ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 136
المشتركون
+724 ساعات
+2087 أيام
+1 20130 أيام
أرشيف المشاركات
"በኦፕሬሽን ለሚ" ምክንያት የወግድ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ታፍነው ተወሰዱ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር በወግድ ግንባር ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በጠላት ኃይል ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት 12 ፓራ ኮማንዶዎች እና 2 የፓሊስ አባላት ሲደመሰሱ ከ6 በላይ የሚሆኑት ፓራ ኮማንዶዎች ቆስለው ሌሎች በሸነት ገደል መግባታቸው ይታወቃል:: ከመብረቅ ክፍለ ጦር ሰራዊት መካከል 1ኛ (አዳነ ሀብትነው) ሻለቃ እና ከ2ተኛ (ደምሰው ጎጡ) ሻለቃ የተውጣጡ አሃዶች የጠላት ኃይልን ክፉኛ ያስደነገጠ የጦር ሜዳ ጀብዱ ስለፈፀሙ ጠላት እርስበርስ እየተወናጀለ ነው::
"ኦፕሬሽን ለሚ" የሚባለውና ወግድ ወረዳ ለሚ ቀጠና ውስጥ ካቢ ላይ የተፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት ያስከተለውን ከፍተኛ መደናገጥ ተከትሎ የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ዛሬ ማለትም ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የወግድ ወረዳ አመራሮችን በድንገት በማፈን በታህሳስ 19ኙ ጥቃት ጠርጥረናቸዋል ብለው አስረዋቸዋል:: በዚህም መሰረት የወግድ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮነን አማረ፣ የወግድ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አራጋው እና የወግድ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ እንድሪስ በ105ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ታፍነው መወሰዳቸውን የውስጥ ምንጮች አረጋግጠውልናል:: የወግድ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማናዬ ደሳለው እና የወረዳው መንግሥት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ካሳዬ ጌታቸው ለ105ኛ ክፍለ ጦር ባቀረቡት ምክረ ሀሳብ መሰረት የተፈፀመው አፈና ስረ- ምክንያት ታፋኞች ከፋኖ ጋር ተባብራችሁ ሰራዊታችንን አስመትታችኃል የሚል መሆኑንም ነው የደረሰን መረጃ የሚጠቁመው::
እንደሚታወቀው የአማራ ባንዳዎችን ተጠቅሞ መጣል ልምዱ የሆነው ብልጽግና ወደፊትም ታላላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱዎች በፋኖ ሲፈፀሙ ፋሽስቱ አብይ አጠገቡ ያሉትን የአማራ ባንዳዎች ተጠያቂ ማድረጉ ተገማች ነው:: የአማራ ባንዳዎች ቀን እየጨለመ ነው፤ ነገ ከነገ ወድያ በርካታ ጄኔራሎች እና ሲቪል ባለስልጣናት አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ለአብይ ወታደሮች ሽንፈት እና ሞት ተጠያቂ ናችሁ ተብለው በአደባባይ በስሙኒ ገመድ እንደሚሰቀሉ ግልጽ ነው:: ለዚህ ማሳያው በዛሬው እለት ወግድ ወረዳ ውስጥ የተፈፀመው የአፈና ድርጊት ነው ሲል የመብረቅ ክፍለ ጦር ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ጌታቸው እሸቱ መግለፁን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ሙሉጌታ ሰማኝ ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት አስታውቋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም
#የድሮን_ቅኝት‼️
ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ጀምሮ ቋሪት ጣሊያ ቀጠና አካባቢው የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል ስለሆነም ጥንቃቄ ይደረግ‼️
21/ዐ4/2018 ዓ.ም
መነሻውን ከናዝሬት ከተማ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው መተሀራ ያደረገ የአገዛዙ ኃይል ወደ ሸዋ መተህብላ እየተጓዘ ባለበት በፋኖ ከባድ ጥቃት ተፈፀመበት!
በፋኖ የተከፈተው ድንገተኛው ጥቃት ለመመከት እጅግ አስቸጋሪ ነበር የተባለ ሲሆን፡ በዚህም ለብልፅግና ቡድን የሚያገለግሉ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል።
በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና የተሰማራው የጄነራል አሳምነው ፅጌ ዕዝ ሰራዊት እስከ ናዝሬት እና አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ድረስ በመወርወር በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀመ ድል እየተቀዳጀ ይገኛል።
ቢኒያም መልካ!
