ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 613
المشتركون
+6624 ساعات
+5877 أيام
+1 04130 أيام
أرشيف المشاركات
የክፍለጦሩ መስራች አርበኛ አበበ ሙላቱን ጨምሮ የዕዙ መሪና የአፋብን ከፍተኛ አመራር ራስ መከታው ማሞ በተገኙበት ክፍለጦሩ ደማቅ የተሀድሶ ፕሮግራም አደረገ!!
መጋቢት 04 / 2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ግዙፉ አስቴጎማ ተራራ ክፍለ ጦር በቀጠናው ላይ የተሰጠውን ወታደራዊ ግዳጅ ካጠናቀቀ በኋላ ያሉትን ጠንካራ ሻለቆች ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ እረገድ የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ፣ የአፋብን ልዩ ዘመቻ መሪ አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ፣ ሌሎች የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለጦሩ መስራች አርበኛ አበበ ሙላቱና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኮሩ ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት የክፍለጦሩ ሰራዊትና የአመራር የግዳጅ አፈፃፀም ሁኔታ ከገመገመ በኋላ ለክፍለ ጦሩ ሙሉ ተሀድሶ ፕሮግራም ተደርጓል።
አስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር ከውስጥና ከውጭ በሚገጥሙት ችግሮች በርካታ ፈተናዎች ቢደርሱበትም፣ ትግሉን እየመሩ ያሉ ጠንካራ የክፍለጦሩ አመራሮች ባሳዩት ብልሀት የተሞላበት አመራርና ጀግናው የህዝብ ልጅ ሰራዊቱ ለትግሉ ባለው ቁርጠኛ አቋም ፈተናዎችን ተቋቁሞ ዕዙ በቀጠናው ላይ የሰጠውን ግዳጅ በታማኝነት ሲወጣ የቆየ ጠንካራ ክፍለጦር ነው።
"ላለፉት ከ50 አመታቶች በላይ እንደ አማራ የደረሱብን ችግሮች ብዙ ናቸው፣ ከነዚህም አንደኛው ማነቆ ሆኖ የነበረው አማራ እንዳይተማመንና እንዲገፋፋ ተደርጎ ሲሰሩ የነበሩ የጠላቶቻችንን ሴራዎች ሰብረን ዛሬ ላይ በወንድማማችነት መንፈስ አማራ የራሱ አንድ አታጋይ ድርጅት እንዲኖረው ማድረግ ችለናል።
እንደሸዋም የነበረንን ልዩነት ፈተን አንድነቱን አጠናቀናል" እንኳን ደስ አላችሁ፤ ከአሁን በኋላ አንድ ሆነናል፣ የጠመንጃችንን አፈሙዝ ወደ ጠላታችን ብቻ በማድረግ አማራ ጠሉን የብልፅግና ስርዓት ጥለን ለተበደለው ህዝባችን ነፃነቱን ማወጅ ይኖርብናል። ለዚህም እናንተ ጀግና ተዋጊዎች ድርጅታችሁ የሚሰጣችሁን የተኛውንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ሁኑ ሲል በተሀድሶው ላይ የተገኘው የዕዙ መሪና የአፋብን ከፍተኛ አመራር ራስ መከታው ማሞ መልዕክቱን አስተላልፏል።
እንዲሁም የመሀመድ ቢሆነኝ ኮር ዋና ጦር አዛዥ አርበኛ 100 አለቃ ኤርሚያስ ግጨው በመድረኩ መልዕክቱን እንዳስተላለፈው በድርጅቱ አማካኝነት ዕዙ የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ ለመፈፀም ኮሩ ዝግጁ ሆኖ እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል።
በመጨረሻም በጦር ግንባር ጀብድ ለፈፀሙና አርአያ ለሆኑ የክፍለጦሩ ጀግኖች የማበረታቻ የሞራል ድጋፍና ሽልማት በማበርከት ክፍለጦሩ በተዋረድ ለሚሰጠው አማራዊ ግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን የስምሪት አቅጣጫ በማስቀመጥ ፕሮግራሙ ተቋጭቷል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ስር-ነቀል ለውጥ በተባበረ ክንዳችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 04 / 2018 ዓ.ም
ሁሌም አዲስ መረጃ የሚያገኙበት የፊስቡክ ፒጅ ነው ይወዳጁት!!
