ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 363
المشتركون
+5424 ساعات
+2347 أيام
+1 43730 أيام
أرشيف المشاركات
+2
ሙሉ ቲሙ ፋኖን ተቀላቅሏል!
አዲስ ቅዳም ከተማ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ በቲም ደረጃ በመዉጣት የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር
፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃን በሰላም ተቀላቅለዋል።
በ ፲ አለቃ ቻላቸዉ ባንቲገኝ መሪነት ከጠላት ካምፕ ወጥተዉ ሻለቃችንን ከተቀላቀሉት ዉስጥ፦
1. ፲/አ ቻላቸዉ ባንቲገኝ |ችሎት
2. አንደበት ፀጋየ
3. መላኩ ሽቱ
4. ባዘዘዉ ደጀኔ
5. ደነቀዉ ካሳሁን
6. አንዳርጌ አያና
7. ሞላ ደጉ
የሚገኙ ሲሆን አፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ዋና ሰብሳቢ #ፋኖ_አንሙት_ጌታሁንን ጨምሮ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
ከእነዚህ ወንድሞቻችን ዉስጥ ፲/አ ቻላቸዉ ባንቲገኝ፣ ሞላ ደጉ እና አንደበት ፀጋየ እያንዳንዳቸዉ ሁለት ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በመያዝ በልዩ ጀብድ ሻለቃችንን ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም
ማስረሻ ሰጤ ያለህን ዝና ተጠቅመህ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊትን በማፍረስ የኛን ኃይል እንዲደራጅ አላደረክም-----"
ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም
በፎቶው የምትመለከቱት ሰው "ከፌ" ይባላል በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ተወላጅ ሲሆን የህዝባዊ ግንባሩ በጎጃም ቀጠና ፋይናስ ክፍል በመሆን ሰራዊቱ እንዲበታተን ከዲያስፖራው እና ከ360 ሚዲያ ጋር ሰፊ ስራ የሰራ ነው። በጎንቻ ጠንካራ የሚባለውን ብርጌድ በመሰነጣጠቅ ግጭቶችን በመቀስቀስ በቀጠናው የነበረውን ትግል መራራ ያደረገብን የዶላር ቀለብተኛ ነበር።በወቅቱ ውስብስብ የነበረውን ችግር ብቻችንን ጥርሳችንን ነክሰን በመታገል ቀጠናውን በማስለቀቅ በረሀ ለቀናቸዋል።
በጎንቻም በእነብሴም የነበሩ አፈንጋጭ ኃይሎች በእነብሴ በረሀ (ዞባር) ላይ በመመሸግ ከመርጡለ ማርያም(ጎጃም)መካነሰላም (ወሎ) የሚወስደውን ድልድይ ከ71ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮረኔል አዱኛው ጋር በመመሳጠር ለኮረኔሉ በቀን 50,000 ሺህ ብር በመክፈል ለ5 ወራት ቆይተዋል። ይህንን መሰረት በማድረግ በወቅቱ የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ጠንካራ ኦፕሬሽን በማድረግ መጋቢት 5 ጀምሮ በወሰደው ድርጅትን የማስጠበቅ ተልዕኮ ማስረሻ ሰጤን ጨምሮ ውጅሌዎችን በሁለት ቀናት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በመጥረግ 200 ሰራዊት ወደ እናት ብርጌዳቸው እንዲመለሱ በማድረግ ከጠላት ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ከሀዲዎችን ዳውንት ድረስ አጣድፈናቸዋል።
