ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 349
المشتركون
+17324 ساعات
+2467 أيام
+1 36830 أيام
أرشيف المشاركات
+2
ተቋሙን እያፈራረስነው ነው ‼️
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
#ዲሽቃ_ተኳሽ_እና_ምክትል_ቲምመሪው_ከእነሙሉ ትጥቃቸው መውኬ መንገሻ የተባለው የመከላከያ ሻምበል መሪ ሉባ ገወርጊስ የሚታጀብበትን ውሻ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅለዋል ።‼️
➦660 የክላሽ ተተኳሽ
➦ 6የእጅ ቦንብ
➦የወገብ ትጥቅ በመያዝ ከስርዓቱ በመውጣት ወደ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል
1 ፍቅሩ አበባው...ዲሽቃ ተኳሽ 602ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት
2 ፉአድ ሚፍታሂ ...ምክትል ቲም መሪ 602ኮር 1ኛ ሬጅመንት
3 ሀሰን አብዲ...602ኛኮር 1ኛሬጅመንት
አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስተስፋ
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዚያዊ ሕዝብ አስተዳደር ለወረዳና ንዑስ ወረዳ አመራሮች ስለ አማራ ሕዝብ ሁለተናዊ የህልውና ትግል አጫጭር ስለጠናዎችን ሰጠ።
ሕዝባችን የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የገጠመዉን ሁለተናዊ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚያደረገው ብርቱ ተጋድሎ ሕዝቡ ማድረግ ያለበትን አበርክቶ በእጅጉ ከፍ ለማድረግና አስተዳደራዊ ስራዎችን ፣ የፍትሕ አገልግሎትን ለማሳለጥ ያግዝ ዘንድ ለወረዳና ለአራቱም(4) የንዑስ ወረዳ አመራሮች አጫጭር ስለጠናዎች ስጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኢንጅነር አራጋው ያለው እና የዕዙ ፖለቲካ መኮነን ፋኖ መምህር ጋሻው ሙሉጌታ በጋራ በመሆን ሲሆን ስለ አማራ ሕዝብ ሁለተናዊ የህልውና አደጋ መነሻ ምክንያት ፣ አሁን ላይ ትግሉ ስለደረሰበት ደረጃ ፣ ስለ አማራ ሕዝብ የትግል መዳረሻ እንዲሁም ሕዝብን እንዴት ማደራጀት ፣ መምራት እና ማስተዳደር እንዳለባቸው ለሰልጣኞች በዝርዝር ቀርቧል።
ሰልጣኞች በበኩላቸው ስለተሰጠው ስልጠና በእጅጉ አመስገነው ከዚህ በላይ የትግሉ ደረጃ በሁሉም ዘርፍ ማደግ እንዳለበት እና የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የድል መዳረሻው ቅርብ እንዲሆን ድርጆቱ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል እንደ ድርጅት እንዲሁም ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ እንደ ዕዝ አበክሮ እንዲሰራ ምክር አዘል ሃሳቦችን ሰንዝረዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም
88ኛ ክ/ጦር አይበገሬ ክንዱን አቅምሶ ጠላትን መልሷል!
****//
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም በኮረኔል ምስራቅ የሚመራው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ሠራዊት ከምዕ/ጎጃሟ ሽንዲ ከተማ መነሻውን አድርጎ ወደ ኸረጥ ቀበሌ ከሌሊቱ 9: ሠዓት ጀምሮ በ2 /በዴንድ እና በቡራፈር ቀበሌዎች አቅጣጫ ተንቀሳቅሷል። በጠላት ላይ የበላይነትን የተቀናጀው የጀግኖች አምባ የአፋብኃ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር ሻለቆች/ ሻለቃ 5 እና ሻለቃ 4 እንዲሁም የክ/ጦሩ ቃኝና ማሃንዲስ/ሚደንቅ ቅንጅት እና ጥምረት በከፈቱት ግንባር ጥሩ አድርገው ጠላትን ደቁሰውታል።
ቀጠናው ላይ ጠላት ባሰበው መንገድ መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኮ/ምስራቅ ኸረጥ ላይ ለ30 ደቂቃ እንኳን መቆየት ሳይችል ተጣድፎ ሙትና ቁስለኛውን አንጠልጥሎ በቀበሮ ጉድጓዱ ወደ ሽንዲ ከተማ መመለስ ግድ ሁኖበት ተመልሷል።
በግዳጁ ጠላት ላይ ከባድ ቁሳዊና ሠባዊ ጉዳት ማድረስ መቻሉን የክ/ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ ፋኖ ቻላቸው አያና ገልጿል።
