ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 349
المشتركون
+17324 ساعات
+2467 أيام
+1 36830 أيام
أرشيف المشاركات
ቀን 05/04/2018ዓ/ም የጥንቃቄ መልዕክት  ለዋድ እና አንጀኔ ማሕበረሰብ  እና  ወጣቶች በሙሉ ከቀን 12/03/2018ዓ/ም ጀምሮ እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው አብይ መራሹ ጨፍጫፊ ቡድን በአንጀኔ ቀጠና እና በዋድ አዲስ አለም ንዑሰ ወረዳ መጠነ ሰፊ ወረራ እና ንፁኃንን ማሳደድ የዕለት ከዕለት ተግባሩ አድርጎት ይገኛል ። አሁን ደግሞ ለእኩይ ተግባሩ ማስፈፀሚያ  ወጣቶችን ለማፈንና ወዶ ገብ ዘማች ለመመልመል  በሚል እንቅስቃሴ  ላይ እንዳለ ደርሰንበታል። የስለሆነም የዋድ አዲስ ዓለም እና የአካባቢው ወጣቶች እንዲሁም የአንጀኔ እና የአካባቢው ወጣቶች ይህ ሰው በላ መንግስት ለእኩይ አላማው ማስፈፀሚያ እንዳያደርጋችሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስንል ማሳሰብ እንወዳለን።ይህ ሰው በላ አገዛዝ  አላማው አንድ እና አንድ ነው እሱም አማራን እርስ በዕርሱ ማፋጀት !!! #መረጃው የ99ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

እሸት ክፍለ ጦር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደች። አፋብሃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር የብርሃኑ ጁላ ግትልትል ሰራዊት ላይ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዉበታል። መነሻዉን ከታሪካዊቷ ቦታ ላሊበላ ከተማ እና ላሊበላ ኤሪፖርት(ሽምሽሃ)  አድርጎ  እሸት ክፍለ ጦርን አፍናለሁ በሚል አጎል ምኞት አዳሩን በአምስት አቅጣጫ ማለትም በ ሙጫ በረት፣በአቢሰግ ኪዳነ ምህረት  ፣ በእርፋ ፣ ተካይ መንደር ፣  በታሎ ደብር አስፍቶ ቢመጣም  በነበልባሎቹ እሸት ክፍለ ጦር  ተገርፎ አስክሬኑን እንኳን ሳያነሳ ወደ መጣበት ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ) እና ላሊበላ ከተማ ፈርጥጦ ተመልሷል። ዉጊያዉም ዛሬ ማለትም ቀን 5/2018 ዓ.ም  ከለሊቱ 11 - 8 ስዓት በፈጀዉ  ትንቅንቅም  ከ 15 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ 20 በላይ ቁስለኛ ማድርግ ተችሏል። በመጨርሻም የአገዛዙ ሰራዊት አባላት አብይ አህመድ ለራሱ ወንበር አስጠባቂ አድርጎ ዉድ ህይወታቹህን እየነጠቃቹህ መሆኑን  አዉቃቹህ  ወደ  አማራ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ሲሉ  የእሸት ክ/ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ አያናዉ እንየዉ እና ምክትል አዛዡ አርበኛ ፍቃድ አበባዉ መልዕክት አስተላልፈዋል። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ  ፋኖ ደረበ መኮንን!! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ!! ታህሳስ 5/4/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!         ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም የአገዛዙ 48ኛ ክፍለ ጦር በአንጎት ወረዳ ጉዳት አስተናገደ! ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት በአንጎት ወረዳ ዋና ከተማ አሁንተገኝ ከተማ በጥራሪ ክፍለ ጦር ኤፍሬም ሻለቃና ያሬድ ሻለቃ በተውጣጡ የፋኖ ሰራዊቶችና በተከዜ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ የተወሰኑ የፋኖ አባላቶች በመጣመር በሌሊት በተደረገ ሰርጂካል ኦፕሬሽን በ48ኛ ክፍለ ጦር የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት ላይ በተከፈተ ተኩስ ከአስር በላይ አባላቶቹ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው ማረጋገጥ ተችሏል። በነበረው አውደ ውጊያ መገናኛ የያዘን የአገዛዙ ሰራዊትን ጨምሮ ስድስቱ ህይወታቸው ሲያልፍ አራቱ ቆስለዋል። በተጨማሪም የአገዛዙ ሰራዊት ሰሞኑን ጥራሪ ክፍለ ጦርና ተከዜ ክፍለ ጦር በሚገኙበት አካባቢ  ከፍተኛ ሰራዊት በማሰማራት ከሙጃ ኩልመስክ ጠፈላማይ ሙቅውሀ እና ከወንዳች ይባር እንጃፋት የሸፈነ ከፍተኛ ወረራ በማካሔድ በከባድ መሳሪያ መለየ መገንጠያ አካበቢ አንዲት የሴት አዛውንት በዙ-23 የገደለ ሲሆን ለአማራው ማህበረሰብ ደንታ የሌለው የብልፅግና ሰራዊት በአማራው ላይ የኢኮኖሚ ኪሳራ እንዲደርስበት በማሰብ እንስሳትን በመጨፍጨፍ ቤትን በማቃጠል የጥላቻ ጥጉን ያሳየበትን አካሔድ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ሀቅ ነው።