ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 208
المشتركون
+18224 ساعات
+2627 أيام
+63730 أيام
أرشيف المشاركات
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር የሚገኘው 71ኛ ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸው 4ኛ ዙር ምልምል ልዩ ኮማንዶዎችን ትናንት ሚያዚያ 13/2018 ዓ/ም በታላቅ ድምቀት ተመርቀዋል።
በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የኮርና የክፍለጦር እንዲሁም የሬጅመንት አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች የተገኙ ሲሆን፡ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት የሚያስከብር፣ የአማራን ሕልውና የሚታደግ እንዲሁም ፍትሕ ርትዕ የሚያሰፍን ብቁና ንቁ የፋኖ ኃይል መገንባቱን ታዳሚው ተመራቂዎቹ ካሳዩት ትርኢት አረጋግጧል።
ክፍለጦሩ በየቀኑ ከሚያደርገው ውጊያ ጎን ለጎን ያልተቋረጠ የስልጠና መርሃ ግብር በማካሄድ የጠላትን ቅስም የሚሰብር ብቁና እጅግ ጠንካራ ኃይል ማፍራቱን አጠናክሮ እንደሚቀል አሳውቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ታጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም
በፍርሀት እየተናወጠው ያለው የአብይ አህመድ ሰራዊት የንፁሀን ህይወት መድፍ በመተኮስ ቀጠፈ
========================
ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም.
የፋኖን ብትር መቋቋም ያቃተው የብልፅግና ሰራዊት በዛሬው እለት ፋኖ ከተማ ሊገባ ነው በማለት በፍርሀት ተውጦ በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ደ/ገነት ቀበሌ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ምንም የጥይት ጩኸት በሌለበት ሁኔታ ቀበሌወችን በመድፍ በመደብደብ ንጹኃን ለይ በመተኮስ በማህበር ተሰብስበው በቤት ስራ ላይ የተሰማሩ አ/አርሶአደሮች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት በመቅጠፍ 2 ሰዎችን ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
ህይወቱ ያለፈው ይታያው ክንዴ የተባለ አ/አደር ሲሆን .ተሜ አያሌው እና.አበዛ ከበደ የተባሉት ከባድ ቁስለኛ ናቸው
ስር ዓቱ አማራ ጠል ነው የምንለው በምክኒያት ነው ይኸ ነው ሀገር አስጠብቃለሁ የሚለው የአብይ ሰራዊት ንፁሀንን በከባድ መሳሪያ ህይወት እየቀጠፈ ያለ።
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
"ምኒልክዊያን ዘሎ የገባውን እብሪተኛ ሃይል፣
ዘሎ መዉጣት ነውር ነው እያሉት ነው፣
በሚገባው ቋቋ!!''
"የአሳምነው ልጅ አያውቅም ለቅሦ፣
ማጋደም እንጅ አንድ ተኩሦ ፣
ጠላትን መገንደስ እጅ አይታሰብም ለቅሦ፣
"ምሥራቆቹ ከትላንት የቀጠለው ተጋድሎ ዛሬም ጥላትን በእዚህ መልኩ አጋድመውታል 💪
"ማውራት እና መስራት ይለያያል አመት እስከ አመት አማራን ከፍ አድርገው እያስጠሩት ያሉት ምስራቆቹን መጮህ እንጅ መንካት አይቻልም እያልኩህ ነው 👊
ይልቅ ተኩስ 💪
+2
ሁለት የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባላት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!
ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 46ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በተለያዩ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአገዛዙን የጥፋት መንገድ በመቃወም ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው የምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 15ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የክፍለ ጦሩ አመራሮችም ለአባላቱ ጥሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የፋሽስቱን አገዛዝ በመቃወም ፋኖን የተቀላቀሉት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፡-
ደስታው ይመር - በሰው ሃብት አስተዳደር ሀላፊነት ሲያገለግል የነበረ
አማረ ደጉ - በህግ ክፍል ሲያገለግል የነበረ
እነዚህ የሰራዊቱ አባላት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ጮቢ በር ተመድበው የነበሩ ሲሆን፣ ከዛ ተነስተው በራያ ቆቦ 041 ቀበሌ አማያ በመግባት ለምኒልክ ዕዝ እጃቸውን ሰጥተዋል።
አባላቱ በሰጡት ቃል "ወታደር የህዝብ ዘብ መሆን ሲገባው በተቃራኒው ህዝብን የሚደበድብ እና የሚያሰቃይ ሆኗል" በማለት አገዛዙን የካዱበትን ምክንያት ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የምኒልክ ዕዝ ጀግኖች በሸወይ፣ በጨፌ መንደር እንዲሁም በአምድ አንባ አቅጣጫ ጥቃት ለመክፈት የመጣውን የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሙትና ቁስለኛ አድርገው መልሰውታል። ከዚህ ወታደራዊ እርምጃ ጎን ለጎንም በጠላት ሰራዊት ላይ ሰፊ የማሳመን ስራ በመስራት የታችኛውን የሰራዊት መዋቅር የማፍረስ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
101ኛ ኮር 15ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
አርበኛ ክብሮም ከበደ
ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም
የጀነራል አሳምነው ልጅ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ትናንት እና ዛሬ!!!