በየደረሰበት ንፁሃንን መግደል፣ ሐብት ንብረቱን መዝረፍ እና ማውደምን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ያለው ስርዓቱ አለማየሁ ሞሴ ጉደታ የተባለን የ15 ዓመት ወጣት የተሰጣ በርበሬ እየጠበቀ ባለበት ሁኔታ በጥይት ክፉኛ አቁስለውታል። በተጨማሪም የማህበረሰብ መገልገያ ተቋም የሆነውን የቀበሌ አስ/ፅ/ቤት ያፈራረሰው ሲሆን የአቶ ገበያው አዳነ መኖሪያ ቤትን ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በተወረወረ የሞርተር ቅንቡላ ሙሉ በሙሉ አውድሞታል።
#አገዛዙ ህዳር 22/2018 ኮኪ ቀበሌ አቶ ፈንታሁን ቸኮልን ጨምሮ 3 ንፁሃንን በግፍ የረሸናቸው መሆኑ የሚታወስ ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ
💪88ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ 17 የአድማ ብተና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሣ ሻለቃ የፋኖ ኃይል ትናትና ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ቡሶ ጊዮርጊስ የተባለ አካባቢ ላይ በጣለው ደፈጣ በኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ በሚመራው የአድማ ብተና ኃይል ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በዚህም 5 አድማ ብተናዎች ሲደመሰሱ 15 የሚሆኑት ቁስለኛ ተደርገዋል::
በተጋድሎው በድምሩ 2 ቲም የሚሆን የጠላት ኃይል ከጥቅም ውጭ ተደርጓል ሲል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
+5
የድል መረጃ ‼️
ዛሬ አነጋጉን ጀምሮ ለሰዓታት ደ/ወርቅ ከተማን ተቆጣጥሮ ያረፈደው የአፋብኃ ቲዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የጠላትን ቅስም የሰበረ በርካታ ድሎች የተመዘገበበት ሆኗል።
የአብዮቱ ጅማሮ ወቅት አርበኛ ጫንያለው ተረፈን የገደለው ባንዳው አጥኔን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ተደምስሷል የነብስወከፍ መሳሪያዎችም ተማርከዋል።
በዛሬው አውደ ውጊያ የተገኙ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ድሎች:-
▶ ከሃምሳ (50 )በላይ የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን 16ቱ ሚሊሻ እና ፖሊስ ናቸው።
▶17 ቁስለኛ ሲሆኑ 5ቱ ሚሊሻ መሆናቸውን አረጋግጠናል።
▶ በርካታ የግፍ እስረኞችን አስለቅቋል ።
▶27 ክላሽንኮቭ እና 9 የቃታ መሳሪያ ተማርኳል።
▶1650 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል።
▶29 ቦንብ እስካሁን ምርኮ ተደርጓል።
#ፋኖ_መሠረተ-ልማት #ይጠግናል፤ #ብልጽግና_ያወድማል
═══════════❁✿❁════════════
(ታኅሣስ 07/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)
በአፋብኀ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር በጎንጅ ቆለላ ወረዳ የፋኖ ጊዜያዊ የመንግሥት አስተዳደር የገጠር መንገዶችን በኅብረተሰብ ተሳትፎ እየጠገነ መኾኑን አስታወቀ።
ባለፉት ሳምንታት በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች መንግሥታዊ የአደረጃጀት መዋቅር እየሰራ እንደሆነ የገለፀው የወረዳው ጊዜያዊ የፋኖ መንግሥት፤ መዋቅሩን ወደ ስራ በማስገባት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ተቀዳሚ ተግባር በማድረግ ነፍሰጡር እናቶች፣ ሕፃናትና አቅመ ደካሞችን በማንኛውም ጊዜና ሰዓት ወደ ጤና ተቋም ለማድረስ የሚያስችሉ መንገዶችን ጠግኗል።
ከባ/ዳር -አዲስ አበባ ሀገር አቋራጭ ጥቁር አስፖልት መንገድ በመነሳት
***ከዘማ_ወለቄ_አንጎፌ የሚያገናኝ የጠጠር መንገድ በህብረተሰብ ተሳትፎ በመስራት ለአገልግሎት ምቹ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።
በቀጣይም በሁሉም ቀጠናዎች የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሕዝባዊ ውይይትና ንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አረጋግጧል።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
መረጃው፦
ከአፋብኃ የ102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ጎእንጂ ቆብላ ወረዳ ጊዜያዊ የፋኖ መንግሥት አስተዳደር ሚዲያና ኮምኒኬሽን ክፍል ነው።