ለዚህም እንጃፋት ዙሩያ የአርሶ አደር ሳር ቤቶችን ያቃጠለ ሲሆን እንጃፋት ከተማ ላይም የፋኖ ቤተሰቦች ናችሁ በሚል ሴቶችንና ህፃናቶችን በመደብደብ በማንገላታት የጥላቻ በትሩን ማሳየት ችሏል። አገዛዙ ሽንፈቱ አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ያሳየበት አስፀያፊ ተግባር ስለሆነ ሁሉም የአማራ ህዝብ ይህን አማራዊ ጥላቻ ያለውን አገዛዝ ተረባርቦ በመታገል እድሜውን ከማሳጠር ውጭ አማራጭ የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ በቁርጠኝነት ፋኖን በመቀላቀል እየደረሰብን ያለውን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ሰብዓዊ ኪሳራ ማከም ያስፈልጋል። ያለ መስዋዕትነት ድል የለምና ማንኛውም የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በመታገል ከምን ጊዜውም በላይ አሁን አንድነት የሚያስፈልግበት ጊዜ ስለሆነ በአንድነት አምርረን ይህን ስርዓት መታገል እንዳለበት ጥራሪ ክፍለ ጦር ያሳስባል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል መረጃውን የጥራሪ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አድርሷል ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ታህሳስ 05 / 2018

''የታሪክ ተመራማሪው¡'' አባዱላ ግን ጤናውን ደህና ነው ወይ?😉 ገዢዎቹ የወሎን ህዝብ ''ቡልኻ/የሰጡትን ሳያላምጥ የሚውጥ ፣ የተወራለትን እንደወረደ የሚቀበል የዋህ ብቻ'' አድርገው የማሰባቸው ነገር በጣሙን ይበሰጨኛል። ይህ በረዥም አመታት የፖለቲካ ተሳትፎዬ የታዘብኩት ነገር ነው። የእኚያ የሴራ ጠበብቶቹን እንተወውና የአሁኖቹ ጨቅላዎች እንኳ ቀሽምና ተራ የፕሮፓጋንዳ ሀሳብ ፈጥረው ፣ በሙከራ ደረጃ ሊተገብሩ የሚመጡት ወደወሎ ነው። የዛሬ 5 አመት ገደማ ወረኢሉ አካባቢ የነዳጅ ክምችት መኖሩን የወቅቱ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የነበረው ኢ/ር ታከለ ኡማ በህዝብ ሚዲያ ሳይሆን በፌስቡክ ገፁ ገልፆ ነበር። በርግጥ ያለምንም ቁፋሮ ነዳጅ መኖሩን በአይን ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል። ይህ ከረዥም አመታት በፊት በቅርበት የምናውቀው እውነታ በመሆኑ ፣ መጠቀም ቢቻል ለህዝባችን የሚያቃልለውን ሸክም በማሰብ ጉዳዩን በተቻለን አቅም ለማጣራት ስንሞክር ፣ አንድ ድርጅት ለማጥናት ከሞከረ በኃላ ያለው የነዳጅ ክምችት ቆፍሮ ለመጠቀም ከሚወጣው ኢንቨስትመንት (ሀብት) ጋር የማይመጣጠን መሆኑን በመጠቆም እጢአችንን ዱብ አደረጉት። ከዚያም የታከለ ኡማ ፖስት የፈጠረው አጀንዳ ከወሬ ሳይሻገር በዚያው ተድበስብሶ ቀረ። በወቅቱ የታከለ ኡማን የፌስቡክ ፖስት አጀንዳ መደረጉን ተከትሎ አንዳንድ ግልቦች '' አብይን የሚቃወሙትኮ የወሎን ነዳጅ እንዳያወጣ ለማደናቀፍ ፈልገው ነው!'' የሚል አስቂኝ ፕሮፓጋንዳ ሲፅፉ አይቼ መሳቄንም መሳቀቄንም ፈፅሞ አልረሳውም። ሰሞኑን እንደአዲስ '' በወሎ ነዳጅ ተገኘ!'' የሚለው ዜና እንደትኩስ ድንች ሊላጥ የተፈለገበትንና ፣ የገንጣይ አስገንጣዩ ሀይል የማደጎ ልጅ የሆነው አባዱላ ገመዳ '' አሰብ የኤርትራ አካል ሆኖ አያውቅም። አሰብ የወሎ ክፍለ ሀገር አካል ነው!'' የሚል የተትረከረከ ታሪክ ይዞ ብቅ ካለበት አጀንዳ ጀርባ ያለውን የነማሞ ቂሎ ስሌት ለመረዳት ''ቡልኻ'' አለመሆን ብቻ በቂ ነው። ይህን ተከትሎ በጣም ካሳቁኝ ሰሞንኛ የፌስቡክ ፖስቶች መካከል ግን '' ነዳጁ ሳይወጣና አሰብም ወደወሎ ከመመለሷ በፊት ወሎን ክልል የማድረጉ ስራ መቅደም አለበት!'' የሚለውን ያህል ያሳቀኝ የለም! የነዳጁን ጉዳይ ላለፉት 7 አመታት '' ከነገ ጀምሮ ድፍድፍ ነዳጅ ወደውጭ መላክ እንጀምራለን'' ከሚለው ጀምሮ '' ኢትዮጵያ ከመስከረም ወር ጀምሮ የጋዝ ምርት ወደውጭ መላክ ትጀምራለች'' እስከሚለው