ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 480
المشتركون
-524 ساعات
+677 أيام
+84830 أيام
أرشيف المشاركات
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጷግሜ 03/2017ዓ.ም
ከትጥቅ ትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዱ በዋግኸምራ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ቀበሌ አንዱ ሲሆን ከቀበሌው ማህበረሰብ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ተነገረ።
ጷግሜ 02/2017ዓ.ም የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ውይይት የፋኖ ሰራዊት ከማህብተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት፣የሲቪል አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ እና ከሰራዊቱ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሁም የፍትህ አሰጣጥን
በተመለከተ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በተነሱ የመወያያ ሀሳቦች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁ ታውቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጷግሜ 03 / 2017 ዓ.ም
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባልና የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ሰብሳቢ ወንድማችን አርበኛ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ!!
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#እንመክራለን_እንወያያለን_እንደራጃለን‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋበኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ በሆማ ቦነያ ቀበሌ ሕዝባዊ ውይይቶች አደረጓል ውይይቱን የአፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መ/ር አርበኛ ፋኖ በላቸው ዳኘ የመራው ሲሆን ስለ አገዛዙ እና ተልኮ ተቀብለው ሰርገው የሚገቡ ሃይሎችን በንቃት ተከታትሎ መያዝ እና በቀጠናው ለሚንቀሳቀሰው ለፋኖ አባለት ሪፖርተር ማድረግ እንዳለበቸው በጽኑ መልክቱን ያስተላለፈ ሲሆን አየይዞም ስለ ሕዝባው አስተዳደር ጉዳይ ማብራሪያ ሰቷል በድረጅት አሰራር እና መርሕ እንጅ ማንም በዘመድ አዝማድ የሚሰጥ ፍትሕ እንደሌለ ለሕዝቡ አስረድቷል። አክሎም ትግሉ ሕዝብን እና ሃገርን የማዳን እስከሆነ ድረስ ሕዝባችን እና አባት አርበኞች እራሳችሁን የትግሉ አካል በማድረግ ጥፋተኛውን በመምከር አለፍ ሲልም ለይታችሁ በመያዝ ነፃነታችንን በጋራ እንደናሰፍን ሲል በመድረኩ ለተሰበሰቡት አባት አርበኞች እና ሕዝብ መልክቱን አስተላልፏል‼️
ድል ለአማራ ፋኖ💪
ድል ለአማራ ሕዝብ💪
ክብር እና ሞገስ ለትግሉ ሰመአታት💔
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን💪
አፋበኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ በፍቃዱ በላይ ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
መ/ር አርበኛ ፋኖ በላቸው ዳኜ
03/13/2017 ዓ.ም
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
~ ተጠናክሮ የቀጠለው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ!
የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ያለ ምንም እንከንና ተግዳሮት ከድሉ ጫፍ ይደርስ ዘንድ የትግላችን መሠረቶች ከሆኑ አካላት ጋር የሚደረጉ የውይይት መድረኮች፣ ስልጠናዎችና የግንባታ ትምሕርቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ከእነዚህ መሠረቶች መካከል ሕዝባችን ቀዳሚው ነው።
በዛሬው ዕለትም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በማይ አንገታም ቀበሌ ከሚኖረው ማህበረሰብ ጋር በትግላችን መሠረታዊ ጉዳዮችና በወቅታዊ ሁኔታዎች ዉይይት አድርጓል።
በውይይቱ ለቀበሌው ማሕበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምሕርት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ማሕበረሰቡ ትግሉን በሁለንተናዊ ዘርፍ የሚደግፍበትንና በትግሉ ስለ ሚኖረው ሚና አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አማራ ነኝ የጀግኖችም ዘር ነኝ ለምን አትበለኝ ተወደደም ተጠላም ፈለክም አልፈለክም ተቀበልክም አልተቀበልክም አመንክም አላመንክም!!
ተመቸህም አልተመቸህም መጭው ግዜ የአማራ ፋኖ ዘመን ነው አማራ ማንንም ሳይለማመጥ የማንንም እርዳታ ሳይፈልግ የትኛውንም ምድራዊ ሴራ እየበጣጠስ ከሀይል ወደ ሀይል ይሽጋገራል ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየስማ አማራ ያሽንፋል ቃሌ ነው✊
#ድል ለመላው የአማራ ፋኖ🔥🔥
#ድል ለስፌው የአማራ ህዝብ💚💛❤️
አድስ ትውልድ!!
