ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 256
المشتركون
-824 ساعات
+887 أيام
+1 19430 أيام
أرشيف المشاركات
#እማ❤
ዉለታሽ ብዙ ነዉ _ለአንቺ ቃላት የለም
እናት መመኪያ ነሽ_ ኑሪ ለዘላለም!
ለልጆችስ ስትይ_ መከራን የገፋሽ
የማታማርሪ_ቸግሮ ቢከፋሽ!
አርሰሽ እና አርመሽ_ አጭደሽ አሂደሽ
ልጅሽን በማዘል_ ከወንድ እኩል በረሽ!
ምን ቃላት ይገኛል_ እናትን መግለጫ
ምስጋና ማይበቃት_ በቃላቶች ምርጯ!
እናም ዉለታሽን_ ከፍሎ ሚጨርሰዉ
በዚህ ዓለም ሲኖር_ስለማይገኝ ሰዉ!
እድሜሽን ያርዝመዉ_ እንደ ማቱ ዛላ
የማትጠገቢዉ_ ማር እና ወለላ❤👏!!
AAki Man Z Menz
የምንፈልገዉን ትተን መሆን ያለበትን ነገር ማድረግ ብንችል ዋጋ አንከፍልም እኔ መሪ ልሆን ወደዚህ ትግል አልገባሁም ስለዚህም መክፈል ያለብንን ነገር ለመክፈል ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል ። እስኪ ግላዊዉ ነገር ይቅርብን ጥያቄያችን የህዝብ ጥያቄ ነዉ ለሁሉ ነገር እንቅፋት መሆን አስቸጋሪ ችግር ነዉ ።
©አርበኛ ሳሙኤል ባልዕድል
የሁለት ወረዳ አመራሮች ላይ ጥቃት ተፈፀመ! በጥቃቱ አጃቢዎቻቸው ሲገደሉ አመራሮች ክፉኛ ቆስለዋል::
በትናንት በስቲያው የገነቴ ከተማ አቅራቢያ የደፈጣ ጥቃት የብልጽግና ቁልፍ አመራሮች መመታታቸው ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጤና ተቋም ከተገኘ ምንጭ ማረጋገጥ ተችሏል::
ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ወደ ወግዲ እና መካነሰላም አቅጣጫ ሲጓዙ በነበሩ የወረዳ አመራሮች ላይ ከትናንት በስቲያ ማለትም ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በርካታ ጠላት ተመቷል:: የቦረና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገበያው በቀለ ጭንቅላቱ ላይ ክፉኛ መቁሰሉ የታወቀ ሲሆን የቦረና ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው ስዩም ጭምር ወገቡ ላይ ከባድ ጉዳት እንዳስተናገደ ተረጋግጧል:: የወረዳው ብልጽግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሮህማን ደረሰ ደግሞ የግለሰብ ቤት ውስጥ ገብቶ ተደብቆ ሊተርፍ ችሏል::
ከዚህ በተጨማሪ የወግድ ወረዳ የብልጽግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሀመድ ግዛውም መቁሰሉ ታውቋል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይመር ሁሴን ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል:: በኮሎኔል ጠጁ ሙላቴ የሚመራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር እና አድማ ብተና ከሰላም አስከባሪዎች ጋር በመሆን የእጀባ ስራ እሰራለሁ ብሎ ዙሪያውን ቢያንዣብብም እንኳን የወረዳ አመራሮችን ሊያተርፍ ራሱ የጥይት እራት ሆኗል::
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ (ሸዋንግዛው ካሣ) ሻለቃ ፋኖዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 33 የጠላት ኃይል ያቆሰሉ ሲሆን 13 ጠላት ደምስሰዋል:: በሰሞኑ ውጊያ ተተኳሽ እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ወደ ፋኖ ገቢ ሆኗል::
የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ አለልኝ ተሰማ የወረዳ አመራር መምታት ኮሎኔል ከመደምሰስ ጋር እኩል ነው ምክንያቱም ዋና አስገዳዮቻችን የወረዳ አመራሮች ናቸው ያለ ሲሆን በአመራሮች ላይ የምንወስደው እርምጃ ወደፊትም የሚቀጥል ይሆናል ብሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
#ጥብቅ_ጥንቃቄ‼️
በምስራቅ ጎጃም እነማይ ወረዳ ዲማ፣ ቅድስጌ እንዲሁም ሸበል በረንታ ወረዳ ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ @የድሮን_ቅኝት ተካሂዷል። መረጃውን ሸር በማድረግ ለፋኖ አመራር እና አባላት እንዲሁም ህዝባችን ጥብቅ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።
ማሳሰቢያ:-
ሰራዊታችን አባላት እና አመራር በሙሉ ከሁለት እና ከዛ በላይ ሆኖ በት/ት ተቋማት፣ የምግብና ቦታዎች እና ስጋት ባሉ ቦታዎች ላይ ላይ ሁለት እና ከዛ በላይ ተሰብስቦ መቆም ይሁን መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም
የብአዴን አካድሚ ሃይሎች ገመና
በ Ashenafi Genan
................................................