የቅርቡ ድስኩር ድረስ ብዙ ስለሰማን በዝርዝር ማውራት አልፈልግም። በቅፅበት '' የታሪክ ተመራማሪነት'' ካባ ደርቦ ብቅ ያለው አባዱላ ገመዳ ግን '' አሰብ የወሎ ክፍለ ሀገር አካል እንጂ የኤርትራ ሆኖ አያውቅም!'' እያለ ሲደሰኩር ህዝቡ '' የምን አሰብን ነጥለህ ማውራት አመጣህ ? ኤርትራ ራሷ የኢትዮጵያ አካል ነበረችኮ!'' ብሎ የማይጠይቀው መስሎት ይሆንን ? '' አለቆችህ ከማራኪዎችህ ጋር ተደራድረው ያንን የጥቁር ቀን የገንጣይ አስገንጣይ ስምምነት ከተፈራረሙ በኃላ አሰብ የወሎ ክፍለሀገር ነበር ብለህ በአደባባይ እብደትህን እያረጋገጥክልን ነውን ?'' የሚል ተጠይቅ እንደሚነሳበትስ ጠፍቶት ነውን ? '' Reclaiming port Assab means reclaiming the 1993 referendum of Eritrea.'' መሆኑስ ተሰውሮበት ነውን ? ሁሉም አይደለም! ነገርግን ማህበረሰቡን በመናቅና ሞኝ አድርጎ በመቁጠር ፣ በቀሽም ፕሮፓጋንዳ ''እጥጥ ሙጥጥ'' ያለባቸውን ህዝባዊ ድጋፍ የመማተር ቅዥበራ ወይም ዝብረቃ ብቻ ነው! ዘሪሁን ገሠሠ

ሰበር ዜና የአርሶ አደር መሳሪያ እና ሀብት ለመዝረፍ የመጣው የአገዛዙ ቅልብ ሀይል በወገራ ወረዳ በጀጀህ ሀሙሲት ዙሪያ ተደመሰሰ።   የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር  አሀድ የሆኑት የጎንደሬ በጋሻው እና ታድሎ ብርሃን ክፍለ ጦር የተወጣጡ አባላት  ከአካባቢው የአርሶ አደር አደረጃጀት  ጋር በጥምረት ተህሳስ 4/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት ድረስ ለመግደልና ለመዝረፍ ከመጣው የአገዛዙ ተላላኪ  ሀይል  ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ በማድረግ   ተደምሷል ። ሰሞኑን ተስፋ የቆረጠው አገዛዙ  ሰራዊት  በወገራ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች  የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት በመዝረፍና በማቃጠል ለማስፈራራት  በጀጀህ ሀሙሲት  ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ሞት ወይም ነፃነት ያሉት አርሶ አደሮች ከዳግማዊ ቴውድሮስ (5ተኛ)ኮር  አካል ከሆኑት ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር   ቴውድሮስ ብርጌድ እና ከታድሎ ብርሃን ክፍለ ጦር  ጣሰው ብርጌድ  አባላት ጋር በመቀናጀት ለዝርፊያ የመጣውን የአገዛዙን ሀይል  አስከሬን ሰብሶቦ በለቅሶ እንዲመለስ  አድርገውታል ። በአውደ ውጊያው ከ17 በላይ የአገዛዙ ሀይል ሲደመሰስ ከ11 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ። አርሶ አደሮቹ ከእንግዲህ በህልውናችንና በሀብታችን ለመጣብን ዘራፊ ስርዓት የምንበረከክበት ሞራል የለነም በማለት ነፃነት ትግሉ ቆርጠው ተነስተዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )

''ኢትዮጵያ ትፈርሳለች እንጅ ስልጣን አንለቅም'' የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር በመድገም፣ በማሽሞንሞን እና ሽጉጤን እጠጣለሁ በማለት የሚታወቁት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ሰሞኑን ከፋና ብሮድካስት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አነጋጋሪ መልዕክት ሲናገሩ ተደምጠዋል። የሀገራችን ኢሊቶች የአማራም ሆነ የኦሮሞ፣ የትግራይም ሆነ ሌሎች ቁጭ ብሎ ለመነጋገር ቦታ ስጡ፤ ከዚያ ውጭ ግን ስልጣን በትጥቅ በክላሽ መቆጣጠር አይቻልም፤ ምን አልባት በግጭት ሀገሪቱን እናፈርሳት ካልሆነ በስተቀር ብለዋል። አክለውም ከ3 አመታት በፊት የትግራይ ህዝብ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው በማለት ህዝብ ላይ የጥላቻ መርዛቸውን በራጩበት አንደበታቸው መለስ ብላው ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ዛሬም ትላንትም ወደፊትም አብረው ናቸው፤ ''እንነጣጥላቸው ብንል ውሸት ነው'' በማለት ራሳቸውንም ውሸታም መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

