ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 414
المشتركون
+1324 ساعات
+277 أيام
+1 21530 أيام
أرشيف المشاركات
+1
🔥#የድል_ዜና_ማክሰኝት‼️
በላይ ዘለቀ ዕዝ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጋራ በመሆን ማክሰኝት ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸው ተሰምቷል!
በአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ስር የሚገኘው ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር እና በአፋሕድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ስር የሚገኘው አፄዎቹ ክ/ጦር ዛሬ ጥቅምት 20/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ባደረጉት ተጋድሎ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ስር የምትገኘው ማክሰኝት ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ማስገባታቸውን መረብ ሚዲያ ከአፄዎቹ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
በውጊያው በርካታ ቁጥር ያላቸው የጡት ቆራጩ ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን፡ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል።
20/ዐ2/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ከቤ ጉበኛ ብርጌድ
ከአቤ ጉበኛ ብርጌድ
አማራ ጠሉን ጨፍጫፊውን እንዲሁም የአብይ ወንበር አስጠባቂና ባንዳ የብልጽግና ተላላኪ አመራር እና ተላላኪ ሚሊሻወች፣ ፖሊስ ፣ ትልቁን ሽልማት ለማግኘት ከሽመልስ አብዴሳ ቃል ተገብቶላቸው የመጡ የኦሮሞ ልዩ ሀይሎች በሙሉ የጠበቁት ሳይሆን ያልጠበቁትን የሞት ፅዋ እየቀመሱ እያዩ የመጡበትን መንገድ ቢናፍቁም የሰማይ መንገድ ሆኖባቸዉ እንደ እግር እሳት(🔥) የሚባላው ተናዳፊው የአማራ ፋኖ ሞትን እንደ ሰማዕታት እንጂ እንደ ሞት የማያስፈራው ጠላት አለ በተባለበት ምሽግ ሁሉ እየገባ ታሪክና ጀብድ እየፈፀመ ይገኛል።
በመሆኑም በቀን 16/02/2018 ዱርቤቴ ከተማ ደምስሶ የገባው ነበልባሎቹ(🔥 ) የአቤ ጉበኛ ልጆች ከ 20 በላይ ተላላኪ ሚሊሻና ከ15 በላይ የሚሆን የሽመልስ አብዴሳ ሰራዊት ጉረሮ ለጉሮ በጨበጣ በሳንጃ ረፍርፈው ከ30 በላይ ክላሽ መሳሪያወች እንዲማረኩ አድርገው በክብር አርፈዋል ።እኛም ጓዶቻችሁ የተሰዋችሁለትን የአማራ ህዝብ አደራ ተቀብለናል የጀመራችሁትን ትግልም እንጨርሰዋለን በስማችሁ ታሪክ እንፅፋለን ጀግኖቻችን።
የአቤ ጉበኛ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
በረከት ፀሐይነህ፤
ዶክተር አብደላ እድሪስ
የፅናት ተምሳሌት
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት
።።።።።፡።።።።።።።።።።
ዶ/ር አብደላ እንድሪስ በዋናነት በጦርነት ግንባር ቀርቦ በመዋጋት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በፋኖ ንቅናቄ ውስጥ የሞራልና የስትራቴጂ መሪ በመሆን የሚሰራ አርበኛ የአማራይቱ ልጅ የፋኖ አንድነት: በደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሽዋ ፋኖን ከተለያዩ ክፍሎች በማደራጀትና በማዋሀድ ለትግሉ ስኬት ቁልፍ ሚና በመጫወት ግንባር ቀደም ከሚሰለፉት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል አንዱ ነው።
የሞራል ልዕልና ለፋኖ ተዋጊዎችና ለህዝቡ ትግሉን የመምራት፣ የማነሳሳት እና የጽናት ምልክት በመሆን እየሰራ ያለ ጀግና ብቁ አርቆ አሳቤ በትምህርት ደረጃ የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ያለው ። የፋኖ እንቅስቃሴን ከፖለቲካ እና ከስትራቴጂ አንፃር የመምራት ብቃት ከመኖሩም በላይ ከወታደሩ እስከ ማህበራዊ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚወዱት በአጭሩ፣ ዶ/ር አብደላ እንድሪስ የሸዋ ፋኖ እንቅስቃሴን የሚወክል፣ የሚያደራጅ እና ስትራቴጂያካዊ መረጃዎችን የሚያቀርቡ ቁልፍ ጀግና ነው።