https://www.facebook.com/abil.edm
"ከሞላሌ መሀልሜዳ ሲያመራ የነበረ ጠላት በደፈጣ ሲመታ ከአንኮበር ተነስቶ እንቅስቃሴ ያደረገው ጠላት በሁለቱ ዕዞች ጥምረት ከበባ ገብቷል"
ቀን 03/07/2018 ዓ.ም ከሞላሌ ወደ መሀልሜዳ ሲያመራ የነበረ የጠላት ሀይል ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር በደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለጦር 3ኛ እና 4ኛ ሻለቃ ቃኝዎች በጥምረት አንገዋ የተባለ ቦታ ላይ ተመቷል።ጠላት ከሞላሌ ወደ መሀልሜዳ ሎጀስቲክ በመቀባበል ላይ ባለበት ሰዓት በተጣለው ደፈጣ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።
ወዲህ ደግሞ ከአንኮበር ተነስቶ ደረፎ ወደሚባል ቦታ ሲንቀሳቀስ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የጣይቱ ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ በደፈጣ ሲመታ 4ኛ ሻለቃ ተቆርጦ ከባድ ጉዳት አስተናግዷል። ።በዚህ ጥቃት በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ መሆኑን ከውስጥ የወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል።
ጠላት ጫና ሲበዛበት ሀይሉን አጠናክሮ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ላይ እያለ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር አንድ ሻለቃ በማሳተፍ ከኋላ በመክበብ አስጨንቀውታል።
በቀጠናው ያለው ውጊያ የቀጠለ ሲሆን በቅርቡ አንድነትን ያበሰሩት ሁለቱ ዕዞች በአንድነት ማግስት በመናበብ እና በመተጋገዝ ለጠላት ራስ ምታት ሆነዋል።
መረጃ፦መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
💪💪 ድል ለፋኖ💪💪
በቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ምዕ/ጎጃም ዞን ጅጋ ከተማ የመሸገው የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፤40 መሳሪያ ተማረከ💪💪💪💪
========================
ቀኑ መጋቢት 03/2018 ዓ.ም ነው። ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ንስሮቹ 77ኛ ክ/ጦር ጅጋ ከተማ የመሸገውን የጠላት ሀይል በመደምሰስ የጠላትን ትጥቅ ሙሉ በሙሉ ለመማረክ ትልቅ ወታደራዊ ዕቅድ በማቀድ፣የጠላትን አቀማመጥ እና የታጠቀውን መሳሪያ ሲያጠኑ ሰንብተዋል። የሌሊቱ ግርማ ሞገስ በጸጥታ ሰፍኗል፤ በነፋሳት እንቅስቃሴ እየተቃኝ በጨረቃ ብርሃን እየተመራ ለሚጓዝ የነጻነት ታጋይ መንፈስን ያድሳል።
ንስሮቹ የሻለቆቻቻውን ወታደራዊ ወትሮ ዝግጁነት ከአረጋገጡ በኋላ በፍጹም ወታደራዊ ጥበብና ምስጢር ጠባቂነት ግርማ ሌሊቱ ሳይበግራቸው በንስር ዓይኖቻቸው ግራና ቀኙን እያሰሱ ጠላት ወደ መሸገበት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጅጋ ከተማ ገሰገሱ።
ከሌሊቱ 9:00 ላይ የጠላት የቁም ምሽግ በንስሮቹ 77ኛ ክ/ጦር በአርፒጅና በቦንብ ተደረማመሰ፤የጠላት አስከሬንም ተደራረበ። ንስሮቹ እየፎከሩ በጠላት ምሽግ እየተረማመዱ ከአዘርባጃን በልመና መጥቶ የዕቃ መጋዝን ውስጥ የተከማቼ በርካታ ክላሸንኮቭ በመማረክ ታላቅ ጀብድ ፈጽመዋል።
ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ንስሮቹ 77ኛ ክ/ጦር በዛሬው ዕለት ከ9:00- 11:00 በአደረጉት የሌሊት አውደ ውጊያ ፦
➡️32 ክላሸንኮብ
➡️6 አብራራው
➡️1 ኤስኬስ
➡️15 የክላሽ ካዝና
➡️በርካታ የክላሽና የብሬን ተተኳሽ የማረኩ ሲሆን፤
ከ80 በላይ ሚሊሻ፣ፖሊስ፣አድማ ብተና ሀይል ተደምስሷል። ከፍተኛ የሆነ የአገዛዙ ሀይል ከፍኖተሰላም ወደ ጅጋ የተንቀሳሰ ሲሆን አስከሬኑን በ2 አይሱዚ እና በሦስት ፓትሮል መኪና ወደ ፍኖተሰላም ሲያመላልስ አርፍዷል።
➡️የአፋብንን የምህረት አዋጅ የተቀበሉ ህይወታቸውን አተረፉ፤ እምቢ ያሉ ከቆፈሩት ምሽግ ተደፉ፤
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 04/2018 ዓ.ም