አድስ አስተሳስብ!!
አድስ ተስፋ!!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም😍
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሰበር_ወለጋ‼
፨፨፨፨፨፨፨፨
ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ጫንጮ ቀበሌ ለግዜው ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው ከባድ ጦርነት መከላከያ ትናንትና ማታ ሀይል በማስጨመርና ወደ ቦታው ማቅናቱን ተከትሎ ዛሬ በጧቱ ጀምሮ በከባባድ መሳርያ የታገዘ ከባድ ጦርነት መጀመሩን የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል‼
ጳግሜ 03/2017ዓ.ም
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሲቀልዱበት የነበሩትን የሞባይል ካሜራ አስይዞ ጨረቃን ሲያስቀርፃቸው አስመሸ።
ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን እ.ኤ.አ በ1905 አዲሱን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሃሳብ (Relativity theory) በጊዜው ለነበሩ ሰዎች ሲያስተዋውቅ ሰዎቹ ተረት ተረት ነው ብለው ስቀውበት ነበር። የሚገርመው መብሰላቸው ላይቀር ማገዶ መፍጀታው ነው። አንስታይን ሊያስረዳቸው ሞከረ እነሱ ግን ሳቁበት። ቀለል አድርጎ በምሳሌ ነገራቸው እነሱ ግን አፌዙበት። ነገር ግን እያደር ፅንሰ ሀሳቡ እየገባቸው መጣ። ሳቃቸውን በራሳቸው ላይ አደረጉ። በእሱ ግን ተደነቁ። አጨበጨቡለት፤ የኖቤል ሽልማትን ሸለሙት።
በስነፈለግ ሳይንስ የሚከሰቱ የተፈጥሮ ዑደቶችን አስመልክቶ መጋቤ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አቡሻህር መነሻ አድርጎ የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ ደቂቃና ሰዓት ጠቅሶ በጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም የጨረቃ ግርዶሽ በኢትዮጵያና በተወሰኑ የአለማችን አካባቢዎች ላይ እንደሚከሰት ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ይህ ነው ተብሎ ሊነገር የሚችል አንዳች የሆነ ነገር የሌላቸው ባዶዎች ንግግሩን ተረት ተረት ነው ብለው ሲያጣጥሉ፣ ተምረናል ባይ ቀለም ቅቦች ደግሞ ሲሳለቁበት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። የሳቃቸው ምንጭ ሳይንሳዊ እውቀት አልነበረም። ጥላቻና ድንቁርና ብቻ ነበር እንጂ።
ዛሬ ቀኑ ደርሶ በአንድ በኩል ባዶ ቆርቆሮዎቹ ሮዳስ የተናገረው ካልተሳካ አፋቸውን በእሱ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ሊከፍቱ፤ በሌላ በኩል ያሉት ደግሞ ዶ/ር ሮዳስ የተነበየውን ትንቢት በጉጉት ሊመለከቱ ተዘጋጅተው ሳሉ ተፈጥሮ ሰዓቷን ጠብቃ የጨረቃን ቀለም መቀየር ጀመረች፤ ቆየት ብላም በመሬት ጋረዳቻት በዚህም የአቡሻህርን ቀመር ትክክለኛነት የዶ/ር ሮዳስን ትንቢት እውነተኛነት አረጋግጣለች። ይህ ዛሬ የሚታዩ ዘመናዊ የስነፈለግ መተንበያ መሳሪያዎች ሳይሰሩ፣ አሜሪካ ሳትፈጠር፣ ናሳ ሳይቋቋም፣ ኢንተርኔት ሳይታሰብ ከ1800 ሺ ዓመታት በፊት የተሰራ ቀመር ነው።