አማራ የጀግኖች አውድማ የነፃነት መከታ መሆኑ የታሪክ እውነታ ነው። ይህንን እውነታ በደሙና በዕውቀቱ ያረጋገጠው ደግሞ ከታሪካዊው የሚኒሊክ ሰፈር ከጋዲሎ ምድር የበቀለው አርበኛው ኢሳያስ ደመቀ ነው። እርሱ ገና ለጋነቱን በጋዲሎ ተራሮች ላይ ሲያሳልፍ በውስጡ የሚመላለሰው አንድ ትልቅ ራዕይ ነበር የአማራን ህዝብ ህልውና በፅኑ መሰረት ላይ ማቆም እና የአንድነት መሃንዲስ መውሰድ ነው።
የአርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ትልቁ ጀግንነት የሚጀምረው ከመሳሪያው በፊት በበሰለ አስተሳሰቡ ነው። የአማራ ትግል ዛሬ ላለበት ከፍታ እንዲበቃ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል በተለይም በሸዋ ምድር የሚንቀሳቀሱት ሁለቱ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅ ሆነው፣ በአንድ ዓላማ እንዲሰለፉ በማድረግ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ወስዷል። ልዩነት ለጠላት ይመቻል አንድነት ግን ለነፃነት ያበቃል የሚለው መርሁ ዛሬ በሸዋ ምድር ለሚታየው ብረት ነክ ኃይል ዋነኛ ማገዶ ሆኗል።
የግንባር ውሎ ከዲሽቃው ጀርባ የጦር ሜዳው በጭስና በባሩድ ሲታጠን ኢሳያስ በመሪነት ትእዛዝ በመስጠት ብቻ አይወሰንም። በትከሻው ላይ ያንገተውን እስናይፐሩን አቅንቶ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት የሚጋፈጥ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የዲሽቃው ድምፅ በሸዋ ተራሮች ላይ ሲያስተጋባ ጠላት ይርዳል ደፋርና ቆራጥ የሆኑት የፋኖ አባላት ደግሞ ወኔያቸው ይታደሳል። እኔን ቀድማችሁ አትለፉ፤ እኔን ከሞትኩኝ ነው ለህዝባችሁ የምትሞቱት! የሚለው የኢሳያስ ቃል በእያንዳንዱ ተዋጊ ልብ ውስጥ እንደ አረንጓዴ ቢጫ ቀዬ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ይውለበለባል።
የአንደበተ ርቱዕነቱ ጥበብ ከአውደ ውጊያው መልስ ደግሞ አርበኛ ኢሳያስ መድረክ ላይ ይቆማል። እዚያ ላይ ስመ-ጥሩና የሚገራርሙ ቃላትን እየመረጠ ሲናገር ንግግሩ የብዙዎችን ልብ ይገዛል። ለአንድዬ ነፍሴን ለህዝቤ የሚለው ፅኑ እምነቱ የዛሬው የሸዋ አንበሳ ነገም የአማራን የመኖር ነፃነት የሚያበስር መሆኑን ማሳያ ነው።የነገው የአናብስቱ ስብስብ ዛሬ በሸዋ ምድር የሚታየው ይህ ጀግና ነገ ከሶስቱም ማዕዘናት ከበላይ፣ ከቴዎድሮስና ከሚኒሊክ አናብስቶች ጋር በመሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን በድል ጎዳና እንደሚመራ ጥርጥር የለውም።
አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ማለት ለጠላት የማይበገር ብረት ለወገኑ ደግሞ የነፃነት ጮራና የመከታ ጋሻ ነው። የዘመኑ የታሪክ አሻራ በዕውቀት የታነጸ፣ በአመለካከት የላቀ እና በተግባር የተፈተነ ጀግና። የሸዋው አንበሳ ዛሬም በጽናት ቆሟል የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ፣ የነፃነትን ጎህ ለመቅደድ ግንባር ቀደመ ከሚወሰዱት የአማራ ልጆች አንዱና ዋነኛው አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ
ወንድሜ መከታዬ ሁሌም የምታምነው ገብርኤል እንዲጠብቅህ ፀሎቴ ነው!! Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር
የአርበኛ ኤፍሬም ተሾመ አጭር የህይወት ታሪክ
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በቆራጥ ልጆቹ ደም የሚፃፍ የታሪክ መዝገብ ነው። በዚህ መዝገብ ውስጥ ስማቸው በደመቀ ቀለም ከሚሰፍሩ ጀግኖች መካከል አንዱ በለጋነት ዕድሜው ለህዝብ ህልውና መረጋገጥ መሥዋዕትነትን ያስቀደመው አርበኛ ኤፍሬም ተሾመ ነው። አርበኛ ኤፍሬም ማለት የቃሉ ታማኝ የክብር ዘበኛ እና ለነፃነት የሚከፈልን ዋጋ በተግባር ያስመሰከረ የዚህ ትውልድ ኩራት ነው።
አርበኛ ኤፍሬም ተሾመ ሰኔ 19 ቀን 1993 ዓ.ም በሸዋ ምድር በማጀቴ ገምዛ ወረዳ ልዩ ስሙ "መሀል ሳሊማኖ" በሚባለው አካባቢ ከአባቱ ከአቶ ተሾመ ጋሻው እና ከእናቱ ከወይዘሮ በላይ ተስፋዬ ተወለደ። በቤተሰቡ ውስጥ በልዩ እንክብካቤ እና በስነ-ምግባር ታንጾ ያደገው ኤፍሬም ከልጅነቱ ጀምሮ ለወገኑና ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር እያሳየ አድጓል።