የአማራን ህዝብ የተተወ ማህበረሰብ በማድረግ የህዝባችንን ሁለንተናዊ መብት እና ጥቅም አሳልፎ ሲሰጥ የነበረው ሃይል ዛሬም በትግላችን ውስጥ ሰርጎ በመግባት ፈተና ሆኖብን ቆይቷል!!
በተለይም አካባቢያዊነትን ለጥሬ ስልጣን ሲጠቀምበት የነበረው ቡድን ዛሬም እውነተኛ የህዝብ ልጆች የጀመርነውን ትግል ለማሳነስ እየሞከረ ይገኛል።
ከብአዴን አካዳሚ የተፈለፈሉት ነውረኞች የአማራን ህዝብ ትግል ለማነወር ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም!!
አማራነትን አብዝተው ይፀየፉታል!!
በአማራ ስም መነገድን እንጅ በአማራ ስም ዋጋ መክፈልን ይፈሩታል!!
ስብዕናቸው የደላላ እና ተጠቅሞ መጣል ነው።
በህዝብ ጥቅም ተደራዳሪ ነው!!
ነቀርሳው ቡድን በአማራ ህዝብ ስም ይምላል፣ይገዘታል ግን ምርኮኛ ነው!!
የአማራ ፓለቲካን ለስልጣን ማስጠበቂያ እንጅ ለህዝቡ መብት እና ጥቅም የሚቆጭ አይደለም!!
ራስ- ጠል እና ንቅል ሲሆን ስነ ልቦናው ደግሞ ተንበርካኪ ነው።
ተቸንካሪ እና ገባሪ ባህሪያቱ ደግሞ መገለጫዎቹ ናቸው!!
አማራነትን ለመናኛ ፍላጎታቸው ብቻ ይጠቀሙበታል!!
ብአደናዊነት በአካዳሚው የፈለፈላቸው አረሞች የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል መደበኛ ጠላት ናቸው!!
ብአዴናዊ አካዳሚ የፈለፈላቸው ሃይሎች መነሻቸው ጥቅም እና መዳረሻቸው ደግሞ አማቺዝም ፓለቲካን ለልዩ ጥቅም ማስከበሪያ አድርጎ መቀጠል ነው።
ከነቀርሳው ብአዴን አካዳሚ የተፈለፈለው ሃይል ማህበራዊ መሰረቱ የተዛባ፣የህዝብ ውግንና የሌለው፣ራስ ጠል እና ጥገኛ ቡድን ሲሆን በአማራ ህዝብ ጥቅም እና በስልጣን ህልውናው ላይ አይደራደርም!!