ከክስተቱ በኋላ ባዶዎቹ በተበሳጨ ስሜታቸው የጨረቃ ግርዶሽ ጥቅሙ ምንድነው ወደሚል ጥያቄ ተሸጋግረው እያየንና እየታዘብን ነው። መቼስ ለመብላት የሚኖር ስለሆዱ አካባቢ ቢያወራ የሚገርም ባይሆንም የጨረቃ ግርዶሽ ጥቅሙ ምንድነው የሚል ሁሉ የሚከተሉትን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ማለትም የሐዋ ሥራ 2፥20 እና ራዕ 6፥12ን ያነብ ዘንድ እጋብዘዋለው። ነገር ግን ከጨረቃ ግርዶሹ ጀርባ አብዛኞቻችን ኢትዮጵያዊያን ደስ ያለን ዓለም የተለያዩ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ተጠቅሞ የሚያውቀውን የስነፈለግ ክስተት አባቶቻችን አቡሻህር በተሰኘ ቀመር ማወቅ በመቻላቸው ነው። ደስታችን አገር በቀል በሆነው እውቀት ነው። እናም ወዳጄ መስራት ባትችል እንኳን የሚሰሩ ኦጆችን አክብራቸው። የሰራሃቸው ከሌሉ እንኳን የተሰሩትን ተቀበላቸው፤ አክብራቸውም።
የዘመን አቆጣጠራችን፣ ከመስከረም እስከ ጳጉሜ ያሉ ወሮቻችን፣ ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉ ቀኖቻችን፣ ከሴኮንድ እስከ ደቂቃ ያሉ ሰዓቶቻችን የምንኮራባቸው የአገር በቀል እውቀት ትሩፋቶቻችን ናቸው። ወገን ቆም ብለን እናስብ።
አውሮፓዊቷ ኃያል አገር ጀርመን በላይብዝሽ ዩኒቨርሲቲዋ ውስጥ ለምን የግዕዝ ቋንቋን እንደምታስተምር ያወቀ ግን አለ? ኢትዮጵያዊ ተብለህ ቂጥህን ወትፈህ በየሚዲያው በአገር ሀብትና እሴት ላይ አሽሟጥጥ፣ ይወገዱ ይጥፉም በል። ምንም የሌላቸው ባዶዎች በጥላቻቸውና በድንቁርናቸው እንቁዎቻችንን እያጣጣሉ የማንነትና የሞራል ውዳቂዎች እንድንሆን ብዙ እየጣሩ ነው።
ትኩረት ለአገር በቀል እውቀትም።
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተናገሩት የጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል ! / የአሜሪካው ምርምር ተቋም ናሳ/
ከ6 ዓመታት በፊት በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና በዶክተር ጌትነት ፈለቀ በተዘጋጀው አንድሮሜዳ መጽሐፍ ገጽ 193 ላይ ጳጉሜን 2/ 2017 እንደሚታይ ቀድመዉ የነገሩን የፀሀይ ግርዶሽ (የጨረቃ ደም መስሎ መታየት) እንደማይቀርና የሙሉ ጨረቃ ግርዶሽ መታየቱ እና የጨረቃ ደም መምሰል የሚከሰት እዉነታ መሆኑን ናሳ አረጋግጧል ።
ኢትዮጵያዊ ዕውቀትን የሚዘክሩ በስነ-ፈለክ ፣ዐውደ-ጠፈር እና መሰል ሳይንሳዊ መስኮች ምርምሮች
የሚያሳዩ በርካታ መጽሃፍትን በመፃፍ እንዲሁም
ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ከቀሰመው በማያልቀውተዝቆ በማይደርቀው እንደ ውቅያኖስ በጠለቀ እውቀቱ ሰፊ ትንታኔ በመስጠት የምናውቀው ሳይንቲስት መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ ከስድስት አመታት በፊት ከስድስት አመታት በፊት በአንድሮ ሜዳ መፅሐፍ ገጽ 193 ላይ ቀድሞ የነገረን እዉነት እንደሆነ ያረጋገጠዉ ናሳ እንዳለው የጨረቃ ግርዶሽ በአውስትራሊያ፣ እስያ፣ አፍሪካ እና አውሮፓ ከምድር ግማሽ ላይ በሆነው ክፍል ይታያል። ብሏል ።
መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳሰ ታደሰ ጳጉሜን 2
ከምሽቱ 12፡21 (6:21 PM) - ደማቋ ሙሉዋ ጨረቃ በምሥራቅ አድማስ መውጣት እንደምትጀምር
እና ከምሽቱ 12፡28 (6፡28 PM) መሬት ጨረቃን መከለል ስትዠምር ድብዝዙ ግርዶሽ መታየት እንደሚጀመር እንዲሁም ከምሽቱ 2፡30 ላይ (8፡30 PM) ተጠባቂው ሙሉው የጨረቃ ግርዶሽ ዠምሮ ጨረቃ ደም የምትመስልበት ሰዓት መሆኑንና ከምሽቱ 3፡52 (9:52 PM) ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (ደም መምሰሏ) ማብቂያ እንደሚሆን በቪዲዮ ማብራሪያ ከሰጠበት በኋላ የናሳ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በጥናት በደረሱት መሰረት "በተለያዩ ሰአት አቆጣጠሮች በሴፕቴምበር 7 እና 8 አጠቃላይ "የጨረቃ ግርዶሽ በአለም አቀፍ ደረጃ ይከሰታል ክስተቱንም ከ 7 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የማየት እድል ይኖራቸዋል ሲል Space.com ዘግቧል ።
