። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ፅጌ ኮር ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ይሄን ሰራዊት ይዞ እኮ ነው በጣም ደነፋችሁ ያለ 😂 የen*ጭ*ቅ ልጅ 😂🤣 አይ ገለቴ አልቀርብሽም ውድ አማራዊያ ቻናላችን የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል ከግንባር እየሰራች ትገኛ
+1
ይሄን ሰራዊት ይዞ እኮ ነው በጣም ደነፋችሁ ያለ 😂 የen*ጭ*ቅ ልጅ 😂🤣 አይ ገለቴ አልቀርብሽም ውድ አማራዊያ ቻናላችን የእለት ከዕለት የትግሉን እንቅስቃሴ በመከታተል ከግንባር እየሰራች ትገኛለች።   ይወዳጁን!! ለመላው አማራ ተደራሽ እንዲሆን ቻናላችን ጆይንና ሸር  ያድርጉ! 👇 👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk  

አባታችን
አባታችን

"ወደድንም ጠላንም የአማራ አንገቱ አንድ ነው" አማራ የተደቀነበትን የሕልውና አደጋ ቀድመው የተረዱት ደጃዝማች ፀሀዩ እንቁስላሴ የጣሊያን የአምስት አመት ወረራ ሶስት ታናናሽ ወንድሞቻቸውን ደጃዝማች ክፍሌ እንቁ ሥላሴ፣ ቀኛዝማች ታደሰ እንቁስላሴ እና ደጃዝማች ወርቁ እንቁሥላሴ በመያዝ በዱል በገደሉ የጠላትን ጦር ረፍት ያሳጡ አርበኛ ናቸው። በልማትና በአስተዳደር ስራቸው የተመሠከረላቸውና አንቱ የተባሉ ናቸው። የጎጃም እንደራሴ ሆነው ጎጃምን ባስተዳደሩበት ወቅት የደብረ ማርቆስ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ያሰሩትና የደብረማርቆስ ከተማ ልዩ ምልክት የሆነውን የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን አደባባይ ያስገነቡት ደጃዝማች ፀሀዩ እንቁስላሴ ናቸው። በወቅቱ ለገበያም ለምንም የሚመጣውን ባላገር እያስተባበሩና አብረው ድንጋይ እየተሸከሙ ያሰሩት የንጉስ ተክለሀይማኖት አደባባይ አሁን ድረስ የከተማው ድምቀትና ልዩ ምልክት ሆኗል። በደብረማርቆስ  የመጀመሪያውን ባንክ በመክፈት ያስጀመሩትም እኚሁ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ሥላሴ ናቸው። አርበኛው ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁ ሥላሴ ፋሽስት ጥሊያን ከተባረረ ከዓመታት በኋላ የተማሩ የአማራ ወጣቶችን ወደ ቤታቸው ጠርተው በአማራው ላይ የተደቀነውን የኅልውና አደጋ በሚመለከት አወያይተዋቸው ነበር። «እንዳያችሁት ፋሽስት ጥሊያን ፊት ለፊትና በጀሌዎቹ አማካኝነት አገሩ ድረስ ወጥቶ ቤቱን ያቃጠለው፤ የዘረፈው፤ የገደለው፤ ባገሩ እንዳይኖር ያሰደደው በብዛት አማራውን ነው። ይህ ጠባሳ በቀላሉ የሚጠፋ አይደለም። እንደሚመስለኝ ከእንግዲህ በኋላም ማንም ቢመጣም የሚገድለውና ጠላት የሚያደርገው አማራውን ነው፤ አማራ ዛሬ ካልተደራጀ ወደፊት የሚገድለው ጠላቱ ብዙ ነው። ለይቶ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም ፤ የሳይንት አይልም፡፡ እኛም ወደድንም ጠላንም የአማራው አንገት አንድ ነው። እናንተ ምን ታስባላችሁ?» ብለው ሁሉም ያልበቁትን አስተያየት በጥያቄ መልክ እንዳነሱላቸው አቶ ብርሀኑ አስረስ «የታሕሳስ ግርግርና መዘዙ. . .ማን ይናገር የነበረ. . .» በሚል ርዕስ ለአንባቢ ባቀረቡት መፅሐፍ ገልፀዋል። እንዲህ ብለው ከተናገሩ ከጥቂት አመታት በኋላና ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ እሳቸውንና ወንድሞቻቸውን ለማፈን ከተንቀሳቀሰው ሰራዊት ጋር ብርቱ ውጊያ አድርገው በመጨረሻ በቀረቻቸው አንድ ጥይት ራሳቸውን አጥፍተው የክብር መስዋዕትነትን ተቀብለዋል። በዚህ የተበሳጨው የደርግ ሰራዊት ሬሳቸውን በትውልድ ቀያቸው በመርሀቤቴና ሰላሌ እንዲጎተት አድርጎል። ሶስት ወንድሞቻቸው በደርግ እጅ ወድቀው ተረሽነዋል። በእኚህ አማራ የተደቀነበትን የሕልውና አደጋ ቀድመው በተረዱ አርበኛ ስም ፋኖ ምንም አይነት አደረጃጀት አለመሰየሙ የሚገርም ነው። ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የሚጀመር ከሆነ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በሚቢል ደረጃ ሊፈርስ ይችላል ተባለ። ለግለሰብ ስልጣን ሲባል በዕርስ በዕርስ ጦርነት ዉስጥ ያለዉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአሁኑ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የሚጀመር ከሆነ ሰራዊቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ይፈርሳል ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ 78ኛ ክፍለጦር ወታደራዊ መኮነን ለጣቢያችን ተናግሯል። ሰራዊቱ ላለፉት ሰባት አመታት በዉስጥ ጦርነት የደከመ በመሆኑ ከጎረቤት ሀገር ጋር ለሚደረገዉ ጦርነት በቂ አቅም እና ጉልበት የለዉም ብሏል። በሁመራ በኩል የተሰማራው ሰራዊት ለዚህ ጦርነት የማይመጥን ነዉ ያለዉ መኮነኑ ከሰሞኑ ከተለያዩ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወጡ የሰራዊት አባላት ዕድሜያቸው ያልደረሱ በመሆናቸዉ ለሀገሪቱም ዋጋ ያስከፍላሉ ብሏል። የቀይባህር ጉዳይን በጦርነት ለማስመለስ የተለያዩ የጦርነት ዝግጅቶች እያደረገ ያለዉ አገዛዙ ከጅምሩ በርካታ ፈተናዎች ገጥመዉታል።የአማራ ህዝብን በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ለማድረግ ቢታሰብም ህዝቡ ከኤርትራ ጋር ጦርነት የማይፈልግ መሆኑን በይፋ አስታዉቋል። በአሁኑ ሰአት የአማራ ህዝብ በጦርነት ወደብ ሳይሆን የሚፈልገው ህልውናውን ማረጋገጥ ብቻ ነዉ በማለት ለአገዛዙ ጠንከር ያለ ምላሽ ሰቷል።የኦህዴድ ብልፅግናዉ አገዛዝ ጦርነት ለመጀመር በቂ ዝግጅት ያድርግ እንጂ ሰራዊቱ ግን ለዚህ ጦርነት የሚመጥን አደለም ተብሏል። ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አባ ተስፋዬ ቁሜ ለፋኖ ትፀልያለህ ተብለው ቤተክርስቲያን ደጃፍ ተ*ገ*ደሉ። በዛሬው እለት በአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ
አባ ተስፋዬ ቁሜ  ለፋኖ ትፀልያለህ ተብለው ቤተክርስቲያን ደጃፍ ተ*ገ*ደሉ። በዛሬው እለት በአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ፈንድቃ ቀበሌ መድሃኒያለም ገዳም ዓለም በቃኝ ብለው ገዳም የተቀመጡ አባት አቡሃይ ተስፋየ ቁሜ የሚባሉ የ 80 ዓመት አዛውንት የ ፋኖ መረጃ ትሰጣለህ በሚል በ08/01/2018 ዓ.ም ከገዳሙ ውስጥ በመግባት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ደጋግመው በጥ*ይ*ት በመ*ም*ታት እ*ረ*ሽ*ነዋቸዋል። ምን አደረጉ ዓለም በቃኝ  ብለው የሰማይ ቤትን ናፍቀው የተቀመጡ አባት መ*ግ*ደ*ል? ፈጣሪ ፍርዱን ያስቀምጥ!!! ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#አንድነቱ_እየመጣ_ነው💪 የአፋብኃና የአፋህድ አንድነት በቅርቡ ሊበሰር ነው‼️ 2018 የመጀመሪያ ወራቶቾ የልዩነት መንገዶች የሚዘጉበትና አንድነት የሚበሰርበት ፣ አንድ ፋኖ ፣አንድ አማራ የምንሆን