የጋራ ማንነት እና አንድነት የጋራ ስነ-ልቦና አማራነትን እጅግ አብልጦ የሚውድ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ እና ሌሎች የአማራ የሆኑ ህዝቦች የጋራ የሆነውን ማንነት (የጋራ ስሜት፣ ታሪክ፣ እሴት) በማመን እና መተሳሰሩን በማጠናከር ላይ ያለ ለህዝቡ ያለው ፍቅር የጀግንነት እና የፍቅር እሴቶችን የሚንጸባረቅ በዘመናዊው ትግል ውስጥ ያለው ትርጉም የህልውና ጥያቄ: በዘመናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማራነት የህዝብን መብትና ደህንነት ማስከበር ከሚለው ጥያቄ ጋር አብልጦ የሚወድ ሰው ማለት የህዝቡን ህልውና (መኖር) አደጋ ላይ የሚያደርሱ ነገሮችን በመከላከል እና በማንነቱ ሳይሸማቀቅ ለመቆም ከፍተኛ ዝግጁነት ያለው የታማኝነት ጥብቅና፣ ለህዝቡ መብት መቆም፣ መስዋዕትነት መክፈልን ከማንነቱ ጋር ያዛመደ ጀግና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ሆኖ በመስራት የአማራን ህዝብ ነፃ ለማውጣት በከፈትኛ ተነሳሽነት ሞራል እየሰራ ያለ ጀግና ቅንነትንና ትህትናን በደሙ አዋህዶ የያዝ የአሳምነው ልጅ
ለዘመናት እንደ አረም አንቆ ይዞ ወደ ማቅና መቀመቅ አውርዶ ሥራዓት አልበኝነትን አንግሶና ነግሶ በሁለት ቢላዋ የሚበሉ ህዝብና ሀገርና በማፍረስና በማጥፋት ላይ ካለው ደናቁርት ስብስብ ማለትም የአብይ አህመድ እና የብአዴን መሀይሞች ስብስብን በዕውቀት ልህቀት ተፈጥሮአዊና ሰባአዊ መብቶች ተከብረው በህይወት የመኖር ህልውናን ለማስክበር የሚያስችል ህዝባዊ የፖለቲካ ልዕልናን ለማረጋገጥ ከብረት የጠነከረ የትግል ዓላማን ከአነገቡ ልህቃን ታጋዮች ጋር እየታገለ ያለ የዘመናችን ዕንቁ አርበኛ ዶክተር አብደላ እድሪስ አብዱ ለህልውናቸውና ለነጻነታቸው ከሚታገሉት ጀግኖች ዶክተር አንዱ ነው። ይቀጥላል....................
+5
ህዝባዊ አደረጃጅቱ እንደቀጠለ ነው
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ከትግሉ ጎን ለጎን የህዝብን አደረጃጀት እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም ክፍለ ጦሩ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌውች የህዝብን አደረጃጀት የአማራ ፋኖ እስትራቴጂካዊ ስራቱን በሚመጥን መልክ በኤፍርታ ግድም ወረዳ በየሰርዶ ቀበሌ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመውጣት አደረጃጃት ተፈጥሯል።
በመድረኩም አሁን የፋኖ ቁመና ምን ይመስላል በሚል ከደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩና እና የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር አመራሮች ግንዛቤ የተሰጠ ከመሆኑም በላይ ማህበረሰቡ ፋኖ በሚያስተዳድረው ቀጠና በሰላም እየወጣ በመግባት ላይ ሲገኝ ጠላት መከላከያ በሚገኝበት ቀጠና ደግሞ አሁን የገበሬው የሰብል ወቅት ከመሆኑም በላይ ሰብላቸውን ለመሰብሰብ እንደተቸገሩም ከማህበረሰቡ መሰረታዊ ጥያቄውችም ተሰንዝረዋል። ህዝቡም እኛ ፋኖ ነን ከልጆቻችን ጋር አብርን እንሞታለን አማራ ነፃ ሲወጣ ነው አገር ሰላም የምትሆነው ስለዚህ እንዲያውም እኛንም አደራጁን አብርን እንዋጋለን በማለት ህዝባዊ ውይይቶች በሰላም ተጠናቀዋል።
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
ጥቅምት 20/ዐ2/2018 ዓ.ም
🎯 የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝና አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ኃይሎች በጥምረት በጠላት ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ ድል ተቀዳጁ።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ክ/ጦሮችና አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ክ/ጦሮች የጋራ ጠላትን በጋራ መደምሰስ የሚል እቅድን አንግበው የጠላት ኃይል ሰፍሮ በሚገኝባቸው በተለያዩ ከተማዎች ሰርጎ በመግባት አስደናቂ ጀብዶችን ሰርተዋል።