እሸት ክፍለ ጦር አዳራቸዉን ታላቅ ጀብድ ፈፅመው እጅን በአፍ የሚያስጭን ታሪክ ሰርተዉ ድል አስመዝግበዋል::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ቃኝዎች አዳራቸዉን በተለምዶ "ሳይና በር" ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ መሽጎ የሚገኘዉን የአገዛዙ 65 ክፍለ ጦር በመቶ አለቃ አረጋ የምትመራዉ 4ኛ ሻለቃ ሰራዊት ላይ በጨለማ የማያዳግም እረምጃ ወስደዉበታል።
ንስሮቹ የእሸት ክፍለ ጦር ቃኝወችም ሰኞ ለማክሰኞ አዳር ከምሽቱ 3:00 እስከ ሌሊቱ 7:00 ባደረጉት ማጥቃትም ቁጥሩ ያልታወቀ የአገዛዙ ሰራዊት በቦንብ አረር እንደ በቀሎ እሸት ሲጠበስ ቀሪዉ ነፍሰ አዉጭኙን በየገደሉ እየተንከባለለ ማደሩ ታዉቋል።
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም
ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ በተደረገ ተጋድሎ በርካታ ድሎችን አስመዘገቡ‼️
በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ደሴ ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ተከታታይ መደበኛ ውጊያ በማድረግ ጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
የተወርዋሪ ሻለቃዋ አናብስቶች ደሴ ዙሪያ ወረዳ ላይ ብዙ ቀበሌዎችን በመቆጣጠር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የህዝቡን አስተዳደራዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ሰፊ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ::
ሳምንቱን ያለማቋረጥ በተደረገው መደበኛ ትንቅንቅና ተጋድሎ በርካታ ድሎች የተመዘገቡ ሲሆን በትናትናው ዕለት ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ተለያየን እና ዚሃ ላይ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ተወርዋሪ ሻለቃዋ ከልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር ጋር በመጣመር በርካታ የፋሽስቱ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ቀጠናውን በማስከበር ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
07/ዐ4/2018 ዓ.ም
+1
የ10 ዓመት ህጻን ልጅ አስገድዶ የደፈረ ግለሰብ በእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት ህግ ክፍል በቁጥጥር ውሎ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ወሳኔ ሰጥቷል።
ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም
የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት ህግ ክፍል አገልግሎት #በጠላት_ቀጠና በእነማይ ወረዳ ጠልማ ቀበሌ ንፋሳም ማርታ ጎጥ ወጣት ስመኘው በላይነህ የ10 ዓመት ህጻን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ የደፈረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል በወረዳው የፍትህ አካል ውሳኔ ተሰጥቷል።
ወጣቱ ስመኘው የ10 ዓመቷን ህፃን በጠልማ ቀበሌ ንፋሳም ማርታ ጎጥ ከብት በምታሰማራበት ሰዓት በአካባቢው ማህበረሰብ ሰው አለመኖሩን አይቶ ህፃናን **** ወደ ጫካ በመጎተት በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ መድፈሩን ችሎቱን ለያዘው የፈትህ አካል የእምነት ቃል ሰጥቷል።
በተኮላንተፈ አንደበት እና ፍርሃት እና ድንጋጤ በተሞላበት ትንፋሽ ማርታ ጎጥ ወጣት ስመኘው አስገድዶ እንደደፈራት ህፃን *** ቃል ሰጥታለች። ከዚህ በተጨማሪ በንፋሳም ማርታ ጎት ስትጮህ የደረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች የአይን እማኝ ምስክርነት እና የህክምና ማስረጃዎችን በመቀበል በወረዳው ጊ/መንግስት የፍት አካል ግራ እና ቀኙ ታይቶ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ የገንዘብ ቅጣት እና የእስራት ውሳኔ አርፎል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ትውልድ!