አርበኛ ኤፍሬም ተሾመ መሠረታዊ ትምህርቱን በማጀቴ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ተከታትሎ አጠናቋል። በመቀጠልም በማጀቴ ሀይስኩል ከ9ኛ-10ኛ ክፍል ያለውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቋል። የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት በጠበቀው መልኩ ባይመጣለትም ተስፋ ሳይቆርጥ የአባቱን ፈለግ በመከተል የሙያ ብቃቱን ለማሳደግ በመወሰን ወደ መንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋም በመግባት በሹፍርና ሙያ ብቁ ሆኖ ወጣ። በዚህም ሙያው ተሰማርቶ ህይወቱንና ቤተሰቡን ሲረዳ ቆይቷል። ከሹፍርናው ጎን ለጎን ደግሞ በሞባይል ጥገና ሙያ ከፍተኛ ክህሎት የነበረው ሲሆን በታታሪነቱና በትህትናው በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ የተወደደ ወጣት ነበር።
አርበኛ ኤፍሬም ለአቅመ አዳም ሲደርስ በሀገር ባህልና ወግ መሠረት ከወይዘሪት ሰላም ይርጋ ጋር ትዳር መሠረተ። በትዳር ህይወቱም ታማኝ የሰው ልጅ አክባሪ አምላኩን ፈሪ እና ለቤተሰቡ ተቆርቋሪ የነበረ ሲሆን የነገ ተስፋ የሆነች የአንድ ሴት ልጅ አባትም ነበር።
በ2014 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ የተረዳው የያኔው ብላቴና ኤፍሬም ተሾመ የግል ኑሮውንና ቤተሰባዊ ምቾቱን ወደ ጎን በመተው "የአማራ ሕዝብ በማንነምቱ እይጠፋ ሳለ የእኔ መኖሬ ትርጉም አይኖረውም" በሚል ጽኑ እምነት ወደ ፋኖ ማሰልጠኛ ተቋም ገባ።
በዚህም በማጀቴ ፋኖ ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ ወታደራዊ የአካል ብቃት እና ፖለቲካዊ ስልጠናዎችን በልዩ ብቃት አጠናቋል። በዚህ ሂደት ውስጥ እንደ አርበኛ አሰግድ መኮንን፣ አርበኛ 50 አለቃ እንግዳ አዘነ፣ አርበኛ 50 አለቃ እሸቱ ቸርነት እና አርበኛ ሻምበል ሽታው መኮንን ካሉ አንጋፋ አመራሮች ጋር በትከሻ በመሰለፍ ወታደራዊ ስልጠናውን በብቃት አጠናቋል።
በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያውን የፋኖ ሰራዊት ወታደራዊ ግዳጅ በእግረኛ ተዋጊነት በተለያዩ የጦር ግንባሮች የጠላትን ሴራ ሲያከሽፍ ቆይቷል። ነሃሴ 2015 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ ላይ በመቶ መሪነት ተመድቦ የጠላትን ምሽግ በመስበር ተወዳዳሪ የሌለው ጀግንነቱን በተግባር አስመስክሯል። በዚህ አውደ ውጊያ ላይ ባሳየው ጀብድ የልዩ ዘመቻ መሪ እስከመሆን የደረሰ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን በሹፍርና ሙያው የፋኖ ሰራዊቱንና አመራሩን በአስቸጋሪ ቦታዎች ሁሉ በፍጥነትና በጥንቃቄ በማድረስ "አሞራው" የሚል የቅጽል ስም ተሰጥቶታል። ከዚህም በተጨማሪ የአርበኛ አሰግድ መኮንን የቅርብ አጃቢ ሆኖ በታማኝነት አገልግሏል።
አርበኛ ኤፍሬም ተሾመ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ፣ የአፄ ዘርያእቆብ ኮር፣ የአፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር አባል በመሆን ለአራት ዓመታት ያህል በተለያዩ የኃላፊነት ድርሻዎች ያለመታከት ሲያገለግል ቆይቶ ሚያዚያ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከሀገር ጠላት ጋር አንገት ለአንገት በተናነቀበት መራር አውደ ውጊያ ላይ ብርቱ ክንዱን የጠላት ኃይል ላይ ካሳረገፈ በኋላ በተተኮሰች ጥይት ተመቶ በተወለደ በ25 ዓመቱ ውድ ህይወቱን ለወገኑ ነፃነት መሥዋዕት አድርጓል።
የጀግናው አርበኛ የቀብር ሥነ-ሥርዓትም ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በማጀቴ ኮበኮብ ጽብኃ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮት ፣ የፋኖ ሰራዊት አባላት ፣ ወላጆቹ፣ ጓዶቹና የአካባቢው ህዝብ በተገኘበት በክብር ተፈጽሟል።
አርበኛ ኤፍሬም በአካል ቢለየንም የከፈለው መሥዋዕትነት ግን የነፃነት ችቦ ሆኖ ለትውዱ ሲያበራ ይኖራል። በየትግል ሜዳው የምናጣቸው ጓዶቻችን የውድቀታችን ምልክት ሳይሆኑ ለነፃነት የሚከፈሉ የክብር እዳዎች ሆነው የሚኑሮ ሲሆኑ አርበኛ ኤፍሬም ተሾመም በደሙ የፃፈው ታሪክ ለሚቀጥለው ትውልድ ስንቅ ለጠላት ደግሞ የሽንፈት ማኅተም ሆኖ በታሪክ ምዕራፍ ለትውልድ ሲዘከር ይኖራል።
ለጀግናው አርበኛ ኤፍሬም ተሾመ ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ!
ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑረው!