#አንድነቱ_እየመጣ_ነው💪 የአፋብኃና የአፋህድ አንድነት በቅርቡ ሊበሰር ነው‼️ 2018  የመጀመሪያ ወራቶቾ የልዩነት መንገዶች የሚዘጉበትና አንድነት የሚበሰርበት ፣ አንድ ፋኖ ፣አንድ አማራ የምንሆንበት ወራት ነው🙏 አንድ አማራ ብቻ💪 #እየመጡ_ነው💪 10/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ዓፄ እያሱ ክ/ጦር አፋብኃን ተቀላቀለ!     ከዚህ ቀደም በሌላ አደረጃጀት ስር የቆዩ ብርጌዶችን ከነባር የአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ሰራዊት ጋር በማጣመር ዛሬ መስከረም 10/2018 ዓ.ም " ዓፄ እያሱ " የተሰኘ አዲስ ክፍለ ጦር ተመስርቷል። አዲሱ  ዓፄ እያሱ ክፍለ ጦር ከዛሬ መስከረም 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ ) "ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮርን ተቀላቅሏል።     አንድነት ጠላትን ለማሸነፍ ወሳኝ መሆኑን በማመን 639  የፋኖ ሰራዊት ዓባላትን  ከ21 በላይ የቡድን መሳሪያ (ብሬንና ስናይፐር) እንዲሁም ዲሽቃ ትጥቆችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በመያዝ ነው በአንድነት የአማራን ህዝብ ከፈፅሞ ጥፋት አደጋ ለመታደግ በቁርጠኝነት  ለመታገል በመወሰን ነው አፋብኃ በላይ ዕዝን ለመቀላቀል እንደቻሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች አርበኛ ጌትነት አለባቸውና አርበኛ ጌታቸው መኩሪያ አረጋግጠዋል። እኒህ 639 እና ከሌሎችም ሀይሎች ጋር በመሆን ክፍለ ጦር የተመሠረተ ሲሆን የዓፄ እያሱ ክ/ጦር ሊቦ ከምከም፣እብናት፣ፎገራ፣አስታ፣አምቦ ሜዳን ጨምሮ ሰፊ ቀጠና የሚሸፍን ቀጠና መሰረት አድርጎ የተደራጀ ክ/ጦር ነው።     የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር አመራሮችና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች አንድነትን ፈልገው መምጣታቸውን በማድነቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።    አፋብኃ /ሰሜን አማራ ቀጠና      በላይ ዘለቀ ዕዝ      መስከረም 10/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ይህ የራሽያ ወይም የቻይና ጦር አይደለም የአማራ እናት የወለደችው ዘመን የወለደው ጀግናው የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ ነው አለቀ ደግሞ ፎቶው AI ነው ሲሉ ለነበሩ ባንዳዎች ላክላቸውማ ! ኢሄስ ቪዲዮ ምንድነው ትሉን ይሆን ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ፊታውራሪው ግዮን ብርጌድ በዛሬው ዕለት ጠላት ላይ ጥቃት ሰነዘረ!! =========== በዛሬው ዕለት አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር ፊታውራሪው ግዮን ብ
+2
ፊታውራሪው ግዮን ብርጌድ በዛሬው ዕለት ጠላት ላይ ጥቃት ሰነዘረ!! =========== በዛሬው ዕለት አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለ ጦር  ፊታውራሪው ግዮን ብርጌድ ከሰከላ ግሽ አባይ ከተማ በመነሳት  ወደ ዳንካ ተንቀሳቅሶ የነበረው ወራሪና ዘራፊ የጠላት ሀይል ስቦ በማስከባት በክንደ ነበልባሎቹ አባግስ ሻለቃና ግትም ሻለቃ በተሰነዘረበት ጥቃት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ ሰከላ ግሽ አባይ ከተማ ፈርጥጧል። አሸባሪው ሀይል የአርሶ አደር ቤት በመግባት ሊጥ ደፍቷል፣የነጋዴዎችን ሱቅ ዘርፏል፣ለህጻናት የመጣውን ከበሳ ጤና ጣቢያ የሚገኝ ፕላምፕሌት ዘርፏል። የጠላት የራስ ምታት የሆኑት አናብስቶቹ አባግስ ሻለቃና ግትም ሻለቃ ጠላት ላይ በአደረሱት ጥቃት፡- ============= ጠላት ከነጋዴ ሱቅ የዘረፈውን ላርጎ ፈሳሽ ሳሙና፣ጃንጥላ ሙሉ በሙሉ መማረክ ተችሏል፤ 10 የዝናብልብስ፣7 ከስክስ ጫማ መማረክ ተችሏል፤ በአሸባሪው ቡድን ታፍኖ ሊረሸን የነበረ ወጣት ማስለቀቅ ተችሏል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! ግዮን ብርጌድ ህ/ግንኙነት    መስከረም ፱/፳፻፲፰    ጎጃም-ዓምሓራ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የኤርትራ ጦር!! በኢትዮጵያ "የቀይ ባህር መዳረሻ" ጥያቄ ምክንያት በብልጽግናና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር
የኤርትራ ጦር!! በኢትዮጵያ "የቀይ ባህር መዳረሻ" ጥያቄ ምክንያት በብልጽግናና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እና የጦር ተሽከርካሪዎችን እያከማቸ መሆኑን የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። ይህ እንቅስቃሴ በቀጠናው የጦርነት ስጋትን ከምንጊዜውም በላይ እየጨመረ ለመምጣቱ ማሳያ ነው። ምንጮቹ እንዳሉት፣ የኤርትራ ጦር በደባ-ስማ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የጋማ ከብቶች፣ ግመሎች እና አህዮችን እያሰባሰበ ነው። እነዚህ እንስሳት ለሎጂስቲክስ ድጋፍ ሊውሉ እንደሚችሉ ይገመታል። ከዚህም በተጨማሪ፣  ከባድ የጦር ተሽከርካሪዎች ወደ አካባቢው እየተጠጉ መሆኑንና ወታደራዊ ልምምዶችም እየተካሄዱ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል። ኤርትራ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገችባት የምትገኘው ደባ-ስማ ለብልጽግና የባህር በር ጥያቄ ማጠንጠኛ ከሆነችው የአሰብ ወደብ በ58 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያው የድንበር ከተማ ቡሬ ደግሞ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ወሳኝ የድንበር ከተማ ናት። ይህ የወታደራዊ እንቅስቃሴ የታየው፣ የብልጽግና ባለስልጣናት "የባህር በር መብታችንን በኃይልም ቢሆን እናስከብራለን" የሚሉ አስተያየቶችን ካሰሙ ከሳምንታት በኋላ ነው። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ይህንን የብልጽግና ፍላጎት "አደገኛ ዕንደራ" ሲል በጽኑ አውግዞ ነበር። አሁን በመሬት ላይ እየታየ ያለው እንቅስቃሴም የኤርትራ መንግስት ዛቻውን በተግባር ለማሳየት የወሰደው እርምጃ ሊሆን ይችላል የሚል አንድምታ ተሰጥቶታል። የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የአመራር ምደባና ሽግሽግ ተካሔደ። ================================================= የአፋብሃ ምዕ/አማራ ቲወድሮስ ዕዝ 5ኛ ክፍለ ጦር ‎የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድን  የአመራር ምደባና ሽግሽግ አካሔደ። #የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ   5ኛ ክፍለ ጦር  የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ለሁለት ቀናት ባካሔደው ውይይት አዲስ የአመራር ምደባና ነባር የአመራር ሽግሽግ አካሒዷል። የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ አርበኛ #ደመላሽ_አድነው እንዳሉት የብርጌድ አመራሩን እርስ በርስ በማገማገም፣ የነፃ ወረዳ መዋቅር አመራር እና የቀጠና አስተባባሪዎችን በወሰድነው ነጥብ  የአመራር ምደባና ሽግሽግ አስፈላጊ ሁኖ በመገኘቱ; ✅ሙሉ ሀላፊነትታቸውን ያለተወጡ አማራሮችን በማውረድና አዲስ አመራሮችን ወደፊት በማምጣት እንዲሁም  ✅ነባር አመራሮችን  የቦታ ሽግሽግ በማድረግ  ነበልባሉ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድን የነበረውን  ለጠላት