CBN News በበኩሉ ክስተቱን ሀይማኖታዊ መልክ በማየት በሰራው ዘገባ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርቧል ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የደም ጨረቃዎች በተለያዩ ቦታዎች ተጠቅሰዋል፤ እነዚህም በኢዩኤል መጽሐፍ፣ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ ሲል በጀመረው ጥልቅ ዳሰሳ።
የደም ጨረቃዎች በመጀመሪያ በኢዩኤል 2፡31፡- “ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ” ተብሎ ተነግሯል። ሐዋርያው ጴጥሮስ ያንን ትንቢት በሐዋርያት ሥራ 2፡20 ደጋግሞታል።
ከዚያም የፍጻሜው ዘመን መጽሐፍ የራእይ 6:12 እንዲህ ይላል:- “ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ እነሆም፥ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ ጨረቃም እንደ ደም ሆነ።
እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች ጨረቃ ወደ ደም ቀይ መለወጧን የፍጻሜው ዘመን እየደረሰ መሆኑን የሚያሳይ ሰማያዊ ምልክት እንደሆነ ይናገራሉ ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የታልሙድ የአይሁድ አስተምህሮዎች የጨረቃ እና የፀሐይ ግርዶሾች ለረጅም ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ምልክት ይታዩ እንደነበር ያመለክታሉ።
ከታሪክ አኳያ፣ የደም ጨረቃ መከሰት ከእስራኤል ጋር በቀጥታ በተያያዙ አንዳንድ በእውነት ዓለምን በሚለዋወጡ ክስተቶች መሆናቸውን የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት የሚያጠኑ የክርስቲያን መሪዎች፣ እንደ ፓስተር ጆን ሄጊ እና ፓስተር ማርክ ቢልትዝ ያሉት የሀይማኖት መሪዎች ገልፀዋል ባለፈው ሺህ ዓመት ውስጥ ሶስት ግርዶሾች ጎልተው የወጡ ሲሆን ይህም ከአይሁድ ህዝብ ዋና ዋና ክስተቶች ጋር ይገጣጠማል። ከ1493-1494፣ 1949-1950 እና 1967-1968 ተከስተዋል ብለዋል ።
በመሲሐዊ ትንቢት የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮጄክት መሠረት ታልሙድ እንዲህ ይላል፡- “የእኛ ረቢዎች አስተምረዋል፣ ፀሐይ በግርዶሽ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎች ዘንድ መጥፎ ምልክት ነው፣ ጨረቃም ግርዶሽ በሆነ ጊዜ፣ እስራኤል በጨረቃ፣ ጣዖትን አምላኪዎች በፀሐይ ስለሚቆጥሩ... በፀሐይ ግርዶሽ ከሆነ፣ በምሥራቅ መጥፎ ሰዎች ይኖራሉ፣ እርሱ ለእስራኤል መጥፎ ምልክት ነው፤ በምዕራብ ለሚኖሩት መጥፎ ምልክት በሰማይ ውስጥ ቢሆኑ ለዓለሙ ሁሉ መጥፎ ምልክት ነው። ብለዋል ።
እንደ ናሳ ዘገባ፣ የምድር ጥላ ጨረቃን ሙሉ በሙሉ በሚሸፍንበት ጊዜ አጠቃላይ ደረጃው ለአንድ ሰዓት ከ22 ደቂቃ ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል። በአጠቃላይ ምድር በጨረቃ ፊት ለፊት ለማለፍ ሶስት ሰአት ከ29 ደቂቃ ይወስዳል። ሲል ገልጿል ።