አርበኛ ሲራክ ሹመቴ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የባህል እና መዝናኛ ተጠሪ
ከአንደበቱ ክፉ ቃል የማይወጣው ጀግና፤ የተግባር ሰው፤ ትንሹ ገብርዬ ነበር። በትናንትናው ዕለት የክብር መስወዕት የተቀበለው ይህ ጀግና፣ ከአባቱ ጀግንነትንና ታማኝነትን የወረሰው ባለአደራው አርበኛ አንደበት ክንዳለም ይህ ነው፡፡
ድምጸዊ ፋሲል ደመወዝ፤
‹‹ጋይንት ላይ ተወልደህ የፈራህ እንደሆን፤
ወገራ ተወልደህ የፈራህ እንደሆን፤
እናቱን ጠይቋት ሽል ቀይራ እንዳይሆን›› ሲል የተቀኘው ለእንደዚህ አይነቱ ጀግንነትን በደም ከቤተሰቡ የወረሰውን አንደበት ክንዳለምን የመሠለውን ጀግና ለመግላጽ ነው፡፡ ከአባቱ የጀግንነትና የታማኝነት ዲኤንኤ የወረሰው አርበኛ አንደበት ክንዳለም፤ ትናንት የክብር መስዋዕትነትን የተቀበለው እንዴት ነው? የሚለውን ሂደቱን በአጭሩ እንገልጻለን፡፡
ከቀኖች ሁሉ የተለዬ መጥፎ እና ልዩ መልከም የሚባል ቀን ባይኖርም፤ ልክ እንደየካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ሁሉ፤ ወይም እንደ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለት፤ ወይም እንደ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ፣ ጋሽ ስመኘው መብራቱ፣ ሜጄር ጄኔራል ውባንተ አባተ፤ አርበኛ ምህረት አሳዬንና እልፍ ጀግኖችን እንደተነጠቅንባቸው ዕለቱት ሁሉ፤ የትናንቷ ዕለትም የቀን ጎደሎ ልንላት እንችላለን፡፡ ከቀን ብቻ አይደለም አንዳንድ ወሮች ጭምር ልብ ሰባሪዎች ናቸው። ትናንት ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም ከንፋስ መውጫ ከተማ ወደ ሳሊ እንቅስቃሴ ያደረገውን የጠላት ኃይል፤ ክፍለ ጦሩን ይዞ አይቀጡ ቅጣት ይቀጣው ጀመር። በዚህ ምት በከፍተኛ ሁኔታ የተደናገጠና የፈረሰው የጠላት ሠራዊት፤ ሳሊ ላይ ከፊት ለፊቱ ያገኘውን ንፁሀን ሁሉ እየረሸነ ወደ ንፋስ መውጫ ይፈረጥጥ ነበር።
የዚህ ምሽግ ሰባሪው ሠራዊት ደግሞ በቀጥታ ሲመራ የነበረው፤ በልበ ደንዳነው አርበኛ አንደበት ክንዳለም ነበር። ቀደም ሲል እንደገለጽነው ምርኮ የግሉ ነው። በትናንቱ ውጊየም፤ ኦራል ሙሉ ሎጅስቲክስ ጨምሮ በርካታ ኃይሉ ተተኳሹ፣ መሳርያና ሎጅስቲክሱን በመማረክ፤ የብልጽግናን ጨካኝ ሠራዊት አርቃኑን ማስቀረት ተችሎ ነበር ።
ልበ ሙሉው አንደበት በለመደው አልበገር ባይነቱ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኃላ የማያቀው፤ ለአጃቢዎችም ይሁን አብረውት ላሉት ጓዶች ተመለስ ተብሎ የሚመለስ ተዋጊ አልነበረም፡፡ ሲበዛ ትንታግ የጠላት እራስ ምታት ነበር። ታዲያ ጠላት ነቅሎ በሚፈረጥጥበት ቅጽበት፤ የቀን ጎደሎ ነውና ከጠላት በተተኮሰች ጥይት ሳሊ ላይ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም በተወለደ በ24 ዓመቱ በጀግንነት የአባቶቹን ቃል አክብሮ ተሰውቷል።
ጀግና ይሞታል ትግል ይቀጥላል፡፡ የአባቱን እና የወንድሞቹን ትግል ታምኖ አያሌ ጀብዱዎችን ፈጽሞ ለአማራ ህዝብ ክብርና ህልውና ሲል አንድያ ነፍሱን የሰጠውን ወንድማችንን ራዕይ እና ዓላማ፤ እኛም አስቀጥለን ታሪክህን በደማቁ እንጽፋለን፡፡
ጀግና ሞቱ የጀግንነት ነው! ትግልህን እንጠብቃለን! ቃልህንም እናከብራለ! ነፍስህን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን!!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር !!!
ጎንደር ፤አማራ፤ኢትዮጵያ
ከአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር በጀግናውና ልበሙሉው ፋኖ ሻለቃ አንደበት ክንዳለም የክብር መዋዕነት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ !!!