ከመጋቢት 01 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን የፈጀው አውደ ውጊያ የንፁሀን ጭፍጨፋ እና የተጠናከረው የማህበረሰብ ዝርፊያወች‼️
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 64ኛ ክፍለ ጦር እና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ 1ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ቁጥቋጥ እና አራጤ አካባቢው ከየካቲት 30 - መጋቢት 02/2018 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በአደረጉት ትንቅንቅ ሶስት ቀናቶች በተደረገው አውደ ውጊያ በረካታ የጠላት ሀይል ሲደመሰስ በረካቶች ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል።
በአገዛዙ የእናት ጡት ነካሽ በሆዳቸው በአደሩ ቅጥረኛ አመራሮች በግፍ ከተገደሉት፣ ሀብት ንብርታቸው ከወደመባቸው እና ከተዘረፋበቸው ንፁኃን መካከል:-
1ኛ. አያሌው ሸንቁጥ አጋም ቦርቦር በፀበል ላይ እንዳለ የተገደለ
2ኛ. መነኩሴ እሙሃይ ታሪኳ ቁስለኛ
3ኛ.ለፀበል የመጣች ስሟን ማግኜት ያልቻልናት ሴት ቁስለኛ
4ኛ. አቶ መርከቡ አስርስ እግሩ የተቆርጠና ቤቱ የወደመበት
5ኛ. አቶ ሸገው ያዜ ቤቱ የወደመበት
6ኛ. አቶ አየለ በለጠ ቤቱ የወደመበት
7ኛ. አቶ በለጠ አለሙ ቤት የወደመበት
8ኛ. አቶ አያዩ ክብርት 3(ሶስት) ማዳበሪያ ማሽላ ጭነው የወሰዱበት
9ኛ. ወጣት ጌታቸው ሀብታሙ
10ኛ. ወጣት ይናገር ብዙአየን
11ኛ. ወጣት አማራ አዱኛው
12ኛ. ወጣት አወቀ አዱኛው ሞተር
13ኛ. ወጣት ወንዳለ ውዱ
14ኛ. ወርቄ ታደሰ
15ኛ. ውዴ እንቢያ 16,000 ብር ሸቀጣ ሸቀጥ
16ኛ. እመይዋ ባሴ 36,000 ብር ሸቀጣ ሸቀጥ
17ኛ. አቶ አሸንፍ ክብርት የፀጉር ቤት ማሽን የወሰዱበት
18ኛ. አቶ ጌትነት አበር ከባድ ድብደባ የተፈፀመበት
29ኛ. ውባለ ጫኔ ከባድ ድብደባ የተፈፀመበት
20ኛ. ያደግድጉ ታደለ ከባድ ድብደባ የተፈፀመባት ሲሆኑ አገዛዙ በሸበል በረንታ ወረዳ ህዝብ ለይ የጭካኔ በትሩን በዚህ ልክ አሳርፎ ወጥቷል።
አዲስ ትውል፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
መጋቢት 04/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
<<የጠላት ዕቅድ>>
ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን በደረሰን መረጃ መሰረት:-
🕳 የጠላት አውናዊ ኩነት "3ቱን"መድፍ በመያዝ አንዱን ሰቀላ፣ ሁለተኛውን ወይራ፣ ሶስተኛው ቢቸና ከተማ አደባባይ አዘጋጅቶ መያዙን
🕳 የጠላት አውናዊ ዕቅድ፦በርሃ በርሃውን በከባድ መሳሪያ መደብደብ፣ዲማ ለመግባት የቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ
🕳 ጠላትን በአዋጊነት እየመሩ ያሉት የፌደራልና የክልል የጦር መኮነኖች መሆናቸውን
🕳 በርካታ የጠላት ኃይል ተሰባስቦ ያለበት ሁኔታ መኖሩን
🕳 በጠላት ኃይል በኩል መድፍ፣ ዙ-23፣ዲሽቃ፣ፔፒና መሰል መሳሪያዎች በመያዝ የኃይል አሰላለፉን ያሰፋ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል፡፡
🕳 ከዚህ ጋር ተያይዞ በወገን በኩል ያለ ስራዊታችን ያልተገባ መስዋዕትነት ላለመክፈል የተናበበ ዕቅድና ቅድመ ሁኔታ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
🕳 በሌላ መረጃ የቀበሀና፣ ገደብና መሰል ቀጠና ያለ የወገን ኃይል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ከማድረግ ባሻገር ቅድመ ዝግጅት ያስፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ፦ መረጃው ከአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ነው፡፡
መጋቢት 03/2018 ዓ/ም
በሸበል በረታ እና በእነማይ ወረዳ አገዛዙ በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያወችን እየፈፀመ ነው
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
መጋቢት 03/2018 ዓ. ም