አለም በሰበር ዜና መልክ ትላንትና ዛሬ እየዘገቡት የሚገኘው የምድር ጥላ በጨረቃ ላይ ወድቆ ወደ ቀይ ቀይ ቀለም መለወጥና የጨረቃ ግርዶሽ በተለይም ሦስቱ ኢትዮጵያዊያን ነገሥታቶች ካሲዮፕያ (Cassiopeia)፣ሰፌውስ (cepheus) እና አንድሮሜዳ (Andromeda) በጠለቀ እውቀቱ ለብዙዎቻችን ያሳወቀን ፣ በዓለማዊ እውቀቱ ቢሆንም እስከ ዶክትሬት ዲግሪ [ PhD in astronomy (degree of philosophy in astronomical science )] ድረስ የዘለቀው የቅድስት ቤተክርስቲያንን የዘመን አቆጣጠር በፀሐይና በጨረቃ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማመሳጠር አስልቶ ነገረን መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ቀድሞ ደርሶበት አሳዉቆናልና ክብር ይገባል ።
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ባለፉት 18 ወራት በሕገወጥ መንገድ 223 ሺሕ ኢትዮጵያውን ወደ ዓረብ አገሮች መሄዳቸው ተነገረ
#Ethiopia: ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) እ.ኤ.አ. ከ2024 እስከ ሰኔ 2025 ድረስ በኢኮኖሚያዊ ችግርና በጦርነት ምክንያት፣ በሕገወጥ መንገድ በየመን አቋርጠው ወደ ዓረብ አገሮች የተጓዙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 223 ሺሕ መድረሱን አስታወቀ፡፡
እ.ኤ.አ. 2024 ጨምሮ እ.ኤ.አ. የ2025 የመጀመሪያ ስድስት ወራት በምሥራቅ የስደተኞች መተላለፊያ መስመር የሆኑትን ጂቡቲንና የመንን አቋርጠው ወደ ዓረብ አገሮች ከተጓዙ 238,000 የአፍሪካ ቀንድ ዜጎች መካከል፣ 97 በመቶ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን፣ ሶማሊያ ሁለት በመቶና አንድ በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የሌሎች አገሮች ዜጎች መሆናቸውን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት ስደተኞች በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ምክንያት ወደ ዓረብ አገሮች ለመጓዝ የሚገደዱት 97 በመቶ የሚሆኑት በኢኮኖሚ ችግር፣ ሦስት በመቶ...
አይ አብይ አህመድ የእጅህን ይስጥህ ፈጣሪ
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"ከዚህ በፊት የከፋፈሉንን እና ያጣሉንን ጉዳዮች ትተን በአማራዊ ስሜት የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነው።"
አርበኛ ሄኖክ አዲሴ በርታልን !!
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ በቢቸና ከተማ፣የትመን ከተማ፣ወይራ ጠልማ ቀበሌ እንዲሁም ደባይ ጮቄ ብርጌድ እና የክፍለ ጦሩ ጥምር ኃይል በጋራ በመሆን በማህበረ ብርሃን ቀበሌ የሚገኜውን የአረመኔው ሰራዊት ላይ ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።
በየትመን ከተማ ጠላት ይጠቀምበት የነበረው ካንፕ በቦንብ እና RPG መሳሪያዎች በኮስትር ልጆች ወድሟል ተቃጥሎል።
ጳጉሜ 03/2017 ዓ.ም
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
03/13/2017 ዓ.ም
➳የፋኖ ቤተሰቦችን ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፀመ‼️
➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 2ኛ /ተፈራ ዳምጤ/ ክፍለ ጦር መዝገበ ጮቄ ብርጌድ በደብረ ሰላም ቀበሌ ኑዋሪ በሆኑት አቶ ጌትነት እንየው ላይ ሰዴ ከተማ ቤተ-ክርስቲያን በሄዱበት ፋኖ ልጅ አለህ በማለት በዚህ መልኩ ተደብድበው ህክምና ላይ ይገኛል ።
