ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 389
المشتركون
-324 ساعات
+2587 أيام
+1 43630 أيام
أرشيف المشاركات
ሰበር ዜና! ፋናየ ውቤ ክ/ጦር በጠላት ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጸመ!      በትላንትናው እለት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ገደማ የጠላት ኃይል በርካታ ተሽከርካሪዎችን ከባህር ዳር ወደ ጎንደር አጅቦ በማለፍ ላይ እያለ በክንደ ፈርጣማዎቹ የፋናየ ውቤ ክ/ጦር አርኖ ጋርኖ ብርጌድ መክት ሻለቃ ፋኖዎች አማካኝነት ጥቃት ተፈጽሞበታል። ።      በጥቃቱ የጠላት ኃይል ከፍተኛ መደናገጥ የተስተዋለበት ሲሆን ጥቃቱ ላይ የተረፉት ሲያጅቡት የነበረውን በርካታ ተሽከርካሪዎችን በመተው እግራቸው ወደመራቸው አቅጣጫ ፈርጥጠዋል።         ብልጽግና ጥምር ኃይል እያለ የሚጠራውን አራጅ ቡድን ከእንፍራዝ ከተማ ለእገዛ የተላከ ሲሆን በጥቃቱ የቆሰሉትንና አስከሬኑን ሰብስቦ ሊመለስ ችሏል።             ➢ በዚህ ድንገተኛ ጥቃት               ** 05 ጠላት የሞተ               ** 12ቱ ጠላት ቁስለኛ ሲሆኑ 4ቱ ከባድ ቁስለኛ በመሆናቸው በፍጥነት ወደ ጎንደር ለከፍተኛ ህክምና መላካቸውን ለማወቅ ችለናል።               ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን           አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ  አብነት ሞላ                                  ህዳር 16 /2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ እና አሳምነው ዕዝ አሃዶች በጥምረት በተለያዩ ግንባሮች ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች እና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ብሩኬ ደምሴ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት የብልፅግና አራዊት ሰራዊት ላይ በተለያዩ ግንባሮች ድል ተጎናፅፈዋል:: ህዳር 15/2018 በሶስት ግንባር ወደ ማጥቃት የገቡት የእምዬ ምኒሊክ እና የአሳምነው ፅጌ ልጆች በአካድ ግንባር ብቻ የስርዓቱ ወታደር አብዛሀኛው ተከቦ ሲደመሰስ ከፊሎቹ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል። በዚሁ ግንባር ከ10 በላይ ክላሽ እና በርካታ ተተኳሽ የተማረከ ሲሆን ምሽጉ በጀግኖቹ ተሰብሮ ጠላት ሲፈረጥጥ እየተከታተሉ እንደ ንብ እየነደፉት ነው። በሌላኛው በነጋሽ ግንባር ያለው ምሽግም በመክት ሻለቃ የተደረማመሰ ሲሆን ጥላት ሬሳውን እያዝረከረከ ፈርጥጧል:: በሌላኛው በፉርሴ ግንባርም ስበር ሻለቃዎች የአብይን ሆድ አደር ውሃ ውሃ እያስባሉት ሲሆን ነውር ጌጡ የሆነው የዘረኛና ጨፍጫፊ ቡድን ከደሴ ተጨማሪ ሃይል የጨመረ ቢሆንም ኬላ ቦታዎችን በመያዝ በደፈጣ እያበራዩ ወደ መጣበት መልሰውታል:: በዚህ የተበሳጨውና በእግረኛ ሰራዊቱ ብሎም በመካናይዝዱ ውጤት ማምጣት የተሳነው ፋሽስቱ አገዛዝ አየር ሃይሉን በመጠቀም በድሮን ጥቃት የንፁሃኖችን ህይወት ቀጥፏል:: በተጨማሪም ቤትና ንብረትም አውድሟል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም

ድፕሎማሲያዊ መረጃዎች * በምስራቅ አፍሪካ በርካታ ቀጠናዎች ሰፊ የሆነ ፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ሲሆን ቀጠናው በሙት መንግስታት /በደካማ መንግስታት/ እጅ ወድቋል። ስለሆነም በሃያላኖቹ ፍጥጭ ደግሞ ምስራቅ አፍሪካ ላይ አድሱ ጦርነት በተባበሩት አረብ ኤምሬት፣በሳውድ አረቢያ ፣በአሜሪካ፣በቻይና ፣ በእስራኤል፣በኢራን እና በሰሜን አፍሪካዊቷ ግብፅ በኩል ሁለት ጎራዎች ተፈጥረዋል። ሁለቱም ጎራዎች ከሱዳን ፣ከኤርትራ እና ከኢትዮጲያ የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ከሚያተርፉት ብሔራዊ ጥቅም አንፃር ሲሆን በአንፃሩ ከጅቡቲ ፣ ከሞቃድሾዋ ሱማሌም እና ከኬንያ አንፃር ደግሞ ሌላ የሃይል አሰላለፍ እየተፈጠረ ይገኛል። በጥቅሉ ምስራቅ አፍሪካን የመቀራማት እና በእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ሃገራቶች እንድፈርሱ እና የደካማ መንግስታት መናሃሪያ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው። ስለሆነም ትግላችን እና ቀጠናው ምን ይመስላል የሚለውን በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን። ከእኛ አንፃርስ ምን እናድርግ የአማራ ሃይሎች?? ነገረ-ሱዳን * የምስራቅ አፍሪካዊ ግዙፍ ሃገር የሆነችው ሱዳን 35 ጊዜ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተደረገባት ሲሆን በአሁኑ ስዓት 18 ሃገራት በውክልና ጦርነት እየተሳተፉ ይገኛሉ።  