ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 393
المشتركون
+724 ساعات
+2667 أيام
+1 44330 أيام
أرشيف المشاركات
ትግል የምትታገለው ብቻ ሳይሆን የምትጠብቀውም ነው!!
ከሰሞኑ ሰንፈጥ ያለ የማጥራት ስራ በመጀመራችን ሀቀኛ ታጋይና ህዝቡ በደስታ እየደገፈን ነው።
በአንፃሩ ወመኔዎችና ቀላዎጭ ሾተላዮች እየለየላቸው ነው።ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል በአጭር ጊዜ ታጥበን ተለቃልቀን የህዝብ ሮሮ የማይደመጥበት ሁነት እንፈጥራለን።
በተጀመረው ጥልቀት ያለው ምርመራና ጠንከር ያለ ርምጃ የነጋበት ጅብ በቀኝ በግራ እየተራወጠ ቀድሞ ባዘጋጀው ጎሬ ዘሎ እየገባ ነው።
ጥልቅ የማጥራት ርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል።ህዝብን የሚያማርሩ የትግላችን ጥገኞች መመንጠር በመጀመራቸው በአንዳንድ አካባቢዎች አንፃራዊ አዎንታዊ ለውጦች ተስተውለዋል።
ጥልቅ እርምቱ የህዝብ ቅሬታ ከመፍታትና የውስጥ ንፅህናን ከማስጠበቅ በላይ ትግልን በመጠበቅ በኩል ሁነኛ ፋይዳ ያለው መሆኑ ታምኖበት እየተከወነ ነው።ተጠናክሮም ይቀጥላል።
ከጥገኞች ጋር የዓላማ ትስስር ያላቸው ሁሉ ሳይጠሩ አለን ብለው ሲመጡ ይስተዋላል።ይህ የተንኮል ትስስር በጣጥሰን አሽቀንጥረን ከመጣል የሚገታን አንዳች ምድራዊ ኃይል ግን የለም።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
+1
ዛሬ በቀን 21/03/2018 ዓ/ም በሰከላ ወረዳ በብልፅግና ሠራዊት ንፁሃን ላይ ያነጣጠረ የተፈፀመውን ዘግናኝ እና ኢ - ሰብዓዊ ድርጊት ያወገዘ የተቃውሞ ሠልፍ ተከናውኗል።
"የአማራ ትንሳኤ በአንድነታችን እውን ይሆናል"!!
...የተፍረከረከው የጠላት ኃይል በተባበረ ክንዳችን ድባቅ ይመታል። አማራ እና አማራነት የኢትዮጲያ ምሰሶ ይሆናል።ይሄን ለማሳካት የሁላችንንም በጎ ተሳትፎ ይጠይቃል። አንድነት ስለጠየቅን ብቻ የሚሰጠን ሳይሆን በጥረታችን እና ለአንድነት የሚደረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴም ይፈልጋል።
አንድነትን መጠየቅ ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ፣አርበኛ አስረስማረ ዳምጤ መሪዎቻችን እንደሆኑ ሁሉ ዋርካው ምሬ ወዳጆ፣ አርበኛ ሔኖክ አድሴ እና ሌሎች የሚኒልክ ዕዝ አመራሮች፣ አርበኛ ደሳለኝ ፣አርበኛ ባዩ አለባቸው እና ሌሎች የአሳምነው ዕዝ አመራሮች ፣አርበኛ ሀብቴ ወልዴ፣አርበኛ ሳሙኤል ባለድል እና ሌሎች የበላይ ዕዝ አመራሮች ፣አርበኛ ንጉሴ ዋለልኝ ፣ሻለቃ ክንዱ እና ሌሎች የቢዛሞ ዕዝ አመራሮችም መሪዎቻችን መሆናቸውን ከማመን ይጀምራል!!