በአገዛዙ አራጅ ስራዊት የጦር መኮንኖች፣ በምስ/ጎጃም ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ባንዳ "ገበሬው/ አለኸኝ ሰማ እና አበባው" መንገድ መሪ #ባንዳ በመሆን በሸበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ የሚኖር ማህበረሰብ ሀብት ንብረት እየዘረፍ እና እያወደሙ ንፁሀንን በከባድ መሳሪያ እየገደሉ ይገኛል።
የBm 107፣ መድፍ፣ ዙ23 እና ሞርተር እየዘነበባቸው ከምንም ሳይቆጥሩት ጠላትን የሚያርበደብዱ የበላይ ዘለቀ የአብራክ ልጆች የአማራ እናት አምጣ የወለደቻቸው የብልፅግናን ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ አድረገው ሲመልሱ በንዴትና እብሪት ይህንን በምስል ላይ የምታዩትን ቅንቡላ በንፁሀን ማህበረሰባችን ላይ በግዴለሽነት ከየካቲት 30- መጋቢት 03/2018 ዓ.ም እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ድርስ እየወረወረ ይገኛል።
የአፋብን ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
በዛሬው ዕለት #_የ11ኛ_ዕዝ_104ኛ_ኮር_መሃንዲስ የሆኑ ስድስት የአገዛዙ ሰራዊቶች 5 ጥቁር ክላሽና 1 ስናይፐር በመያዝ አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነዉ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ 16ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
#ወደሉ_ባንዳ_ተወግዷል‼️
ንፁሃኖችን እያሳፈነና እያስረሸነ የነበረው የአድማ ብተና ሻምበል አመራር በሲቪል እየተንቀሳቀሰ የስለላ ስራ እየሰራ ባለበት በቁጥጥር ስር ውሎ ተደመሰሰ::
ከብልፅግና አገዛዝ ጋር በመሰለፍ ወገኑ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው የአድማ ብተና አባልና ሻምበል አመራር የሆነው ግለሰብ በሲቪል እየተንቀሳቀሰ ንፁሃኖችን እያሳፈነና እያስረሸነ የከረመ ሲሆን ይህንኑ የተለመደ የባንዳነት ተግባሩን ለማስፈፀም በሲቪል እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወልድያ አቅራቢያ ስሪንቃ ከተማ በ11ኛ ክፍለ ጦር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበታል::
በቀጣይም ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ፀረ-አማራ ባንዳዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች ገልፀዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 3/2018 ዓ.ም
03/ዐ7/2018 ዓ.ም
አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ድል እያስመዘገበ ይገኛል‼️
መጋቢት 1/2018 ዓ.ም በነበረው የሙሉ ቀን ውጊያ የብልጽግና አሽከሩ ቅልብ ሰራዊት ወዠድንና ቆተትን ይዞ ነበር፡፡ እነዚህን ቦታዎች ሲይዝ በርካታ ወታደር በሞት፣ አስራ ሰባት ወታደር ለከባድ የአካል ጉዳት ዳርጎ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የብልጽግና ስርዓት ለየትኛውም የሰው ልጅ ህይወት ግድ አይሰጠውም ፤ ወንበሩ ይኑርለት እንጅ፡፡
በዚህ መሠረት ነበር በአማራ ሳይንት ዴንሳ የተሠማራው የአብይ ወንበር ጠባቂ ና የጀኔራል ዘውዱ ሎሌ የሆድ አደር ካድሪዎችን ወሬ አምኖ አራት ቀጠና ላይ የሰፈረው፡፡ እነዚህ ቀጠናዎችም ዴንሳ፣ወርቅ ማውጫ፣ ወዠድና ቆተት ሲሆኑ ጀግኖቹ የአትሮንስ ሻለቃ ፋኖ አባላት (ድምፅ አልባ ድሮኖች) በረቂቅ ወታደራዊ ጥበብ ከበባ ውስጥ በማስገባት ከአፈር ጋር ሲቀላቅሉት ውለዋል፡፡
በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የጠላት ሃይል በወዠድ፣ በቆተትና በመጥቅ በደንብ የተቀጠቀጠ ሲሆን በጥቅሉ ከሃያ ሶስት አስከሬን በላይ ና ከሰላሳ ሶስት በላይ ቁስለኞች ጭኖ መውጣቱን የውስጥ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ከቁስለኞቹ ውስጥ አስራ አምስቱን ወደ አማራ ሳይንት መሸኘቱ የታወቀ ሲሆን ግብስብሱ ሰራዊት ከሁለቱ ቀጠናዎች ማለትም ከቆተትና ከወዠድ እንደ ጌሾ ተከትክቶ ለቅቋል፡፡
©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