የአማራን ህዝብ ጥቅም ከ50 ዓመት በላይ አሳልፎ ሲሰጥ የነበረ ቡድን ሲሆን የፖለቲካ አስተምሮው ደግሞ ወደር የለሺ ተላላኪነት ነው።
ነቀርሳው ቡድን የአማራ ብሔርተኝነት የሚፈራ ስልጣኑን በአውራጃዊነት መንፈስ እና በቡድን ሲካፈል የኖረ ሲሆን በስሩ የፈጠራቸው ትላልቅ ተቋማትንና መዋቅሩን ደግሞ የህዝብ መምቻ ፣የትግል መቀልበሻ እና የህልውናው ማስቀጠያ አድርጓቸዋል።
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ህዝብ እና በልጆቹ ትግል የተጀመረውን አቢዮት ለመቀልበስ የባንዳ ምልክት ሆኖ እያገለገለ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በአካዳሚያቸው ያሳደጉት ማስረሻ ሰጤ እና መስፍን ከፈለኝ /በአማራ ህዝባዊ ድርጅት /ስም ተደራድረናል ሲሉ አድስ የተሸናፊነት ትርክት ለመፍጠር ሞክረዋል!!
በእርግጥ ማስረሻ ሰጤ እና ቡድን በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ምንም ተፅዕኖ የሌላቸው እንድሁም ህዝብን ለማደናገር ብቻ የሚጠቀሙበት መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
ህዝብ እውነታውን ያውቃል!!
የማስረሻ እና ቡድኑ ፍላጎት ተልከስካሺነት እና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብቻ እንደሚውል ግልፅ ነው!!
ስለሆነም የአዲሱ ትውልድ ትግል መነሻው እና መድረሻው የሚታወቅ ዓላማው ደግሞ የአማራ ህዝብ ከገጠመው ብሔራዊ የህልውና አደጋ እንዲወጣ እንጅ በምስለ አማራዎች ፍላጎት እና ይሁንታ የጀመረነው አብዮት እንደሌለ ይታወቃል!!
ትግላችን እና ዓላማው ከግለሰቦች በላይ ነው!!
ህዝባችንን ለረጅም ዘመናት በስርገት ሲፈትነው የነበረው አክሺክላ እና ተላላኪ ቡድን ተሸንፏል!!
በተላላኪነቱ የተሰጠውን አጀንዳም አክሺፈንበታል!!
ስለዚህ የአማራ ፋኖን የህልውና ትግል ርባና ቢስ ለማድረግ ላይ ታች የምትሉ የብአዴን አካዳሚ ሃይሎች ልታርፉ እና ልታፍሩ ይገባል!!
የአማራ ህዝብ እና የልጆች ትግል ያሸንፋል!!
የጥገኞች፣የተላላኪዎች እና የታካኪ ሃይሎች ፍላጎት አይሳካም!!
ደም የገበርንበትን ትግል ለበርባኖች አሳልፈን አንሰጥም!!
ትግላችን ከሎጥ ፓለቲካ ነፃ ነው።
የሰሞነኛው የእጅ ሰጡኝ ማደናገሪያ ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል የሚደረግ መፍጨርጨር ነው!!
ህዝባችን እውነታውን ያውቃል!!
የብልፅግና እጅ አስታጣቢዎች በየወረዳው አድስ የማጭበርበሪያ ካርድ አድርገው የያዙት የምርጫ ጉዳይም ፍሬ ቢስ ህልም መሆኑ የታወቀ ነገር ነው!!
በእርግጥ ብልፅግና በህይዎት ዘመኑ ከእውነት ጋር ታርቆ አያውቅም!!
በየሰፈሩ በአበል እና በኮንቴነር ወዶ የገባውን ገባሪ ቡድን በመጠቀም በፋኖ ስም ለመነገድ የተለመደ የብአዴን አካድሚዎች ፍሬ ነጭ ውሸት ነው!!
ትግላችን በየቀኑ እያደገ፣እየዘመነ እና ማህበራዊ መሰረቱን እያጠናከረ እንጅ በአሉታዊ ፕሮፓጋንዳ እና በሃሰተኞች ጩኸት ቢሆን እስከ አሁንም እንጠፋ ነበር!!
አሸንፍናቸው፣እንደ ዱቄት ተበትነዋል፣በየገዳሙ ናቸው ወዘተ ወዘተ የብልፅግና በሬ ወለደ ወሬ አያልቅባቸውም!!