አማራ አንድ ድርጅት አንድ መሪ ያስፈልገዋል ስንል አርበኛ መከታው ማሞ፣ አርበኛ ደረጀ በላይ ፣አርበኛ ጌታ አስራደ እና ሌሎች የአፋኃድ መሪዎችንም አማራነታቸውን እና የድርጅታችን አካል እንደሚሆኑ አምኖ መቀበል ግድ ይላል። ያ ማለት ከፀረ አንድነት ተግባር መቆጠብ ማለት ነው። ይሄን ስናደርግ ቀሪው ሁለት(2)ቡድን ብቻ ይቀራል ማለት ነው።እነሱም:-
▶️ ልዩነታችንን የራሳችን ማጥፊያ መሳሪያ ያደረገው ብልፅግና እና የብልፅግና ሳይበር ሚሊሻ
▶️ የሰፈር ተንደባላዩ ተክለ ብአዴን እና አቅመቢስ ጎጠኛ።
ማሳሰቢያ:- አማራ እና የአማራ ፋኖ ወደ አንድ እየመጣ በሄደ ቁጥር የብልፅግና የሳይበር ሚሊሻ እና ጎጠኛው ቡድን ድምበር የለሽ ግንኙነት ፈጥረው አዲስ የመነጣጠል ዘመቻዎች ይጀምራሉ። ሀሰተኛ ፌክ Fb አካውንት በመክፈት የመሪዎችን ስም ማጥፋት፣ የስልክ ቅጅዎችን አስመስሎ አየር ላይ ማዋል እና ህዝብን ውዥምብር ውስጥ የሚከቱ አጀንዳዎችን በተናበበ ሁኔታ ይለቃሉ። ይሄን ሁኔታ ቀድመን በመረዳት የጠላት እቅድ ተባባሪ ባለመሆን መተባበር ተገቢ ነው።
አማራ ያሸንፋል !!
ትግል የምትታገለው ብቻ ሳይሆን የምትጠብቀውም ነው!!
ከሰሞኑ ሰንፈጥ ያለ የማጥራት ስራ በመጀመራችን ሀቀኛ ታጋይና ህዝቡ በደስታ እየደገፈን ነው።
በአንፃሩ ወመኔዎችና ቀላዎጭ ሾተላዮች እየለየላቸው ነው።ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል በአጭር ጊዜ ታጥበን ተለቃልቀን የህዝብ ሮሮ የማይደመጥበት ሁነት እንፈጥራለን።
በተጀመረው ጥልቀት ያለው ምርመራና ጠንከር ያለ ርምጃ የነጋበት ጅብ በቀኝ በግራ እየተራወጠ ቀድሞ ባዘጋጀው ጎሬ ዘሎ እየገባ ነው።
ጥልቅ የማጥራት ርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል።ህዝብን የሚያማርሩ የትግላችን ጥገኞች መመንጠር በመጀመራችን በአንዳንድ አካባቢዎች አንፃራዊ አዎንታዊ ለውጦች ተስተውለዋል።
ጥልቅ እርምቱ የህዝብ ቅሬታ ከመፍታትና የውስጥ ንፅህናን ከማስጠበቅ በላይ ትግልን በመጠበቅ በኩል ሁነኛ ፋይዳ ያለው መሆኑ ታምኖበት እየተከወነ ነው።ተጠናክሮም ይቀጥላል።
ከጥገኞች ጋር የዓላማ ትስስር ያላቸው ሁሉ ሳይጠሩ አለን ብለው ሲመጡ ይስተዋላል።ይህ የተንኮል ትስስር በጣጥሰን አሽቀንጥረን ከመጣል የሚገታን አንዳች ምድራዊ ኃይል ግን የለም።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
የብልፅግና ቅልብተኞች በያቅጣጫው መለፍለፋቸውን እና ማምታታቸውን ቀጥለዋል!!
እኛ ደግሞ እውነቱን እስክታወጡ ድረስ አንፋታችሁም አፋጠን እንጠይቃችኋለን!?
ለምን እና እንዴት የብልፅግናን ተላላኪ ጆሮ እና እጅ የቆረጠ ሰው ለጠላቱ ብልፅና ወዶ እና ፈቅዶ እጁን ሰጠ???
