ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 721
المشتركون
+4524 ساعات
+1767 أيام
+1 15530 أيام
أرشيف المشاركات
የአገዛዙ ወታደሮች በምዕራብ አማራ ቀጠና ቡሬ ወረዳ ሰርተከዝ ማርያም ቤተክርስቲያን በተሰበሰቡ አማኞች ላይ ጥቃት ፈፀሙ!
ትናንትናው የካቲት 01/2018 ዓ.ም በምዕራብ አማራ ቀጠና ቡሬ ወረዳ ሰርተከዝ ቀበሌ የማሪያምን ቤተክርስቲያን የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ለማክበር ከህጻናት እስከ አዛውንት በተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀይማኖት አባቶች ላይ የፀረ አማራው ብልፅግና ወታደሮች ከፍተኛ የሆነ ድብደባና ወከባ መፈፀማቸው ተሰምቷል።
የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን በተሰቡበት የጠላት ሃይል ከበባ በመፈጽም #የቃል ኪዳኑን ታቦት በተሸከመው ካህን እና ምዕመናን ላይ የተኩስ እሩምታ በመክፈት የቃል ኪዳኑን ታቦት ከካሀኑ ላይ ወርውሮ መሬት በመጣልና ቄስ ጌትነት ገላው የተባለ ታቦቱን ተሸክሞ የነበረ የቤተክርስቲያን አገልጋይ አስረው እንደወሰዱት እና በርካታ ንጹሃን አርሶ አደሮችን አግተው መውሰዳቸውንም በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ለ77ኛ ክ/ጦር መረጃውን አድርሰዋል።
አሸባሪው ሀይል የሀይማኖት ተቋማትን በተደጋጋሚ የምሽግ ቦታ ከማድረግ በዘለለ የቤተክርስቲያኗን ቅርሶች በመዝረፍ አማኞቿን በመግደልና በማንገላታት እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
መረጃው በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
ትግሉ ፅናት ይጠይቃል!!
የካቲት 02/2018 ዓ.ም
በአማራ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋ በመቃወም ለአማራ ህዝብ ነፃነት የህልውና ትግል ለማሻገር የተንኮታኮተውን የአገዛዙ ኃይል ለመቅበር እና ትግሉን ቀጥ ባለ ቁመና በመምራት ጫፍ ለማድርስ በ64ኛ ክፍለ ጦር የሚገኙ አመራር እና አባላት
ድርጅቱ እና ህዝባችን የሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ እየታገሉ ይገኛል።
የጀግኖች ስብስብ የኮስትር ግርፎች የሽፈራው ልጆች ከውስጥም ከውጭም ያለውን ጫና ተቆቁመው ክፍለ ጦር የተሻለ ቁመና ይዞ እንዲሄድ ሌት ተቀን ድምፃቸውን አጥፍተው እየሰሩ ይገኛል።
የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል መሪዎቹን መርጦ ወደ አንድ መምጣቱ እና ቀጥ ያለ ቁመና እየያዘ መምጣቱን ተከትሎ በክፍለ ጦሩ እየታዩ የሚገኙት አንዳን የጠላት ተልኮ ተሸካሚ ቅርብ ወራጆች ድርጅቱ በፋይናስ እና ኦዲት ኢንስፔክሽን ወደ መሬት ወርዶ መስራት ሲጀምር አገዛዙ አስርጎ ያስገባቸው ተለላኪዎች ታጋይ መሳይ የሌባ ስብስቦች ተልዕኮቸውን ፈፅመው ከህዝብ እና ከድርጅቱ የዘርፍት ገንዘብ በኦዲት እንደሚጠየቁ እርግጠኛ ሲሆኑ እጅ እየሰጡ ይገኛሉ።
ትግሉ እየጠራ ነው!!