ቀጠናውን ተቆጣጥረን ፍተሻ ሲደረግ ከተገኙት ማስታወሻ መካከል በፎቶው የሚታየው የከፌ ይገኙበታል ። የማስታዋሻ ገጾችን አንድ በአንድ በማገላበጽ ተመልክቻቸዋለሁ ከበርካታ ገጾች መካከል በጥር ወር 2017 ዓ.ም በነበራቸው ውይይት "ማስረሻ ሰጤ ያለህን ስምና ዝና በመጠቀም የአማራ ፋኖ በጎጃምን ሰራዊት በማፍረስ የኛ ኃይል እንዲደራጅ አላደረክም ለዚህ ስራ ማስፈፀሚያ የተሰጠህ 7,000,000(ሰባት ሚሊዮን ) ብር የት እንዳደረስከው አይታወቅም የሚል ትችትን ከፌ ማቅረቡን የሚያሳይ መረጃ በራሱ የእጅ ጹሑፍ አስፍሯል። በቀጣይ ባሉት ገጾች በአንዳድ የጎጃም ቀጠና አሉ የሚሏቸውን አፈንጋጮችና ኃይል የሚያስኮበለሉትን ሰዎችና ቀጠናዎችን በመለየት በገንዘብ ለመግዛት የቀረበውንም ዝርዝር አግንተናል።
የትግሉን ተፈጥሯዊ ባህሪ በመረዳት በህዝባችን እና በሰራዊታችን ላይ የተጣበቁ ሚዝጌሮችን በወቅቱ እጅግ መራር ትግል በማድረግ መንቀል በመቻላችን የጎጃም ትግል ወጥ ሁኖ እንዲመራ ለማድረግ በአደረግነው ግብግብ እንደነዚህ ያሉ የእፍኝት ልጆች ትልቅ ዋጋ አስከፍለውናል።
የጎጃምን ቀጠና ለማወክ የተንቀሳቀሱትን ቡችላዎች በማጥዳት ቆሻሻ ገንዳ የወረወርናቸውን በማንሳት ብልፅግና ሰው ያገኘ መስሎት ጮቤ እየረገጠ ይገኛል።
ከፌ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በፈለገ ብርሀን ከተማ የ17 አመት ታዳጊ አስገድዶ በመድፈር፣በጎንቻ ሲሶ እነሴ በባርጃኖ እና አውጃ ቀበሌ ሁለት ተጨማሪ ታዳጊ ሴቶችን አስገድዶ የደፈረ መሆኑን በተጎጅ ቤተሰቦች በወቅቱ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ እና 9ኛ ክ/ጦሮች ቀርበው የከሰሱ ሲሆን ሁለት ንፁሀንን በመግደል በወንጀል የሚፈለግ ሰላቶ ነበር ።
የብልፅግና ስርዓት እንደዚህ ያሉ ነውረኞችን ከፊት በማድረግ ህዝብን ለማደናገር የሚሔድበት እርቀት ሽንፈቱን ያመነበት አጋጣሚ መሆኑን ማስገንዘብ እፈልጋለሁ።
እነዚህን ጣፊያዎችን በመታገል በጽናት የቆማችሁ አመራሮች የሰራዊት አባላትና ህዝባችን የሌቦችን ፍፃሜ በማያታችን በእጅጉ ልትኮሩ ይገባል።
አማራነት ወይም ሞት
ክብር በጀግንነት ለተሰው ጓዶች
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
+1
ገባሪው እና የቁጥቋጦው ስር ጉባኤተኛ ጭምብሉ ተገልጧል!!
በፀረ-ብልፅግና ትግሉ ውስጥ የተደበቀው አሺክላ በስርገት ትግላችንን ሲፈትነው ከቆየ በሗላ ወደ መደበቂያ ዋሻው ማምራቱ የሚጠበቅ ነው።
ጥር 2017 ዓም በጠራራ ፀሃይ ዳውንት ላይ ጉባኤውን አድርጎ የነበረው አፋህድ በእንጀራ ልጆቹ ተከድቷል።
ህዝባችን እውነተኛ የትግል መሪዎቹን እና ድርጅቱን ይጠብቅ ስንል የነበረው መሰል ሰራጊዎችን ለመከላከል መሆኑን በተደጋጋሚ አሳውቀናል።
ስለሆነም የአማራን ህዝብ ትግል ለመጥለፍ አበክረው የጠላትን አጀንዳ ሲገዙ ከነበሩት ጥቂቶቹ እንዲህ በግልፅ በህዝባችን ላይ ክህደትን ፈፅመዋል።
አፋህድ አሁንም ራሱን ይፈትሺ እና ያጠራ ዘንድ እንጠይቃለን።
አፋህድ በሰርጎ -ገቦች እና ቅጥረኛ ባንዳዎች የህልውና ትግላችን እየፈተነው ይገኛል በማለት ከዓመት በፊት ተናግረናል።
የብዙዎች ጣልቃ ገብነት በህልውና ትግሉ ላይ እንቅፋት ቢሆኑም በአይበገሬ አማራዎች መራራ ተጋድሎ እዚህ ደርሷል።
በዘመናት መራራ ተጋድሎ ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶችን አልፈናል!!
በመሰል ከሃዲዎች የሚጠለፍ ትግል ፈፅሞ አይኖረንም!!