በትላንትናው እለት የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካል የሆኑት ጎ/በጋሻው ክ/ጦርና ጥቁር አንበሳ ክጦር አሃዶች እንዲሁም አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ እዝ በአርበኛ ታርቆ ከበደ የሚመራው አሃድ በጋራ በመሆን በምዕራብ በለሳ አበየና ድርቃ ልደታ በተባሉት አካባቢዎች የብልጽግናን ወንበር አስጠባቂ ኃይል ሲያበራዩት ውለዋል።
በውጊያው የሞቱበትን
3 መከላከያዎችና
3 ሚሊሻዎችን ድርቃ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ላይ ቀብሮ የሄደ ሲሆን ሌሎች ቁጥራቸው በርከት ያሉ የመከላከያና የሚሊሻ ቁስለኞችን ወደ አርባያ ከተማ ይዞ ፈርጥቶ አምልጧል። የአርባያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞችም ቁስለኞችን ለማትረፍ ሽር ጉድ ሲሉ ተስተውለዋል።
🎯 ከዚሁ የአንድነት ዜና ሳንወጣ
ዛሬ ጥቅምት 19ለ 20 2018 ዓ.ም አጥቢያ ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር አሃዶችና አፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ አፄዎቹ ክ/ጦር ማክሰኝት ከተማ በ3 አቅጣጫ ዘልቆ በመግባት የጠላትን ኃይል መውጫ መግቢያ አሳጥተውት አርፍደዋል።
ለሰዓታት ያህል ከተማዋን በቁጥጥር ስር አድርገዋት የቆዩ ሲሆን የከተማዋ ሚሊሻና የስርዓቱ አገልጋይ ካብኒዎች እግራቸው ወደአመራቸው መፈርጠጣቸውን የመረጃ ምንጫችን ገልጿል።
ቁጥራቸው በእውን ማወቅ የማይቻል የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
🎯 ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል ሰፍሮ በሚገኝባቸው ከተሞች
አምባ ጊዮርጊስና
አዲስ ዘመን ላይ ከትላንት ማታ ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያደረጉ ነው።
ማታ አመሻሽ ላይ
ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አምባ ጊዮርጊስ ከተማ ላይ በ3 አቅጣጫ በመግባት በአብይ ጡት ቆራጭ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል። በጥቃቱ
5 የመከላከያ አባላት ወዲያውኑ ሲሞቱ
8ቱ ደግሞ ክፋኛ በመቁሰላቸው የተነሳ በሪፈር ለከፍተኛ ህክምና ደባርቅ ከተማ ተልከዋል።
የጠላት ኃይል ቁሳዊ ፣ ሰባዊና ፖለቲካዊ ኪሳራን ያስተናገደበት ጥቃት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
🎯 የጠላት ኃይል ማዘዣ ጣቢያ በሆነችው አዲስ ዘመን ከተማ ላይ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር በ3 የውጊያ ግንባሮች እየተፋለሙ ይገኛል።
በስተ ምስራቅ አቅጣጫ አፄ እያሱ ክ/ጦር
በስተ ስሜን አቅጣጫ መብረቅ ክ/ጦር በ2 ግንባሮች
በስተ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ፋናየ ውቤ ክ/ጦር
ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ብርጌዶችና
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አካል የሆነው ነብዩ አሳምነው ብርጌድ የአዲስ ዘመን ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን መሬቶች በመጠቀም በጠላት ኃይል ላይ የበላይነትን ወስደዋል።
ከእብናት ድጋፍ ለመስጠት የሚመጣን የጠላት ኃይል አፄ እያሱ ክ/ጦር አግዶ ይዞ እንዳያልፍ ያደረገ ሲሆን አዲስ ዘመን ከተማ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን ግብስብስ ኃይል ያለምንም ስጋት ምሽጉ ድረስ ዘልቆ በመግባት እልህ አስጨራሽ የፊት ለፊት ውጊያ ማካሄድ ተችሏል።
በውጊያው
ከ15 በላይ ሲሞት
12 የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በከተማው ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸው ታውቋል
🎯 በአጠቃላይ ከሰሞኑ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተደረጉ ያሉ ወታደራዊ ዘመቻዎች የጠላት ኃይል ከፍተኛ ቁሳዊ ፣ ሰባዊና ፖለቲካዊ ኪሳራዎችን ያስተናገደበት ግዳጅ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
+3
........... #የአደረጃጀት_ዜና !! .............