"206ኛ ኮር በሰጠኝ ነፃነት የጓደኛየን አቤል ሲሳይን ህይወት ታድጊያለሁ"
ታህሳስ 2018/ዓ.ም
ቢኒያም መልካና አቤል ሲሳይ በአረመኔው ሰራዊት ታፍሰው ድንገት ጅማ በሚገኘው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገናኙት ከአሰላና ሻሸመኔ ከተሞች ታፍሰው በጭነት መኪና ታጭቀው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ጥልመቱን እየጣሱ በሚጓዙበት ጊዜ ነበር።
ከእናቶቻቸው እቅፍ ተፈልቅቀው በጨካኞች መዳፍ የወደቁት እነዚህ ብላቴናዎች በጦላይ ማሰልጠኛ ካምፕ ለ4 ወራት በሚደንቅ ፍቅር መራራውን ህይወት እየተጎነጩ ከቆዩ በኋላ ስልጠናውን ጨርሰው እንደነገሩ ተመርቀው ጎጃም ክ/ሀገር የምትገኘውን 32ኛ ክ/ጦር ሲቀላቀሉ የ17 ዓመትና የ16 ዓመት ታዳጊዎች ነበሩ።
ከማሰልጠኛ ካምፕ እስከ ጎጃም ድረስ እረጅም መንገድ በሌትና በቀን ተጉዘው ደብረ ማርቆስ ሲደርሱ አዳዲስ የሰራዊት አባላት በየ ክ/ጦሩና ሻለቃዎች ሲበተኑ እነዚህ ሁለት ተዳጊዎች የ32ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሬጅመንት 4ኛ ሻምበል ጋንታ 1 ላይ ሳይነጣጠሉ ተመደቡ ።
ተዓምር እስከ ሚመስል ድረስ እጣፋንታቸው እስከ መጨረሻ አብሮነት የሆነላቸው ቢኒያም እና ሲሳይ በጋንታዋ ካሉ 8 ወታደሮች 5ቶች በሞት ሲለያቸው ከቀሪ አንድ ጓደኛቸው ጋር በፍርሀት ተውጠው እረጅሙ ሌሊት እስኪ ነጋ ይናፍቁ እንደነበር ከቀናት በፊት ቢኒያም መልካ 206ኛ ኮርን ከተቀላቀለ በኃላ እንዳጫወተኝ ነግሪያችሁ ነበር።
ነገሩ እንዲህ ነው፦
ቢኒያም መልካ ስርዓቱን በመክዳት ከደብረ ኤልያስ ወረዳ በማርዘነብ ቀበሌ ከመሸገው የአረመኔው ሰራዊት 32ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሬጅመንትን ለቆ በመውጣት 206ኛ ኮርን ከተቀላቀለ በኋላ ለጓደኞቹ በአደረገው ጥሪ መሰረት በሞት ጥላ ስር አብሮት የነበረውን አቤል ሲሳይን ጨምሮ ንጉሴ ቻሌ፣ ማንደፍሮ ደሴ የተባሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላትን ተቀብሎ የነፃነት አየርን እየተነፈሱ ይገኛሉ።
የአረመኔው ሰራዊት ፋኖ ኩላሊት ያወጣል፣ አንገት ይቆርጣል የሚለውን ውሸት በማጋለጥ ጓደኛችን ያስተላለፈውን መልዕክት ተማምነን መጠን ያየነው አቀባበል ከጠበቅነው በላይ ሁኖብናል ያሉት የቢኒያም ጓደኞች የለበስነው ዩኒፎርም ሰልችቶናል እንደ ቢኒ ልብሳችንን ቀይሩልን እያሉ ሲጣደፉ ተመልክቻለሁ።
"እዚህ ሰቀቀን የለም! እዚህ ርሀብ ጥም ፍርሀት ሰቆቃም የለም! አትፍሩ እኔም እንደናተ ተጠራጥሬ ነበር ልብሴን እንኳ የቀየሩልኝ እዚህ በመጣው በደቂቃዎች ውስጥ ነው የናፈቀኝን ነፃነት አግኝቻለሁ እናተም በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል" በማለት ለቀድሞ ጓዶቹ መልዕክት ያስተላለፈው ቢኒያም መልካ 206ኛ ኮር በሰጠው ነፃነት ከማሰልጠኛ እስከ ጋንታ ድርስ አብሮት መከራ የተቀበለውን የአቤል ሲሳይን ነፍስ መታደጉ እንዳስደሰተው ገልጿል።
ቀን በቀን የአረመኔውን ሰራዊት ፍርስርስ እያደረግነው የምንገኘው እኛ! በፀና አላማ፣ በስነ ምግባር በታነፀ ሰራዊት ፣ በማይቋረጥ የህዝብ ድጋፍ ፣ በመርህና በህግ በሚመራ ትግልና መሪ ታግለን የመጨረሻውን ድል እንደምንጎናጸፍ አንጠራጠርም።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ሰራዊቱን ለማዘመን እና የሰራዊትና አዋጊውን የትግል ቁመና ለመቀየር የታለመ የኮር እና ክፍለ ጦር እስከ ሬጅመንት አወቃቀሩን ሰርቶ ጨርሷል ።