አይበገሬው ትውልድ ያሸንፋል🙏
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ከቀጠናዉ ሃይሎች ጋር አብረን እንሰራለን ማለት ለነሱ የትሮይ ፈረስ እንሆናለን ማለት አይደለም፣ ይሄ ትርክት ባለቤትነቱ ''የፖለቲከኛ ምርኮኞች'' እየተባሉ ይጫኑ ለነበሩት ለኤህዴኖች እና ለብአዴኖች እንጅ ለአዲሱ ትዉልድ አብዮተኞች አይደለም።
አጋርነት ሲነሳ ቀድሞ ሊነሳ የሚገባዉ ነገር የትግሉን ተሸካሚወች ታማኝነት እና ገቢራዊነት ነዉ ሊሆን የሚገባዉ። የአዲሱ ትዉልድ የፋኖ መሪወች ከፖለቲካ ምርኮኞች የተለዩ ናቸዉ ብለን ካሰብን እና ከተማመንባቸዉ ለአጋርነት በር ክፍት መሆኑን በpublic discourse ማሳየት ማለት -
1. ለሃገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጭ ላሉ አካላት አማራ አግላይ ጠቅላይ ነዉ ተብሎ የተሰራበትን ትርክት ለማፍረስ ይጠቅማል።
2. ለአጋርነት እና አብሮ መስራት ፍላጎት ማሳየት በትርክት የተበረዙትንም ሆነ አዲስ ሃይል መኖሩን ለተጠራጠሩት ሃይሎች መግቢያ በሩን ማሳያ center of attention መፍጠር ማለት ነዉ።
3. በጠላት በኩል ያለዉን የፍርሃት pressure ለመጨመር ብቻ ሳይሆን አጋር አካላትም አማራጭ በር አለመኖሩን ሲያዉቁ ከጠላት ጋር ያላቸዉን መካረር እንዳይቀንሱ ለማድረግ ትልቅ የፖለቲካ ብስለት ነዉ።
4. ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች አጋርነት ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት በpublic discourse ብቻ ሊያስገኙት የሚችሉት ጥቅም ሲሆን ፣ ተግባራዊነቱ ላይ ከdiscourse በዘለለ ታማኝነት እና የፋኖ ራስ በቅነት የሚረጋገጥበት፣ የቀጠናዉን የፖለቲካ web fabric and dynamism መሰረት ያደረገ ግምገማ ተደርጎበት፣ የአሰላለፍ እና የአጋርነት strategic depths ጥናቶች እንዲሁም የሃያላን እና hostages አቋም እና ፖሊሲ ተመርምሮ ወደ ተግባር የሚገባበት የመተማመኛ ስራ ነዉ።
ጠቅለል ሲል ፋኖ ''የፖለቲካ ምርኮኞች'' ን ታሪክ እና ምግባር ተሸካሚ እና አስፈፃሚ እንዳይሆን ሆኖ በፀኑ አብዮተኞች የተገነባ የአማራወች መተማመኛ ዋስ ነዉ። ይሄ ደጋፊዉ የሚያምንበት ብቻ ሳይሆን ለመሪወች የሚሰጥም 'ቀብድ' ነዉ❗️
አዲስ ትዉልድ ፣አዲስ ተስፋ፣አዲስ አስተሳሰብ❗️
በቢቸና ከተማ በዛሬው ሌሊት 7:30 ከተባበሩት ማደያ ጎን የሕዝብ ላይብራሪ የመሸገው አድማ በትንና ሚኒሻ ላይ ጠቅል ሻለቃ ማጥቃት አካሄደ።
02/04/2018 ዓ.ም
በደብረ ማርቆስ ከተማ ለስብሰባ የተገኙ 5(አምስት) ሴት ካድሬዎች በአረመኔው ሰራዊት መደፈራቸው ታውቋል።
ታህሳስ1/2018ዓ.ም
በከፍተኛ ወታደራዊ ሽፋን እጀባ ተደርጎላቸው ለስብሰባ ደብረ ማርቆስ የተገኙ ከተለያዩ ከተሞች ከተገኙት አመራሮች መካከል አምስት የብልፅግና ፓርቲ ካድሪዎችን ጨምሮ በአረመኔው ሰራዊት መደፈራቸው ተረጋግጧል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ በጭንቀት ተወጥረው የተገኙት ካድሬዎች በተለየ እጀባ እንዲንቀሳቀሱ የተደረገ ሲሆን ይከዳሉ ተብለው የተገመቱ ካድሬዎች ቀበሌ 10 በሚገኘው 15ኛ ሻለቃ ወታደራዊ ካምፕ እንዲተኙ የተደረጉ 3 ሴት ካድሬዎች በሌሊት በአረመኔው ሰራዊት መደፈራቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በማርክላንድ ሆቴል ከነበሩት ቅምጥል ካድሬዎች መካከል በአረመኔው ሰራዊት የጦር አመራሮች ጭምር ሁለት ሴት ካድሬዎች የተደፈሩ ሲሆን በደረሰባቸው ጥቃት ተሸማቀው ወደ ስብሰባ ቦታው እንዳልገቡ ተረጋግጧል።