ፋኖን ማጥፋት የሚቻል ቢሆን እስከ አሁንስ ምን እያደረጉ ነበር??
ምኞት አይከለከልም!!
ጥገኛው ልሂቅ የብአዴን የፋይናስ ተቋማት በሚወረውሩለት አበል ህዝቡን አብዝቶ የሚንቅ እና ምቾትን የሚወድ መሆኑ የታወቀ ነው።
ነገር ግን በአማራ ስም ማልቀስ፣መነፍረቅ፣ተበደልኩ፣ ተገፋሁ እያለ ሲያላዝን ደግሞ የጉድ ነው!!
በአማራ ህዝብ አንጡራ ሃብት ተምሮ በስልጣን ስም ከአገዛዙ ወንበር ስር ሲማቅቅ የሚውለውን ራስ-ከድ ልሂቅ በታሪክ እንፋረደዋለን!!
የአማራን ህዝብ ትግል በወደረኞች እና በቅጥረኛ ባንዳዎች ለመጥለፍ የሚደረገውን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት እያስተካከልነው ወደ ፊት የምንቀጥል ይሆናል!!
ትግላችን ውስጥ የነበሩ ረጃጅም እጆች መነሻቸው እና መድረሻቸውም ተለይቷል!! በዘላቂነት እጃቸውን ለመቁረጥ ጠንካራ ስራዎችንም እየሰራን እንገኛለን!!
መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል!!
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊
ዝንተ ዓለም ዓምሐራ🔐
ወይራው አማራ
+1
በስሩ ያሉ ነፃ ቀጠናዎችን በስኬት አደራጅቶ መጨረሱን የአዮ ጓጉሳ ጊዜያዊ መንግስት አሳወቀ!
*//
የ88ኛ ክ/ጦር ከሚያተዳድራቸው ወረዳዎች ውስጥ አዮ ጓጉሳ አንዱ ነው። ወረዳው ትርፍ አምራች ብቻ ሳይሆን የበርካታ ጀግኖች መብቀያ ጭምር ነው። ከጠላት ጋር በተደረገ ትንቅንቅ ነፃ የወጡ ቀበሌዎቹን ለቀጣይ የአማራ ህዝብ ትግል ዝግጁ በሚያደርግ ሁኔታ እና እራሱን በራሱ ፖለቲካዊ ፣ማህበሳዊና መልካም አስተዳድራዊ መስተጋብሮቻቸውን የሚያሳልጡበትን የቀበሌና የንዑስ ቀበሌ አደረጃጅት ማደራጀታቸውን በፋኖ ደርጉ መንግስት የሚመራው የወረዳው አስዳድር ፅ/ቤት አሳወቋል።
🙏ክብር ለውጤቱ ለደከሙት!
አዲስ(ትውልድ ፣ አስተሳሰብ ፣ተስፋ)
+1
#መብረቁ የጠላት እራስ ምታት ሁኖ ቀጥሏል‼️
ከሰዴ ወረዳ በሌሊት በተለያዩ አቅጣጫ በመዉጣት ወደ አፍቀራ ቀበሌ ወጦ የነበረዉ የጠላት ሀይልን የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር እየቀጠቀጠ በመመለስ ቄሳጤ ማሪያም የምትባል ቦታ ላይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 7:00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ በማድረግ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ተችሏል በተደረገው ማጥቃት የጠላት ሀይል የመከላከያ አመራሮች ጨምሮ ከ11 በላይ አስክሬን መነሳቱን በርካታ ቁስለኛ ሲጎጎዝ እንደነበር ከአካባቢው ባሉ ነዋሪወች ማረጋገጥ ተችሏል።
የፋኖን ሀይልን መቋቋም ያቃተዉ የጠላት ሀይል ሰዴ ወረዳ ከተማ ላይ በመሆን የአዲስ አለም ቀበሌ የ1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ተቋምን በሞርተር በመደብደብ አዉድሟል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አስቸኳይ ‼️ከምሽቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ በሸዋ ቀጠና የምዕራብ ወሎ አዋሳኝ ቦታዎች የድሮ ቅኝት ተካሂዷል ጥንቃቄ ይደረግ!!
ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም
ዘራይና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦሮች በዳባት ውጊያ ድል ቀንቷቸዋል!!
🔸የደጃዝማች 4ኛ ኮር ዘራይ ክፍለጦር ሸጋው ውበት ብርጌድ
ከዳባት ከተማ በስተ ምስራቅ በኩል ቃርሃ ቀበሌ የመጣ የብልፅግና ወራሪ ቡድን በጀግናው የፋኖ ሰራዊት ወደመጣበት ተመልሷል።
የዘራይ ክ/ጦር ሸጋው ውበት ብርጌድ ከፊሉን ጠላት ቆርጦ በማስቀረት የድምሰሳ የተሳካ ውጊያ አድርገዋል።በርካታ የብርሃኑ ጁላ ግብስብስ ሰራዊት ተደምስሷል ቀሪውም ቆስሏል የቀረው ወደ ዳባትና ወቅን ከተሞች እግሬ አውጭኝ ሩጠው ሸሽተዋል።
🔸በዳባት አቅራቢያ ውጊያ በሌላኛው የመሬት ገፅ በመጠጋት ውጊያ በመክፈት ስልታዊ ወታደራዊ ድጋፍ ያደረገው የዳ/ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ይታየው ብርጌድ ሲሆን በዚህ ግንባርም ለጊዜው በአሃዝ ያልተረጋገጠ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
ሞት አይፈሬው 206ኛ ኮር ከጠላት ጉሮሮ 27 ክላሽ ማርኳል"
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ሞት አይፈሬው 206ኛ ኮር በተለያዩ ግንባሮች በዛሬው ዕለት ባደረገው ተጋድሎ እጅግ አስደናቂ በሆነ ትንቅንቅ ከጠላት ጉሮሮ 27 ክላሽ ማ*ር*ኳል።
በራሱ ፍላጎት እየተክለፈለፈ ከአምበር ከተማ በመነሳት ወደ ጃማ ከተማ በማቅናት ጥቃት ለማድረስ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስና ደጃች ተድላ ጓሉ ሻለቃ በፈፀሙት የማ*ጥ*ቃት ው*ጊ*ያ ጠ-ላ-ትን ከምድር ደባልቀው 27 ክላሽ ፣በርካታ ካዘና፣የደረት ትጥቅና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁስ ማ-ር-ከ-ዋል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀትር 6:00 ስዓት በወሰደው ጠንካራ ውጊያ ጠላትን ያጋደሙት የ206ኛ ኮር አሃዶች 45 በላይ ጠላት የደ-መ-ሰ-ሱ ሲሆን ከ22 በላይ የጠላት ኃይል ከባድ ቁ-ስ-ለ-ኛ ሁነዋል።
የአረ-መ-ኔ-ው ሰራዊት፣አድማ ብተና እና ሚኒሻ በታ-ጨ-ደ-በት ውጊያ ጠላትን ቅስም በመስበር አስደናቂ ጀብድ የፈፀመው 34ኛ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ድል ያስመዘገበ ጠንካራ ክ/ጦር ሲሆን በዚህ ስዓት 15 የጠ-ላ-ት ከባድ ቁ-ስ-ለ-ኞች በጫካ ወድቀው እንደሚገኙ ታውቋል።
በተያያዘ ውጊያ 206ኛ ኮር የ14 ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ከሻለቆች ጋር በመቀናጀት ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ማርዘነብ ከተማ ላይ በደረሰው የጠላት ኃይል ላይ በፈፀሙት ፈጣን ማጥቃት ተመሳሳይ ድል የተገኘ ሲሆን የአረመኔው ሰራዊት ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዶ 23 አ-ስ-ክ-ሬን ተሸክሞ ተመልሷል።
አዲስ ትውልድ !አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ዘራይና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦሮች በዳባት ውጊያ ድል ቀንቷቸዋል!!