በድሮው የአማራ ፋኖ በጎጃም የነበሩ 9 ክፍለ ጦሮችንና በውሳጠቸው ያሉ ብርጌዶችን በሰው ሀይል ብዛት በማሰልጠንና በማስከዳት በትጥቅ ግዥና ምርኮ ካጠነከረ በኋላ አሁን ያለውን አደረጃጀት በጣም በረቀቀና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ማደራጀት ችሏል።
ከዚህ በታች የተቀመጠው አወቃቀር በቅደም ተከተል የበፊቱና የአሁኑ ተቀምጧል። እንበርታ ማሸነፋችን እውን ነው 💪
ይህ የድሮው የአማራ ፋኖ በጎጃም አወቃቀር ነው 👇
1ኛ ክፍለ ጦር ፦
✔️ ባህርዳር ብርጌድ
✔️የጣናው መብረቅ ብርጌድ
✔️ አንሙት ያዛቸው ብርጌ
✔️ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ
2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር፦
✔️ደጋ ዳሞት ብርጌድ
✔️መብረቁ ብርጌድ
✔️ ዮሀንስ አለማየሁ ብርጌድ
✔️መዝገበ ጮቄ ብርጌድ
✔️መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ
3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር፦
✔️ግዮን ብርጌድ
✔️ዘንገና ብርጌድ
✔️ስሜነህ ደስታ ብርጌድ
✔️ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
✔️አቤ ጉበኛ ብርጌድ
✔️ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ
✔️ቢትወደድ አያሌው መኮነን ብርጌድ
4ኛ ጃዊ ክፍለ ጦር፦
✔️በላይ ዘለቀ ብርጌድ
✔️አንድነት ብርጌድ
✔️ገሞራው ብርጌድ
✔️አባይ መተከል ብርጌድ
5ኛ መንገሻ አቲከም ክፍለ ጦር ፦
✔️ቡሬ ዳሞት ብርጌድ
✔️ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ
✔️ጓጉሳ ወንበርማ ብርጌድ
✔️ወርቅ አባይ ብርጌድ
✔️አረንዛው ዳሞት ብርጌድ
6ኛ ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር፦
✔️ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ
✔️ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ብርጌድ
✔️ቀስተ ደመና ብርጌድ
✔️ጅበላ ሙተራ ብርጌድ
✔️በላይ ዘለቀ ብርጌድ
✔️ስናን አባጅሜ ብርጌድ
7ኛ ሀዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር፦
✔️ተድላ ጓሉ ብርጌድ
✔️የቦቅላ አባይ ብርጌድ
✔️አብራጃት ብርጌድ
✔️አዋበል መብረቁ ብርጌድ
8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር፦
✔️ሽፈራው ገርባው ብርጌድ
✔️አባ ኮስትር ብርጌድ
✔️ደባይ ጮቄ ብርጌድ
✔️ዛንበረሀ ብርጌድ
9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር ፦
✔️አባይ ሸለቆ ብርጌድ
✔️አረንዛው ጎንቻ ብርጌድ
✔️ሶማ ብርጌድ
እና ተጨማሪ ኮማንዶ ዩኒቲ ነበሩ ✍️
ከዚህ ቀጥሎ ደሞ አሁን በአዲስ መልክ የተደራጀው የኮር አወቃቀር ከነ አመራሮቹ ነው 👇👇
፩/102ኛ ኮር :-
1.ሰብሳቢ ~ዘውድዓለም አዱኛ
2.ም/ሰብሳቢ ~ ምስጋነው ይታየው
3.ወታደራዊ አዛዥ .~ኮሎኔል ሸጋው ሁነኛው
3.1.ምክትል አዛዥ~፶/አ መኳንት አበጀ
3.2.ዘመቻ. ~፻/አ ይንገስ
3.3.አስተዳደር. ~፻/አ ስራው ወ/እግዚአብሔር
3.4.ስልጠና ~አብርሃም አድማስ
3.5.ሎጅስቲክስ. ~ጌታቸው አጥናፉ
3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ዘላለም ጥላሁን