የሱዳን ተፈላሚዎቹ ጀኔራል ሃምዳን ደጋሎ /ሄሚቲ/ እና ጀኔራል አልቡርሃን ሃገራቸውንና እና ህዝቧቿን እያጠፉ ቀጥለዋል። በዋናነት የተባበሩት አረብ ኤምሬት የሱዳንን የወርቅ ማዕድን እና የቀይ ባህር ጅኦ ፓለቲካዊ ስትራቴጅ አካል ለመሆን በማሰብ የጀመረችውን የድሮን እና ከባድ መሳሪያዎች ድጋፍ አጠናክራ ለሄሚቴ ሃይሎች ስትደግፍ  ባላንጣዋ ሳውድ አረቢያ ደግሞ ከአልቡርሃን ጎን ተሰልፋ ታላቁን ሃገር ሱዳንን እያፈረሱት ይገኛሉ። ጦርነቱ መሸናነፍ ያለው በርካታ ሰብአዊ ሃብት የወደመበት ሲሆን የሱዳን በርካታ ከተሞች ባግዳድ ሆነዋል። ነገረ-ኢትዮጲያ **** ኢትዮጲያ ቀደም ባሉት ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ ላይ የቀጠናውን የበላይነት በመውሰድ ታላቅ ሚናዋን ስትወጣ የነበረች ሃገር ብትሆንም የአብይ አህመድ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በሗላ የምስራቅ አፍሪካን ሰላም አሳጥቶታል።  የቀጠናው ቀውስ ጠማቂ መንግስት የሚል ስያሜንም አግኝቷል። ሃገረ መንግስቱም በእርስ በእርስ ጦርነት ለመፍረስ አንድ ሀሙስ የቀረው ነው ተብሎም ይታሰባል!! ኢትዮጲያ በአሁኑ ስዓት እጅግ ደካማ መንግስታት ከሚባሉት ውስጥ በዋናነት የምትጠቀስ ሲሆን በእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ሰላም የሌላት ሃገር ከሆነች 7 ዓመታትን አስቆጥራለች። በተለይም የሃገረ መንግስቱ /core state/ የሆኑት ትግራይንና አማራን በመነጠል የሃገሪቱን የፓለቲካ እና የስልጣን የበላይነትን ወደ ደቡብ ኢትዮጲያ ለመውሰድ በሚል የተፈጠረው ጦርነት ሃገሩን ወደ ማፍረስ እያመራው ሲሆን ጦርነቱንም በተከታታይነት የሚቀጥል አድስ ሃገር እና አድስ ጦርነት ለማዋለድም በሰሜኑ ኢትዮጲያ የጀመረውን የእርስ በእርስ ግጭት ወደ ምስራቅ ኢትዮጲያ እየወሰደው ይገኛል። ሰሞኑን በድሬድዋን፣ በጅቡቲ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢዎች አዳድስ ትንኮሳዎችን ለመፍጠር በብልፅግና ሃይሎች በኩል አንዳንድ የሳተላይት ምስሎች እየታዩ ነው። ኢትዮጲያ እንደ ሌሎች ሃገሮች በታሪክ ሺሚያ እና በውጮች ጣልቃ ገብነት ሳይታወቅ በድንገት ልትፈርስ የምትችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። በአሁኑ ስዓት አብይ አህመድ አድስ ጦርነት ለመፍጠር እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን በተለይም ከኤርትራ እና ከትግራይ ሃይሎች የጀመረው እሰጣ ገባ ወደ ጠቅላላ ጦርነት ሊያመራ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን አወዛጋቢ የሆኑ ሺምግልናዎችን ደግሞ ወደ ኤርትራ እና ትግራይ እየላከ መሆኑ ታውቋል!! የእንግሊዝ፣የአሜሪካ እና የኬንያ አሸማጋዮችን መላኩ የተረጋገጠ ነው። በእርግጥ እንደ ቀጠና ብቻ ሳይሆን በምዕራባውያን በኩልም አዳድስ ጫናዎችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ግልፅ ነው። ነገረ -ኤርትራ **** በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ካሉት ሙት አገዛዝ የተሻለ እና ጠንካራ ስትሆን ከውጮች ጣልቃ ገብነት አንፃር ተገማች አይደለችም!! ነገር ግን ከሱዳኑ አልቡርሃን  እና ከግብፅ ጋር ባላት ወታደራዊ ስትራቴጅ እና አጋርነት ተነስታ ከብልፅግናው ሃይል ጋር አይቀሬ ጦርነት ውስጥ ሊገቡ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለ ይታወቃል። የብልፅግናው መንግስት የስም ማጥፋት ዘመቻ እና ክስ የአስመራውን መንግስት ሰላም ነስቷል። ኤርትራ ሉአላዊ ሃገር ሆና እስከቆየችበት ጊዜ ድረስ በቀይ ባህር እና በአሰብ ወደብ ላይ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከሰጥቶ መቀበል መርህ ውጭ በጉልበት ለመጠቅለል በአብይ አህመድ መንግስት በኩል ያልተገደበ የጦርነት ጉስማ በአስመራው መንግስት በኩል በጥንቃቄ እየታየ ሲሆን ብልፅግና የሃገር ውስጥ ሰላሜን ያጣሁት በኢሳያስ በኩል በሚደረግ ድጋፍ ነው በሚል ክስ በፓርላማ እና ለሃገራት ኢምባሲዎች ሲከስ ይስማል። በተለይም የሃገሪቱ ትልቅ ም/ቤት ላይ የሚሰሙት ዛቻዎች እና ፍሬ ቢስ ትችቶች ለአስመራው መንግስት በቂ ዝግጅት እንዲያደርግ ዕድል ሰጥቶታል። ስለሆነም የተባበሩት አረብ ኤምሬት በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ላይ ከብሔራዊ ጥቅሟ አንፃር እያደረገች ያለችውን ሌላ አዳድስ የሙት መንግስታትን ለመፍጠር የምታደርገውን እገዛ አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን ሰሞኑን ለዚሁ ዓላማ የሚውል የጦር መሳሪያ በሞያሌ በኩል ወደ ኢትዮጲያ እያስገባች መሆኑ ታውቋል። እንደሚታወቀው የደካማው አብይ መንግስት ከወራት በፊት ጀምሮ በኢትዮ ጅቡቲ በኩል አዳድስ መሳሪያዎች እንዳይገቡ ያደረገ ሲሆን የሃገሪቱን የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ጭምር ወደ ደቡብ ኢትዮጲያ ክፍል እያዛወረው መሆኑ የተረጋገጠ ነው። ይሄ የሚያሳየው ሃገሪቱን የመበተን አዝማሚያ መሆኑን ልብ ይሏል!! ስለሆነም የሃገሪቱ እና የቀጠናው አሰላለፍን በተመለከተ የአማራ እና ሌሎች የኢትዮጲያ ሃይሎችስ ምን ማድረግ አለባቸው ትላላችሁ ወገን?? ሃሳብ አስተያየታችሁን አጋሩ!! ሰናይ ቀን ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

ህዝባችን ላይ የአብይን ሴራ ቀድመን ስላስተማርነው እና ስለነገርነዉ በሚደረገዉ ኢሰባዊ ድርጊት የሚወዘግብ ሳይሆን አሞቱን ክትት አርጎ ወደትግል እንድቀላቀል ይረዳዋል። ትክክለኛዉ የአማራ ፋኖ የአማራን ህዝብ እንኳን በአሰቃቂ ሊገለዉ ሸክሙ ሲከብደዉና እንቅፋት ሲመታዉ አይወድም። አማራ ግፍ ሲሰራበት ይጠነክራል እንጅ አይፍረከረክም ተወደደም ተጣላ ማሸነፉ አይቀርም ። አማራ ያሸንፋል ። ፋኖ አሰፋ መሰለ አሳምነው

የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ እና አሳምነው ዕዝ አሃዶች በጥምረት በተለያዩ ግንባሮች ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች እና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ብሩኬ ደምሴ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት የብልፅግና አራዊት ሰራዊት ላይ በተለያዩ ግንባሮች ድል ተጎናፅፈዋል:: ህዳር 15/2018 በሶስት ግንባር ወደ ማጥቃት የገቡት የእምዬ ምኒሊክ እና የአሳምነው ፅጌ ልጆች በአካድ ግንባር ብቻ የስርዓቱ ወታደር አብዛሀኛው ተከቦ ሲደመሰስ ከፊሎቹ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል። በዚሁ ግንባር ከ10 በላይ ክላሽ እና በርካታ ተተኳሽ የተማረከ ሲሆን ምሽጉ በጀግኖቹ ተሰብሮ ጠላት ሲፈረጥጥ እየተከታተሉ እንደ ንብ እየነደፉት ነው። በሌላኛው በነጋሽ ግንባር ያለው ምሽግም በመክት ሻለቃ የተደረማመሰ ሲሆን ጥላት ሬሳውን እያዝረከረከ ፈርጥጧል:: በሌላኛው በፉርሴ ግንባርም ስበር ሻለቃዎች የአብይን ሆድ አደር ውሃ ውሃ እያስባሉት ሲሆን ነውር ጌጡ የሆነው የዘረኛና ጨፍጫፊ ቡድን ከደሴ ተጨማሪ ሃይል የጨመረ ቢሆንም ኬላ ቦታዎችን በመያዝ በደፈጣ እያበራዩ ወደ መጣበት መልሰውታል:: በዚህ የተበሳጨውና በእግረኛ ሰራዊቱ ብሎም በመካናይዝዱ ውጤት ማምጣት የተሳነው ፋሽስቱ አገዛዝ አየር ሃይሉን በመጠቀም በድሮን ጥቃት የንፁሃኖችን ህይወት ቀጥፏል:: በተጨማሪም ቤትና ንብረትም አውድሟል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም

''ይህ ትውልድ ለመከራ ሳይሆን ለድል የተኳለ ትውልድ ነውና እናሸንፋለን'' ይህን ያለው አቢዮተኛው የትውልዱ መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነው። አንተ ደግሞ ለድል የተኳለው ትውልድ መሪ ነህ አለቃ! ክፋት
''ይህ ትውልድ ለመከራ ሳይሆን ለድል የተኳለ ትውልድ ነውና እናሸንፋለን'' ይህን ያለው አቢዮተኛው የትውልዱ መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነው። አንተ ደግሞ ለድል የተኳለው ትውልድ መሪ ነህ አለቃ! ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም! አንድ አማራ! እስከምፃት አማራ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

ገና ከዚህ የከፋ ጭካኔ እናያለን፤ ለሚመጣው ራሳችሁን አዘጋጁ ! ተስፋ እየቆረጠ የመጣው አገዛዙ፣ካድሬዎቹና ቅጥረኛ ጨፍጫፊ ሰራዊቱ ወደ ፊት አሁን ከምናየው የከፋ እንደሚያደርጉ በእጅጉ ይጠበቃል (አስካሁን ያላደረጉትና ያላሳዩን የአገዳደል አይነት ባይኖርም።) የአገዛዙ ጭካኔ አሁን ከምናዬው በላይ መሆኑንን ያሳለፍናቸው 7 ዓመታት ኀያው ምስክሮች ናቸው። ኦሮሞ ክልል ሻሸመኔ ላይ 2011 ዓ.ም የሰው ልጅ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ እርቃኑን ተዘቅዝቆ እንጨት ላይ ተሰቅሏል።በመተከል የ7 ወር ፅንስ በቢላ ሸልቅቀው በመውጣት መሬት ላይ ጥለው አይተናል። በወለጋ አማራዎች በአገዛዙ ገዳይ ኃይላት በአንገታቸው ሳይሆን በማጅራታቸው በገጀራ እየተገዘገዙ ሲገደሉ አይተናል። በተመሳሳይ ቦታ ነፍሰጡር እናቶች፣ህፃናት፣ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቤት ተዘግቶባቸው በአሳት ተለብልበው የከሰለ ገላቸውን ተመልክተናል። በወለጋ አማራዎችን "ስብሰባ እናድርግ" በሚል ጠርተው እንደተሰበሰቡ 10 ደቂቃ ባልሞላ ውስጥ በቁጥር 500 የሚሆኑ ንፁሃንን የሽመልስ አብዲሳ ገዳይ ሰራዊት በጥይት አረር በመጨፍጨፍ ድንገት የተዘጋ ቤታቸውን ሳይከፍቱ ቀርተዋል።በቤንሻንጉል የከበረ የሰው ልጅ ገላ በግሬደር እንደ ቆሻሻ ተዝቆ በአንድ ጉድጓድ ሲቀበር ያየነው እኛው ኀያው ምስክሮች ነን። ከላይ የጠቀስናቸውን ለጊዜው ለታሪክ እንተዋቸውና በዚህ እጭር ጊዜ ውስጥ የሆነውን ስንመለከት፦ በአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት፣ የእነ ባለምላይ ጡት ከደረታቸው በቢላ ተቆርጦ፣ ቆዳቸው እንደ በግ ተገፎ መንገድ ላይ ተጥለው አይተናል። በሰከላ ከ10 ያላነሱ ንፁሃንን ሰብስበው በመውሰድ ምላሳቸውንና ብልታቸውን በመቁረጥ፣አይናቸውን በማውጣትና ሌሎች የአካል ክፍሎቻቸውን ደግሞ በመቆራረጥ ት/ቤት ውስጥ ጥለዋቸው ሄደዋል። እንደቢቢሲ አማርኛ ሰሞንኛ ዘገባ እንኳን ብንመለከት ከ 5 ዓመት ሕፃን እስከ 70 ዓመት ያሉ አሮጊቶችን "ብትገሉኝ ይሻላል" እየተባሉ በሕብረት እንደ እንስሳ ደፍረዋል። ህዳር 13/2018 ዓ.ም(ከ3ቀናት በፊት) በመተከል ወረዳ ቡለን ቀበሌ ከ56 በላይ ንፁሃንን ነፍሰጡር እናቶችን ጨምሮ አገዛዙ በአደባባይ አስጨፍጭፎ እንደ ለመደው በጅምላ አስቀብሯል። በአርሲ በርካታ ክርስቲያኖች ማንነትና ዕምነት ተኮር ጭፍጨፋው ተፈፆሞባቸዋል። በድሮን አረር እያከሰለ በጅምላ የሚገድላቸውን ሕፃናትና ሴቶችም ሳንዘነጋ ነው። ይህንን ከሰው ተራ የወጣ ጨካኝ ስራውን እንዲያቆም የአገዛዙ አለቃ ሲጠየቅ "...ዛፍ ትከሉ፤ለአስክሬኑ ጥላ ይሆናል። የእኛ ወታደሮች የተደፈሩት በገጀራ ነው፤የእናንተ ሴቶች በሕብረት እንደ እንስሳ ቢደፈሩ ምን ችግር አለው?" የሚል መልስ በአደባባይ ይሰጣል። በዚህ ጨካኝ ሰው በላ ጠባዬ የምናውቀው አገዛዙና ካድሬዎቹ በደቡብ ወሎ ዞን እንደለመድው ፋኖ መሳይ ቅጥረኛ ግለሰቦችን አሰማርቶ በመጥረቢያ እጅ ሲቆርጥ አሳይቶናል። የሚገርመው ግን ዘግናኝ ድራማውን ለመስራት የፃፉት ስክሪፕት(script) ይሁን ተውኔቱን የሚሰራው ሰው አመራረጥ ላይ መሸወዳቸው ነው። ድርጊቱን በጭካኔ የፈፀመው ግለሰብ ከ12 ቀናት በፊት ለአገዛዙ እጅ እንደሰጠ በፎቶ አስደግፈው ማውጣታቸውን ዘንግተዋል። ከዚህ የባሰው አላዋቂነታቸውንና አስቂኙ ጉዳይ ደግሞ የአገዛዙ የሳይበር ሚዲያ ቅጥረኞች ያሰራጩት "በቁጥጥር ስር ዋለ" የሚለው ዘገባ ነበር። በሺዎች ከሚቆጠሩ ፋኖዎች መካከል ድርጊቱን የፈፀመውን ግለሰብ ብቻ ፈልጎ፣ መርጦና ለይቶ " በሌሎች ፋኖዎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ እንዴት ተቆጣጠረው፣?የት ስፍራ ላይ ባደረጉት ውጊያ፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የትኛው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት ክፍለጦር ያዘው፣? ድርጊቱን ፈፀመ በተባለ ማግስት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር የሚያውል አቅም አገዛዙ ቢኖረው ኖሮ ለምን "ፅንፈኛ" የሚለውን አካል አመራሮች መያዝ አልቻለም፤? ፋኖንስ እንደሚለው በሳምንት ማጥፋት ተሳነው፣?የድርጊቱ ፈፃሚ አካል የእውነት ፋኖ ቢሆን ሊደርስበት የሚችለውን አደጋ በመረዳት ለአገዘዛዙ ለዛውም በሰዓታት ልዩነት እጁን ይሰጣል ወይ? የሚሉ በጣም ቀላል የምርመራ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል። ነገሩ ግን "አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ" አይነት የጉብል ጨዋታ ነው። ይህ አሳዛኝ የአገዛዙ ድርጊት ሰሞኑን በመተከል የጨፈጨፋቸውን አማራዎች፣በአርሲ ያረዳቸውን ክርስቲያኖችን፣በአማራ ክልል ከጭፍጨፋው አልፎ በሕብረት የደፈራቸውን ከ3ሺህ የሚልቁ ሴቶችንና በሰከላ ብልታቸውንና ምላሳቸውን እየቆረጠ የገደላቸውን ንፁሃን አማራዎች እውነታ ፈፅሞ አይቀይረውም። ማጠቃለያ የአገሬ ህዝብ ሆይ...እኛ ጫካ ውለን ጫካ የምናድረው የአብይን አህመድን ከሰው ባህሪ የወጣ ጨካኝ አገዛዝ አስወግደን ለዜጎች ምቹ የሆነ ስርዓት ለመፍጠር ነው። እንጂ አጅ ለመቁረጥ፣ብልት ለመቁረጥ፣ጡት ለመቁረጥና ንፁሃንን ለመጨፍጨፍ ቢሆንማ አብይ አህመድ ከበቂ በላይ አይደለም ወይ?