#BCA መረጃ ከታች በፎቶ የሚታየው ግለሰብ ስሙ አቶ ታደሰ ገብረዮሐንስ ይባላል። ባሕርዳር ጊዮርጊስ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው ፋሚሊይ ፎቶ ቤት ባለቤት ነው። በግፍ እስረኛ በሆነው በተከበሩ አቶ ክ
#BCA መረጃ ከታች በፎቶ የሚታየው ግለሰብ ስሙ አቶ ታደሰ ገብረዮሐንስ ይባላል። ባሕርዳር ጊዮርጊስ አደባባይ ፊት ለፊት ያለው ፋሚሊይ ፎቶ ቤት ባለቤት ነው። በግፍ እስረኛ በሆነው  በተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ የሥርዓቱ የሃሰት ምስክር ሆኖ ለመመስከር የዝግጅት ሥልጠና ወስዶ ዝግጁ ሁኗል። መኖሪያ አድራሻ:- ➛ባሕርዳር ቀበሌ 14 አኮቴት አደባባይ አካባቢ ➛ መኪና ሰሌዳ ቁጥር    B-49808 ToccEN ➛ አብሮት የሚሰራው የጠበቃ ስም           -  ጠበቃ ግሩም አየለ ይባላል የሚገለገልባቸው ስልክ ቁጥሮች :- -0918760328 -0910599965 -0910945979 -0934587400 -0912906696 -0935982725 ናቸው። ይሄ የመጀመሪያ ደረጃ ማስጠንቀቂያ አይደለም። በወንድማችን ላይ የሃሰት ምስክርነት በመስጠት እኖራለሁ ተብሎ ታስቦ ከሆነ እናያለን።

ይህ ነው አማራነት ወንድ ሁሉ በኦሮሙማው መንግስት ወንበር ጠባቂ ሰራዊት እየተገረፈ አንገቱን አቀርቅሮ ከተማ በተቀመጠበት ሰዓት እነዚህ የሴት አርበኞች የዘመናችን ጣይቱዎች በጫካ በቂ የነፃነት ትንፋ
+1
ይህ ነው አማራነት ወንድ ሁሉ በኦሮሙማው መንግስት ወንበር ጠባቂ ሰራዊት እየተገረፈ አንገቱን አቀርቅሮ ከተማ በተቀመጠበት ሰዓት እነዚህ የሴት አርበኞች የዘመናችን ጣይቱዎች በጫካ በቂ የነፃነት ትንፋሽ ይተነፍሳሉ አንተስ አንችስ ምን እየሰራሽ ነው እየሰራህ ነው ከተማ የተቀመጣችሁ ወጣቶች ሳይረፍድብህ/ሽ ወደ የህዝብ ልጅ ፋኖ ተቀላቀሉ ።

ሀሰተኛ መረጃ ነው!! ሀጎስ የሚባል የፋኖ መሪ በጎንደር አይታወቅም!!      ባለፉት ዓመታት ልዩ ኃዬልን በማፍረስ ፋኖንና መላ አማራን ትጥቁን አይደለም ቀበቶውን እናስወልቀዋለን በሚል እብሪት አማራ ላይ ጦርነት የከፈተው ዓብይ አህመድ መራሹ ፋሽስት ቡድን ያልገመተውና ያልተነተነው አፀፋዊ ርምጃ ተወስዶበት እየፈራረሰ ይገኛል።    ነገሩ ወዲህ ነው በጠለምት፣ወልቃይት ጠገዴና አካባቢው በተለይም የተከዜ ተፋሰስ እና ዘሪማ ተፋሰስ የዓብይ ባለስልጣናትና የጦር መሪዎች ከነ ጌታቸው ረዳ ጋር የማዕድን ቁፋሮ ህገ ወጥ ኔትወርክ አላቸው። ታድያ የማዕድን ብዝበዛው ዝም ብሎ የሚሰራ ሳይሆን የጥቅም ኔትወርኩ አካል የሆነ የታጠቀ ቅጥረኛ ጥበቃ ቡድን ያስፈልጋቸዋል።በጥንቃቄም ተመልምሎ ተዘጋጀ።   ከዚህ በፊት በማይጋባ፣በጠለምትና አካባቢው ንፁሃን የጨፈጨፈ፣ከተከዜ ወደ ሰሜን ከተከዜ ወደ ደቡብ እየተዛወረ ከአማራ ግዛት አለ ስትለው ከትግራይ ግዛት የሚሻገር በወንጀል ተጨማልቆ ተስፋ የቆረጠውን ሀጎስ የተባለ ግለሰብ ከግብራበሮቹ ጋር መልምለው ለወርቅ ማውጣት ተግባር የታጠቀ የጥበቃ የኃይል አማራጭ አድርገው በቅጥረኝነት በደሞዝና በጥቅማ ጥቅም ተሰማራ።(የማዕድን መንግስታዊ ዝርፊያ እስከ ኔትወርኩ በቀጣይ በሰፊው ይፋ የምናደርግ ሁኖ)...   ይህ ቡድን ከዚህ ቀደም በፈፀመው ወንጀል በፋኖ ሲታደን ትግራይ ሽሬ መሽጎ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በኦህዴድ ጀኔራሎች የዝርፊያ ኔትወርክ ከለላ እየተሰጠው ከወርቅ ማዕድን በዝርፊያና በቅጥረኝነት ተሰማርቶ ቆይቷል።    ጦርነትን በድል የመቋጨት ስንፈተ አቅም ያጠቃው ዓብይና ቡድኑ በቅርቡ በሀሰተኛ የሚዲያ ጫጫታ ብዥታ ለመፍጠር በማለም የወርቅ ዝርፊያ ተባባሪ የሆነውን ቡድን የፋኖ መዋቅር አካል የነበረ በማስመሰል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት ተጋግጠዋል። በየትኛው ድርጅት ?በየትኛው ክ/ጦር?በየትኛው ብርጌድ ተጠርንፈው እንደነበረ ያልተረጋገጠ መሆኑን መገንዘቡ ነገሩ የተለመደ የሴራ ቅጥፈት መሆኑን የሚያጋልጥ ሲሆን ባለፉት ዓመታት በፋኖ ትግል አሰላለፍ ምንም አበርክቶ እንዳልነበራቸው ትጥቃቸውና ጠቅላላ ቁመናቸው ልብ ብሎ ለተመለከተ አስቂኝና አሳቃቂ የከሸፈ ትወና ነበር።ተመሳስለው የሚሰራጩ የጠላት መረጃዎች ራሳችን እንጠብቅ እያልን ሀጎስ ምህረት የሚባል በፋኖ የሚፈለግ ወንጀለኛ እንጅ የፋኖ አመራር አልነበረም ኖሮም አያውቅም ።      እየለየን ዱባና ቅል ለየቅል!!               ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

እንደ ኢትዮጵያ ባለች ብዙ ማንነት እና ፍላጎት በታጨቀባት ሐገር ውስጥ ለዚያውም መንግስት መር የአዲስ ሐገር ማዋለድ ፕሮጀክት በሚሰራበት ሁኔታ አባዱላ እና ባጫ ደበሌ ወይም ክንፈ ዳኛው ከመቀሌ ከኢትዮጵያ ተገንጥለን ሀገር እንሆናለን የሚለው ፉከራቸው ዕውን የሚሆንበት ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ። ምክንያቱም :- 1/ መገንጠል በህገመንግስቱ ተፅፎ የተፈቀደ ነፃ መብት ሆኗል ። 2/ የሐገሪቱ የግዛት ምስረታ (State Formation ) ገና አልተጠናቀቀም ። 3/ የመገንጠል መብት የፈቀዱ ቡድኖች አሁንም ከፊት ሆነው ፖለቲካውን እየመሩት ነው ። 4/ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የአማራን ርስት እና አፅመ - ርስት መውረር እንደ ፖለቲካ ፕሮግራም እና ግብ የሚቆጥሩ ናቸው ። 5/ ሁሉም ያበቡት ( Flourish ) ያደረጉት በአማራ ውድቀት ላይ ነው ። 6/ ሁሉም ከብሔራዊነት ይልቅ የመደብ እና የብሔር ጥቅም ማስጠበቅ ላይ ናቸው ። ጉልበት ያላቸው ሀገራት እና ኃይሎች ሁሉ መድፍ ተኩሰው ጥይቱ እስካረፈበት ድረስ የኔነው በሚሉበት በዚህ ዘመን ፣ ሮኬት አስወንጭፈው ያረፈበት ድረስ ድንበር በሚከልሉበት በዚህ የፖለቲካ ሽቅድምዲሚያ ዘመን የእነ አባዱላ እና አብይ አህመድ የአማራን ለም መሬት በድጋሜ ለመውረር መዘጋጀታቸው የሚገርም አይደለም ። ስለዚህ የአማራ ህዝብ ሆይ :- የአባቶችህን ርስት በደምህ ታጥራለህ ? ወይስ ዳር ቆመህ ነፃ አውጪህን ፋኖን እየተራገምክ አይንህ እያዬ ሀገር አልባ ትሆናለህ !? ምርጫው የአንተ ነው ። ለመላው የአማራ ህዝብ :- ዘመኑ አሁን ነው ፣ ትግሉ ዘርፈ ብዙ ነው ፣ ዕቅዱ የረጅም ጊዜ ነው ፣ አብዮቱ አብይን ከመጣል ባሻገር ነው ፣ የአብዮቱ ሀሳብ የገዘፈ ነው ። ድል ለጀግናው አማራ ! ድል ለጀግናው ፋኖ ! አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !! አርበኛ ማርሸት ፀሐው የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ የህ/ግ/ኃላፊ

አሳዛኝ ዜና የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ተገደሉ። (#EOTCTV ታኅሣሦ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ) የኅዳር ጽዮን ማርያምን በዓል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ
አሳዛኝ ዜና የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ተገደሉ። (#EOTCTV ታኅሣሦ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ) የኅዳር  ጽዮን ማርያምን በዓል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር በምትገኘው በሐረቶ ማርያም በዓሉን አክብረው ሲመለሱ ሻንቡ ከተማ መዳረሻ ሲደርሱ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ እና በርካታ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማኅበራት አገልጋዮች በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ተወስደው የቆዩ ሲሆን ሌሎቹ ተፈትተው ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል:: መረጃው የEOTCTV ነው

አለቃዬ ሻለቃ ሙላቴ ላደረክልን መልካም ስራ ሁሉ ከልብ እናመሰግንሃለን። በሄድህበት መልካሙን ሁሉ እመኝልሃለሁ። የአማራነት ልክ Mulatie Sisay 🙏 ለመላው የምእራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ በየደረጃው ላላችው አመራሮች፣ የትግል አጋሮቸ እና ለመላው የጎጃም ህዝብና የትግላችን ደጋፊዎች ከሁሉ አስቀድሜ አማራዊይና ወንድማዊ ሰላምታየ በያላችውበት ይድረሳችው ማለት እፈልጋለው!!!! ወራሪውና ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን መንግስት መር እና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ ሃብትና ንብረት ዘረፋ እና ማውደም፣ አማራነትን የመፀየፍና የማጥፋት እኩይ ተግባር በመቃወም ከነበርኩበት የቀድሞው የመከላከያ ሰራዊት፣ ከወቅቱ የአብይ አህመድ የግል ካንፓኒ ከአባልነትና አመራርነት ለቅቄ በመውጣት የአማራን ህዝብ ትግል በቀድሞው የአማራ ፋኖ በጎጃም የአሁኑ ቴወድሮስ እዝን ተህሳስ 12/ 