64ኛ ክፍለ ጦር የትግሉን መነሻ እና መድርሻ፣ ዓላማ ያለው፣ ጠላት በስሙ ሲጠራ የሚያስፈራ ጠላትን መመከት እና መደምሰስ የሚችል የሰለጠነ ሰራዊት እየገነባ ይገኛል።
በክፍለ ጦራችን የአማራን ህዝብ ተዋርሰው በሆዳቸው ያደሩ ተራ ግለሰቦች ከአማራ ህዝብ ጠላት ጋር በማበር በባንዳነት በመሳተፍ የራሳቸውን ወገን አሳልፈው ክብራቸውን አዋርደው በተራ ጥቅማ ጥቅም አማራነታቸው በመሸጥ #እንቁ_ጀግኖችን በሸበል በረንታ በየኮሬ የኩበት አካባቢው ቀበሌ ከአንዴ ሁለቴ በከበባ አስበልተው የክ/ጦር አመራሮችን በጠላት ጥይት ለማስመታት ሲሰሩ ቆይተዋል።
እነዚህ የአማራ ህዝብ የደም ግብሮች ከአገዛዙ ጋር በመሰለፍ የአማራ ህዝብ ታሪክ ያጠፉ ባንዳዎች መሆናቸውን ለታሪክ መዝግበን ይዘናል።
የአማራ ህዝብ ዘብ የጀግኖች የአርበኞች ስብስብ ብዙ ጀግኖች የወደቁበት የአማራ ፋኖ ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እየሰራን እንገኛለን።
የፋኖን ዩኒፎርም በመልበስ በትግላችን ተመሳስለው የአገዛዙን ስረዓት የሚደግፉ፣ የፋኖን ስም የሚያጥላሹ፣ በትግሉ ስም ህዝባችንን እና ተዋጊው ወታደሩን በእንግልት ሲያሰቃዩ የቆዩ ግለሰቦች መሆናቸው ክፍለ ጦሩ ከህዝብ እና ከፋኖ አባላቱ የተሰጠው ጥቆማ ተቀብሎ የኦዲት ስራ እየሰራ መሆኑን እና እርምጃ እንደሚወሰድባቸው በማወቃቸው ወደ ጠላት መግባታቸውን ማሳወቅ እንወዳለን።
አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 02/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
ሰበር ሰበር የድል ዜና !!!
ከ50 በላይ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ሲደመሰሱ ቀሪዎች ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። በካምፕ ዉስጥ ከተጠረነፉት የአድማ ብተና እና ሚሊሻ አባላት አንድ አባል ብቻ ሲቀር ሌሎች ሙት እና ቁስለኛ ሆነዋል።
በቀን 02/06/2018 ዓ.ም የአፋብን ምዕ/አ/ቀ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ እና 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር የክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ ሻለቃ አንድ(1) ሻምበል በተሳተፉበት አዉደ ዉጊያ በመተከል አዉራጃ ፓዊ ወረዳ መንደር 21 ቀበሌ ላይ ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት በተደረገዉ አስገራሚ ኦፕሬሽን:-
1.ከ50 በላይ ተላላኪ ሚሊሻ እና አድማ ብተና ሲደመሰሱ ቀሪዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቆስለዋል።
2.ሶስት/3/ ብሬን፣ 55 ክላሽንኮቭ፣ 4 አብራራው፣ 6 ኤስኬኤስ መሳሪያዎችን ማግኘት/መማረክ/ ተችሏል።
3.አጅግ በጣም በርካታ ተተኳሽ እስከ ትጥቁ እና የእጅ ቦንቦችን ማግኘት ተችሏል።
ማስረጃዉን በፎቶ ይዘን እንመለሳለን ።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ !!!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
በስማዳ ወረዳ ፋኖ በፈፀመው የከበባ ማጥቃት የጠላት አከርካሪን በመስበር ድል ተቀዳጀ!