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ )
#የቴዎድሮስ_ዕዝ_201ኛ_ኮር_የ54ኛ_ክፍለጦር_
ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
በዚህም አዲስ ተዋቅሮ የተጠናቀቀው 54ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት የመብረቁ ተፈራ ብርጌድ ፣ የመዝገበ ጮቄ ብርጌድ እና መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድን ያካተተ ሆኖ ተመስርቷል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሬጅመንቶች የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሬጅመንቶች አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
የክፍሐጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በዕዙ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ማርሸት ፀሐው ደምሴ ፣ በዕዙ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ይትባረክ አንዳርጌ እና በዕዙ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
ከጀግኖች ማህደር
ሲበዛ ዝምተኛ ነው ብዙ መስራት እንጅ ብዙ ማውራት የማይሆንለት መልከ መልካም ቆራጥ መሪ ነው
፲ አለቃ ሽፈራው ቢያዝን አማራዉ ተራራው ተወልዶ ያደገው በምስ/ጎጃም ዞን በፋኖ አደረጃጀት ቁይ ደባይ ጮቄ ብርጌድ በ ናብራ ቀበሌ ሲሆን ገና ልጅነቱን ሳይጨርስ በሀገር ፍቅር ስሜት በመንገብገብ ኸነ ሙሉ ግሮማ ሞገሱ የነበረውን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በ17ዓመቱ በመቀላቀል የፋኖ አብዮት እስኪፈነዳ ድረስ በተለያዩ ሙያዎችና ሀላፊነቶች አገልግሏል!! #፲አለቃ_ሽፈራው_ቢያዝን
ከዛም ያለበት ተቋም ፍፁሞ አላማውን ስቶ ከሀገር መከላከያ ወደ ግለሰብ አብይ አህመድ ዙፋኖ ጠባቂ ሲሸጋገር ከተቋሙ በመውጣት ታሪካዊዉን የፋኖ የነፃነት ተጋድሎ በመቀላቀል ከአባልነት ጀምሮ የናብራ 4ኛ ሻለቃ ወታደራዊ አዛዥ በመሆን ሻለቃዋ ዛሬ ላይ ላለችበች አስፈሪ ግርማ ሞገስ እንድትበቃ አስችሏታል!!!ሻለቃዋን በትክክለኛ ወታደራዊ ዲሲፒሊን በማስቃኘት በጣም በርካታ የቡድንና የነፍስወከፍ መሳሪ እስካፍንጫዋ በማስታጠቅ የጉጅሌው ብርሀኑ ጁላን ጦር አፈር ድሜ እያስጋጠው ይገኛል በዚህ ጀግና ፊታውራሪነት
ለአብነትም:-
- የካቲት 26/2016 ናብራ ድል ሜዳ
-ዘመቻ 100 ተራሮች ምሽግ በመስበር
በርካታ መሳሪያ መማረካቸው
-ታህሳስ 26/2016 ዓ.ም ናብራ ድል ሜዳ ጠላትን በመረፍረፍ መሳሪያ መማረኩ
ከብርጌዱ ውጭ ሻለቃዋን በመምራት
* ዋብር የተከበቡ አመራሮችን
* ስናን ገደማላ ከንጉስ ተ/ሐይማኖት ብርጌድ ጋር
* አባኮስትር ጋር በርካታ ጊዜ በዲማ በወይራ የቀብሃና
* መዝገበ ጮቄ ብርጌድ ሰዴ ላይ ባንዳ ሚሊሻና ፖሊስ
እንዲሁም በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪ መማረክ በአጠቃላይጦሩ የተሟላ ከሚሊተሪ ጀምሮ ትጥቅ እስከአፍንጫው በማስታጠቅ ለጠላት ረመጥ የሆነ ጀግና ነው
ይታደሉታል እንጅ አይታገሉትም እንዲሉ ጀግንነትን እስከጥግ የታደለው ሽፈራው ቢያዝን የዛሬ የብርጌዳችን ወሳኝ የነገው ጄኔራላችንን አሁን የጀግንነት ወኔ የበለጠ ጠንክሮ እንዲወጣ ሁሉም የትግሉ በርታ ይለው ዘንድ በማሳሰብ በሌላ ጊዜ በሌላ
ጀግኖች ታሪክ እስከምንገናኝ ቸር ተመኘሁ
ጀግኖቻችንን በህይወት እያሉ እናጀግናቸው
ክብር ለጀግኖቻችነ