አቶ ጌትነት እንየው የ72 ዓመት ሽማግሌ ሲሆኑ በግብርና የሚተዳደሩና አርሶ ከማደር ውጭ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንኳን በቅጡ ለይተው የማይረዱ በርካታ ቤተሰብ በመምራትና ታዋቂ የሀገር ሽማግሌ የሆኑ ምስጉን አርሶ አደር ናቸው።
ነገር ግን አማራ ከመሆናቸውና በተጨማሪ ታደለ ጌትነት የሚባል ልጃቸው መዝገበ ጮቄ ብርጌድ ውስጥ የአማራን ህዝብ ከመጥፋት ለመታደግ እንደ ሁሉም አማራ ወጣት እየታገለ ስለሚገኝ ለመደብደባቸው ትልቁ ምክንያት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ።
የአቶ ጌትነት እንየው የመኖሪያ ቤት ለከተማው ቅርብ በመሆኑ የተወሰኑ የሚኒሻ አባላት ወደ ቤት በመሄድ የቦንብ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርጉም የመዝገበ ጮቄ ብርጌድ ሻለቃ ሶስት መረጃ ስለደረሳት ተከታትላ ጥቃቱን በማክሸፍ ጥቃት አድራሾችን ወደ መጡበት በማባረር መልሳለች ።
ከዚህ በፊት በርካታ ጊዜ የፋኖ ቤተሰቦችን ማሰር፣ ማንገላታት ፣ መግረፍ እንዲሁም ከማዳበሪያና ምርጥ ዘር እንዲሁም ከየትኛም የማህበረሰብ አግልግሎት ውጭ በማድረግ እንደ አማራ ህዝብ ከሚደርሰው ግፍ በተጨማሪ የተለየ ጭቆናና አፈና ሲፈፀም ቆይቷል።
ሁኖም ግን በፋኖ በኩል በሆደ ሰፊነትና በአስተዋይነት ከሚገባው በላይ ትግስትን ተላብሰን ሆድ አደር ሚኒሻና የብልፅግና አመራር በእኛ ቤተሰቦች ላይ የሚያደርሰውን በእነሱ ላይ ከማድረግ ተቆጠበን ቀይተናል ። ከዚህ በኋላ ግን ለየትኛውም ቤተሰቦቻችን ላይ ለሚደርስ ጥቃት ትይዩ ዕርምጃ የምንወስድ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን ።
በመጨረሻም የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የባንዳ ቤተሰቦች ይህንን አስነዋሪ ድርጅት የሚሰሩ የቅርብ ቤተሰቦቻችሁን ጥብቅ ምክርና ማሳሰቢያ እንድትሰጡ ከወዲሁ እናሳስባለን።
መዝገበ ጮቄ ብርጌድ
ድል ለተገፋው አማራ ህዝብ
ክብር በጀግንነት ለተሰው ሰማዕታት
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
ዶክተር ሮዳስ🙏
ብቻህን በእወነት አንተ ከናሳ በላይ የምርምር ተቋም ነህ!
የቤተክርስቲያን እውቀት ድግምት ሳይሆን ጥበብ እንደሆነ ይህ ማሳያ ነው።
ወደ ምድር በጥልቅ ወርዳ ወደ ሰማይ በግርማ ወጥታ እውቀት የምትበረብረው ቅድስት ቤተክርስቲያን ሞጎሳ መለኮት ነው።
➾አርበኛ ዘመነ ካሴ በአፋብኃ ሲምፖዚየም ያስተላለፈው ታሪካዊ መልዕክት እና ድንቅ ንግግር‼
የተከበራችሁ የዚህ ውይይት ተሳታፊዎችና ተከታታዮች
ክቡራን የማሕበራት ተወካዮች
የተወደዳችሁ የመገናኛ ብዙሃን ሙያያተኞችና ድርጅቶች
ውድ የድርጅታችን አፋብኃ አመራሮችና የሠራዊታችን አባላት
ሁላችሁም በመላው ዓለም ያላችሁ አማራዎችና የአማራ ወዳጆች፤
በቅድሚያ የአክብሮት ሠላምታዬ ይድረሳችሁ!!
ከትናንት ጀምሮ እየተካሔደ ያለው ውይይትና እየቀረበ ያለው መልዕክት የአማራ ወገናችን ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ለመታደግ የሚያደርገው የሕልውና እና የፍትሕ ርትዕ ትግል አንድ ሁነኛ መገለጫ ነው።
ዛሬ በዚህ መድረክ ተሰባስበን ስንመክር በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት ለመመከት፡ ከምንግዜውም በላይ ንቃት ፈጥረን፡ አደረጃጀት አበጅተን፡ የትናንትን ጉድለት በዛሬ ጥረት አሟልተን ፡ነጋችንን የተሻለ የማድረግ ቁርጠኝነታችንን የምናድስበት ነው።
ባለፉት ሁለት ዓመታት የአማራነት ንቃትና መሰባሰብ ከእነውስንነቶቹ አመርቂ የሚባል እድገት አሳይቷል። ግዙፍ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም በመፍጠር የመደራጀት ያደረ የቤት ስራችንን መመለስና ማረም ጀምረናል!!
