ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

الذهاب إلى القناة على Telegram

This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.

إظهار المزيد
4 433
المشتركون
-124 ساعات
-147 أيام
-8530 أيام
أرشيف المشاركات
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ዩኒቨርሲቲው በጁምዓ ቀን ከ5:30 ቡሃላ ምንም አይነት ፕሮግራም እንዳይኖር እንዲሁም ከሰዓት ከ7:30 ብቻ እንዲጀምር ጠይቋል:: ህብረቱ እንደገለፀው የዩኒቨ
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ዩኒቨርሲቲው በጁምዓ ቀን ከ5:30 ቡሃላ ምንም አይነት ፕሮግራም እንዳይኖር እንዲሁም ከሰዓት ከ7:30 ብቻ እንዲጀምር ጠይቋል:: ህብረቱ እንደገለፀው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት አካዳሚክ ክፍል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ማስተካከያ እንደሚያደርግ አሳውቋቸውል:: ••• እንደሚታወቀው በሕግ ደረጃ ከ1985 ጀምሮ በጁምዓ ቀን ከ5:30 - 7:30 በመንግስት መስሪያ ቤቶች የእረፍት ሰዓት ነው:: ሆኖም ግን ትምህርት ቤቶች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ሕግ ውጭ በመሆን በዚህ ሰዓት አገልግሎት በመስጠት የሙስሊሞችን መብት በተደጋጋሚ ሲጥሱ ተስተውሏል:: https://t.me/EHEMSU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የሰላም ሚኒስትር በዩኒቨርሲቲው አዲሱ የተማሪዎች የስነ ምግባር መመሪያ ውስጥ ያሉ አድሎኣዊ ድንጋጌዎችን እና አሰራሮችን እንዲመረምር ጠየቀ! ህብረቱ
+2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የሰላም ሚኒስትር በዩኒቨርሲቲው አዲሱ የተማሪዎች የስነ ምግባር መመሪያ ውስጥ ያሉ አድሎኣዊ ድንጋጌዎችን እና አሰራሮችን እንዲመረምር ጠየቀ! ህብረቱን ጥያቄውን ያቀረበው ለሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ በተለይም ከኒቃብ እና የጀመዓ ሰላት ጋር ተያይዞ እየደረሱ ስላሉ የመብት ጥሰቶች ለማብራራት በጻፈው ደብዳቤ ነው። ህብረቱ ችግሩ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለወራት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቢጥርም በዩኒቨርሲቲው በኩል ችግሩን የመፍታት ፍላጎት ባለመኖሩ እንዳልተሳካም አውስቷል። ህብረቱ እና ሙስሊም ተማሪዎች ለሰላምና ሰላማዊ ትግል ካላቸው ጽኑ አቋም የተነሳም በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሙሉ ወጪ የጣት አሻራ መመርመሪያ ማሽኖችን ለዩኒቨርሲቲው ለማስገባት ዝግጁ ቢሆኑም ነገር ግን የዩኒቨሪሲቲው አስተዳደር ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ችላ በማለት እንዲባባስ እያደረገ ይገኛል ሲል ደብዳቤው አብራርቷል። አሁንም ድረስ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ በተለይም ኒቃብ በሚለብሱ እህቶች ላይ በተለይም ግቢ መግቢያ በሮች ላይ ትንኮሳዎች እየተካሄዱ በመሆኑ ጉዳዩ በአስቸኳይ እልባት የማያገኝ ከሆነ ወዳልተፈለገ ደረጃ ሊያመራ እንደሚችልና ወደዚያ ቢያመራም ብቸኛ ተጠያቂ ዩኒቨርሲቲው እንደሚሆን አሳስቧል። በመሆኑም የሰላም ሚኒስትር የሐገሪቱን ሰላምና መረጋጋት እንዲያስጠብቅ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት አስቸኳይ እና ቆራጥ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። aaumsu https://t.me/EHEMSU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዩኒቨርሲቲው ያሉ ሙስሊም ተማሪዎችን መብት እና ክብር ለማስጠበቅ ቆራጥ እና አስቸኳይ እርምጃ እንዲ