4. ፖለቲካ መምሪያ ~ማንችሎት ጥላሁን
5.ፋይናንስ መምሪያ ~ኤፍሬም ሽባባው
6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ .~ ዲ/ን አብነት
7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~ ይፍረድ ወዴ
8. አደረጃጀት ~ዮሃንስ አያሌው
፪/105ኛ ኮር:-
1.ሰብሳቢ ~ ያሬድ በቀለ
2.ም/ሰብሳቢ. ~ደመላሽ አንድነው
3.ወታደራዊ አዛዥ ~፶/አ ስማቸው ቢሻው
3.1.ምክትል አዛዥ ~ ፻/አ ገረመው አጋዥ
3.2.ዘመቻ ~አንዳርጌ ቻሌ
3.3. አስተዳደር ~ማረ ቢያዝን
3.4.ስልጠና ~.ኮማንዶ ፍቅሩ ዘውዱ
3.5.ሎጅስቲክስ ~ዋ /ሳጅን ብርሃኑ ናቃቸው
3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ግዛቸው መንበር
4.ፖለቲካ መምሪያ. ~ሽገዛ ሙሉጌታ
5.ፋይናንስ መምሪያ ~.መልሰው ፍቃዱ
6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~ፍሬዘር መንግስት
7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~.ዘላለም አዲስ
8. አደረጃጀት ~.አበባየሁ ባንታምላክ
፫/109ኛ ኮር:-
1.ሰብሳቢ ~ጎበዜ ጌታቸው
2.ም/ሰብሳቢ ~ክንፈመላክ ካሳ
3 ..........~ታዘበው ስየ
3.1. ምክትል አዛዥ ~፻/አ መለሰ አይናለም
3.2.ዘመቻ ~ንብረት ደሴ
3.3.አስተዳደር ~.ወርቅነህ የኔጌጥ
3.4.ስልጠና ~ደሳለኝ ዘውዱ
3.5.ሎጅስቲክስ ~ባህሩ አናጋው
3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~፻/አ ጊዮን
4.ፖለቲካ መምሪያ ~አማረ ካሴ
5.ፋይናንስ መምሪያ ~አዝመራው ቢያድግልኝ
6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~የቻለ አድማሱ
7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~.ስማቸው አባታለም
8. አደረጃጀት ~አለልኝ አያና
፬/201ኛ ኮር:-
1.ሰብሳቢ ~ ላይችሉህ ገበየሁ
2.ም/ሰብሳቢ ~ እሱባለው ባምላክ
3.ወታደራዊ አዛዥ ~ኮሎኔል አደመ ልጃለም
3.1. ምክትል አዛዥ ~፶/አ ደጉ ፈንታሁን
3.2.ዘመቻ ~ ፶/አ መኳንት ዓለም
3.3.አስተዳደር ~ ሻለቃ ዘላለም ጥላሁን
3.4.ስልጠና ~ ፲/አ ባለውጊዜ ባንተይርጋ
3.5.ሎጅስቲክስ ~.ተመስገን አድማስ
3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ ተበጀ ማተቤ
4.ፖለቲካ መምሪያ ~አረፋይኔ ተጎድ
5.ፋይናንስ መምሪያ ~ሙላቴ ዓለምነህ
6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~ሃብታሙ የሱፍ
7.ጊዜአዊ መንግስት መምሪያ ~አዳንከኝ እያሱ
8. አደረጃጀት ~አንለይ እንየው
፭/206ኛ ኮር :-
1.ሰብሳቢ ~ዳሞት አለኸኝ
2.ም/ሰብሳቢ ~መቻላቸውን ታፈረ
3.ወታደራዊ አዛዥ ~.፶/አ ዘላለም ደሴ
3.1. ምክትል አዛዥ ~፻/አ ደመቀ ዳምጤ
3.2.ዘመቻ ~በላይ ብዙአየሁ
3.3.አስተዳደር. ~አየነው 3.4.ስልጠና ~ሎጀስቲክ ፻/አ ክርስቲያን ደመላሽ
3.5.ሎጅስቲክስ ~፻/አ አስረስ ምህረቴ
3.6.ኢንዶክትሪኔሽን ~ስለሽ ጌታቸው
4.ፖለቲካ መምሪያ ~ጌራወርቅ ዳኛው
5.ፋይናንስ መምሪያ ~የኔነህ ፈንታሁን
6.ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ~ባዬ ደስታ
7ጊዜያውመንግሥትመምሪያ. ~መንግሥቱ አማረ
8, አደረጃጀት ~ደረሳቸው
እጅ የሰጠ ፋኖ የለም ...!