አይበገሬነቱን የበለጠ ለማጠናከር እንዲመሩ ምደባ ሰጥተናቸዋል ብለዋል። የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ም/ጦር አዛዥ ሻለቃ #የኔአለም_ዘለቀ በበኩላቸው መሪ ስትሆን ጥበበኛ፣ ታጋሽ፣ አስተዋይ፣ቅን፣ከቤተሰባዊነት አስተሳስብ ነፃ መሆን እንደሚገባ ወንድማዊ አምክሮ ሰጥተው  አዲስ  እና ነባር የብርጌድ አመራሮች እንዲሁም የነብልባሉ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድ አባላት መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። ነበልባሉ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድ በቋሪት የአመራር ምደባ እና ሽግሽግላይ: 1) የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ም/ጦር አዛዥ ሻለቃ የኔአለም ዘለቀ፣ 2) የግዙፉ የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ አረበኛ ደመላሽ አድነው፣ 3) ግዙፉ የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክ/ጦር  ወታደራዊ አዛዥ  ፶ አለቃ ይበልጣል መልካሙ፣ 4) ግዙፉ የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክ/ጦር አደረጃጅት ኃላፊ አርበኛ አንለይ እንየው እና 5) የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ወታደራዊ መሪዎችና የብርጌድ  አመራሮች በተገኙበት  የአመራር ምደባው ተካሂዷል። በዚህ መሰረት ፥ 1. ሰብሳቢ ዲ/ን ደሳለኝ  ቻላቸው 2. ም/ሰብሳቢ ፋኖ እሱባለው ታደሰ 3. ወታደራዊ  አዛዥ ፶ ካሳሁን ጌታነህ 4. ምክትል ወታደራዊ  አዛዥ  ፲ አለቃ መማር አለባቸው 5. ወታደራዊ አስተዳድር  አርበኛ ሽታየ አስታጥቄ 6. ፋይናስ ኃላፊ ፋኖ  ሙሉቀን ደሳለው 7. ዘመቻ ሻለቃ ዘገየ ምኒበል 8. ም/ል ዘመቻ  ፋኖ ሽዋነህ ሙሉጌታ 9. ፖለቲካ ዘርፍ  ፋኖ አማረ በላቸው 10. ስልጠና መምሪያ ፲ ተፈራ በየነ 11. የሰው ኃይል ፋኖ ይናገር ጌታነህ  በመሆን ቃለ-ማህላ በመፈፀም ተመርጠዋል ሲል የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ  ህዝብ ግንኙነት ጊዚያዊ ተወካይ ፋኖ በላይ ሞገስ  ተናግሯል። (መሰከረም 9/01/2018ዓ.ም) ዘመኑ አማረ የ5ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦር በጊሸራቤል ወረዳ ነፃ በወጡ ቀበሌዎች ህዝቡን በማወያየት የህዝብ አስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ ይገኛል:: በዚህም የጎፍ ክፍለጦ
+2
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦር በጊሸራቤል ወረዳ ነፃ በወጡ ቀበሌዎች ህዝቡን በማወያየት የህዝብ አስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ ይገኛል:: በዚህም የጎፍ ክፍለጦር ዛሬ መስከረም 10/2018 ዓ.ም የጊሸራቤል ወረዳ ደል ቀይ አንባ ቀበሌ ህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#አስደማሚ_ጦር_እየተገነባ_ነው ፋኖን የመለቃቀም ስራ ነው የቀረን ከማለት ወደ AI የተሸጋገረው የብልፅግና ጩኸት ወዳጀ ይህ ትንታግ ሰራዊት ገና ማዕበል ሆኖ ይውጥሀል ፎቶ በስልጠና ላይ የሚገኙ ሰል
+4
#አስደማሚ_ጦር_እየተገነባ_ነው ፋኖን የመለቃቀም ስራ ነው የቀረን ከማለት ወደ AI የተሸጋገረው የብልፅግና ጩኸት ወዳጀ ይህ ትንታግ ሰራዊት ገና ማዕበል ሆኖ ይውጥሀል ፎቶ በስልጠና ላይ የሚገኙ ሰልጣኝ የፋኖ አባላት ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