በቀጠናው ሸረፍ ጎዴ ላይ የነበረው የጠላት ብልፅግና ወታደሮች የኮንክሪት ምሽግ እና ወገዳ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል።
በአፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስር ከሚገኙት ከእስቴ ደንሣ ብርጌድ እና ከስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ወደ ጠላት ካምፕ ተወርውሮ በመግባት ለ8:00 ሰዓታት ባካሄዱት የጨበጣ ውጊያ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ታላቅ ድል ማስመዝገባቸውን የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለሚዲያችን በላከው መረጃ አስታውቋል።
ውጊያው የተካሄደው ትናንት የካታት 01/2018 ዓ/ም ከጧቱ 2:00 ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን ገደማ ድረስ በስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማና አከባቢው ላይ ሲሆን፡ በዚህም ፋኖ ድል የተቀዳጀበት፡ በአንፃሩ ደግሞ የአገዛዙ ኃይል በርካታ ጓዶቹንና ይዞታዎቹን ያጣበት ትንቅንቅ ነው የተካሄደው።
የፋኖ የማጥቃት አቅም በምን ያህል ደረጃ እንዳደገ በታየበት በዚህ የቆረጣና የከበባ ማጥቃት፡ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ የተደርጉ ሲሆን ቀሪው ኃይል ሕይወቱን ለማትረፍ አከባቢውን ለቆ መፈርጠጡ ታውቋል።
የጠላት ኃይል በስማዳ ወረዳ ውስጥ ሸረፍ ጎዴ ተራራ እና አቦ ቤተክርቲያን ዙሪያ ሰርቶት የነበረው የኮንክሪት ምሽግ ድርምስምሱ የወጣ ሲሆን፡የፋኖ አባላቱ ይዞታቸውን በማስፋት ወገዳ ከተማን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በአሁን ሰዓት ተቆርጦ የቀረ የጠላት አባል ካለ ለማጥራት የአሰሳ ስራ እየሰሩ መሆኑን ነው የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለሚዲያችን በላከው መረጃ ያስታወቀው።
በቀጠናው የሚገኘው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ከወደ ፋኖ በሚፈፀምበት፡ ከሳንጃ ውግ ጀምሮ የጨበጣ፣ የደፈጣና የፀረ ሽምቅ እርምጃ አከርካሪው ተሰብሮ ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን ቆሞ መዋጋት ሳይችል ቀርቶ ቀጠናውን ለቆ መሸሹን ጣቢያችን ከጉና ክፍለጦር ለማረጋገጥ ችሏል።
በተያያዘ ዜና!
ከወደ ፋኖ የሚወሰድበትን እርምጃ መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል ከአንዳቤት ፣ ከአርብ ገበያ ፣ ከማሰሮ ደንብ ፣ ከልጫና ከግንዳጠመም ፣ ከወለላ ባህር ፣ ከአጃ ፣ ከአይሳ ፣ ከእብናት ፣ ከጎሀላ ፣ ከሀሙሲት ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ተጠራርጎ መውጣቱን የጣቢያችን የግንባር ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል።
+1
በደብረ ማርቆስ ከተማ 206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 7:35 በጠላት ፓትሮል ላይ በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 9 ሚኒሻዎች ሙትና ቁስለኛ ሁነዋል።
ይካቲት 2/2018 ዓ.ም
======================:============
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን መፈንጫ በሆነችው ደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:35 ከማረሚያ ቤት ወደ መሐል አደባይይ ሲሔድ በነበረ ፓትሮል ላይ የኮሩ አዳኝ ቡድን በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 3 ሚኒሻዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ 6 ሚኒሻዎች ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሁነዋል።
ጨለማን ተገን በማድረግ በሌሊት ንፁሐንን አፍነው ማረሚያ ቤት አድርሰው ሲመለሱ በነበሩ ሚኒሻዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የከፈተው አዳኝ ቡድኑ በፓትሮሏ ስፖንዳ መሐል የተሳካ የቦንብ ጥቃት በመክፈት የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።
ከቀናት በፊት በደብረ ማርቆስ ከተማ አስደናቂ የቦንብ ጥቃት የፈፀመው አዳኝ ቡድኑ ከሁለት ቀን በኋላ ተመሳሳይ ድል የተቀናጀ ሲሆን እስከ አሁን በተፈፀሙ ተከታታይ አስደናቂ የከተማ ኦፕሬሽኖች ምንም አይነት መስዋትነት በወገን ኃይል በኩል አልተመዘገበም።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ከሀገር መነጠቅ ወደ ነፃነት/የሀገር ባለቤትነት — የህልውና ጥሪ ለአማራ ልጅ ሁሉ!
ዛሬ አማራ መሆን ዋጋ እየአስከፈለ ባለበት፣ በገዛ ሀገሩ እንደ ባዕድ በሚቆጠርበት እና የመጠለያ ካምፖች የብዙዎች ብቸኛ "ቤት" በሆኑበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ከታዳጊ ተማሪው እስከ አንጋፋው ምሁር፤ ከገበሬው እስከ ነጋዴው ድረስ ልባችንን ለአንድ እውነት እንክፈት።
ለምን አሁን?