+2
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዩኒቨርሲቲው ያሉ ሙስሊም ተማሪዎችን መብት እና ክብር ለማስጠበቅ ቆራጥ እና አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ! ህብረቱ ለምክር ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ በዘንድሮው አመት በዩኒቨርሲቲው አዲስ ከጸደቀው የተማሪዎች ስነምግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ ጋር በተያያዘ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ በተለይም ከኒቃብ እና የጀመዓ ሰላት ጋር ተያይዞ እየደረሰ ስላለው ችግር በሰፊው አብራርቷል። ህብረቱ ችግሩ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለወራት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቢጥርም በዩኒቨርሲቲው በኩል ችግሩን የመፍታት ፍላጎት ባለመኖሩ እንዳልተሳካም አውስቷል። ይህም በእንዲህ እንዳለ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ በተለይም ኒቃብ በሚለብሱ እህቶች ላይ በተለይም ግቢ መግቢያ በሮች ላይ አሁንም ድረስ ትንኮሳዎች እየተካሄዱ እንዳሉ በመጥቀስ ጉዳዩ በአስቸኳይ እልባት የማያገኝ ከሆነ ወዳልተፈለገ ደረጃ ሊያመራ እንደሚችል ተብራርቷል። በተጨማሪም ህብረቱ ፕሬዝደንቱና ስራ አስፈጻሚውን ጨምሮ ምክር ቤቱን በተደጋጋሚ በጉዳዩ ዙሪያ ለማነጋገር ቢሞክርም ከምክር ቤቱ ምላሽ አለማግኘቱ እና በዚህ ወቅት ምክር ቤቱ ከተማሪዎች ጎን አለመቆሙ ኃላፊነቱን አለመወጣት ብቻ ሳይሆን ሙስሊሙ ማህብረሰብ በምክር ቤቱ ላይ የጣለውን አደራ መክዳት እና የታሪክ ተወቃሽ መሆንም ጭምር በመሆኑ ምክር ቤቱ በአፋጣኝ መፍትሄ ያበጅ ዘንድ ጠይቋል። ህብረቱ የደብዳቤውን ግልባጭ ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ እ/ጉ/ከ/ም/ቤት፣ ለኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት አስገብቷል። ©️ aaumsu https://t.me/EHEMSU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የጁምዓ ሰላት ሰዓት እንዲከበር አሳሰበ። ህብረቱ ለዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት እና በግልባጭ ለአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ባስገባው ደብዳቤ የሐ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የጁምዓ ሰላት ሰዓት እንዲከበር አሳሰበ። ህብረቱ ለዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት እና በግልባጭ ለአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ባስገባው ደብዳቤ የሐገራችን መንግስት ሙስሊም ሰራተኞች የጁምአ ሰላትን እንዲሳተፉ ለማድረግ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አርብ ከ 05፡30 እስከ 07፡30 እንዲዘጉ መመሪያ ያወጣና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የዩንቨርስቲው አመራሮች ለመመሪያው መተግበር ቁርጠኛ መሆናቸው የገለጹ ቢሆንም ባለፉት ጊዜያት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በውጤታማነት አለመተግበሩን ጠቅሷል። ህብረቱ የትምህርት ዘመኑ ሁለተኛ ሴሚስተር እየተጀመረ በመሆኑ የተማሪዎች ህብረት እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉም የአካዳሚክ መርሃ ግብሮች የጁሙዓ የሰላት ጊዜን በሚመለከት የመንግስት እና የዩኒቨርሲቲ መመሪያዎችን መተግበራቸው እንዲከታተሉና ስህተቶችን እንዲያርሙ አጥብቀን አሳስቧል። ህብረት በየካምፓስ ተወካዮቹ አማካኝነት ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተል እና የሚፈጸሙ ጥሰቶችን የሚያሳውቅ መሆኑንና ከዚህ መመሪያ ውጭ የሆነ ማንኛውም አካል ተጠያቂ የሚሆንበትም መንገድ እንዲመቻች ጠይቋል። የህብረቱ ተወካዮች ከተማሪዎች ህብረት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የተማሪዎች ህብረትም ጥያቄው ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ አፈጻጸሙን እንድሚከታተል ገልጿል። የአአዩሙተህ በካምፓስ ጀመዓዎቹ አማካኝነት አተገባበሩን የሚከታተል ሲሆን የዩኒቨርሲቲያችን ሙስሊም ተማሪዎች በየትምህርት ክፍሎቻቸው እንዲከታተሉ እና ለህብረቱ እንዲያሳውቁ እናሳስባለን። ©️ AAUMSU https://t.me/EHEMSU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ተወካዮች በዩኒቨርሲቲው የረመዳን ዝግጅት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ጋር ተወያየ። በውይይቱም ወቅት የህብረቱ ተወካዮች መደረግ ስላለባቸ
+1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ተወካዮች በዩኒቨርሲቲው የረመዳን ዝግጅት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ጋር ተወያየ። በውይይቱም ወቅት የህብረቱ ተወካዮች መደረግ ስላለባቸው ዝግጅቶችና ከዚህ በፊት ስለነበሩ ችግሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ተወካዮቹ የካፌ እና ለተራዊህና ተሃጁድ ሰላቶች የበር መውጫና መግቢያ ሰዓቶች ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ እንዲስተካከሉ አስታውሰዋል። በተጨማሪም የመጀመሪያ ቀን የሱህር ምግብ አለመዘጋጀት ወይም በቂ ያለመሆንን ባለፉት አመታት ሲታይ የነበረ ችግር በመሆኑ እንዲፈታ ያሳሰቡ ሲሆንም የተማሪዎች ህብረትም ዘንድሮ ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንዲቀረፍ እንደሚሰራ አሳውቋል። ሌላው ከምግብ ጥራት ጋር በተያያዘ በተለይ በሱህር ሰዓት የሚዘጋጁ ምግቦች በአብዛኛው ጥራታቸውን ያልጠበቁ መሆናቸውን የተገለጸ ሲሆን የተማሪዎች ህብረት በየጊዜው ቁጥጥር እንዲያደርግ ስምምነት ተደርሷል። ከዚያም በተጨማሪ ከተማሪዎች ህብረት ከሚመደቡ ተቆጣጣሪዎች በተጨማሪ በየካምፓሱ ከሙስሊም ተማሪዎች አንድ አንድ ተቆጣጣሪ እንዲመደብ ከስምምነት ተደርሷል። ሌላው በውይይቱ የተነሳው ነጥብ የሸዋልን ስድስት ቀናት ለሚጾሙ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው አገልግሎት እንዲሰጥ የሚል ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ውይይት እንዲደረግ በመስማማት ውይይቱ ተጠናቋል:: ©️ AAUMSU https://t.me/EHEMSU

"የሙስሊሞች ጉዳይ ያላሳሰበው ከኛ አይደለም" - ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) https://t.me/EHEMSU

"በጁምዓ ምክንያት ጧት 5:30 የሚጀምረው የመውጫ ፈተና ወደ 7:30 ... ተቀይሯል::" የሚል ዘገባን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ጧቱን ሰርቷል:: የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አመሻሹን ባወጣው
+1
"በጁምዓ ምክንያት ጧት 5:30 የሚጀምረው የመውጫ ፈተና ወደ 7:30 ... ተቀይሯል::" የሚል ዘገባን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ጧቱን ሰርቷል:: የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አመሻሹን ባወጣው ማስታዎቂያ ደግሞ ምንም አይነት የሰዓት ለውጥ አልተደረገም ብሏል:: ፈተናውን ከየት አምጥተው ሊፈትኑት ነው? ወይንስ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የተለዬ ነው? የማይሰማ የለ! ብቻ ግን በሕግ እንደተፃፈው እና ትምህርት ሚኒስቴር እንዳፀናው ጁምዓ ቀን ከ5:30-7:30 በመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራም ሆነ ትምህርት የለም:: ሰዓቱ የጁምዓ ነው:: https://t.me/EHEMSU

ይህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው:: በቻናሉ ከዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች እና የህብረቱ የዕለት ተዕለት ክዋኔዎች ይቀርባሉ:: በአላህ ፍቃድ እና እርዳታ ከዚያም ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር በሚኖር መናበብና መተጋገዝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች መብታቸው ተከብሮ ይማሩ ዘንድ እንተጋለን:: መረጃዎች ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ይደርሱ ዘንድ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ:: @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU

የነገ Exit Exam ተፈታኝ ተማሪዎችን ሁሉ መልካም ጁምዓ እና ፈተናን ተመኘን:: አላህ ለስኬት በር ከፋች ያድርግላችሁ:: https://t.me/EHEMSU

NOTE: ስለ መውጫ ፈተናው የሰዓት መቀየር ትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ከማውጣቱ በፊት እንደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ "ሰዓቱ አልተቀየረም!" እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ "ፈተናው 7:00 ነው የሚጀምረው!" አይነት መግለጫዎች ነበሩ:: ሆኖም በዚህ ጉዳይ ያናገርናቸው የከፍተኛ ት/ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ሓይሎም ስዩም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናው 7:30 እንደሚጀምር አሳውቀዋል:: መረጃውን ላልሰሙት አሰሙ! https://t.me/EHEMSU

የExit Exam ሰዓት ለውጥ እንደተደረገ ትምህርት ሚኒስቴር በይፋ አሳውቋል:: ፍትሐዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም! https://t.me/EHEMSU
የExit Exam ሰዓት ለውጥ እንደተደረገ ትምህርት ሚኒስቴር በይፋ አሳውቋል:: ፍትሐዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም! https://t.me/EHEMSU

ጁምዓ ሶላት ኒቃብ እና ጀመዓ ሶላት ••• በትምህርት ተቋማት! ከ5:30-7:30 በጁምዓ ቀን ትምህርት መስጠት የማይፈቀድ መሆኑ በተደጋጋሚ ቢገለፅም ከወረቀት ባሻገር ትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎች ጥያቄ መሠረት ለመውጫ ፈተና ያወጣውን ፕሮግራም መቀየሩ ማረጋገጫ ነው:: እንደዚህ ከሆነ ሕግን ጥሰው ለምን በጁምዓ ሰዓት ያስተምራሉ የሚል ጥያቄ ከተነሳ መልሱ እነርሱ በጥላቻ እና በእብሪት ሰክረው ለመተንኮስ እና ለመረበሽ ሲሞክሩ ዝም ስላልናቸው ይሆናል:: ኒቃብ ለብሶ መማር የሚከለከል ነገር እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ቢገለፅም እንደ ማስረጃ ግን በዲላ ያለፈው ክስተት ጥሩ ነው:: ለምን ይከለክላሉ የሚል ጥያቄ ከተነሳ መልሱ እነርሱ ከሕግ ውጭ ሲንቀሳቀሱ በሕግ አግባብ የሚታገላቸው ሙስሊም ተማሪ ስለሌለ ይሆናል:: በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ መስገድ መብት ነው የሚል ሙግት ቢኖርም በተግባር ግን በሸይኻ ፋጢማ ትምህርት ቤት አይተናል:: ከሕግ ውጭ ሆነው ጫና ቢያሳድሩም በሕግ አግባብ በተደረገ ትግል ተማሪዎቹ የመስገጃ ቦታ ተሰጥቷቸው እየሰገዱ ይገኛል:: እነዚህ የዚህ አመት ክስተቶች መብቶቻችንን ምን እንደሆኑ ለምን ሊነጥቁን እንደሚፈልጉ እና እንዴት መውሰድ እንደምንችል አሳይተውናል:: መስገድ መብት ነው:: መልበስ መብት ነው:: በነፃነት መኖር ክብር ነው:: ለምን ይከለክላሉ የሚል ጥያቄ ከተነሳ ከነፃነት ዝቅ አድርገው ክብርን ለመግፈፍ ይሆናል መልሱ:: እንዴት ይስተካከል ከተባለም ሳይሰለቹ ሳይደክሙ ሳይታክቱ በመታገል ይሆናል መልሱ:: ነፃነት በነፃ አይገኝም! መብት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም! https://t.me/EHEMSU

አርብ እለት በሚሰጠው ፈተና ላይ የጁሙአ ሰላትን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ሚኒስቴር የሰአት ማሻሻያ ተደርጓል:: " ሰመራ ዩኒቨርሲቲ" https://t.me/EHEMSU
አርብ እለት በሚሰጠው ፈተና ላይ የጁሙአ ሰላትን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ሚኒስቴር የሰአት ማሻሻያ ተደርጓል:: " ሰመራ ዩኒቨርሲቲ" https://t.me/EHEMSU

የExit Exam የመፈተኛ ሰዓት ለጁምዓ እንደተቀየረ ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ: ደብረ ብርሐን ዩኒቨርሲቲ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አሳውቀዋል::
+2
የExit Exam የመፈተኛ ሰዓት ለጁምዓ እንደተቀየረ ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ: ደብረ ብርሐን ዩኒቨርሲቲ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አሳውቀዋል::

እርስዎ በሚማሩበት ትምህርት ቤት በጁምዓ ቀን
Anonymous voting

Guyyaa Jumu'a fi qormaataa bahimsaa( Exit Exim) UPDATE! •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• Ministeerri barnoota mirga barattootaa cabsun guyyaa jumu'aa qormaata bahumsaa(Exit Exam) keennu waan yaadef gamtaan keenya xalayaa komii galchuu isaa nii beekamaa. Kanumarran kan ka'ee bakaa bu'oota gamtiichaa guyyaa har'aa deebi waajjira ministeera de'taa dhaabbilee barnoota olaanoo ministeera barnootaarraa isaanitti keennamen jijjirraa sagantaa akka godhee beeksiiseera. Haaluma kanaan Qormaanni bahumsaa jumu'aa dhuufu sa'ati 7:30-10:00 akka tahuu ibseera. Kunis qaamota dhimmichi isaan ilaallatutti akka beeksiisan ibsaniru. ta'us hanga ammatti beeksiisa ifaan wanta ibsan hin jiru. Nutis haaloota jiran hordoofun sirreessuf kan hoojjannu ta'u isaa ni beeksiisnaa. Gamtaa barattoota Musliimaa dhaabbiilee olaanoo Ityophiyaa! https://t.me/EHEMSU