‹‹ጋይንት ላይ ተወልደህ የፈራህ እንደሆን፤
ወገራ ተወልደህ የፈራህ እንደሆን፤
እናቱን ጠይቋት ሽል ቀይራ እንዳይሆን›› ድምጸዊ ፋሲል ደመወዝ
አርበኛ አንደበት ክንዳለም፤ በ1994 ዓ.ም ከአባቱ ሻለቃ ክንዳለም ዓለምነው እና ከእናቱ ከወ/ሮ ተስፋነሽ አረጋ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ጋይንት አውራጃ ይትበሀ ገብርኤል ልዩ ስሟ አሳኔ ጎጥ ተወለደ። እንደማንኛም አማራዊ ልጅ ያደገው አንደበት ክንዳለም፤ እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ክፍል አቃቤት ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ6ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ዳሞት ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 8ኛ ክፍል ይትበሀ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 9ኛ ክፍል ንፋስ መውጫ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።
አንደበት ክንዳለም በአባቱ እና በአማራ ህዝብ ላይ ስርዓቱ በሚያደርስበት ግፍና በደል ምክንያት፤ ለሀገር እና ለህዝብ ካለው ፍቅር የተነሳ ነበር ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አገር መከላከያ ተቋም 2013 ዓ.ም ተቀላቅሎ አገሩን ለማገልገል የወሰነው። ነገር ግን እንዳሰበው ያልሆነለት አንደበት ክንዳለም አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየሰራው ባለው ግፍ ተማሮ፤ በአማራነት መደራጀትን መርጦ ወደ ተወለደበት ጋይንት ተመልሶ ከአባቱ ጎን ሌላኛውን የትግል ጉዞ የጀመረ ነበልባል ነበር።
ከልጅነቱ ጀምሮ ትግልን አብሮት አድጓል። የልጅ አዋቂ ነው። ለእውነት የታገለ፣ ለእውነት የተሰዋ። ሌቦችን አብዝቶ ይጠየፋል። በጦሩ ተወዳጅ ለማህበረሰቡ አዛኝና የአባቱ ምትክ ነው ሲሉ የሚሳሱለት ሲበዛ ልበ ደንዳና ተዋጊ ነበር አንደበት ክንዳለም።
ከልጅነቱ የአባቱን ፈለግ ተከትሎ አማራነትን ለማጥፋት መሀሉን ዳር ያደረገው የዐቢይ አህመድን ጨካኝና ዘረኛ ሥርዓት ያለምንም የእድሜ፣ የፆታና የሀይማኖት ልዩነት በአማራነታቸው ብቻ ሲጨፈጨፍ ለተመለከተው አንደበት ክንዳለም፤ የእግር እሳት ሆኖበታል ። አባቱ ክንዳለም ዓለምነው በጀኔራል አሳምነው ጽጌ መሪነትና አስተባባሪነት፤ አማራን ለማስከበር ከነሻለቃ አስቻለው ደሴ፣ ከነሻለቃ ጥጋብ ተፈራ፣ ከነሻለቃ የሽዋስ አሰፋ፣ ከነሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ እና ሌሎች የአማራ ውድ ልጆች ጋር በመሆን፤ በአጣዬ፣ ኬሚሴ፣ መተከል ዘምቷሌ ተዋግቷል አዋግቷል። በዚህም የአማራን ሞት መቀነስ የቻለ የህዝብ ባለውለታ ነበር፡፡
ከኋላም ጭምብል አጥላቂዎቹ አማራዎች፤ ‹‹ባጎረስኩ ተነከስኩ›› የሆነበት ክንዳለም ዓለምነው፤ የአማራ ሕዝብ ልጅ የሆኑትን ሁሉ ማሳደድን የፖለቲካ ግቡ ያረገው ብአዴንም፤ አርበኛ ክንዳለም ዓለምነውን ወደ ጋይንት እስር ቤት እንዲገባ አደረገው። ጀግና የማይጠፋበት የጋይንት ምድር፤ በነሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴና በራሱ በልጁ አንደበት ክንዳለም ድንቅ ኦፕሬሽን፤ ከእስር ቤት እንዲወጣ አደርገውት፤ ወደ ጠነሰሰው የትግል ሜዳ እንዲመለስ አደረጉት፡፡
ሻለቃ ክንዳለም ዓለምነው ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ህውሓት ‹‹ከአማራ ጋር የማወራርደው ሒሳብ አለኝ›› ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት፤ እብናት፣ ዳውንት፣ ወገል ጤና፣ ጋሸና ፣ አበርገሌ፣ ቅራሪ ወንዝ ከወንድሞቹ ከነዘማች ሞላ፣ ከነሜጀር ጀኔራል ከፍያለው ደሴ፣ ከነጀኔራል ውባንተ አባተ፣ ከነ ራስ አርበኛ ደረጀ በላይ እና በርካታ የአማራ ሕዝብ ውድ ልጆች ጋር ተሰልፎ የተዋጋ ያዋጋ ጀግና ነበር።
በህወሓት ውጊያ ሰዓት ሻለቃ ክንዳለም ዓለምነው በውድ ወንድሙ እና የትግል አጋሩ ስም የሰየማትን አስቻለው ደሴ ሻለቃ በመመስረት፤ አያሌ ጀብድ ሰርቶበታል። ሻለቃ ክንዳለም ዓለምነው ከህወሓት ውጊያ መልስ፤ ሻለቀዋን ወደ ብርጌድ በማሳደግ ሻለቃ አስቻለው ደሴ ብርጌድን ከሌላኛው የትግል ጓዱ፣ የአፍሪካ ህብረቱ ሠላም አስከባሪው ኮኮብ፣ የወታደራዊ ሳይንስ ሊቁ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ ጋር በመሆን፤ ጠንካራ መዋቅር ሲፈጠር አንደበት አብሮ መስራች ነበር።