በአዲስ ቅዳም ከተማ ፣ አካባቢው እና በመላዉ አለም ለምትገኙ የትግላችን ደጋፊዎች==================
አጭበርባሪ የብልፅግና ወኪሎች የተለያዩ ቴክኒኮችን በመጠቀም ለተለያዩ የትግል ድጋፎች የሚሆን በሚል የፋይናንስ እና ሎጅስቲክ ድጋፍ በብርጌዳችን አመራሮች ስም እየተጠየቁ እንደሆነ ደርሰንበታል።
በመሆኑም ሁሉም የትግላችን ደጋፊዎች የምታደርጉት ድጋፍ የአጭበርባሪዎች ሲሳይ ሳይሆን በህጋዊ መንገድ ለትግሉ እንዲደርስ ከተፈለገ በስልክም ሆነ በሌላ መንገድ ድጋፍ የሚጠይቃችሁ ግለሰቦች ሲኖሩ ቀጥታ ወደ ብርጌድ አመራሮች በማሳወቅ ህጋዊነቱን እንድታረጋግጡ ስንል በአክብሮት እናሳስባለን።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!
ጥቅምት 19/2018 ዓ/ም
#የምሽቱ_ጮማ_ዜና_ተቀበል
እነዚህ ወታደሮች፦"ጦርነት በቃን! ወገኖቻችን ላይ መተኮስ አንገፈገፈን"በማለት በዛሬው ዕለት ተመካክረው ከአሀዳቸው በመጥፋት ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ-ጦርን የየተቀላቀሉ የመከላከያ አባላት ናቸው።
ከመካከላቸው 1 ሬጅመንት አመራር፣ 6 ሻምበል መሪ እና 5 ምክትል ሻምበል መሪ አመራሮች ይገኙበታል።
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
+2
🔥#እድሜ_ያልበገራቸው_የነፃነት_ታጋዮች‼️
በአማራ ምድር በፋኖነት ለአማራነት ዋጋ እየከፈሉ ካሉ በርካታ እድሜ ያልበገራቸው የነፃነት ታጋዮች (ጀግኖች) ውስጥ #ከጎንደር_ሰማይ_ስር ያሉ እንቁዎች‼️
እነዚህን የእድሜ ባለፀጎች በማረፊያ እድሜያቸው ለአማራነት ዋጋ እየከፈሉ ያሉ አርበኞች ናቸው።
በቀጣይ በዱር በገደሉ እየተዋደቁ ያሉ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ ያሉ አባት አርበኞችን እናስታዋውቃችኋላን።
በርቱ ክንደ ብርቱ ነፃ አውጭወቻችን👏👏
ተቃውሞ ሰልፍ እና ሻማ ማብራት በስቶኮልም
💚💛❤️✊🇸🇪
በአማራ ህብዝ ላይ እየተፈጸሙ ያሉትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች የጦር ወንጀሎች እና ንጹሀን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የድሮን ጥቃት እናውግዝ ‼️
ቀን : November 1,2025
ሰአት : Klockan 15 till 17
Plats : Medborgarplatsen Torg
አዘጋጅ: ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
On October 18, 2025, a mother was killed by an Abiy regime drone strike in Dehna Mariam Kebele, less than 5 kilometers from Bahir Dar, with her baby strapped to her back. Miraculously, the baby survived. #AmharaGenocide
በአማራ ክልል ያለውን ጦርነት መረጃ ከፈለጎ ከታች ያለውን link በመንካት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇
https://t.me/abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167 የአማራ ድምፅ ሚዲያ የእናተ ድምፅ
+1
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው‼️
ከዘመቻ አባ ናደው መጠናቀቅ በኋላ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችና ዕዞች ወደ ቤተ-አማራ የገባው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰና እየኮበለለ ምኒልክ ዕዝን በስፋት እየተቀላቀለ ነው::
የኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ኦሮሚያ ላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲፈፅመው የነበረውንና ዛሬም እየፈፀመው ያለውን ግፍ በተመሳሳይ የመከላከያ መለዮ ለብሶ ወደ አማራ ክልል በመግባት የሚፈፅመውን ግፍ እያየን እኩል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተብለን ልንጠራ አንችልም ያሉ አባላቶቹ ባለፉት አስር ቀናቶች ብቻ 46 ክላሽ 4 ጀሌ 11350 የክላሽ ተተኳሽ እንዲሁም 90 F1 የእጅ ቦምብ በመያዝ ከ50 በላይ ሰራዊት ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል::
ፋኖን ከተቀላቀሉት የሰራዊቱ አባላቶች መካከልም 1 ሬጅመንት አመራር 6 ሻምበል መሪ እና 5 ምክትል ሻምበል መሪ አመራሮች ይገኙበታል:: በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝን ሰራዊት የማፍረስና የማስኮብለሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
19/ዐ2/2018 ዓ.ም
@hageremedianews
+4
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
ሻለቃ መሪውንና ብሬን ተኳሹን ጨምሮ 11 የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖን ተቀላቀሉ!
ጥቅምት 19 / 2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ዋግሹም ብርጌድን የተቀላቀሉት:-
1. ሻለቃ ምስጋናው እንየው:- የፖሊስና የሚሊሻ አዛዥ
2. ወርቁ አድሴ:- ብሬን ተኳሽ
3. ኮንስታብል የኋላው ግርማይ:- የአገዛዙ ፖሊስና ሌሎች ስምንት ሚሊሻዎች የብልፅግናን ስርዓት በመጥላት ከድሃና አምደወርቅ ዱራ ግንባር ተነስተው ዋግሹም ብርጌድን ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።
ሲቀላቀሉ ይዘውት የመጡት ትጥቅ አንድ ስኪ፣አንድ ምንሽር፣አንድ M-40፣ስምንት ክላሽ፣330 የክላሽ ተተኳሽ፣ስድስት የእጅ ቦምብ፣40 የስኪና የምንሽር ተተኳሽ፣ 11 የወገብ ትጥቅ ይዘው ተቀላቅለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 19 / 2018 ዓ.ም
+1
ይኽ ሕፃን ተአምራት አውግቸው ይባላል። ገና የ ፪ ዓመት ሕፃን ሲኾን ከናኖ ጃዊው የአሩሲ ፍጅት በእግዚአብሔር ተአምር ተርፏል።
እናቱ ወ/ሮ ስምረት ሸዋንግዛው በሰማዕትነት ስታርፍ እርሱ በጀርባዋ ታዝሎ ነበር። ሰዎች ሲደርሱ ከእናቱ አስከሬን ላይ ተጣብቆ ተገኝቷል። አባቱም ተሰውቷል። እግሩ ላይ የደረሰበት አደጋ ከመክበዱ የተነሣ ይቆረጥ አይቆረጥ የሚለው የሐኪሞች ውሣኔ እየተጠበቀ ነው።
ከኃይለ ማርያም ማሞ ሆስፒታል ወደ ወላይታ ክርስቲያን ሆስፒታል ሪፈር ተደርጓል።
ኹለቱ ከፍጅቱ የተረፉት ሕፃናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል። ሕፃን ስንታየሁ ሸዋንግዛው በኃይለ ማርያም ማሞ ሆስፒታል ሕክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች።
ከሰማዕታቱ በረከት የሚሻማ የሚያሳክም ይገኝ ይኾን?
©ዓባይ ነህ ካሤ
+2
አሁን በደረሰን መረጃ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሌ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ 5 ምእመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ አድርሰዋል።
መረጃ ሰጭዎቻችን አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