በአማራነት ላይ የተፈጠረው ንቃትና መሰባሰብ የዘመናት የጥቃት አዙሪትን ለመስበር በሚያስችል ግለት ውስጥ ይገኛል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ራሳችንን አጠናክረናል !! ለሕልውናው የሚሰለፍ ሕዝባዊ ኃይል ፈጥረናል!!
ሊያጠፋን የተነሳውን ጠላት በመመከት ማሸነፍ እንደምንችል አረጋግጠናል !!
የዕጣፈንታችን ወሳኞች እኛ ነን ብለን ስንነሳ የመናጆነት፣ የተከታይነት፣ የአጃቢነት ልማዶችን ሰብረን የአማራዊ ማንነታችን እና ፍላጎቶቻችን በአማራ ልጆች የሚወሰንበት ምዕራፍ ለመክፈት ነውና ጀምረነው ብዙ ርቀት ሔደናል።
የተከበራችሁ የዚህ መድረክ ተሳታፊዎች፤
አማራዎች ራሳችንን ብሎም አገራችንን ለማዳን አብዛኛውን የትግል መንገድ ሞክረነዋል።
በዜግነት ፖለቲካና በአገር አንድነት ትግል አልፈናል። ሆኖም በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት አልመከትነውም።
በዚያ መንገድ ኢትዮጵያን ከመስቀለኛ መንገድ መታደግ አልተቻለም።
አሁን ለረጅም ጊዜ ያልሔድንበት በአማራነት ተደራጅቶ ራስን የመታደግ ትግል የጊዜው ቁልፍ ተልዕኮ ነው።
አማራና አማራነት የዚህ ዘመን ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
በአማራነት ላይ በተከፈቱ ጥቃቶች ውስጥ ገና ከማለዳው እነደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ የገለጡት የወል ጥቃት መረዳት ተዳፍኖ የቀረ ነበር።
ኋላም እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያነሳሱት የአማራ ንቃት ቅስቀሳ ብዙም ሳይሻገር ቀርቷል።
በረጅሙ ታሪካችን ውስጥ አማራነታችን ላይ ጥቃቶች በቀጠሉበት፥ በአማራነት መሰባሰብ እና የጋራ ተቋም መፍጠር ሳንችል ቀርተን አማራን የሚያሕል ሕዝብ የሕልውና አደጋ ውስጥ ይገኛል።
ተቃርኖው ይገርማል !!
አገር የመሠረተ ሕዝብ ፣ ይብዛም ይነስም የአገሪቱን ተቋማት የመሠረተና የመራ ሕዝብ፣ ለሺህ ዘመን ፀንተው የቆሙ መንፈሳዊ ተቋማትን ያደራጀ ሕዝብ ፣ ለዘመናት አገር የጠበቀ አርበኝነት ያለው ሕዝብ ፥ ራሱን ከሕልውና ጥቃት የሚመክትባቸው ተቋማት አጥቶ ዛሬ ላይ ደረሰ።
አማራዎች ራሳችንን የምንጠብቅበት ሥርዓት፣ ፍላጎታችንን የምንገልጥባቸው አማራዊ ተቋማትን መፍጠር ዳገት ሆኖብን መኖራችን መገታት አለበት።
ይህ ትግል "የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ሕልውና በዘላቂነት የማረጋገጥ ነው" ስንል የሕልውና መሠረቶቻችንን የሚሸከሙ ተቋማትን የመትከል መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።
የፋኖ አንድነት ተቋማዊ ጉዞ የዚያ ምሰሶ ይሆናል!!
በአማራነት ተለይቶ መጠቃት በታወጀበት ዘመን እንኳ አባቶቻችንና እናቶቻችን ስለአገር እንጂ ስለአማራነታቸው አልመከሩም ፡ አልተሰባሰቡም፡ አልተደራጁም።
ስለአገር ዋጋ መክፈላቸው ባልከፋ ፥ ሲከፍሉት የኖሩት ዋጋ ግን በአማራነታቸው ላይ የተከፈተውን የጥፋት ጦርነት ሊያስቆመው አልቻለም።
የትናንት አለመደራጀት ለዛሬ ያወረሰን ምን እንደሆነ በውል ተገንዝበን ተነስተናል !!
ትናንት ያልሠራነው ሥራ ቁጭት ካወረሰንና ለዛሬ ብርቱ ትግል ስንቅ ከሆነን በቂ ነው።
ነጋችንን የምናሳምረው ግን በዛሬ የተባበረ ጥረታችን ነው!!