ኤሳውና ያዕቆብ በአንድ ማህጸን ጀምሮ ሲገፋፉ እንደነበረውና በኋላም ኤሳው ብኩርናውን በምሥር ወጥ እንደሸጠው ሁሉ፤ አርበኛ ክንዳለም ዓለምነው ከልጆቹ ጊዜውርቅ ክንዳለምና አንደበት ክንዳለም ጋር ለአማራ ህዝብ ክብር ሲዋደቅ፤ ከብልጽግግና ድርጎ ጠባቂ ባንዳዎች አርበኞቹን አስከበቧቸው፡፡ ከፍተኛ ሀይል ይዞ ከከበባቸው የጠላት ሀይል ጋር ብርቱ ትንቅንቅ ሲያደርጉ የዋሉት፤ አባት ሻለቃ ክንዳለም ዓለምነውና ታናሹ ልጅ አርበኛ ጊዜወርቅ ክንዳለም፤ በጀግንነት ወደቁ፡፡ ዕለቱም የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር፡፡ መከራ ያበረታው፣ ጀብድም መጽናኛው የሆነው ጀገናው እና ልበ ደንዳናው አንደበት ክንዳለም ደግሞ፤ በጀግነነት ምሽጎችንን ሰባብሮ፤ የወንድሙንና የአባቱን ጠላቶች ረፍርፎ፤ በጀግንነት ከከበባው ወጣ።
አባቱ ሻለቃ ክንዳለም ዓለምየነው ከተሰዋ በኋላ፤ ራሱን ለማጽናናት እና የአባቱን ራዕይ ለማስቀጠል፤ ኃይል የማሰባሰብ ስራ ላይ ባለበት ሰዓት፤ በአገዛዙ ገዳይ ቡድን እጅ ስር በመውደቁ እንዲረሸን በወረደበት ትዕዛዝ መሰረት እስር ቤት ገባ። መከራ ያልበገረው አንደበት ግን ስራውን አልፈታም ነበር። እስር ቤት እያለም የጠላትን ቁመና ሲገመግምና የአባቱን ትግል ስለሚያስቀጥልበት የትግል መስመር ያወጣና ያወርድ ነበር።
በዚያ የእስር ቤት ቆይታው ልክ እንደ አባቱ ምትክ እሚያየው እና ከአባቱ ጎን ተሰልፎ ዋጋ የከፈለው ሻለቃ መንግስት፤ እስር ቤት ካለው አንደበት ክንዳለም ጋር በመመካከር፤ ጦር ሰብስቦ በወንድሙ ስም በሻለቃ ክንዳለም ዓለምነው ስም ክንዳለም ሻለቃ ብሎ መስርቶ ያዋጋ ጀመር።
አንደበት መከራን እና ስቃይን ገና ከልጅነት ተለማምዶት የገባበትን እስር ቤት በመስበር ወደ ትግል ሜዳው ሲመለስ፤ በአባቱ ስም የተሰየመችውን ሻለቃ እንዲመራ በኃላፊነት ይመራት የነበረው አጎቱ ሻለቃ መንግስት ዓለምነው፤ ኃላፊነቱን እንዲረከበውና የአባቱን አደራ እንዲወጣ ሲያስረክበው፤ በልበ ሙሉነት ስለሚያምንበት ነበር።
ጀግናው አንደበት ክንዳለም ያባቱ ልጅ ነውና በገባበት አውደ ውጊያ ሁሉ ምርኮ፣ በጠላት ላይ አያሌ ጀብዶችን ተቀዳጅቶ መውጣት የቀን ተቀን ስራው ሆነ። አንደበት በአባቱ ስም የተሰየመችውን ሻለቃ ይዞ የአንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር ሲመሰረት ከፍተኛ ተሳትፎ ነበረው፡፡
አንደበት በትግል ጠላፊዎች ከትግሉ ራሱን እንዲያገልና ከትግል እንዲወጣ ያልሞከሩት ሴራም ክፋትም አልነበረም። ‹‹አባቴ ወንድሜና ሌሎች የትግል ወንድሞቼና አጋሮቼ ለአማራነት ሲሉ አንድያ ነፍሳቸውን ለሰጡለት ትግል፤ እስከመጨረሻው ታምኜ እዘልቃለው›› ሲልም አሳፍሯቸው የትግል ጠላፊዎችን ሸኝቶ፤ አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦርን በመሪነት ተረክቦ በርካታ አውደ ውጊያዎችን አድርጓል።
ላለፍት ሶስት ዓመታት ከደብረታቦር እስከ ጋይንት እስቴ፣ ስማዳ የቀጠናው ተናዳፊ አራት ዓይና፤ ስናይፐር አባባይ፤ ክንደ ፈርጣማ፤ የዓላማ ሰው እና አደራ አስቀጣይ ጀግና ፋኖ ነበር። አርበኛ አንደበት ምንም እንኳን ስ አንደበት ይባል እንጂ፤ አንደበቱ ግን ሲበዛ ቁጥብ ነው። ሚዲያዎች ጀብዱውን እንዲዘግቡለት ሲጠይቁት እንኳን፤ ‹‹ሥራ ላይ ነኝ መልሼ ልደውልልህ፣ ከእኔ ይልቅ እከሌን ብትጠይቀው ይነግርሃል፣ ሠራዊት እያደራጀሁ ስለሆነ መልሼ እደውልልሃለሁ›› እና የመሳሰሉትን ምክንያች እየጠቀሰ፤ ከቃለ ምልልስ ይሸሻል እንጂ፤ በየሚዲያው እየወጣ የሠራዊቱንና የእሱን ጀብዱዎች እንኳን መናገር አይችልም ነበር፡፡
በኢትዮጵያ የጥበብ እና የፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ አዲስ እና እጅግ አሳሳቢ ክስተት ተፈጥሯል። የሀገሪቱ አንጋፋ እና ተወዳጅ የሙዚቃ ኮከብ የሆነው የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የረጅም ዘመን የቅርብ ወዳጅ እና የዘወትር የስቱዲዮ አጋሩ የሆነው የሱፍ ያሲን፣ ዛሬ ከሰዓታት በፊት በፌደራል ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የቤተሰብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
እንደ ቤተሰብ መረጃ፣ ስድስት በሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተፈጸመው ይህ ድንገተኛ ዘመቻ፣ በህግ ጥላ ስር ከማዋል ባለፈ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የታየበት ነው። ፖሊሶቹ የሱፍ ያሲንን ከገዛ ቤቱ እና ቤተሰቡ ፊት በሀይል እየደበደቡ መውሰዳቸው፣ እርምጃው ህጋዊ ማጣራትን ሳይሆን ማስፈራራትን እና የኃይል ርምጃን ያማከለ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። ግለሰቡ እስካሁን የት እንደታሰረ እና በምን ወንጀል እንደተጠረጠረ በይፋ የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም፣ የእስረኛው አያያዝ ግን በሀገሪቱ ያለውን የጸጥታ ሀይሎች የኃይል እርምጃ አሳሳቢነት በድጋሚ አጉልቶ አሳይቷል ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።