የንጹሐን ሰቆቃ፦ እናቶች በየሜዳው ሲወልዱ፣ አባቶች ልጆቻቸውን በረሃብ ሲቀብሩ፣ ተማሪዎች የትምህርት ገበታቸው በመጠለያ ድንኳን ሲተካ ዝምታው ይብቃ።
የማንነት ጥቃት፦ መሳደድ፣ መፈናቀል እና መገፋት የአማራ ዕጣ ፈንታ ሊሆን አይገባም።
የምሁራንና የተማሪዎች ኃላፊነት፦ እውቀትና ጉልበት ካልተባበረ፣ ታሪክ ነገ በሁላችንም ላይ ይፈርዳል።
ጥሪያችን፡
ይህ የዘር ማዳን ጥሪ ነው። መከፋፈልን ወደ ጎን ትተን፣ በምክንያታዊነት እና በበሰለ መንገድ ተሰባስበን ለወገኖቻችን ድምፅ እንሁን። በመጠለያ ካምፕ ላለው ወገናችን ነፃነት፣ ለተሳደደው ወንድማችን መከታ፣ ለቆሰለችው እናታችን ፈውስ የምንሆነው በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው።
"አንድነት ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ ህልውናም ጭምር ነው!
መነሻቸውን ከፍኖተሰላም አድርገው ወደ ጂጋና ሆዳንሻ እየተቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በተወሰደ ሽምቅ ጥቃት ከ24 በላይ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!
ጥቃቱ የተጠናና እጅግ ፈጣን ነበር የተባለ ሲሆን፡ የጠላት ወታደሮች ተሳፍረውበት ከነበረው ተሽከርካሪ ሳይወርዱ ነው በቦምብና በክላሽ ያለቁት።
በተመሣሣይ፡ ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ፋኖ በፈፀመው የከበባ ጥቃት ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
በዚህም የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛውን የሚያነሳበት አፍታ እስኪያጣ ድረስ ከባድ የጥቃት ዶፍ ወርዶበታል።
*
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እንዲሁም 1ኛ ሻለቃ አባላት ትናንት የካቲት 01/2018 ዓ/ም ማለዳ ከፍኖተ ሰላም ወደ ጂጋና ሆዳንሽ ከተማ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በፈፀሙት የሽምቅ ጥቃት ከ24 በላይ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል መቀዳጀታቸውን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ከማለዳው 12:00 ሰዓት አካባቢ ላይ ሲሆን፡ የጠላት ወታደሮች ተሳፍረውበት ከነበረው ተሽከርካሪ ሳይወርዱ ነው በቦምብና በክላሽ ያለቁት።
በዚህ ጥቃት ዘጠኝ የአገዛዙ ወታደሮች ወዲያውኑ ሲገደሉ ከ15 በላይ የሚሆኑት ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን፡ በድምሩ ከ24 በላይ ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ነው መረብ ሚዲያ ከ109ኛ ኮር ለማረጋገጥ የቻለው።
በተመሣሣይ፡ ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ፋኖ በፈፀመው የከበባ ጥቃት ከባድ ጥቃት በመሰንዘር ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
በዚህም የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛውን የሚያነሳበት አፍታ እስኪያጣ ድረስ ከባድ የጥቃት ዶፍ ወርዶበታል።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ በወሰዱት የቆረጣ ጥቃት ድል መቀዳጀታቸው ታውቋል።
የፋኖ አባላቱ፡ ወደ ዳማ ማርቆስ እየተጓዘ የነበረውን የጠላት ሰራዊት ነው ከበባ ውስጥ በማስገባት በፈፀሙበት ጥቃት አስከሬኑን ሳያነሳ ወደ መጣበት እንዲፈረጥጥ ያስደረጉት።
ይህ በእንዲህ አንዳለ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99 ክ/ጦር ስር 3ኛና 4ኛ ሬጅመንት በጋራ በመሆን ወደ ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ እየተጓዘ በነበረ የጠላት ኃይል ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተቀዳጅተዋል።
አፋብን ለዓለም አቀፍ ሚዲያወች ስለ ወቅታዊ የአማራ ትግል ማብራሪያ ሰጠ።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ባዘጋጀው የሚዲያ ብሪፊንግ መድረክ የአማራ የህልውና ትግል ጠቅላላ ሁኔታ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታ፣ የጦርነቱ አጀማመር፣ ትግሉ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ስለ ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ ስለ ምርኮኞች እና የጦርነት ህግ አተገባበር፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራን የህልዉና ትግሉን በመረዳት ረገድ ስላለው ክፍተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ቀርቧል።
በተጨማሪም ከጋዜጠኞቹ ለቀረቡት ጥያቄወች በመምሪያ ኃላፊው በኩል ማብራሪያ እና ምላሽ ቀርቧል። በሚዲያ ብሪፊንግ መድረኩ ላይ ሮይተርስ፣ ኒውዮርክ-ታይምስ፣ ፍራንስ-24፣ አሶሼትድ-ፕሬስ፣ አልጃዚራን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያወችን የወከሉ እና ሌሎች የውጭ ሚድያ የግል ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።
አንድ ስንሆን እንዲህ መደመጥ እንጀምራለን!!
“ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ሁኖ የፋኖን ሰራዊት ያዝዛል” ብለው ፕሮፓጋንዳ ሊሰሩ የሚሞክሩት ‘የአስተሳሰብ ድንክ መሀይማን’ አብይ አህመድ ከአረብ ኢምሬቱ ቢንዛይድ በቀጥታ እንደሚታዘዝ የምትነግሩን ራሳችሁ አይደለም ወይ? ብለን አቻ ምላሽ አንሰጥም። ተላላኪነትን በታሪክም ሆነ አሁናዊ ታሪካችን ላይ አይገኝም። እንደ ህዝብ የተደረገብንን የዘር ፍጅት ‘ተላላኪነት በሚል ሾተላይነት’ እንዲዳፈን (Deny) እንዲደረግ አንፈቅድም። የሆነብንን ሁሉ አንረሳም።
፤
የትም ቦታ ላይ ይሁን ግን ‘በመሪ የሚታዘዝ ኃይል መኖሩን’ ማመናችሁ በቂ ነው። It is enough for them to believe that there is a millitary power that is guided by a chain of command from wherever you are.
፤
የቦሌ መንገዱ በር በእጃችን እስኪገባ በሱዳንም ሆነ በሱማሌ፣ በኤርትራም ሆነ በጅቡቲ፣ በኬንያም ሆነ በደቡብ ሱዳን መሿለኪያ በሮች ሁሉ ተዟዙረን የዲፕሎማሲ አቅማችንን እየገነባን “ዓለም ላይ ሊኖረን የሚገባውን የግንኙነት መረብ” እናሳልጣለን። በዚያ መስመር ውስጥ አፍሪካም ሆነ አሜሪካ፣ አውሮፓም ሆነ ኤስያ እንዲሁም አረቡ ዓለም አሉ።
፤
በህፃን ልጅ እጅ ላይ ያለውን ስልጣን እንዳይፀና እንዳደረግነው ሁሉ ከእጁ ነጥቀን ለሀገር የሚበጅ ተግባርን እንሰራበታለን። ይህ የነገን ጮራ መውጣት ያክል ቅርብ ነው።
፤
ፍርሀትና ስጋት ብዙ እንደሚያናግር ብናውቅም ከመሆን የማይገድበንን ነገር “የአብይ ሳይበር፣ የጁላ እግረኛና የይልማ አየር ሀይል” ተረባርበው ያልቀለበሱትን የፋኖን ትግል በከዳተኛ የወሬ ድሪቶ ልትመክተው አትችልም።
፤
እንዴትስ ተሁኖ!?