ይሕ ትውልድ ለነገ የሚያሻግረው የጥቃት ውርስ ሊኖር አይገባም !!
ይሕ የእኛ ትውልድ የቤት ሥራውን ሳይሠራ ቀርቶ የነገው ትውልድ ጥፋትን እና ፈፅሞ መገፋትን ሊወርስ አይገባም!!
ስለዚህ እንሰባሰብ !!
በአማራነታችን እንደራጅ !!
በአማራነት የመደራጀትና የመታገል ጉዳይ ግለሰባዊ እና ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን መተው ይፈልጋል።
በመካከለችን ያለ ትናንሽና መለስተኛ ቅራኔና ፀብን፥ ኩርፊያና ልዩነትን በመተውና በማቆየት ለወል ፍላጎታችን መሰለፍን ይጠይቃል።
ብሔርተኝነት እንደዚያ ነው !!
ከትናንትም ሆነ ከዛሬ ነገሮቻችን መካከል መርጦ መዘንጋት እና ለይቶ ማንሳትን ይፈልጋል !!
ስለጋራ አማራዊ ፍላጎታችን የመሰለፍ ጥሪ ነው !!
ያን ስናደርግ እንኳን ለአማራ ትውልድ፥ ለኢትዮጵያ እና ለሰው ልጆች ሁሉ የሚተርፍ ቁምነገር እንሠራለን!!
የጋራ ጥቃት አንገሽግሾን የወጣን ታጋዮች ሁሉ እንደአማራ ስንመክር፣ እንደፋኖ ስንነጋገር ከባድ የመሠለን ቀላል እንደሚሆን አይተናል። የራሳችንን ጉዳዮች በራሳችን ለመወሰን "የእብድ ገላጋይ..." አያሻንም። እናም የጀመርነው የአንድነት ጉዞ የተማከለ አማራዊ አታጋይ ተቋም በመመስረት የሚቋጭ ይሆናል።
ይሕ የአዲሱ አመት ድላችን ሆኖ ይመዘገባል!!
የተወደዳችሁ የሕልውና ትግሉ ተሰላፊ ምሑራንና ማሕበራት፤
ያለነው እንቅልፍ አልባ ዘመን ነው። እኛን ለማጥፋት ፍፁም ጭካኔ እና ሙሉ ቆራጥነት ያለው ገዢ ጠላት ነው የገጠመን።
የምናሸንፈው ከአጥፊው ጠላታችን በላይ ስንጨክን፣ ከገጠመን ደመኛ በላይ ስንተጋ፣ ከእነሱ በላይ ስንደራጅና አንድ ስንሆን፣ ከጠላቶቻችን በላይ ቆራጦች ስንሆን ነው።
ከእነሱ በላይ ስንሠራ እንጂ በእነሱ ልክ እየተራመድንም አይደለም።
ስለሆነም በዓለም ዙሪያ ያላችሁ የአማራ ምሑራን፣ የዲያስፖራ ማሕበራት፣ ሰፊው በወጭ አገር ያለህ ወገናችን እንድትሰባሰቡ በአንድ እንድትቆሙ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ።
ስለወገናችን የምንቻቻልበት፣ ስለራሳችን የምንመክርበት፣ የምንተሳሰብበት ፣ በእያንዳንዳችን ላይ ልዩ ተልዕኮ የወደቀብን ወቅት አሁን ነው።
ከዚህ ወቅት በቀር ስለአማራና አማራነት የምንሰለፍበት የምንሠራበት የተለየ ጊዜ የለም። ዛሬ ነው !!
እናም የአማራ ማሕበራት ከተበታተነ ጉዞ ውጡና ተሰባሰቡ!!
በየአሕጉሩ አንድ ጠንካራ ሕብረት አቁሙ!!
ምሳሌ ሁኑ!!
የአንድነት ፤ የዲፕሎማሲ ፣ የአድቮኬሲና ትብብር ምሳሌ ሁኑ!!
በመጨረሻ ግን በዋነኛነት ፥ በመላው ዓለም የምትገኙ ማሕበራት፣ ምሑራንና መገናኛ ብዙሃን ሁሉንአቀፍ አማራዊ ጉዳዮቻችን የሚመከሩበት "የአማራ የምክክር ጉባኤ" በፍጥነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀርባለሁ።
አርበኛ ዘመነ ካሴ
የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ተሰፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ‼
አንድ አምኃራ እስከ ምፅአት አምኃራ‼
ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