የዚህ ዜና የፖለቲካ እና የደህንነት ስበት የሚያርፈው ከየሱፍ ያሲን ግለሰባዊ ማንነት ይልቅ፣ ከቴዲ አፍሮ ጋር ባለው እጅግ የጠበቀ ትስስር ላይ ነው። የሱፍ ከቴዲ አፍሮ ጋር በየቀኑ አብሮ የሚውል፣ በስቱዲዮ ስራዎቹ የማይለይ እና የልብ ወዳጁ መሆኑ ይታወቃል። በፖለቲካዊ እና የደህንነት ትንታኔ መነጽር ሲታይ፣ የጸጥታ ሀይሎች የቴዲን የቅርብ ሰው በዚህ መልኩ በኃይል እና በድብደባ መውሰዳቸው፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በራሱ በድምጻዊው ላይ የተቃጣ የስነ-ልቦና ጫና እና የማስጠንቀቂያ መልዕክት ሊሆን ይችላል የሚል ጠንካራ ስጋት ፈጥሯል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፌዴራል ፖሊስ የሱፍን በምን ጠርጥሮ እንደወሰደው አልገለጸም።
የብልፅግና መዋቅር እየፈረሰ ነው
ሚያዚያ 13/2018 ዓ/ም፣
በዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ-ጦር በጎንጅ ቆለላ ወረዳ በሠራው ኦፕሬሽን የብልጽግና ታማኝ አገልጋዮች በጅምላ ራቁቱን ትተውት እየወጡ ነው።
በዛሬው ዕለት ከጎንጂ ብልጽግና አምልጠው የመጡ፦
1. ተናኘ ጥላሁን -መንታ ደብር ሚሊሻ
2. ደረጃው ተናኜ -ፓራ ኮማንዶ እና
3. ተሻለ አገኘሁ -ሚሊሻ
እስካሁን ከአገዛዙ ጋር በቆዩበትም ሕዝባቸውን እና መላ የፋኖ ታጋዩን ተንበርክከው ይቅርታ ጠይቀዋል። ተብሏል በጣም ደስ ይላል ሰዉ ስተቱን አዉቆ ሲመለስ ለይቅርታ ሲንበረከክ🥰
ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም
አገዛዙ የፋኖን ምት መቋቋም ሲያቅተው የአርሶ አደሮችን ሀብት እና ንብረት መዝረፉን ቀጥሏል:-
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋት አውራጃ ጣርማበር ወረዳ እና በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ አርሶ አደሮች ላይ የአገዛዙ ጦር ሰራዊት አባላት መጠነ ሰፊ የንብረት ዝርፊያና የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸሙ የገኛል።
1. በጣርማበር ወረዳ የተፈጸሙ የዝርፊያ ዝርዝሮች (ሚያዝያ 12/2018 ዓ.ም)
➾አርሶ አደር ደበበ አበቤ መንገታ፡ 7 ኩንታል ማሽላ፣ 1,600 ብር ጥሬ ገንዘብ፣ አንድ ጭነት ባቄላ፣ ሁለት የፍየል ሙክት እና አንድ የሞባይል ስልክ ተዘርፈዋል።
➾ወይዘሮ የትምወርቅ ንጉሴ10 ጭነት ማሽላ፣ 2 ጭነት ጤፍ እና አንድ የፍየል ሙክት ተወስዶባቸዋል።
➾አቶ የጎሽሜ ነገሠ (ወይራ አምባ)፡ 6 ኩንታል ጤፍ ተዘርፈዋል።
➾አቶ ደሣለኝ ተሥፋዬ፡ 20 ኩንታል ማሽላ ተዘርፎባቸዋል።
➾ቄሥ አለማየሁ ወ/ዮሀንስ፡ 4 ኩንታል ማሽላ ተዘርፈዋል።
በተጨማሪም በወንደሠን ንጉሴ፣ መረሻ ሞገሰ እና ጌትነት ዳኛቸው የተባሉ ግለሰቦች በድምሩ 9 ከብቶች የተዘረፉ ሲሆን፣ ንብረታቸውን ለማስመለስ የጠየቁ አርሶ አደሮች 81,000 ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ተረጋግጧል።
2. የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሁኔታ (ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም)
በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ በኩል የምርጫ ካርድን በሃይል ለማከፋፈል የተደረገ እንቅስቃሴ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ህዝቡ "ይህ ድርጊት በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና የሚያራዝም በደማችን ላይ የሚደረግ ድራማ ነው" በማለት ካርዱን አንቀበልም ማለታቸው ተገልጿል።
በአካባቢው ያለው የፋኖ ሃይልም አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አርበኛ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴ ጉማ ተራራ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመከታተል መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን ኮሩ ገልጿል።
'' ክብር ለትግሉ ሰማዕታት ''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰበር ዜና!