የአረመኔውን ስርዓት ተነጥፈው በሚያገለግሉ ባንዳዎች ላይ አገዛዙ የሚያደርሰው ክህደት የተለመደ ቢሆንም ስርዓቱን በአመራርነት በሚያገለግሉ ሴት ካድሬዎች ላይ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተፈፀመው አስገድዶ መድፈር የአረመኔው ሰራዊት ለአማራ ህዝብ ያለውን ጭካኔ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
ክብሩን ያልጠበቀ መጨረሻው ክብርን አራቁቶ መውደቅ ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአገዛዙ ጥምር ጦር በጥምረት እየከዳ ነው ።
የኮለኔሩን አጃቢ ጨምሮ ጠላት የሚተማመንባቸው አባሎቹ እየከዱ ፋኖን እየተቀበሉ ነው ።
1,ጊዜው ይርጋ መከላከያ የኮለኔር አረጋኸኝ 304ኮር ዘመቻ ሀላፊ አጃቢ የነበረ
2,ዳኛቸው ተመስገን የአድማ ብተና አባል
3,መኳንንት አበው ሰላም አስከባሪ አባል
ስማቸው ከላይ የተጠቀሱት የአረመኔው የአብይ አህመድ ሰራዊት አባላት የነበሩ ሲሆን አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ ግልፅ ጭፍጨፋ እንድናደርግ ትእዛዝ ሲሰጠን ፀረ ህዝብነቱን በመረዳት እና በአንፃሩ ፋኖ ከህዝቡ ወጥቶ ለህዝቡ እንደሚታገል ህዝቡ ራሱ ምስክር ሁኖት ስላየን ወደ ህዝብ ልጅ ፋኖ ለመቀላቀል ወስነናል ብለዋል ።
በዚህም መሰረት ከዳንግላ ከተማ በወውጣት ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦርን በይፋ ተቀላቅለዋል ።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ።
ሀብቴ ወልዴ
ወዳጄ ሀብቴ የሚገርም ስብእና ያለው ወጣት ታጋይ ነው በውትድርና ሂወትም ያለፈ የተረጋጋ ታጋይ ነው
ሀብቴ ጥፋቶች ካሉበት ቶሎ የሚታረም ለአማራ አንድነት ብዙ የደከመ እንደ ድካሙ ፍሬ ያላየ ግን አሁንም ተስፋ ሰንቆ የሚታገል ጀግና ነው
ሀብቴ በነ ዋዋ ጎቤ ሞራል የሚታገል ምርጥ አማራ ነው ብዙ ፈተናዎችንም ያለፈ ነው
እንደ አማራ አንድነት ናፋቂ ሁሉንም የአማራ ፋኖ ዋጋ እንደሚሰጥ ሰው እስኪ ስላደረከው ሁሉ እናመሰግናለን እንበለው
ይሄው ነው
አማራነት ያሸንፋል ❗️
በድል የተንበሸበሸዉ አዉደ ዉጊያ!!!
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 7ኛ ቀኑን ያስቆጠረው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ሰራዊት በበረሃ አናብስቶቹ የፋኖ ብርቱ ክንድ ተቀጥቅጦ እንደ ቅጠል ረግፏል።
በዛሬዉ እለት ማለትም በቀን 01/04/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት ድረስ ቀኑን ሙሉ በተደረገ አዉደ ዉጊያ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር የጦር ጠበብቶቹ (መሀንዲሶቹ) በወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ጌጤ አለሙ፣ ም/ወ/አዛዥ 50 አለቃ ተገኘ ደጀን፣ በዘመቻ መሪ 50 አለቃ ወተቱ ተስፉ፣ ም/ዘመቻ፣ ወታደር ቻሌ አበበ እንዲሁም የክ/ጦሩን ቃኝ እና መሃንዲስ ጦር አዛዦች እና ዘመቻዎችን ጨምሮ በየሻለቃዉ ያሉ ጦር አዛዦች እና ዘመቻዎች በሰሩት ድንቅ ጥበብ የተሞላበት ኦፕሬሽን:- ደረቅ ወንዝ፣ ፍል ዉሃ፣ ብሔራዊ ከተባሉ ቦታዎች ላይ ድንቅ ተዓምር የተባለለት ፍልሚያ ተካሂዷል።
በዚህም አዉደ ዉጊያ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
ጠላት በዙ-23 እና መካናይዝድ የታገዘ ዉጊያ ቢያደርግም የፋኖን ከባድ ምት ግን መቋቋም አልቻለም።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!!
ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
የአማራ ህዝብ እርቃኑን እንዳይቀር ...
የአማራ ህዝብ እርቃኑን አይቀር ዘንድ አርበኛ ዘመነ ካሴን ወለደ ። በዚህ ህዝብ ላይ የ 60 እና የ 70 ዓመት ፀረ አማራነት ትርክት ዲያቢሎስን በሚያስንቅ ተንኮል ጭምር የጭካኔ ክምር በትርክት ጠማቂዎች ተጫነበት ። ከዚህ ውል የለሽ ዘላለማዊ የባርነት ትብታብ እንወጣ ዘንድ የአማራ ህዝብ የነፍጥ አታጋይወንድ ልጅ ሲፈልግ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከጥቂት ቆራጥ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ተገኘ ። በወቅቱ ብልፅግናን በአፈሙዝ ለመታገል አደባባይ መውጣት ቀርቶ ማሰብ እብድ ያሰብል ነበር ። ያኔ አርበኛ ዘመነ ካሴን አብደሐል እንዴት እንደዚህ ምታስብ ያሉት ጥቂቶቹ አልነበሩም ። አርበኛው ለአማራ ህዝብ አንድያ ህይወቱን ለመስጠት ከአላማው ጋር የቆረበት ወቅት ስለነበረ በአደባባይ የቅድመ አቢዮት ስራዎችን መስራት ጀመረ ።
አርበኛው በተላያየ ጊዜ ለአዲሱ ትውልድ ታሪካዊ መልዕክቶቹን በጠላቶቹ ተከቦ ማሰማት ጀመረ ። ከመልዕክቶቹ ውስጥ ለአብነት ያክል ፦ ናዳውን ጭድ ውስጥ በመደበቅ ማሸነፍ እንደ ማንችል ፣ ያለን አማራጭ ማሸነፍ ብቻ እንደሆነ ፣ የሚያስከብረን ክንዳችን ብቻ እንደሆነ ፣ ቀኝ ፊትህን ሲመታህ ግራ አይኑን ማጥፋት እንዳለብን ፣ ህቅታየ አስካለች ድረስ ዘመነ ፋኖ አታሠልጥን አትበሉኝ ፣ ወልቃይት ላይ ከተሸነፍነ አራት ኪሎ ላይም እንሸነፋለን ፣ ጎጃም ጎንደር ወሎ ሽዋ አንድ አማራ ፣ በየ ከተማው የእሳት ኳሶችን አደራጀ መራ ፣ በማረሚያ ቤት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አማራዎችን አደራጀ መራ ፣ አማራ ምዕራብ ምስራቅ ፣ ደቡብ ሰሜን የለውም አማራ አማራ ነው ፣ አማራ ሲሏችሁ አትሸማቀቁ ፣ ካልሰለጠነ እና ካልተደራጀን መጭው ጊዜ እንደ ህዝብ መኖር እንደማያስችለን ጠቆመ ፣ ጠላት ወደ ገጠር ሲወጣ እኛ ከተማ እንገባለን በማለት በአጠቃላይ እኒህን እና መሠል የተግባር ስራዎችን በጠላት ፊት ገጥሞ በማሸነፍ የአማራን ህዝብ የመከራ እና የባርነት ትብታብ ሰባብሮ አማራነት ህያው ማንነት መሆኖኑን ድብታ ውስጥ ለነበረ ሁሉ አሳየ ። በአካል ገዝፎ ፣ አማራን ለማጥፋት ጥርሱን አግጥጦ የነበረውን የብልፅግና አሳማ ከተማ ላይ ተኩስ በመክፈት ይሄን ቅዱስ አቢዮት እንካችሁ ያለ እንክት ፣ ድርቅ ያለ ልበ ሙሉ ጀግና ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ መሆኑን አሳየ ።
በማያሻማው የራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ወርቃማ የትግል ሂደት ውስጥ ከውስጥም ከውጭም እርሱን ለመቅበር ያልተወጣ ዳገት ያልተቆፈረ ገደል አልነበረም ። አርበኛ ዘመነ ካሴ ግን ለቀባሪዎቹ ከማዘን እና ቂም ከመያዝ ይልቅ እጃቸው አፈር ነክተው ስለመቆሸሹ ብቻ ያስብ ነበር ። " የ እውነት ቤቷ እግዚአብሔር ነው " እንደሚባለው ሁሉ ያኔ የእረሱን መውደቅ ይመኙ ከነበሩት ምናምንቴዎች ውስጥ ግማሹ ፔስታል እንደበላ ላም ኮስሶ ፣ ግማሹ ፍርፋሪ ፍለጋ አረጋ ከበደ ጉልበት ስር ተደፍቶ ፣ ግማሹ ዶላሩ አልቆ እርስ በእርሱ ሲጣላ እና ሲካሰሰ ፣ ከፊሉ ግራ በመጋባት አገጩን በእጁ በመደገፍ ዋጅማ የበላ በሬ መስሎ አየተከባለለ ፣ በጣት የሚቆጠሩት ደግሞ የትግል መቅኒያቸው ፈሶ የሚኒሻ አበል እየተቀበሉ ድምቢጥ ወፍ አክለው ቲክታክ ላይ በነጠላ ዜማ እያየናቸው ተስተውለዋል ። ነገር ግን እነዛ አውነትን ትክክለኛ የዓላማ አጋር ፣ ፅናትን ምግባቸው ፣ ሰማዕታትን የትግሉ ጉልበት ፣ መሪን ተስፋ ፣ ህዝባቸውን ቤዛ እንዲሁም ተቋማቸውን መከታ ያደረጉ ከአበርኛ ዘመነ ካሴ ጎን የነበሩት ብርቱ እና ንቁ ወንድሞቹ ግን ዛሬም በነፃነት መንገድ ድላቸውን እያሰቡ በወርቃማ ብርሐን ላይ ይጓዛሉ ።
ከዚህ በፊት አማራነት መገደያ ፣ መፈናቀያ እና መታጎሪያ ኢትዮጵያ ኮድ ነበር ። ዛሬ ላይ በዝች ትንሽ የአብዮት ጉዞ እኩልነት ፣ ነፃነት እና ፍትህ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያን ሁሉ አማራነት መከበሪያ እና ማስከበሪያ ፣ መታገያ እና ማታገያ ኮድ ሁኖ ብቅ ብሏል ። ዛሬ ላይ አማራ የሚባል ብሔር የለም የሚል ልሂቅ የለም ። ዛሬ ላይ ለ አንድ ክልል ብየ ህገ-መንግስት አልቀይርም የሚል አጉራ ዘለል የለም ። ዛሬ ላይ ብሔርህ ምንድነው ሲባል አማራ ነኝ ለማለት የሚሸማቀቅ የአማራ ወጣት የለም ። ዛሬ ላይ አማራነትን በጎጥ ካባ ወሽቆ ማሰነስ አይቻልም ። ዛሬ ላይ ፋኖን አሻጋሪ እንጀ አሸባሪ የሚለው ምድራዊ ኃይል የለም ። ዛሬ ላይ የሰኔ 15 ድሪቶ ፖለቲካ የአማራን ወጣት በጎጥ መከፋፈል አይቻልም ። ዛሬ ላይ ሶስት ጥቁር ክላሽ ነው ይዘው ውርውር የሚሉ የሚለን የለም ። ስለዚህ ዛሬ ላይ የአማራ ፋኖ የምስራቅ አፍሪካ አንድ ትልቅ ተገዳዳሪ ኃይል መሆን ችሏል ።
በአጠቃላይ አማረነትን በማነወር ፣ በመወንጀል ፣ በመፈረጅ እና በመቀማት በተሰራው ፀረ-አማራነት ትርክት ራስ-ጠል አማራ ፈጥሮ እያሰቃየን ባጅቶ ነበር ። ዛሬ ላይ ራስ-በቅ ሁነን በማንነታችን ሊኖረን በሚገባ ኑባሪያው መገለጫዋች በሀሳብ ፣ በገንዘብ እና በድርጊት ተቃራኒ ሁነው የሚገኙትን ራስ-ጠል አማሮችን እስከ ምንጫቸው በማድረቅ ዘለዓለማዊ የአማራ ቤት በመስራት ላይ እንገኛለን ። በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን ድንገት አቢዮቱን ከብልፅግና ትክሻ ላይ እንዲፈርስ በህይወት ያሉም የለሉም አመራሮች እና አባላት ብዙ ውድ ዋጋ ከፍለዋል ። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ግዙፉን ድርሻ ይወስዳል ። ይሄ እንዲሆን ደግሞ የጀነራል አሳምነው ፅጌን ወርቃማ ህልም ውልፍት ሳይል የሚያሳካ አዕምሮ እና አቢዮቱን የሚሸከም ትክሻ ሲፈለግ የተገኘው ከራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ብቻ ነው ። ይሄ ደግሞ መሬት ላይ የሚታይ ሀቅ ነው ።
ለማንኛውም መልካም ህዝብ ጀግና መሪን ይፈጥራል
ጀግና መሪ ደግሞ አዲስ ጀግና ትውልዱ ይፈጥር እና ህዝቡን የተከበረ ያደርገዋል ።
አርበኛ ዘመነ ካሴ በጨለማ ዘመን ፈጣሪ ለአማራ ህዝብ የሰጠው መሪ ነው ።
ክብር እና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት !
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !
አርበኛ መምህር ግሩም ምሳሌ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ም/የፖ/መምሪያ ሃላፊ
በተራ ፕሮፓጋንዳ የማይናወጥ ሰራዊት ገንብተናል።
የአረመኔው ሰራዊት በክረመት ወራት አፍኖ ደብረ ማርቆስ ከተማ ሲያሰቃያቸው የነበሩ ወጣቶችን ከገደለ በኋላ ጥቂቶቹን የተሀድሶ ስልጠና ሰጥቻለው በሚል ትናት የለቀቃቸው ሲሆን ከጅበላ ሙተራ ሻለቃ በሴት መድፈር፣ በዝርፊያና ግድያ ወንጀሎች እርምጃ ሊወሰድባቸው ሲል ጠላትን የተቀላቀሉ አጥፊዎቹን በመጨመር 33 የጅበላ ሙተራ ሻለቃ አባላት ከድተው ተቀላቅለዋል የሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እያሰራጨ ይገኛል።
አለም አቀፍ የጦር ወንጀሎችን ጨምሮ አይኑን በጨው አጥቦ የሚያሰራጫቸውን ውሸቶች እንደ ጦርነት የሚጠቀመው አረመኔው ስርዓት ተመሳሳይ ውሸቶችን መንዛቱን ቀጥሏል ። ይህ በእንዲ እንዳለ 206ኛ ኮር በአስደናቂ ሁኔታ በሰራዊቱ ወሰስጥ የተሰገሰጉ እጆችን እየመነጠረ ሲሆን ክ/ጦሮችና የሰራዊት አባላት ጠላትን ለመደምሰስ ትዕዛዝን ብቻ እየተጠባበቁ ይገኛል።
በስሁት ምኞት እራሱን የሚያረካው የብልፅግና ካድሪ ወጣቶችን ሰብስቦ ለጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ያስረከበ ሲሆን የታሸገ ውሀ አስጨብጦ ፎቶ ካነሳቸው በኋላ ሶስቶችን ዛሬ መረሸኑ ታውቋል።
ለአላማው የታመነ ህዝባዊነትን ከራሱ ህይወት ያስቀደመ በተራ ፕሮፓጋንዳ የማይናወጥ ሰራዊት ገንብተናል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ፎቶ-1 የጅበላ ሙተራ ሻለቃ በግዳጅ ቀጠና
ፎቶ- 2 በአረመኔው ታፍነው እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል
+1
ሰበር ዜና ✊
ፋኖ ለመከላከያ የምህረት አዋጅ ማቅረቡን ተከትሎ ለሰላም የመጡትን የአገዛዙ ወታደሮች አቀባበል አደረገ‼
ሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ 35ኛ ክፍለ ጦር 5ተኛ ሬጅመንት አባላት 1እስናይፐር 1 ብሬን 3"ክላሽ በመያዝ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል!!
+2
#ክርስቲያን ታደለ ብርጌድ!!
በጎቤ ክ/ጦር ስር የምትገኘዉ በወንድማችን በክቡር አቶ ክርስቲያን ታደለ ስም የተሰየመችዉ ''ክርስቲያን ታደለ ብርጌድ'' ታላላቅ ጀብዶችን እየፈፀመች ትገኛለች።
የአቋም መግለጫ
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ
ESFNA በአርሲ ዞን ላይ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን ጭካኔ የተሞላበት ጥቃትና ግድያ በፍጹም ያወግዛል።
የ ESFNA አባላት በአርሲ ዞን ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባላት ላይ በተፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት እጅግ በጣም አዝነናል፣ እጅግም ደንግጠናል። ንጹሐን ዜጎች በእምነታቸው ምክንያት ሆን ተብሎ የደረሰባቸው ኢሰብአዊ ጭፍጨፋና ግድያ ሊታሰብ የማይቻልና ልብን የሚሰብር ድርጊት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለዘመናት የቆየውን የአብሮነት እና የሃይማኖት መቻቻል ባህልና ልምድ የሚሰብር ነው።
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለሦስቱም አብርሐማዊ ሃይማኖቶች፡ ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድ መንፈሳዊ መኖሪያ ቤት ሆና ቆይታለች። ኢትዮጵያ ከትውልድ አገራቸው ስደትና በደል ሲደርስባቸው ለመጀመሪያዎቹ የእስልምና ተከታዮች መሸሸጊያ የሰጠች አገር ናት። ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለሺህ ዓመታት በላይ እንደ ታሪኳ፣ ባህሏ እና የሞራል መሠረቷ ማዕዘን ድንጋይ አድርጋ ያቆየች አገር ናት። የአገራችን ታላቅነት በዚህ ዘላቂ በሆነው የሃይማኖትና የብሄረሰብ ልዩነቶችን በአንድ ሰንደቅ ስር የማስተናገድ ችሎታና ልበ ሰፊነት ላይ የተመሠረተ ነው።
ESFNA ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በአንድ ድንኳን ስር ለማሰባሰብ የተፈጠረ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፣ ይህንን አሰቃቂና አረመኔያዊ ወንጀል በጥብቅ ያወግዛል። በማንኛውም ሃይማኖታዊ ወይም ብሄረሰብ ቡድን ላይ የሚፈጸም ጥቃት በራሷ በኢትዮጵያ ላይና፣ እንደ ህዝብ በምንጋራቸው የጋራ እሴቶች ላይ እንደደረስ ጥቃት አድርገን ነው የምናየው።
ወንጀለኞቹን ፈጣን እና ወሳኝ በሆነ መንገድ ለፍርድ እንዲያቀርቡ ለባለሥልጣኖች አሰቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን። እንደዚህ ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶችን እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ መቅረት አለበት። የፍትህ መዘግየት የፍትህ እጦት ነው።
በዚህ አስከፊ ግዜ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ከሁሉም እምነትና የፓለቲካ አስተሳሰብ፣ የጥላቻና የበቀል ስሜትን እንዲቋቋሙ ሰጥብቀን እናሳስባለን። ወገኖቻችን ከአምላክ በተሰጣቸው መብት መሰረት ፈጣሪን ሲያወድሱ፣ ጥቃት ሲደርስብቸው ዝም ብለን ማየት አንችልም። ዛሬ እንደ ህዝብ፣ እንደ ሐይማኖታችንና ዝንባሌአችን በፀሎትና በምልጃ ወደ ፈጣሪ በአነእድነት የምንቀርብበት ሰአት ነው።
የነዚህ በከንቱ የፈሰሰው የንጹሐን ደም፣ ወደ በለጠ አንድነት እንጂ ወደ መከፋፈል እንዳይወስደን፣ በህብረታችን ለነሱ ሞት የከበረ ዋጋ እንሰጣለን። ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ በሰላም የሚኖርባት፣ የሚፀልይባትና የሚያልምባት አገር እንድትሆን ጽኑ ምኞትና ፀሎታችን ነው።
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA)
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ዙ23 ማራኪዎቹ ካላኮርማ ክፍለጦር የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ::
ጠላትን በደፈጣ ጥቃት እና በሽምቅ የመምታቱ ረፍት የመንሳቱና የማማረሩ ብሎም የማፍረሱ ተጋድሎ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ ቃኝ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ውድመን የተባለ ቦታ በሁለት ኦራል እና በአንድ ፓትሮል ይንቀሳቀስ የነበረ ጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከዘመቻ አባ ናደው ማግስት በርካታ እግረኛ ሰራዊት ወደ ቤተ-አማራ ያስገባ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህ አራዊት ሰራዊቱን ምኒልክ ዕዝ በየ ቀጠናው እንዲገባ ካደረገው በኋላ በሁሉም ቀጠና ያለ ሰራዊቱ በደፈጣ ጥቃት ጠላትን እየመታ እረፍት እየነሳና ተረጋግቶ እንዳይቀመጥ ብሎም እየተመረረ እንዲኮበልል በማድረግ ማጥቃት ቀርቶ ተረጋግቶ እንዳይከላከል አድርጎታል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ምኒልክ ዕዝ በቂ ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረጉንና ለአዲስ ትልቅ ድል መዘጋጀቱን ያወቀው ጠላት ከተለያዩ አካባቢዎች መካናይዝድ እና አንዳንድ ንብረቶችን በማሸሽ ላይ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