፤
የቁስ ሰቀቀን ያለባቸው ሁሉ የዚህን ትግል ቅድስና በፍፁም ሊረዱት አይችሉም። እኛ የረከባ ጥጃ ጠብቀን አላደግንም። የነፃነትን ታሪክ ሀሁ ብሎ ያስተማረን ህዝብ ልጆች ነን። በትግላችን የክብር (Dignity)፣ ኩራት (pride)ና ማንነት(identity) ታሪክ እየተፃፈ ነው።
፤
📷 ለማንኛዉም ከታች ያለው ምስል ጎዣም አማራ ውስጥ ሲሆን በቪዲዮ ጥሪ ከኤርትራ የሚያዝዘው ዘመነ ካሴና በቪዲዮ ጥሪ ከኤርትራ የሚታዘዙት የተባሉት እነ ማንቼ የትላንት ውይይታቸው ላይ የተነሳ ፎቶ ነው።
©️Manchilot
የአፓርታይዱ የአብይ አህመድ አገዛዝ በንፁሃን ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመ።
ጥር 30/2018 በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 011 ቀበሌ ሰርኮ አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ስርዓት ንፁሃንን በድሮን በመጨፍጨፍ ጠላቻውን በአደባባይ ገልጿል።
በድሮን ጥቃቱ አንድ ወጣት ህይዎቱ ሲያልፍ ከ 6 ቱ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በጥቃቱ በርካታ እንስሳቶች መገደላቸውንም ማረጋገጥ ተችሏል። የአማራ የሆነን ሁሉ ማጥፋት የሚያስደስተው ጨፍጫፊ ስርዓት ስድስት የንፁሃንን ቤት ማውደሙም ተረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 1/2018 ዓ.ም
ጉና ክፍለ ጦር
የዓምሐራ ፋኖ በሥማዳ መዳረሻ ወገዳ ከተማና ዙሪያ ገባው ድልን ተቀዳጅቷል❗
[የካቲት 01/2018ዓ.ም]
ዓምሐራን የነካ
የለውም በረካ
እንዲል የቤተ ዓምሐራው ዓምሐራ በዓምሐራ ሕዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥፋትን ሲፈጽም የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ጠርንፎ ለመውጣት በተዘጋጀበት ሰዓት የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የባዬው መልካሙ፣ የፍቃዴ አለባቸው፣ የአበበ፣ የሸጋው (ገብርዬ)ና ጥንቅሹ የግብር ልጅ የሆነችው ጠንካራዋና አይበገሬዋ እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ እና የሢሣይነው ራዕይ አሥቀጣይ የሆነችው ሥማዳ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ በጋራ የተቀናጀ አውደ ውጊያን ሲያደርጉ ውለዋል። የዓምሐራ ፋኖ የአገዛዙን የተለያዩ ምሽጎችን በክንዱ ሰባብሯል፤ ተቆጣጥሯል። ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እሥከ ቀኑ 11:00 በዋለው እልህ አሥጨራሽ ትንቅንቅ የዓምሐራ ፋኖ ድልን ተቀዳጅቷል። ዓምሐራ ፋኖ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል፣ የቁሥና የሥነልቦና ኪሳራ አድርሷል። የአገዛዙ ታጣቂዎችና የአገዛዙ የቡድን መሣሪያ እሥከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ ምርኮ ሆኗል። የወገዳ ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጠላት የምጽአት ቀን ይደርሥለት ዘንድ ''ሸረፍ ጎዴ'' ተራራን እየተማጸነ ይገኛል።
በኮንክሪት የተሰራው የአቦ ምሽግ በዓምሐራ ልጆች ተጋድሎ ተሰብሯል። የጠላት ብዙዎቹ ምሽጎች ሲሰባበሩ ጠላት የመጨረሻ መዳኛዬ ወዳለውና የቁም ምሽግ ወደሰራበት ''ሸረፍ ጎዴ'' 360° ተራራ ሩጦ ገብቷል። ጠላት ሸረፍ ጎዴ ተራራን አድነኝ ሲል በተማጽኖ ይገኛል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊
አፋብን
ሰሜን ዓምሐራ ቀጠና
በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
የካቲት 01/20178ዓ.ም
+1
የብልፅግና ካዝናና የጦር ካንፕ ባዶውን እየቀረ ነው!!!
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
✔️ አያሌው ደመቀና ደጉ ደረበ የተባሉ ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከአዴትና ከባህርዳር አንድ ሁለት እግርና አንድ ሰደፍ ክላሽ በመያዝ በቀን 01,06,2018ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦርን ተቀላቀሉ።
➯ በሌላ ዜና :-
✔️ በቀን 01,06,2018ዓ.ም የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት መነሻውን መኮድ በማድረግ የ22ኛ ክፍለጦር ሻለቃዎችን ለማጥቃት ወደ ባህርዳር ዙሪያ ተንተላ ይጎዲ ቀበሌ የተንቀሳሰቀሰው የጠላት ሀይል ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ልዩ ስሙ ተንተላ ይጎዲ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ በ22ኛ ክፍለጦር ሻለቃዎች በተደረገበት ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት የተበሳጨው ሰው በ*ላው የፋሽስቱ ሰራዊት ሞላ ሳለ የተባለ የ60 አመት ንፁሀን አዛውንትን ባህርዳር ዙሪያ ይጎዲ ቀበሌ ላይ በግፍ እረሽኗል።
ፋኖ አማረ ጌታቸው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ገልጿል ግንኙነት!
የካቲት 01,2018ዓ.ም
ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!
አዲስ ተስፋ!