ምክንያቱም..
እጁ እሚያሰጥ እንጅ እጅ እሚሰጥ ፋኖም አማራም የለም፡፡ በታሪካችንም የለም፡፡
ሰሞኑን በቆላድባ እና በማክሰት አ-ረ-መ-ኔዉ የአብይ አገዛዝ እጅ ሰጡ እያለ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ የነበረዉም እ-ጅ-ም እ-ግ-ር የሌላቸዉ ህዝብን ሲያንገላቱ ሲያግቱ በተዘዋዋሪ አገዛዙን ሲያገለግሉ የፋኖን ስም ሲያጠለሹ የነበሩ በሆዳቸዉ የወደቁ ሆ-ድ አ-ደ-ር ሰ-ላ-ቶ-ዎ-ችን ነዉ፡፡
ምክንያቱም በፅናት እና በቁርጠኝነት የሚታገሉ ሌሎች ፅኑ ፋኖዎች እስካሉ ድረስ..
ይህ ትግል በጽናት፣ በቁርጠኝነት እና በአንድነት ፣በህብረት አረመኔው የአብይ አገዛዝ አስወግደን እንደምጥል እርግጠኛ ሁኘ እነግራችሀለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህን ትግል ላንጨረስ አልጀመርነዉም፡፡
ትግሉም ከአለት ላይ የተመሰረተ ነዉ..!
አሸንፈናል፡፡
ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነዉ፡፡
© Fano Amare Achenef
ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስተዳደር በዛሬዉ እለት በደድ እየሱስ አቦ ቀብሌ ሰፊ ሕዝባዊ ዉይይቱ እንደቀጠለ ነው።
@@@@@@@@@@@@@@@@
ስለሆነም ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት በሚያስተዳድራቸዉ ቀበሌዎች እየተዘዋዎረ የሕዝብ መድረኮችን በማመቻቸት ሕዝባዊ ውይይት እያካሄደ ድርጅታዊ መዋቅሩን እያጠናከረ ሲሆን በዛሬዉ እለት ጊዚያዊ መንግስቱ የ54ኛ ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊዉ እና የ201ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ በተገኙበት #በደድ እየሱስ አቦ ቀብሌ ውይይት አካሂዷል::
የህዝባዊ መድረኩም የመልካም አስተዳደር በመገምገም ህገወጥ ጮቄ ላይ የመሬት ወረራን እና አጠቃላይ የፋኖ ትግል አሁን ላይ የደረሰበትን ሁኔታ ግንዛቤ መስጠት ተችሏል ።
አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
የቴወድሮሰ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ለአባት አርበኞች ጦር ስልጠና ተሰጠ‼️
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራር በወረዳው ከሚገኘው የገደብ ቀበሌ አባት አርበኞች ስልጠና ተሰጥቷል ።
በስልጠናውም፦
_ ስለ ፋኖ ትግል መሰረታዊ ምክንያቶች
_ ስለ ፍትህ አሰጣጥ እና ስለቀበሌ አደረጃጀት
_ ስለ አዲሱ ኮርና ክፍለ ጦር አደረጃጀት
_ ትግሉ ስለደረሰበት ደረጃ በሰፊው ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን የተመረጡት አመራሮች በቀጣይ በቁርጠኝነት ፣በግልፀኝነትና በታማኝነት ድርጅታቸውንና ህዝባቸውን እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል።
ህዝባቸውን እና ራሳቸውን ከጠላት ለመጠበቅ ከቲም ጀምረው እስከ ሻለቃ ድረስ በመደራጀት የጠላት መምጫ በሮችን በመለየት የሌሊት ደፈጣ በመስራት መተሳሰር እንዳለብን የጋራ መግባባት ተደርሷል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
ታህሳስ 21/20018ዓ.ም
የመንገድ እገዳው መነሳቱን ስለማሳወቅ
የአማራ ብሔራዊ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ኛ ክፍል ከዚህ በፊት ➡️ከዱርቤቴ_ቁንዝላ ደለጎ
➡️ከባህር ዳር ጭንባ ቁንዝላ ደለጎ
➡️ከዱርቤቴ ዝብህስት ወገዳ
➡️ ከዱርቤቴ ሀሙሲት ማማላ
➡️ከዱርቤቴ _ዲላሞ ልሁዲ
መንገዶች ተዘግቶ እንደ ነበር ይታወቃል አሁን መንገዶች የተዘጉባቸው ምክንያቶች የተወሰኑ ስለተቀረፉ እና የመጪውን በአል ምክንያት በማድረግ
ከነገ ማለትም ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ
በቦታዎች ላይ የጣላቸዉ የእንቅስቃሴ ገዶች የተነሱ መሆኑን ማረጋገጥ እንወዳለን ትዛዙን አክብራችሁ እገዳዎችን በትግስት ስጠባበቁ የነበራችሁ አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ ባለሀብቶች ና መላው ህዝባችንን አሳያችሁት ጨዋነት ማመስገን እንወዳለን ።
ፋኖ ምስጌ ዘድንግል የ 55 ተኛ ክፍል ጦር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
ትግላችን የጌቶች እራት ግብዣ ሳይሆን፣ የሕዝብ ሕልውናን የማስከበር መራራ ጉዞ ነው።
ታላቁ አብዮተኛና የታጋዮች መሪ ማኦ ሴቱንግ እንዳለው "አብዮት የጌቶች እራት ግብዣ አይደለም!" አብዮት ጥልፍ የመጥለፍ ያህል ቅጥ ያጣ ትዕግስትም አይደለም። አብዮት በግፈኞችና በጭቁኛች መካከል የሚደረግ፣ ሕይወት የሚከፈልበት፣ ደምና ላብ የሚፈስበት የሕልውና ጦርነት ነው። ዛሬም በሀገራችን እያካሄድነው ያለው ትግል፣ በምቾት ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚነጋገሩበት "የሊቃውንት ክርክር" ሳይሆን፣ መጪውን ትውልድ ከባርነት ቀንበር ለማውጣት የሚደረግ መሪር ፍልሚያ ነው።
አምባገነኑ አገዛዝ ሰሞኑን በትግላችን ሂደት ውስጥ የተከሰቱ ጥቃቅን ስህተቶችን፣ የሰው ልጅ ባህርይ የፈጠራቸውን ድክመቶች መዝዞ እና የውሸት ታሪኮችን አቀናብሮ ፣ ሌት ተቀን በሚዲያዎቹ የፕሮፓጋንዳ ማሽን ሲያጮህ እያየን ነው። ይህ ድርጊት "ሌባ ቀድሞ ይጮኻል" እንደሚባለው ነው።
በየቀኑ በድሮንና በከባድ መሣሪያ የንጹሐንን ደም እንደ ጎርፍ የሚያፈስ አገዛዝ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እናቶችን ለረሃብና ለስደት የዳረገ አገዛዝ፣ ታሪክ የማይረሳውን የጅምላ ግድያ በሕዝባችን ላይ የፈጸመ አገዛዝ... ዛሬ ስለ ሰብዓዊነትና ስለ ሞራል ሊያስተምረን መሞከሩ በታሪክ የታየ ትልቁ የቀልድ ድራማ ነው።