23ኛ ክፍለ ጦር ማጥቃት የመጣን ጠላት ስበው በማስገባትና በመደምሰስ 3 የቡድን መሳሪያ እና 45 የነፍስ ወከፍ ክላሽ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም በሶስት መድፍ፣ በአራት ዙ23፣ ቢ ኤም 107 ፣ 82 ሞርተር ጨምሮ በበርካታ እግረኛ ታጅቦ ከድላንታና ደሴ የመጣው በተሬና በጉና አድርጎ፣ ከጊምባ የመጣው የጠላት ሀይል በሜ/ጀ ዘውዱ ሰጣርጌ አስተባባሪነት በተንታ ግንባር ወደ ደለቅ በአጅባር ግንባር፣ እንድሁም በበርበር ወደ ደበቅና ከመቅደላ ወረዳ ከማሻ ከተማ በባዙራ አድርጎ ወደ ደበቅ፣ በአጠቃላይ በአምስት አቅጣጫ 23ኛ ክፍለ ጦር ላይ የማጥቃት ውጊያ ከፍቶ ውሏል::
ጠላት መጣ ሲባል ልባቸውን የሚምኑት አልሞ ተኳሽ የአሳምነው ፅጌ ልጆች ጥላትን ስቦ በማስገባትና መልሶ በመክበብ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ጀኔራሉ ሙትና ቁስለኛውን እንኳን ለማውጣት ፋታ ሳይሰጡት ወደመጣበት እንድፈረጥጥ አድርገውታል።
በዚህ ውጊያ አገዛዙ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከማስተናገዱም በተጨማሪ ውጊው አሁንም የቀጠለ ሲሆን እስካሁን ባለው ተጋድሎ
2 (ሁለት) ብሬን
1 (አንድ) ስናይፐር
45 (አርባ አምስት) የነፍስ ወከፍ ክላሽ
በተጨማሪም አንድ የሬጅመንት ዘመቻ አመራርን ጨምሮ የፋሽስቱ ሰራዊትም ተማርኳል ሲል የ23ኛ ክፍለ ጦር ህ/ግንኙነት ለኮራችን ባደረሰው መረጃ አረጋግጠናል።
ቀሪዎቹን መረጃዎች ሲጠቃለሉ የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ተጠናክኖ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ104 ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም
ዛሬም ከ14 በላይ የሚሆኑ የጠላት ሀይል ፋኖን ተቀላቅለዋል።
የሚሊሻ ሻለቃ አዛዡ እና ፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የመከላከያ ጋንታ መሪ ቲም መሪ ብሬን ተኳሾችን ይዘው ተቀላቅለዋል።
1.50አለቃ ደመቀ ጌቴ......የሚሊሻ ሻለቃ አዛዥ
2.ይገርማል ጌትነት.......ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ
3.ኮ/ል መለሰ አያልሰው..........ፓሊስ
4.ዘርጋ ዳንኤል...25ክ/ጦር መከላከያ ጋንታ መሪ ብሬንተኳሽ
5.ዮሴፍ አበበ....25ክ/ጦር መከላከያ ቲም
መሪ ..
6.አትንኩት ተስፋ....ፓራ ኮማንዶ
7.ሙሉሰው ስራው.....ፓራኮማንዶ
8.ላቃቸው ማዕዛ....ፓራኮማንዶ
ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለጦርን ሲቀላቀሉ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በዛሬው ቀን ብቻ በቋሪት ወረዳ ስድስት የሚሊሻ አባላት ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል
ዛሬ_የተቀላቀሉት፦
1. መልካሙ ገደፋዬ ( ሻምበል መሪ)
2. ምኒበል ወርቅነህ (SKS)
3. ሙሉዓለም ጎሹ ሞገስ ( ቲም አዛዥ] (ያልተተኮሰበት አዲስ ክላሽ ከ30 ጥይት ጋር)
4. መንግሥቱ ይርጋ (ጥቁር ክላሽ ከ30 ጥይት ጋር — ከሰከላ ወረዳ መከላከያን አንገት አስደፍቶ የነጠቀው!)
5. እንደግ ደመመው ___ ጅንፎ SKS
6. እሱባለው አበባው __አብራራው
"መጀመሪያውኑ መሣሪያ ለማምጣት እንጂ ሀገር በታኝን ሥርዐት ለማጽናት አልሄድንም!" ያሉት ሚኒሾቹ አክለውም"ባዕድ ሀገር የነበርን ይመስለን ነበር፤ ከሕዝብ ጋር እንደመኖር ያለ ነፃነት የለም!"ሲሉ ገልፀዋል ።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም
