ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

الذهاب إلى القناة على Telegram

This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.

إظهار المزيد
4 434
المشتركون
-424 ساعات
-167 أيام
-9130 أيام
أرشيف المشاركات
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቁ ባሉት መሠረት ተማሪው በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ጥያቄ እያቀረበ ነው! አሁንም ገና ነው ጥያቄዎቻችንን እናስገባ! ቅሬታ ማቅረቢያው https://www.facebook.co
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቁ ባሉት መሠረት ተማሪው በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ጥያቄ እያቀረበ ነው! አሁንም ገና ነው ጥያቄዎቻችንን እናስገባ! ቅሬታ ማቅረቢያው https://www.facebook.com/share/p/1LNAiWkmeA/ ነው:: መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም! https://t.me/EHEMSU

# Waajjiri Mummee ministeraa gaaffiiwwan keessan barumsaan , fayyaadhaan , ikonomii fi wantoota bu'ura ta'an kaanin walqabatan gaafadhaa. Qaamni dhimmichi ilaallatu deebii ni kenna jedhe jira. Kanaafuu nuti gaaffiwwan barattootni muslimaa mana barumsaa kessatti qabnu fi akkasumas gaaffiwwan uffata obboleettiwwan keenya hijabaa fi niqaaba ilaalchisee akkasumas dhimma karaa qilleensaan ( airportin) walqabatee jiru dafnee ha gaafannu . Jalqaba linki kanaan gara postichaa seenaa . https://www.facebook.com/share/p/1LNAiWkmeA/ San booda gaaffiwwan armaan gadi koomanti irratti barressaa ergaafi. Warri dandeessan copy paste gochurra yaaduma keessanin barressa. Kabajamoo mummicha ministera akkuma ibsitanitti gaafilee qeebaluuf qophii tahu keessaniif galatooma. Nuti muslimoonni barnootaafi dhabbata mootummaa keessatti keessattu dubartiin muslimaa sababa hijaabaa fi niqaabaan akkasumas akkata raawwii solaataan walqabate bilisummaan amanti keenyaa sarbamu jiraachu isaa sin beeksisu barbaadna . # barnootaa fi hojiiwwaan kan irratis ta'e mirga dubartoota muslimaa ilaalchisee heera itoophiyaa keewwata 27 irrati ifaan akkuma ibsametti namni kamu amantaa filate hordofuu, gabbaru fi ibsachu mirga qaba. Haa ta'u malee qabatamaan : 2ffa damee barnootaan : naannoowwan garagaraa ( fknf godina guraagee aanaa gunchireetti , aksuum , yuniivarsitii dillaatti ,yuniivarsitii jimmaatti , yuniivarsitii addis abaabaafi kkf....) Niqaaba ,Hijaaba fi uffata amantaa islaamaa mulli'isan kan sababa uffachuu isaanitiin barnoota isaani irra arihamaa jiru. ( fkf gunchireetti bara 3 isaan guute jira . ) Yeroo qormaata biyyoolessaa sababa uffannaa isaanitiin akka qormaata hin fudhanne godhamaa jiru.(fkf barattootni muslimaa aksuumitti formi hin guunne, hanga harra yeroo qormaata irra taa'an uffata keessan baasa kan jedhaman jiru ) sarbamu fi dhiibamun mirgaa irraan gahamaa jira. solaataan walqabatees mirgi isaani daangeffamaa jira . Gaaffiin keenya : mootummaan dubartoonni muslimaa mirgi isaani eeggameefi sodaa tokko malee barumsa isaani akka hordofan tarkaanfiin qabatamaan fudhatamaa jiru maali ?? furmaannis yoom kennama ?? 4ffaa Dhaabbata mootummaa ( fknf karaa qilleensaa keessatti ) Dhiirri muslimaa areeda isaanii fi akka amantaan isaani ajajutti uffatani akka hin qacaramne ugguramaa jiru . Dubartootni hijaaba uffatanis akkasuma akka hin hojjanne dhorkamaa jiru. gaafin keenya mootummaan dhaabbanni heeraa fi seeraan ala mirga amantii namaa dhiiban akka waan kana sirreessan tarkaanfiin fudhatamaa jiru maali ?? Gaaffi yaachiisaa kana deebii fi ibsa ballaa hatattamaan akka nu kennitan fi furmaata akka nuuf kennitan kabajaan isin gaafanna . https://t.me/EHEMSU

ይህ የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ ነው ••• ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ! ጠይቁን ብለዋልን ጥያቄዎቻችንን በጨዋ ደንብ አሰናድተን እንጠይቅ:: መልስ እንሰጣለን ብለዋልና
+2
ይህ የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ ነው ••• ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ! ጠይቁን ብለዋልን ጥያቄዎቻችንን በጨዋ ደንብ አሰናድተን እንጠይቅ:: መልስ እንሰጣለን ብለዋልና መልሳቸውን እናውቅ ዘንድ ጥያቄዎቻችንን እናቅርብ:: ሁላችንም እንጠይቅ ••• ለጥያቄያችን ትኩረት እስኪሰጡ ድረስ ••• ድምፃችንን ሰምተው መልስ እስኪሰጡ ድረስ! ቅሬታ ማቅረቢያው https://www.facebook.com/share/p/1LNAiWkmeA/ ነው:: መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም! @EHEMSU

በሚጠየቁ ጥያቄዎች ዙሪያ የሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አሳውቋል:: የተደገሰልን ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንጠይቅ ••• ስለ መብቱ የቆመ
በሚጠየቁ ጥያቄዎች ዙሪያ የሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አሳውቋል:: የተደገሰልን ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንጠይቅ ••• ስለ መብቱ የቆመ ትውልድ እንዳለ ያውቁ ዘንድ እንጠይቅ ••• መብቱን ለመውሰድ የተዘጋጀ ትውልድ እንዳለ ይረዱ ዘንድ እንጠይቅ! ቅሬታ ማቅረቢያው https://www.facebook.com/share/p/1LNAiWkmeA/ ነው:: መብት በትግል እንጅ በልመና አይገኝም!

ይህንን ሀላፊነት መወጣት ቀላል ቢሆንም እያደረግን ላለው ሁሉን አቀፍ ትግል ግን ትልቅ ሚና ይጫወታል:: መብታችንን ለማስመለስ በምናደርገው ትግል ጥቂት ነው ብለን የምንተወው ሚና የለም:: ዛሬ የምንወረውራት ጠጠር ተደምራ ተራራን ትሰራለች ••• ኢንሻ አላህ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ትምህርት ስርዓቱ ጠይቁኝ ባሉት መሠረት ጥያቄዬን እንደሚታየው አቅርቤያለሁ:: ይህ የትግላችን አንዱ አካል ነው:: ፈጠን ብለን በተቀናጀ ሁኔታ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ በሙስሊም
+1
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ትምህርት ስርዓቱ ጠይቁኝ ባሉት መሠረት ጥያቄዬን እንደሚታየው አቅርቤያለሁ:: ይህ የትግላችን አንዱ አካል ነው:: ፈጠን ብለን በተቀናጀ ሁኔታ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን በደል እናሰማ:: ቅሬታን ማቅረቢያው https://www.facebook.com/share/p/1LNAiWkmeA/ ነው:: ፈጠንንንንን በሉሉሉሉሉ! የላካችሁበትን @MohammadamminM ላኩልኝ:: Let us do it! @MohammadamminKassaw

እንፍጠን ••• ቀነ ገደቡ ዛሬ ነው!   ■ የጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት  በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚና ሌሎች አምራች ጉዳዮችም ላይ ጠይቁኝና ምላሹን በሚመለከታቸው አካላት እሰጣለሁ ብሏል። ስለሆነም በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስላለው የሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ እንዲሁም ስለዚህ እኛ ፈጥነን የእህቶቻችንን የአለባበስ ጉዳይና የአየር መንገዱን ጉዳይ እንጠይቅ። ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 2 የመጨረሻው ቀን ነው! መጀመሪያ በዚህ ሊንክ ወደ ፖሰቱት ጽሑፍ ግቡ። https://www.facebook.com/share/p/1LNAiWkmeA/ ከዚያ እነዚህን ጥያቄዎች ኮመንት ላይ ጻፉና ላኩላቸው። የምትችሉ ከቀጥታ ኮፒ ፔስት ይልቅ በራሳቸው አገላለፅ ሃሳቡን ጻፉትና ጠይቁ። ጥያቄዎቹ:- ①) ክቡር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንደገለጻችሁት ጥያቄዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናችሁን ስላሳወቃችሁን እናመሰግናለን። እኛ ሙስሊሞች በትምህርትና በመንግስት ተቋማት በተለይም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሒጃብና ኒቃብ አለባበስ ምክንያት እንዲሁም በሶላት አፈጻጸም ላይ እምነት ነጻነታችን እየተገደበ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን። √ በትምህርት እና በተለያዩ የስራ መስኮች የሙስሊም ሴቶችን መብት በተመለከተ፤ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 27 ላይ በግልጽ እንደሰፈረው እያንዳንዱ ሰው የመረጠውን ሃይማኖት የመከተል፣ የማምለክ እና የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም በተጨባጭ፦ 1) • በትምህርት ዘርፍ፡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች (ለምሳሌ ጉራጌ ዞን ጉንችሬ፣ አክሱም፣ ዲላ ዩኒቨርስቲ፣ ጅማ ዩኒቨርስቲ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ…) ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች (ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ) ኒቃብ፣ ሒጃብ እና ሌሎች ኢስላማዊ አለባበሶችን በመልበሳቸው ምክንያት፡ ከትምህርት ገበታቸው እየተባረሩ ነው። (ለምሳሌ በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከ3 አመት በላይ ሆኗቸዋል) በብሔራዊ ፈተናዎች ወቅት በአለባበሳቸው ምክንያት ፈተና እንዳይፈተኑ እየተደረጉ ነው። (ለምሳሌ፦ በአክሱም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፎርም አልሞሉም፣ እስከዛሬ በበርካታ የትምህርት ተቋማት ላይ ልክ ፈተና ሲቀመጡ ኢስላማዊ ልብሳችሁን አውልቁ የሚባሉባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ።) ትንኮሳ እና መድልዎ እየደረሰባቸው ነው። ከሶላት ጋር በተያያዘም የእምነት ነፃነታቸው እየተገደበ ነው። ጥያቄያችን፡ መንግስት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠብቆ፣ ያለምንም ሥጋትና መድልዎ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ምን አይነት ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው? መቼስ መፍትሄ ይሰጣል? 2)• በመንግስት ተቋማት (ለምሳሌ በኢትዮጵያ አየር መንገድ)፡ ሙስሊም ወንዶች እምነታቸው ስለሚያዛቸው ፂማቸውን በማስረዘማቸው እና ሱሪያቸውን በማሳጠራቸው ምክንያት የመቀጠር እድል እየተነፈጋቸው ነው። ሒጃብ የሚለብሱ ሙስሊም ሴቶች የመስራት መብታቸው እየተገደበ ነው። ጥያቄያችን፡ እነዚህ ተቋማት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ አሰራሮችን እንዲያስተካክሉ እና ኃይማኖታዊ ነፃነትን እንዲያከብሩ መንግስት ምን አይነት ቁጥጥር እና የማስተካከያ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው? ለዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ በዝርዝር እንድታብራሩልን እና ተገቢውን ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን:: @EHEMSU

በመጨረሻም ሁላችንም የሃይማኖት ተቋሞቻችንንና የአስተምህሯችንን ክብር፣ ልዕልናና ቅድስና እንጠበቅ በማለት ጉባኤያችን የአደራ መልዕክቱንና ጥሪውን ያቀርባል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ - ለሰላም፣ ለመተባበር እና ለአብሮነት ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ መጋቢት 2 ቀን 2017 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በወቅታዊው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተካሄደ ያለውን ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረገው ክብረ-ነክ፣ የትንኮሳ፣ የጥላቻና ጸብ ቀስቃሽ ዘመቻዎችን አስመልክቶ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሠጠ መግለጫ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 “የሃይማኖት ንጽጽር - በከፍተኛ የሃይማኖት ሊቃውንቶች መካከል በሕግ፣ በሥርዓት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ በዶግማዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ የሰከነ ውይይት ነው፤ በአማኞች መካከል የሚደረግ ሥርዓት የለሽ እና አንዱ ሌላውን የሚያውገዝ፣ የሚያጠልሸ እና ክብረ-ነክ መሆን ወንጅል ነው፤” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበራዊ ሚዲያውን እድገትና ተደራሽነት መስፋትን ተከትሎ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ በአወንታዊነት እና በአሉታዊነት የሚፈረጅ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ተሠርተው አየር ላይ ሲውሉ እናያለን፤ አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በመክፈት የተለያዩ ግለሰቦችን ወደመድረካቸው በመጋበዝ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በደጋፊነት እና በነቃፊነት ላይ ተሰልፈው የጦፈ ክርክር ሲደርጉም እንመለከታለን፡፡ ዘርፉና የመገናኛ መድረኩ የራሱ የሆነ የአጠቃቀም መመሪያ ያለውና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ የሚጠበቅ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች መድረኩን ከዓላማው ውጪ ለሆነና ለግልና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ በማድረግ በተለያዩ ሃይማኖት/እምነት ተከታዮች መካከል መተማመኑ እና መከባበሩን የሚሸረሽሩ ይዘቶችን፣ ክብረ ነካዊ በሆነ አቀራረብ ግልፅ ጥላቻን የመስበኩ ልምምድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ይገኛል፡፡ ይህ ዓይነቱ አቀራረብና ልምምድ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በመደበኛ የአምልኮ መርሀ ግብር ላይ በፊት ለፊት መድረኮች ሲቀርብ አይተናል፡፡ ልምምዱና አቀራረቡ ከወዲሁ ሊታረምና በሕግና ሥርዓት ሊከናውን እንደሚገበው ጉባኤያችን በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህ አንፃር ከሰሞኑ የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች የተቀደሰ የጾም፣ የጸሎትና በከፍተኛ ደረጃ የመንፈሳዊ እነፃ ላይ በሚገኙበት ጊዜ ከመንፈሳዊነትና ከሃይማኖቶች መሠረታዊ ዕሴት ጋር የሚቃረን ተግባር በማኅበራዊ ሚዲው በስፋት እየተሠራጨ ይገኛል፡፡ በተለይም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጽያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታየረተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡ ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡ በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሠጡ እና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡ ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊታቸው በመታረም የሕግ የበላይነትን እንዲስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡ በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት የሌላቸው ብቻ ሳይሆን የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። እንዲህ ያሉት ክብረ-ነክ የሆኑ ተግባራትና አስተያየቶች ሁሉ ድርጊቱ ለተፈፀመባቸው እምነት ተከታዮችን በእጅጉ የሚያስቆጡ ብቻ ሳይሆኑ መላ ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ የሚያስቆጡ ናቸው፡፡ የመከባበርና የአብሮነት እሴቱን በመሸርሸር በሀገራችን የሰላምና የሰላማዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደቱንና ጥረቱን እንዳይያሳካ ያደርጋሉ፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አንዱ የሌላውን እምነት ለመስደብ ወይም ለማዋረድ በፍፁም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የእምነት ነፃነት እና የማምለክ መብት ለሁሉም ማህበረሰቦች የተጠበቀ ሲሆን ይህ መብት የሌሎች አማኞችን መብት በመጋፋና ስሜት በመንካት ለጠብ ማነሳሽነት ሲውል በዝምታ ሊታለፍ አይገባውም፡፡ ይህንን ከባድ ጥፋት በዘላቂነት እንዲታረም የሚመለከታቸው አካላት አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ይህንንና ተመሳሳይ ተግባር በፈፀሙና በሚፈጽሙ አካላት ላይ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን። ለእንደዚህ አይነት ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ለወደፊቱ የሃይማኖትን ስም ማጥፋት ለመከላከልና የሁሉም እምነት ተከታዮች ክብርን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ በእጅጉ ይረዳል። በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ምሁራን እና መላ ሕብረተሰቡ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር፣ መግባባትና መረዳዳት ይበልጥ ሊያጠናክሩ በሚያስችሉ የጋራና የተመረጡ አጀንዳዎች ላይ በሕግ፣ በሥርዓትና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመሩና ግልጽ ዓላማና ግብ የተቀመጠላቸው ውይይቶችና ምክክሮች በተጠናከረ መልኩ በማከናውን በሃይማኖቶች መካከል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን እንደ ሚያጠናክሩ ይጠበቃል፡፡ በቅርቡ ጉባኤያችን ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመዳሰስና በመተንተን ሀገራዊ ዓውዱንና ተግዳሮቶች ታሳቢ በማድረግ፣ እንዲሁም ተቋሙ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል የመተዳደሪያ ደንቡን አሻሽሏል፡፡ የተሻሻለው ደንብም በተቋማት መካከል አለመከባበርን፣ አለመቻቻልን የሚሰብኩ፣ ጥላቻን የሚቀሰቅሱና ግጭትን የሚያባብሱ ተንኳሽና ክብረ-ነክ ንግግሮችንና ተግባራትን የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በራሳቸው ተቋም ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት እንዲኖር የሚያደርግ ድንጋጌ በደንቡ ላይ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ችግሮን በዘላቂነት ለመፍታትም ከአባል የሃይማኖት ተቋማት የሚወከሉ የሕግና አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች የሚካተቱበት የተከላካይ ግብር-ኃይል አደረጃጀት በጊዜያዊነትና በቋሚነት በማደራጀት የቅደመ መከላከል ሥራዎች ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡ ግብር-ኃይሉም ችግሮችንና የችግር አዝማሚያዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመስጠት ሙያዊ እገዛ በማድረግ ሕግና ሕጋዊነትን የማስጠበቅ ሥራ በመስራት የሀገር ሰላምንና የሃይማኖት ተቋማትን ክብርና ልዕልና የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡ የሁለቱም እምነት ተከታዮች እና አማኞች በማኅበራዊ ሚዲያው ባለው አሉታዊ ዘመቻና በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ሳይረበሹ የጾም፣ ጸሎትና የንስሀና ተግባሮቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጉባኤያችን ይመክራል፡፡ የሕግ አስከባሪ አካሉም፣ በአማኞች መካከል ያለው ሰላምና መከባበር የሚያውኩ፣ ሕገ-ወጥ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ በማድረግ ሕግና ሥርዓት የማስጠበቅ የተለመደ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤያችን ጥሪውን ያቀርባል፡:

ሸሐዳ እንኳ ያለ ነቢ ስም አይሞላም! ••• ወአሽሀዱ አን-ነ-ሙሐመደን ረሱለላህ! @EHEMSU

We love Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) more than ourselves! @EHEMSU

Muhammad (صلى الله عليه و سلم) ! @EHEMSU

May our parents and soul sacrificed for Allah's Messenger ﷺ ! @EHEMSU

Our greatest dream is to be the neighbor of Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) in Jennah ! @EHEMSU

We are the nation of Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) ! @EHEMSU

Our leader is Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) ! @EHEMSU

Our way is the way of Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) ! @EHEMSU

Prophet Mohammad (صلى الله عليه و سلم) is our great teacher! @EHEMSU

ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በዋንጫ የተሸለመችውን ዚክራ በሐሩን ሚዲያ እያየሁ ነበር:- ጠያቂ:- ኒቃብ እንደሚሉት አዕምሮሽን ጋርዷል? በትምህርትሽ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል? ዚክራ:- በፍፁም! በፍፁም!
ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በዋንጫ የተሸለመችውን ዚክራ በሐሩን ሚዲያ እያየሁ ነበር:- ጠያቂ:- ኒቃብ እንደሚሉት አዕምሮሽን ጋርዷል? በትምህርትሽ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል? ዚክራ:- በፍፁም! በፍፁም! እንደውም አግዞኛል:: ኒቃብ ፊቴን ልሸፍንበት እንጂ አዕምሮዬን ሊጋርድ አልተቀመጠም:: Congrats again 🎉🎉🎉 @MohammadamminKassaw