ምንስ ለማግኜት ነው??
+1
ተልዕኮ በመውሰድ ወደ ጠላት ቤት ተቀላቅሎ የነበረው ፋኖ ሁለቱን የብልጽግና ሚሊሻ አመራሮችን በማስወገድ ተመለሰ!
ፋኖ ተስፋው ይባላል። አስቀድሞ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ አባል የነበረ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ተልዕኮን በመቀበል ወደ ብልጽግናው ቤት ጎራ ብሎ በመቀላቀልና በመመሳሰል አስፈላጊውን መረጃ ለወገን (ለፋኖ) ሲሰጥ ከቆየ በኋላና ሌሎችንም ተልዕኮዎች ሲፈጽም ከቆየ በኋላ በመጨረሻ አንድ የሚሊሻ ጠርናፊና አንድ ሻምበል መሪን ካስወገደ በኋላ ግዳጁን በመወጣት ወደ 14ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ተቀላቅላል።
በተያያዘ ዜና ወርቁ አወቀ የተባለው የመከላከያ ተብየ አባል ከ32ኛ ክፍለ ጦር ወደ በረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።
ህዳር 21/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ ፋኖ!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
+1
ከአገዛዙ በተሰጣቸዉ ተልዕኮ መሠረት በእገታና ዝርፊያ ድርጊት ላይ ተሰማርተው የነበሩ የአድማ ብተና አባላት በፋኖ ቁጥጥር ስር ዋሉ!
በፋኖ ቁጥጥር ስር የዋሉት የአድማ ብተና አባላቱ፣ በፋኖ ስም ዝርፊያና እገታ ፣እንዲሁም አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ወንጀሎችን እንዲፈፅሙ ከአገዛዙ ተልዕኮ ተቀብለዉ በየአካባቢዉ መሰራጨታቸዉን ገልፀዋል።
ፋኖ፣የትግሉን ገፅታ ለማበላሸት እንዲሁም በፋኖና በህዝቡ መካከል ቅሬታና ጥርጣሬን ለመፍጠር ከብልፅግና ተልዕኮ ተቀብለዉ በእንደዚህ አይነት እኩይ ድርጊት ተሰማርተው በሚገኙ ወንጀለኞች ላይ ከወትሮዉ በተለየ ሁኔታ ጥብቅ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን መረብ ሚድያ ለማረጋገጥ ችሏል።
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር
በጀነራል ተፈራ ማሞ የተሰየመችው ብርጌድ ሻለቃ አንድን (መብረቁ እየተባለች የምትጠራውን እንደስሟ መብረቅ የሆነችውን ሻለቃ ) ለከተማ ኦፕሪሽን ሸማቂዎቹን በመላክ አስገራሚ ጀብድ ፈፀመች።
ቀን 22/03/2018 ዓ ም የብልፅግና የዕድሜ ማራዘሚያ እየተባሉ በህዝባቸው ላይ የመከራ ቀንበር እንዲሸከም የሚያረጉ ዙፋን ጠባቂ ሚሊሻዎች ውስጥ አምስቱ (5) የሚሆኑት በመብረቁ ሻለቃ ሸማቂዎች ወደ ፈጣሪያቸው የተሸኙ ሲሆን ሶስት የሚሆኑት ደሞ በህክምና ላይ ነፍስ ውጭ ነፍስ ጊቢ ላይ እንደሚገኙ በውስጥ መረጃችን ማረጋገጥ ችለናል።
ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ኦፕሪሽን የተደረገው በአረርቲ ከተማ በቀን 19/03/2018 ዓ ም ከምሽቱ 1:45 አካባቢ ላይ መጠጥ ቤቶችን ለማዘጋት ሲንቀሳቀሱ እንደሆነ ሸማቂዎቹ ለሚዲያችን አስታውቀዋል።
ድል ለአፋብኃ
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት
ለበልባል ክፍለ ጦር ሚዲያ ክፍል
ህዳር 20/03/2018