መልሱን ለእናንተ ትቼዋለሁ። አገዛዙ አቀናብሮ በለቀቀው ዘግናኝ ቪዲዬ የሚያገኝው ትርፍ የለም። ይልቁንስ ሊያደናግረው የፈለገው የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ዓለምአቀፉ ማኀበረሰብ የአገዛዙን ጠባይ ቀድሞ ያወቀ በመሆኑና የሰራውን የውሸት ድራማ የመመርመር አቅማቸው ከአገዛዙ የሳይበር ሚዲያ ዳፍንታሞች የላቀ በመሆኑ ሊፈጥር የማችለው ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ጫና የለም። ዛሬ ላይ አገዛዙ በዲፕሎማሲው፣በሚዲያ፣በፖለቲካው እና መሬት ላይ ባሉ ውጊያዎች እየተሸነፈ እንደሆነ ጠንቅቆ ተረድቶታል። ይህ ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ከቶታል። በመሆኑም አሳዳጊዎቹ ከስልጣን ሲለቁ በሶማሌ ፣በጭና፣በማይካድራ፣በሲዳማ፣በመተከልና በሌሎች የኢትዬጵያ ክፍሎች እንዳደረጉት የንፁሃን ጭፍጨፋ ምን አልባትም ከዛ የከፋ ጭፍጨፋ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ በቂ ማሳያ ነው። ስለሆነም ያለፈው አይግረመን ሊመጣ የሚችለው የከፍ ነውና። ይህንን በማሰብ ሁሉም አማራና ሌሎች ዜጎች ከወዲሁ ራሳቸውን በማደራጀት በአገዛዙ ለሚመጣ የሚችለውን ጭፍጨፋ መመከት ይኖርባቸዋል።

በተሻሻለው የመልሶ ማደራጀት ትግበራ በአዲስ የተቋቋመው ጊዜያዊ መንግስት በዘርፉ በርካታ ተግባራት እየተከወኑ ይገኛል ሲል 206ኛ ኮር አስታወቀ። ህዳር 16/2018 ዓ.ም   በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር ጊዜያዊ መንግስት መምሪያ በስሩ ያሉ የክ/ጦር እና የወረዳ አደራጀት መሪዎችን ካዋቀረ በኋላ ለደጀን፣ባሶሊበን፣አዋባል እና ወረዳዎች ጊዜአዊ መንግስት አስተዳደር አመራሮች ልዩ ልዩ ስልጠና መስጠቱን አሳታውቋል።  በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ የትኩረት አቅጣጫ የሆነው የህዝብ አስተዳር፣የፍትህ አሰጣጥ እና ወንጀል መከላከልን በበላይነት የሚመራው ጊዜያዊ መንግስት በሰራዊቱ ላይ የሚፈፀመውን ጫና የሚያቃልል ሲሆን በቴዎድሮስ ዕዝ ስራ አስፈፃሚ ተገምግሞ የፀደቀው የጊዚአዊ አስተዳደር አዋጅና መመሪያ ለታሳታፊዎቾ ቀርቦ ቀናትን የወሰደ ውይይት ተካሒዷል ሲልም አክሎ ገልጿል።  መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን በተቀላጠፈ መልኩ እያከናወነ የሚገኘው 206ኛ ኮር በሚያስተዳድራቸው ሁሉም ቀበሌዎች የጊዜያዊ መንግስት ቢሮዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸውን በማረጋገጥ የ206ኛ ኮር ጊዜያዊ መንግስት መምሪያ ኃላፊ ፋኖ መንግስቱ አማረ ለኮሩ ሚዲያ ክፍል አስታውቋል ።   አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

‎አፋብኃ አሳምነው እና ምኒሊክ ዕዝ በጥምረት በሰሩት ኦፕሬሽን የጠላት ሀይል ሙት ቁስለኛ እና ሙርከኛ ሆነ ‎================ ‎ አፋብኀ ም/አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ልጅ እያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር አሀዶች እና አሳምነው ዕዝ አፄዘራያቆብ ኮር ቡርኬ ደምሴ ክ/ጦር አንድ ሻለቃ በጋራ በጨፍጫፊው ስርዓት ላይ ታላቅ ጀብዱ በመፈጸም ሙት ቁስለኛ እና ምርኮ አድርገውታል። ‎ ‎ህዳር 15/2018 ዓ ም በሶስት ግንባር ወደ ማጥቃት የገቡት የእምዬ ሚኒሊክና የአሳምነው ፅጌ ልጆች በአካድ ግንባር የስርዓቱን ወታደር ከበባ ውስጥ አስገብተው አብዛሀኛውን ደምስሰው የቀረውን ደግሞ ቁስለኛና ሙርኮኛ አድርገውታል ። ‎ ‎እነዚህ ጥምር የፋኖ ሀይሎች በአካድ ግንባር ያለውን ምሽግ ደርምሰው በመግባት ጠላትን እያስፈረጠጡ በመንደፍ ከ10 በላይ የነብስ ወከፍ መሳሪያ እና በርካታ ተተኳሽ ማርከዋል:: ‎ ‎በነጋሽ ግንባር የገባውም የመክት ሻለቃ የጠላትን ምሽግ ደረማምሶ በመግባት ጠላት ሬሳውን እያዝረከረከ እንዲፈረጥጥ አድርጓል። ‎ ‎በሶስተኛው የፉርሴ ግንባር የገባችው ስበር ሻለቃ ደግሞ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ጠላት መግቢያ መውጫ አጥቶ ሲርበደበድ ውሏል:: ‎ ‎የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው ፋሽሽቱ የአብይ አህመድ ስርዓት ተጨማሪ ሀይል ከደሴ ለማስገባት ቢሞክርም የሚኒሊክ የመንፈስ ልጆች በደፈጣ አራግፈውት ባለበት እንዲቆም ተደርጓል:: ‎ ‎የፋኖ ጠንካራ ምት ያበሳጨው የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን በንጹሀን እና በምርኮኛ የአድማ ብተና አባላት ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል:: ‎ ‎በዚህ የድሮን ጠቃት የተጎዱ የአድማ ብተና አባላትን የፋኖ ሀይል እያሳከመ ይገኛል:: ስርዓቱ ይህንን የድሮን ጠቃት የፈጸመው ምርኮኛ የለኝም ለማለት እንደሆነ ከውስጥ አዋቂ የመረጃ ምንጮቻችን ማረጋገጥ ችለናል:: ‎ውጊያው የቀጠለ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል !! ‎መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ነው:: ‎ ‎ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎

ገለልተኛ አካላት በአማራ ክልል ምን እየተፈጠረ ነው ? የሚለው ማጣራት ይኖርባቸዋል። ምድር ከባዱን ጭካኔ በዚህ ዘመን እያስተናገደች ነው። ጭካኔ የተሞላበት አገዳድል በተለይም በአማራክልል በተደጋጋሚ እያየን ነው።  የባለምላይን ጡት ቆርጠው ፣ቆዳ ገፈው   ገድለው ማንኩሳ ላይ አሳይተዋል። መራዊ  ገበሬዎችን  ብልታቸውን ቆርጠው ገለው ከአስከሬኑ ላይ ጥለው አሳይተውናል። ፈንድቃ መነኩሴውን ከቤተክርስቲያን በራፍ ለፋኖ ትፀልያለህ ብለው በአሰቃቂ ሁኔታ ገለው አሳይተውናል። ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገበሬ ገለው ሬሳውን በመኪና እየጎተቱ አሳይተውናል።  ሰከላ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ከቤት ወስደው ጫካ ከደፈሩ በኋላ በአስቃቂ ሁኔታ አካሏን በቢለዋ ቦጫጭቀው ገለዋታል። እዚሁ ሰከላ 7 ሰዎችን ምላሳቸውን ቆርጠው ፣አይናቸውን አውጥተው ፣ብልታቸውን ቆርጠው ከትምርት ቤት ላይ ሬሳቸውን ጥለው አሳይተውናል።   ይህ በጥቂቱ የገለፅሁት አብይ አህመድ ትዕዛዝ ሰጦ በቀጥታ  እየፈፀመው ያለው አረመኔያዊ ድርጊት ማሳያ ሲሆን በእጅ አዙር ደግሞ  የሚሊሻ ፣የፖሊስና የአድማ ብተና አባላትን ፋኖ መስለው በየመንገዱ እንዲዘርፉ ፣አስገድደው እንዲደፍሩ ፣ በጭካኔ እንዲገሉ ትዕዛዝ ተሰጧቸው ማህበረሰቡን እያወናበዱ መሆኑን ደንበጫ አካባቢ የያዝናቸው በቂ ማሳያ ናቸው።     አብይ አህመድ ይህን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚፈፅመው በተለያዩ ምክንያት ነው። 1. የአማራ ጥላቻ ስላለበት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመበቀል እና ለማጥፋት 2. ሕዝቡን አሸማቆና አስፈራርቶ በፍርሃት ቆፈን ምንም እንዳያደርግ ለማድረግ 3. ፋኖ በዚህ ጭካኔ ተበሳጭቶ በገፍ እየከዳ ያስቸገረውን መከላከያ በበቀል እንዲያ እንዲያደርግ እና ገዳይናቸው ከሄዳችሁ ይገሏችኋል የሚል ቅስቀሳ ለማድረግ ብሎም ከፋኖ ሰዋዊ ስብዕና ለማውጣት 4. ፋኖን በአሸባሪነት ለመክሰስ ምንም አይነት የጦር ወንጀል የማይሰራ ፣በአለማበፍ ማህበረሰብ የተመሰከረለት የነፃነት ታጋይ በመሆኑ ያበሳጨው  ፋኖ መሳይ አካላትን በማሰማራት ጭካኔ እንዲሰሩ እያደረገ እንዲህ ያሉ አካላትን ፋኖ ለመያዝ ሲሞክር ደግሞ በጉጃው እየያዘ የሚፈልገውን ስራ እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም ገለልተኛ አካላት የአማራ ሕዝብ ምን እየደረሰበት እንደሆነ ገብተው ቢመረምሩ ጥሩ ነው። ሕዝባችን በጅምላ እደተደፈረ ነው፤በጅምላ እየተገደለ ነው፤ በጅምላ እየተፈናቀለ ነው። ጀሮ ያለው ለሰባዊነት የቆመ የትኛውም አካል ከአማራ ሕዝብ ጎን ሊቆም የሚገባበት ስዓት ነው። ጊዜው ይረዝማል እንጅ አብይ አህመድና ካቢኔው በአለም አቀፍ የጦር ወንጀል እና ዘር ማጥፋት መጠየቃቸው የማይቀር ጉዳይ ነው። ሩዋንዳ እና ሌሎች አካባቢዎች የተደረገው የየዘር ጭፍጨፋ በጊዜው ትኩረት እንዳልተሰጠው በኋላ ግን ማንም ከተጠያቂነት እንዳላመለጠ ታሪክ ምስክር ነው። ይህ ትውልድ  ላለመጥፋት ራሱን ለመከላከል  የሚያደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል አለም ትኩረት ሰጥቶ ሊከታተለውና ከጎኑ ሊሆን ይገባል። ©አርበኛ እስቲ በል ዓለሙ

ሰበር አምስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ! ህዳር 16/2018 ዓ.ም የአገዛዙ ስረዓት በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በመረዳት በአገዛዙ ስረዓት ተስፋ በመቁረጥ 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር የክፍ ጦሩ ቀኝ እና መሀንዲስ አባል ከነበሩት ውስጥ:- 1ኛ. አየነው እንዳይፈር 1 ኮርያ ክላሽ 150 ጥይት 3 ካዘና 2ኛ. አለበል አምሳሎ ኮርያ 1 ክላሽ 30 ጥይት 1 ካዘና 3ኛ. ወንዱ አንተ 1 ኮርያ ክላሽ 150 ጥይት 3 ካዘና 4ኛ. ሀብታሙ ፀገው 1 ኮርያ ክላሽ 150 ጥይት 3 ካዘና በመያዝ ከእነማይ ወረዳ ማህበርብረሃን ቀበሌ ከሚገኘው የጠላት ካንፕ ወጥተዋል። 5ኛ.መንግስቱ በላቸው የትውልድ ቦታ ሸበል በረንታ ሊዲ ቀበሌ ሲሆን በሸበል በረንታ ወረዳ የት/ት ፅ/ቤት ኃላፊ የነበርው ባንዳ ግዛቸው ጫኔ አታሎት እንዳስገበው ይናገራል። በሸበል በረንታ ወረዳ የዕዱኃ ቀበሌ የሚገኜው የአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት አስፈፃሚ አካላት እያካሄዱት ያለውን ዘር ተኮር የንፁሀን ጭፍጨፋ፣ዝርፊያ፣ ውድመት መሰል ነገሮችን ለህዝባችን የማይጠቅሙ መሆናቸውን በመረዳት ህዳር 16/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀለ። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ! ፋኖ ሐብታሙ የሱፍየቴድሮስ እዝ  የ201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት             ህዳር 16/2018 ዓ.ም

የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት በየጊዜው እየፈረሰ ይገኛል ።።።።።።።።።።።።።።።።። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል/አፋብኃ/ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጉና ክፍለ
+1
የአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት በየጊዜው እየፈረሰ ይገኛል ።።።።።።።።።።።።።።።።። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል/አፋብኃ/ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ  ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ የሚኒሻ መዋቅሩን በየቀኑ እያፈረሰው ይገኛል። 1.መኳንንት ሹመት ከነሙሉ ትጥቁ 2.ደስታዬ ወጣባቸው ከነ ሙሉ ትጥቅ ወጥተዋል።

እዉነቱ ተጋልጧል::እጅ ያስቆረጠዉ እራሱ ብልጽግና/ኦነግ/ኦህዴድ ነዉ ========================= ብልጽግና እጅ አስቆርጦ ፋኖ ቆረጠ ይላል:: መስጊድ አቃጥሎ ፋኖ አቃጠለ ይላል::ዘርፎ ፋኖ ዘረፈ ይላል::አማራዎችን በገፍ በወለጋ እና በመላዉ ኦሮሚያ ጨፍጭፎ ሸኔ ጨፈጨፋቸዉ ይላል::በአርሲ እና በልልዩ ልዩ ቦታዎች ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን በጅምላ ጨርሶ : ቤተክርስቲያንን አቅጣትሎ ሲያበቃ እረ ፈጽሞ ምንም የተገደለ ክርስቲያን ወይም ደግሞ የተቃጠለ ቤተክርስቲያን የለም ይላል:: ---- በተለይ አማሮች ሳትሸወዱ ይሄን የብልጽግና ወንጀል በርትታችሁ አጋልጡ:: አማራ ነኝ እያሉ እስክስታ መደለቅ:የአማራ ብሄረተኛ ነኝ እያሉ አሽኮለሌ መለፍለፍ አይደለም ቁምነገሩ:: አማራ ህዝብ ላይ የተቃጣ የስነልቦና ሰለባ እና ወረራ ተቀናጅቶ መጥቷል::ፋኖ አራጅ ነዉ ዘራፊ ነዉ ዘረኛ ነዉ ለማስባል ብዙ የተቀመረ ተንኮል አለ::ሁሉንም ቀበቷችሁን አጥብቃችሁ አጋልጡ:: ከተሜ ነኝ የምትል አማራ :- እንቶኔ እንቶኔን ኢተርቪዉ አረገች: እንቶኔ እንዲህ በላ እንዲህ ተገለበጠ እያልክ የምታጠፋትን እሩብ ያህል ሰዓትህን ሰጥተህ የብልጽግናን ሀሰት አጋልጥ:: በእዉነተኛ አካዉንታችሁ ከፈራችሁም በብዕር አካዉንት ብልጽግና/ኦነግ/ኦህዴድን ከማጋለጥ እና አረመናዊነቱን ከመናገር አትቦዝኑ:: ከብልጽግና በኩል የሚመጣ ማንኛዉንም የዉሸት ወሬ ተቀብለህ የምታራግብ ማስታወሻ የተነሳህ የአማራ አክቲቪስት ግን ቆም ብለህ አስብ:: =============== The truth has been exposed: The one who cut off the hand is the Abiy Ahmed government — the very perpetrator of the genocide. The Prosperity Party/OLF/OPDO committed the crimes and then shifted the blame onto others. The Prosperity Party under Abiy Ahmed has carried out serious genocidal acts while constantly shifting responsibility. They burned mosques — then claimed that FANO was responsible. They robbed civilians — then shifted the blame. They massacred Amharas in large numbers across Wellega and the wider Oromia region — then said it was the ‘Shene’ group that carried out the killings. In Arsi and many parts of Oromia, they brutally killed Christians and burned countless churches — yet their commissions falsely declared that “no such incidents occurred.” Despite all this, Western taxpayer money continues to flow freely to Abiy Ahmed’s criminal government. The international community must conduct an honest investigation and help Ethiopians stop this brutal genocidal regime.

አራዊት ሰራዊቱ በዓለም በር ከተማና አካባቢ ባሉ አምሐሮች ላይ የሚፈጽመው ግፍ ሕዳር14/2018ዓ.ም                       ወይዘሮ  አበበች ወንድይፍራው በዓለም በር ከተማ የምትኖር እሕት ሥትሆን መተዳደሪያዋም የመጠጥ ግሮሰሪ ነበር። ወይዘሮ አበበች በተደጋጋሚ ፋኖን ታግዣለሽ፣ ፋኖ ከቤትሽ ይጠቀማል እንዲሁም በጥቅሉ ፋኖነትን እየተገበርሽ ነው በሚል በአገዛዙ  ከደብረ ታቦር ከተማ እሥከ ወረታ ከተማ ተደጋጋሚ እሥር ተፈጽሞባታል። አገዛዙ በሐሰት ውንጀላ ያሰራትን ወይዘሮ አበበች ወንድይፍራው  ከእሥር ነጻ አድርጓት የግሮሰሪ ሥራዋን እየከወነች ቤተሰቧን እያሥተዳደረች ባለችበት ሁኔታ ጨካኞች በአረመኔነት ገድለዋታል።                  የእሕታችን አበበችን ነፍሥ የቀጠፈው ድርጊት ዕውነታ የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ባለበት ከተማ፣ አድማ ብተና ባለበት ቀጠናና በጥቅሉ የብልጽግና ወታደሮች ባሉበት ጭካኔን የተላበሰ አሥነዋሪ ግብር በመሐል ዓለም በር ከተማ ላይ ተፈጽሟል። ወ/ሮ አበበች ላይ የተፈጸመው ድርጊት ግሮሰሪዋ ላይ ሲጠጡ በነበሩ ታጣቂዎች ነው። የግድያው ምክንያትም ገዳዮቹ የሟችን የ16 ዓመት ሴት ልጅ አሥገድደው ለመውሰድ ሢሞክሩ ልጀን አትወሥዱም በሚል በተፈጠረ እሰጥ አገባ ነው። በመጨረሻም ወይዘሮ አበበች ልጄን አልሰጥም ብላ ነብሰ በላዎቹ ጋር ሥትታገል በጭካኔ ተኩሰው ገድለዋታል።                          ይህንና መሰል ድርጊቶች ከደብረ ታቦር እሥከ ባሕር ዳርና ከደብረ ታቦር እሥከ አዲሥ ዘመን ባሉ መዳረሻዎች የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት  በሕዝባችን ላይ አሥነዋሪ ድርጊት በተደጋጋሚ ይፈጸማል። በተለዬና በልዩ ሁኔታ አለም በርና ዙሪያው ለአካባቢው ማሕበረሰብ ምድራዊ ሲኦል ከሆነ ከራርሟል። የወይዘሮ አበበችን ግድያ ለአብነት አነሳን እንጅ አእላፋት ንጹሐን አምሐሮች ገፈት ቀማሾች መሆናቸው በተደጋጋሚ የሚሰራው ግድያ ምሥክር ነው።                    አገዛዙ አሥተዳድረዋለሁ በሚለው ቀጠና ዓለም በር ከተማ ላይ የተፈጸመው  በራሳቸው በአገዛዙ እጆች እንደሆነ አረጋግጠናል። ከገዳዮቹ  ጋር የከተማው ነዋሪ ወጣቶች አብረው የነበሩ ሲሆን በወይዘሮ አበበች ላይ የፈጸሙት ግፍ የአማራ ፋኖን ለማሥጠላትና ፋኖ ይህን አደረገ ለማለት የታለመ ቆሻሻ ድራማ ነው። በዚህ ቀጠና ከዓመት በላይ እዬኖረበት ያለው የአገዛዙ ታጣቂዎች ናቸው። ዕውነተኛ ፋኖዎች ከዓለም በር ከተማ በብዙ ማይሎች ርቀት ላይ ባሉበት ሁኔታ አገዛዙ ሥማቸውን ለማጥፋት የሄደበት የጭምብል ፈጠራዊ ድርሰት  ሆነ ተብሎ ፋኖነት እንዲጠላ ለማድረግ ነው። በተመሳሳይ ፋኖነትን ጭምብል ያደረጉ አካላት በተለይም ወደ ብልጽግና ቤት ተመልሰው የገቡ አካላት ሕዝብን የሚያማርር ሥራ እየፈጸሙ እንደሆነ እናውቃለን፤ ሕዝባችንም ሁኔታውን ደርሶበታል። ሥለሆነም በሕዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለው አሥነዋሪ ግብር በአገዛዙ የታቀደ ይሁንታ ነውና እየተተገበረ ያለው የአካባቢው ማሕበረሰብ በየሰፈሩ በመደራጀት ገዳዮችን አትግደሉኝ ማለት አለበት። በመጨረሻም ከደብረ ታቦር ወረታ ያለውን የሲኦል መሥመር ለማሥተካከልና የማሕበረሰቡን፣ የተሳፋሪውንና የአሽከርካሪዎችን ችግር ለመፍታት ይቻል ዘንድ ተቋማችን ፩ኛ ኮር በዝግጅት ላይ ያለ ሲሆን የችግሩ ሰለባ አካላት አካባቢውን ከወሮበሎች ነጻ ለማድረግ በቅርብ ቀናት የሚዘርፉ፣ የሚያግቱና የሚገድሉ ወዶ ገብ የብልጽግና ቅልብተኞች ላይ ርምጃ እንወስዳለን። ከመቼ እሥከመቼ የሚለውን በቀጣይ ቀናት ወይንም ከሰዓታት በኋላ በመግለጫችን  የምናሳውቅ ይሆናል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊ አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ 🔐 ፩ኛ ኮር🔐 ምሥል፦ በጨካኞች የተገደለችው እሕት ወ/ሮ አበበች ወንድይፍራው Hakealew Alebachew