ሰፊውና የተከበረው ሕዝባችን እንደሚያውቀው፤;በትግል ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶች የትግሉ ዓላማዎች አይደሉም። እነርሱ የጦርነት መራራ ገጽታዎች ናቸው። በእሳት መሐል አልፎ አበባን ሳይጠውልግ ማምጣት አይቻልም። የእኛ ዓላማ ሕዝባችንን ነፃ ማውጣት እንጂ ሕዝባችንን መበደል አይደለም። በስሜት፣ በስህተት ወይም በሁኔታዎች አስገዳጅነት የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ካሉ፣ እነዚህ ድርጊቶች የትግላችንን ዓላማ መነሻ መድረሻ እንዳልሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እኛ የእነዚህ ድርጊቶች ደጋፊዎች ሳንሆን፣ ስህተቶቻችንን የምናርም፣ ጥፋተኞችን የምንቀጣና ወደፊት የምንገሰግስ የሕዝብ ልጆች ነን።
በአውሮፓ፣ በአሜሪካም ሆነ በአየርላንድ የታዩት ታላላቅ የነፃነት ትግሎች ሁሉ እንዲህ ዓይነት ፈተናዎችን አልፈዋል። ታጋዮች በስህተት የፈሰሰን እንባ በማበስ ነው ድልን የተቀዳጁት። አገዛዙ እኛን አቅፎና ደግፉ ከያዘን እንስፍስፉ ሕዝባችን ሊነጥለን ቢሞክርም፣ እኛ ግን ከሕዝባችን ጋር በጥብቅ የተሳሰርን ነን። የሰው ልጅ ስህተት ይሠራል። አምባገነኖች ግን ግፍን "መንግሥታዊ ፖሊሲ" አድርገው ይሠሩታል። በእኛና በእነሱ መካከል ያለው ልዩነት ይህ ነው።
ስለሆነም፤ ለአስተዋዩና ጥበበኛው ሕዝባችን የምንለው ነገር ቢኖር፤ የአገዛዙን የፕሮፓጋንዳ መጋረጃ ቀደህ እውነተኛውን የታጋይ ልጆችህን ዓላማ እይ። ድክመታችንን አርመህ፣ ስህተታችንን መክረህ ከጎናችን ቁም! ካንተ የተለየን አይደለንም፤ እኛ የአንተ ቁጣና የነፃነት ፍላጎት ውጤቶች ነን። ዲሲፕሊን የድላችን መሠረት ነው።
የሕዝባችን ጭቆና እንቅልፍ የሚነሳችሁ ታጋዮቻችንም፤ እያንዳንዱ ጥይትና እያንዳንዱ ርምጃ የሕዝብን ክብር የሚጠብቅ ሊሆን እንደሚገባ ለአፍታም መዘንጋት የለብንም። ጠላት የሚጠቀምበትን ክፍተትም መፍቀድ አይገባንም።
በፕሮፓጋንዳ የምትገነባው የሐሰት ግንብ፣ በሕዝባዊ ጽናት መናዱ አይቀሬ ነው። የንጹሐን ደም የጮኸብህ አንተ እንጂ፣ ለነፃነት የወጣው ታጋይ አይደለም። ትግላችን የጌቶች እራት ግብዣ ስላልሆነ መስዋዕትነት ይኖረዋል፤ መስዋዕትነቱ ግን ወደ ታላቅ ድልና ነፃነት የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ ነው።
እንፅና!
© Estibel Alemu Zerihun
+3
የአገዛዙ ግፍ!
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አራጋው እንዳለ መኖሪያ ቤትን በብልጽግና አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ትናንት ታህሳስ 20/2018 ዓም በዶዘር አፍርሶታል።
ልጆቹንና ሚስቱንም ሜዳ ላይ በትኖ የቤት እቃውን በሙሉ ጭኖ በዘረፋ መውሰዱንም የአይን እማኞች ተናግረዋል።
1. ሀብትሸት ሞገስ … የዳባት ከተማ ከንቲባ
2. ሻለቃ ዳንኤል ታረቀኝ…
3. አዲሱ ሙሌ … የዳባት ከተማ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ የቤት ማፍረሱን እና ዘረፋውን እንደፈፀሙና እንዳስፈፀሙ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።