🔸የደጃዝማች 4ኛ ኮር ዘራይ ክፍለጦር ሸጋው ውበት ብርጌድ
ከዳባት ከተማ በስተ ምስራቅ በኩል ቃርሃ ቀበሌ የመጣ የብልፅግና ወራሪ ቡድን በጀግናው የፋኖ ሰራዊት ወደመጣበት ተመልሷል።
የዘራይ ክ/ጦር ሸጋው ውበት ብርጌድ ከፊሉን ጠላት ቆርጦ በማስቀረት የድምሰሳ የተሳካ ውጊያ አድርገዋል።በርካታ የብርሃኑ ጁላ ግብስብስ ሰራዊት ተደምስሷል ቀሪውም ቆስሏል የቀረው ወደ ዳባትና ወቅን ከተሞች እግሬ አውጭኝ ሩጠው ሸሽተዋል።
🔸በዳባት አቅራቢያ ውጊያ በሌላኛው የመሬት ገፅ በመጠጋት ውጊያ በመክፈት ስልታዊ ወታደራዊ ድጋፍ ያደረገው የዳ/ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ይታየው ብርጌድ ሲሆን በዚህ ግንባርም ለጊዜው በአሃዝ ያልተረጋገጠ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
በዛሬው እለት የተሰሩ ጀብዶች
#በሉማሜ_ከተማ_ብቻ_18_ሚኒሻዎች_ተቀበሩ‼️
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
ልጆቻችሁን አምጡ እነሱ ካልመጡ እናተን ጥቁር ልብስ እንኳ አናስለብሳችሁም እያለ ሲደነፋ የነበረው የአረመኔው ሰራዊት በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 አስክሬን በሉማሜ ከተማ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ/ክርስቲያን ቀብሯል።
#በአምበር_ወጀል_ሉማሜ_የተቋቋመው_አስለቃሽ ኮሚቴ ከተሞችን በተኩስ እያናወጠ ፊቱን ሲነጭ፣በሉማሜ ፣አምበር ከተሞች ባሉ የጤና ተቋማት የተዘረጉ ከባድ ቁስለኞች ከጣረ ሞት ጋር በሚያደርጉት ግብግብ ጩኸታቸው አድማስ ተሻግሮ ይሰማል።
እነዚህ እንከፎች በአንድ ጉድጓድ የተቀበሩ ሚኒሻዎች መካከል ሲሆኑ፦
1.ሀይማኖት ሙንየ ---- እነቢ ጭፋር
2.ደራጅ ሺፈረው ---- ወጀል
3.ወድምነህ ጫኔ ------ የዳበና
4.አስጨንቅ ባድማው ----የዳበና
5.ዋልቴ መሠረት ------- ዝንዳ
6.አበዋ ሞስነህ -------- ፅ/ማሪያም
7.በቃሉ እውነቱ -------- የደዋራች,
8.አዱኛው መጌ ---------- ፅ/ማሪያም
9.አሻግሬ/ዘንጉ/ --------- ፅ/ማሪያም
10.ደመላሽ ሙላት -------- ሉማሜ
11.መብት ----------- ሉማሜ
12.ደሴ አላምር --------- ሉማሜ
13.ናቄ አባተ --------------- ሉማሜ
14.ሞላ መቅጫ ------------- ከ ሉማሜ ይገኙበታል።
እስከ አሁን ከሆስፒታል በወረፋ እየወጡ ያሉ ሟቾች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ አሰክሬን አከፋፋይ ኮሚቴው ስራ በዝቶበት አምሽቷል ።
አንድነት ሀይል ነው
የኮረኔል ፈንታውን ኮቴ ሲያፈነፍን የነበረው የብልጽግና ወታደር ትናንት በወንዶች ጎዳና ከኮረኔል ፈንታው ሀይል ጋር ፊትለፊት ተገናኙ አዎ የሆነው እንደነገርኳችሁ ነው
የኮረኔል ልጆች ቅጽበታዊ ውሳኔ ወሰኑ ምክንያቱም ሁሌም ለምንም ነገር ቀድመው የተዘጋጁ ናቸውና
በወራሪው ሀይል በኩል ግን ፋኖን ያህል እዳ በዚህ ቅጽበት ከፊትለፊታቸን እናገኛለን ብለው አልጠበቁም ቢገናኙም በዚህ ፍጥነት አደጋ ይጥላሉ ብለው አልገመቱም
ለብልጽግና ወራሪ ሀይል ያቺ ቅጽበት ሲኦል ሆነችባቸው የተኩስ እሩምታ በባንዳ ላይ ዘነበ ከጀርባ የድርሳን ልጆች በመምጣት የኮረኔልን ሀይል ተቀላቀሉ አንድነት እና ጀግንነት ተደማምረው ተአምር ተፈጠረ
በብልጽግና በኩል ትልልቅ ባንዳዎች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል ከኋላ የደረሰው የፋኖ ሀይል ደሞ የማረካቸው አሉ በቅርቡ ይገለጻል
ይሄው ነው
አማራነት ያሸንፋል ❗️
#እናመሰግናለን!!!