2017 ዓ/ም ተቀላቅየ የምችለውን ሞያዊይና አማራዊ ግዴታየን ድርጅቱ የሰጠኝን ተልእኮ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ተንቀሳቅሸ የምችለውን ሁሉ አስተዋፅኦ ሳደርግ ሙቆየቴን መግለፅ እወዳለው። ለእውነት ይህ አንድ አመት ቆይታየ በህይወት ዘመኔ አይረሴው ትዝታየ፣ ታሪኬ መሆኑን በህይወት እስካለው የምናገረው፣ ሲመቻችልኝም የምፅፈው ልዩ የህይወቴ ምእራፍ መሆኑን መቸም አልዘነጋውም። እንደ ድርጅት አመራር፣ እንደ ታጋይ ብሎም እንደ ህዝብ ላደረጋችውልኝ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ ከውስጤ ፍቅር በማልሰስትበት አንደበቴ በንፁህ አማራዊ ወንድምነት ምስጋናየ ልባዊ ነው። ካበረከትኩት በላይ እያመሰግናችው፣ በምሄድበት የስምሪት ቀጠና ሁሉ ለደህንነቴ በቂ ጥበቃና ከለላ እየሰጣችው፣ ለመስጠት ከማይሰስተው እጃችው እና ከማይነጥፈው ኪሳችው ስንቄም ትጥቄም በመሆን ላደረጋችውልኝ መልካም ነገር ሁሉ ከማመስገን ውጭ ሌላ ምንስ ላደርግ እችላለው? በአንድ አመት ቆይታየ በተለይም በአመራር ስልጠና፣ በማስተማርያና በልዩ ልዩ ዶኮመንት ዝግጅት ብሎም ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ፣ በአደረጃጀት ክለሳወች የበኩሌን አስተዋፅኦ በማበርከት አሁን ላለው ግዙፉ የቴወድሮስ እዝ የበኩሌን አስተዋፅኦ ጠጠር እንደወረወርኩ ይሰማኛል። አማራ የሚጠነክረውና አሸናፊ ሁኖ የሚወጣው በሚወለደው አማራዊ አንድነት ብቻ መሆኑን ባለኝ ፅኑ እምነት ለአማራ አንድነትም መሪወችን በማናገር፣ ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ አሁን ላለው የአንድነት የተስፋ ብርሃንም የምችለውን ሁሉ እንዳደረኩ ይሰማኛል ለዚህም ሃሳቤን ሳትንቁ ከጎኔ ለነበራችው ለአራቱም ግዛት ከፍተኛ አመራሮች ሁላችውንም ከልብ በመነጨ ትህትና አመሰግናችዋለው። ሁሉም የቀጠና አደረጃጀቶች ወጥና ተመሳሳይ የአደረጃጀት እና የአመራር አቅም ግንባታ እንዲኖር በማሰብና ያቅሜን አበርክቶ ለማድረግ ወደ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ እዝ በማቅናት በተለይም በአመራር ስልጠና ላይ በማተኮር የበኩሌን አስተዋፅኦ ለማበርከት ድርጅቴን በጠየኩት መሰረት ለተደረገልኝ መልካም ምላሽ ምስጋናየን እያቀረብኩ የቴወድሮስ እዝ ሞያዊይና ወንድማዊ ድጋፌን በጠየቀኝ ወቅት በማንኛውም ሰአትና ቦታ በመገኘት የምችለውን ሁሉ ለማበርከት ዛሬም እንደትናንቱ ዝግጁ መሆኔን ልገልፅ እወዳለው። ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ እንደመጣው አንተን ማግኘቴ፣ ስንገናኝም ያሳየኸኝ ፍቅርና አክብሮት፣ የጣልክብኝ እምነት በጉዞየ ሁሉ ጉልበቴ ነበርና ሁሌም እንደምለው ፈጣሪ ጥላና ከለላ ሁኖ ለእኛው ለተገፋነው ህዝቦች ሲል የማቱሳላን እድሜ ያድልህ ወንድማለሜ!!!!! የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ወንድምና እህቶቸ ያደረጋችውልኝ መልካም አበሬታ፣ ድጋፍና ማበረታታት በነበረኝ ቆይታና በቀጣይም ለሚኖረኝ ጉዞ ጉልበቴ ነበርና በያላችውበት ወንድማዊ እና ልባዊ ምስጋናየ ይድረስልኝ። አርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ፣ አርበኛው ወንድሜ ሃብቴ ወልዴ፣ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ፣ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል፣ አርበኛ መከታው ማሞ፣ ኮል ማነገረው፣ እዮቧ የሸዋው፣ ደርቤ ወሎየው እና ስማችውን ያልጠቀስኳችው ወንድሞቸ ስለሁሉም ወንድማዊ አቀራረባችውና ምክራችው ሁላችውንም ከልብ አመሰግናለው። በመጨረሻም ለሁሉም የፋኖ አመራሮች የማስተላልፈው ወንድማዊ ምክር አንድ አለመሆናችን ብዙ የግል ህይወታችን ወደጎን ጥለን በገባን ልክና መጠን የምንታገልለት ህዝባችን እየደረሰበት ያለውን የማያቋርጥ ግፍና መከራ፣ በዱር በገደሉ በየሰአቱ ለሚለዩን እህትና ወንድሞቻችን በአጠቃላይ እንደ ህዝብ አየደረሰ ያለውን ሰቆቃ ለማሳጠርና በአንድ ልብና መንፈስ ተናበንና ተነጋግረን የጋራ በትራችን በጠላት ላይ ለማሳረፍና የሞት አፋፍ ላይ ያለው ጠላታችን በእኛው እንዝላልነት እድል እያገኘ መሆኑን ተገንዝባችውና የሚሄደውን ጠመዝማዛ የአንድነት ጉዞ አሳጥራችው አንድነታችን ባረዘመ ጊዜ እንድታበስሩን ወደማዊ ጥሪየ ነው። ድል ለአማራ ፋኖ!!!!!!

ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር ህንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር ህንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢጣለል አስፓ
+4
ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር ህንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር ህንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢጣለል አስፓልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ ሀገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ደንበር። ከፋኖ ጋር ወደ ፊት!!!

በገባሪዎች እና ወዶ-ገብ ባንዳዎች የሚቆም ትግል የለም!! "አማራነትን ለመናኛ ጥቅም" ያዋሉ የትውልዱ ጠላት ናቸው። የህልውና ትግላችንን በስርገት የጠላትን ተልዕኮ በመቀበል ሲያውኩ  የነበሩትን ሁሉ እያራገፍናቸው እንቀጥላለን። የዓላማ ፅናት የሌላቸው እና የህልውና ትግሉን በቁስ ስቀቀን፣በስልጣን ጥመኝነት እና በራስ ወዳድነት መንፈስ የአማራን ህዝብ ትግል ለመበተን መሞከር ክህደት ነው። የአማራ ህዝብ በየአዝማናቱ የገጠመውን ብሔራዊ የህልውና አደጋ በመመከት ረገድ የአማራ አርበኞች የአንበሳውን ድርሻ ቢወሰዱም የህዝባችን ጥያቄዎች በመመለስ ረገድ ደግሞ እምብዛም አልነበረም። ስለሆነ ከ500 ዓመት በፊት የገጠመንን ብሔራዊ የህልውና አደጋ መልኩን ቀይሮ በፋሺስቱ አብይ አህመድ መንግስት እንደ አድስ ማገርሸቱ ይታወሳል። ስለዚህ በፋሺስቱ አብይ አህመድ የተጀመረውን ወረራ ለመመከት በምናደርገው ርብርብ ደግሞ የአማራ ፋኖ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው። ትግላችን ፀረ -ሰው የሆነውን የአብይ አህመድ ስርዓት በመንቀል አድስ ስርዓት እና ስሪት መትከል ነው። በገባሪዎች እና ቅጥረኛ ባንዳዎች የሚቆም የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል የለም። የህዝባችን ተቀዳሚ ጠላት እና የባንዳ ምልክት የሆነው የአማራ ብልፅግና በሁሉም የአማራ ግዛቶች ያሰማራው አረመኔ ሰራዊት እየተቀጠቀጠ፣እየተማረከ እና እየከዳ ባለበት ስዓት አስርጎ ያስገባቸው እና በተልዕኮ የህልውና ትግሉ ላይ ተጣብቀው ሚና ያልነበራቸውን ምስለ ታጋዮች እጅ እየሰጡኝ ነው በማለት በቴሌቪዥን መስኮት እያስነገረ ይገኛል። እኛ ግን ወዶ ገቦቹ ፈፅሞ እርባ እና ቢስ እና ቢስታቢስቴን አበርክቶ የሌላቸው ናቸው ስንል በኩራት እንናገራለን። "ጲላጦሶች" ሆይ ጀምበራችሁ ጠልቃለች!! ቀሪዎቹ የዳውንት ሙሺሮች መንገዱ ክፍት ነው ቀጥሉ......ወደ ቤታችሁ ብልፅግና!! ከጥር 2017 ዓም ጀምሮ ዳውንት ላይ የከለባት ጉባኤ ያደረገውን ሃይል   በአማራ ትግል ውስጥ አስተዋፅኦ እንደነበረው ለማለት የተሄደበት ርቀት አገዛዙ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ስለመሆኑ ማሳያ ነው። ስለሆነም በገባሪዎች እና በወዶገቦች የሚሰራ የፓለቲካ ዝሙት ከርኩሰትነቱ ውጭ ምንም የሚያመጣው ተጨባጭ ለውጥ የለም። ስለሆነም እኛ የምንተማመነው በዓላማችንና በትግል መስመራችን እንጅ በግለሰቦች ስም የተንጠለጠለ ትግል አልጀመርንም። ትግላችን ከግለሰቦች እና ከፓርቲ በላይ ነው። በገባሪዎች እና በወዶገቦች የሚጠንክር ትግል እንጅ የሚቀለበስ የህዝብ ትግል የለም!! ቅርብ ወራጆች እና ተላላኪዎቻቸው በየፌርማታው እየተራገፉ እውነተኛ የህዝብ ልጆች ደግሞ በድል አድራጊነት ደምቀው የህዝባችንን ሁለንተናዊ ጥቅም የምናስከብር ይሆናል። አማራነት አሸናፊነት ነው ስንል በተግባር መገለፅ እና በዓላማ መፅናት መሆኑን ልብ ይሏል🙏 መዳረሻው ድል እና ነፃነት የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል። ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

የድል ዜና‼ ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ከባድ ተጋድሎ ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ ወጤ ቀበሌ ልዩ ስሙ መርካቶ ከተማ ላይ የአማራ ፋኖ በወለጋ በአርበኛ አለፈ ሽባባው የሚመራው ጌጤ ግርማ መብረቅ ክ/ር ከፍተኛ ድልን ተጎናጽፏል። በትናንትናው ዕለት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ሙተና ቁስለኛውን ትቶ መፈርጠጡን ተከትሎ መከላከያ በከባባድ መሳርያዎች አጅቦ ሙትና ቁስለኛውን እንዲያነሳ ካደረገው በኋላ ማታ ላይ ሀይለኛ ሀይለኛ ምሽጎችን አስቆፍሮ የኦሮሚያን ልዩ ሀይል ሀይል አስጨምሮ ምሽግ አስይዞት የወጣ ሲሆን በዛሬው ዕለት ማለትም  ታህሳስ 04/2018ዓ.