03/ዐ7/2018 ዓ.ም
ዛሬም የብልፅግናው ሰራዊት የጠዋቷን ጀንበር ከጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር ጋር አሳልፈዋል!!!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
መጋቢት 03/2018ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ በርካታ የብልፅግናው ወታደሮች በየቀኑ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለትም በርካታ የሰራዊቱ አባላት በሁሉም የአማራ አፅመ ርስቶች የሚገኙት የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂዎች የአማራ ህዝብ ነፃ አውጭ የሆነውን ጀግናው የአማራ ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ መነሻቸውን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ ደራ ጉንዶ መስቀል በማድረግ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር 3ኛ ቀስተ ንህብ ሻለቃን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መቀላቀላቸውን የከፍለጦሩ ም/የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አርበኛ ዲ/ን ያሬድ ታመነ ለኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል።
አርበኛው እንደገለፀው እራሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብሎ የሚጠራው የአማራን ህዝብ ሀብት እና ንብረት እያወደመ ህዝቡን እየጨፈጨፈ የሚገኘውን አውዳሚ ስርዓት በመቃወም ከ6ኛ ዕዝ 15ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ጋንታ 2 የመጡ በብልፅግናው አድሏዊ አሰራር ተቃውመው ክፍ ለጦራችንን ለተቀላቀሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በክፍለ ጦራችን አመራሮችና በቀስተ ንህብ ሸለቃ የፋኖ ሰራዊት ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው በመግለፅ አሁንም ባለማወቅ ከአገዛዙ ጋር ለተሰለፉ ሃይሎች የምህረት እጃችን መዘርጋቱን በማሳሰብ በውድቀት ዋዜማ ላይ ለሚገኘው አንባገነን ስርዓት ሞታቸውን የውሻ ሞት እንዳያደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
አንድነታችን አሸናፊነታችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል
አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ድል እያስመዘገበ ይገኛል::
መጋቢት 1/2018 ዓ.ም በነበረው የሙሉ ቀን ውጊያ የብልጽግና አሽከሩ ቅልብ ሰራዊት ወዠድንና ቆተትን ይዞ ነበር፡፡ እነዚህን ቦታዎች ሲይዝ በርካታ ወታደር በሞት ፣ አስራ ሰባት ወታደር ለከባድ የአካል ጉዳት ዳርጎ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የብልጽግና ስርዓት ለየትኛውም የሰው ልጅ ህይወት ግድ አይሰጠውም ፤ ወንበሩ ይኑርለት እንጅ፡፡
በዚህ መሠረት ነበር በአማራ ሳይንት ዴንሳ የተሠማራው የአብይ ወንበር ጠባቂ ና የጀኔራል ዘውዱ ሎሌ የሆድ አደር ካድሪዎችን ወሬ አምኖ አራት ቀጠና ላይ የሰፈረው፡፡ እነዚህ ቀጠናዎችም ዴንሳ፣ወርቅ ማውጫ፣ ወዠድና ቆተት ሲሆኑ ጀግኖቹ የአትሮንስ ሻለቃ ፋኖ አባላት (ድምፅ አልባ ድሮኖች) በረቂቅ ወታደራዊ ጥበብ ከበባ ውስጥ በማስገባት ከአፈር ጋር ሲቀላቅሉት ውለዋል፡፡
በዚህ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የጠላት ሃይል በወዠድ፣ በቆተትና በመጥቅ በደንብ የተቀጠቀጠ ሲሆን በጥቅሉ ከሃያ ሶስት አስከሬን በላይ ና ከሰላሳ ሶስት በላይ ቁስለኞች ጭኖ መውጣቱን የውስጥ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ከቁስለኞቹ ውስጥ አስራ አምስቱን ወደ አማራ ሳይንት መሸኘቱ የታወቀ ሲሆን ግብስብሱ ሰራዊት ከሁለቱ ቀጠናዎች ማለትም ከቆተትና ከወዠድ እንደ ጌሾ ተከትክቶ ለቅቋል፡፡
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 3/2018 ዓ.ም