ለአዲስ ቅዳም ከተማ እና አካባቢው ኗሪ የተላለፈ የምስጋና መልዕክት!!!
ትላንት ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም ፀረ አማራዉ የብልፅግና ስብስብ አዲስ ቅዳም ከተማ ላይ ጠርቶት በነበረዉ ህዝባዊ መድረክ ላለመሳተፍ ቤት ዘግታችሁ ሀገር ለቃችሁ ለነበራችሁ ወገኖቻችን በሙሉ የአፋብኃ ቴዎድሮስ /እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር እዉቅና እና ምስጋና ይሰጣል።
ይህ ትላንት ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም የተከበረው ህዝባችን በፀረ አማራዎች ጉባኤ ላለመካፈል ያደረገዉ የተቃዉሞ አይነት ሙቶ የበሰበሰዉ የብልፅግና ስርዓት ህሌናቸዉን ለሆዳቸዉ ካስረከቡ ዉስን የካድሬ ቤተሰቦች በስተቀር ለመላዉ ህዝባችን አፍንጫ ከመጥፎ ሽታ በላይ መከርፋቱን ያስመሰከረ ተግባር ከመሆኑም በተጨማሪ ከተማ እና ከተማ አካባቢ የሚኖረዉ ህዝባችን በአብዬዎቱ ዉስጥ የነበረዉን የቀደመ የትግል ሚና ከጀርባ አጥንትነት ወደ ታጋይ አታጋይነት ምዕራፍ ማሸጋገሩን በተግባር ያየንበት ሁኖ አጊንተነዋል።
በመሆኑም ነፃነት ወዳዱ የተከበርከዉ ህዝባችን በሰራኸዉ አኩሪ ተግባር እኛ ልጆችህ እጅግ በጣም መኩራታችንን እና መተማመናችንን አየገለፅነ ለቀጣይም ይህንን ፀረ አማራ የሆነ የብልፅግና ቡድን ከዚህ በከፋ ሁኔታ አምርራችሁ በመቃዎም ግባተ መሬቱ እንዲፋጠን የሚያደርግ የተለመደ ስራችሁን እንድትሰሩ አደራ በማለት ለዛሬ ተግባራችሁ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ ብለናል። በድል እንገናኝ!!!
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ🙏
የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር
ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም
መረጃ ‼️
ከመሼ በቤተል በቀራንዮ መድኃኔዓለም አድርጎ በበርካታ ቅጥቅጥ የተጫነ ወራሪ ወደ አማራ ክልል ሲያመራ ስለታየ ወደ ሽዋና ወደ ጎጃም የሚያስገቡ መንገዶች በደፈጣ ይጠበቁ!!
ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም
#የድሀ_ኢትዮጵያን_ልጆች_በሜዳ_ቀርተዋል‼️
"እዛው ጠዶት ሚካኤል ግንባር ላይ ነን!
ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶዎቹ የእግር መረገጫ እስኪጠፋ ድረስ ምሽጉን በጠላት አስከሬን ሞልተውታል።"
#ሀገር_ለማፍረስና_ለአብይ_አህመድ_የተከፈለ_ዋጋ‼️
14/ዐ4/2018 ዓ.ም