ጁምዓ እና የመውጫ ፈተና (Exit Exam) UPDATE! •••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የትምህርት ሚኒስቴር በጁምዓ ቀን የተማሪዎችን መብት በመጣስ ከ5:30 - 8:00 የመውጫ ፈተና ለመስጠት ማሰቡን ተከትሎ ህብረታችን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቅሬታ ደብዳቤ  ማስገባቱ ይታወቃል:: ይህንንም ተከትሎ የህብረቱ ተወካዮች በዛሬው እለት ከትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ዴኤታ ፅ/ቤት በተሰጣቸው መልስ በፕሮግራሙ ላይ ማስተካከያ እንዳደረጠ አሳውቋል::  በዚህም መሠረት በመጪው ጁምዓ የሚሰጠው Exit Exam ከ7:30-10:00 እንደሚሆን ገልፇል:: ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት እንዳሳወቁ ገልፀውልናል:: ሆኖም ግን እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በይፋ ማስታዎቂያ ያሳወቀው ነገር የለም:: እኛም የሚኖሩ ሁነቶችን እየተከታተልን ለማስተካከል የምንሰራ መሆናችንን እንገልፃለን:: የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተናን (Exit Exam) በመጪው አርብ በጁምዓ ሰዓት ማለትም ከ5:30-8:00 ለመስጠት ያወጣውን ፕሮግራም
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተናን (Exit Exam) በመጪው አርብ በጁምዓ ሰዓት ማለትም ከ5:30-8:00 ለመስጠት ያወጣውን ፕሮግራም እንዲቀይር ጠየቀ! ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ጥር 27 / 2017 ዓ.ል •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ባስገባው ደብዳቤ ጁምዓ የሙስሊሞች ሳምንታዊ በዓል መሆኑንና ከ5:30-7:30 በሀገር ደረጃ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እረፍት መሆናቸውን ጠቅሶ በዚህ ሰዓት የፈተና ፕሮግራም ማውጣት የሙስሊም ተማሪዎችን እሴቶችን እና መብቶችን መጋፋት እንደሆነ ገልፇል:: መሠል ጥፋቶች መደጋገማቸው ሙስሊሙን ተማሪ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያራርቁ በመሆናቸውም ተመሳሳይ ችግሮች በዘላቂነት እንዳይፈጠሩ መስመር እንዲደረገም ጠይቋል:: የደብዳቤው ግልባጭ ለፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ገብቷል:: https://t.me/EHEMSU

በቅድመ 1966 ዓ.ል የነበሩ አባቶቻችን ስለ ጁምዓ ቀን የነበራቸው ጥያቄ ከስራ ውጭ እንዲሆን አልያም ከ5:30 - 9:00 ክፍት እንዲሆን ነበር:: የዚያኔ ባይሳካም ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ በ1985 ዓ.ል በሽግግር መንግስቱ ከ5:30 - 7:30 ከስራ ውጭ ይሁን የሚል ተወሰነ:: ሆኖም ግን በሕግ ፀና የተባለውን መብት ከ32 አመታት ቡሃላ ጥሶ ት/ሚኒስቴር በጁምዓው ቀን ከ5:30-8:00 ሰዓት ፈተና ካልፈተንኩ እያለ ነው:: ይህ ትውልድ መሠል ጥፋቶችን ችላ ብሎ የሚያልፍ ከሆነ በአባቶቹ ትግል ላይ አፈር ከመነስነሱም ባሻገር ሀላፊነቱን በራሱ እጅ መቅበርም ነው:: በቃ ሊባል ይገባል:: በቃን እስኪሉ ድረስ! https://t.me/EHEMSU

ት/ሚኒስቴር Exit Examን በጁምዓው ከ5:30 - 8:00 ለመስጠት እንደወጠነ ነው:: እዚህጋ ጥያቄ አለን ••• የሚፈተን ሙስሊም ተማሪ የላቸውም? ወይንስ ጁምዓ ለሙስሊም ምን ማለት እንደሆነ አያ
ት/ሚኒስቴር Exit Examን በጁምዓው ከ5:30 - 8:00 ለመስጠት እንደወጠነ ነው:: እዚህጋ ጥያቄ አለን ••• የሚፈተን ሙስሊም ተማሪ የላቸውም? ወይንስ ጁምዓ ለሙስሊም ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም? ወይንስ በጁምዓ ቀን ከ5:30 - 7:30 የመንግስት ስራ ዝግ እንደሆነ አያውቁም? ወይንስ ምንም ቢፃፍ ምንም ቢሆን ሙስሊሙ ተማሪ ከትምህርቱ እና ከጁምዓው መምረጥ አለበት? ዘላቂ መፍትሔ ያሻል ••• ይህ የመጀሪያ ስህተታቸው አይደለም ••• የሪሜዲያል ተማሪዎችን ፈተና ከዒድ ጋር አድርገው ብዙ ተማሪ ላይ ተፅዕኖ መፍጠራቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው:: https://t.me/EHEMSU