ም በጧቱ እስከ ምሽጋቸው ድረስ ዘለቀው በመግባት የአማራ ፋኖ በወለጋ በአርበኛ አለፈ ሽባባው የሚመራው ጌጤ ግርማ መብረቅ ክ/ር በቆፈሩት ጉርጓድ ቀብሯቸዋል። በዛሬ በጧቱ በጀመረው ከባድ ተጋድሎ እስከ አሁን ቁጥሩ ያልተገለጠ በዬ ሻለቆች ብዛት ያለው የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳርያ የተማረከ ሲሆን ሙትና ቁስለኛውን ለመቁጠር ያዳግታል። እንዲሁም ከ20 በላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ያለምንም ጉዳት እጃቸውን የሰጡን ሲሆን በአሁኑ ስዓትም እንክብካቤ እዬተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን በፎቶና በቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎችን ለሰፊው ህዝባችን ለማሰራጨት አካባቢው ላይ ኔትወርክ መያዙን ተከትሎ ለግዜው ባንችልም በቅርብ ቀን የምናሳያቹህ ይሆናል። በተያያዘ ዜና በአሁኑ ስዓት መከላከያ እንደለመደው በከባባድ መሳርያዎች ታጅቦ የልዩ ሀይሉን አስክሬንና ቁስለኛ በአምቡላንስ በኦራልና በህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ወደ ጉቶ ጊዳ ወረዳ ኡኬ ከተማ እያጋዘ ሲገኝ በኦሮሚያ ልዩ ሀይል አስክሬን ላይ ምሽግ ለምሽግ እዬተረማመዱ አይበገሬ ክንዳቸውን ሲያሳዩት የዋሉት ፋኖዎቻችን የተገኘውን ምርኮ በሙሉ በመያዝ ወደ ነጻ ቀጠናቸው በሰላም ተመልሰዋል። ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ‼ ድል የጭቁኖች ተስፋ ለሆነው ፋኖ‼ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን‼ ፋኖ ዳዊት አማረ የአማራ ፋኖ በወለጋ ህ/ግንኙት ሀላፊ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!         ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ከ16 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ 18 ያህሉ መቁሰላቸው ታወቀ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦርና አሳምነው ኮር ሁለት ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ቃኝዎች በጥምረት በወሰዱት አፀፋዊ ምላሽ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ተደርጓል። ታህሳስ 03/2018 ዓ/ም መነሻውን ጋዝጊብላ ወረዳ አስከተማ ያደረገው የአገዛዙ ጥምር ጦር በሦስት አቅጣጫ ማለትም ከአዲ በር በምቆጎ አቅጣጫ፣ከአንሳይ ዋሻ በምዮ አቅጣጫ እንዲሁም በላይ በደጋው አድርጎ ወደ ቁልቋል አርባተንሳ አቅጣጫ አድርጎ በመምጣት የጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ፋኖዎችን አፍናለሁ ብሎ የመጣውን ጦር  ሆን ተብሎ ወደ ውስጥ ሰርጎ እንዲገባ በማድረግና ስትራቴጂክ ቦታዎችን ይዞ ሰፊ ሰዓት በመስጠትና ቦታ በመያዝ እንደ እብድ ውሻ እየተክለፈለፈ የመጣውን የብልፅግና ጥምር ጦር የሚሉት ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል። ከታህሳስ 02 እስከ 03/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በመድፍ፣በሞርተርና በዲሽቃ የታገዘ ጥቃት የከፈተ ቢሆንም ተወርዋሪዎቹ የጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ልጆችና የወንድሞቹ ጋሻዎች ምስራቆቹ የሐውጃኖ ክፍለ ጦር ቃኝዎች በቅንጅት ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:30 ሰዓት ድረስ ጠላትን በሚገባው ቋንቋ አነጋግረው ከ16 በላይ ሙትና 18 ያህል ቁስለኛውን ይዞ ወደ ነበረበት ጉድጓድ መሸሸጊያው አስከተማ አስፈርጥጠው አስመልሰውታል። በመጨረሻም የአማራና የአገው ህዝብ ህልው ማንነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ በቁርጥ ቀን ልጆቹ በጋራና በቅንጅት በመመከትና በመደምሰስ ተከባብረንና ተቻችለን የምንኖርባትን የአባቶቻችን ኢትዮጵያን እንመሠርታለን ሲሉ የሐውጃኖ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር አርበኛ ፋኖ ካሳ አበበ እና የጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ፋኖ ጣሰው አለልኝ በጋራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ  ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ታህሳስ 04 / 2018 ዓ.ም