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግሥት ሚዲያ ክፍል ኃላፊ
ስናን አባጅሜ ሻለቃ በደፈጣ ጥቃት አደረሰች
ቀን ታህሳስ 07/2017 ዓ.ም
በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በም/ጎጃም ዞን ስናን ረቡዕ ገበያ ከተማ መሽጎ በሚገኘው የአረመኔው ምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ዙፋን አስጠባቂ ጦር ላይ የደፈጣ ጥቃት በማድረግ ጉዳት ማድረስ ተችሏል
የደፈጣ ጥቃቱን የፈፀሙት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር አባል የሆነችው ጀብድ መስራት የማይሰለቻት የስናን አባጅሜ ሻለቃ ስትሆን በዚህ የማጥቃት ስራም በጠላት ላይ በህይወትም በቁስም ከፍተኛ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።ከጠላትም የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ከነተተኳሹ መማረክ የቻሉ ሲሆን በወገን በኩል ያለምንም ጉዳት በመውጣት በሰላም ወደካንፓቸው መልሰዋል።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
Hailemariam Kiber Temesgen
አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ሕፃናት በግዳጅ ወደ ውትድርና እየመለመሉ ለግዳጅ እየዋሉነው።
የብልፅግና አረመኔ ሰራዊት ዓለም አቀፍ የጦር ህግን በመተላለፍ ሕፃናትን ለጦርነት እያዋለ መሆኑ በተደጋጋሚ እያሳዩ ነው።
በዛሬው ዕለትም 10 አይሱዙ በላይ የሆኑ ህፃናት ተገደው ብርሸለቆ ካንፕ እንደተገኙ ማረጋገጥ ተችሏል። በማስረጃ መጋለጡ ያሳሰቡ የብርሸለቆ ማሰልጠኛ ሀላፊ ልጆችን ወደ ማርቆስ በመላክ አብማ ሆቴል አሽጓቸው እንደሚገኝ ማወቅ ችለናል። ህፃናቱ እየተራቡ በመሆኑም ማህበረሰቡን እየለመኑ ይገኛሉ።
በእንዲህ አይነት ወንጀል የተጨማለቀው የብልፅግና አመራርን በዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ለመክሰስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ማህበራትም እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
የፕሮፖጋንዳ ጋጋታ ከመንገዳችን አያቆመንም። የምንናገረውን እየፈፀምን፤ የፈፀምነውን እየተናገርን እንቀጥላለን።
በዚህ የጦርነት ሂደት አገዛዙን ያላንከራተትንበት ቦታ የለም። ከሶማሊ ላንድ እስከ ጅቡቲ፣ ከኤርትራ እስከ ፖርት ሱዳን፣ ከቀይ ባህር እስከ አባይ ግድብ፣ ከድሮን ፌስቲባል እስከ ባሌ፣ ከምምክር ኮሚሽን እስከ አፍሪካ ህብረት፣ ከኢጋድ እስከ ሰላም ካውንስል ፣ ከሰልፍ እስከ አጭበርባሪ ሽማግሌወች፤ ሁሉንም ተዟዙሮ ውርደትን ብቻ እንዲከናነብ አድርገነዋል።
ሐቀኛ ዓላማ የያዘው የፋኖ ተጋድሎ ያሸንፋል። በየእለቱ ግፍ እየተፈፀመበት ያለው የአማራ ህዝብ የነፃነት ችቦውን ያበራል። የደፈሩን፣ የጨፈጨፋን፣ መንገድ ዘግተው ያደኸዩን፣ በመጥፋታችን ላይ የተሳተፉ እና የተዘባበቱ ሁሉ ለፍትህ ይቀርባሉ። የሒትለርን ሰወች የዳኘው የኑረምበርግ ችሎት እንዲቋቋም ዓለም ባይተባበረን እንኳን ለፍትህ እና ለርትዕ ቀናኢ የሆነው ህዝባችን በድሉ ማግስት ግፈኞችን በፍትህ ይፋረዳቸዋል።
ወደ መጨረሻው መንገድ የሚወስደን መንገድ መራር መስዋዕትነት እና ፅናት የሚጠይቅ ቢሆንም ይሳካል።
አልመጣም ሲሉት መጣ አሁን ገና
ነፋስ ያዘለው መስሎ ዳመና
እንዲል ዳኘ ዋለ የአገዛዙ ቅልብ ካድሬ ድንፋታው ልክ ባጣበት በዚህ ዕለት አስደናቂዋ 74ኛ ክፍለ ጦር በከፈተችው ድንገተኛ ማጥቃት ደብረ ወርቅ የከተመውን ጠላት ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ችላለች። ሌሊቱን በጀመረ አረመኔውን ሰራዊት የማፅዳት ኦፕሬሽን በርካታ ኃይል ተደምስሷል፣ ተማርኳል፣ ቁንጮ የጠላት ካድሬም ተሸኝቷል።
ይቀጥላል...
አስረስ ማረ ዳምጤ
ሰበር ሰበር ‼️
201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር ደብረ ወርቅ ከተማን ተቆጣጠረ ዝርዝሩን ይዘን እንቀርባለን..
© ይበልጣል ጌቴ
